You are on page 1of 7

ቀን 24/01/2011 ዓ.

ከሀገር ውስጥ የአቅራቢ ወኪሎች ጋር የተደረገ ውይይት


የስብሰባ ቦታ ………………. እምቢልታ ሆቴል
ሰዓት……………………….. 3፡15-6፡30
የውይይት መነሻ አጀንዳዎች
1. ስለጨረታ ዝግጅትና ተሳትፎ እውቅና ገለጻ ማድረግ- በጨረታ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር
(ሰይፉ ኢሳ)
2. የተጫራቾች የአፈጻጸም መመዘኛ መስፈርቶች ገለጻ ማድረግ- በውል አስተዳደር ዳይሬክቶሬት (
ወንደሰን ቀረመንዝ)
3. ከአቅራቢዎች ጎን የሚነሱ ነጥቦች ላይ ውይይት ማድረግ
አጀንዳ አንድ፡- ስለጨረታ ዝግጅትና ተሳትፎ እውቅና የተደረገ ገለጻ
በቅድሚያ በኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ጎይቶም ጊጋር የመክፈቻ ንግግር የተደረገ ሲሆን

የአምስት አመት የረጅም ጊዜ እቅድ ክለሳ መደረጉንና በክለሳ ወቅትም የኤጀንሲው የሥራ እንቅስቃሴ የቀጥታ

መስመር ፍሰት የነበረው መሆኑ የተገመገመ በመሆኑ ከዚሁ ግኝት በመነሳት ኤጀንሲው በዙሪያው ካሉ

የባለድርሻ አካላትና አቅራቢዎች ጋር የቅርብ ግንኙነት እንዲፈጠር ታስቦ እየተሰራ እንደሆነና የዚህ ስብሳበም

የእቅዱ አካል መሆኑን በመግለጽ ስብሰባውን በይፋ ከፍተዋል፡፡

በመቀጠልም በጨረታ አስተዳደር ዳይሬክተር ገለጻ የተደረገ ሲሆን የሚከተሉት ነጥቦች ላይ ትኩረቱን ያደረገ

ውይይት ተካሒዷል፡፡

 እስከ 2010 እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር በተደረገ አሰሳ የሀገር ውስጥ አቅራቢዎች ድርሻ ከ 20 ፐርሰንት

በታች መሆኑን ግምት ውስጥ በማስገባት የሀገር ውስጥ ወኪሎች ጋር መወያየት ማስፈለጉን፣,

 በጨረታ ተሳትፎየተጫራቾችን የምዝገባ ፍላጎት በመጨመር እና የተመዘገቡ መድኃኒቶች ያሏቸው

አቅራቢዎች በአሁኑ ሰዓት ወደ ጨረታ ለመሳተፍ እየመጡ ባለመሆኑ የማበረታታት ስራ

የኤጀንሲውና የሀገር ውስጥ ወኪሎች መሥራት እንዳለባቸው የተገለጸ ሲሆን አንደማሳያ የ 2010

ዓ.ም ጨረታዎች ሲታዩ ለጨረታ ከተሳተፉ አቅራቢዎች ውስጥ የተመዘገቡት 36 ፐርሰንት ብቻ


ሲሆን ነገር ግን ጨረታ ላይ ከወጡት መድኃኒቶች ውስጥ 52 ፐርሰንት ያህሉ ግን በመድኃኒትና ምግብ

ቁጥጥር ባለስልጣን የተመዘገቡ እንደነበር፣

 በኤጅንሲው እና በሀገር ውስጥ ወኪሎች መካከል የተግባቦት ችግር መኖሩንና የጨረታዎች ክትትል እና

ተገቢው ሰነድ እንዲቀርብ የሚደረግ የወኪል ካምፓኒዎች ድርሻ ከፍተኛ ቢሆንም የተወሰኑ

ካምፓኒዎች ላይ የክትትል ድከመት በሞኖሩ የግዥ ሒደቶች መጓተት እንደገጠማቸው፣

 በገለጻው ማጠቃለያ ላይ የአቅርቦት ሰንሰለቱን ለማስተካከል ቅርብ የሆነ ግንኙነትና ትብብር

በማድረግ ብቁ የሆኑ ተጫራቾችን ወደ ሀገር ውስጥ በመጋበዝ እና እንዲያስመዘግቡ በማበረታታት

የአቅርቦቱን ሰንሰለት ማሻሻል እንደሚገባ ተገልጿል፡፡

አጀንዳ ሁለት፡-የተጫራቾች የአፈጻጸም መመዘኛ መስፈርቶች የተደረገ ገለጻ


በመቀጠልም ኤጀንሲው ግለሰባዊ፣ የስራ ሒደት እና ተቋማዊ የመለኪያ መስፈርቶችን ያደራጀ በመሆኑ ይህን

ለማሳካት የአቅራቢዎችን አፈጻጸም መለካት ለመጀመር ማቀዱን እና ይህንም ለማስኬድ Average

Supplier Rating Score የሚባል ዘዴ እንደሚጠቀም የተገለጸ ሲሆን በአጠቃላይ የአቅራቢዎችን አፈጻጸም

በማየት በሚከተሉት ምድቦች እንደሚከፋፈሉ ተገልጿል፡፡

ሀ. እጅግ በጣም ጥሩ አፈጻጸም ያላቸው አቅራቢዎች

ለ. በጣም ጥሩ አፈጻጸምያላቸው አቅራቢዎች

ሐ. ጥሩ አፈጻጸም ያላቸው አቅራቢዎች

መ. አጥጋቢ አፈጻጸም ያላቸው አቅራቢዎች እና

ሠ. ደካማ አፈጻጸም ያላቸው እቅራቢዎች በሚል እንደሚመደቡ ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡

ወደዚህ ሥርዓት ለመግባት ያመች ዘንድ በቅድሚያ በኤጀንሲውና አቅራቢዎች በኩል የነበሩ የሥራ

እንቅስቃሴዎች ላይ በተደረገ አሰሳ ደካማ ጎኖች የተለዩ መሆናቸው የተገለጸልጾ ሲሆን እንደሚከተለዉ ቀርቧል

እነዚህም
 የክፍያ መዘግየት

 ከመጫኚያ ወደቦች በተቀመጠው ክፍለ ጊዜ ጭነቶችን አለማንሳት

 ደካማ የውል አስተዳደር

 የአቅራቢዎችን አፈጻጸም መመዘን አለመቻል

 በውስጥ እና በውጭ አሰራር ርዝማኔ የሚፈጠር ተደጋጋሚ የክምችት መሳሳት

 የተጋነነ የባንክ ክፍያ

 ተደጋጋሚ የክፍያ ጊዜ የማራዘሚያ ጥያቄዎች

መሆናቸውን ለተሰብሳቢው ገለጻ ተደርጓል፡፡

አጅንዳ ሶስት፡- ከአቅራቢዎች ጎን የተነሱ ነጥቦች ላይ የተደረገ ውይይት

ከላይ በተቀመጡ ሁለት አጀንዳዎች ላይ በኤጀንሲው ገለጻ ከተደረገ በኋላ እድሉ ወደ ተሳታፊ የአቅራቢ

ወኪሎች የተሰጠ ሲሆን

 የአፈጻጸም መለኪያዎች ላይ

 በአቅርቦት ጊዜ ሰሌዳ ላይ

 በጨረታ አስተዳደር ላይ

 በውል አስተዳደር ላይ

 በክፍያ ሁኔታዎች ላይ

 በጭነት አያያዝ እና ርክክብ ላይ

እንደመነሻ ይሆናቸው ዘንድ ሊነሱ የሚችሉ የተሞክሮ እና የማስተካከያ ሀሳቦች ላይ ውይይት የማድረግ እድል

ቀርቧል፡፡ ይህን ተከትሎ የሚከተሉት ነጥቦች በተሳታፊዎች ቀርቧል፡፡

 የውል ማስከበሪያ ዋስትና ጸንቶ የሚቆይበት የጊዜ እርዝማኔ አንድ አመት መሆኑ ተጨማሪ ወጭ

እያመጣ እንደሆነ እና ወደ ስድስት ወር የሚያጥርበት ሁኔታ ቢመቻች፣


 አየር መንገድ መቆየት ያለበት 21 ቀን ነው ቢባልም ከዚያ ባነሰ ጊዜ ውስጥ እቃው ተነስቶ አያለ

የመጋዘን (demurrage cost) ክፍያ አቅራቢዎች የተጠየቁበት ሁኔታ እንዳለ፣

 የአቅራቢዎች ዋና መስሪያ ቤት አድራሻ እና የአምራች አድራሻ የተለያየ ሲሆን ክፍያ ላይ አስተካክሉ

መባሉ ሌላ ችግር እየፈጠረ እንደሆነ፣

 የውል ማስከበሪያ ዋስትና ከተፈረመ ውል ጋር እናመጣ የነበረው ልምድ በመቀየሩ ኤጀንሲው በፈለገ

ጊዜ ስንጠየቅ በአስቸኳይ መባሉ በእኛ እና በአቅራቢዎች ላይ የሥራ ጫና እየፈጠረ እንደሆነ፣

 ኤጀንሲውና እና አቅራቢዎች የሚገናኙበት ወጥ የሆነ እና ተቋማዊ የሆነ መገናኛ መንገድ ቢፈጠር

ማለትም ኢ-ሜል ወይም አውቶሜትድ የሆነ መልስ ሊሰጥ የሚችል ሥርዓት ቢዘረጋ፣

 ተከላ የሚፈልጉ የሕክምና መሳሪያዎችን ግዥ በተመለከተ አዲስ የተጀመረው የ 70/30 የአከፋፈል

ሥርዓት የጊዜ ገደብ ያልተቀመጠለት በመሆኑ በተለይም ትላልቅ አቅራቢዎችን እንዲያፈገፍጉ

እያደረገ እንደሆነ፣

 ቀድሞ የታወቀ የክፍያ ክፍለጊዜ ባለመኖሩ የአሰራር ሒደታችንን እያራዘመብን እንደሆነ፣

 በተለያዩ የአሰራር መጓተቶች ምክንያት ዘግይቶ የተከፈተ ክፍያ ላይ ሁሌም አስቸኳይ ነው የሚል

የጭነት ጥያቄ ጫና እየፈጠረ እንደሆነ፣

 በጨረታ ሰነዱ ላይ የሚመለከተውን የግምገማ እና ሌሎች ክፍለጊዜዎችን ኤጀንሲው የማይጠብቅ

በመሆኑ አቅራቢዎች በሀገር ውስጥ ወኪሎች ላይ አመኔታ እንደዳይኖራቸወ ከማድረጉም በላይ እና

ዘግይተው የሚወጡ የምዘና ውጤቶች ደግሞ በጨረታ ለመሳተፍ ያላቸውን ፍላጎት እየቀነሰ

እንደሆነ፣

 የኤጀንሲውን የመረጃ ደህንነት ለመጠበቅ በሚል የግዥ ሰራተኞችና አቅራቢዎች ግንኙነት እየራቀ

እንደመጣና የሠራረተኞች ተደራሽነት አናሳ ደካማ እንደሆነ፣

 ቀድሞ የሚደረግ ፍተሻ ባለመኖሩ የኢትዮጵያ ጭነት ተቀባይ ከተረከበ በኋላ እና ከኢትዮጵያ የጭነት

መዳረሻ ላይ ከደረሱ በኋላ የሽረት ጊዜያቸው ያለፈባቸውን እና ጎደሉ የተባሉ ምርቶችን እንድንተካ
ግፊት መደረጉ አግባብነት እንደሌለውና በተለይም የህክምና መሳሪያያዎች ጉድለት እየተስተዋለ

እንደሆነና ይህንም ክፈሉ መባሉ ተገቢ እንዳልሆነ፣

 የጨረታ አከፋፈት ግልጸኝነት እንደሚጎለው፣

 የግዥ ክፍል የቢሮ አቀማምጥ ሥርዓት የተከተለ አለመሆኑን፣

 የሥጋት አፈታት ሥርዓት አለመኖሩ ሁሌም ኤጀንሲው በሥጋት ውስጥ እንደሆነ፣

 የሞባይል ቴክኖሎጅን ለአቅርቦት ሰንሰለቱ ለመጠቀም ቢቻል፣

 በተቀመጠው ጊዜ ገደብ ግባቶችን ለማስገባት የኢትዮጵያ የጭነት አጋሮች ጋር ተገቢው ሰነድ

እንዲቀርብ እና ተከታታይ ግንኙነቶች መኖር እንዳለባቸው፣

 የህክምና መሳሪያዎችን በተመለከተ የ FMHACA ምዝገባን መሰረት አድርጎ ምዘና መካሔዱ እጅግ

ታዋቂ የሆኑ አለማቀፋዊ አምራቾች እጅግ የተንዛዛ የምዝገባ ሒቱን በመተው እየራቁ እንደሆነ፣

 የሕክምና መሳሪያዎች የመስፈርት አዘገጃጀት በጣም ደካማ እንደሆነና አንዳንዴም ለተወሰኑ

አቅራቢዎች ያደላ እንደሆነ እና የፍላጎት መግለጫ ዝግጅት ሲደረግ ከኤጀንሲው ውጭ ያሉ አካላት

እንዲካተቱ መደረጉ አግባብነት እንደሌለው፣

 የህክምና መሳሪያዎች አምራች ድርጅቶችን ጉብኝት በማድረግ የማረጋገጥ ሥራ ቢሠራ፣

 የተጋነነ የህክምና መሳሪያዎች ዋጋ ልዩነት ከምን እንደመጣ ዳሰሳ ሳይደረግ ወደ ኮንትራት አዋርድ

መሄድ እንደሌለበት፣

 ኤጀንሲው ገለልተኛ በሆኑ አካላት የሚገመገምበት አካሔድ ቢኖር፤

በተሳታፊዎች ሀሳብ ከቀረበ በኋላ ከኤጀንሲው በኩል ለእነዚህ መልስ የሚሆኑ ሀሳቦች የቀረቡ ሲሆን

በሚከተለው መልኩ ቀርበዋል፡፡

 የግንኙነት ሥርዓት ለመዘርጋት የተጀመሩ ሥራዎች ያሉ በመሆኑ በቅርቡ የተግባቦት ሥርዓት

ይስተካከላል፤
 ኤጀንሲው ክፍያ የሚፈጽመው በመጀመሪያ በቀረበው ሰነድ ላይ በተመለከተው አድርሻ በመሆኑ

በክፍያ ጊዜ መቅረብ ያለበት አድራሻ እና የመጀመሪያው አድራሻ ተመሳሳይ መሆን አለበት፤

 ኤጀንሲው የራሱ የሆነ የባዮሜዲካል ባለሙያዎች በምጠና ክፍል፣ በግዥ ክፍል፣ በውል አስተዳደር

ክፍልና በሥርጭት ክፍል በቂ ሙያተኞች ያሉበት ሲሆን የኤጀንሲው ሙያተኞች ያልተሳተፉበት

የሕክምና መሳሪያዎች የፍላጎት መግለጫ (የመስፈርት ዝግጅት) እንዳልተከናወነ፤

 የክፍያ ጊዜ ቀድሞ የማይተነበይበት ምክንያት የውጭ ምንዛሬ ፈቃጅ አካል የተለየ አካል በመሆኑ

እንደሆነ፣

 ግልጸኝነትን በተመለከተ ማነኛውንም ጥያቄ ቀጠሮ አስይዞ ማነጋገር እና የተለየ ጥቆማም ካለ

በማኛውም ሰዓት ለመቀበል ኤጀንሲው ዝግጁ እንደሆነ እና ሌሎች አስፈላጊ የማሻሻያ

ዘዴዎችንም ለመከተል ኤጀንሲው ዝግጁ እንደሆነ፤

 በአቅርቦት ሰንሰለቱ ላይ ግንኙነታችን ጥሩ የመተማመን ደረጃ ላይ ከደረሰ ያለምንም የውል እና

የጨረታ ማስከበሪያ ግዥ ለመፈጸም ኤጀንሲው ዝግጁ እንደሆነ፤ ነገር ግን እስካሁን ያለውን

ሥርዓት ለማስተካከል ኤጀንሲው ዝግጁ እንደሆነ፤

 ረጅም የግምገማ ሒደትን በተመለከተ ኤጀንሲው ከመልሶ ቅየሳ በኋላ በአጭር ክፍለጊዜ ውስጥ

የግምገማ ሒደቶችን እያጠናቀቀ እንደሆነና ለወደፊትም ወደ ማዕቀፍ ግዥ በማዘንበል የበለጠ

ቀልጣፋ የምዘና ሒደት እንደሚያጎለብት አቅጣጫ እንደተቀመጠ፤

 የ 70/30 የሕክምና መሳሪያዎችን ክፍያ በተመለከተ ቀሪ 30 ፐርሰንቱ እቃው በገባ አንድ አመት

ውስጥ የሚፈጸም መሆኑን በውል ላይ እያሰርን እንደሚቀጥል ውሳኔ ላይ ተደርሷል፤

 የአቅራቢዎችና የኤጀንሲው ግንኙነትም ቀጣይነት ያለው እንደሚሆን እና አለማቀፋዊ የሆኑ

የመመዘኛ መስፈርቶችና ሒደቶችን የተከተለ ምዘና በማድረግ አቅርቦቱን ለማሻሻል

እንደሚሰራ፤

 ኤጀንሲው ወደ ፊት ክፍያ እንዳይዘገይ ቀድሞ አመታዊ ፍላጎቱን ለብሔራዊ ባንክና ለመንግስት

እያሳወቀ በመሆኑ የክፍያ መዘግየት እንደማይኖር፤


 የቆጠራ ጉድለት ሲፈጠር ማን መጠየቅ እንዳለበት የሚገልጽ የርክክብ ማንዋል ተዘጋጅቶ ወደ

ትግበረ የተገባ ሲሆን ሁሉም በጉዞ ሒደት ላይ የተነካኩ አካላትን ተጠያቂ የሚያደርግ ሥርዓት

እንደሚዘጋጅ፤

 ኤጀንሲው የአቅርቦት ሠንሰለት መለኪያና መገምገሚያ የማዕቀፍ ሕግ ለማስቀመጥ የሚያስችል

አሰራር ለማዘጋጀት በሒደት ላይ እንደሆነ፤

 ኤጀንሲው በአጋር ድርጅቶች፣ በውስጥ እና በውጭ ኦዲተሮች እየተገመገመ በየጊዜው የማሻሻያ

ሥራዎች እየሰራ የመጣ ድርጅት እንደሆነ፤

 የመረጃ አያያዝ ሥርዓትን ለማዘመን በውጭ አማካሪዎች የታገዘ ጥናት እየተካሔደ ሲሆን ይህን

ለማስተካከል የማሸሻያ ትግበራ ለማድረግ በመሥራት ላይ እንደሆነ፤

የሚሉ መልሶች የተሰጡ ቢሆንም የቀረቡትን ሁሉንም ነጥቦች ኤጀንሲው እንደግባት ወስዶ ለማስተካከል

እደንደሚሰራ እና ይህ የተጀመረው የጋራ መድረክ በእየ ስድስት ወሩ የሚቀጥል እንደሆነ በመግለጽ የእለቱ

ውይይት ከቀኑ በ 6፡30 ላይ ተጠናቋል፡፡

You might also like