You are on page 1of 6

የ ”ዮጵ ታለንት የቴሌቭዥን ሾው” የመጨረሻ

ውድድር አሸናፊዎችን በሽልማት ስፖንሰር


ለማድረግ የተዘጋጀ እቅድ

_______________________

ሚያዚያ 2014
ቀን: 03/08/14 ዓ.ም
ቁጥር: ማሰፊፕ/ /14/2014

ለ____________________________

የስፖንስርሽፕ ድጋፍ ስለ መጠየቅ

”ዮጵ የትወና ታለንት ሾው“ የተሰኘው ይህ የቴሌቪዥን የትወና፣ የክህሎት ውድድር በ”ማኅሌት ሰለሞን
የፊልም ፕሮዳክሽን“ እና ”በ ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን’’ (ETV) የጋር ትብብር እየተዘጋጅ ዘወትር ቅዳሜ 11፡30
ላይ የ 60 ደቂቃ የስርጭት ቆይታን ተጠቅሞ የሚቀርብ አዝናኝና ቁም ነገር አዘል እና አስቂኝ እንዲሁም
ከፍተኛ የደረጃ ጥራቱን የጠበቀ እጂግ ተወዳጅ ሳምንታዊ የቴሌቪዥን ፕሮግራም ነው፡፡
ይህ ”ዮጵ የትወና ታለንት ሾው“ የተሰኘው የቴሌቪዥን የትወና፣ የክህሎት ውድድር የፕሮግራም ይዘት
ጥራቱንና እጂግ ተወዳጅነቱን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያጨመረ ስርጭቱን ለተመልካች ማድረስ ከጀመረ እነሆ
ከግማሽ አመት በላይ ያስቆጠርን ሲሆን የዝግጂታችን አንደኛ ምእራፍ (ሲዝን) አሸናፊዎችን አውዳድረን
በታላቅ ድምቀትና ክብር ለመሸለም ቅድመ ዝግጂታችንን አጠናቀን ከወዲሁ እንገኛለን፡፡
በመሆኑም ድርጅታችሁ ለዚሁ ለ”ዮጵ የትወና ታለንት ሾው“ የመጨረሻ ሶስት አሸናፊዎችን በመሸለም
ለፕሮግራሙ ድምቀት የበኩሎን አስተዋጽኦ እንዲያደረጉ፣ ስፖንሰር በማድረግ የድርጂታችን ተባባሪ በመሆን
አብረውን ቢሰሩ የድርጅታችሁን የዳበረ መልካም ስምና ዝናን ይበልጥ ያጎላዋል ብለን እናምናለን፡፡
በተጨማሪም የእናንተው ድርጅት ይህ ”ዮጵ የትወና ታለንት ሾው“ መዝጊያን የአንድ ሰአት የመዝናኛ
ዝግጂታችንን የስፖንስርሽፕ ድጋፍ በማድረግ በመላው አለም ለሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ምርትና
አገልግሎቶቻችሁን እንዲያስተዋውቁ በአክብሮት እየጠየቅን ስለ ፕሮግራሙ አጠቃላይ ይዘት እና
የስፖንሰርሽፕ ድጋፍ እንዲሁም ተያያዢ ጥቅማጥቅሞቹ ከዚህ ደብዳቤ ጋር ሰፋ ያለ ማብራሪያን አባሪ
በማድረግ በላክነው ፕሮፖዛል ውስጥ ማግኘት የሚችሉ መሆኑን እያሳወቅን ድርጅታችሁ ለሚያደርግልን
ድጋፍና አዎንታዊ ምላሽ በማህሌት ፊልም ፕሮዳክሽን፣ ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን (ETV) እና በሰፊው
የፕሮግራሙ ታዳሚዎች ስም አስቀድመን ከልብ የምናመሰግን መሆኑን በትህትና እንገልጻለን፡
ከሰላምታ ጋር

ማህሌት ሰለሞን
ዋና ስራ አስኪያጅ
ማህሌት ሰለሞን ፊልም ፕሮዳክሽን : +251 911 242 242 : mishuyid@gmail.com

”ዮጵ የትወና ታለንት ሾው


መግቢያ
ድርጅታችን ማህሌት ሰለሞን ፊልም ፕሮዳክሽን በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን (ETV)) ከሚተላለፉት የተለያዩ
ፕሮግራሞች መካከል በህዝብ ዘንድ እጅግ ተወዳጂነትን ያተረፈውና በተመልካች ብዛት ቀዳሚ ከሆኑት ፕሮግራሞች መካከል
አንዱ የሆነውን ” የዮጵ ታለንት ሾው “ን በማዘጋጅት ለመላው ኢትዮጵያውያን የመዝናኛ ስርጭት ዘወትር ቅዳሜ 11:30
የ 45 ደቂቃ የሽፋን ቆይታ በቴሌቭዢን መስኮት ወስዶ ውድድሩንና ሙያዊ እጋዛውን በማካሄድ የከረመ ሲሆን አሁን ደግሞ
እነሆ የዝግጅቱን የመጨረሻና የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድርን በታላቅ ድምቀት ለማቅረብ አስፈላጊ መሰናዶዎቹን ከወዲሁ
አጠናቆ ከታሪካዊው የምእራፍ ጫፍ ላይ ይገኛል።

የፕሮግራሙ ራዕይ
በጥበባዊ ክንዋኔ የሙያ ዘርፍ በጥራትም ሆነ በውበት ደረጃውን የጠበቀ የመዝናኛ ፕሮግራም በማቅረብ የሞያው ኮከብ
ባለሙያዎችን ማስተዋወቅና በኢንዱስትሪው ውስጥ የብቃት ደረጃን ሊያሳይ የሚችል ስራን በማቅረብ ለውጥ ማምጣት
የሚችል አወንታዊ ተፅዕኖ መፍጠር፤

የፕሮግራሙ ዓላማ
1. በሞያው የላቀ ክህሎት ያላቸውን ተወዳዳሪዎች አንጥሮ በማውጣት እና እነርሱን በመጠቀም ብቃትና ደረጃውን
የጠበቀ ስራ ለተመልካች ማቅረብ፤

2. በውበቱ የላቀ ብቃትና ደረጃውን የጠበቀ ፕሮግራም በማዘጋጀት ተመልካችን ማዝናናት እና ፕሮግራሙን ብሎም
የቴሌቪዥን ጣቢያውን ተወዳጅና ተናፋቂ ማድረግ፤

3. በሙያቸው የበቃ ክህሎት ኖሮአቸው ይህንን አቅማቸውን አሳይተው ኮከብ የሚሆኑበትን እድል ላጡ ባለሙያዎችን
አመቺ የሆነ መድረክ መፍጠር፤

4. ጥቂት ድጋፍ ቢያገኙ የሀገራቸው ኮከብ መሆን የሚችሉ ባለሙያዎችን የክህሎት ክፍተታቸውን በመሙላት ብቁ
ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ማስቻል፤

5. ለክዋኔ ጥበብ ኢንዱስትሪው ብቁ የሆኑ ባለሙያዎችን ፈትሾና አንጥሮ በማሳየት እና ብቃታቸውን እንዲያረጋግጡ
በማስቻል ተሳታፊ እንዲሆኑ ማበረታታት፤

የፕሮግራሙ ቅርጽ
በዚህ በአይነቱ ልዩ በሆነ ዮጵ ታለንት ሾው ሳምንታዊ ዝግጅቶች ላይ ለትወና ጥበብ ዘርፍ ዝንባሌውና ተሰጥኦው
ያላቸው ከመላው የሃገሪቷ ክልሎች የተወጣጡ ወጣቶችን በፍላጎት ላይ ብቻ በሚደረግ ምዝገባና የቅድመ ማጣሪያ
ምልመላ ችሎታቸውን የሚያሳዩበትንና ከማህበረሰቡ ጋር ሊተዋወቁ የሚችሉበትን መድረክ ላይ ቀርበው ስለ
ኢትዮጵያ ሀገራችን እና ስለ ኢትዮጵያውያን ባህል፣ ታሪክ፣ ስራ፣ ልማት፣ ማህበረሰባዊ ጥበባት ሃይማኖት፣ ፖለቲካና
የአኗኗር ዘይቤ፣ እሴት፣ ትውፊት፣ አፈታሪክ፣ ደካማና ጠንካራ ገጽታዎች፣ እና በመሳሰሉት ላይ ብቻ የሚያተኩሩ
መነባንቦችን በውድድሩ ዳኞች ፊት በመተወን የእርስ በርስ ውድድራቸውን ይጅምራሉ፡፡

በስራቸው ልቀት እና በዳኞች የመገምገሚያ መስፈርት መሰረት ከተወዳዳሪዎች መሀከል የተሻለ ብቃትን ያስመዘገቡት
ተወዳዳሪዎች ወደ ቀጣዩ የውድድር ዙር እንዲሸጋገሩ ይደረጋሉ። በዚህ በተጋጋለ መንፈስ ውድድሩ የሩብ ፍጻሜ
ዙርን እና የግማሽ ፍጻሜ ዙርን አካሂዶ በመቀጠል በመጨረሻው ዙር ላይ አሸናፊ የሚሆኑት ሶስት (3) ተወዳዳሪዎች
ተሸላሚ የሚያደርግ ይሆናል፡፡ ተወዳዳሪዎች በቀዳሚነት የሚያገኙት የገንዘብ አልያም ተመጣጣኝ የሆነ ቁሳዊ
ሽልማት ሲሆን በቀጣይም ለወደፊት በኢንዱስትሪው ውስጥ ታዋቂ ሆነው ሊቆዩ የሚያስችላቸው የስራ ሁኔታ
ይመቻችላቸዋል፡፡

የፕሮግራሙ ዳኞች
ከላይ ከጠቀስናቸው የትያትርና የፊልም ትወና ዘርፎች ጥበባትን በሚወክሉና በሙያዊ ተሰጥኦቸው እና ስኬታቸው
እጂግ ከተከበሩትና የዳኝነት ሚናቸውን በብቃት እየተወጡ ከሚገኙት ውስጥ

• የፊልም ባለሙያ፣ መምህርት፣ ደራሲ፣ ዳይሬክተር፣ ተዋናይት እናም የአይዶል ዳኛ ማህሌት ሰለሞን ፣

• ክቡር የፊልምና የትያትርና ባለሙያ፣ በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የትወና ትምህርት ሌክቸረር ፕሮፌሰር ሙልጌታ ጃዋሬ

• የፊልም ባለሙያ፣ ዳይሬክተር እና በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የትወና ትምህርት ሌክቸረርና እጩ ዶክተር አንተነህ
ሰይፉ፣

እና ሌሎችንም ጨምሮ በበሳልና ዝነኛ የመድረክ አስተዋዋቂዎች እየተመራ የተለያዩ አዝናኝ አስተማሪ ፕሮግራሞችን
በአገር ውስጥና በውጭ ሀገር ለሚኖሩ ኢትያዊያን ታዳሚዎች በ ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን (ETV) የሚቀርብ ነው፡፡

የፕሮግራሙ የስርጭት መርሃ ግብር


በበሳልና ዝነኛ የመድረክ አስተዋዋቂዎች እየተመራ የተለያዩ አዝናኝ አስተማሪ ፕሮግራሞችን በአገር ውስጥና በውጭ
ሀገር ለሚኖሩ ኢትያዊያን ታዳሚዎች በ ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን (ETV) መዝናኛ ቻናል ላይ የመላው አለም የሳተላይት
ስርጭት እሁድ የ 60 ደቂቃ የአየር ላይ የሽፋን ቆይታን ተላብሶ የሚቀርብ ነው፡፡

ከስፖንሰርሺፕ አድራጊው የምንጠይቀው የድጋፍ አይነቶች


የዮጵ ታለንት ሾውን አንደኛ ምእራፍ የመጨረሻ ሶስት አሸናፊዎችን በድርጅትዎ ስም ለመሸለም በገንዘብ
የስፖንሰርሽፕ ድጋፍ እንዲያደርጉልን የመዝናኛ ዝግጂታችንን በምርትና አገልግሎታችሁ ስም የክብር ስፖንሰር
በመሆን ከማህሌት ሰለሞን ፊልም ፕሮዳክሽን ፣ ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን (ETV) እንዲሁም ከሌሎች አጋር ድርጅቶች
ጋር በትብብር እንዲሰሩ የገበያ እድልን የሚፈጥር ነው።
የስፖንሰርሺፕ ድጋፍ አድራጊው ጥቅማ ጥቅሞች
ለዮጵ የቴሌቭዢን ታለንት ሾው ልዩ የመዝናኛ ፕሮግራም የመጨረሻ ዝግጅት የአሸናፊዎች አሸናፊ ሽልማትን
ስፖንሰርሺፕ ድጋፍ በማድረጉ ድርጂታችሁ ከፕሮግራሙ አዘጋጆች ከማህሌት ሰለሞን የፊልም ፕሮዳክሽን እና
ከ ETV የቴሌቭዢን ቻናል የሚከተሉትን የማስታወቂያ ጥቅማ ጥቅሞችን የሚያገኝ ይሆናል።
1. የፕላቲነም ደረጃ የክብር ስፖንሰር ካደረገ ብር 500,000.00
 የስፖንሰርሺፕ ድጋፍ አድራጊው ከፕሮግራሙ አዘጋጆች ጋር በድርድር የሚወሰን

2. የ 1 ኛ ደረጃ የክብር ስፖንሰር ካደረገ ብር 400,000.00


 ፕሮዳክሽኑ ያለቀለት የ 45 ሰከንዶች ማስታወቂያ በየጣልቃው አራት (4) ጊዜ ይተላለፋል፡
 የዝግጅቱ የ 1 ኛ ደረጃ የክብር ስፖንሰር መሆኑን አስመልክቶ በፕሮግራሙ የመድረክ መሪዎችና አስተዋዋቂዎች
ስድስት (6) ጊዜ በተደጋጋሚ ምስጋና ይቀርባል። ስለ ምርትና አገልግሎታችሁ ሰፊ ገለጻ ይቅርባል ።
 የቴሌቭዥን ስክሪን ላይ ሎጎ/ አርማ(Pop-up Logo) ይደረጋል።
 6 የግርጌ ተንቀሳቃሽ ጽሁፍ (Scroll Text) ማስታወቂያ ይሄዳል

3. የ 2 ኛ ደረጃ የክብር ስፖንሰር ካደረገ ብር 300,000.00


 ፕሮዳክሽኑ ያለቀለት የ 45 ሰከንዶች ማስታወቂያ በየጣልቃው ሶስት (3) ጊዜ ይተላለፋል፡
 የዝግጅቱ የ 2 ኛ ደረጃ የክብር ስፖንሰር ስፖንሰር መሆኑን አስመልክቶ በፕሮግራሙ የመድረክ መሪዎችና
አስተዋዋቂዎች አራት (4) ጊዜ በተደጋጋሚ ምስጋና ይቀርባል።
 4 የግርጌ ተንቀሳቃሽ ጽሁፍ (Scroll Text) ማስታወቂያ ይሄዳል

4. የ 3 ኛ ደረጃ የክብር ስፖንሰር ካደረገ ብር 200,000.00


 ፕሮዳክሽኑ ያለቀለት የ 30 ሰከንዶች ማስታወቂያ በየጣልቃው ሶስት (3) ጊዜ ይተላለፋል፡
 4 የግርጌ ተንቀሳቃሽ ጽሁፍ (Scroll Text) ማስታወቂያ ይሄዳል

5. የ 4 ኛ ደረጃ የክብር ስፖንሰር ካደረገ ብር 150,000.00


 ፕሮዳክሽኑ ያለቀለት የ 30 ሰከንዶች ማስታወቂያ በየጣልቃው ሁለት (2) ጊዜ ይተላለፋል፡
 4 የግርጌ ተንቀሳቃሽ ጽሁፍ (Scroll Text) ማስታወቂያ ይሄዳል
ቅድመ ምስጋና
ድርጅታችሁ ለዚህ ለዮጵ የቴሌቭዢን ታለንት ሾው የመጨረሻ ዝግጅት የአሸናፊዎች ሽልማትንና የአንድ ሰአት
የመዝናኛ ዝግጂትን የስፖንሰርሺፕ ድጋፍ እንደሚያደርግልን በመተማመን በፕሮግራሙ አዘጋጆች በማህሌት ሰለሞን
የፊልም ፕሮዳክሽን እና በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን (ETV) እንዲሁም በመላው የፕሮግራሙ ተወዳዳሪዎችና ተከታታዮች
ስም በቅድሚያ ምስጋናችንን ከልብ እናቀርባለን።
ማህሌት ሰለሞን የፊልም ፕሮዳክሽን
ሚያዚያ 2014

You might also like