Professional Documents
Culture Documents
ELU
ELU
1) የሙስና ምንነት፣
በአደራ የተሰጠን ሥልጣን ለግል ጥቅም ማዋል፣ እምነትን ማጉደል ወይም አለመታመን፣ በጉቦ፣
በምልጃና በአድሎ ሃቅን፣ ውሳኔን ወይም ፍትህን ማዛባት ነው (Transparency International
2008)፡፡
ሙስና የመንግስትን ሥራ ሥነምግባራዊ እና ህጋዊ መሠረት ባለው መመሪያና ደንብ ላይ ተመርኩዞ
ማከናወን አለመቻል ነው ይለዋል /የሙስና ቅኝት በኢትዮጵያ 1993/፡፡
ሙስና ለግል ወይም ለቡድን ጥቅም ሲባል ሥርዓቶችን፣ ህጎችን፣ ደንቦችን፣ አሰራሮችን፣ መርሆዎችን
የመጣስ ማንኛውም ተግባር ነው (Kato, 1995)፡፡
ሙስና የፖለቲካና የመንግስት አስተዳደራዊ ኃላፊነትን ካለመወጣት የሚመነጭ፣ ማህበራዊና
አስተዳደራዊ ሥርዓቶችን የመጣስ የሥነምግባር ግድፈት ሲሆን ይህም ለግል ጥቅም ሲባል በህዝብ
የተሰጠ ሥልጣንና ኃላፊነትን አላግባብ በመጠቀም ህግና ደንብ የመጣስ እኩይ ተግባራትን
ያካትታል / ቻርለስ ሳን ፎርድ 1998/፡፡
2) የሙስና ወንጀል ልዩ ባህሪያት
የሙስና አንዱ ባህሪ በተለያዩ ዘርፎች እና በተለያየ ደረጃ ከታችኛው እርከን ጀምሮ እስከ ከፍተኛው
እርከን ድረስ የሚከሰት መሆኑ ነው፡፡
የአፈጻጸሙ ሂደትና ሥልት እንዳይደረስበት ለማድረግ በከፍተኛ ጥናት፣ በጥንቃቄና በሚስጢር
የሚፈጸም ነው፡፡
3) በማደግ ላይ ያለዉ የህብረተሰቡ የፀረሙስና ትግል
ሙስናና ብልሹ አሰራርን ከመከላከል አንጻር ሙሰኞችን በማጋለጥና ኢ-ሥነምግባራዊ ድርጊቶችን
በግልጽ በመኮነን የሚያበረክተዉ አስተዋጽኦ ጉልህ ነዉ፡
የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ በሥነምግባር ግንባታ ሥራ ረገድ ቁልፍ ሚና መጫወት
ጀመሩ፣የህብረተሰቡ የሚዲያ አጠቃቀም ማደግ፣የማህበራዊ ሚዲያዎች ተጠቃሚዎች መበረካት
ችግሩን ለመከላከል በሚደረገዉ ጥረት አጋዥ ሚና ይኖረዋል፡፡
4) ተግዳሮቶች፤
የተደራጀ ፖሊሲ ያለመኖር፣
በአንዳንድ የመንግስት አመራሮች ትኩረት ያለማግኘት፣
በሀገሪቱ ያለው የፖለቲካ አለመረጋገት፣
የኑሮ ዉድነት መጨመር፣
5) የፀረ-ሙስና ትግል ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች፤
ተቋማዊ አደረጃጀትና አሠራር ማጠናከር፣
የሥነምግባር እና የሞራል ዕሴቶች ግንባታ ማጠናከር፣