You are on page 1of 3

ቀን --------------------

በህንፃ ላይ ሊፍት ለመግጠም የተደረገ ስምምነት

አንቀጽ አንድ
የውሉ መጠሪያ

ይህ ውል በ------------------------------ ፣አድራሻ ------- ፣ ------------------ ክ/ከ ፣ወረዳ --------፣


የቤ.ቁጥር ------------------- ፣ የስልክ ቁጥር ------------------------ የሆነው ከዚህ በኋላ ውል ሰጪ
እየተባለ በሚጠራው
እና
በ ኤች-ቲኬ ኤሌክትሮ ሜካኒካል ኃ/የተ/የግ/ማህ ፣አድራሻ አ.አ ፣ ልደታ ክ/ከ ፣ወረዳ 01 ፣ የቤ.ቁጥር
403/31 ፣ የስልክ ቁጥር 0911432321 የሆነው ከዚህ በኋላ ውል ተቀባይ ተብሎ በሚጠራው መካከል
የተደረገ ውል ነው፡፡

አንቀጽ ሁለት
የውሉ አላማ
ውል ሰጪ ------------------- አካባቢ በሚገኘው ----------- ህንፃ ላይ ---------- አሳንሰር
እንዲገጠምላቸው ስለፈለጉ ይህንንም ውል ተቀባዮች በዚህ ውል መሰረት ለመግጠም በመስማማታቸው
ሁለቱም ተዋዋይ ወገኖች ወደውና ፈቅደው ይህንን የውል ስምምነት አድርገዋል፡፡
አንቀጽ ሶስት
የውል ተቀባይ ግዴታ
3.1 ውል ሰጪ ከ ----------------- የሚያስመጣውን ------------- አንሳንሰር ከሳይት ዝግጅት ጅምሮ እስከ
ምርት ሂደት ቁጥጥር በማደረግ በጥራትና በጥንቃቄ በመስራት በትክክል መገጠሙን አረጋግጦ ለውል ሰጪ
ለማስረከብ ተስማምቶል ፡፡
3.2 ውል ተቀባይ ከላይ በአንቀፅ 3.1 ግዴታ የገባበትን ስራ አሳንሰሩ ሳይት ከደረሰበት ቀን ጀምሮ በ
------------------- የስራ ቀናት ውስጥ ሰርቶና አጠናቅቆ ለማስረከብ ግዴታ ገብቷል፡፡ ሆኖም በሲቪል ስራ
(የእስካፎልዲንግ፣የመብራት አቅርቦት፣ የጠረባ ሰራተኛ እና ማንኛውም የኮንክሪት ስራ) መዘግየት ቢደርስ
ውል ተቀባይ ከውል ሰጪ ጋር በመነጋገር በውሉ ላይ የተቀመጠው ጊዜ በስምምነት ሊራዘም ይችላል፡፡
3.3 ውል ተቀባይ ስራውን በጥራት ሰርቶ ሲያስረክብ ለ አንድ አሳንሰር ቫትን ጨምሮ ብር
--------------------- /------------------------------------------------/ እንዲከፈለው የተስማማ ሲሆን
የክፍያውም ሁኔታ፡-
ሀ. ቅድመ ክፍያ ከ አጠቃላዩ --------- ማለትም
-------------------- /------------------------------------------------------------------/ ሊፍቱ ሰይት
ሲደርስ የሚከፈል ይሆናል፡፡
ለ፡ ------------------ ማለትም -------------------------- / -----------------------------------------/
የገጠማ ስራ ሲጠናቀቅ የሚከፈል ይሆናል፡፡
ሐ፡ ------------------ ማለትም -------------------------- / -----------------------------------------/
ቴስቲንግ እና ኮሚሽኒንግ ስራ ሲጠናቀቅ የሚከፍል ይሆናል፡፡
ሆኖም በፓወር መዘግየት ቢያጋጥም ውል ሰጪ 4.4 ላይ የገባውን ግዴታ ተፈፃሚ የሚያደርግ ሲሆን
ሊፍቱን በሌላ ፓወር አማራጮች በመጠቀም/ ጀነሬተር/ አስነስቶ ክፍያው እንዲፈፀምለት ተስማምቶል፡፡
እንዲዚሁም ውል ሰጪ ለሊፍቱ ሚሆነውን በቂ ፓወር ባስገባ ግዜ ውል ተቀባይ ሊፍቱን ቴስቲንግ እና
ኮሚሽኒንግ በማድረግ ያስረክባል፡፡
3.4 ውል ተቀባይ በ 3.1 ላይ የገባውን ግዴታ ካጠናቀቀ በኋላ የቅድመ መከላከል ጥገና እና ሰርቪስ በየወሩ
ስለሚያስፈልግ በተጨማሪ በመሀል ብልሽት ሊያጋጥም ስለሚችል የተወሰነ ሁለቱ ወገኖች
በሚስማሙበት በወር የሚከፈል ብር ተመድቦ የሚሰራ ይሆናል፡፡
አንቀጽ አራት
የውል ሰጪ ግዴታ
4.1 ውል ሰጪ ለውል ተቀባይ ከላይ በአንቀፅ 3.1 የተጠቀሰውን የአሳንሰር ገጠማ ስራ በጥራትና በወቅቱ
ሰርቶና አጠናቅቆ ሲያስረክብ ቫትን ጨምሮ ብር
--------------------- /------------------------------------------------/ ለመክፈል ተስማምቷል::
4.2 ውል ሰጪ ለሊፍት የሚያስፈልገውን የእቃ አቅርቦት፣የእስካፎልዲንግ፣የመብራት አቅርቦት፣ የጠረባ
ሰራተኛ እና ሌሎች ማንኛውንም ሲቪል ስራ በራሱ የሚሸፈን ይሆናል፡፡
4.3 ከባድ እቃዎች ሲንቀሳቀስ ተጨማሪ የሰው ሃይል ወይም ማሽነሪ ያመቻቻል፡፡
4.4 ለሊፍቱ የሚሆነውን ፓወር ከውል ተቀባይ ጋር ቅድሚያ በመመካከር ሊፍቱ ቴስቲንግ እና ኮሚሽኒንግ
/በሀይ ስፒድ/ ከመደረጉ በፊት ማስገባት ይኖርበታል ሆኖም በፓወር መዘግየት ምክንያት ቢያጋጥም ውል
ሰጪ ሌላ የፓወር አማራጮችን /ጀነሬተር/ በመፈለግ ሊፍቱን ተሞክሮ ለመረከበ ግዴታ ገብቶል፡፡

አንቀጽ ስድስት
የውል ስራዎችን ባለማጠናቀቅ የሚከተሉ ጉዳዮችን በተመለከተ
6.1 በውል ሰጪ/ደንበኛ/ ወይንም በውል ተቀባይ /ድርጅት/ የተነሳ ከውል ማቋረጥ ምክንያት ለሚደርሰው
ጉዳት ካሳ የመጠየቅ መብት አላቸው ውል ተዋዋዮች አንድ ወገን ውል ቢያፈርስ የፁፍ ማስጠንቀቂያ
መስጠት ይጠበቅባቸዋል፡፡

አንቀጽ ሰባት
ውል የሚፈርስበት ምክንያት
ይህ ውል በሚከተሉት ምክንያቶች ሊፍርስ ወይንም ሊቋረጥ ይችላል
1. በሁለቱም ተዋዋዮች ስምምነት መሰረት
2. የውል ጊዜ ሲያልቅ ሲፈፀም ሲጠናቀቅ
3. ከተዋዋይ ወገኖች አንዱ የገባውን ግዴታ አለመወጣቱ በተጨባጭ ሲረጋገጥ፡፡
4. በሁለቱ ተዋዋዮች መካከል ስምምነት ወይም ግጭት ቢፈጠር በመወያየት የሚፈታ ሲሆን ካልሆነ
ግን በኢትዮጵያ ህግ መሰረት የሚፈታ ይሆናል፡፡
አንቀጽ ስምንት
ለውል ተገዢ ስለመሆንና ጸንቶ ስለሚቆይበት ጊዜ
6.1 ይህ የአሳንሰር ገጠማ ስራ ስምምነት ውል በሁለቱ ተዋዋይ ወገኖች ከተፈረመበት ቀን ጀምሮ የፀና
ይሆናል፡፡
6.2 ይህን ስምምነት ውል ለማፍረስ የሞከረ ወይም ያፈረሰ ወገን ውሉን ላከበረ ወገን ብር 15,000.00
(አስራ አምሰት ሺህ) ካሣ ከፍሎ ውሉ የፀና ይሆናል፡፡
6.3 ይህ ውል ስማቸው ከዚህ በታች የተገለፁት ምስክሮች ባሉበት ዛሬ ------------------ ዓ.ም ተፈረመ፡፡
ስለ ውል ሰጪ ስለ ውል ተቀባይ
ስም ------------------------ ስም --------------------

ፊርማ.................... ፊርማ.......................

ቀን ------------------- ቀን ---------------------

ምስክሮች
ስም ፊርማ
1. ___________________ _______________
2. ___________________ _______________
3. ___________________ _______________

You might also like