Professional Documents
Culture Documents
History
The Ethiopian scholar and righteous Abba Giorgis is an Ethiopian scholar who occupies a
prominent position next to Saint Yared. Giorgis was born in the region of Wello, Borena
province from his father Hizbe Sion and his mother Emne Sion [1357 E.C]. Abba Giorgis
learned his first church teaching from his father Hizbe Sion. Later his father send him for more
education to Lake Stephen Monastery (ሀይቅ እስጢፋኖስ ገዳም) where Abba Samuel of Garma
taught him the hymns of Yared. He was also serving the fathers in the Lake Stephen Monastery
by grinding grain. The stone Abba Giorgis used to grind grain is still exist in the monastery.
Abba Giorgis start to compose hymns and write books at early age. Hereafter at the time of
Emperor Dawit Abba Giorgis start to engage in teaching of the children of the royal family, and
continued to write different books. He also played a leading role in defending the teaching of the
Church from external and internal enemies suppressing different heresies which arose at that
time.
It was at that time that King Yeshaq intended to inaugurate a church in the region of Shewa and
Giorgis was invited to be present on this occasion. His poor health did not really allow him to go.
But the king insisted, and Giorgis was obliged to attend. During his return he died in the middle
of the journey. His students according to his wish took him to Gasitcha and buried him.
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጭ
Add languages
መጣጥፍ
ውይይት
ለማንበብ
አርም
ማዘጋጀት
ታሪኩን አሳይ
ጠቃሚ መሣሪያዎች
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጭ
በደብራቸው
ኢትዮጵያዊው ሊቅና ጻድቅ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጭ የተወለዱት በ፲፫፻፶፯ ዓ.ም. በወሎ ክፍለ ሀገር በቦረና
ወረዳ ሸግላ/ሰግላ በተሰኘች ቦታ ነው ። አባታቸው ሕዝበ ጽዮን ከተከበሩ መምህራን ወገን የሆኑ የቤተ
መንግሥት ባለሟል ፤ መጽሐፍትን የሚያውቁ ጥበብ የተሞሉ ሲሆን የሰግላ አገረ ገዢም ነበሩ ። እናታቸው
እምነጽዮንም ከወለቃ ሹማምንት ወገን የሆኑ ደግ ሰው ነበሩ ።
አተዋጽዎቻቸው[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
በዚህም በቀሰሙት ዕውቀታቸው በዜማ በኩል ከቅዱስ ያሬድ ቀጥለው የሚጠሩ አባ ጊዮርጊስ ናቸው ።
በቤተመቅደስም ዘማሪ ማኅሌታይ ተብለው ይጠራሉ ። በዚያም ዘመን ለነገሥት ፣ ለካህናት ፣ ለመኳንንት ፣
ለንቡራነእድ ፣ ለመሳፍንት ፣ ለሁሉም የቤተመንግሥት ሠራተኞች አስተማሪ ሆኑ ። በአንድ ወቅት ግብፃዊው
ጳጳስ አቡነ በርተሎሜዎስ “ሥላሴን አንድ ገጽ” ብለው ያምናሉ ተብለው በተከሰሱ ጊዜነገሩን እንዲያጣሩ
ከተመረጡት ከቄስ ሐፄ ተከሥተ ብርሃንና ከሐይቁ መምህር ከዐቃቤ ሰዓት ዮሴፍ ጋር አብሮ ተልኮ ነበር፡፡
እነዚህ ሦስት አበውጳጳሱን ካነጋገሩ በኋላ ክሱ ውሸት መሆኑን በማረጋገጥ ስለ ምሥጢረ ሥላሴ
የሚገልጠውን የጳጳሱን እምነት በጽሑፍ ይዘው መጡ፡፡ ሊቅነታቸውን የተረዱት ዓፄ ዳዊት አባ ጊዮርጊስን
ወደ ቤተመንግሥታቸው በማስገባት የስምንቱም ልጆቻቸው መምህር አድርገዋቸው ነበር ። ከእነርሱም
ውስጥ ቅዱስ የተባለው ንጉሥ ቴዎድሮስ እንዲሁም በተለያዩ ጊዜ የነገሡት ንጉሥ እንድርያስ ፣ ዓፄ
ይስሐቅ ፣ ንግሥት እሌኒ እና ዓፄ ዘርአ ያዕቆብ ይገኙበታል።
ዐፄ ዳዊት በጋብቻ እንዲዛመዱዋቸው ጥረው ነበር ነገር ግን አባ ጊዮርጊስ ራሳቸውን የመንግሥተ ሰማያት
ጃንደረባ ማድረግን ስለመረጡ በማስተማሩና በብሕትናው ጸንተው የአመክሮ ጊዜያቸውን ሲጨርሱ አቡነ
በጸሎተ ሚካኤል ገዳም ገብተው መንኩሰዋል ።
ተጋድሎዋቸው[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
በዘመኑ ለተነሱ ለሁሉም የሃይማኖት ችግሮች አጥጋቢ መልስ በመስጠት የተዋህዶ ጠበቃ ፣ አይሁድን እና
ሌሎች መናፍቃንን በጉባዔ ያሳፈሩት ሊቅ ክፉዎችና ምቀኞች በየጊዜው እየተነሱ መከራን ያደርሱባቸውና
ይከሱዋቸው ነበር ።
በአንድ ወቅት በሸዋ ይፋት ራሳቸውን ቤተ እስራኤል እያሉ የሚጠሩ አይሁድ ነበሩ ፡፡ ከአቡነ ዜና ማርቆስ
ጀምሮ ብዙ መምህራን ወደነዚህ ሕዝቦች እየተሠማሩ ወንጌልን አስተምረዋል ፡፡ አቡነ ዜና ማርቆስ ወደ
ክርስትና ለተመለሱት ቤተ እስራኤላውያን በእመቤታችን ፣ በቅዱስ ሚካኤል ፣ በአባኖብና በሰማዕቱ በጊጋር
ስም አራት አብያተ ክርስቲያናትን አሠርተው ነበር ፡፡ ሁለቱ የመጀመሪያዎቹ አሁንም አሉ ፡፡ ይህ ሁሉ
ቢሆንም ቤተ እስራኤላውያኑ ሙሉ በሙሉ ወደ ክርስትና አልተመለሱም ነበር ፡፡ ከእነዚህ አይሁድ መካከል
አንዱ ከክርስቲያኖች ጋር በነገረ ሃይማኖት ለመከራከር ጥሪ አቀረበ ፡፡ “ክርስቲያኖች ከረቱኝ ወደነርሱ
ሃይማኖት እገባለሁእኔ ከረታኋቸውም ወደኔ ሃይማኖት ይገባሉ” ሲል ነገሩን ጥብቅ አደረገው ፡፡ ዐፄ
ዳዊት ይህን ጉዳይ ሲሰማ በጣም ስለ ተናደደ ሊቃነ ካህናቱን ፣ ንቡራነእዱንና የመጻሕፍት ዐዋቂዎችን ሁሉ
ከየሀገሩ እንዲሰባሰቡ አዘዘ፡፡አይሁዳዊው በአንድ ወገን መምህራኑ በአንድ ወገን ሆነው ክርክሩን ጀመሩ፡፡
የመጀመርያው እድል የተሰጠው ለአይሁዳዊው በመሆኑ ቀጥሎ ያለውንጥያቄ አቀረበ ፡ “እናንተ
የእግዚአብሔር ልጅ ነው የምትሉት ይሄ ክርስቶስ እውነት የእግዚአብሔር ልጅ ከሆነ፣ ወደ ቢታንያ በመጣ ጊዜ
አልዓዛር የተቀበረበትን ቦታ ሳያውቅ ቀርቶ "አልዓዛርን የት ቀበራችሁት?" ብሎ እንደጠየቀ በወንጌላችሁ
ተጽፏል፡፡ ለዚህ መልስ ስጡኝ፣እኔንም ከመጽሐፈ ኦሪቴ ጠቅሳችሁ ጠይቁኝ?” ሲል የመከራከርያ ነጥቡን
አቀረበ፡፡ በዚህ ጊዜ አባ ጊዮርጊስ ታሞ አልጋ ላይ ነበር ፡፡ ሊቃውንቱም “እንዲህያለው ነገር ያለ እርሱ
አይሆንምና አባ ጊዮርጊስ ይምጣ” ሲሉ ለዐፄ ዳዊት ጥያቄ አቀረቡ ፡፡ አባ ጊዮርጊስም በአልጋ ላይ እያለ
እንዲመጣ ተደረገ፡፡በአልጋ ላይ ሆኖም በጉባኤው ላይ ተገኘ፡፡ ጉባኤተኞቹ የቀረበውን ጥያቄ ነገሩት ፡፡ አባ
ጊዮርጊስ የሰጠውን መልስ ገድሉ በሚከተለው መንገድ ይገልጥልናል “እኔ ግን በወንጌል ሳይሆን በኦሪት
እከራከርሃለሁ፡፡ የምኩራብ መጻሕፍት ሁሉ ለቤተ ክርስቲያን የታወቁ ናቸውና ፡፡ ምኩራብ ዘራች
ቤተክርስቲያንም አጨደችው፤ ምኩራብ ፈተለችው ቤተ ክርስቲያን ለበሰችው ፤ አዳምን በገነት
ሳለ አዳም ሆይ ወዴት ነህ? ብሎ የጠየቀው ማነው? አብርሃምንስ ሚስትህ ሣራ ወዴት ናት? ብሎ የጠየቀው
ማነው? እስቲ መልስልኝ? ሰይጣንንስ ከወዴት መጣህ? ብሎ የጠየቀው ማነው? እግዚአብሔር አብ
አይደለምን?” በዚህ ጊዜ አይሁዳዊው መልስ አጥቶ ዝምአለ ፡፡ ንጉሡ ፣ ሊቃውንቱና መኳንንቱም እጅግ
ተደሰቱ፡፡
ቅዱስ አባ ጊዮርጊስ እንደ ሰማዕት ግርፋትንና እሥራትን የተቀበሉ ፣ እንደ ሊቃውንት የመናፍቃንና
የከሀድያንን ክርክር የረቱ ፣ እንደ መሐንዲስ ሐናጺ ፣ የሕግና የሥርዐት የሚስጥራትና የትርጉዋሜያት
መምህር ፣ የጸሎትና የትምህርት መጻሐፍት ደራሲ ፣ የሥርዓተ ገዳምና ማኅበረ መነኰሳት አባት እንዲሁም
ቢያንስ የአንድ ትምህርት መሥራች ሲሆኑ በግዞት በሄዱባቸውና በታሰሩባቸው ቦታዎችም ሆነ
በተሾሙባቸው እንደ ደብረዳሞ ገዳም በመሰሉ ቦታዎች ሁሉ ሲያስተምሩና ሲገስጹ ኖረዋል ። በድርሰቱም
እስካሁን በሃገራችን ተወዳዳሪ የላቸውም ። እጃቸው ከብዕር ተጨማሪ ከጠንካራ ሥራ ሳይቦዝኑ ዋሻ
ሲፈለፍሉ የውሃ ጉድጉዋድ ሲቆፍሩ ድልድይ ሲሠሩ ኖረዋል ። አንደበታቸውና ሕሊናቸው ከምስጋና
ሳያቁዋርጡ ለቤተክርስቲያን ጸሎትና ምስጋና ሥርዓት ሲተጉ ኖረው በፅድቅና በቅድስና ሕይወት እንዳጌጡ
ለተዋህዶ ኮከብ ሆነው በተወለዱ በ፷ ዓመታቸው በ፲፬፻፲፯ ዓ.ም. ሐምሌ ፯ ቀን አርፈዋል ።
ተማሪዎቻቸውም በመረረ ሐዘን ሆነው አፅማቸውን በጋስጫ ራሳቸው ፈልፍለው በእመቤታችን ቅድስት
ድንግል ማርያም ስም በሠሩት ገዳም ውስጥ አስቀምጠውታል ። በትምህርታቸው የተመሰጡት ምዕመናን
እና የቤተክርስቲያን ሊቃውንት በኛ ዘመን የተነሱት አዲሱ ዮሐንስ አፈወርቅ ሲሏቸው ዓፄ ይስሐቅ ደግሞ
መናፍቃንን ሁሉ በማሳፈራቸውና በረቂቅ ድርሰቶቻቸው የኢትዮጵያ ቄርሎስ ብለዋቸዋል ።