You are on page 1of 35

በኢፊዲሪ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ የለውጥ ስራ አመራር አተገባበር

ማኑዋል(ረቂቅ)
በኢፊዲሪ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ የለውጥ ስራ አመራር አተገባበር
ማኑዋል(ረቂቅ)

መግቢያ
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ በትምህርት ፣ በስልጠና ፣ በምርምር ፣ በምልከታ ፣በትንተና እና በስርጸት

ብቃትና ብስለት ያላቸው ሳይንሳዊና ዘመን ተሻጋሪ ሃሳቦችን በማመንጨት የህዳሴውን መድረክ የአመራር ጥያቄ

ሊመልስና የህዳሴውን ጉዞ ቀጣይነት ማረጋገጥ የሚያስችል የአመራር መገንቢያ ተቋም ሆኖ በሚኒስትሮች ም/ቤት

ደንብ ቁጥር 321/2006 የተቋቋመ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት ተቋም ነው፡፡

አካዳሚው ከመንግስት ስትራቴጃዊ የእቅድ ዘመን ውስጥ የሚጠበቅ ውጤትን ለማሳካት የአካዳሚውን

ስትራቴጅዎች ወደ ዕለት ተዕለት በመመንዘር አስከ ታችኛው ፈጻሚ በማውረድና ከሰራተኞች ጋር መግባባት

በመፍጠር የግለሰቦች፣የቡድን አፈጻጸመሞችን ብሎም አካዳሚውን በውጤታማነት ለመምራት የሚያስችል

የክትትልና ድጋፍ፣ግምገማና ግብረ መልስ እንዲሁም ሱፕረቪዥን ስራዎችን በማከናወን የመረጃ ስርአት ልውውጡ

እስከ ታችኛው ፈጻሚ ለማስተሳሰር፤የለውጥ መሳሪያ አተገባበርን ተቋማዊ በማድረግ ለማጠናከር፤በአጠቃላይ ስራን

በውጤታማነት ለመምራት የሚያስችል የተለያዩ የለውጥ መሳሪያ አሰራርና አተገባበር መመሪያና ማኑዋሎችን

በመፈተሽ ፣በማቀናጀትና በማደራጀት አንድ ወጥ የለውጥ ስራ አመራር ስርዓት ማኑዋል ለማዘጋጀት ነው፡፡

ማኑዋሉ በክፍል አንድ አጠቃላይ ሁኔታዎች፣ በክፍል ሁለት የለውጥ ሥራ አመራር ሥርዓት አተገባበር ማንዋሉ

ዓላማ እና መርህ፣ በክፍል ሶስት የለውጥ ሥራ አመራር ሥርዓቱ ዋና ሥራዎች፣ በክፍል አራት የለውጥ ሰራዊት

አደረጃጀት፣ በክፍል አምስት የአፈጻጸም ማሻሻያ አወሳሰድና ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች፣ በክፍል ስድስት የልዩ ልዩ አካላት

ተግባርና ሃላፊነት፣ በክፍል ሰባት ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች፣ በክፍል ስምንት የመልካም አስታዳደር ሁኔታን እንዲሁም

በክፍል ዘጠኝ የስብሰባ አፈጻጸምን አካቷል፡፡

Page | 1
በኢፊዲሪ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ የለውጥ ስራ አመራር አተገባበር
ማኑዋል(ረቂቅ)

ክፍል አንድ

1. አጠቃላይ ሁኔታዎች
1.1 ትርጓሜ
1.1.1. “የትብብር ቡድን” በተቋሙ ውስጥ ተለይቶ የተሰጠውን አገራዊ ተልዕኮ ለማሳካት የሚያስችለውን

የጋራ ዓላማና አሰራር እንዲሁም አመላካከት፣ ክህሎትና ዕውቀትን በመያዝ በተደራጀና በተቀናጀ መንገድ ለለውጥ

በቁርጠኝነት የተነሳ የመንግሥትና የህዝብ የተደራጀ ኃይል ማለት ነው፡፡

1.1.2. “የመንግስት መዋቅር” ማለት በተቋሙ ውስጥ የሚገኙና የተቋሙ የሠራዊት አካል ሆነው ከከፍተኛ

አመራር እስከ ሰራተኞች ደረስ እንደ አንድ አካል የሚዋሃዱበትና የተቋም ተልዕኮን በጋራ ለማሳካት

የሚንቀሳቀሱበት አደረጃጀት ማለት ነው፡፡

1.1.3. “የህዝብ አደረጃጀት” ማለት የዜጋውን ጥቅም ለማስጠበቅ ህዝብን ወክሎ ከተቋማት ጋራ የሚሰራ

በተለያየ መልኩ የተደራጀ የህዝብ አካል ማለት ነው፣

1.1.4. “የህዝብ አደረጃጀት አካላት” የሲቪክ ማህበራትን ማለትም የብዙሃንና የሙያ ማህበራት፣ ሌሎች የጋራ

ፍላጎቶቻቸውን፣ ሙያቸውንና የተሰማሩበትን ሥራ መሰረት አድርገው በማህበር የተደራጁ የሕዝብ አደረጃጀቶችንና

ልማታዊ የግል ሴክተሩን የሚያጠቃልል ነው፡፡

1.1.5. የትብብር ቡድን አደረጃጀት ማለት በአንድ የስራ ክፍል ማለትም በተመሳሳይ ወይም በተዛማጅ ተግባራት

ዙሪያ የሚደራጁበት እንዲሁም ለተሻለ አፈጻጸም የሚዘጋጁበትና የጋራ ተልዕኮ ያለው አደረጃጀት ነው፡፡

1.1.6. “የተቋም የበላይ አመራር” ማለት አካዳሚውን በበላይነት የሚመሩ የአካዳሚው ፕሬዚዳንት እና

በምክትል ፕሬዚዳንቶች ደረጃ ያሉ ተሿሚዎችን ያጠቃልላል፡፡

1.1.7. “የተቋም መካከለኛ አመራር”   ማለት   በመንግስት   ተቋማት የስልጣን ተዋረድ መሠረት ከበላይ

አመራር ቀጥሎ ባለው አደረጃጀት ውስጥ   በሙያው   አመራር   የሚሰጥ   በሜሪት   የተመደበ   ሙያተኛ

አመራር ነው፣ 

1.1.8. የቡድን መሪ በመንግስት ተቋማት አደረጃጀት የስልጣን ተዋረድ ከመካከለኛ አመራር ቀጥሎ ያለውን

አደረጃጀት የሚመራ በሜሪት የተመደበ አመራር ነው፡፡

Page | 2
በኢፊዲሪ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ የለውጥ ስራ አመራር አተገባበር
ማኑዋል(ረቂቅ)

1.1.9. “ሰራተኛ” ማለት በአካዳሚው በቋሚነት ተቀጥሮ የሚሠራ ሰው ነው፡፡ ሆኖም የአካዳሚው ፕሬዚዳንት

እና በምክትል ፕሬዚዳንቶች ደረጃ ያሉ ተሿሚዎችን ይጨምራል፡፡

1.1.10. ‘‘ምዘና“ ማለት በአካዳሚው የሥራ ክፍሎች የእቅድ አፈፃፀምን በውጤት ተኮር ሥራዎች ከዕቅድ

አንጻር መመዘን ማለት ነው፣

1.1.11. ማለት የሥራ ክፍሎች የዕቅድ አፈጻጸም ምዘና ተካሂዶ በሚቀርበው ውጤት እና መጨረሻ ላይ ውሳኔ

በሚሰጠው አካል በጸደቀው የተጠቃለለ ውጤት መሠረት በፅሑፍ፣ በገንዘብና በቁሳቁስ የሚሰጥ የሥራ አፈፃፀም

ምላሽ ወይም ማበረታቻ ሆኖ እንደ አስፈላጊነቱ ከእነዚህ ውስጥ በከፊል ወይም ሁሉንም ሊያካተት ይችላል፡፡

1.1.12. ‘‘ግብረ-መልስ“ በአካዳሚው የስራ ክፍሎች በየደረጃው በሚካሄደው የክትትልና ግምገማ እና

ሱፐርቪዥን እንዲሁም ሌሎች ተጓዳኝ ተግባራት ዙሪያ የመፈጸም ብቃት፣ ጥንካሬና እጥረትን በመለየት

መረጃዎችን የመያዝ፣ የአፈጻጸም አዝማሚያን የማመላከት እንዲሁም ለቀጣይ ግብዓት እያደረጉ መሄድን

የሚያካትት በጹሁፍ የተደገፈ አሰራር ማለት ነው፡፡

1.1.13. “የግብ አፈፃፀም ደረጃ“ (Performance level) በየእቅዱ የተቀመጡ ግቦች የአፈፃፀም ውጤት ደረጃ

በመቶኛ የሚያመላክት ነው፡፡

1.1.14. “ዕቅድ“ የልማት ዕቅድ(Development Planning) ሲሆን አንድ ተቋሙ የተቋቋመበትን ዓላማ ለማሳካት

እንዲችል ያለበትን የመፈጸምና የማስፈጸም አቅም (ሰብዓዊ፣ ቁሳዊና ገንዘብ) ባገናዘበ ሁኔታ ውጤት-ተኮር

/አመልካች ሥራዎቹን በቅደም ተከተል የሚተልምበት የአሰራር ስርዓትና ሂደት ነው፡፡

1.1.15. “ክትትል„፡-ፕሮግራሞች/ፕሮጀክቶች/ተግባራት አተገባበር በተቀመጠላቸው የጌዜ ሰሌዳና ግብዓት

(ገንዘብ፣ ቁሳቁስ፣ የሰውሃይል…) መሰረት እየተከናወኑ ሥለመሆናቸው የምናረጋግጥበት ተከታታይ የሥራ ሂደት

ሲሆን ይህም ሪፖርቶችን በመቀበል፣ በቢሮ የተሰሩ የወረቀት ሥራዎችን (Desk Review) በማየት፣ በመስክ ምልከታ

ወይም ተጠቃሚዎችን በመጠየቅ ሊከናወን የሚችል ነው፡፡ ትኩረቱም በአተገባበር ሂደት የሚያጋጥሙና የተለመዱ

እንቅፋቶችን (የቁሳቁስ፣ የገንዘብ፣ የክህሎት…) መፍትሄ እየሰጡ ስራው እንዲፋጠን ማድረግ ነው፡፡

1.1.16. “የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት„፡- የሥራ ክፍሎች የሥራ ክንውኖች፣ ግኝቶችና አጠቃላይ አፈጻጸሞች ሊሰሩ

ከታቀዱት ጋር በማነጻጸር በመተንተን ለሚመለከታቸው አካላት በጽሁፍ/በምስል ወይም በመድረክ የማቅረብ ሂደት

ሲሆን ይህንኑ መሰረት በማድረግም ፈጻሚዎች፣ አስፈጻሚዎችና ባለድርሻ አካላት/ተጠቃሚዎች በአተገባበር ወቅት

ያጋጠሙ ችግሮችንና የተገኙ ውጤቶችን ለመገምገም የሚረዳ መረጃ ነው፡፡

Page | 3
በኢፊዲሪ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ የለውጥ ስራ አመራር አተገባበር
ማኑዋል(ረቂቅ)

1.1.17. “ሱፐርቪዥን„ በትግበራ ላይ ላሉት አላማ ፈጻሚዎች የፕሮጀክቱን/ ዕቅዱን አተገባበር የሱፐርቪዥን

ቡድኑ በመስክ በመመልከት ወይም ቀደም ሲል በሪፖርት /በክትትል ወቅት የተሰበሰቡ መረጃዎችን መሰረት በማድረግ

የአፈጻጸም የመረጃዎችን ተአማኒነትና ተቀባይነት የማረጋገጥበት ተግባርና ሙያዊ የማሻሻያ አስተያየት ነው፡፡

1.1.18. “ግምገማ„ የእቅድ አፈጻጸም ከትግበራው ጀምሮ፣ አጋማሽ ወይም መጨረሻ ወቅቶች ክትትልና ዕቅድን

መሰረት በማድረግ የሚከናወን የአሰራር ሂደት ነው፡፡

1.1.19. “ስትራቴጂክ ዕቅድ” ማለት አንድ መስሪያ ቤት /የስራ ክፍል ወደፊት ባሉ ከ 3 - 5 ዓመት ጊዜያት

ሊያከናውናቸው ያሰባቸውን ዋና ዋና ስራዎችና የአፈፃፀም አቅጣጫዎች የያዘ የመካከለኛ ጊዜ ዕቅድ ነው፡፡

1.1.20. “ግብ” ማለት አንድ የሥራ ክፍል እንዲያሳካ ወደሚፈልገው ዓላማ ለማሳካት ሊያስመዘግብ የሚገባውን

ውጤት የሚያመላክት የዕቅድ አካል ነው፡፡

1.1.21. ግብ ተኮር ተግባር ማለት በየደረጃው የተዘጋጁ እና ግቦችን ለማሳካት የሚከናወኑ እና ከግብ መግለጫ

የሚመነጩ ዋና ዋና ተግባራት ናቸው፡፡

1.1.22. “ ዝርዝር ተግባር” ማለት አንድን ግብ ለማሳካት እንዲያስችሉ ተደርገው የተቀረፁና በቅደም ተከተል

የሚከናወኑ ስራዎች ማለት ነው፡፡

1.1.23. “ክብደት” ማለት ስራዎች በሚወስዱት የዕውቀት፣ የገንዘብና ሌሎች ግብዓቶች እንዲሁም በስራዎቹ

ውስብስብነት አንፃር ደረጃ ለማውጣትና ለመለየት የሚሰጥ ነጥብ ነው፡፡

1.1.24. ተገልጋዮች ማለት አካዳሚው ከሚሰጣቸው አገልግሎቶች በቀጥታ የሚያገኙ አካላቶች ናቸው፡፡

1.1.25. “ሌሎች ተገልጋዮች” የሚባሉት የህዝብ አደረጃጀት ያልሆኑ ያልሆኑ ነገር ግን ከመንግስት ተቋማት

አገልግሎት የሚያገኙ ግለሰቦች፣ የግል እና የመንግስት ተቋማት ናቸው፡፡

1.1.26. የቅርብ የስራ ኃላፊ፡- ማለት በፌደራል የመንግስት መስሪያ ቤቶች ውስጥ ስራንና ሰራተኛን በቅርበት

የሚከታተልና የሚመራ ሰው ነው፤

1.1.27. የአፈጻጸም አዝማሚያ ፡- ማለት በየደረጃው ያለውን የውጤት ተኮር እቅድ አፈጻጸምን በሚመለከት

በየጊዜው በሚደረግ ግምገማ ጥንካሬንና ጉድለትን በሚገልጽ መልኩ እየተያዘ የሚሄድ የአፈጻጸም አመላካች መሳሪያ

ነው፤

1.1.28. የአፈጻጸም መረጃ፡- ማለት ከእቅድ ዝግጅት እስከ አፈጻጸም ምዘና ስለተፈጸሙ ክንውኖች በየደረጃው

በሰነድነት የሚያዝ መረጃ ነው፤

Page | 4
በኢፊዲሪ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ የለውጥ ስራ አመራር አተገባበር
ማኑዋል(ረቂቅ)

1.1.29. የአፈጻጸም ስምምነት፡- ማለት በሰራተኛው እና በቅርብ ኃላፊው እንዲሁም በስራ ሂደትና ከስራ ሂደቱ

በላይ በሆነ ሃላፊ መካከል የውጤት ተኮር ዕቅድን ለመፈጸም የሚደረግ መግባባት ወይም ውል ነው፤

1.1.30. የተሻለ ፈጻሚ፡- ማለት በአንድ የስራ ክፍል ውስጥ ካሉት ሰራተኞች ውስጥ በሚካሄዱ የአፈጻጸም

ግምገማዎች በውጤት ተኮር ስራ አፈጻጸሙ ከፍተኛና ከዚያ በላይ አፈጻጸም ያስመዘገበ ሰራተኛ ነው፤

1.1.31. ማበረታቻ፡- ማለት በስራቸው የተሻለ አፈጻጸም ያስመዘገቡ ሰራተኞች በቁሳቁስ፣በገንዘብ እንዲሁም

በዓይነት የሚበረታቱበት ስልት ነው፡፡

Page | 5
በኢፊዲሪ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ የለውጥ ስራ አመራር አተገባበር
ማኑዋል(ረቂቅ)

ክፍል ሁለት

2. የለውጥ ሥራ አመራር ሥርዓት አተገባበር ማንዋሉ ዓላማ እና መርህ


2.1 የማንዋሉ ዓላማ

የዚህ ማኑዋል ዓላማ የአካዳሚው እቅድ፣ሪፖርት፣ ክትትልና ግምገማ እንዲሁም የግንኙነት ጊዜ ወጥ ለማድረግና

የለውጥ መሳሪያዎች ቅንጅታዊ አተገባበርን ውጤታማ ለማድረግ፣ የቡድን አደረጃጀትን ለማጠናከር፣ የመረጃ

ልውውጥ ሥርዓቱ እስከ ፈጻሚው ድረስ ለማስተሳሰር፤ በአጠቃላይ ስራን በውጤታማነት ለመምራት የሚያስችል

የተለያዩ የለውጥ መሳሪያ አሰራርና አተገባበር መመሪያና ማኑዋሎችን በመፈተሽ ፣በማቀናጀትና በማደራጀት አንድ

ወጥ የለውጥ ስራ አመራር ስርዓት ማኑዋል ለማዘጋጀት ነው፡፡

2.2 የማኑዋሉ አተገባበር መርህ

1. የተቋማት ስትራቴጂያዊ ግቦች ከአገራዊ ፖሊሲና ስትራቴጂዎች የመነጩ መሆን አለባቸው፤

2. የተቋማት የዕቅድ ዝግጅት፣የአፈጻጸም ግምገማና ምዘና የውጤት ተኮር ሥርአትን የተከተለ መሆን አለበት፤

3. የስራ አፈጻጸም ግምገማና ምዘና በተቋም፣በስራ ሂደትና በፈጻሚ ደረጃ በተናበበና ሚዛናዊ በሆነ መልኩ

መከናወን አለበት፤

4. በተቋም አመራርና መላው ሰራተኛ መካከል ስለ ውጤት ተኮር ስርአት በቂ ግንዛቤና የጋራ መግባባት መፈጠር

አለበት፤

5. በተቋማት የውጤት ተኮር ዕቅድ ዝግጅትና የአፈጻጸም ግምገማ የህዝብ አደረጃጀት ሙሉ ተሳትፎ መኖር

አለበት፤

6. የውጤት ተኮር አፈጻጸም ክትትልና ግምገማ በአንድ የተወሰነ ወቅት ብቻ የሚከናወን ሳይሆን ከዕቅድ

ዝግጅት ምዕራፍ ጀምሮ በትግበራና ማጠቃለያ ምዕራፍ ውስጥ በተደራጀና በተቀናጀ አግባብ በተከታታይ የሚከናወን

የዕለት ተዕለት ተግባር ሊሆን ይገባል፤

7. የውጤት ተኮር ዕቅድ የአፈጻጸም መረጃ በአግባቡ መያዝ አለበት፤

8. የውጤት ተኮር አፈጻጸም ምዘና ቀድሞ ስምምነት የተደረሰባቸውን ግቦች፣መለኪያዎችና ዒላማዎች

በተግባር አፈጻጸም ከተገኙ ውጤቶች ጋር በማነጻጸር የሚከናወን ይሆናል፤


Page | 6
በኢፊዲሪ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ የለውጥ ስራ አመራር አተገባበር
ማኑዋል(ረቂቅ)

9. የውጤት ተኮር ዕቅድ ላይ የተቀመጡ ግቦች በላቀ ደረጃ ለማስፈጸም ቅንነተ፣ ግልጸኝነትና ተጠያቂነት

ያለው አሰራር መከተል፣

10. ተአማኒነት፣ ወቅታዊነትና ተደራሽነት ያለው መረጃ ላይ የተመሰረተ የዕቅድ ዝግጅት፣ የዕቅድ አፈጻጸም

ሪፖርት፣ ክትትል፣ ምዘና፣ ግምገማና ግብረመልስ ሥርዓት መከተል፣

11. የተቀናጀ፣ የተደራጀ፣ ተመጋጋቢና ተደጋጋፊ አሰራርን መከተል፣ እና ለጋራ ውጤት/ስኬት የመስራት ባህልን

ማጎልበት፤

12. በጀትን ከስትራቴጅ ጋር ማያያዝ ክትትልና ግምገማም ማድረግ

13. የለውጥ መሳሪያዎችን አቀናጅቶ መተግበር ናቸው፡፡

ክፍል ሶስት

3. የለውጥ ሥራ አመራር ሥርዓቱ ዋና ዋና ሥራዎች


3.1 የተቋም የውጤት ተኮር ዕቅድ ዝግጅት

1) አካዳሚው የመንግስት የልማት ዕቅድ ዘመንን መሰረት ያደረገ የአስር ዓመት መሪ እቅድ ያዘጋጃል፤

2) የአስር ዓመት መሪ እቅድ መነሻ በማድረግ የአምስት አመት ዕቅድ ያዘጋጃል፤

3) የአስር እና የአምስት አመት ዕቅድ ዝግጅት የበላይ አመራሩ ሃላፊነት ሆኖ በዕቅድ፣በጀትና ለውጥ ስራ አመራር

ዳይሬክቶሬት በራሱ ወይም በተቋሙ የበላይ አመራር በሚዋቀር ኮሚቴ ከተዘጋጀ ብኋላ በተቋሙ የስራ አመራር

ኮሚቴ የጋራ መግባባት ተደርሶበት ይጸድቃል፤

4) በዕቅድ ዝግጅት ሂደት የመንግስትና የህዝብ አደረጃጀት ተሳትፎን በማረጋገጥ በተቋም ተልዕኮ ፣ራዕይ

እሰቶችና ስትራቴጂዎች ላይ የጋራ መግባባት ሊፈጠር ይገባል፡፡

5) አካዳሚው ከአምስት አመት የውጤት ተኮር ዕቅዱ የተወሰደ ዝርዝር አመታዊ ዕቅድ ያዘጋጀል፤

6) ዓመታዊ የውጤት ተኮር ዕቅድ በዕቅድ፣በጀትና ለውጥ ስራ አመራር ዳይሬክቶሬት ከተዘጋጀ በኋላ በሰራተኛና

በሚመለከታቸው አካላት በማወያየትና ተገቢውን ግንዛቤ እንዲያዝበት በማድረግ በአካዳሚው የስራ አመራር

ኮሚቴ የጋራ መግባባት ተደርሶበት ይጸድቃል፤

Page | 7
በኢፊዲሪ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ የለውጥ ስራ አመራር አተገባበር
ማኑዋል(ረቂቅ)

7) የተቋም የውጤት ተኮር ዕቅድ በዋነኛነት ከዕይታዎች አንጻር የተቀረጹ ስትራቴጂያዊ ግቦችን፣የስትራቴጂያዊ

ግቦች መግለጫ፣የግቦችን ምክንያትና ውጤት ትስስር የሚያሳይ ስትራቴጂያዊ ማፕ፣መለኪያዎችንና የመለኪያ

መግለጫዎችን ፣መነሻዎችን ፣ዒላማዎችን ፣ስትራቴጂያዊ እርምጃዎችን ፤የአፈጻጸም ክትትል ግምገማ ስርአትን

እንዲሁም የሚያስፈልግ በጀትን ማካተት አለበት፤

8) በየደረጃው የሚዘጋጁ ዓመታዊ የአፈጻጸም ግቦች ዒላማዎች እንዲሁም ግብ ተኮር ተግባራት ጥረትን

የሚጠይቁ እና ሊተገበሩ የሚችሉ መሆን አለባቸው፤

9) በተቋም ደረጃ ለሚዘጋጁ ስትራቴጂያዊ ዕይታዎች ፣ግቦችና መለኪያዎች ክብደት ይሰጣል ለዕይታዎች

የሚሰጠው ክብደት ድምሩ 100% ሆኖ ለተገልጋይ ዕይታ 20-25%፣ ለፋይናንስ ዕይታ 10-15%፣ ለውስጥ አሰራር

ዕይታ 30-40% እና ለመማማርና እድገት ዕይታ 20-30% ባለው ገደብ ውስጥ ማረፍ አለበት፡፡በዚሁም መሰረት

ለአራቱ ዕይታዎች የሚሰጠው ክብደት በተመለከተ ድምሩ 100% ሆኖ ለተገልጋይ ዕይታ 20%፣ ለፋይናንስ ዕይታ

10%፣ ለውስጥ አሰራር ዕይታ 40% እና ለመማማርና እድገት ዕይታ 30% ይሆናል፡፡፤ሆኖም የእይታ ክብደቱ ለመቀየር

በእቅድ፣በጀትና ለውጥ ስራ አመራር ዳይሬክቶሬት በኩል ወይም ለማኔጅመንት በማቅረብ የሚወሰን ይሆናል፡፡

10) በዚህ አንቀጽ በተራ.ቁጥር (9) ላይ የተገለጸውን የዕይታዎች ክብደት በተቋም፣በስራ ክፍል እና በግለሰብ

ፈጻሚ ደረጃ በተመሳሳይ የሚወሰድ ይሆናል፤

11) በየደረጃው የሚዘጋጅ የውጤት ተኮር ዕቅድ ተቋሙ/የስራ ክፍሉ እንዲያከናውን የተቋቋመበትን ዋና ዓላማ፣

የመንግስት ፖሊሲና ስትራቴጂዎችን፣ አዳዲስ የመንግስት አቅጣጫዎችንና ሌሎች ነባራዊ ሁኔታዎችን ከግምት

ባስገባ መልኩ ከውጤት ተኮር ዕይታዎች (የተገልጋይ ዕይታ፣ የፋይናንስ ዕይታ የውስጥ አሰራር ዕይታ፣የመማማርና

ዕድገት ዕይታ) የተቀመጡ መለኪያዎችና ዒላማዎች ከሚጠበቁ ውጤቶች አንጻር የተቃኙ መሆን አለባቸው፤

12) በየደረጃው የሚዘጋጅ የውጤት ተኮር ዕቅድ ላይ የሚቀመጡ ግቦች ፣የግብ መግለጫዎች፣መለኪያዎች፣

የመለኪያ መግለጫዎች ፣መነሻዎች ፣እና ዒላማዎች የተናበቡ ሊሆኑ ይገባል፤

13) የአካዳሚው የስራ ክፍሎች በጀት አመቱ በገባ በመጀመሪያው ወር ውስጥ ከአምስት አመት የውጤት ተኮር

ዕቅድ የተመነዘረ አመታዊ ዕቅዳቸውን አዘጋጅተውና በየደረጃው ለሚገኙ አካላት አውርደው ወደ ተግባር መግባት

አለባቸው፤

14) የዕቅድ ክለሳን በተመለከተ የአካዳሚው አመራር እንዲያውቁት በማድረግ የተቋሙ የ 5 ዓመት የስትራቴጅክ

ዕቅድ የዕቅድ ክለሳ እንደአስፈላጊነቱ በ 2 ዓመት ተኩል መደረግ ይኖርበታል፡፡ የዓመታዊ ዕቅድ ደግሞ በዓመት

እንደአስፈላጊነቱ አንድ ጊዜ በአንደኛው ግማሽ ዓመት መጨረሻ በዕቅድ ክለሳ ወቅት የሚወጣ ፤የሚቀነስ ወይም
Page | 8
በኢፊዲሪ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ የለውጥ ስራ አመራር አተገባበር
ማኑዋል(ረቂቅ)

የሚጨመር ካለ በቂ አሳማኝ ምክንያት በጽሁፍ ለበላይ አመራር መቅረብ ይገባዋል፡፡ ከበላይ አመራር ይሁንታ ሲያገኝ

ዕቅዱ የሚከለስ ይሆናል፡፡

15) በአካዳሚው የስራ ክፍሎች የቀጣይ በጀት ዓመት የፕሮግራም በጀት ዓመታዊ መነሻ ዕቅዶቻቸውን

በሚጠናቀቀው በጀት ዓመት እስከ የካቲት 30 ድረስ ለዕቅድ፣በጀትና ለውጥ ስራ አመራር ዳይሬክቶሬት ማቅረብ

አለባቸው፡፡

16) የተለያዩ የለውጥ መሳሪያዎችን ፣የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል ከአካዳሚው

አመታዊ እቅድ አቀናጅቶና አስተሳስሮ ማቀድ ያስፈልጋል፡፡

3.2 የስራ ክፍሎች የውጤት ተኮር ዕቅድ ዝግጅት

1) በስራ ክፍል ደረጃ ዓመታዊ ዕቅድ በሚዘጋጅበት ወቅት የስራ ክፍሉን ተግባርና ሃላፊነት እንዲሁም ጠንካራና ደካማ

ጎኖች በአግባቡ መለየት አለባቸው፣

2) ግቦች ለስራ ክፍሎች የሚወርዱት በተቋሙ ግብ የሚያወርድ ቡድን አማካይነት ይሆናል፤

3) ለእያንዳንዱ የስራ ክፍል የሚወርዱት ግቦች በተቋሙ የስራ አመራር መጽደቅ አለባቸው፤

4) የስራ ክፍል የውጤት ተኮር ዕቅድ የሚዘጋጀው ከተቋሙ ውጤት ተኮር እቅድ ተመንዝረው የወረዱ ስትራቲጂያዊ

ግቦችን መሰረት በማድረግ ነው፤

5) የስራ ሂደት የውጤት ተኮር ዕቅድ በዋናነት የስራ ሂደቱን ግቦች ፣የግቦቹን መግለጫ፣መነሻዎችን መለኪያና

ዒላማዎችን ይይዛል፤

6) በስራ ሂደት ደረጃ ለተቀረጹ ግቦችና መለኪያዎች የክብደት ነጥብ ይሰጣቸዋል፤

7) የተዘጋጀውን የውጤት ተኮር ዕቅድ መሰረት በማድረግ በስራ ሂደት ደረጃ የድርጊት መርሃ ግብር መዘጋጀት አለበት፤

8) የስራ ሂደቱ የውጤት ተኮር ዕቅድ ሰራተኛውን ባሳተፈ መልኩ ከጸደቀ በኋላ ግብ ተኮር ተግባራትን መሰረት አድርጎ

ለሰራተኞች መውረድ አለበት፤

9) የአካዳሚው የስራ ክፍሎች አመታዊ እቅዳቸውን በስራ ክፍላቸው በመገምገምና በዘርፍ በማጸደቅ በበጀት አመቱ

በመጀመሪያው ወር ወደ ስራ መግባት አለባቸው፤

10) በዕቅድ ዝግጅት ወቅት የእቅድ፣በጀትና ለውጥ ስራ አመራር ዳይሬክቶሬት አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋሉ፡፡

3.3 የሰራተኛ/የግለሰብ/ የውጤት ተኮር ዕቅድ ዝግጅት

1) የሰራተኛው የውጤት ተኮር ዕቅዱን ሲያዘጋጅ የግሉን ጠንካራና ደካማ ጎኖች በአግባቡ መለየት ይኖርበታል፤

Page | 9
በኢፊዲሪ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ የለውጥ ስራ አመራር አተገባበር
ማኑዋል(ረቂቅ)

2) ሰራተኛው የግል ዕቅዱን የሚያዘጋጀው በስራ ሂደቱ ደረጃ ከተዘጋጁ የግብ መግለጫዎች ላይ ግብ ተኮር ተግባራት

በማውረድ ቀጣይ መሻሻልን በሚያመላክት መልኩ በግብ መልክ በማስቀመጥ ይሆናል፤

3) የሰራተኞች የውጤት ተኮር እቅድ ሲዘጋጅ ከስራ መዘርዝር ጋር የተናበበ መሆኑን ማረጋገጥ ይገባል፤

4) የሚዘጋጀው የሰራተኛው የውጤት ተኮር ዕቅድ ከአቅም በታች እንዳይሆን ማድረግና ለስራ ሂደቱ ብሎም

ለተቋሙ ግብ ስኬት ቀጥታ አስተዋጾዖ ሊያበረክት የሚችል መሆኑን ማረጋገጥ ይገባል፤

5) የሰራተኛው የውጤት ተኮር ዕቅዱን ማሳኪያ የድርጊት መርሃ ግብር በማዘጋጀት ለቅርብ ሃላፊው በወቅቱ

ማቅረብ አለበት፤

6) ዒላማዎች የተቀመጡ ስታንዳርዶችን ታሳቢ እንዲያደርጉ ማድረግ፤

3.3.1 የአፈጻጸም ስምምነት

1) የስራ ሂደት መሪ ወረዱለትን ግቦች ለማሳካት ከሚመለከተው የበላይ ሃላፊ ጋር የአፈጻጸም ስምምነት

መፈራረም አለበት

2) የሰራተኛው የውጤት ተኮር ዕቅዱን ለማሳካት ከሚመለከተው የቅርብ ሃላፊ ጋር የአፈጻጸም

ስምምነትመፈራረም አለበት፤

3) የአፈጻጸም ስምምነቶች የመጀመሪያ ወር ውስጥ መጠናቀቅ አለባቸው፤

4) የተፈረሙየአፈጻጸም ስምምነቶች በአግባቡ በሰነድነት መያዝ አለባቸው፤

3.4 የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት

1) የአካዳሚው የስራ ክፍሎች በዓመት ውስጥ በበላይ ሃላፊዎች(በዘርፍ) የተረጋገጡ 4 ወቅታዊ ሪፖርቶች

(የመጀመሪያ ሩብ ዓመት፣ የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት፣ የዘጠኝ ወር እና አመታዊ) ከዕቅድ አንጻር ተተንትነው

ለእቅድ፣በጀትና ለውጥ ስራ አመራር ዳይሬክቶሬት በተጠናቀቀው ሩብ ዓመት የመጨረሻ (25 ኛው) ቀን ድረስ

ማቅረብ አለባቸው፡፡

2) ለሪፖርት ማቅረቢያ ከተቀመጠው ጊዜ ያዘገዩ የስራ ክፍሎች በሚዘጋጅ የአካዳሚው ሪፖርት የእቅድ፣በጀትና

ለውጥ ስራ አመራር ዳይሬክቶሬት ከሚያጠቃልለው የአፈጻጸም ውጤት ላይ እስከ 3 ነጥብ ተቀናሽ ይደረግባቸዋል፡፡

3) የሚቀርቡ ሪፖርቶች በመረጃ የተደገፉና ስራዎች ያሉበትን ደረጃ በትክክል በሚያሳይ መልኩ መሆን አለበት፡፡

4) አካዳሚው ሪፖርት አቀራረብ ወጥነት ያለው እንዲሆን በውጤት ተኮር መመሪያ ላይ በተቀመጠው ፎርማት

መሰረት ይሆናል፡፡

3.5 የክትትል፣ ድጋፍና ሱፐርቪዥን ስርዓት


Page | 10
በኢፊዲሪ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ የለውጥ ስራ አመራር አተገባበር
ማኑዋል(ረቂቅ)

1) በየደረጃው ያለው ሀላፊ የውጤት ተኮር ዕቅድ ክንውንን በተመለከተ ተገቢውን መረጃ መያዝና ማደራጀት

አለበት፣

2) ዕቅድ፣በጀትና ለውጥ ስራ አመራር ዳይሬክቶሬት በአካዳሚው የስራ ክፍሎች የጎንዮሽ ሥራ ክትትልና ድጋፍ

በሚያደርጉበት ወቅት ችግር ፈቺ፣ ወቅቱን የጠበቀ እና አስተማሪ የሆነ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡

3) የለውጥ ስራ አመራርና መልካም አስተዳደር ቡድን በአካዳሚው የስራ ክፍሎች በየወሩ በመገኘት በለውጥና

መልካም አስተዳደር ስራዎች ዙሪያ ክትትልና ድጋፍ የሚያደርግ ይሆናል፡፡

4) የዕቅድና በጀት ቡድን ለአካዳሚው የስራ ክፍሎች ለሱፐርቪዥን የሚሆን ቼክሊስት ከእቅዳቸው በመነሳትና

በማዘጋጀት እንዲሁም የሱፐርቪዥን ቡድን በማደራጀት በዳይሬክቶሬቱ በማጸደቅ በአመት አራት ጊዜ

(ጥቅምት፣ጥር፣ሚያዚያ እና ሐምሌ ወር) ሱፐርቪዥን እንዲካሄድ ያደርጋል፡፡ በሐምሌ ወር የሚደረገው

ሱፐርቪዥን የዓመታዊ እቅድ አፈጻጸም ምዘናን የሚያካትት ይሆናል፡፡

5) በሱፐርቪዥን/በምልከታ የተገኙ መረጃዎችን በሪፖርት በማደራጀት ሱፐርቪዥን ለተደረገበት ሥራ ክፍል

በግብረ መልስ አደራጅቶ ይልካል፡፡ ለአካዳሚው የበላይ አመራርም ያቀርባል፡፡

6) በየደረጃው የሚካሄደው የክትትልና ግምገማ ሂደት የመፈጸም ብቃት ፣ጥንካሬና እጥረትን በመለየት

መረጃዎችን የመያዝ ፣የአፈጻጸም አዝማሚያን የማመላከት እንዲሁም ግብረ መልስ የመስጠትንና ለቀጣይ ግብአት

እያደረጉ መሄድን ማካተት አለበት፤

7) የተሰጠውን ግብረ መልስ መሰረት በማድረግ የእቅድ በጀት እና ለውጥ ስራ አመራር ዳይሬክቶሬት ባለቤትነት

በአካዳሚው የሚገኙ የስራ ክፍል ሀላፊዎች ጋር በግብረ መልሱ ዙሪያ የውይይት መድረክ የሚያዘጋጅ ይሆናል፡፡

8) ከተፈጠረው የውይይት መድረክ በኋላ የአካዳሚው የበላይ አመራር የተሰጠውን ግብረ መልስ መነሻ በማደረግ

አቅጣጫ ያስቀምጣል፤ ይገምግማል፤ እንደ አስፈላጊነቱ እውቅና እንዲሁም የእርምት እርምጃ ይወስዳል፤

3.6 የግምገማ ስርዓት

3.6.1 ግምገማ የሚካሄድባቸው ደረጃዎችና ጊዜያት

1. በፈጻሚ ደረጃ

1) በአካዳሚው በሁሉም የትብብር ቡድን አደረጃጀቶች ሳምንታዊ፣ ወርሃዊና የሩብ አመት እና የግማሽ ዓመት

የውጤት ተኮር ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ይካሄዳል፡፡

2) ዳይሬክቶሬቶች በየአስራ አምስት ቀኑ ከሁሉም የትብብር ቡድን መሪዎች ጋር የውጤት ተኮር ዕቅድ

አፈጻጸም ግምገማ ይካሄዳል፡፡


Page | 11
በኢፊዲሪ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ የለውጥ ስራ አመራር አተገባበር
ማኑዋል(ረቂቅ)

3) በትብብር ቡድን ውይይት ወቅት በየወሩ የስራ ክፍሉ ሰራተኞች አቅም በሚገነቡ እና ከስራ ክፍሉ ጋር

ተያያዥነት ያላቸውን የመወያያ አጀንዳዎች በመቅረጽ የእርስ በርስ መማማር መደረግ ይኖርበታል፡፡

2. በዳይሬክቶሬት ደረጃ

1) ዳይሬክቶሬቶች በየአስራ አምስት ቀኑ ከሁሉም የትብብር ቡድን መሪዎች ጋር የውጤት ተኮር ዕቅድ

አፈጻጸም ግምገማ ይካሄዳል፡፡

2) በየወሩ፣የ 3 ወር፣የ 6 ወር፣የ 9 ወር እና አመታዊ እቅድ ከሁሉም ሰራተኞች ጋር የውጤት ተኮር አፈጻጸም ላይ

ግምገማ መካሄድ ይኖርበታል፡፡

3. በዘርፍ ደረጃ

1) የዘርፍ ሃላፊዎች በስራቸው ከሚገኙ መካከለኛ አመራሮች (ዳይሬክቶሬቶች) ጋር በየ 15 ቀኑ የውጤት ተኮር

አፈጻጸም ላይ ግምገማ መካሄድ ይኖርበታል፡፡

2) የ 3 ወር፣የ 6 ወር፣የ 9 ወር እና አመታዊ እቅድ ከዘርፉ ሰራተኞች ጋር የውጤት ተኮር አፈጻጸም ላይ ግምገማ

መካሄድ ይኖርበታል፡፡

4. በአካዳሚ/በተቋም ደረጃ

1) በየወሩ በተቋም የበላይ ሀላፊ በሁሉም የስራ ክፍሎች የውጤት ተኮር አፈጻጸም ላይ በተቋም ማናጅመንት

ክትትልና ግምገማ መካሄድ ይኖርበታል፡፡

2) የ 3 ወር፣የ 6 ወር፣የ 9 ወር እና አመታዊ እቅድ የውጤት ተኮር አፈጻጸም በጠቅላላ ሰራተኞች ውይይት

ይካሄዳል፡፡

3) የህዝብ አደረጃጀቶች ከመንግስት መዋቅር ጋር በመሆን የ 3 ወር፣የ 6 ወር፣የ 9 ወር እና አመታዊ እቅድ

የአካዳሚውን የውጤት ተኮር አፈጻጸምን ይገመግማሉ፡፡


3.7 የግብረ መልስ አሰጣጥ ስርዓት
1) በየደረጃው የሚካሄደው የክትትልና ግምገማ ሂደት የመፈጸም ብቃት፣ ጥንካሬና እጥረትን በመለየት

መረጃዎችን የመያዝ፣ የአፈጻጸም አዝማሚያን የማመላከት እንዲሁም ግብረ መልስ የመስጠትንና ለቀጣይ ግብዓት

እያደረጉ መሄድን ማካተት አለበት፡፡

2) የሚዘጋጁ ዓመታዊ ዕቅዶች ከመንግስት ፖሊሲና ስትራቴጂዎች፣ ከባለፈው ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም፣ የስራ

ክፍሉ/አካዳሚው እንዲያከናውን ከተቋቋመበት ዓላማ እና ሌሎች የእቅድ ጥራት (SMARTER) መገምገሚያ

መስፈርቶችን ያሟላ ስለመሆኑ ታይቶ በየደረጃው ግብረ መልስ መሰጠት አለበት፡፡


Page | 12
በኢፊዲሪ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ የለውጥ ስራ አመራር አተገባበር
ማኑዋል(ረቂቅ)

3) በአካዳሚው ለሚዘጋጁ ሪፖርቶች ከወቅታዊነት፣ ከጥራት፣እና ከአፈጻጸም ደረጃ አኳያ ታይቶና ተመዝኖ

በየደረጃው ግብረ-መልስ በዕቅድ፣በጀትና ለውጥ ስራ አመራር ዳይሬክቶሬት መሰጠት አለበት፡፡

4) ለአካዳሚው የስራ ክፍሎች ከሱፐርቪዥን እና ምዘና የሚገኙ መረጃዎች በማካተት ግብረ መልስ በዕቅድ

በጀት እና ለውጥ ስራ አመራር ዳይሬክቶሬት ተዘጋጅቶ ሱፐርቪዥን ለተካሄደባቸው ወይም ለተመዘኑ የአካዳሚው

የስራ ክፍሎች እንዲሁም ለከፍተኛ አመራሩ እንዲደርሳቸው ይደረጋል፡፡


3.8 የአፈጻጸም ምዘና
3.8.1 የተቋም አፈጻጸም ምዘና

1) የተቋም አፈጻጸም ምዘና በአመት ሁለት ጊዜ እንደ ቅደም ተከተሉ በጥር ወርና በሃምሌ ወር ውስጥ ይካሄዳል፣

ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ ተቋማት የሩብ አመቱን እና የዘጠኝ ወር የአፈጻጸም አዝማማሚያቸውን እየገመገሙና

እያመላከቱ መሄድ ይገባቸዋል፣

2) የተቋም የውጤት ተኮር አፈጻጸም ምዘና የሚካሄደው በተቋም የግቦች አፈጻጸም ውጤት ላይ በመመስረት ነው

3) የተቋሙ የግቦች እቅድ አፈጻጸም በየግማሽ አመቱ መጨረሻ የተመዘገበው የግቦች አማካይ የአፈጻጸም ውጤት

ይሆናል፣ይህ የግቦች አፈጻጸም የምዘና ውጤት ከተቋሙ አጠቃላይ የአፈጻጸም ውጤት 80% ድርሻ ይይዛል፤

4) ተቋሙ ዋና ዋና መስፈርቶችን በያዘ የምዘና ቅጽ መሰረት በየግማሽ አመቱ በህዝብ አደረጃጀት አመራሮች

ወይም ተወካዮች መገምገምና መመዘን አለበት፣ይህ የግምገማና የምዘና ውጤት ከተቋሙ አጠቃላይ የአፈጻጸም

ውጤት 20% ድርሻ ይይዛል፤

5) በዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ(3.8.1) በተራ.ቁ.3 እና 4 የተመከቱት የምዘና ውጤቶች ድምር የተቋሙ አጠቃላይ

የ 100% የውጤት ተኮር አፈጻጸም ውጼጽ ይሆናል፣

6) ከህዝብ/ተገልጋይ እርካታ ጋር የተያያዙ ግቦች አፈጻጸም ሙያው ብቃት በጠበቀ መልኩ በተደረገ አመታዊ የዳሰሳ

ጥናት የተረጋገጠ መሆን አለበት፣

7) የተቋም የውጤት ተኮር አፈጻጸም ምዘና ውጤት በሰራተኛውና በህዝብ አደረጃጀት የጋራ ውይይት

ሊካሄድበትና በተቋሙ የስራ አመራር ኮሚቴ ሊጸድቅ ይገባል፣

8) የአጠቃላይ የስራ ክፍሎቹ የምዘና ውጤት አማካኝ የተቋሙ የምዘና ውጤት ተደርጎ ይቀመጣል፡፡

3.8.2 የስራ ክፍል አፈጻጸም ምዘና

Page | 13
በኢፊዲሪ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ የለውጥ ስራ አመራር አተገባበር
ማኑዋል(ረቂቅ)

1) እያንዳንዱ የስራ ክፍል ከተቋሙ የወረዱለትን ግቦች አፈጻጸም በመገምገም የውጤት ተኮር አፈጻጸሙን

መመዘን አለበት፣

2) የስራ ክፍል የውጤት ተኮር አፈጻጸም ምዘና የሚካሄደው ለስራ ሂደቱ በወረዱለት ግቦች ክብደት ስሌት ላይ

በመመስረት ይሆናል፣

3) የስራ ክፍል የውጤት ተኮር አፈጻጸም የምዘና ውጤት የስራ ሂደቱ ግቦች አማካኝ የአፈጻጸም ውጤት ነው፣

4) የስራ ክፍል የውጤት ተኮር አፈጻጸም ምዘና የሚካሄደው በየስድስት ወሩ ሲሆን ወቅታዊነታቸውን ጠብቀው

በተከታታይ በተያዙ መረጃዎች ላይ ተመስርቶ መሆን አለበት፣

5) የስራ ክፍል የውጤት ተኮር አፈጻጸም ምዘና የተቋም የውጤት ተኮር የአፈጻጸም ምዘና ከመካሄዱ በፊት

መጠናቀቅ ይኖርበታል፣

6) የስራ ክፍል የውጤት ተኮር አፈጻጸም ምዘና በለውጥ ሰራዊት የጋራ ውይይት ተካሂዶበት በስራ ክፍል ሃላፊ

መረጋገጥና ቀጥሎ ባለው ሃላፊ መጽደቅ አለበት፣

3.8.3 የዳይሬክተሮች የአፈጻጸም ምዘና

1) የዳይሬክተሮች የውጤት ተኮር አፈጻጸም ምዘና የሚከናወነው የስራ ክፍልን የግብ አፈጻጸም ውጤት እና ሌሎች

የአመራር ውጤታማነት መመዘኛዎችን በሰረት በማድረገ ነው፣

2) የዳይሬክተሮች የውጤት ተኮር አፈጻጸም ምዘና ውጤት የሚሰላው የስራ ክፍልን የግብ አፈጻጸም ውጤት

ከ 70% በመለወጥና ሌሎች የአመራርነት ክህሎትና ብቃትን ለመመዘን የሚያስችሉ መመዘኛዎችን የቅርብ ሃላፊው

ከ 15% በመመዘን፣የትብበር ቡድን ከ 10% እና በራሱ በተመዛኙ ከ 5% በመመዘን በሚገኘው የ 100% አጠቃላይ

ውጤት ይሆናል፤

3) የዳይሬክተሮች የሚመዘነው በየግማሽ አመቱ መጨረሻ ላይ ይሆናል፤

3.8.4 የሰራተኛ አፈጻጸም ምዘና

1) የሰራተኛ የውጤት ተኮር አፈጻጸም አዝማሚያ ክትትልና ግምገማ የሚካሄደው ፣የትብበር ቡድን አደረጃጀት

አግባብ በየሳምንቱ ይሆናል፤

2) የሰራተኛ የውጤት ተኮር አፈጻጸም አዝማሚያ ክትትልና ግምገማ የሚካሄደው የሰራተኛውን የሳምንት ውጤት

ተኮር እቅድ አፈጻጸም መሰረት በማድረግ ነው፤

3) የሰራተኛው የባህሪ አፈጻጸም በመማርና እድገት ውስጥ ከሚቀረጹ ግቦች አማካይነት ከስራው ጋር ተያይዘው

በየሳምንቱ ሊታቀዱና ክትትልና ግምገማ ሊደረግባቸው ይገባል፤


Page | 14
በኢፊዲሪ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ የለውጥ ስራ አመራር አተገባበር
ማኑዋል(ረቂቅ)

4) በየሳምንቱ የተካሄደው የሰራተኞች የውጤት ተኮር እቅድ አፈጻጸም አዝማሚያ በቅርብ ሀላፊ ተረጋግጦ

በሰነድነት መቀመጥ አለበት፤

5) በሰራተኛው ወርሃዊ የውጤት ተኮር እቅድ አፈጻጸም አዝማሚያ መረጃ ላይ ተመስርቶ በተከናወነ የአፈጻጸም

ውጤት መሰረት የወሩ የተሻለ ሰራተኛ በትብበር ቡድን ከተለየ በኋላ በስራ ክፍል ሀላፊው ይጸድቃል፤

6) የሰራተኛ አፈጻጸምን ለመመዘን ከውስጥና ከውጭ ተገልጋዮች የሚሰበሰቡ መረጃዎች ግብአት ሊሆኑ ይገባል፤

7) የሰራተኛ የግማሽ አመት የውጤት ተኮር አፈጻጸም ምዘናየሚከናወነው የየሳምንቱንና የየወሩን አፈጻጸም

እንዲሁም የስራ ሂደቱን የግማሽ አመት የውጤት ተኮር እቅድ አፈጻጸም ውጤት መሰረት በማድረግ በየግማሽ አመቱ

መጨረሻ ላይ የሰራተኛውን አፈጻጸም ከእቅድ ጋር በማነጻጸር ከ 70% እና በእቅድ አፈጻጸም ሂደት አስፈላጊ የሆኑ

ባህሪያት አፈጻጸምን ከ 30% በመውሰድ ነው፡፡

8) ከ 30% የሚወሰደው የሰራተኛ የባህሪያት አፈጸጸም ምዘና ፣የትብበር ቡድን ከ 15%፣ የቅርብ ሃላፊ ከ 10% ፣እና

ተመዛኙ ከ 5% ድርሻ በመስጠት በሶስትዮሽ የሚካሄድ ይሆናል፡፡

9) በተራ ቁጥር 7 የተጠቀሰው የ 70% ምዘና እና በተራ ቁጥር 8 የተጠቀሰው የ 30% የሶስትዮሽ ምዘና ድምር

የተጠቃለለ የሰራተኛ የ 100% የውጤት ተኮር አፈጻጸም ምዘና ውጤት ይሆናል፤

10) የተጠቃለለ የሰራተኞች የውጤት ተኮር አፈጻጸም ምዘና በዓመት ሁለት ጊዜ ማለትም የመጀመሪያው ስድስት

ወር እና የበጀት አመቱ ከተጠናቀቀ ብኋላ ባሉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ መከናወን አለበት፤

11) በየስድስት ወሩ መጨረሻ ላይ የሚካሄደው የሰራተኞች የውጤት ተኮር አፈጻጸም ምዘና ውጤት በሰራተኛው

ተፈርሞና በሚመለከታቸው የቅርብ ሃላፊዎች ጸድቆ ከሰራተኛው የግል ማህደር ጋር መያያዝ አለበት፤

12) በተቋም፣ በዳይሬክቶሬት እና በሰራተኞች ደረጃ የተካሄደው የውጤት ተኮር አፈጻጸም ምዘና እርስ በርሱ

የተናበበና ከግሽበት የጸዳ እንዲሆን አስፈላጊውን ክትትልና ድጋፍ ይደረጋል፡፡ የባህሪ የምዘናና የውጤት ተኮር ምዘና

ውጤት እንዲናበቡ ማድረግ፤


3.9 የውጤት ተኮር ሥራ አፈጻጸም ምዘና ደረጃ አሰጣጥ
በበጀት ዓመቱ በመጀመሪያው ስድስት ወር መጨረሻና በዓመቱ መጨረሻ ላይ የተሰጠና የጸደቀ የተቋም፣

የዳይሬክቶሬቱ የሰራተኛ የውጤት ተኮር ሥራ አፈጻጸም ምዘና ነጥብ በሚከተሉት አምስት የአፈጻጸም ደረጃዎች

ውስጥ ይወድቃል፣

1. በጣም ከፍተኛ አፈጻጸም፡- በዚህ የአፈጻጸም ደረጃ የሚመደብ ተቋም፣ የስራ ክፍልና ሰራተኛ የውጤት ተኮር
ጥቅል የዕቅድ አፈጻጸም ውጤቱ የመቶኛ ስሌት 95% እና በላይ ባለው ነጥብ ስር ያርፋል፤
Page | 15
በኢፊዲሪ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ የለውጥ ስራ አመራር አተገባበር
ማኑዋል(ረቂቅ)

2. ከፍተኛ አፈጻጸም፡- በዚህ የአፈጻጸም ደረጃ ውስጥ የሚመደብ ተቋም፣ የስራ ክፍልና ሰራተኛ የውጤት ተኮር
ጥቅል የዕቅድ የአፈጻጸም ውጤቱ የመቶኛ ስሌት ከ 80% -94.99% ባለው ነጥብ ስር ያርፋል፣

3. መካከለኛ አፈጻጸም፡- በዚህ የአፈጻጸም ደረጃ ላይ የሚመደብ ተቋም፣ የስራ ክፍልና ሰራተኛ የውጤት ተኮር
ጥቅል የዕቅድ አፈጻጸም ውጤቱ የመቶኛ ስሌት ከ 65%-79.99% ባለው ነጥብ ስር ያርፋል፤

4. ዝቅተኛ አፈጻጸም፡- በዚህ የአፈጻጸም ደረጃ ላይ የሚመደብ ተቋም፣ የስራ ክፍልና ሰራተኛ የውጤት ተኮር ጥቅል
የዕቅድ አፈጻጸም ውጤቱ የመቶኛ ስሌት ከ 55%-64.99% ባለው ነጥብ ስር ያርፋል፤

5. በጣም ዝቅተኛ አፈጻጸም፡- በዚህ የአፈጻጸም ደረጃ ላይ የሚመደብ ተቋም፣ የስራ ክፍልና ሰራተኛ የውጤት
ተኮር ጥቅል የዕቅድ አፈጻጸም ውጤቱ የመቶኛ ስሌት ከ 55% በታች የሆነ ነው፣
3.10 ድህረ ምዘና ተግባራት
1) መካከለኛ አፈጻጸምና ከዚያም በላይ ውጤት ያስመዘገቡ የስራ ክፍሎች ፣የስራ ክፍል ሀላፊዎችና ሰራተኞችን

በመለየትና የማበረታቻ መመሪያን መሰረት በማድረግ የእረከን ጭማሪ ፣የዕውቅና ሽልማትና የማበረታቻ ክፍያ

ለመስጠት አመቺ ሁኔታዎችን መፍጠርና ተግባራዊ ማድረግ ይገባል፤

2) በክትትል ግምገማና ምዘና በተገኘው ውጤት መነሻነት የሰራተኞችን እና የስራ ክፍል ሀላፊዎችን ብቃት

በስልጠናና ምክር በማጎልበት ቀጣይ ስራቸውን በሚጠበቀው የአፈጻጸም ውጤታማነት ደረጃ እንዲያከናውኑ

ለማድረግ ክፍተትን መሰረት ያደረገ የአቅም ግንባታ ስራዎችን ማከናወን ይገባል፤

3) የአፈጻጸም ምዘና ሲከናወን ዝቅተኛ አፈጻጸም ያስመዘገቡ ሰራተኞች በዚህ በአንቀጽ ቁጥር (2) መሰረት

በተቋሙ በሚደረግላቸው የአቅም ግንባታ ስራ ከዚያ በኋላ በተካሄዱት ሁለት ተከታታይ ምዘናዎች አፈጻጸማቸውን

ወደ መካከለኛ ደረጃ ካላሻሻሉ ካሉበት ደረጃ አንድ ደረጃ ዝቅ ብለው እንዲሰሩ ይደረጋል፤

4) የአፈጻጸም ምዘና ሲከናወን በጣም ዝቅተኛ አፈጻጸም ያስመዘገቡ ሰራተኞች በዚህ በአንቀጽ ቁጥር (2) መሰረት

በተቋሙ በሚደረግላቸው የአቅም ግንባታ ስራ ከዚያ በኋላ በተካሄዱት ሶስት ተከታታይ የምዘና ጊዜ አፈጻጸማቸውን

ካላሻሻሉ ከተቋሙ እንዲሰናበቱ ይደረጋል፤

3.11 ስለ ቅሬታ አቀራረብ

1) የስራ ክፍል ሀላፊ ወይም ሰራተኛው በተሰጠው የውጤት ተኮር ስራ አፈጻጸም ምዘና ውጤት ቅር የተሰኘ

እንደሆን ቅሬታውን ለቅርብ ሃላፊው በማቅረብ እንዲታይለትና ውሳኔ እንዲሰጠው መጠየቅ ይችላል፤

2) በዚህ አንቀጽ ቁጥር (1) መሰረት የስራ ሂደት መሪው ወይም ሰራተኛው በቅርብ ሃላፊው በተሰጠው ውሳኔ

የማይስማማ ከሆነ በመንግስት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 1064/2010 አንቀጽ 77/5 እንዲሁም በዲሲፕሊን
Page | 16
በኢፊዲሪ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ የለውጥ ስራ አመራር አተገባበር
ማኑዋል(ረቂቅ)

አፈጻጸምና ቅሬታ አቀራረብ ስነ ስርአት ደንብ ቁጥር 77/94 አንቀጽ 29 መሰረት ውሳኔ እንዲሰጠው በተቋሙ

ለተቋቋመው የቅሬታ አጣሪ ኮሚቴ በጹሁፍ ማቅረብ ይችላል ፤ኮሚቴውም በደንቡ አንቀጽ 33/2 መሰረት ውሳኔውን

ለሰራተኛው በጹሁፍ መስጠት አለበት፤

3) በዚህ አንቀጽ ቁጥር (1) መሰረት የስራ ሂደት መሪው ወይም ሰራተኛው በዲሲፕሊን አፈጻጸምና ቅሬታ

አቀራረብ ስነ ስርአት ደንብ ቁጥር 77/94 አንቀጽ 32 እና 33 መሰረት ምላሽ ካላገኘ ወይም በተሰጠው ውሳኔ ቅር

ከተሰኘ በዚህ ደንብ አንቀጽ 35/1 መሰረት ለመንግስት ሰራተኞች አስተዳደር ፍርድ ቤት ይግባኝ የማቅረብ መብት

አለው፤
ክፍል አራት

4. የትብብር ቡድን አደረጃጀት


የትብብር ቡድን በተለያዩ እርከኖች የተዋቀሩ የመንግስትና የህዝብ አደረጃጀት አካላትን የመገንባት ጉዳይ ነው፡፡ ዋነኛ

ይዘቱም በአመለካከት፣ በአሰራርና አደረጃጀት እንዲሁም በክህሎትና በዕውቀት ደረጃ ተቀራራቢነትና ከሞላ ጎደል

ወጥነት ያለው ፈጻሚ ኃይል መፍጠርን የሚመለከት ነው፡፡


4.1 የመንግሥት መዋቅር አካላት
1) የተቋሙ የበላይ አመራር

2) መካከለኛ አመራር፣

3) የስራ ቡድን

4) መላው ፐብሊክ ሰርቫንት

4.2 የህዝብ አደረጃጀት አካላት

1) የብዙሀንና ሙያ ማህበራት አደረጃጀቶች፣ብዙሃን ማህበራት የሚባሉት የተደራጁ የህብረተሰብ ክፍሎችን

የሚይዙ ሲሆኑ እነዚህም የተደራጁ የፆታ፣ የእድሜ ወይም የሙያ ማህበራት እንደ ሴቶችና ወጣቶች፣ መምህራን፤

ሰራተኛ ወ.ዘ.ተ ያሉትን የሚያጠቃልሉ ናቸው።

2) አጋር የህዝብ አደረጃጀቶች፡- በዚህ ደረጃ የሚታዩት በአብዛኛው የግል ልማታዊ ባለሃብት አደረጃጀቶች

ናቸው። ባለሃብቱ በነፃ ገበያ ኢኮኖሚ ማዕቀፍ እየተገነባ ላለው ስርዓት ሞተር ነው፡፡

3) ሌሎች ተገልጋዮች፡- ሌሎች ተገልጋዮች የሚባሉት ከላይ በህዝብ አደረጃጀት ከተጠቀሱት ውጭ የሆኑ ነገር

ግን ከመንግስት ተቋማት አገልግሎት የሚያገኙ ግለሰቦች ወይም ሌሎች የመንግስት ተቋማት ናቸው፡፡ ለምሳሌ

Page | 17
በኢፊዲሪ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ የለውጥ ስራ አመራር አተገባበር
ማኑዋል(ረቂቅ)

ከገንዘብ ሚኒስቴር በበጀት ጉዳይ ላይ አገልግሎት የሚያገኙ የመንግስት ተቋማት “ሌሎች ተገልጋዮች’’ በሚለው

ምድብ ውስጥ ይሆናሉ፡፡ በሰራተኛው አስተዳደር አገልግሎት ወይም በሪፎርም ዕገዛ በኩል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን

አገልግሎት የሚያገኙ ተቋማትና ግለሰቦችም እንደዚሁ “ሌሎች ተገልጋዮች” በሚለው ምድብ ውስጥ ይሆናሉ::
ክፍል አምስት

ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች

5. የአፈጻጸም ማሻሻያ አወሳሰድ

1) ተቋማት በየወቅቱ በሚደረጉ የውጤት ተኮር አፈጻጸም ግምገማዎች መሰረት በተለዩ ክፍተቶች ላይ የማሻሻያ

እርምጃዎች መውሰድ አለባቸው፤

2) የተቋም የበላይ ሃላፊ በተለያዩ ክፍተቶች ላይ መወሰድ የሚገባቸውን የማሻሻያ እርምጃዎች ተፈጻሚነት

በቅርበት መከታተል ይገበዋል፤

3) የስራ ክፍል በየወቅቱ በሚደረጉ የክትትልና ድጋፍ እንዲሁም የውጤት ተኮር አፈጻጸም ግምገማዎች መሰረት

በታዩ የአመለካከት ፣የእውቀትና የክህሎት ክፍተቶች እንዲሁም አሰራርና አደረጃጀት ላይየማሻሻያ እርምጃዎች

መውሰድ አለባቸው፤

4) የስራ ክፍል መሪዎች በስራ ሂደቱም ሆነ በሰራተኞች የውጤት ተኮር አፈጻጸም ዙሪያ የተሰጡትን የማሻሻያ

እርምጃዎች ተፈጻሚነት በቅርበት መከታተል ይጠበቅባቸዋል፤

5) የሰራተኞች የማሻሻያ እርምጃ በውጤት ተኮር አፈጻጸም ሂደት ወቅት በስራ ላይ ያጋጠሙትን ችግሮች

ለመፍታት ከአመለካከት ፣የእውቀትና የክህሎት ክፍተቶች እንዲሁም አሰራርና አደረጃጀት አኳያ ያለውን ጥንካሬና

ዕጥረት በመለየት የራስ አቅም ማጎልበቻ ዕቅድ በማውጣት ተገባራዊ ማድረግን ያካትታል፤
ክፍል ስድስት

6. የልዩ ልዩ አካላት ተግባርና ሃላፊነት

6.1. የበላይ ሃላፊ ተግባርና ሃላፊነት

1) የተቋሙ የአምስት አመት እንዲሁም አመታዊ እቅድ በመላው ሰራተኛ ተሳታፊነት በውጤት ተኮር ስርአት

መሰረት እንዲዘጋጅ ማድረግ፤

2) ዕቅዱ ከአገራዊ ራዕይ፣ከፖሊሲዎችና ስትራቴጅዎች ጋር የተሳሰረና የተናበበ መሆኑን ማረጋገጥ፤

Page | 18
በኢፊዲሪ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ የለውጥ ስራ አመራር አተገባበር
ማኑዋል(ረቂቅ)

3) የውጤት ተኮር ስርዐቱ ከበጀት ጋር የተሳሰረ መሆኑን ማረጋገጥ፤

4) የተዘጋጀው ዕቅድ የህዝብ አደረጃጀት ተሳትፎን ግብአት እንዲዳብርና የተሟላ ግንዛቤ እንዲያዝበት

አስፈላጊውን ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፣

5) የመካከለኛ አመራሩን የአመራር ክፍተቶች ለይቶ መደገፍና ማብቃት፤

6) ለዕቅድ ስኬት አስፈላጊ ግብአቶችን በወቅቱ ማሟላት ፤

7) የውጤት ተኮር እቅድ ትግበራና የአፈጻጸም ውጤታማነት በየጊዜው መከታተል ፣መደገፍ፣መገምገም እና

በበላይነት መምራት፤

8) ለመመሪያው ውጤታማነት ከሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ጋር በቅንጅት መስራት፤

6.2. የስራ ክፍል ሀላፊ ተግባርና ሃላፊነት

1) የተቋሙን ተልዕኮ፣ዕሴቶች፣ራዕይና ስትራቴጂ በሚገባ መረዳትና ከሰራተኞች ጋር የጋራ ማድረግ፣

2) የስራ ክፍሉን ጠንካራና ደካማ ጎን መለየት ፤

3) የተቋሙን ስትራቴጂያዊ ግብ በመመንዘር የስራ ሂደቱን ግብ እንዲሁም የግብ መግለጫዎችን እና የሚጠበቁ

ውጤቶችን ከሰራተኛው ጋር በመሆን ማዘጋጀት፤

4) ለሰራተኞች አፈጻጸም ሪፖርት ተገቢውን ግብረ መልስ በወቅቱ መስጠት፤

5) የስራ ክፍሉን የአቅርቦት ችግር መፍታት ፤

6) የስራ ክፍሉን አፈጻጸም የሚሻሻልበትን ስልት መቀየስና ተግባራዊ ማድረግ፤የሚገኙ ምርጥ ተሞክሮዎችን

መቀመር፤

7) በራሱና በስሩ ባሉ ሰራተኞች ዘንድ በአመለካከት ፣እውቀትና ክህሎት ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን ለመድፈን የግል

አቅም ማጎልበቻ ዕቅድ በማውጣት ተግባራዊ እንዲሆን አስፈላጊውን ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፤

8) የስራ ክፍሉን የማብቃትና ማቅናት ሥራዎችን የመስራት እና ጥሩ የስራ ከባቢን መፍጠር፤

9) የስራ ክፍሉን ተከታታይ መረጃዎች ላይ በመመስረት የስራ ሂደቱንም ሆነ የሰራተኞችን ወቅታዊ የውጤት ተኮር

አፈጻጸም ግምገማና ምዘና ማካሄድ፤

6.3. የቡድን መሪዎች ተግባርና ኃላፊነት

1) የተቋሙን ተልዕኮ፣ ዕሴቶች፣ ራዕይና ስትራቴጂ በሚገባ መረዳትና ከሠራተኞች ጋር የጋራ ማድረግ፣

2) የቡድኑን ጠንካራና ደካማ ጎን መለየት፣

Page | 19
በኢፊዲሪ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ የለውጥ ስራ አመራር አተገባበር
ማኑዋል(ረቂቅ)

3) ለሠራተኞች አፈጻጸም ሪፖርት ተገቢውን ግብረ-መልስ በወቅቱ መስጠት፣የቡድኑን አፈጻጸም የሚሻሻልበትን

ስልት መቀየስና ተግባራዊ ማድረግ፤ የሚገኙ ምርጥ ተሞክሮዎችንም መቀመር፣

4) በራሱና በሥሩ ባሉ ሠራተኞች የተግባራትን አፈፃፀም በላቀ ደረጃ ለመፈፀም የሚያስፈልጉ እውቀትና ክህሎት

ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን ለመድፈን የግል አቅም ማጎልበቻ ዕቅድ በማውጣት ተግባራዊ እንዲሆን አስፈላጊውን

ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፤

5) ቡድኑን የማብቃትና እንዲሁም ምቹ የሥራ ከባቢን መፍጠር፤

6) የቡድኑን ተከታታይ መረጃዎች ላይ በመመስረት የሰራተኞችን ወቅታዊ የውጤት ተኮር አፈጻጸም ግምገማና

ምዘና ማካሄድ፤

6.4. የሰራተኞች ተግባርና ሃላፊነት

1) የተቋሙን ተልዕኮ፣ዕሴቶች፣ራዕይና ስትራቴጂ በሚገባ መረዳት፤

2) የተመደቡበትን የስራ መደብ ሃላፊነትና ተግባራት በሚገባ ማወቅ፣መረዳትና ራስን ለትግበራ ዝግጁ ማድረግ፤

3) የውጤት ተኮር ስርአትን በአግባቡ መረዳትና ተግባራዊ ማድረግ፤

4) የግለሰብ የውጤት ተኮር እቅድ አዘጋጅቶ መፈጸም፤

5) በተጨባጭ የአፈጻጸም መረጃ ላይ በመመስረት አሰራርን ለማሻሻል ተገቢውን ጥረት ማድረግ፤

6) ለተግባራት አፈጻጸም መነሻ የሆኑ ከዕውቀትና ከክህሎት አንጻር የሚታዩ ጠንካራና ደካማ ጎኖችን መለየትና

የመፈጸም አቅምን ለማሳደግ ተገቢውን ጥረት ማድረግ፤

7) ፈጻሚው የራሱን መረጃ በአግባቡ መያዝ፤

6.5. የዕቅድና በጀት ዝግጅት፣ ክትትልና ግምገማ ቡድን ተግባርና ሃላፊነት

1) የተቋሙ የአምስት አመት እንዲሁም አመታዊ የውጤት ተኮር እቅድ ዝግጅትን ስራን መምራት፤ ማስተባበርና

መከታተል፤

2) በጸደቀው የውጤት ተኮር ዕቅድ መሰረት የተቋም ስትራቴጂያዊ ግቦች በየስራ ክፍሎች እንዲወርዱና ዓመታዊ

የውጤት ተኮር እቅድም በየስራ ክፍሎች እንዲዘጋጅ ማስተባበር ፣መከታተልና መደገፍ፤

3) የጸደቁ የስራ ክፍሉን ዓመታዊ የውጤት ተኮር እቅዶችን በማሰባሰብ ከበጀት ጋር የተሳሰረ የተቋም ዓመታዊ

የውጤት ተኮር ዕቅድ በማዘጋጀት በተቋም የበላይ ሃላፊ እንዲጸድቅ በማድረግ ለየስራ ክፍሎች

ማሰራጨት፣ትግበራውንም መከታተል፤

Page | 20
በኢፊዲሪ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ የለውጥ ስራ አመራር አተገባበር
ማኑዋል(ረቂቅ)

4) የየሩብ ዓመት የውጤት ተኮር እቅድ አፈጻጸም ሪፖርቶችን ከየስራ ክፍሎች በማሰባሰብና በመገምገም

ግብረመልስ መስጠት ፤በተቋም ደረጃ የውጤት ተኮር አፈጻጸም ሪፖርቶችን በወቅቱ ማዘጋጀት፤

5) የአፈጻጸም ሪፖርቶችን በመተንተን ለተቋም የበላይ ሃላፊ ውሳኔ ማቅረብ ፤ሲጸድቅም የአፈጻጸም ደረጃን

የሚያመላክት መረጃ ማዘጋጀት፤

6) በውጤት ተኮር ዕቅድ ላይ በተቀመጡት መለኪያዎችና ዒላማዎች መሰረት የተቋም ስትራቴጂክ ግቦች

የአፈጻጸም አዝማሚያን በመገምገም ለተቋም የበላይ ሃላፊ ማቅረብ፤

7) ስትራቴጂያዊ ግቦች የአፈጻጸም ደረጃን ለማወቅ የሚረዱ የዳሰሳ ጥናቶችን ማካሄድ፤

6.6. የለውጥና መልካም አስተዳደር ቡድን ተግባርና ሃላፊነት

1) በውጤት ተኮር አፈጻጸም ምዘና መመሪያ ላይ የተቋሙ የስራ ሃላፊዎችና ሰራተኞች በቂ ግንዛቤ መያዛቸውን

ማረጋገጥ፤

2) የውጤት ተኮር ስርዐት በተቋሙ በአግባቡ መተግበሩን መከታተል፤

3) በውጤት ተኮር ስርዐት ትግበራ ዙሪያ ቴክኒካዊ ድጋፍና ምክር መስጠት፤

4) በተቋም፣በስራ ሂደትና በፈጻሚዎች ደረጃ የተካሄደው የውጤት ተኮር አፈጻጸም ምዘና እርስ በርሱ የተናበበና

ከግሽበት የጸዳ እንዲሆን አስፈላጊውን ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፤

5) የውጤት ተኮር አፈጻጸም ምዘና ስርዓቱ ለተቋሙ እያስገኘ ያለውን ውጤት መከታተለልና መገምገም፤

6) የበላይና መካከለኛ አመራሩ በባለቤትና ቀጣይነት ባለው ሁኔታ እንዲመራው ማድረግና የተቀናጀ የለውጥ ስራ

አመራር ስርዓት የማስፈን ስራውን የዘወትር ስራው አድርጎ እንዲይዘው ማስቻል፤

6.7. የሰው ኃብት ስራ አመራር የስራ ሂደት ተግባርና ኃላፊነት

1) የሰራተኞች የውጤት ተኮር አፈጻጸም ምዘና ውጤት ወቅቱን ጠብቆ እንዲሞላና ለሰው ሃብት ስራ አመራር

የስራ ሂደት እንዲደርስ ክትትል ማድረግ፤

2) የሰራተኞች የውጤት ተኮር አፈጻጸም ምዘና ውጤት መረጃዎችን በአግባቡ መያዝ ፤የአፈጻጸም መረጃ ትንተና

በማዘጋጀትም ጥቅም ላይ እንዲውሉ ማድረግ፤

3) ከውጤት ተኮር አፈጻጸም ውጤት በመነሳትም የሰው ሃብት ልማትን ለማሳደግ የሚያስችል አሰራር መዘርጋት

እና ተግባራዊ ማድረግ፤

ክፍል ሰባት
Page | 21
በኢፊዲሪ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ የለውጥ ስራ አመራር አተገባበር
ማኑዋል(ረቂቅ)

7. ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች

1) በወሊድ ምክንያት ስራ ላይ የማይገኙ ሴት ሰራተኞችን በሚመለከት- ከወሊድ ፍቃድ ጋር በተያያዘ ምዘናው

በሚካሄድበት ግማሽ አመት ውስጥ ሶስት ወር እና በላይ በስራ ገበታቸው ላይ ከተገኙ ስራ ላይ የነበሩበት ጊዜ ታስቦ

የውጤት ተኮር ስራ አፈጻጸም ምዘና ይሞላላቸዋል፤ስራ ላይ የተገኙበት ጊዜ ከሶስት ወር በታች ከሆነ ግን ከዚያ በፊት

የነበረው ግማሽ ዓመት የውጤት ተኮር ስራ አፈጻጸም ምዘና ውጤት እንዲያዝላቸው ይደረጋል፤

2) በህክምና የተረጋገጠ ስራ ለመስራት የማያስችል ህመም ፤በማረሚያ ቤት ሆኖ ጉዳዩን በወቅቱ ለሚሰሩበት

ተቋም ማሳወቅ ያልቻሉ እና በሰው ሰራሽ ፣በተፈጥሮ አደጋ ምክንያት ወይም ደግሞ መስሪያ ቤቱ ባወቀውና

ተቀባይነት ባለው በሌላ ምክንያት ፣በመደበኛ ስራቸው ላይ ያልተገኙ እና ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ

ሰራተኞችን በሚመለከት ምዘናው በሚካሄድበት ግማሽ ዓመት ውስጥ ሶስት ወር እና በላይ በስራ ገበታቸው ላይ

መገኘታቸው ከተረጋገጠ ስራ ላይ የነበሩበትን ጊዜ መሰረት ያደረገ የውጤት ተኮር ስራ አፈጻጸም ምዘናና

ይሞላላቸዋል፤ ከሶስት ወር ካነሰ ግን ከዚያ በፊት የነበረው ግማሽ ዓመት የውጤት ተኮር ስራ አፈጻጸም ምዘና

ውጤት እንዲያዝላቸው ይደረጋል፤

3) ለሙከራ ጊዜ የተቀጠሩ ሰራተኞች አፈጻጸም በዚህ መመሪያ መሰረት የቋሚ ሰራተኞች የውጤት ተኮር ስራ

አፈጻጸም ምዘና አሞላል ስርአትን በመከተል የሚፈጸም ሆኖ የሙከራ ጊዜው የሚጠናቀቀው ከግማሽ አመት

አፈጻጸም ምዘና ወቅት ጋር በአንድ ጊዜ ከሆነና ሰራተኛው በሙከራ ምዘና ውጤት ቋሚ ሆኖ ከተቀጠረ የሙከራ ጊዜ

ምዘና ውጤት የግማሽ ዓመት አፈጻጸም ውጤት ተደርጎ ይያዛል፡፡ከዚያ ውጪ ከሆነ ቋሚ ከሆነበት ጊዜ ብኋላ ላለው

ጊዜ የውጤት ተኮር አፈጻጸም ምዘና የሚሞላለት ይሆናል፤

4) በዝውውር የሚመጡ ሰራተኞች በምዘናው ወቅት ሶስት ወር እና በላይ በተዛወሩበት መስሪያ ቤቱ ከስሩ

ይኽው ተመዝኖ የግማሽ ዓመት የምዘና ውጤት ሆኖ የሚሞላቸው ሲሆን የሰሩበት ጊዜ ከሶስት ወር በታች ከሆነ

በፊት በነበሩበት መስሪያ ቤት ውጤታቸውን ተመዝኖ መምጣት አለበት፣

5) በዕቅድ ውስጥ ያልተካተቱና በበላይ አመራሩ የሚሰጡ ተጨማሪ ስራዎች እንዲሁም ከተቋሙ ተልዕኮ ጋር

ተያያዥነት ያላቸው ሳምንት እና በላይ ጊዜ የሚወስዱ ወይም ከሳምንት በታች ሆነው በተደጋጋሚ የሚመጡ

የኮሚቴ ስራዎች ክብደት ተሰጥቷቸውና በመረጃ ተደግፈው የምዘና ሂደቱ ውስጥ የሚካተቱ ሲሆን አፈጻጸሙም

የኮሚቴ አባላት እንደ ሰራዊት በመገምገም ፣የአፈጻጸም ምዘና በማድረግና በኮሚቴው ሰብሳቢ በማጸደቅ ውጤቱ

ለሚመለከታቸው የስራ ሂደቶች እንዲደርስ በማድረግ ይሆናል፤


Page | 22
በኢፊዲሪ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ የለውጥ ስራ አመራር አተገባበር
ማኑዋል(ረቂቅ)

ክፍል ስምንት

8. የመልካም አስታዳደር ሁኔታን በተመለከተ

8.1. የመልካም አስተዳደር መርሆዎች

1) ተሳትፏዊነት

2) የጋራ መግባባት

3) ፈጣን ምላሽ መስጠት

4) ግልፅነት

5) ተጠያቂነት

6) ፍትሃዊነት

7) የህግ የበላይነት

8) ቅልጥፍናና ውጤታማነት

8.2. የመልካም አስተዳደር ዕቅድ ዝግጅት እና ትግበራ

1) የመልካም አስተዳደር ችግሮች መለያ የመረጃ ምንጮች

ከዜጎች፣ከህዝብ አደረጃጀት (ሙያና ብዙሃን ማህበራት ወይም ልዩ ልዩ አደረጃጀቶች) እና ከባለድርሻ አካላት

ከሚቀርቡ ቅሬታዎችና ጥቆማዎች (በመድረኮች፣ በአስተያየት ማሰባሰቢያ መዝገብና በሃሰብ መስጫ ሳጥኖችና፣

በአካል የሚቀርቡ)፣ከዕቅድ አፈጻጸም ክትትልና ድጋፍ (ሪፖርት፣ ሱፐርቪዥን፣ ግምገማ)፣ከዳሰሳ ጥናቶች፣

ከህትመትና ኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ

2) በስራ ክፍሎች የመልካም አስተዳደር እቅድ ዝግጅት

የአካዳሚው የስራ ክፍሎች የስራ ክፍላቸውን ሁኔታ በመፈተሽ በዋና ስራዎቻቸው ላይ ችግር ወይም ማነቆ

የሚሏቸውን ከውስጥና ከውጭ በመፈተሽና በመለየት እቅዳቸውን በዋናው እቅዳቸው ውስጥ በማካተት በመርሃ

ግብሩ መሰረት መተግበር ይጠበቅባቸዋል፤በተመሳሳይ ሪፖርታቸውንም በዚሁ መልክ በማካተት ለእቅድ፣በጀትና

ለውጥ ስራ አመራር ዳይሬክቶሬት በዚህ ማኑዋል በተቀመጠው የሪፖርት ማቅረቢያ ጊዜ መላክ ይኖርባቸዋል፡፡

ክፍል ዘጠኝ

9. የስብሰባ አፈጻጸም

Page | 23
በኢፊዲሪ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ የለውጥ ስራ አመራር አተገባበር
ማኑዋል(ረቂቅ)

ተቋማት የዕለት ከዕለት ስራቸውን ለማከናወን ከሚገለገሉባቸው የስራ አመራር ዘዴዎች አንዱ ስብሰባ ነው፡፡ ስብሰባ

አዳዲስና የተለያዩ ሀሳቦችን ለማመንጨት፣ ወሳኝ መረጃዎችን በተገቢው ሁኔታ ለማስተላለፍ፣ ለችግሮች መፍትሄ

ለመሻት፣ ጠቃሚ ውሳኔዎችን ለመወሰን እና በአጠቃላይ በአንድ ሰው ጥረት ውጤት የማያስገኙ ጉዳዮችን ሁለትና

ከዚያም በላይ በመሆን ውጤታማ አድርጎ ለመከወን የሚያስችል ቁልፍ መሳሪያ ነው፡፡

የስብሰባ አይነቶችን፣ ለውይይት መቅረብ የሚገባውን የአጀንዳ አይነትና ሊፈጅ የሚገባውን ተገማች ጊዜ ለይቶ

ማስቀመጥና ተግባራዊ ማድረግ።

1) ሳምንታዊ ስብሰባ

 አላማው ሳምንታዊ የስራ አፈፃፀምን እና የቀጣይ ሳምንት ዕቅድን መገምገምና ከስራ ጋር የተያያዙ

ያጋጠሙ ችግሮችን መፍታት ነው፡፡

 ከ 30 ደቂቃ - 1 ሰዓት በላይ መፍጀት አይጠበቅበትም።

2) ወርሀዊ ስትራቴጂክ ስብሰባ

 አላማው በተቋሙ የረዥም ጊዜ ስኬት ላይ ተጽኖ ሊያሳድሩ የሚችሉ ወሳኝ ጉዳዮችን በተመለከተ ውይይት

ማድረግ ነው።

 ከ 2 - 4 ሰዓት በላይ መውሰድ አይጠበቅበትም።

3) ወርሃዊ የአፈፃፀም ስብሰባ

 አላማው የስራ ክፍሎች ወርሃዊ እቅድ አፈጻጸማቸውን፤ ያጋጠሙ ችግሮችን እንዲሁም ቀጣይ የትኩረት

አቅጣጫ በጋራ የሚገመግሙበት የግንኙነት ጊዜ ነው

 ከ 1-2 ሰዓት በላይ መፍጀት አይጠበቅበትም።

4) የሩብ ዓመት ስብሰባ

 ይህ ስብሰባ አጠቃላይ በሩብ አመቱ የተከናወኑ ተቋማዊ ስትራቴጂክ ዕቅድ አፈጻጸሞችን በተጨማሪም

የተቋሙን አጠቃላይ ከስራ ሂደቶችና ሰራተኞች ጋር የተገናኙ ቁልፍ ጉዳዮችን ለመገምገም የሚውል ነው፡፡

 ከአንድ ቀን መብለጥ የለበትም።

5) የግማሽ ዓመት ስብሰባ

 ይህ ስብሰባ አጠቃላይ በግማሽ አመቱ የተከናወኑ ተቋማዊ ስትራቴጂክ ዕቅድ አፈጻጸሞችን በተጨማሪም

የተቋሙን አጠቃላይ ከስራ ሂደቶችና ሰራተኞች ጋር የተገናኙ ቁልፍ ጉዳዮችን ለመገምገም የሚውል ነው፡፡

 ከአንድ ቀን ተኩል በላይ መብለጥ የለበትም።


Page | 24
በኢፊዲሪ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ የለውጥ ስራ አመራር አተገባበር
ማኑዋል(ረቂቅ)

6) ዓመታዊ ስብሰባ

 ዓመታዊ ዕቅድና የእቅድ አፈጻጸም የሚገመገምበት ሲሆን፣

 ከ 1 – 2 ቀናት መብለጥ የለበትም።

ማኑዋሉን ስለማሻሻል

አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ይህ ማኑዋል በኢፊዲሪ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ ሊሻሻል ይችላል፡፡

Page | 25
በኢፊዲሪ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ የለውጥ ስራ አመራር አተገባበር
ማኑዋል(ረቂቅ)

አባሪዎች

Page | 26
በኢፊዲሪ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ የለውጥ ስራ አመራር አተገባበር ማኑዋል(ረቂቅ)

ቅጽ-1

1. የተቋም / የስራ ክፍል/ ቡድን እና የግለሰብ ፈጻሚ የ 6 ወር የውጤት ተኮር ዕቅድና ሪፖርት ማቅረቢያ ቅጽ

የስራ ክፍል/ዳይሬክቶሬት፡- ----------------------------------------------

ዕቅድ/ሪፖርቱ የሚሸፍነው ጊዜ ከ --------------------------- እስከ ---------------------------

ዕይታዎች/ የስራ ክፍሉ /ቡድኑ ዓመታዊ ዕቅድ የአፈጻጸም ሪፖርት


ከታች ግቦች
እይታዎቹ ዋና ዋና /ዝርዝር ክብደት ዒላማ ክንውን ንጽጽር ያጋጠመ ችግርና የተወሰደ
ቢዘረዘሩ/ ተግባራት መፍትሄ
ለተገልጋይ
20-25%፣

ለፋይናንስ
ዕይታ 10-
15%፣

ለውስጥ
አሰራር ዕይታ
30-40%
ለመማማርና
እድገት ዕይታ
20-30%

ፈጻሚ ስም፡- ------------------------- የኃላፊ ስም፡- -------------------------------


ፊርማ፡- ------------------------------ ፊርማ፡- -------------------------------------
በኢፊዲሪ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ የለውጥ ስራ አመራር አተገባበር ማኑዋል(ረቂቅ)

ቀን፡- ----------------------------- ቀን፡- ---------------------------------------

ቅጽ-2

2. የስራ ክፍል /የግለሰብ ፈጻሚ ሳምንታዊ የውጤት ተኮር ዕቅድና የአፈጻጸም ሪፖርት ማቅረቢያ ቅጽ

የስራ ክፍል /የግለሰብ ፈጻሚው ስም ፡- ------------------------- ቀን፡- ከ-----------/-----------/---------- እስከ -------/---------/-------

ዕቅድ የአፈጻጸም ሪፖርት


የስራ ያጋጠመ ችግርና የተወሰደ
ዝርዝር የሚከናወንበት ጊዜ
ሂደት/የፈጻሚ መለኪያ ዒላማ መፍትሄ
ተግባራት
ግቦች ሰ ማ ረ ሀ ዓ ክንውን ንጽጽር

የቅርብ ኃላፊ አሰተያየት፡- --------------------------------------------------------------------------------------------------------------------

የፈጻሚው /አመራሩ አስተያየት፡- -----------------------------------------------------------------------------------------------------------

Page | 1
በኢፊዲሪ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ የለውጥ ስራ አመራር አተገባበር ማኑዋል(ረቂቅ)

ቅጽ-3

3. የግለሰብ ፈጻሚዎች የባህሪ መገምገሚያ መነሻ መስፈርት ቅጽ

የስራ ክፍል፡- --------------------------


ምዘናው የተሞላለት ፈጻሚ ስም፡- ---------------------------- ምዘናውን የሞላው ስም፡- -----------------------
የስራ መደብ፡- --------------------------------------
ግምገማው የሚሸፍነው ጊዜ ከ ---------------------- እስከ ---------------------

ስራዎች በሚከናወኑበት ሂደት አስፈላጊ የሆኑ


ለመስፈርቱ ባህሪያት አፈጻጸም(30%)
ተ/ቁ የባህሪ መግለጫ መስፈርቶች የተሰጠው አስተያየት
ክብደት 5% 15% 10% አፈጻጸም
ከ 30%
1 የተቋሙን ራዕይና እሴቶች ተላብሶ ስራን መተግበር 10%
2 የቅርብ ሃላፊን ሳይጠብቅ ስራና ማከናወን 5%
ከለውጥ ሰራዊቱ ጋር በመግባባትና በቡድን ስሜት መስራት 15%
3

ልምድን በማካፈል ሌሎች በአመለካከት በክህሎትና በእውቀት ያለባቸውን ክፍተት ለሞሙላት ያለ 10%
4
ጥረት

Page | 2
በኢፊዲሪ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ የለውጥ ስራ አመራር አተገባበር ማኑዋል(ረቂቅ)

5 የአቅም ማጎልበቻ ተግባራትን በማቀድና በመተግበር የራሱን አቅም ለማጎልበት የሚደረግ ጥረት 15%
6 ለውጥ የሚያመጡ አዳዲስ ሃሳቦችንና አሰራሮችን ማመንጨትና መተግበር 5%
7 ተገልጋዮችን በተገቢው ክብርና ስነምግባር ማስተናገድ 10%
8 ታታሪና ስራ ወዳድ መሆን 10%
9 በመልካም ስነምግባርና ተልዕኮ ፈጻሚነት ለሌሎች ምሳሌ መሆን 10%
10 ከኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና ተግባር የጸዳ መሆን 10%
ማስታዎሻ፡- 5% በግለሰቡ የሚሞላ ፣15% በትብብር ቡድን የሚሞላ እንዲሁም 10% በቅርብ ኃላፊ የሚሞላ ይሆናል፡፡

ነጥብ ለመቀነሱ የተሰጠ አስተያየት


የግለሰብ አስተያየት _______________________________________________________________________________________________________________

የትብብር ቡዴኑ አስተያየት __________________________________________________________________________________________________________

የቅርብ ሀላፊው አስተያየት_____________________________________________________________________________________________________________

Page | 3
በኢፊዲሪ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ የለውጥ ስራ አመራር አተገባበር
ማኑዋል(ረቂቅ)

ቅጽ-4

4. የግለሰብ ፈጻሚዎች የ 6 ወር የአፈጻጸም ምዘና ማጠቃለያ

የሰራተኛው ሙሉ ስም ከነአያት ---------------------- የስራ መደቡ መጠሪያ --------------------- ደረጃ -----

የሥራ መደብ መጠሪያ ---------------------------------------------

የአፈጻጸም ምዘናው ጊዜ ከ ----------------------- አስከ ----------------------------

የምዘና የውጤት ተኮር እቅድ አፈጻጸም

ጊዜያት
አፈጸጸምን ከእቅድ ጋር ስራዎች በሚከናወኑበት ሂደት አስፈላጊ የሆኑ ባህሪያት አጠቃላይ

በማነጻጸር (70%) አፈጻጸም (30%) ውጤት


በተመዛኙ የተሰጠ በቡድን የተሰጠ በቅርብ ኃላፊ ከ 100% የአፈጻጸም

ውጤት (5%) ውጤት (15%) የተሰጠ ውጤት ደረጃ


(10%)

በአፈጻጸም ወቅት ሰራተኛው ያሳያቸው ጠንካራ ጎኖች፡-


-------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
-------------------------------------------------------

በአፈጻጸም ወቅት በሰራተኛው የታዩና መስተካከል የሚገባቸው

ክፍተቶች፡--------------------------------------------------------------------------------------------------------------------
---------------------------------------------

የቅርብ ኃላፊው ሙሉ ስም ------------------------------------- ፊርማ ---------------------- ቀን ---------------

በውጤት ተኮር አፈጻጸም ምዘና ውጤት ተስማምቻለሁ

የሰራተኛው ስም ------------------------------------- ፊርማ ---------------------------------- ቀን ----------------


በኢፊዲሪ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ የለውጥ ስራ አመራር አተገባበር
ማኑዋል(ረቂቅ)

በውጤት ተኮር አፈጻጸም ምዘናው ውጤት በሚከተለው ምክንያት አልተስማማሁም

የሰራተኛው ስም ------------------------------------- ፊርማ ---------------------------------- ቀን ----------------

Page | 1
በኢፊዲሪ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ የለውጥ ስራ አመራር አተገባበር
ማኑዋል(ረቂቅ)

ቅጽ- 5

5. የስራ ክፍል መሪ የአመራርነት ክህሎትና ብቃት የአፈጻጸም መመዘኛ ቅጽ

የአፈጻጸም ደረጃ
ለመስፈርቱ
የአመራርነት ክህሎትና ብቃት መገለጫ ውጤት በጣም በጣም
ተ/ቁ የተሰጠው ከፍተኛ መካከለኛ ዝቅተኛ አስተያየት
መስፈርቶች ከፍተኛ ዝቅተኛ
ክብደት
5 4 3 2 1
አፈጻጸምን የመከታተል ፣ወቅታዊ 10%
1
ግብረ መልስ የመስጠት ብቃት
የስራ ሂደቱን በማስተባበር በሳራዊት 15%
2
አግባብ የመምራት ብቃት
ሰራተኞችን የመደገፍና የማብቃት 15%
3
አቅም
በስራ ሂደቱ ተልዕኮዎች ላይ ያለው 15%
4
ተጨባጭ የዕውቀትና የክህሎት ደረጃ
የጸረ ኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና 10%
5
ተግባርን የመታገል ሁኔታ
ህዝብን በማገልገልና ህዝብን ጥቅም 10%
6
የማስቀደም ብቃት
በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ተልዕኮን 5%
7
የመወጣት ብቃት
ከተቋም የሚሰጥን ተልዕኮ በወቅቱ 10%
8
የመፈጸም ብቃት
የሰራተኛን አፈጻጸም ሚዛናዊ በሆነ 5%
9
መልኩ የመመዘን ብቃት
የባህሪ ውጤት ድምር
የባህሪ ውጤት ከ 30 የተቀየረ
የዕቅድ አፈጻጸም ውጤት ከ 70
የተጠቃለለ የስራ ሂደት መሪው ውጤት ከ 100

የስራ ክፍሉ ኃላፊ/ዳይሬክተር ስም፡- ------------------------- የቅርብ ኃላፊ ስም፡- -----------------

ፊርማ፡- ------------------------------ ፊርማ፡- -------------------------------------

ቀን፡- ----------------------------- ቀን፡- ---------------------------------------


በኢፊዲሪ መለስ ዜናዊ አመራር አካዳሚ የለውጥ ስራ አመራር አተገባበር
ማኑዋል(ረቂቅ)

ቅጽ-6

6. የህዝብ አደረጃጀት የተቋም አፈጻጸም መመዘኛ ቅጽ (20%)

የአፈጻጸም ደረጃ
ለመስፈርቱ ውጤት በጣም በጣም
ተ/ቁ መመዘኛ መስፈርቶች የተሰጠው ከፍተኛ መካከለኛ ዝቅተኛ አስተያየት
ከፍተኛ ዝቅተኛ
ክብደት
5 4 3 2 1
የህዝብ አደረጃጀት በዕቅድ ዝግጅትና 10%
1 አፈጻጸም ውይይት ላይ በተቀመጠው
የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ከማሳተፍ ብቃት
የህዝብን የማገልገልና ህዝብን ጥቅም 15%
2
የማስቀደም ብቃት
የተቋሙን የዜጎች ቻርተር ለተገልጋዩ 15%
3 /ዜጋው ግልጽ የማድረግና በስታንዳርዱ
መሰረት አገልግሎት የመስጠት ብቃት
በዜጋው/በተገልጋዩ የሚሰጡ 10%
4 አስተያየቶችን በመቀበልና እንደ ግብአት
ወስዶ ማስተካከያ የማድረግ ብቃት
የተለዩ የውስጥና የውጭ የመልካም 15%
5 አስተዳደር ችግሮችን በተቀመጠው
ዕቅድ መሰረት የመፍታት ብቃት
የአመራሩ ቁርጠኛ ሆኖ የመምራት 10%
6
ብቃት
የተለዩ ኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና 15%
7 ተግባርን በስትራቴጂው መሰረት
የመቀነስ ብቃት
የህዝብ አደረጃጀት አቅም የመገንባት 10%
8
ብቃት
የተጠቃለለ ውጤት(100) ከ 100%

Page | 1

You might also like