You are on page 1of 3

የቀለም አቅርቦት ውል ስምምነት

ውል ሰጪ፡ ቤአኤካ ጠቅላላ ንግድ ስራ ኃ/የተ/የግ/ማ አድራሻ አዲስ አበባ ክ/ከተማ ጉለሌ
ወረዳ 18/16 የቤ.ቁጥር 121/13/5

ውል ተቀባይ ፡ ሻይኒንግ ስቶን ኢንተርናሽናል ቢዝነስ አድራሻ አዲስ አበባ ክ/ከተማ


ወረዳ የቤ.ቁጥር .

አንቀፅ አንድ

የውሉ አላማ

ውል ሰጪ ለውል ተቀባይ ከሚያመርታቸው ቀለሞች ውስጥ ነጭ የትራፊክ ቀለም


ብዛት 8627 እንዲሁም ቢጫ የትራፊክ ቀለም ብዛት 18616 አምርቶ ለውል ተቀባይ
እስከ ቀን 2 ዐ 12 ለማቅረብ የተደረገ ስምምነት ነው፡፡

አንቀፅ ሁለት

የውል ሰጪና ተቀባይ ግዴታ

2.1 ውል ተቀባይ በተሰጠው የዋጋ ማቅረቢያ መሠረት አንዱን የ 150 ሊትር ነጭ ቀለም
ተ.እ.ታ ጨምሮ በብር 155.00 ( አንድ መቶ ሃምሳ አምስት ብር) እና አንዱን ባለ 150
ሊትር ቢጫ ቀለም ተ.እ.ታ ጨምሮ በብር 184.00 (አንድ መቶ ሰማንያ አራት ብር)
ለመግዛት ተስማምተዋል፡፡

2.2 ውል ሰጪ የሚያመርታቸውን ቀለሞች ውል ተቀባይ ቅድመ ክፍያውን ፈጽሞ


የምርት ትእዛዝ ከሰጠበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15/አስራ አምስት/ የሥራ ቀናት ውስጥ
አቅርቦ ያጠናቅቃል፡፡
2.3 ውል ተቀባይ የተመረተለትን ምርት አዲስ አበባ ከሚገኘው የውል ሰጪ መጋዘን
ይረከባል፡፡

አንቀፅ ሦስት

የክፍያ አፈፃፀም ሁኔታ

ይህ ውለታ እንደተፈፀመ ውል ተቀባይ የአጠቃላይ ግዢውን ብር 4762529.00 (አራት


ሚሊየን ሰባት መቶ ስልሳ ሁለት ሺህ አምስት መቶ ሃያ ዘጠኝ ብር) 50% በመቶ ብር
2,381,264.5 ዐ (ሁለት ሚሊዮን ሶስት መቶ ሰማንያ አንድ ሺ ሁለት መቶ ስድሳ አራት
ብር ከሃምሣ ሳንቲም) ይከፍላል፡፡ ቀሪውን ብር 2381264.50 (ሁለት ሚሊየን ሶስት
መቶ ሰማንያ አንድ ሺህ ሁለት መቶ ስልሳ አራት ብር ከሃምሳ ሳንቲም) አጠቃላይ
ምርቱን በተረከበ በ 2 (በሁለት) ወራት (60) ስድሳ ቀናት ውስጥ አጠናቆ ገቢ ያደርጋል፡፡
በዋስትናነትም ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የሚዘጋጅ የባንክ ጋራንቲ (Unconditional Bank
Guarantee) ማስያዝ ይኖርበታል፡፡

አንቀፅ አራት

ውሉ የሚፀናበት ጊዜ

ይህ ውል ሁለቱ ወገኖች ከተፈራረሙበት ጀምሮ


የፀና ይሆናል፡፡

ውል ሰጪ ወል ተቀባይ

ስም ስም
ሃላፊነት ሃላፊነት

ፊርማ ፊርማ

ቀን ቀን

እማኞች

ስም ፊርማ ቀን
.
.
.

You might also like