You are on page 1of 2

1.

መግቢያ
ኢትዮጵያ በታሪኳ በርካታ መንግስታትና መሪዎችን ያስተናገደቸ እድሜ ጠገብ አገር ብትሆንም

የእድሜዋንና በዘመናዊ የመንግስት ምስረታ ውስጥ ያላትን ታሪክ ያህል በዲሞክራሲና በሰብዓዊ አያያዝ

የተሻለ ተራምዳለች ለማለት አያስደፍርም፡፡ ከዛ ይልቅ በየዘመናቱ የመጡ መንግስታት ከዲሞክራሲያዊ

የመንግስት መዋቅር ምስረታ ይልቅ የተቆናጠጡትን ስልጣን በጉልበት ለማስጠበቅ በወሰዷቸው የሃይል

እርምጃዎች ምክንያት ለብዙ ሰብዓዊ ቀውስ ምክንያት የሆኑበትን ታሪክ ገዝፎ እናገኘዋለን፡፡

በዘመናዊው የአገረ መንግስት ምስረታም የአገራችን ታሪክ በግጭቶችና በእርስ በእርስ ጦርነቶች

የሚታውቅ ሲሆን በተለይም የ1966ዓ/ም የኢትዮጵያን አብዮት ተከትሎ የስልጣነ ወንበሩን

የተቆናጠጡት የወቅቱ ኮሎኔል በኋላም የአገሪቱ ፕሬዝዳን የሆኑት ፕሬዝዳንት መንግስቱ ኃ/ማርያም

አገርን ባስተዳደሩበት 17 ዓመታት ያጋጠማቸው ከዚህ የተለየ አልነበረም፡፡ ፕሬዝዳንቱ የስልጣን

ወንበሩን የተቆናጠጡበት ወቅት በአገሪቱ ታሪክ የፖለቲካ ትኩሳትና ተሳትፎው እጅግ ከፍተኛ ደረጃ ላይ

የደረሰበት ከመሆኑም በተጨማሪ የተለያየ የፖለቲካ ፍላጎት ያላቸው በአውሮፓና በሰሜን አሜሪካ

የተፈጠሩ የፖለቲካ አስተሳሰቦች አገር በቀል ከሆኑ የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር ተዳምረው የፖለቲካ

ጡዘቱን የጨመሩበት ወቅት ነበር፡፡ ይህም እጅግ የተለያየ ፍላጎት ያላቸው ቡደኖችን በአንድ አውድ ላይ

በማገናኘት አገሪቱ ውስጥ ያልተፈለገ መስዋእትነት ያስከፈለ መሆኑ እሙን ነው፡፡ በወቅቱ ለተፈጠሩ

ግጭትና ውድመቶችም የአንበሳውን ድርሻ ወሳጅ መሆን አለባቸው ተብሎ የተበየነባቸው ፕሬዝዳንት

መንግስቱ ኃ/ማርያም ላይ ያለው እይታም አብዛኛውን ኢትዮጵያዊ በሁለት ጎራ ከፍሎ የሚያነታርክ

ኩነት ሆኖ ይሄው ድፍን 30 ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ የንጉሱን ሹማምንት ጅምላ ግድያ ፣ የቀይ ሽብር አዋጅን ተከትሎ በከተማዎች የተካሄደውን

የወጣቶች እልቂት ጨምሮ በትግራይ ፣ በኤርትራና በሌሎቹም የአገሪቱ ክፍሎች በተካሄዱ ጦርነቶች

ምክንያት ላለፈው የዜጎች ህይወት በተጠያቂነት የሚያስቀምጧቸው ዜጎች የመኖራቸውን ያህል

ፕሬዝዳንቱ የነበራቸውን አገር ፍቅር ፣ በግል ስብእናቸው ከሌሎቹ የአፍሪካ መሪዎች በተለየ ሁኔታ
ሙስናን የሚፀየፉ ያላቸውን ጊዜ ፣ ጉልበትና የፋይናንስ አቅም ለአገር ፍቅር ያዋሉ መሪ ናቸው

በማለት ዛሬም ድረስ ስማቸውን የሚያነሱ በርካቶች ናቸው፡፡

2. የፕሮፖዛሉ ዓላማ
የዚህ ፕሮጀክት (ፕሮፖዛል) ዋና ዓላማ የወቅቱን ፖለቲካ ሲመሩ የነበሩትን ጓድ መንግስቱ ኃ/ማርያም

የማውገዝና የማወደስ ሳይሆን ፕሬዝዳንቱ አንድን ትልቅና ገናና አገር በመምራት ለ17 ዓመታት የቆዩ

መሪ በመሆናቸውና በነዚህ አመታትም እንደማንኛውም የአገራችን መሪዎች የሰሯቸው ጥፋቶች

ቢኖሩም የነበራቸውን የአገር ፍቅር ከምንም በላይ ደግሞ በኢትዮ ሱማሊያ ጦርነት ወቅት ውድ

ህይወታቸውን ለእናት አገራቸው ሲሉ የሰው ውድ የኢትዮጵያ ሰራዊት ልጆቻቸው እንዳይቸገሩና

አባቶቻቸው ለአገር ለሰሩት ውለታ ልጆቻቸውን በማሰባሰብ የአበዮታዊት ኢትዮጵያ ህፃናት አምባን

በመገንባት ለሰሩት ስራ ፣ አገሪቱ ከድህነት እንድትወጣ የትምህርትን አስፈላጊነት በመገንዘብ በአገሪቱ

የመሰረተ ትምህርት እንዲስፋፋና ዜጎች ሁሉ የትምህርት እድል እንዲያገኙ ላደረጉት አስተዋፅኦ ፣

አገሪቱ አንድነቷ እንደተጠበቀ ከውጪ ወራሪና ከውስጥ የተለያየ ፍላጎት ያላቸው ሃይሎች አገሪቷን

ለአደጋ እንዳይዳርጓት ለወቅቱ ይዋጃል ብለው ባሰቡት የፖለቲካ እሳቤ ለአገሪቱ ላደረጉት ውለታ ይሆን

ዘንድ በስማቸው አንድ ግብረ ሰናይ ድርጅት (ፋውንዴሽን) ለማቋቋም የቀረበ መነሻ ሃሳብ ነው፡፡

You might also like