You are on page 1of 2

ሳልታመንህ ያሳለፍኩትን ዓመት፡

ሳስበው አላገኘሁም አይመጣልኝም ትዝብት፡፡

ፊትህን ፈልጌ ያለቀስኩት ቀናት ፡

የጠረንህ ናፈቆት ስያስሰለቸኝ ጥማት፡

ድረስልኝ እባክህ ፍጠንልኝ አባ፡

ደሪቃለሁ እኮ ያልኩት በእምባ፡

አልረሳቸውም እግሮችህን ይዤ፡

ካንተ በቀር ለላ አልፈልግም እኔ፡

ባርከን ባክህ ቀይረው ዘመነን፡

ብዬ ስጣራ በለቅሶ ድምፅ፡

የሚያውቀው ጠረንህ ስሞላ ልቤ ውስጥ፡

ሳላውቅ እደሰታለሁ በመገኘትህ ውስጥ፡

ያደረቅ ማንነት ስቀየር በደስታ፡

ልቤ ብቻ አይደለም ቆዳዬም ስለሰልስ፡

ምንም ሳልታጠብ ምንም ሳልቀባ፡

ሞገስህ ይታወቀኛል እንዳለ ከኔ ጋር፡

አየሩ ይስማማኛል ዉሃውም ይመቸኛል፡

የጎደለኝ ነገር መች ይታወሰኛል፡

ለሊቱን በደስታ ቀኑንም በደስታ፡

ባንተ ጠረን ልቤሙሉ ሆኜ ሺ ገዳይ፡

ጀግንነት ይሰማኛል ምንም ሁነታ ሳይ፤

ሁነታ ስያስፈራራኝ ሮጬ አንተ ጋ፡

እቅፍ ስታደርገኝ ስሰማኝ አብሮነትህ፡

የት አለ ሁነታ የት አለ ፍራቱ፤

ለካ ምንም የለም እንዲሁ ነው ስጋቱ፡

ውሸት ነው ሁነታው እንዲሁ ነው ፍራቱ፡


አንተን ያልታመንኩበት ቀን አላስታዉስም፡፡

በርግጥ ዕልፍ ግዜ ደክማለሁ ዕልፍ ግዜ ወድቃለሁ፡

ጠዋት ወድቄ ማታ ቆማለሁ፡

ማልነሳ መስሎኝ ጠዋት አልቅሼ ተስፋ ቀርጬ፡

ከሰዓት በሆኣላ ቆሜ ሳይ ባንተ እገረማለሁ፡

ባትኖርልኝ ኖሮ ምን እሆን ነበር፡፡

አንዳንዴ ለኔ እግዚኣብሔር አትመስልም፡

ሁለ የምትምረኝ ሁለ የምትመክረኝ፡

ከኔ እኔን ለመጠበቅ በጣም የምትጥርልኝ፡

አሳድገህ የኔን ወግ ማዕረግ አይተህ፡

ለመደሰት እንደቸኮለ አባት ነው የማይህ፡፡

ምንም ማለት አልችልም እወድሃለሁ በጣም እወድሃለሁ!

የትም ብትኖሩ ምንም ሁነታ ዉስጥ ብትሆኑ ኢየሱስ ይወዳችሆኣል፤ እርሱን እመኑ በርሱ ታመኑ ፡ መልካም እረኛ እርሱ
ብቻ ነው፡፡

You might also like