You are on page 1of 1

ከቀን ወደ ቀን የሀገሬ ብቻ ሳይሆን የዓለም ነገር እያሳሰበኝ መትዋል የኔም ድርሻ ይህ ከሆነ ብዬ ለናንተ እንዲ አጋራው

አውቆ ፈልጎ የተፈጠረ ያለ ምንም ሰው ያለ አይመስለኝም እባካቹ የማውቃቹ የማላቃቹ እንዲሁም የምታቁኝ ሰዎች
በሙሉ በቀን አንዴ ሰው ብቻ ስለሆናቹ ያገኛችሁትን ማሰብ መቻልን ለመልካም ነገር ብቻ እንጠቀምበት በየትኛውም
አጋጣሚ የሚያለያይን ነገር በተቻላቹ አቅም ላለመስማት ወይም ለመራቅ እንሞክር መልካም ነገርን አብዝተን እናስብ
እናድርግ እንገፋፋ….

ትላልቅ ሽማግሌዎች በየትምህርት ቤቱ እየሄዳቹ ለ 10 ደቂቃም ቢሆን ልጆችን ምከሩ ገፅፁ መርቁ

ወጣቶች አዋቂ ሳይሆን ልጅ ለመሆን ሞክሩ እንደልጅነት እድሜ ለመሆን ሁላችን እንጣር
እናቶች ቤት ውስጥ በጋራ እንዲበላ በጋራ እንዲፀለይ በጋራ ቡና እነዲጠጣ አድርጉ

የዕድር ተቋማት ሰው ከመሞቱ በፊት ቁጭ ብላቹ መፍትሄ ፍጠሩ አጥፊን ለዩ አንድ ስላረጋቹ ነገር ለዩ ካላገኛቹ ስለ
ሞትም ቢሆን አንድ ካረጋቹ ሰለዛ አንድነታቹ አስቡ በዛም አንድ ስለሆናቹ በዛ ማዕድ ተቋደሱ

በመጨረሻም የሃይማኖት አባቶች ስለ አንድነት ከመስበክ ባሻገር እንዴት እንደሚተገበር አብራቹ እየሆናቹ አሳዩን
በናነንተው ፀሎት ስላለን ጸልዩልን ፈጣሪ አምላክ ዓለማችንን ሰላም ጤና ለፍጥረት ሁሉ የምትመች ያድርግልን፡፡

You might also like