You are on page 1of 7

በአብክመ ብልጥግና ፖርቲ አዘጋጅነት የምሁራን ሚና ለቅቡል ሀገረ መንግስት ግንባታ በሚል ርዕስ በመንግስት

እና በግል ኮሌጆችና በፖሊቴክኒክ ኮሌጆች ደረጃ የተካሄደ ውይይት ማጠቃለያ ሪፖርት፡፡

1.መግቢያ

የምሁራን ሚና ለቅቡል ሀገረ መንግስት ግንባታ መወያያ ሰነድ ላይ በብልጽግና ፓርቲ አስተባባሪነት በየደረጃው
ለሚመለከተው አካል በቂ ኦረንቴሽን በመስጠት በዞንና በወረዳ የፓርቲ ጽ/ቤቶች፤ በዞንና በወረዳ ስራና ስልጠና
መምሪያና ጽ/ቤቶች እንዲሁም በኮሌጅና ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ዲኖች በጋራ የተደራጀ መድረክ እንዲመቻች በማድረግ
ለውይይት በሚያመች መልክ የምሁራን መድረኩ በክልላችን በሁሉም ዞኖችና ወረዳዎች ውይይት ተደርጓል፡፡

ውይይቱም በዋናነት የምክክር መድረኩ ዋና አላማ ምሁራን በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ በቂ ግንዛቤ ኑሯቸው በሀገረ
መንግስት ግንባታ ሂደት የራሰቸውን አስተዋፆ ማበርከት እንዲችሉ ያለመ ሲሆን ሀገራችን በኢኮኖሚው፤ በዴሞክራሲ
ስርዓት ግንባታና በዲፕሎማሲ ደረጃ እንዲሁም የገጠማትን በርካታ የውስጥና የውጭ ጠላቶች በመቋቋም
እያስመዘገበችው ያለውን ድል በሌላ በኩል በርካታ ተግዳሮቶ ያሉባት መሆኑን የምክክር መድረኩ ማጠንጠኛ ሆኖ ።

ምሁራኑ በሀገር ግንባታ ያለውን የፖለቲካ ባህል በማሳደግ፣ቀጣይነት ያላቸው ጠንካራ ተቋማትን በመገንባት፣እየታዬ
ያለውን የፅንፈኝነትና አክራሪነት ሁኔታን በመታገል እንዲሁም ምቹ የሆነ ሰላም የተረጋገጠበት ሀገር ከመገንባት አንፃር
ምሁራኑ ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው ታሳቢ ተደርጎ የተፈጠረ መድረክ ነው።

2. ውይይት ርዕስ ፤የውይይቱ አካሄድ፤አመራር

2.1 .ምሁራን ሚና ለቅቡል ሀገረ መንግስት ግንባታ

2.2. በውይይቱ ተሳታፊ

 በክላላችን በሚገኙ የመንግስትና የግል ኮሌጆች መምህራንና ሰራተኞች መካከል የተደረገ ሲሆን የምክክር
መድረኩ ሁለት ቀናትን የሸፈነ ነበር

2.3 ውይይቱን የመሩት

 የኮሌጅ ዲኖች እያስተባበሩ በዞን፤በወረዳና በከተማ አስተዳደር ደረጃ የሚገኙ የመንግስትና የፓርቲ አመራሮች
መድረኩን መርተውታል

3.የዝግጅት ምዕራፍ
በዝግጅት ምእራፍ የተከናወኑ ተግባራት የሚከተሉት ናቸዉ

 የባነር ዝግጅትን በተመለከተ ያሉት ሁኔታ፡-

 የመድረኩን ዓላማ ሊያስተዋውቅ የሚችል ባነር በሁሉም ኮሌጆች ተዘጋጅል፡የአዳርሽ ዝግጅትን


በተመለከተ፡-
 ኮሌጆች ያላቸውን የተሰብሳቢ ቁጥር መሰረት በማድረግ ሳቢና ማራኪ በማድረግ ተዘጋጅቷል፡፡

 የሻይ ቡና ዝግጅት እና ሌሎች የተሰሩ ስራዎች፡-

 ወረዳዎች፤ የከተማ አስተዳደሮች፤ ዞን መምሪያዎች፤ ኮሌጆችና ፖሊቴክኒክ ኮሌጆች በመቀናጀት


የሻይ ቡና ፕሮግራሙን በጋራ በማዘጋጀት በቂ መስተንግዶ ተደርጓል

4.የተግባር መዕራፍ ፤-

4.1 የመድረክ ተሳታፊ መረጃ

በመድረኩ መሳተፍ የነበረባቸዉ የመንድስት፤የግል ኮሌጅች ፤የአስተዳደር ሰራተኞች በየዞኑ

ተ/ቁ ዞን/ከተማ አስተዳደር መገኘት ያለበት የተገኘ ተሳታፊ አፈጻጸም

በ%
ወንድ ሴት ድምር ወንድ ሴት ድምር

1 ደቡብ ጎንደር 849 342 1191 717 280 997 83.71

2 ማዕከላዊ ጎንደር 431 198 629 390 169 559 88.87

3 ጎንደር ከተማ 110 52 162 107 49 156 96.30

4 ሰሜን ጎንደር 217 74 291 87 36 123 42.27

5 ምዕራብ ጎንደር 50 26 76 47 22 69 90.79

6 ሰሜን ሸዋ 559 273 834 518 257 775 92.9

7 ምዕራብ ጎጃም
717 270 987 654 216 870 88.2
8 አዊ ብሄረሰብ ዞን 590 235 825 537 202 739 90

9 ባህርዳር
474 270 744 247 81 328 44
10 ምስራቅ ጎጃም
582 323 903 556 291 847 93.8
11 ሰሜን ወሎ 310 113 423 298 103 401 94.8

12 ዋግኸምራ 137 75 212 126 46 172 81.3

13 ደሴ ሪጂኦፖሊታንት 185 93 278 184 93 277 99.6

14 ደቡብ ወሎ 558 176 734 499 153 652 88.8

15 ኮምቦልቻሪጂኦፖሊታን 80.89
73 16 89 59 13 72

16 ኦሮሞ 59 23 82 54 20 74 91.35

17 ደ/ብርሃን ሪጂኦፖሊታን 161 86 247 143 80 223 90.28

18 ደ/ማርቆስ ሪጂኦፖሊታን 102 30 132 97 30 127 96.2

19 ደ/ታቦር ሪጂኦፖሊታን 131 52 183 114 43 157 85.8

ድምር 6295 2727 9022 5434 2184 7618 84.43

4.2 በመድረኩ አፈጻጸም ዙሪያ የታዩ ክፍተቶች

 ጽጽቃ ቴክ/ሙያ ኮሌጅ ሪፖርቱ እስከተጠናከረበት ጊዜ ውይይት አላካሄደም ከ 15/05/2015 እንደሚጀምር


ይጠበቃል

 የባህርዳር 44 ፐርሰንት የሰሜን ጎንደር 42.27 ፐርሰንት አፈጻጸም ዝቅተኛ መሆን

4.3 በስብሰባው የተነሡ ዋና ዋና ሀሳቦች

 በአዎንታ
 ዉይይቱ የተሻለ፣ወቅቱን የዋጀ እንዲሁም ምሁራኑን የሚያነቃቃ መሆኑ ማንሳት ችሏል
 ሁሉም ተሳታፊ ሰፊ ዉይይት ማድረግ ተችሏል
 የተመደቡ አመራሮች ትኩረት ሰጥተዉ ዉይይቱን ማሰኬድ መቻሉ
 የሰነድ ዝግጅቱ ከኋላ አመጣጣችንን ሰለሚያሳየን ጥሩ ነበር
 ምሁራንን ሃሳብ መቀበል እና ማዳመጥ መታሰቡም በራሱ ጥሩ ነው
 ውይይቱ የአለውን ነባራዊ ሁኔታ ተረድተን መንግስትን ለመደገፍ ጠቃሚ ነው
 ራሳችንን በማየት እንዳለብ እና የሚፈጠሩ ችግሮች በጋራ ታግለን ማስተካከል እንደሚገባን
 ሁላችንም የተሰጠንን ኃላፊነት በአግባቡ በመወጣት ለሀገር ግንባታ የበኩላችን መወጣት
አለብን
 አመራሩ በየጊዜው አዳዲስ ነገሮችን ለማህረሰቡ ማሳወቅ አለበት
 በአሉታ፤-
 መድረኩ የተዘጋጀው የዩንቨርስቲ መምህራን ጥያቄ ሲያነሱ ነወይ
 የአማራን ሞትና መፈናቀል ማቆም ሳይቻል መንግስት እኛን የሚያወያየን ምን እንድንፈጥር
ነው መጀመሪያ የሚጠበቅበትን ሰርቶ የኛን ድርሻ ቢያሳውቀን አይሻልም ወይ
 ሰነዱ የተዘጋጀው እንደ ሀገር ነው ወይስ ለአማራ ብቻ ነው
 ብልጽግና የኦሮሞን ተረኝነት እንዴት ያየዋል
 -የሚዲያ ነፃነት አለ የተባለው በፊትም ጋዜጠኞች እና የተፎካካሪ ፓርቲ አባላት ይታሰሩ ነበር
አሁንም በተለይም የአማራን ብሄር እየተመረጠ እየታሰረ ነው ምንድን ነው ልዩነቱ?
 -የሰላም ስምምነት ሰነዱ ግልፅ አይደለም ለምን ህዝብ አልተወያየበትም በስምምነቱስ
የወልቃይት እና የራያ ጉዳይ ምን መፍትሄ አገኘ?
 በአዲስ አበባ የሚፈጠሩ ችግሮችን ማስቆም አለመቻል
 ሰነዱ ስለ ሽብርተኛው ኦነግ አሁን ላይ እያደረሰው ስላለው የሰው ህይወት መቅጠፍ ያለው ነገር
የለም፡፡
 ወጣቱ ላይ ሰፊ ስራ እተሰራ ባለመሆኑ ስራ አጥነት ተበራክቷል፣
 የርቀት ት/ቤቶች መብዛትና አላግባብ የሆነ ሰርተፊኬት አሰጣጥ የመንግስት ኮሌጆችንና
ት/ቤቶችን ከተማሪ ውጭ እያደረጋቸው ነው፣
 የአመራሩን ፖለቲካል አቅም ከማሳደግ አንፃር ስራ እየተሳራ አይደለም፣ምደባውም በአቅም
አይደለም፣
 በሀገራችን ወቅታዊ ሁኔታ ጋር ተያይዞ አንዳንድ አካባቢዎች (በተለይ ወለጋ) ጦርነቱ ለምን
መቆም አልቻለም;
 ከአማራ ክልል ወደ አዲስ አበባ በሚወስደዉ መንገድ በአፋኞች ምክንያት በሰላም መጓዝና ደርሶ
መመለስ አስቸጋሪ ለምን ይሆናል; እንዲሁም ከቡሬ ወለጋ ያ፤ያለዉ መንገድ ለምን ክፍት
አይሆነም;
 1 መሬታችን ለሱዳ አስረክበን ሉዓላዊነታችን ተከብሮ ል ማለት ይቻላል ወይ ?
 ለኦሮሞ ተንበርካኪ አማራ አመራር ነው ያለው
 በጦርነቱ ወቅት ሰፈር ለሰፍር ውይይትና ሀብት ፍለጋ ነበር በእርቅ ጊዜ ግን በከተማ ደረጃም
ውይይት አልተደረገ ይህ የሚያሳየው አማራ ምንም አያመጣም በሚል ነው.
 የችግር ሁሉ መንስዔ ህገ መንግስቱ ስለሆነ ለምን አይሻሻልም?
 የሀገር ግንባታ ስራችን ተጠናቃል ማለት ይቻላል ወይ?ኦነግ ሸኔ ኢትዬጵያ አይደለሁም እያለ
ነው.
 የኑሮ ውድነቱ የስሚንቶ ውድነት ሰው መኖር የማይችልበት ደረጃ ደርሶል ምን የታሰብ ነገር አለ?
የሚሉ ዋና ዋና ጥያቄወች ተነስተዋል

4.4 በስብሰባው አከራካሪ የነበሩ ጉዳዮች

 በኦሮሞኛ የተፃፈው መደመር መጽሐፍ ላይ የጠላትን በሬውን እረድ፣ ሚስቱን


አግባበት፣ግደለው፣ቁረጥ የሚል ትርጓሜ ያለው ጽሁፍ አለ፡፡
 ከለውጡ በሓላ በኢኮኖሚው፤በፖለቲካውም እና በማህበራው ዘርፍ ለውጥ የለም
እንዲያውም አማራው እየታረደ፤ እየተፈናቀለ፤በርሀብ እየተሰቃየ ፤የኑሮ ውድነቱ እያሰቃየን
ስለሆነ ለውጥ የለም?
 የወልቃይት እና የራያ ጉዳይ መፍትሔ አላገኘም የሰላም ስምምነቱም ግልፅ አይደለም ለምን?
 የብልፅግና አመራር አብዛኛው ሌባ ነው ይህንን ይዞ ለውጥ አይመጣም የሚሉት ዋና ዋናዎች
ነበሩ?
 ለውጥ ሳይሆን በህዋህት የነበረውን ፖሊሲና መመሪያች ባልቀየርንበት ምኑን ነው የለወጥነው
 በእየመሰሪያ ቤቱ ያለው የመልካም አስተዳደር ችግር ባልተቀረፈበት ሌባ አመራር በበዛበት
እንዴት ሀገር መገንት ይቻላል
 ምሁራን ሲጠይቁ የሚታሰሩ ታርጋ የሚለጠፍባቸው ከሆነ እንዴት ሀሳብ ይሰጣሉ
 እውን የኢኮኖሚ ሪፎርም አለወይ;..ታላላቅ የፌደራል ምንገዶች ተዘግተው ምን ኢኮኖሚ
እድገት ይኖራል…ሰው በነጻነት ሰርቶ በማያተርፍበት ዘመን ለውጥን ማሰብ አያስቸግም ወይ
 የመከላከያ ሪፎርም የሚባለው የለም ከትግራውያን ወደ ኦሮሚያውያን ነው የተለወጠው
እንጅ
 የትም/ት ካሪኩለም በጭፍነየተቀዳ መሆኑ እየጎዳን ነው
 ብልጽግናና ምሁራን በጋራ ለመስራት የተሄደበት ርቀት ምን ያህል በቂ ነዉ
 በአገር ግንባታ ምሁራን አስተዋጽኦ እንዲኖራቸዉ ወደፊት ምን ያህል እድል ለመስጥ
ታስቧል ?
 የትምህርት ጥራት እንዲረጋገጥ የግብዓት አቅርቦት ችግር የመጸሀፍ አቅርቦት ቢታይ?
 የመሰረተ ልማት አቅርቦት ተመጣጣኝ እንዲሆን በብልጽግና ምን ያህል ትኩረት አገኜ ?
 በአዲስ አበባ በሰንደቃላማና በመዝሙር ጉዳይ ያለዉ ዉዝግብ እንዴት ሊፈታ ታስባል ?
 በጦርነት ወቅት ጉዳት የደረሰባቸዉና የተሰዉትን ካሳ ለመክፍል ምን ታስቧል
 ህገ መንግስትን ላለመንካት ፍራቻ የሚታይ በመሆኑ ተጎጂ ሁነናል እንዴት እንታገል ?
 ኪራይ ሰብሳቢነትና ብልሹ አሰራር በቸክሊስት የተሰጠ እንኪመስል ድረስ መቀጠሉ ለምን
 ዘርንና ሀይማኖትን ለማጋጨት አፍራሽ ፕሮፓጋንዳ የሚዘሩ በህግ እየተጠየቁ አይደለም
 በኢኮኖሚ ችግር ዉስጥ እያለን 6.1 ℅ እድገት የሚለዉ አሳማኝነቱ ምን ያህል ነዉ ?
 የፍትህና ህግ አስከባሪ አካላት በሪፎርሙ ምን ለዉጥ አመጡ ?
 ከፖለቲካ ጋር ግንኙነት የሌላቸዉ ዜጎች በየቀኑ እየተጠቁ ለምን ቁርጥ ያለ እርምጃ
አልተወሰደም ?
 ምሁራን በህገመንግስቱ ላይ የሚታየዉ ችግሮችን ቢያነሱም ሰሚ አላገኙም ?
 የወልቃይት ጉዳይ በህግ ይፈታል የሚለዉ እስከመቼ ?
 አማራዉ በሀሰተኛ ትርክት የባይተዋርነት ስሜት ለምን እንዲሰማዉ ይደረጋል ?
 መከላከያ ላይ አሁንም የብሄር ስብጥር ጉድለት ስለሚታይ ቢሰራ ?
 በጦርነቱ የተጎዱ የአማራና የአፋር አካባቢዎች መልሶ ግንባታ ፍጥነት ይጎለዋል
 ፍትሀዊ የሀብት ክፍፍል በዜጎች መካካል እንዲኖር ምን ታሰበ ?
 የዉጭ የፖለቲካ ጫናን ለመቀነስ ምሁራን ተግተዉ እንዲሰሩ እድል ቢመቻች ?
 የኮሌጆች በጀትና የትምህርት ጥራት መቀራረብ አልቻለም ?
 የሃገሪቱ መንግስት ህግን ከማስጠበቅ አኳያ ምን እየሠራ ነው፣ የህዝብ ተንቀሳቅሶ የመሥራት
መብት ፣ ሞት ፣መፈናቀል ፣የገበያ ህገወጥ ስርዓት፣
 መንግስት የምሁሩን ሚና እየተጠቀመበት አልነበረም፣ በተቃራኒው ተሻሉ ምሁራን ወደ
ፓለቲካው ሲጠጉ ይሳደዳሉ ይገደላሉ፣ይታሠራሉ፣አሁን ላይ ምሁሩ ለሃገር ሚና መታሰቡ
መልካም ነው ።ይህ ዓይነት መድረክ ይቀጥል።
 የተማረ ሃይል ቅድሚያ ተሠጦት የሥራ ዕድል እየተፈጠረለት ባለመሆኑ የትም /ት ሥርዓቱ
እና ፍላጎቱ በጣም ወርዷል ፣በቲቬትም እየገጠመ ያለው ይኸው ነው የሚሉና ሌሎች
ተነሥተዋል።
 ምሁራን ለአገር ግንባታ የሚያደርጉት አስተዋጽኦ በቂ ነዉ (አይደለም )
 በችግር ዉስጥም ሆነን የኢኮኖሚ እድገት ተመዘገበ / አልተመዘገበም /

 ብሄርን መሰረት ያደረገዉ ጥቃት በአማራ ላይ ነዉ ? በአማራ ላይ ብቻ ሳይሆን ራሳቸዉንም


ኦሮሞዎችንም ጭምር እየጎዳነዉ ወይስ አይደለም ?
 የደመወዝ ጭማሪ ለኑሮ ዉድነት መፍትሄ ነዉ ወይስ አይደለም ? መፍትሄ አይደለም የሚሉ
ስላሉ
 በብልጽግና ፖርቲ ዉስጥ የሀሳብ ትግል አለ፣ አይ የለም አሁንም ታዛዥነት አለ የሚሉና
በዉስን ደረጃም ቢሆን ትግል አለ

4.5 በስብሰባው የተደረሰበት ማደማደሚያ

 በየመድረኩ መሰል ጥያቄዎቸ ቀርበው በአወያዬቹ አማካኝነት በተጨባጭ መረጃ ጭምር


ማብራሪያ የተሰጠ መሆኑ
 ለውጥ እንዳለ ሁሉ በእርግጥም በተለያየ መልኩ የሚገለጽ ችግር ሀገራችን የገጠማት መሆኑን
ይህንን ደግሞ ከመንግስት ጋር በመቆም መታገል እንደሚገባ
 ሰላም ለሁሉም ስራዎቻችን ወሳኝ በመሆኑ በሰላሙ ስራ ላይ የየድርሻችንን መወጣት ያለብን
መሆኑን
 የተነሱት ችግሮች በውል የሚታወቁ በአጭርና በረጅም ጊዜ የሚፈቱ ግን ደግሞ የመፍተሄው
አካል መሆን እንደሚገባ
 ሁላችንም የየድርሻችንን ስንወጣ የምንፈልገው ሰላም የሚረጋገጥ፤መልካም አስተዳደርን
የማስፈን የዴሞክራሲ ባህላ ግንባታ መሰረት የሚጣልበት በተለይም ደግሞ አገራችን ወደ
ብልጽግና ለምታደርገዉ ጉዞ አንዲረዳ ህዝቡን በማንቃት በጥናትና ምርም ያገባኛል በማለት
ሙህራን የበኩላችሁን ሚና መወጣት አለባችሁ
 ዘላቂ አወንታዊ ሰላም ለማምጣት በምታሰተምሩት የትምህርት ላይ በማስተማር ህዝቡን
በማንቃት መሳተፍ አለባችሁ
 በሌሎች ጥያቄዎች ላይ በቂ ማብራሪያ በመሰጠቱ በአግባቡ መግባት የተደረሰ መሆኑን፣

You might also like