You are on page 1of 9

ርዕስ.

አውቶማቲክ የሻይ ማፊያ ማሽን

የፈጠራ ባለቤት ስም…….


1. አጭር መግለጫ (A bstract)

ይህ ፈጠራ አውቶማቲክ የሻይ ማፊያ ማሽን ሆኖ መያ ዣ ቋሚ መሳይ /2/ የቀዝቃዛ ውሃ መያዣ /3/ ሻይ ማፊያ ክፍል /4/ ሻይ
ማሞቂያ /5/ ክፍሎች የውሃ መቀበያ ቱቦ /6/ የኤሌክትሪክ መቆጣጠሪያ /7/ ፓነልን የያዘ ሆኖ በተደጋጋሚ ሻይን በአጭር ጊዜ ውስጥ
የሚፈለገውን የሻይ ዓይነት ና መጠን ላዩ ላይ በተገጠመ ሜሞሪ አማካኝነት በማስታወስ ማፍላት የሚችል ማሽን ነው፡፡

1
2
ሥዕል 2

ሥዕል 3

3
ሥዕል 4

4
ሥዕል 5

5
አውቶማቲክ ሻይ ማፊያ ማሽን

3.መግለጫ (Background of the Invention)

የፈጠረው ዘርፍ( field of invention)

ይህ የአሁኑ ፈጠራ አውቶማቲክ በኤሌክትሪክ ኃይል የሚሰራ የሻይ ማፊያ ማሽን ሲሆን እንደመያዣ የሚያገለግል ቋሚ
፣የቀዘቃዛ ውሃ መያዣ እና የሻይ ማፊያ ክፍሎችን የያዘ ነው፡፡

ቀደምት ጥበብ (Prior Art)

ከዚህ ቀደም የተሰሩ /የተፈጠሩ/ የሻይ ማፈያ ማሽኖች ሻይን ለማፍላት ሲፈለግ መጀመሪያ የሻይ ውሃን በማሞቅ ውሃውን
እንዲተን፣የተነነውን ተመልሶ እንዲረጋ /እንዲጤዝ/ እና የረጋው ውሃ በማጣሪያ /ፊለተር/ ከላይ ውደታች እንዲጣራ የሚያደርጉ ሲሆን
የተነነውን ውሃ እንዲረጋ ለማድረግ ረጅም ጊዜ የሚውስድበት በመሆኑ ታፈላጊነቱ ይህን ያህል ነው፡፡

በተጨማሪም ከዚህ ቀደም ያሉት ማሽኖች የሙቀት መቆጣጠሪያና መለኪያ የሌላቸው በመሆኑ የሚፈላ ሻይ ላልተፈለገ ሙቀት መጠን
ይጋለጥና በውስጡ የያዛቸው ነጥሬ-ነገሮች በእሳት ይጎዱና ያልተፈለገ መዓዛ እንዲኖራቸው የሚያደርጉ ናቸው፡፡

የፈጠራው ዓላማ (Objective of the Invention)

የዚህ ፈጠራ ዋና ዓላማ በአጭር ጊዜ ውስጥ ተደጋጋሚና በሚፈለገው የሙቀት መጠን፣ የሻይ መጠንና ዓይነት ሻይን የሚያፈላ
በኤሌክትሪክ የሚሰራ አውቶማቲክ የሻይ ማሽንን መፍጠር ነው፡፡ ይህንኑም ዓላማ ለማሳካት ማሽኑ የተለያዩ አካላቶችን የሚጠቀም
ሲሆን በዋናነት

 እንዲመያዣ የሚያገለግል ጐንና ጐን ላይ ቋሚ መሳይ ነገር እና የቀዝቃዛ ውሃ መያዣ ቻምበር /የሻይ መስሪያ ክፍል/
 ውሃ መምጠጫ ቱባ ከቀዝቃዛ ውሃ መያዣ ክፍል ጋር የተገናኘና ፓሞፕ፣
 ማሞቂያ ቻመበር ና በቀጥታ ከማሞቂያ ቻምበር ጋር የተያያዘ የውሃና የሌሎች ነገሮች ማስወገጃ ቱቦ፣ ከሻይ ማፈያ/
ማዘጋጃ ክፍል/ በላይ በኩል በክብ ቅርፅ የተከፋፈለ የሻይ ማደቀቂያ /strainer/ ማላወሻ /agitator/ ሁለቱም እንደ አስፈላጊነቱ
የሚፈቱና ተመልሰው የሚገጠሙ፣እና ማንኛውንም የሻይ ማፍላት ሂደት የሚቆጣጠር፣የኤሌክትሪክ መቆጣጠሪያ ዩኒት የያዘ
ነው፡፡

አጭር ስዕላዊ መግለጫ / short Brief Description of the drawings/

ፈጠራውን ለመረዳት የሚከተሉትን አጭር ስዕላዊ መግለጫ ይመልከቱ

6
ስዕል 1፡- የሻይ ማፊያው ማሽን ፐርስኘክትቭ ቪው የሚያሳይ፣

ስዕል 2፡- በጣም ጉልቶ የሚታይ /በደንብ ገላጭ/ የሻይ ማሽን ፐርስፐክትቭ ቪው፣

ስዕል 3፡- ስኬማቲክ ቪው የሚያሳይ፣

ስዕል 4፡- በጣም ገላጭ የሆነ ስኬማቲክ ቪው የሚያሳይ፣

ስዕል 5፡- ውሃ ሲሞቅ፣ በማሞቂያና ሻይ መስሪያ ቻምበር ውስጥ ያለውን ህደት ስከማቲክ ቪውን የሚያሳይ ነው፡፡

የተበራራ ፈጠራ መግለጫ /Brief Description of the drawings/

በስዕል /2/ የሚያሳየው የሻይ ማፊያ ማሽን ውጫዊ ክፍል ማለትም የታችኛው ክፍል/1/ እና ቋሚ/2/ ፣ቀዝቃዛ ውሃ መያዣ
ክፍል/3/ ሻይ ማዘጋጃ ክፍል /4/፣ ማሞቂያ ቻምበር/5/፣ ውሃ መምጣጫ ቱቦ/6/፣ ከጀርባው የኤሌክትሪክ መቆጣጠሪያ
ዩኒት ያለው መቆጣጠሪያ ፓነል /7/ በአንድ ጊዜ በሁለት ሲኒ ላይ ለመቅዳት የሚያገለግል የፈላ ሻይ ማስወጫ
ቧንባ/8/፣ክዳን/9/ እና የክዳን መያዣ ቀለበት/10/ የሻይ ማሰብሰቢያ /11/ ከነክዳኑ /12/ የያዘ ነው፡፡

በስዕል /3/ ላይ እንደተገለፀው ውሃ ከቀዘቃዛ ውሃ መያዣ ቻምበር/3/ ሻይ በሚፈላበት ጊዜ በውሃ በምጠጫ ቱቦ/6/ በኩል
በሞተር በሚሰራ ፓሞፕ/13/ አማካኝነት ይመጣና በኤሌክትሪክ ኃይል በምሞቀው የማሞቂያ ቻምበር/5/ ይሳብና
በውሃ ማፍሰሻ ቱባ /14/ በኩል ወደ ሻይ ማፈያ ቻምበር/4/ ውስጥ ከላይ በኩል ይገባና ውሃው በሚፈለገው የሙቀት
መጠን በማሞቂያ ቻምበር ውስጥ እንዲሞቅ ይደረጋል፡፡ እንዲፈላ የተፈለገው የሻይ ቅጠል ፣ዱቄት፣ ስር ወይም ሌላ
ዓይነት በሙቅ የሻይ ውሃ/17/ ይሸፈንና፣ በሻይ ማዲቀቂያ/15/ አካላት ማለትም ክብ ቅርፅ ያለውና በስዕል /4/ ላይ
የተገለፀው ሲፈለግ በሻይ ማዘጋጃ ቻምበር ላይ የሚታሰርና ለማፅዳት ሲፈለግ የሚፈታ አካላት ያለው ነው፡፡
በውጫዊ የሻይ ማደቀቂያ በኩል /15/ እንደ ማላወሻ /18/ የሚያገልግል ውሃን /17/ ወደ ከፍተኛ መገለባበጥ
እንቅስቃሴ በሻይ ቅጠል፣ ዱቄት ወይም ስር /16/ ላይ በተደጋጋሚ እንዲፈስ የሚያደርግና ሻይን በአጭር ጊዜ ውስጥ
እንዲፈላ የሚያደርግ ነው፡፡ ማላወሻው /18/ ከኘላስቲክ የተሰራ በአክስል /19/ ላይ የታሰረ ኘሮፐለር /20/ ያለው
ሲሆን ኘሮፐለሩ ለማፅዳት ስፈለግ የሚፈታና ከትንንሽ ማግኔት /21/ ጋር የሚያያዝና በተቃራኒው በኩል በሌላ
ማግኔት /23/ ለዚሁ ተብሎ ከታች በኩል ከሻይ ማፊያ ቻምበር ስር በተገጠመ ሞተር /22/ አማካኝነት የሚሽከርከር
ነው፡፡ ሻይ በዚህ ዘዴ በሚዘጋጅበት ወቅት የሻይ ውሃ /17/ በሚፈለገው የሙቀት መጠን እንዲቆይ ከሻይ ማዘጋጃ
ቻምበር ስር የተዘጋጅው የማሞቂያ ቻምበር/5/ በማሞቅ ነው፡፡ ሻይን የማፊያ ሰዓት ከተሰተካከለና እንደሚፈለገው
ሰዓት ከተሞላ በኃላ የማስወጫ ኮንዲዩት /25/ ውስጥ ያለውን ቫልቭ /24/ በመክፈት የተዘጋጀውን ሻይ በሻይ ማቅጃ
ፓይኘ /8/ አማካኝነት ሲኒ ላይ እንዲቀዳ ማድረግ ነው፡፡

በዚህ መሰረት ሙሉ በሙሉ የሻይ ማፍላት ሂደቱን በአውቶማቲክ መቆጣጠሪያ ዩኒት /በስዕሉ ላይ አልተገለፀም ነገር ግን
ከኮንትሮል ፓኔል /7/ ጀርባ ያለ አካል ነው/ አማካኝነት መቆጣጠሪያ ያለውና የሻይን ጠቅላል የአዘገጃጄት ሂደት ማለትም መጠን ፣
ሙቀትንና ዓይነትን የሚፈላበትን ሰዓት እንደ አስፈላጊነቱ መቀያየር የሚያስችል መሣሪያ ነው፡፡ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ በላይ ላይ ባለው
መግለጫ ወይም ዲስኘለይ /27/ አማካኝነት ቀደም ተብሎ የተፈላ ወይም የተዘጋጀ ሻይ በሜሞሪ አማካኝነት እንዲመዘግብ ተደርጐ
ሲፈለግ ያንኑ የሻይ ስም እንደገና /key -diplay/በመንካት እንዲያፈላ ማድረግ የሚችል ማሽን ነው፡፡

7
በተጨማሪም ይህ የሻይ ማሽን የተለያዩ የሻይ ዓይነትን ለመለያት ከሻይ ማዘጋጃ ቻምበር በላይ ባለው ቀለበት መሳይ ነገር
አማካኝነት ዝርዝራቸው ወደታች አንድ በአንድ ወደ ሻይ ቅጠል ማደቀቂያ እንደወርድ እንደ አስፈላጊነቱ ወደ ላይ እንደመለስ ለዚሁ
ተብሎ እላዩ ላይ በተገጠመ የሜሞር አካል እያታጋዘ የሚሰራ ነው፡፡

4.የመብት ወሰን (claims)

1. ፈጠራው በኤሌክትሪክ ኃይል የሚሰራ አውቶማቲክ የሻይ ማፈያ ማሽን ሆኖ በዋናነት


የቀዝቃዛ ውሃ ማያዣና የሻይ ማዘጋጃ ቻምበር፣
ከቀዝቃዛ ውሃ ማያዣ ቻምበር ጋር የተያያዘ የመምጠጫ ቱቦ፣ፓምፕ እና ማሞቂያ ቻምበር፣
የፈሳሽ ማስወገጃ ቱቦ፣ የተባለውም የፈሳሽ ማስወገጃ ቱቦ በቀጥታ ከማሞቂያ ቻምበር ጋር
የተገናኘና ከሻይ ማዘጋጃ ቻምበር በላይ የተገጠመ፣ የሻይ ማዘጋጃ ቻምበር የተባለው በክብ ቅርፅ
በክፍልፋይ የተከፋፈለና እንደ አስፈላጊነት የሚፈታና የሚታሰር የሻይ ቅጠል ማደቀቂያ፣ ማለወሻና
ፕሮፐለርን፣
የሻይ አፈላልን ሂደት የሚቆጣጠር፣ ከመቆጣጠሪያው ፓኔል በኋላ በኩል የተገጠመ የኤሌክትሪክ
መቆጣጠሪያ ዩኒት የያዘ ነው፡፡
2. በመብት ወሰን 1 ላይ የተጠቀሰው የሻይ ማሽን፣ የሻይ ማላወሻ የተባለው በሞተር ኃይል የሚንቀሳቀስ ማግኔት
ያለውና እንዲሁም ሌላ ከፕሮፐለር ጋር የሚያያዝው ተጨማሪ ማግኔት የያዘ መሆኑ፣
3. በመብት ወሰን 1 ላይ የተጠቀሰው የሻይ ማሽን፣ የማሞቂያ ቻምበር የተባለው በቀለበት መሳይ ቅርፅ የተዘጋጀና
ከሻይ ማዘጋጃ ቻምበር በታችኛው ክፍል በኩል የተገጠመ ሲሆን ውሃን የማሞቅ ሂደት እስከተፈለገ የሙቀት
መጠን የሻይ ማፈያ ቻምበር ውስጥ እንደ አስፈላጊነት ለመመጠን እንዲያገለግል ተደርጐ የተሰራ መሆኑ፣

8
4. በመብት ወሰን 1 ላይ የተጠቀሰው የሻይ ማሽን ፣ እላዩ ላይ በተገጠመ የሚሞሪ ማዕከልና የኤሌክትሪክ ዩኒት
አማካኝነት የተፈለገውን የሻይ ዓይነት ፣ መጠን፣ በምን ያህል ደቂቃ ሻይ መፍላት እንደተፈለገ መጀመሪያ
ዝርዝራቸው በማሽኑ ላይ የተመዘገበውን የሻይ ዓይነት ማፍላት ሲፈለግ /key-display/ን በመጫን ብቻ
የተፈለገውን ዓይነት መርጦ መፍላት የሚችል መሆኑ፣
5. በመብት ወሰን 1 ላይ የተጠቀሰው የሻይ ማሽን ፣ተንቀሳቃሽ ቀለበት የተባለው የተለያዩ የሻይ ዓይነት ዝርዝርን
የያዘ ሲሆን ከሻይ ማዘጋጃ ቻምበር በላይኛው በኩል የተገመጠ መሆኑ ነው፡፡

You might also like