You are on page 1of 44

ረቂቅ የማዕድን ሀብት ልማት ፖሊሲ

ነሐሴ 2012 ዓ.ም

አዲስ አበባ ፤ ኢትዮጵያ


ማውጫ

1. መግቢያ........................................................................................................................................ 1

2. የፖሊሲው መነሻ፣ የሀገሪቱ የማዕድን አለኝታ፣ የዘርፉ ክፍተቶች ................................................................... 3

2.1. መነሻ .................................................................................................................................... 3

2.2. የኢትዮጵያ የማዕድን አለኝታ ....................................................................................................... 5

2.3. የዘርፉ ዋና ዋና ክፍተቶች ........................................................................................................... 6

3. የማዕድን ልማት ፖሊሲ፤ ርዕይ፣ ግቦች፣ ዓላማዎችና ሥልቶች ..................................................................... 7

3.1. ርዕይ .................................................................................................................................... 7

3.2. ግቦች .................................................................................................................................... 8

3.2.1. የማዕድን ዘርፍ ልማት ለመዋቅራዊ ሽግግር .................................................................................. 8

3.2.2. የማዕድን ዘርፍ ልማት ለዘላቂ ማኅበራዊ ለውጥ ............................................................................ 9

3.2.3. ተወዳዳሪ የማዕድን ዘርፍ ኢንዱስትሪ መገንባት........................................................................... 10

3.2.4. ዘላቂ ልማትን የሚያረጋግጥ የማዕድን ዘርፍ ልማት ...................................................................... 10

3.3. ዓላማዎች ............................................................................................................................ 10

3.4. ሥልቶችና መርሆች ................................................................................................................ 10

3.4.1. የማዕድን ዘርፍ ሚናን በአግባቡ መለየት ................................................................................... 11

3.4.2. የአገሪቱን የማዕድን አቅም በቅጡ መለየት፣ በዘመናዊ መረጃ ማጠናቀር .............................................. 12

3.4.3. የማዕድን ልማት ዕቅድና ስትራቴጂ ማውጣት ............................................................................. 12

3.4.4. የአፈጻጸም ክትትል ............................................................................................................. 13

4. ትኩረት የሚሰጣቸው ዋና ዋና የፖሊሲ ጉዳዮች ..................................................................................... 13

4.1. የማዕድን ልማት ለኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ልማት ............................................................................ 14


4.1.1. የከበሩ፣ ቤዝ ሜታልና እና ብረት ነክ (ሜታሊክ) ማዕድናት ............................................................ 14

4.1.2. የፖሊሲ ዓላማ .................................................................................................................. 14

4.1.3. የማስፈጸሚያ ስልቶች፡- ....................................................................................................... 14

4.2.1 የኢንዱስትሪ ማዕድናት ........................................................................................................ 15

4.2.2 ዋና ዋና ችግሮች፡ ............................................................................................................... 15

4.2.3 የፖሊሲ ዓላማ .................................................................................................................. 16

4.2.4 የማስፈጸሚያ ስልቶች .......................................................................................................... 16

4.3.1 ማዕድናት እንደ ግብርና ግብአት፣ ............................................................................................ 17

4.3.2 ዋና ዋና ችግሮች ................................................................................................................. 17

4.3.3 የፖሊሲ ዓላማ .................................................................................................................. 18

4.3.4 የማስፈጸሚያ ሥልቶች ........................................................................................................ 18

4.4.1 የግንባታ/ኮንስትራክሽን እና የገጥ ማዕድናት ............................................................................... 18

4.4.2 ዋና ዋና ችግሮች ................................................................................................................. 19

4.4.3 የፖሊሲ ዓላማ .................................................................................................................. 19

4.4.4 የማስፈጸሚያ ስልቶች .......................................................................................................... 20

4.5.1 የጌጣጌጥ ድንጋዮች/ማዕድናት ................................................................................................ 20

4.5.2 ዋና ዋና ችግሮች ................................................................................................................. 20

4.5.3 የፖሊሲ ዓላማ .................................................................................................................. 21

4.5.4 የማሰፈጸሚያ ሥልት ........................................................................................................... 21

4.6.1 ስለባህላዊና አነስተኛ የማዕድን ሥራዎች ................................................................................... 21

4.6.2 ዋና ዋና ችግሮች ................................................................................................................. 22

4.6.3 የፖሊሲ ዓላማ .................................................................................................................. 22

4.6.4 የማስፈጸሚያ ሥልቶች ........................................................................................................ 22


4.7.1 ስለአካባቢ ጥበቃ፣ ማኅበራዊ ጉዳዮችና ዘላቂ ልማት .................................................................... 24

4.7.1.1 ስለአካባቢ ጥበቃ ............................................................................................................ 24

4.7.1.2 የፖሊሲ ዓላማ ............................................................................................................... 24

4.7.1.3 የማስፈጸሚያ ሥልት ....................................................................................................... 24

4.7.2.1 የማዕድን ልማት ለዘላቂ ማኅበራዊ ልማት .............................................................................. 25

4.7.2.2 የፖሊሲ ዓላማ ............................................................................................................... 25

4.7.2.3 የማስፈጸሚያ ሥልቶች ..................................................................................................... 25

4.8 የማዕድን ኢንቨስትመንትና ገበያ ................................................................................................. 26

4.8.1 የማዕድን ኢንቨስትመንት ...................................................................................................... 26

4.8.1.1 የፖሊሲ ዓላማ ............................................................................................................... 26

4.8.1.2 ማስፈጸሚያ ሥልቶች ...................................................................................................... 27

4.8.2 የማዕድን ገበያ ................................................................................................................... 27

4.8.2.1 የፖሊሲው ዓላማ ........................................................................................................... 28

4.8.2.2 የማስፈጸሚያ ሥልቶች ..................................................................................................... 28

4.9 ተወዳዳሪ የማዕድን ዘርፍ ስለመፍጠር.......................................................................................... 28

4.9.1 የፖሊሲ ዓላማዎች.............................................................................................................. 28

4.9.2 የአፈጻጸም ሥልቶች ............................................................................................................ 29

4.10 የማዕድን ልማት ሕግና አስተዳደር .............................................................................................. 30

4.10.1 ዋና ዋና ችግሮች ................................................................................................................. 30

4.10.2 የፖሊሲ ዓላማ .................................................................................................................. 31

4.10.3.1 የማሥፈጸሚያ ሥልት - ሕጎችን በተመለከተ .......................................................................... 31

4.10.3.2 የማሥፈጸሚያ ሥልት - የአስተዳደርና የምርምር ተቋማትን በተመለከተ ......................................... 32

4.10.3.3 የሰው ኃይል ሥልጠና እና አስተዳደር ................................................................................... 33


4.11 ዘርፈ-ብዙ ጉዳዮች ................................................................................................................. 33

4.11.1 ስለሴቶች መብትና ስለሥርዓተ-ጾታ ......................................................................................... 33

4.11.1.1 የፖሊሲ ዓላማ ............................................................................................................... 33

4.11.1.2 የአፈጻጸም ሥልቶች ........................................................................................................ 33

4.11.1.3 የሠራተኞች መብትና አያያዝ .............................................................................................. 34

4.11.2 የሕፃናት ጥበቃ .................................................................................................................. 34

4.11.3 የአካል ጉዳተኞች መብት ...................................................................................................... 34

4.11.4 ተላላፊ በሽታዎችና ወረረሽኝ ................................................................................................. 34

5. የፖሊሲ አፈጻጸም ማዕቀፍ ............................................................................................................... 34

6. የፖሊሲው የተፈጻሚነት ወሰን .......................................................................................................... 35

7. ፖሊሲውን የማስፈጸም ኃላፊነት ያለበት ተቋም ..................................................................................... 35

8. የባለድርሻ አካላት እና ሚናቸው ........................................................................................................ 35

9. የፖሊሲ ክትትል፣የግምገማ እና የክለሳ ስርዓት ....................................................................................... 37

10. የፖሊሲው ስርጭት ................................................................................................................... 37

11. ፖሊሲው ተፈጻሚ የሚሆንበት ጊዜ ................................................................................................ 37

12. የቃላት መፍቻ .......................................................................................................................... 37


1. መግቢያ

በመዋቅራዊ ሽግግር ሂደት ከፍጹም ድህነት ወደተሻለ ብልጽግና ለመቀየር ለሚታትር አገር ማዕድናትን ጨምሮ የተፈጥሮ

ሀብቶች በእጅ ላይ የሚገኙና የኛን የመጠቀም አቅምን ማደግ ብቻ የሚጠይቁ እድሎች ናቸው፡፡ ይሄን የእድገት መስመር

በአግባቡ በተከተልን ልክ ኢትዮጵያ በጊዜ ሠሌዳ የተመላከተውን የመካከለኛ ገቢ ባለቤት የመሆን ርዕይ ለማሳካትና ለዚህም

የሚመጥን የኢንዱስትሪ ልማት አቅም ለመገንባት ለወጠነቻቸው የግብርና ዝመና እና የአምራች ኢንዱስትሪ መሳካት የማዕድን

ሀብቷን በአግባቡ ማበልጸግና መጠቀም ያስችላታል።

ከጥሬ ዕቃ ግብዓትነት እስከ ተወዳዳሪ ኢንዱስትሪነት አስፈላጊ የሆኑት የማዕድን ሀብቶች ለልማት ወሳኝ የመሆናቸውንና

ለዚህም ሚናቸው በኢትዮጵያ በተለያዩ ጊዚያት በወጡ የልማት ዕቅዶች እውቅና የመሰጠቱን ያህል ኢትዮጵያ ከማዕድን

ልማት በተገቢው ደረጃ መጠቀም አልቻለችም። በተለይም፤-

1. በተለያዩ ነገር ግን ተያያዥ ዘርፎች የሚቀመጡ ግቦች አለመጣጣምና የተቋማት አለመቀናጀት፣ በማዕድናት ዓይነቶችና

ትርጉም ላይ በሚፈጠር የግንዛቤ ክፍተት፣ እንዲሁም ከልማት፣ ከአካባቢ ጥበቃና ከማሕበራዊ ተጠቃሚነት አንጻር

በዘርፉ ዙሪያ በተያዙ ገንቢ ያልሆኑ ግንዛቤዎች ምክንያት ከማዕድን ልማት የሚጠበቀውን ያህል እየተጠቀመች

ባለመሆኑ፡፡

2. የማዕድን ሀብት በባሕርይው አላቂ፣ ዋጋው በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚዋዥቅና ውጤቱም ከእሴት ይልቅ ወደ ኪራይ

ስለሚያደላ፣ በዚህም ምክንያት የተለየ የልማት ሥርዓት የሚስፈልገው ዘርፍ በመሆኑ፡፡

3. ዘርፉ ከዘላቂ ልማት በተለይም ከአካባቢ ጥበቃ፣ ከመሬት አጠቃቀም፣ ከማኅበረሰባዊ የጋራ ተጠቃሚነትና ማኅበራዊ

ደህንነት ጋር የተሳሰረ በመሆኑ፤

4. የማዕድን ሀብት ልማት ከአዋጭነትም ይሁን ከሰላማዊ እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ ስጋት ያለበት፣ በአንጻሩ ከፍተኛ

የመዋዕለ ንዋይ እና የቴክኖሎጂ አቅም የሚጠይቅ በመሆኑ የተለየ ትኩረትና የረጅም ጊዜ ዋስትና ስለሚያስፈልገው፤

5. ማዕድናት ትኩረት የሚያሻቸው፣ የስትራቴጂካዊነትና የጂኦ-ፖለቲካዊ ባሕርይ ሊኖራቸው የሚችል በመሆኑ፤

6. ኢትዮጵያ ላቀደችው ወደ ኢንዱስትሪ ሽግግር ግብ መሳካት በሚደረገው ጥረት፣ በቴክኖሎጂ እና በሰለጠነ የሰው ኃይል

እጥረቶች ምክንያት የሚያጋጥሙ የአጭር ጊዜ ዓለም አቀፋዊ የተወዳዳሪነት ክፍተቶችን በርካሽ የአገር ውስጥ ጥሬ

ዕቃዎችና ግብዓቶች ለማካካስ የማዕድን ሀብት ልማት ወሳኝ በመሆኑ፤

ረቂቅ የማዕድን ሀብት ልማት ፖሊሲ 1


7. በአጠቃላይ በመዋቅራዊ ሽግግር ሂደት የተፈጥሮ ሀብትን በተለይም ማዕድናትን ማልማት፣ ማበልጸግ፣ ማዕድናትን

ለኢንዱስትሪያላዊነት በግብዓትነት መጠቀም የማይታለፍ ርከን የመሆኑ ጉዳይ እና ለዚህም አገሪቷ ያላትን የማዕድን

ሀብት በቅጡ የመለየት ተግባር ከሰሞንኛ ጥረት ባለፈ ልዩ ትኩረት ስለሚያስፈልገው፤

8. ከ1987 ጀምሮ በወጡ የአገሪቱ የተለያዩ የግብርና እና የኢንዱስትሪ ልማት ስትራቴጂዎች፣ ዕቅዶችና ፖሊሲዎች

የማዕድን ውጤቶችን በጥሬ ዕቃነት የሚጠቀሙ የልማት ትልሞች ቢመላከቱም፣ የሀገር ውስጥ የማዕድን ሀብትን

የኢንዱስትሪ ትስስርን፣ የአካባቢ ጥበቃን፣ የማኅበረሰብ ተጠቃሚነትን፣ በዘርፉ የቴክኖሎጂና የሰብዓዊ ሀብት አቅምን

ጨምሮ ተወዳዳሪ ኢንዱስትሪ መፍጠርን፣ በአጠቃላይ ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ በሚያግዝ መልኩ ለማልማት

በሚያስችል ደረጃ በበቂ ሁኔታ የተቃኙ ባለመሆናቸው፤

9. ከዘርፉ የሚፈለገውን አስተዋጽኦ በመለየት ለዘርፉም የሚያስፈልገውን ድጋፍና ክትትል እና የመልካም አስተዳደር

ሥርዓት መዘርጋት አስፈላጊ በመሆኑ፣

10. የማዕድን ልማትና አጠቃቀም እንዲሁም ዘርፉ ከሌሎች ኢንዲስትሪዎች ጋር እንዲተሳሰርና ለሀገር ልማት ተገቢውን

አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ለማስቻል መንግሥት አስፈላጊ የሆኑ ተቋማትን ማደራጀት፣ እንደሁኔታውም ልዩ ትኩረት

ሊሰጣቸውና በራሱ አቅምም ሊያከናውናቸው የሚገባቸውን ሥራዎች በግልጽ መለየትና ማመላከት አስፈላጊ

በመሆኑ፣

11. ከላይ የተጠቀሱት ጉዳዮች ያላሰለሰ ትኩረት የሚሹ በመሆኑና፣ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ

መንግስት አንቀጽ 40 (3) እና 89 (5) መሠረት የተፈጥሮ ሀብት ባለቤትነት የመንግሥትና የሕዝብ መሆኑና

መንግሥትም የተፈጥሮ ሀብትን ለሕዝቡ የጋራ ጥቅምና እድገት እንዲውል የማድረግ ኃላፊነት እንዳለበት የተደነገገ

በመሆኑ ለዘርፉ ልማት መሳካት ይህ የማዕድን ዘርፍ ልማት ፖሊሲ ወጥቷል።

በአጠቃላይ ከሀገሪቱ የመልማት ፍላጎትና የሀገሪቱን የተፈጥሮ ሀብት የማልማት ሕገ-መንግሥታዊ ድንጋጌ መሠረት በማድረግ

የሀገሪቱን የማዕድን ሀብት በአግባቡና በዘላቂነት ለማልማት እንዲሁም ዘርፉ ለሀገር የማኅበራዊና የኢኮኖሚ ልማት

ግብአትነት እንዲያገለግል ማድረግ እንዲቻል የማዕድን ልማት አስተዳደርና የድጋፍ ሥርዓት ማስፈን አስፈላጊ በመሆኑ፤

ዘርፉን ከሌሎች ወሳኝ ከሆኑ የኢኮኖሚ ዘርፎች ጋር በማስተሳሰር መዋቅራዊ ሽግግርና ሀገራዊ ልማት እንዲያመጣ፣ ለልማቱ

አስፈላጊ የሆነውን የውጭ ምንዛሪ እንዲያስገኝ፣ የሥራ እድል እንዲፈጥር፣ የሀገሪቱ ዜጎች ከልማቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ

ረቂቅ የማዕድን ሀብት ልማት ፖሊሲ 2


ለማስቻል ግልጽ የፖሊሲ አቅጣጫዎችን መንደፍና በሥራ ላይ ማዋል አስፈላጊ መሆኑን በማመን ይህንን ለሚቀጥሉት ሃያ

ዓመታት የሚያገልግል ፖሊሲ አውጥቷል።

2. የፖሊሲው መነሻ፣ የሀገሪቱ የማዕድን አለኝታ፣ የዘርፉ ክፍተቶች

2.1. መነሻ

የቅርብ ዘመን የሀገሮች በኢኮኖሚ የመበልጸግና የመልማት ታሪክ እንደሚያሳየው ከኢንዱስትሪ አብዮት እስከ የ21ኛው ክፍለ

ዘመን የዲጂታል ቴክኖሎጂ ድረስ የታዩ ስኬቶችና ሀገራዊ አቅሞች ዕውን መሆን የቻሉት ጥሬ የማዕድን ሀብትን ለተለያዩ

ዘርፎች በግብዓትነት በመጠቀም ነው። ለኢኮኖሚ ብልጽግና፣ለልማትና አጠቃላይ ሀገራዊ አቅም ግንባታ የተጉ፣ እንዲሁም

የሚተጉ ሀገሮች ከራሳቸው የማዕድን ሀብት አልፈው የጎደላቸውን እና የሌላቸውን ለጥሬ ዕቃ የሚውል ማዕድን ከታዳጊ

አገሮች ወስደዋል፤ በመውሰድ ላይም ይገኛሉ። ከዚህ በተቃራኒው የዓለም አቀፍ አመለካከቶች በታዳጊ ሀገሮች በተለይም

በአፍሪካ የማዕድን ሀብት የጥገኝነት፣ የግጭትና የአካባቢ ብክለትና መራቆት ምንጭ፣ በዚህም ሳቢያ የኋላቀርነት ምክንያት

አድርገው የሚያትቱ በመሆናቸው ዘርፉ ለዕድገት ያለውን የማይተካ ሚና በአህጉሩ እንዳይጫወት ተገድቦ ቆይቷል። የግጭት፣

የጥገኝነትና የአካባቢ መራቆት ምንጩ የማዕድን ሀብት ሳይሆን የማዕድን ሀብትን በአግባቡና ከዘርፉ ኃያላን ተጽዕኖ ውጪ

የማልማት፤ የማስተዳደርና የመጠቀም ዕድልና አቅም ማጣት ነው።

በኢትዮጵያ፣ የማዕድንና ተያያዥ (mining and quarrying) ዘርፍ ተጨማሪ እሴት ከ2001 እስከ 2005 የበጀት ዓመታት

በአማካይ በ25.9 በመቶ ሲያድግ የነበረ ሲሆን፣ በ2005 ከአጠቃላይ ሀገራዊ ምርት (Gross Domestic Product -

GDP) የ1.4 በመቶ ድርሻ ነበረው። በ2004 እና በ2005 የበጀት ዓመታት ከአጠቃላይ የወጪ ንግድ ገቢ ውስጥ የማዕድን

ዘርፍ በተለይም የወርቅ ማዕድን የ19 በመቶ ድርሻ የነበረው ሲሆን በተለይ በ2004 የበጀት ዓመት 602.4 ሚሊዮን ዶላር

በማስገኘት ከቡና ቀጥሎ የሀገሪቱ ሁለተኛ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ምንጭ መሆን ችሎ ነበር። በ2010 የበጀት ዓመት በዓለም

አቀፍ የወርቅ ዋጋ መውረድና በአገሪቱ በተከሰተው ግጭት ምክንያት የዘርፉ ለሀገራዊ ምርትና ለወጪ ንግድ የነበረው

አስተዋፅኦ በቅድም ተከተል ወደ 0.4 በመቶ እና 3.6 በመቶ ቀንሷል። ይህም ዘርፉ ልዩ ትኩረት እንደሚያስፈልገው

ያመላክታል።

ረቂቅ የማዕድን ሀብት ልማት ፖሊሲ 3


በኢትዮጵያ ትርጉም ባለው ደረጃ ዘመናዊ የማዕድን ልማት የሚታየው በወርቅ ማዕድን ነው። ይህን ልማት ወደ ሌሎች የከበሩ

ማዕድናት የማስፋፋት ጥረቶች ውስንነት እንዳለ ሆኖ፣ የወርቅ ማዕድን ማውጣት በኢትዮጵያ የረጅም ጊዜ ታሪክ ያለው

የመሆኑን ያህል የውጭ ምንዛሪ ከማስገኘት፣ ለዜጎች የሥራ ፈጠራና የገቢ ምንጭ ከመሆን፤ በገንዘብ ተቋማት እንደ ሀብት

መያዢያነት ከመቆጠር፤ እንዲሁም በሀገር ደረጃ እንደ አንድ ተወዳዳሪ ኢንዱስትሪ ጎልቶ ከመውጣት አንጻር ብዙ ርቀት

አልተሄደም።

የማዕድን ዘርፍ ከሌሎች የኢኮኖሚ ዘርፎች ጋር ካለው ትስስር አኳያ የአሸዋ፣ ኢግኒምብራይት፣ ባሳልትን የመሳሰሉ ድንጋዮች፣

የዕምነ በረድ፣ ግራናይትና የኖራ ድንጋይ ማዕድናት ለኮንስትራክሽን እና ለአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፎች ጠቃሚ ግብአቶች

ናቸው። ነገር ግን የአገሪቷን የኢኮኖሚ ዕድገት ፍጥነት እየመራ የሚገኘው የኮንስትራክሽን ዘርፍ እስከ 70 በመቶ የሚደርሰው

ግብዓት በማዕድናት ላይ እሴት ተጨምሮባቸው ከውጭ ሀገር የሚገቡ ምርቶች በመሆናቸው የኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ

ሊሞላው የሚገባ ክፍተትና አቅም መኖሩን ያሳያል።

ከዚህም በላይ ኢትዮጵያ ለወጠነችው የመዋቅራዊ ሽግግር ዕቅድና የመካከለኛ ገቢ ትልም መሳካት ወሳኝ እንደሆኑ

የታመነባቸውን የአምራች ኢንዱስትሪ እና የግብርና ዝመና ስትራቴጂዎች ከማፋጠን አንጻር ከማዕድን ዘርፍ ልማት ገና

ከፍተኛ ሚና ይጠበቃል።

የማዕድን ሀብትን በባሕላዊ ዘዴ በጥቅም ላይ ማዋል በኢትዮጵያ የብዙ ሺህ ዘመን ታሪክ ያለው ከመሆኑም በላይ የኢትዮጵያ

የጂኦሎጂካል አወቃቀር ጠቃሚ ለሚባሉት አብዛኞቹ ማዕድናት መገኛ መሆኑን ያመላከተው የሥነ ምድር ጥናት፣ እንዲሁም

የማዕድን ፍለጋና ምርመራ የተጀመረው ከሁለት ምዕተ ዓመት በፊት ነው። በተጨማሪም የማዕድን ሀብትን የግብርና ዝመናን

ጨምሮ ለኢንዱስትሪያላዊነት ለማዋል ከፍተኛ ዕምነት ማሳደር ብቻ ሳይሆን ለተግባራዊነቱ በመንግሥት የልማት ዕቅድ

ውስጥ ማካተት የተጀመረው በ1940ዎቹ መጨረሻ ሲሆን የማዕድን ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ሰርቬይን

የመሳሰሉ ወሳኝ ተቋማት የተመሠረቱት በዚሁ ወቅት፣ ከ60 ዓመታት በፊት ነው። በዚህ ሁሉ ዘመን ጥረት ውስጥ

የኢትዮጵያን የማዕድን ሀብት በቅጡና በሚገባው ደረጃ ለሀገር ልማት እስካሁን ማዋል ያልተቻለበት ምክንያት ምንድነው

የሚለው ትልቁ የፖሊሲ ጥያቄ ነው።

ለኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ ልማት ጥረት መውደቅና መነሳት መሠረታዊ ምክንያቶች በሌሎቹ ዘርፎችና መስኮች

እንደሚያጋጥመው ሁሉ የአፈጻጸም ሥልት፣ የተቋማት ዝቅተኛ ብቃትና አለመቀናጀት፣ በውጥኖች መንገራገጭ ተስፋ መቁረጥ

እና በሥርዓታት ለውጥ ምክንያት የትኩረት አቅጣጫዎችና የልማት ቀጣይነት ማጣት፣ በዘርፉ ዙሪያ በተያዙ ያልተገቡ

ረቂቅ የማዕድን ሀብት ልማት ፖሊሲ 4


አመለካከቶችና ግንዛቤ ሳቢያ የተፈጠረ የትኩረት ማነስ ናቸው። ለዚህም ዓይነተኛው መፍትሄ የማዕድን ዘርፍ ልማት የረጅም

ጊዜ ያላሰለሰ ትኩረት እንዲያገኝ ለዘርፉ የሚመጥን ፖሊሲ ማውጣት ነው። በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ

ከዘርፉ የትኩረት አቅጣጫዎች መካከል ኢንቨስትመንትን የሚያስፋፉ ፖሊሲዎችንና ሕጎችን በመቀየስ ልማቱን መምራት

ቀዳሚው ጉዳይ እንደመሆኑ መጠን፣ የዚህ ፖሊሲ ሠነድ ዋና ሚናም የዘርፉን ፋይዳ በአግባቡ በመለየት ትኩረት እንዲሰጠው

በማድረግ፣ የትኩረት አቅጣጫዎችን አጉልቶ በማውጣትና፣ የመፈጸሚያ ሥልቶችን በመንቀስ፣ በዘርፉ የመንግሥትን

አቅጣጫ ማመላከትና በዚህም የማዕድን ሀብትን ልማትና ሀገራዊ አስተዋጽዖ ማሳደግ ነው።

ኢትዮጵያ በመዋቅራዊ ሽግግር ሂደት በኢንዱስትሪ ልማት መበልጸግን ግብ አድርጋ ስትንቀሳቀስ ጥሬ ማዕድናትን ወይም

በከፊል የተሰናዱ የማዕድን ውጤቶችን በግብዓትነት መጠቀሟ የግድ ይሆናል። በልማት ሂደት ውስጥ በሀገር ውስጥ የማይገኙ

ለጥሬ ዕቃነት የሚውሉ ማዕድናትን ከውጭ ማስገባት ግድ እንደሚል ሁሉ በሀገር ውስጥ የሚገኙ ማዕድናትን ለግብዓትነት

መጠቀም አዋጭ ብቻ ሳይሆን የመዋቅራዊ ሽግግር የማይታለፍ እርከን ነው። ሀገሪቱ ለግብዓትነት የማትፈልጋቸውን ወይም

ከራሷ ፍጆታ በላይ በትርፍ የምታመርታቸውን የማዕድን ዓይነቶች ለዓለም አቀፍ ገበያ በማቅረብ የዛሬን ፍጆታ ብቻ ሳይሆን

የነገ የልማት ግቦችን ለማሳካት የተወጠኑ ፕሮጀክቶችን የውጭ ምንዛሪ ፍላጎትበማሟላት ዘርፉ የላቀ ሚና እንዲጫወት

ማድረግ ተገቢ ይሆናል። የማዕድን ዘርፍ የግጭት መነሻ ሳይሆን የማኅበረሰብ የሀብትና የልማት ፍትሃዊ ተጠቃሚነት

ማረጋገጫ አንድ መስክ ማድረግ ያሻል። ከዚህም በላይ የማዕድን ዘርፍ በሥራ ፈጠራ፣ በእሴት፣ በተቋማዊ ብቃት፣ በክህሎት

ይዘት እና በቴክኖሎጂ አቅምልቆ እንደ አንድ አዋጭ ኢንዱስትሪና ኢኮኖሚያዊ አቅም ጎልቶ መውጣት እንደሚችል የሀገራት

ልምድ ያሳያል። የኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ ልማት ፖሊሲም ዘርፉን በአማራጭ ደጋፊነት ሳይሆን ከልማት አንጻር ምትክ

የሌለው ወሳኝ ዘርፍ መሆኑን አጽንኦት ይሰጣል። የኢትዮጵያ የማዕድን ፖሊሲ የማዕድን ዘርፍ አጠቃላይ የሀገሪቱን የአጭር፣

የመካከለኛና የረጂም ጊዜ የዕድገትና የዘላቂ ልማት ግቦች ለማሳካት በሚያስችል መልኩ የተቃኘ ነው።

የማዕድን ዘርፍ ልማት ፖሊሲው የዘርፉን ርዕይ፣ ዓላማ፣ ግብና የማሳኪያ ሥልቶች ያመላክታል፤ የዋና ዋና የትኩረት

አቅጣጫዎችን ይለያል፤ የአገሪቷን ማዕድን ዘርፍ ሚና እና ፍኖተ ልማት ይለያል፣ ያመላክታል።

2.2. የኢትዮጵያ የማዕድን አለኝታ

አንዳንድ መረጃዎች እንደሚያሳዩት፣ በኢትዮጵያ የሥነ ምድር ጥናት፣ እንዲሁም የማዕድን ፍለጋና ምርመራ የተጀመረው

በ1831 ሲሆን፣ እስካሁን በተገኙ መረጃዎች መሠረት አገሪቷ ካላት 1.1 ሚሊዮን ካሬ ኪሎ ሜትር የቆዳ ስፋት ውስጥ 25

በመቶ የሚሆነው የቅድመ-ካምብሪያን (Precambrian) ቅርጸ ልውጥ እና እሳተ-ገሞራ ወለድ ዓለት፣ ተጨማሪ 25 በመቶ

ረቂቅ የማዕድን ሀብት ልማት ፖሊሲ 5


የሚሆነው የመካከለኛው ዘመን (Mesozoic) ንብብር ዓለት፣ እና 50 በመቶ የሚሆነው የቅርብ ዘመን (Cenozoic) የእሳተ

ገሞራና ንብብር ዓለት የጂኦሎጂ ቅንብር ያለው ነው። የቅድመ-ካምብሪያን የጂኦሎጂ ቅንብር በተለይም እንደ ወርቅ፣ ብረት፣

መዳብ፣ እና ኒኬል የመሳሰሉ ማዕድናት አለኝታ መሠረት ሲሆን፣ የመካከለኛው ዘመን የጂኦሎጂ ቅንብር ለነዳጅና ብረታ

ብረት ነክ ያልሆኑ ማዕድናት መገኛ ነው። በአብዛኛው የሀገሪቷን አካባቢ የሚሸፍነው የቅርብ ዘመን የጂኦሎጂ ቅንብር

የተፈጥሮ ዘይትና ጋዝ፣ ፖታሽ፣ ጨው፣ የኖራ ድንጋይ፣ ጀሶ፣ የብርጭቆ አሸዋ፣ ዶሎማይት፣ ቤንቶናይት፣ ዳያቶማይት፣ ሶዳ

አሽ፣ ፑሚስ፣ ኦፓል እና ዲኝ የመሳሰሉ የኢንዱስትሪ ማዕድናት መገኛ ነው።

2.3. የዘርፉ ዋና ዋና ክፍተቶች

በአሁኑ ጊዜ ያለው የኢትዮጵያ የማዕድን ልማት፣ የማዕድን አለኝታን በቅጡ ለመለየት፣ ማዕድናት ለምተው ለማኅበራዊ እና

ኢኮኖሚያዊ ልማት መፋጠን አቅም እንዲሆኑ ለማድረግ፣ እንዲሁም የማዕድን ዘርፍን እንደ አንድ አዋጭ ኢንዱስትሪ

ለማዘመን፤ በየዘመኑ በተለያዩ የልማት ዕቅዶች የመወጠኑንና የመመላከቱን ያህል በሚጠበቀው ደረጃ ላይ አይገኝም።

በእርግጥ፣ ኢትዮጵያ ማዕድናትን ጨምሮ ሰፊ የተፈጥሮ ሀብት ያላት ሀገር መሆኗ የታወቀ ሆኖ ሳለ፣ የተፈጥሮ ሀብቶቿ

በተለይም ማዕድናቶቿ በዝቅተኛ የልማት ደረጃ ላይ መገኘታቸው ሀገሪቷ ከሌሎች የበለጸጉ ሀገሮች አንጻር በልማት ወደኋላ

የመቅረቷ ምክንያትም፣ መገለጫም ነው። የእስከአሁኑ እና የአሁኑ የዘርፉ ታሪክ እንደሚያመላክተው በኢትዮጵያ የማዕድን

ሀብት ልማት ዙሪያ የታዩ ዋና ዋና ችግሮች እና ለዋና ችግሮቹ በምክንያትነት የሚቀርቡ ሌሎች ችግሮች ቢያንስ በአምሥት

ደረጃ ሊከፈሉ ይችላሉ።

• በመጀመሪያ ደረጃ፣ የዘርፉ መነሻ ችግር በኢትዮጵያ የማዕድን ሀብት አለኝታ የመኖሩን ያህል ማዕድናት ለምተውና

በልጽገው ለአገሪቱ ኢኮኖያዊና ማኅበራዊ ልማት በሚጠበቀውና በሚፈለገው ደረጃ ጥቅም ላይ መዋል አለመቻላቸው

ነው፤

• ለማዕድን ዘርፉ አለመልማት፣ በተለይም በኢኮኖሚው ውስጥ ተገቢ ሚና መጫወት ያለመቻሉ ቀጥተኛ ምክንያት

በዘርፉ ያለው ኢንቨስትመንት በመጠን፣ በዓይነትና በጥራት ዝቅተኛ የመሆን ችግር ነው፤

• በዘርፉ ለሚታየው የኢንቨስትመንት ዝቅተኛነት የመጀመሪያ ደረጃ ቅርብ ምክንያቶች፤

o በሀገሪቱ የማዕድን አለኝታ ሽፋን መረጃ በዝርዝርና በጥራት በበቂ ደረጃ አለመኖር፣

ረቂቅ የማዕድን ሀብት ልማት ፖሊሲ 6


o መረጃው በሚገኝበትም ጊዜ መረጃ ከማቅረብ፣ የተቀላጠፈና ፈጣን የፈቃድ አሰጣጥ ሥርዓት ከማስፈን፣

ከማስተዋወቅና አቅም ያላቸውን ባለሀብቶች ከመሳብ ጀምሮ ዘርፉን የማስተዳደር አቅም ውስንነት ይጠቀሳሉ፤

• በዘርፉ ለሚስተዋለው ዝቅተኛ ኢንቨስትመንት በሁለተኛ ደረጃ የሚጠቀሱት ምክንያቶች፣

o አጠቃላይ በዘርፉ የሰለጠነ የሰው ኃይል እና የቴክኖሎጂ አቅም ደካማ መሆን፣

o ከሌሎች የኢኮኖሚ ዘርፎች በዋና ዋና የማዕድን ዓይነቶች ላይ በአግባቡ የተለየ ትርጉም ያለው ፍላጎት

አለመመላከቱና በተቋም ደረጃ መናበብ አለመኖር ናቸው።

• ከላይ ለተጠቀሱት በዘርፉ ለሚስተዋሉ ችግሮችና የምክንያቶች ሁሉ መሠረታዊ ምክንያትም፤

o በሌሎች ዘርፎች እንደሚታየው ሁሉ የዘርፉ ልማት ትኩረት ማጣት በተለይም በሥርዓታት ለውጥ ምክንያት እና

ከዘርፉ ባሕርይ አንጻር በሚያጋጥሙ ውጣ ውረዶች በሚፈጠር ተስፋ የመቁረጥ ችግር የትኩረቶች ቀጣይነት

ማጣት ወይም ሰሞነኛ መሆን፣

o የዘርፉን ልማት ከሌሎች ዘርፎች ልማት ነጥሎ የማየት ችግር ወይም የመዋቅራዊ ሽግግር መሠረቱ የማዕድን

ሀብትን በቅጡ ማልማትና መጠቀም መሆኑን በተገቢው ደረጃ ግምት ውስጥ አለማስገባት፣

o የሥልቶች ግልጽና ወጥ አለመሆን፣

o ከማኅበረሰብ እስከ ፖሊሲ አውጪ ባሉ ተቋማት ስለማዕድን ሀብትና በዘርፉ ስለሚደረጉ ኢንቨስትመንቶች

የተያዙ ገንቢ ያልሆኑ ግንዛቤዎችና አመለካከቶች፣

o የፌደራል መንግሥትና የክልል መንግሥታት የማዕድን አስተዳደር የዘርፉን ሕጎች ለመተግበር የአቅም ውስንነት

መኖር ናቸው።

3. የማዕድን ልማት ፖሊሲ፤ ርዕይ፣ ግቦች፣ ዓላማዎችና ሥልቶች

3.1. ርዕይ

የማዕድን ዘርፍ ልማት ርዕይ በቀጣዮቹ 20 ዓመታት የኢንዱስትሪ ልማት መሠረት የሚሆን፣ ፍትሃዊና ዘላቂ ማኅበራዊ

ተጠቃሚነትን፣ እንዲሁም ዘላቂ ልማትን የሚያረጋግጥ፣ እንደ ዘርፍም ተወዳዳሪ የሆነ የማዕድን ኢንዱስትሪ አቅም መፍጠር

ረቂቅ የማዕድን ሀብት ልማት ፖሊሲ 7


ነው።ይህም ኢትዮጵያ የመካከለኛ ገቢ ሀገር፣ እና ለዚህ የሚመጥኑ አቅሞች ባለቤት እንድትሆን ከተተለመው ርዕይ ጋር

የተጣጣመ ነው።

3.2. ግቦች

የማዕድን ፖሊሲው ዋና ዋና ግቦች በአጠቃላይ ከሀገሪቱ ብሔራዊ ኢኮኖሚያዊ ርዕይ የሚመነጩ እና ኢትዮጵያ

ካስቀመጠቻቸው የልማት ግቦች፣ እቅድና ስትራቴጂዎች ጋር በሚጣጣምና በሚደጋገፍ መልኩ የተቃኙናቸው። በዚህም

መሠረት፣ የዘርፉ መሠረታዊ ግቦችመዋቅራዊ ሽግግርን በማፋጠን አጠቃላይ አቅም መፍጠር ሲሆን፣ በተለይም፤

• የዘርፎች ትስስርን ማጠናከር፣

• የአምራች ኢንዱስትሪና የግብርና ዝመናን ለማፋጠን ማዕድናትን በግብአትነት መጠቀም፣

• ተጨማሪ እሴት በዘርፉ በመፍጠር ለኢኮኖሚው አስተዋጽዖ ማድረግ፣

• ለዘላቂ ማኅበራዊ ለውጥ አጋዥ ዘርፍ ማድረግ፣

• ተወዳዳሪ የማዕድን ኢንዱስትሪ በመፍጠር መዋቅራዊ ለውጥን ማምጣት፣

• በዘርፉ በሚደረግ ኢንቨስትመንት ሰበብ ኢትዮጵያ በሌሎች ወሳኝ ዘርፎች ያላትን እድል ለውጭ ባለሀብቶች

ማስተዋወቅ እንድትችል መነሻና ማደፋፈሪያ ዘርፍ ሆኖ ማገልገል፣

• በዘርፉ የጥናትና ምርምር እንዲሁም ስልጠናዎችን በማበረታታት አጠቃላይ የሰው ኃይልና የቴክኖሎጂ አቅም

መፍጠር፣

የፖሊሲው ዋና ዋና ግቦች ናቸው።

በተጨማሪም፣ ለግብርናው ዘርፍ በግብአትነት የሚውሉ ማዕድናትን ማጥናት፣ ክምችታቸውን መገምገምና ጥቅም ላይ

እንዲውሉ ማድረግ፣ ለኮንስትራክሽንና ለኢንዱስትሪ ግብዓት እንዲሁም ለውጭ ምንዛሪ ማስገኛ የሚሆኑ ማዕድናትፍለጋና

ጥናት በማካሄድ ወደ ምርት እንዲሸጋገሩ ማድረግ፣ በማዕድናት ሺያጭ የውጭ ምንዛሪ ማስገኘት፣ የባሕላዊ ማዕድናት

አመራረትና ግብይትን ማሻሻል፣ እና የአገሪቱን የሥነ ምድር መረጃ ሽፋን ማሳደግ ተያያዥግቦችናቸው።

3.2.1. የማዕድን ዘርፍ ልማት ለመዋቅራዊ ሽግግር

የማዕድን ዘርፍ ልማት ሚና የኢትዮጵያን የልማት ርዕይ ለማሳካት የተነደፈውን የመዋቅራዊ ሽግግር ሂደት ማገዝና ማፋጠን

ነው። የማዕድን ዘርፉ ኢትዮጵያ ላቀደቻቸው የአምራች ኢንዱስትሪ ልማት፣ የግብርና ዝመና እና በዓለም አቀፍ የእሴት

ረቂቅ የማዕድን ሀብት ልማት ፖሊሲ 8


ሰንሰለት ውስጥ ተወዳዳሪ መሆን ለሚችል የአገልግሎት ዘርፍ ግብዓቶችን ያመነጫል። ለእነዚህ የልማት ውጥኖችም

የሚያስፈልጉ ሌሎች ግብዓቶችና የቴክኖሎጂ ፍላጎቶች ከውጭ ለማስገባትና ለመዋቅራዊ ሽግግር ወሳኝ የሆነውን የማክሮ-

ኢኮኖሚ መረጋጋት ለማስፈን የሚያስፈልገውን የውጭ ምንዛሪ በማስገኘት የማዕድን ዘርፉ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል።

የማዕድን ዘርፉ ተወዳዳሪ የኢንዱስትሪ ዘርፍ በመሆን የሥራ ፈጠራ፣ የተጨማሪ እሴት ምንጭ በመሆን ሀገራዊ አቅም

ይፈጥራል።

የማዕድን ዘርፍ ልማት ለሌሎች ዘርፎች መልማት የማይተካ ሚና እንዳለው ሁሉ፣ የማዕድን ኢንዱስትሪ ጤናማ ልማትም

እንደ አንድ አዋጭ የኢኮኖሚ ዘርፍ በሌሎች ዘርፎች የመዘመን ደረጃ ይወሰናል። የማዕድን ሀብትን ለግብዓትነትና ለፍጆታ

የሚጠቀሙ ክፍለ ኢኮኖሚዎች ሲስፋፉ፣ የማዕድን ዘርፍ ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል የሚፈጥር፣ ለኢኮኖሚው እሴት

የሚጨምር አዋጭ ኢንዱስትሪ ይሆናል። በመዋቅራዊ ሽግግር ሂደት ከተሜነት ሲስፋፋ የማዕድን ዘርፍ ልማት በመሬት ዙሪያ

ባሉ የጥቅም ግጭቶች ምክንያት የሚያጋጥሙት ተግዳሮቶች ይቀንሳሉ፤ በአጸፋውም በልማት ሂደት የሚያጋጥሙ የከፉ

ማኅበራዊ ተጽዕኖዎችና የጎንዮሽ ጉዳቶች ይቀንሳሉ። እነዚህ ዕውነታዎች በአጠቃላይ ሀገራዊ ፖሊሲዎች ውስጥ የየዘርፉ

ፖሊሲዎች መጣጣም እንዳለባቸውና የዘርፎቹም ተቋማት መናበብ እንደሚጠበቅባቸው ያመላክታሉ።

3.2.2. የማዕድን ዘርፍ ልማት ለዘላቂ ማኅበራዊ ለውጥ

የማዕድን ልማት ዘርፍ ለዘላቂ ማኅበራዊ ለውጥ ሊኖረው የሚገባው ፋይዳ ሲታሰብ፣ የማዕድን ሀብት አላቂ፣ የተፈላጊነት

ዘመኑ በቴክኖሎጂ ለውጥ ምክንያት ሊያልፍ የሚችል፣ በዓለም አቀፍ ገበያ ዋጋው የሚዋዥቅ፣ እንዲሁም በተለምዶ ከዘርፉ

የሚገኘው ቀጥተኛ ጥቅም ከተጨማሪ እሴት ይልቅ በኪራይ ላይየተወሰነ የመሆኑ እውነታዎች ግምት ውስጥ መግባት

አለባቸው። በዚህም መሠረት፣ የማዕድን ዘርፍ ልማት ዘላቂ ማኅበራዊ ለውጥ ማምጣት የሚችለው በባህላዊም ሆነ በዘመናዊ

የማዕድን ማውጫዎች ከሚገኙ የሥራ ዕድሎች፣ የዕለት ገቢዎችና የማካካሻ ክፍያዎች ይልቅ፣ የማዕድን ዘርፍ ልማት የሌሎች

ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ዘርፎችን ልማት በማፋጠን በመዋቅራዊ ሽግግር ሂደት በሚፈጥረው አጠቃላይ ሀገራዊ አቅም ነው።

ይህ የጋራ ተጠቃሚነት እንዳለ ሆኖ፣ በማዕድን ማውጫ አካባቢ ያሉ ማኅበረሰቦች አንድም የሥልተ ምርት ለውጥ

በማምጣት፣ ሁለትም አቅምና ፍላጎት ያላቸው በማኅበር በመደራጀት በማዕድን ዘርፍ ተወዳዳሪ ኢንዱስትሪ ለመፍጠር

ለሚደረገው ጥረት እርሾ በመሆን ተጠቃሚ መሆን ይችላሉ።

የማዕድን ሀብትን በጋራ ከማልማት በተጨማሪ የአጠቃላይ ማኅበረሰብ ተጠቃሚነት ማረጋገጫ መንገዶች የመንግሥት

የፊስካል መሣሪያዎችና የአልሚዎች ማኅበራዊ ኃላፊነቶች ናቸው። አልሚዎች በሮያሊቲ፣ በገቢና የትርፍ ግብር፣ እንዲሁም

ረቂቅ የማዕድን ሀብት ልማት ፖሊሲ 9


በመሬት መጠቀሚያ ሊዝ መልክ ለፌዴራል፣ ለክልሎችና ለወረዳዎች እንዲከፍሉ የሚጠበቅባቸውን ግዴታዎች፣ እና

ለማኅበራዊ ግልጋሎት የሚጠበቅባቸውን የኮርፖሬት ኃላፊነቶች በአግባቡ መለየት፤ ግዴታዎቻቸውንም ሲወጡ ለሕዝብ

ማሳወቅ በዘርፉ ጤናማ ልማት ለማካሄድ ያግዛል። ከዘርፉ ከሚገኝ ገቢ በአልሚዎችና በመንግሥት ትብብር ብሔራዊ የገንዘብ

ቁጠባ ቋት (ትረስት ፈንድ) በማቋቋም በልማት ሂደት ለሚከሰቱ ጉዳቶች የማካካሻ አቅም ከመፍጠርም በላይ የመጪው

ትውልድን ግምት ውስጥ ያስገባ ማኅበራዊ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ይቻላል።

3.2.3. ተወዳዳሪ የማዕድን ዘርፍ ኢንዱስትሪ መገንባት

በዘርፉ ክህሎትና ሙያ በማዳበር፣ የቴክኖሎጂ ተወዳዳሪነትን በማጎልበትከተከታይነት ወደ ተወዳዳሪነትበመሸጋገር፣ ለዘርፉ

ልማት የሚያግዙ ተቋማትን በመገንባት፣ ዓለም አቀፋዊ ግንኙነቶችንና ትሥሥሮችን በማጠናከር፣ የዘርፉ የመረጃሥርዓቶችን

በማዘመን የማዕድን ዘርፉን ተወዳዳሪ ኢንዱስትሪ ማድረግ ተገቢ ነው።

በተወዳዳሪ የማዕድን ዘርፍ ልማት ውስጥ ከሚታዩት አጠቃላይ አቅሞች መካከልም መንግሥትን፣ የከፍተኛ ትምህርትና

የምርምር ተቋማትን፣ አልሚዎችን፣ ማኅበረሰብንና፣ የልማት አጋሮችን ማዕከል ያደረገ ጥናትና ምርምር ይዳብራል።

3.2.4. ዘላቂ ልማትን የሚያረጋግጥ የማዕድን ዘርፍ ልማት

የማዕድን ዘርፍልማት ጥሩ ካልሆኑ መገለጫዎቹ አንዱ በአካባቢ ላይ የሚያደርሰው ጉዳት ነው። የዘርፉ ልማት ሲታሰብ ዘመኑ

የደረሰበትን ቴክኖሎጂ በመጠቀም እና ዘላቂ የአካባቢ ጥበቃ ዘዴዎችንና ሥርዓቶችን ተግባራዊ በማድረግ አረንጓዴና ዘላቂ

ልማትን ማረጋገጥ አንዱ የማዕድን ዘርፍ ልማት የትኩረት አቅጣጫ ነው።

3.3. ዓላማዎች

የፖሊሲው ዓላማዎችበዝርዝር ዕቅድ ላይ በመጠን፣ በጊዜና በቦታ ተለይተው የሚመላከቱ የዘርፉን መረጃ፣ ኢኮኖሚው

ከዘርፉ የሚያስፈልገውን የግብዓት ፍላጎት፣ የውጭ ምንዛሪ ግኝት፣ ዘርፉ ለኢኮኖሚው የሚኖረው የተጨማሪ ዕሴት የድርሻ

መጠን እንዲሁም ኢንቨስትመንትና ገበያን የሚመለከቱ ናቸው።

3.4. ሥልቶችና መርሆች

የፖሊሲው የማስፈጸሚያ ሥልቶች እንደዘርፉ ዓላማዎችና ግቦች የሚለያዩ ሲሆን፣ በተለይ

• የማዕድን ዘርፍ በኢትዮጵያ የልማት ሂደት ውስጥ የሚኖረውን ሚና በአግባቡ መለየት፣

• የአገሪቱን የማዕድን አቅምና አለኝታ በቅጡ መለየት፣ በዘመናዊ መረጃ ማጠናቀር፣

ረቂቅ የማዕድን ሀብት ልማት ፖሊሲ 10


• የማዕድን ዘርፍ ልማት ዕቅድና ስትራቴጂ ማውጣት፣

• ከዘላቂ ልማት ጋር የሚጣጣም የማዕድን ዘርፍ ልማትንና አጠቃቀምን ማበረታታትና ዕውን ማድረግ፣

• የማሕበረሰባዊ ተጠቃሚነትንና በዘርፉ የተሻለ ኢንቨስትመንት መሳብ፤ የሚያስችሉ የፊስካል መሣሪያዎችን ማስፈን፣

• ቀልጣፋ የማዕድን ዘርፍ አስተዳደር ማስፈን፣

• በመሠረተ ልማት የማዕድን ዘርፍ ልማት ኮሪዶር መፍጠር ዋና ዋና የማስፈጸሚያ ሥልቶች ናቸው።

ዘርፉን በማልማት ሂደት ለኢኮኖሚ ዕድገት ወሳኝ የሆኑና ከፍተኛ የፋይናንስና የቴክኖሎጂ አቅም የሚጠይቁ፣ ነገር ግን ዓለም

አቀፍ ኢንቨስትመንት መሳብ ያልቻሉ ዘርፎችን ለማልማት የአገሪቱን መልካም የፖለቲካ ካፒታል በመጠቀም ከሌሎች የልማት

አጋር አገሮች ጋር መተባበርን ማቀድ የሥለቱ አካል ነው።

የፖሊሲው ዋና መርሕ በዘርፉ የተወጠኑ ዕቅዶችን ዳር ለማድረስ የሚደረግ የፖሊሲ ቀጣይነትና ቁርጠኝነት ነው። የዚህ

መርህቁልፍ መነሻም በሀገሪቱ የሰለጠነ የሰው ኃይል እና ዘመናዊ ቴክኖሎጂ እምብዛም በሌለበት ሁኔታ በዓለም ኢኮኖሚ

ውስጥ ተወዳድሮ መትባት የሚችል የኢንዱስትሪ ልማት እውን ማድረግ የሚቻለው ቢያንስ የማዕድን ሀብትን የመሰሉ ወሳኝ

ጥሬ ዕቃዎችን በሀገር ውስጥ በማምረትና በመጠቀም የመሆኑ ጉዳይ ነው።

የማይጣረሱ ግቦችና ዓላማዎች፣ የዘርፉ ተዋንያንን ፍላጎቶች ግምት ውስጥ ማስገባት፣ ከአካባቢ ክብካቤና ጥበቃ ጋር

የተጣጣመ ዘላቂ የማዕድን ልማትን ማረጋገጥ፣ በተቀናጀ ልማት ግልጽ የማኅበረሰብ ተጠቃሚነት፣ እና የኮርፖሬት ማኅበራዊ

ኃላፊነቶች ተጨማሪ የፖሊሲው መርሆች ናቸው።

3.4.1. የማዕድን ዘርፍ ሚናን በአግባቡ መለየት

የማዕድን ዘርፍ ልማት በአንድ ሀገር የልማት ጥረት ውስጥ ሊኖረው የሚገባው ሚና በአግባቡ አለመመላከቱ በዘርፉ የሚደረጉ

ጥረቶችን በዘፈቀደ የሚመሩ በማድረግ ከዘርፉ ሊገኝ የሚችለውን ጥቅም ያሳጣል። የማዕድን ዘርፍ በታዳጊ ሀገሮች ሲሰጠው

ከነበረው ያልተገባ ሚናዊ ትርክት በመውጣት የዘርፉን ምትክ የሌለው ልማታዊ ሚና መለየት ከዘርፉ የሚገኘውን ሀገራዊ

ጥቅም በተገቢው ደረጃ ለማግኘት ያስችላል። የማዕድን ዘርፍ ሚና በአጠቃላይየኢኮኖሚ ዕድገትንና ዘላቂ ማኅበራዊ ለውጥን

ለማምጣት ዋና ግብዓትና አቅም መፍጠር ነው።

የማዕድን ዘርፍ ሚናን በአግባቡ ለማመላከት የመጀመሪያው ርምጃም የማዕድን ዓይነቶችን በአግባቡ መለየት ሲሆን እነዚህም፤

• የኢንዱስትሪ ማዕድናት፣
ረቂቅ የማዕድን ሀብት ልማት ፖሊሲ 11
• የግንባታ ግብአትና የገጥ/የማጋጌጫ (dimension stones) ማዕድናት፣

• የከበሩ፣ ቤዝ ሜታልና የብረት ነክ (ሜታል) ማዕድናት፣

• የነዳጅ/የኢነርጂ ማዕድናት፣

• የጂኦተርማል ኃይል፣ እና

• የጌጣጌጥ ማዕድናት ተብለው ሊመደቡ ይችላሉ።

ከዚህ አንጻር የሁሉም የአምራች ኢኮኖሚ ዘርፎች መነሻና ግብዓት ማዕድናት በመሆናቸው በኢኮኖሚ ዕድገት ጥረት ውስጥ

የሚኖራቸውን የማይተካ ሚና ማሳየት ተገቢ ነው። ከላይ የተጠቀሱት ዋና ዋና ግቦች የማዕድን ሚናን ያመላክታሉ።በተለይም

ለኢንዱስትሪና ለኮንስትራክሽን ግብዓትነት ለሚውሉ ማዕድናት የሚሰጠውን አነስተኛ ትኩረትና የተዛባ ዋጋ በማስተካከል

ለዘርፉ ልማት የተሻለ አቅጣጫ ማመላከት ይቻላል።

3.4.2. የአገሪቱን የማዕድን አቅም በቅጡ መለየት፣ በዘመናዊ መረጃ ማጠናቀር

ኢትዮጵያ በማዕድን ዘርፍ ያላትን ሀብት በቅጡ የመለየትና በዘመናዊ መረጃ የማጠናቀር የትኩረት አቅጣጫ የልማት

ስትራቴጂዎቿን ካላት ሀብት ጋር ማጣጣም መቻልን፣ ለአምራች ኢንዱስትሪ ልማትና ለግብርና ዝመና ትልሞች መሳካት

የግብዓት አቅሞችን ቀድሞ መለየትን፣ በማዕድን ዘርፍ ተወዳዳሪ ኢንዱስትሪ ለመገንባት አዋጭ መስኮች መለየትን፣ እና

በማዕድን ዘርፍ ልማት በሚደረግ ኢንቨስትመንት ተወዳዳሪነትን ለማጎልበት ቀልጣፋና ወጪ ቆጣቢ ሥርዓት መዘርጋትን

የመሳሰሉ ጉልህ ፋይዳዎችን ታሳቢ ያደርጋል።

3.4.3. የማዕድን ልማት ዕቅድና ስትራቴጂ ማውጣት

ሀገሪቱ ባላት የማዕድን ሀብት፣ ቅድሚያ በሚሰጣቸው የማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት መስኮች፣ እንዲሁም ማዕድናቱን

ለማልማት ባላት አቅም በመመሥረት በጊዜና በዘርፍ የተመላከተ ዕቅድና ስትራቴጂ ማውጣት ከማዕድን ዘርፍ ልማት ሊገኝ

የሚችለውን ጥቅም ያጎለብታል፤ የዘርፉን ተወዳዳሪነትም ይጨምራል።

ሀገሪቱ ያላት እና ሊኖራት የሚችለው የማዕድን ሀብት እስካሁን በተደረጉ ጥናቶች መሠረት የጂኦሎጂ ቅንብሮች የከበሩ፣

የኢንዱስትሪ፣ የግንባታ፣ የጌጣጌጥ ማዕድናትና የነዳጅ አለኝታ፣ በተወሰነ ደረጃ የብረት ማዕድን መሆናቸው ቢታወቅም፣

በዝርዝርና በተሻለ የአለኝታነት መጠን መጠናት ይኖርባቸዋል።

ረቂቅ የማዕድን ሀብት ልማት ፖሊሲ 12


የማዕድን ዘርፍ ኢንቨስትመንት እልህ አስጨራሽ፣ ውድና ስጋት የበዛበት በመሆኑ በተለይ በውጭ ሀገር ገበያ ተፈላጊነታቸው

ከተረጋገጡት ማዕድናት ውጪ ያሉ ለሀገር ውስጥ የግብዓት ፍላጎት ማሟያ የሚውሉ ማዕድናት ልማት የሌሎች ዘርፎችን

መዳበር ወይም የተረጋገጠ ፍላጎት መኖርን ይጠይቃል። ለዚህም በዘርፍ ተቋማት ትብብርና መናበብ ቅድሚያ የሚሰጣቸው

የልማት ዘርፎችና የማዕድን ግብዓት ፍላጎታቸው በአግባቡና በተመጠነ መልኩ ሊለዩ ይገባል።

በማዕድን ዘርፍ ልማት መመላከትና በሕግ መደገፍ ካለባቸው ጉዳዮች መካከል የዘርፉ የመሬት አጠቃቀም አንዱ ሲሆን፣

በማዕድን አለኝታ ዙሪያ የተሻለ መረጃ መኖር ለማዕድን ልማት በተከለሉ ቦታዎች ሌሎች የኢኮኖሚና ማኅበራዊ

እንቅስቃሴዎችን በመገደብ የሀብት ብክነትንና ግጭትን ለመቀነስ ያስችላል።

3.4.4. የአፈጻጸም ክትትል

በማዕድን ዘርፍ ልማት ውስጥ ወሳኝ ግቦች ከተለዩ በኋላ አፈጻጸማቸው በጊዜ ሠሌዳ መመላከት ይኖርበታል። በአጠቃላይም

የውጭ ምንዛሪ ማስገኘት፣ የኢንዱስትሪና የግብርና ዝመናን ማረጋገጥ፣ የማዕድን ሀብት ጥገኝነትን መቋቋም፣ የመጪው

ትውልድ ተጠቃሚነትና የማዕድን ፈንድ ጉዳዮች በአጭር፣ በመካከለኛና በረጂም ጊዜ ይመላከታሉ።

4. ትኩረት የሚሰጣቸው ዋና ዋና የፖሊሲ ጉዳዮች

ከላይ በስፋት እንደተገለጸው የማዕድን ልማት ዘርፉን በተገቢው መንገድ በማስተዳደር ለኢንዱስትሪ እድገት፣ ለግብርና

ዝመናና ከአገልግሎት ዘርፉ ጋር በማስተሳሰር የልማት አቀጣጣይ ግብአት እንዲሆን ማስቻል ዋናው የፖሊሲው ግብ ነው።

ይህንንም ለማሳካት ዘርፉ ከሌሎች ወሳኝ ከሆኑ የኢኮኖሚ ዘርፎች ጋር የሚተሳሰርባቸውን ሥልቶች በግልጽ በማስፈር

መዋቅራዊ ሽግግርና ሀገራዊ ልማት እንዲያመጣ ለማስቻል የፖሊሲ ዓላማዎችንና የማስፈጸሚያ ሥልቶችን መቀየስ በዋናነት

የዚህ ክፍል ዓላማ ነው። ከዚህ ዓላማ ጎን ለጎን ዘርፉ ለልማቱ አስፈላጊ የሆነውን የውጭ ምንዛሪ እንዲያስገኝ፣ የሥራ እድል

እንዲፈጥር፣ የሀገሪቱ ዜጎች ከልማቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል ግልጽ የፖሊሲ አቅጣጫዎችን እና ፖሊሲውም ተግባራዊ

የሚደረግባቸውን ሥልቶች መንደፍና በሥራ ላይ ማዋል አስፈላጊ ነው። ለዚህም በዋናነት ማዕድናቱ በፍለጋ፣ በምርመራ፣

በማልማትና በማምረት ሂደትና በአጠቃላይ በኢንቨስትመንት ፍላጎት የሚኖራቸውን ልዩነት ከግንዛቤ በማስገባት፣ ማዕድናቱን

በየባሕሪያቸው በንዑስ ዘርፎች በመለየት፤ እንደ ልዩ ባሕሪያቸው፣ ጥቅማቸው እና የአለኝታቸው አይነት፣ የሚያስፈልጋቸው

ትኩረት፣ ድጋፍ፣ ክትትልና አስፈላጊም ሲሆን የመንግሥት ተሳትፎ ተመላክቷል። ይህ ክፍል በየንዑስ ዘርፉ የሚታዩ

ችግሮችን፣ የፖሊሲ አቅጣጫ እና የፖሊሲ አፈጻጸም ስልቶች እንደሚከተለው ይቀይሳል፡፡

ረቂቅ የማዕድን ሀብት ልማት ፖሊሲ 13


4.1. የማዕድን ልማት ለኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ልማት

4.2. የከበሩ ብረት ነክ ማዕድናት፣ ቤዝ ሜታልና እና ብረት ነክ (ሜታሊክ) ማዕድናት

በከበሩና ቤዝ ሜታልና እንዲሁም በብረት ነክ ማዕድናት መስክ ሀገሪቱ ተስፋ ሰጭ ምልክቶች እንዳሏት የሚያሳዩ ጥናቶች

ቢኖሩም እስካሁን ከወርቅ በስተቀር በሌሎቹ ማዕድናት ይህ ነው በሚባል ደረጃ ሊለሙና ሊመረቱ የሚችሉ ክምችቶች

ስለመኖራቸው የተረጋገጠ ነገር የለም። ይህም በዚህ ረገድ ገና ሰፊ ሥራ መከናወን እንዳለበት የሚያመላክት ነው።

በዚህ ዘርፍ የሚመደቡ አብዛኛዎቹ ማዕድናት ከፍለጋ ጀምሮ ወደልማት እስኪገቡ ድረስ ከፍተኛ ወጪ፣ እውቀትና ልምድ፣

ለዘርፉ የሚያስፈልጉ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ድጋፎች፣ ጊዜ፣ ያለመታከትንና ዕድለኝነትን ይጠይቃሉ። ማዕድናቱ ኢኮኖሚያዊ

በሆነ ደረጃ ለምተው ሊመረቱ የሚችሉ መሆናቸው ተረጋግጦ ወደ ልማትና ምርት ቢሸጋገሩ እንኳን ለማጣራት፣ ለማበልጸግ፣

ለማቅለጥና ወደ ፋብሪካ ምርትነት እንዲለወጡ ለማዘጋጀት ከፍተኛ የቴክኒክ ችሎታና ብቃት፣ ኢንቨስትመንትና ቴክኖሎጂ

እንዲሁም ሌሎች በርካታ ምቹ ሁኔታዎች ይፈልጋሉ።

ስለዚህ በዚህ መስክ ሊኖር የሚገባው የፖሊሲ አቅጣጫ ማዕድናቱን ኢኮኖሚያዊ በሆነ ደረጃ ለማምረት በሚቻልበት መጠን

ፈልጎ ማግኘት፣ በአግባቡ እና በቀጣይነት ማምረት የሚቻልበትንና በአጭርና በመካከለኛ ጊዜ እንደ የውጭ ምንዛሪ ማግኛ

ዘዴ መጠቀም፣ በረጅም ጊዜ ደግሞ ማዕድናቱን የማበልጸግ፣ የማጣራት እንደሁኔታውም የማቅለጥ እንዲሁም የፋብሪካ

ውጤቶችን ለማምረት የሚያስችል አቅምን መገንባት ይሆናል።

4.2.1. የፖሊሲ ዓላማ

የከበሩ፣ ቤዝ ሜታልና እና ብረት ነክ ማዕድናትን በተመለከተ የፖሊሲው ዓላማ ማዕድናቱን በበቂ መጠን ማግኘት፣ ዘላቂ

በሆነ መንገድ ማልማት፣ ማምረት እና ለገበያ ማቅረብ መቻል፣ በሀገር ውስጥ በተቻለ መጠን መበልጸግ የሚችሉበትን ሁኔታ

ማመቻቸት፣ በረጅም ጊዜ ደግሞ እነዚህን ማዕድናት ማጣራትና ማቅለጥ ወደ ፋብሪካ ምርት መለወጥ (ፍብረካ) የሚያስችል

አቅም መገንባት ነው።

4.2.2. የማስፈጸሚያ ስልቶች፡-

• የጂኦሎጂ መረጃዎች በተሻለ ደረጃ፣ በጥራት እና በሥፋት የሚሰበሰቡበትን፣ የሚተነተኑበትን፣ በየጊዜው

የሚሻሻሉበትን እና የማዕድን ግኝቶችን ለማፋጠን በሚያስችል መልኩ ለተጠቃሚዎች በቀላሉ

የሚሰራጩበትን መንገድ ማመቻቸት፣

ረቂቅ የማዕድን ሀብት ልማት ፖሊሲ 14


• የግል ዘርፉ በሥፋት በማዕድናቱ ልማት እንዲሰማራ ያልተቋረጠ የማስተዋወቅ/ፕሮሞሽን ሥራ መሥራት፣

ለኢንቨስተሮች አስፈላጊውን ማበረታቻና ድጋፍ መስጠት፣

• የተመረቱ ማዕድናት ያለምንም ችግር ለሀገር ውስጥም ሆነ ለውጭ ሀገር ገበያ የሚቀርቡበትን ሥርዓት

መዘረጋት፣

• ማዕድናቱ ሲገኙና መመረት ሲጀምሩ፣ በሀገር ውስጥ የሚጣሩበትን እና የሚቀልጡበትን ለፍብረካ

የሚውሉበትን መንገድና ዘዴዎችን የሚያጠና የሀገር ውስጥ አቅም መገንባትና አስፈላጊ ሲሆንም በረጅም ጊዜ

በሥራ ላይ እንዲውሉ የሚያበረታታ አካል ማቋቋም፣ እና

• ማዕድናትን በሀገር ውስጥ ለሚያበለጽጉ ድርጅቶች ተገቢውን እገዛ፣ ድጋፍና ማበረታቻ መስጠት ናቸው።

4.3. የኢንዱስትሪ ማዕድናት

በሀገር ውስጥ የኢንዱስትሪ ልማት ለማምጣት ማዕድናት ያላቸው ሚና ከፍተኛ ነው። በተለይም ደግሞ የኢንዱስትሪ

ማዕድናትን ለሀገር ውስጥ የኢንዱስትሪ ግብአትነት እንዲውሉ በማድረግ የሀገር ውስጥ ኢንዱስትሪን ተወዳዳሪነት መጨመርና

ማረጋገጥ አስፈላጊ ነው። ማዕድናት ለሀገር ውስጥ ኢንዱስትሪ ግብአት እንዲሆኑ ከማስቻል ጎን ለጎን፣ በጥሬ እቃነት ለውጭ

ገበያ የሚፈለጉ የኢንዱስትሪ ማዕድናትን በአገር ውስጥ የማበልጸግ ሥራ መሥራት መቻል እሴት ስለሚጨምር ለኢኮኖሚው

ከፍተኛ ድጋፍ ይሆናል።

በርካታ የኢንዱስትሪ ማዕድናትን እንደግብአት በመጠቀም በሀገር ውስጥ የተለያዩ ኬሚካሎችን፣ መገልገያ ቁሳቁሶችን፣

ማዳበሪያ፣ እና በርካታ የኢንዱስትሪ ውጤቶችን በማምረት የዘርፎች ትስስርን ማጠናከር ይቻላል። ለዚህም ተገቢው የፖሊሲ

አቅጣጫ የኢንዱትሪ ማዕድናትን በልዩ ትኩረት ወደ ኢንዱስትሪ ግብአትነትና ወደ ተፈላጊ ቁሳቁሶች የሚለወጡበትን ሁኔታ

ማመቻቸት ይሆናል።

4.3.1. ዋና ዋና ችግሮች፡

• በኢንዱስትሪ ማዕድናት ላይ የተደረጉ ጥናቶች በበቂ ሁኔታ ያለመኖር፣

• የኢንዱስትሪ ማዕድናትን በግብአትነት መጠቀም የሚችሉ በቂ ኢንዱስትሪዎች ያለመኖራቸው፣ ያሉትም ቢሆኑ

በአብዛኛው ከውጭ በሚመጣ ግብአት ላይ የተመሰረቱ መሆናቸው፣

ረቂቅ የማዕድን ሀብት ልማት ፖሊሲ 15


• የኢንዱስትሪ ማዕድናት ለሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ እድገት ሊያበረክቱ ስለሚችሉት ጠቀሜታ በቂ

እውቀትና ግንዛቤ ያለመኖር ናቸው።

4.3.2. የፖሊሲ ዓላማ

የፖሊሲው ዋና ዓላማ የኢንዱስትሪ ማዕድናት ያለመታከት እንዲፈለጉ፣ ሲገኙም፣ እንዲለሙና ተመርተው በተመጣጣኝ ዋጋ

ለሀገር ውስጥ ፍብረካ በስፋት እንዲውሉ ማስቻል ነው።

4.3.3. የማስፈጸሚያ ስልቶች

• በኢንዱስትሪ ማዕድናት ላይ እስካሁን የተደረጉ ጥናቶችን በማጠናቀር ለሀገር ውስጥ ኢንዱስትሪዎች ሊውሉ

የሚችሉ የኢንዱስትሪ ማዕድናት ቆጠራ ማድረግና ሪፖርት ማዘጋጀት፣

• በቀጣይም ሀገሪቱ ያላትን የኢንዱስትሪ ማዕድናት እውቀትና መረጃ በየጊዜው ከፍ ለማድረግ ተከታታይ ጥናት

ማድረግና የመረጃ ቋቱን ማሳደግና ማሻሻል፣

• በጥናት ላይ የተመሰረቱ መረጃዎችን በመጠቀም የተለያዩ ለኢንዱስትሪ አገልግሎት የሚውሉ ማዕድናትን

እያጠናና እየለየ፣ እነዚህ ማዕድናት የት እንደሚገኙ፣ በምን አይነት የክምችት መጠን እንደሚገኙ፣ ለምን አይነት

ምርት/የፋብሪካ ግብአትነት ሊውሉ እንደሚችሉ፣ ማዕድናቱን ወደ ምርት ለመለወጥ የሚኖረውን ሂደት፣

የሚያስፈልገውን ኢንቨስትመንት፣ የገበያ ሁኔታ ሥራውን በትንሹ በመጀመር ቀስ በቀስ ማሳደግ የሚቻልበትን

ሁኔታ እያጠና ለሀገር ውስጥ አልሚዎች በሥራው ላይ እንዲሰማሩ የሚያስተዋውቅ፣ የሚያበረታታ እና

የሚደግፍ መንግሥታዊ አካል ማቋቋም።

• በሀገር ውስጥ የሚገኙ የኢንዱስትሪ ማዕድናትን በግብአትነት የሚጠቀሙ ኢንዱስትሪዎች እንዲስፋፉ

ማበረታታት እና ተገቢውን ድጋፍ ማድረግ፤ እና

• በኢኮኖሚ፣ በኢንዱስትሪና ግብርና ልማት መስክ የተሰማሩ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችን የግሉን የኢኮኖሚ

ዘርፍ በማስተባበር ማዕድናትን ለማበልጸግና ለሀገራዊ ኢንዱስትሪ ግብዓት ሊውሉ የሚችሉባቸውን ዘዴዎች

በሥራ ላይ ለማዋል ተባብረውና ተደጋግፈው የሚሰሩበት ሥርዓት መዘርጋት ናቸው።

ረቂቅ የማዕድን ሀብት ልማት ፖሊሲ 16


4.4. ማዕድናት እንደ ግብርና ግብአት፣

በኢትዮጵያ የግብርናውን ክፍለ ኢኮኖሚ ማዘመን የመዋቅራዊ ሽግግር ጥረት ወሳኝ አካል ነው። የግብርና ዝመና እውን

ከሚሆንባቸው ዋና ዋና ሥልቶች መካከለም በዘርፉ አጠቃላይ የማምረቻ አቅሞችን መገንባት፣ የውሃ ሀብትን

በማልማትየዘርፉን የዝናብ ጥገኝነት መቀነስ፣ የመሬትና የሠራተኛ ምርታማነትን መጨመር፣ ዘመናዊ፣ ዘላቂና ከአካባቢ ጥበቃ

ጋር የሚጣጣሙ ማዳበሪያዎችን የጸረ አረምና የጸረ ተባይ መድኃኒቶችን አጠቃቀም ማጎልበትና፣ ድህረ-ምርት ብክነትን

መቀነስ ተጠቃሽ ናቸው። በነዚህ የግብርና ዘርፍ ማዘመኛ ሥልቶች ውስጥ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ የማዕድናት

አስተዋጽኦ የላቀ ነው። የውሃ ሀብትን ለግብርና ዝመና በማዋል ሂደት ውስጥ ለመስኖ ሥራ የሚውሉ የግንባታ ግብዓቶች፣

ዘመናዊ የግብርና መሣሪያዎችን ለማምረት የሚያስፈልጉ የብረታ ብረት ግብዓቶች፣ የመሬት ምርታማነትን የሚጨምሩ

የግብርና ግብአቶች የሚገኙት ከማዕድናት ነው። የመዋቅራዊ ሽግግርና የዚሁ አካል የሆነው የግብርና ዝመና እየተፋጠነ ሲሄድ

አብዛኛዎቹን ተፈላጊ ማዕድናት በማልማት ጥቅም ላይ የማዋሉ ፍላጎት የሚፈጠር ሲሆን፣ በአጭርና በመካከለኛ ጊዜ ለግብርና

ግብዓት የሚሆኑ ማዕድናትን በማበልጸግ ለልማት ወሳኝ የሆኑ ግብዓቶችን በራስ አቅም የመተካትን ግብ ማሳካትና አገሪቱ

የምታወጣውን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪም ማዳን ይቻላል።

4.4.1. ዋና ዋና ችግሮች

• ለግብርና ግብአት ሊሆኑ በሚችሉ ማዕድናት ፍለጋ ምርመራ እና ማምረት ተግባር ላይ በቂ ትኩረት ተሰጥቶ

ያለመሠራቱ፣

• ከተወሰኑ ለግብርና ግብአት ሊሆኑ ከሚችሉ ማዕድናት በስተቀር ለግብርና ግብአት ሊሆኑ የሚችሉ ማዕድናት

በሥፋትስለመኖራቸው በበቂ ደረጃ ያለመረጋገጡ፣

• የግብርና ግብአት ሊሆኑ በሚችሉ ማዕድናት ላይ ትኩረት ሰጥቶ መዋዕለ ነዋይ ማፍሰስ የሚፈልግ የግል

ኢንቨስትመንት በበቂ መጠን ያለመኖር፣ እና

• የግብርና ግብአት ሊሆኑ የሚችሉ ማዕድናት በበቂ መጠን ቢገኙ እንኳን ወደ ማዳበሪያ ወይም ወደ ሌላ

የግብርና ግብአት ለመለወጥ የሚያስችል በቂ ዝግጅት ያለመኖሩ ናቸው።

ረቂቅ የማዕድን ሀብት ልማት ፖሊሲ 17


4.4.2. የፖሊሲ ዓላማ

• ለግብርና ግብአት ሊውሉ የሚችሉ ማዕድናትን አለኝታ በአግባቡ ማወቅና ወደ ልማት ሊሸጋገሩ በሚችሉበት

ደረጃ ማድረስ፣

• በሀገር ውስጥ የሚገኙ የግብርና ግብአት ማዕድናትን በመጠቀም የግብርና ግብአቶችን ማምረትና ለሀገር

ውስጥና ለውጭ ሀገር ገበያ ለማቅረብ የሚያስችል አቅም መገንባት።

4.4.3. የማስፈጸሚያ ሥልቶች

• መንግሥት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ የግብርና ግብአት ሊሆኑ የሚችሉ የማዕድናት አለኝታዎች ወደ ምርት ደረጃ

የሚሸጋገሩበትን እና አዳዲስ ክምችቶችም የሚገኙባቸውን ሁኔታዎች ለማመቻቸት፤በጀት ይመድባል፣ ትኩረት

ሰጥቶ ይሠራል፣

• ለግብርና ግብአት የሚሆኑ ማዕድናትን ለማግኘትና በኢኮኖሚያዊ ደረጃ ለማምረት የሚያስችሉ ጥናቶችን

ለማካሄድ መዋዕለ ነዋይ ለሚያፈሱ አልሚዎች (ኢንቨስተሮች) ድጋፍና ልዩ ማበረታቻ ይሰጣል፣

• በሀገር ውስጥ የሚገኙ ለግብርና ግብአት የሚሆኑ ማዕድናትን ተጠቅመው በሀገር ውስጥ የግብርና ግብአቶችን

ለማምረት ለሚፈልጉ አልሚዎች ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ይደግፋል፣ ያበረታታል፣

• የግል ባለሀብቶች በሀገር ውስጥ የግብርና ግብአቶችን እንዲያመርቱ ከመደገፍና ከማበረታታት ጎን ለጎን

መንግሥት በዚህ ዘርፍ የሚያየውን ክፍተት ለመሸፈን አስፈላጊውን የአቅም ግንባታ ሥራ ይሠራል፣

• መንግሥት በራስ አቅም ወይም ከግሉ ዘርፍ ጋር በጋራ በመሆን የሀገር ውስጥ ማዕድናትን ተጠቅሞ ለግብርናው

ዘርፍ አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶችን ለመፈብረክ አስፈላጊውን ያደርጋል።

4.5. የግንባታ/ኮንስትራክሽን እና የገጥ ማዕድናት

በሀገራችን ለኮስትራክሽን አገልግሎት ሊውሉ የሚችሉ ማዕድናት በስፋት እንደሚገኙ ይታወቃል። የኮንስትራክሽን እና የገጥ

ማዕድናት ከጥንት ጀምሮ ለግንባታና ለተለያዩ ግልጋሎቶች ጥቅም ላይ ሲውሉ የነበረ ሲሆን፣ በአሁኑ ጊዜም የአገሪቱን

ኢኮኖሚ ፍጥነት እየመራ በሚገኘውየኮንስትራክሽን ዘርፍበግብአትነት እየዋሉ ይገኛሉ። የኮንስትራክሽን ዘርፉ ከፍተኛ መጠን

ያለው ጥሬ ማዕድናትን በግብአትነት የሚጠቀም መሆኑ ቢታወቅም፣ ከውጭ አገር የሚገቡ በመካከለኛና ከፍተኛ ደረጃ እሴት

ረቂቅ የማዕድን ሀብት ልማት ፖሊሲ 18


የተጨመረባቸው ለግንባታዎች ማጠናቀቂያ (finishing) የሚውሉ የማዕድናት ውጤቶችን በሰፊው በመጠቀም ላይ

ይገኛል። ከኮንስትራክሽን ወጪዎች በንጽጽር ከውጭ ሀገር የሚገቡ ግብአቶች ድርሻ ከፍተኛ መሆኑ አገሪቷ ባሏት

የኮንስትራክሽንና የኢንዱስትሪ ማዕድናት ላይ እሴት በመጨመር እውን ለሚደረግ የዘርፎች ትስስር መዳበር ያላትን ከፍተኛ

አቅም ያሳያል።

የሀገር ውስጥ የኮንስትራክሽን ማዕድናትን በአግባቡና ዘላቂነት ባለው መንገድ መጠቀም የሀገርን ሀብት ለሀገር ኢኮኖሚያዊና

ማኅበራዊ እድገት በማዋል ራስን የመቻል ጥረት የሚያዳብር ከመሆኑም በላይ ሀገሪቱ ከውጭ ለምታስገባቸውየኮንስትራክሽን

ማዕድናት ተዋጽኦዎች የምታወጣውን ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ለሌላ የልማት ተግባራት እንድታውል እድል ይሰጣታል።

ለኮንስትራክሽን ዘርፍ በግብአትነት የሚያገለግሉ፣ ነገር ግን ማዕድን ስለመሆናቸው እንኳ በስፋት የማይታወቁ አሸዋ፣ ጠጠር፣

የተለያዩ አይነት ድንጋዮችንና መሰል የኮንስትራክሽን ማዕድናትን እንደ ትልቅ ሀብት በመቁጠር ለዘርፉ ወጥ የሆነ መልካም

አስተዳደርና የአጠቃቀም ሥርዓት ማስፈን የዘርፉን ልማት ለማፋጠን፣ የመሬት አጠቃቀምን ጨምሮ ተገቢ የአካባቢ ጥበቃ

ለማድረግ፣ ግጭቶችን ለመቀነስና መንግሥት ከዘርፉ በሚሰበስበው ገቢ የማኅበረሰብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ያግዛል።

4.5.1. ዋና ዋና ችግሮች

• አብዛኛዎቹን የኮንስትራክሽን ማዕድናት እንደ ማዕድን እስካለመቁጠር የሚደርስ የግንዛቤ ክፍተትና በዚህም

ምክንያት፣ ንዑስ ዘርፉ አናሳ ትኩረት የተሰጠው መሆኑ፣

• በሀገር ውስጥ በበቂ መጠንና ጥራት የኮንስትራክሽን ማዕድናትን በማውጣትና በማዘጋጀት ለኮንስትራክሽን

ዘርፉ አስፈላጊውን ግብአት ማቅረብ ያለመቻል፣ እና

• የገጥ (የማጋጌጫ) ድንጋዮችን (dimension stones) በአግባቡ አዘጋጅቶ በበቂ መጠንና ጥራት ለገበያ

ለማቅረብ ያለመቻል ናቸው።

4.5.2. የፖሊሲ ዓላማ

• የኮንስትራክሽንና የገጥ (የማጋጌጫ) ድንጋዮችን/ማዕድናትን (dimension stones) በተፈለገው መጠንና

ጥራት በዘላቂነት ማምረት፣ ማዘጋጀት እና ለሀገር ኢኖሚያዊና ማኅበራዊ ልማትጥቅም ላይ እንዲውሉ

ማስቻል።

ረቂቅ የማዕድን ሀብት ልማት ፖሊሲ 19


• ከሀገር ውስጥ ጥቅም ጎንለጎን፣ የገጥ (የማጋጌጫ) ድንጋዮችን በበቂ ጥራትና መጠን በማምረትና በማዘጋጀት

ለውጭ ገበያም በስፋት እንዲቀርቡ ማድረግ።

4.5.3. የማስፈጸሚያ ስልቶች

• ባለሀብቶች በኮንስትራክሽን እና በተለይም በገጥ (የማጋጌጫ) ድንጋዮች/ማዕድናት ልማትና አዘገጃጀት ሥራ

ላይ እንዲሰማሩ አስፈላጊውን ድጋፍና ማበረታቻ መስጠት፣

• የኮንስትራክሽን ማዕድናትን አጠቃቀም ለማሻሻል እንዲሁም አዳዲስ ዘዴዎችን በሥራ ላይ ለማዋል

የሚያስችሉ ጥናትና ምርምሮች እንዲስፋፉ መደገፍና ማበረታታት።

4.6. የጌጣጌጥ ድንጋዮች/ማዕድናት

በኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች የጌጣጌጥ ድንጋዮች/ማዕድናት አለኝታዎች መኖራቸው ይታወቃል። የጌጣጌጥ

ድንጋይ/ማዕድናት የዘመኑ የጥራት ደረጃ በሚጠይቀው መጠን በሀገር ውስጥ በአግባቡ ተቆርጠውና ተውበው/ተሠንየው

(ተዘጋጅተው) የተለያዩ ጌጣጌጦች ቢሰራባቸው በጥሬው ወደ ውጭ ከሚላኩት ድንጋዮች የተሻለና ከፍያለ ዋጋ ሊያስገኙ

ይችላሉ። ከፍተኛ ቁጥር ላለው የሰው ኃይልም የሥራ እድል ይፈጥራሉ። በዚህ ንዑስ-ዘርፍ ሊኖር የሚችለውን የእጅ-ጥበብ፣

እየተዳከመ ከመጣው የወርቅና የብር ጌጣጌጥ ሥራ ጋር በማያያዝ ለረጅም ዘመን የኖረውን የጌጣጌጥ ሥራ ታሪካዊና ባህላዊ

ቅርስ እንዲያንሰራራ በማድረግ፣ ለወደፊቱ ትውልድ እንዲተላለፍ ከማድረግም በላይ ለሀገሪቱ ከፍተኛ ጥቅም ማስገኘት

ይቻላል። ሀገራችን ከፍተኛና ወደፊት በሰፊው ሊለማ የሚችል የቱሪዝም ሀብት ያላት በመሆኑ፣ እነዚህን የጌጣጌጥ የእጅ-

ጥበብ ሥራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ በማድረግ፣ የሀገር ውስጥ የጌጣጌጥ ገበያው ከቱሪዝም ልማቱ ጋር በመደጋገፍ

ከፍተኛ ጥቅም እንዲያስገኙ መሥራት አስፈላጊ ነው።

4.6.1. ዋና ዋና ችግሮች

• ንዑስ ዘርፉ የተበታተነና በቂ ትኩረት የተሰጠው ያለመሆኑ፣

• በሕጋዊ መንገድ ከሚመረተው ያልተናነሰ የሥውር ገበያ መኖሩ፣

• በንዑስ ዘርፉ በቂ ስልጠናና የሰው ኃይል ልማት ያለመሠራቱ፣ በተለይም ድንጋዮቹን የመቁረጥና

የማስዋብ/የማሠነይ ሥልጠና የሚሰጥ አካል በሀገር ውስጥ ያለመኖሩ፣ ቢኖርም ደካማ መሆኑ፣

ረቂቅ የማዕድን ሀብት ልማት ፖሊሲ 20


• የወርቅና የብር ጌጣጌጥ ሥራ ጥበብ እየተዳከመ መሄዱ፣ እና

• የአመራረት ዘዴ ጉድለት በመኖሩ የሚመረቱ ድንጋዮች ጉዳት የሚደርስባቸው መሆኑ ነው።

4.6.2. የፖሊሲ ዓላማ

• የጌጣጌጥ ድንጋዮች/ማዕድናትን ፍለጋና ምርመራ ሥራ በማስፋፋት ምርቱን ማሳደግ፣ የድንጋዮቹን ዕሴት

የመጨመር እና ጌጣጌጦችን የመሥራት ክሕሎትን በማሳደግ ንዑስ ዘርፉ ለሀገር ልማት የሚያበረክተውን

አስተዋጽኦ ከፍ ማድረግ።

4.6.3. የማሰፈጸሚያ ሥልት

• የጌጣጌጥ ድንጋዮች/ማዕድናት ፍለጋ፣ ምርመራና የማምረት ሥራዎችን መደገፍና ማበረታታት፣

• ለንዑስ ዘርፉ ልዩ ትኩረት በመስጠት በሀገር ውስጥ ዕሴት የመጨመር ሥራን ማስፋፋት፣

• በሀገር ውስጥ ዕሴት ከመጨመር ጎን ለጎን፣ በጥሬው ወደውጭ የሚላከውን የጌጣጌጥ ድንጋይ/ማዕድን መጠንና

ጥራት መጨመር፣

• ለንዑስ ዘርፉ ልማት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ የሚሠራ አካል ማደራጀት፣

• የጌጣጌጥ ድንጋዮችን የመቁረጥ፣ የማስዋብ/የማሠነይ እና ጌጣጌጥ የመሥራት ሞያ የሚያሰለጥን አካል

ማቋቋም፣ እና

• በሀገር ውስጥ ከከበሩና በከፊል ከከበሩ ድንጋዮች ጋር ወርቅንና ወይም ብርን በመጨመር ጌጣጌጥ ለሚሰሩ

ዕደጠቢባንና ድርጅቶች ተገቢውን ድጋፍና ማበረታቻ መስጠት ናቸው።

4.7. ስለባህላዊ የማዕድን ሥራዎች

በሀገራችን የተለያዩ ክፍሎች በርካታ ቁጥር ያላቸው የባህል ማዕድን አምራቾች ከፍተኛ መጠን ያለው ወርቅ ያመርታሉ። ይህ

ምርት ለሀገር ልማት ማስፈጸሚያ እንደ አንድ የውጭ ምንዛሪ ምንጭ የሚቆጠር ነው።

ሆኖም ግን ከሚመረተው ወርቅ ውስጥ ከፍተኛ መጠን ያለው ወርቅ ወደ ውጭ በኮንትሮባንድ መልክ ይወጣል። ከዚህ ንግድ

ጋር በተያያዘም ከሕግ ያፈነገጡ የተደራጁ ቡድኖች እየተፈጠሩ ነው። በአንዳንድ አጋጣሚዎችም ባህላዊ አምራቾች የሕጋዊ

ባለፈቃዶችን ይዞታ የሚጋፉበት፣ ለምርት ያዘጋጁትን ወርቅ አዘል ድንጋይና አፈር የሚነጥቁባቸው ሁኔታዎችም ይታያሉ።
ረቂቅ የማዕድን ሀብት ልማት ፖሊሲ 21
በአካባቢ ላይ የሚደርሰውም ጉዳት በቀላሉ የሚገመት አይደለም፡፡ በአንጻሩም፣ ዘርፉ በአግባቡ ከተያዘና አስፈላጊው ድጋፍ፣

ክትትልና ቁጥጥር ከተደረገበት ከሚያስገኘው የውጭ ምንዛሪ ባልተናነሰ ከፍተኛ ቁጥር ላላቸው ዜጎች የሥራ ዕድል

የሚፈጥርና ወደ አነስተኛና መካከለኛ የማዕድን ሥራ የማደግ ዕድሉም ከፍተኛ ነው።

4.7.1. ዋና ዋና ችግሮች

• በኮንትሮባንድ የወርቅ ንግድ ላይ የተሰማሩ ሰዎችና ቡድኖች መበራከት፣

• ሕጋዊ የማዕድን ማምረት ወይም የፍለጋ ሥራ ከሚያካሂዱ ባለፈቃዶች ጋር አላስፈላጊና ተገቢ ያልሆነ

ውድድርና የይዞታ መጋፋት፣

• በንዑስ ዘርፉ የተሰማራው ከፍተኛ ቁጥር ያለው የሰው ኃይል በጣም በስፋት የደን ምንጠራና ቁፋሮ

ስለሚያካሂድ በአካባቢ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰ መሆኑ፣

• ወርቁን ከሌላ አካል ለመለየት እንደ መርኩሪ ያለ ኬሚካል ጥቅም ላይ የማዋል አሠራሮች እየተለመዱ

መምጣታቸውና ይህም በአካባቢ፣ በሰውና በእንስሳት ላይ ሊደርስ የሚችለውን ጉዳት እያሰፋ መሆኑ፣ እና

• ኋላቀር በሆነው የአመራረት ዘዴ ምክንያት ከሚሰበሰበው ወርቅ በላይ ሳይሰበሰብ የሚቀረው ወርቅ የሚበልጥ

መሆኑ ነው።

4.7.2. የፖሊሲ ዓላማ

የባህላዊ የማዕድን አምራቾች በአግባቡ ተደራጅተው፣ ተገቢው ስልጠናና እገዛ እየተደረገላቸው ሥራቸውን ዘላቂ ልማትን

ሊያግዝ በሚችል መልክ እንዲሠሩና ቀስ በቀስም ወደ አነስተኛና መካከለኛ ደረጃ የማዕድን አምራች ድርጅቶች እንዲለወጡና

እንዲያድጉ ማድረግ።

4.7.2.1. የማስፈጸሚያ ሥልቶች

• የክልል የማዕድን አስተዳደር አካላት በአግባቡ እንዲጠናከሩ ተገቢውን ድጋፍ ማድረግ።

• በባህላዊ የማዕድን ማምረት ሥራ ላይ የተሰማሩ ሰዎችን የሚደግፍ፣ የሚያደራጅ፣ ሥልጠና የሚሰጥ

ሥራቸውንም የሚከታተልና የሚቆጣጠር የኤክስቴንሽን ተቋም ማደራጀት።

ረቂቅ የማዕድን ሀብት ልማት ፖሊሲ 22


• የፌደራልና የክልል የማዕድን አስተዳደር አካላት በመተባበርና በመቀናጀት ከባህል የማዕድን አልሚዎች

የኤክስቴንሽን ተቋም ጋር በቅርበት በመሥራት በባህል አምራቾች ንዑስ ዘርፍ የሚታዩትን ችግሮች

ለማስወገድና ንዑስ ዘርፉ ለዘላቂ ልማት አስተዋጽኦ እንዲያደርግ የሚያግዝ ሥርዓት መዘርጋት።

• የባህል የማዕድን ሥራዎች ወደ አነስተኛና/ወይም መካከለኛ ደረጃ የማዕድን ሥራዎች ከፍ እንዲሉ

የሚቻልበትን ሁኔታ መፈለግ፣ ማመቻቸት፣ ማበረታታትና እገዛ ማድረግ።

• የባህላዊ የማዕድን ሥራዎች የሚካሄዱባቸውን አካባቢዎች ሰትራቴጂክ የአካባቢና የማኅበራዊ ተጽእኖ/ጉዳት

ግምገማ እንዲሠራ ማድረግና በዚሁ ላይ ተመስርቶ የአካባቢና የማበኅበራዊ ማናጅመንት እቅድ ማዘጋጀት።

• የባህላዊ የማዕድን ማምረት ሥራዎች የሚካሄዱባቸውን አካባቢዎች ሰትራቴጂክ የአካባቢና የማኅበራዊ

ተጽእኖ/ጉዳት ግምገማ ጥናት ሥራዎችን የአካባቢና ማኅበራዊ ማናጅመንት እቅዶችን በአግባቡ

የሚያስፈጽም፣ የሚሠራ፣ የሚከታተልና የሚቆጣጠር እንዲሁም ቀደም ሲል የደረሱ ጉዳቶችን እያጠና

እንዲታከሙ የሚያደርግ፣ ለዚሁ ዓላማ ብቻ የሚሠራ ተቋም ማደራጀት።

• የባህላዊ የማዕድን አምራቾች ለአካባቢ እና ማኅበራዊ ጉዳት ማቃለያ፣ መልሶ ማልሚያ ለዘላቂ ማኅበራዊ

እድገትና አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማትን ለማደራጀት ከሚያገኙት ገቢ በትንሹ እንዲያዋጡ ማድረግ።

• በቂ የኤክስቴንሽን ሠራተኞች ማሰልጠን የሚያስችል ሥርዓት መዘርጋት።

• በባህል የማዕድን አምራቾች የሚመረቱ ማዕድናት ሳይባክኑ የሚመረቱበትን ዘዴ በሥራ ላይ እንዲውል

ማድረግ።

• በባህል አምራቾች የሚመረተው የማዕድን ምርት ለገበያ በተቀላጠፈና በአስተማማኝ ሁኔታ እንዲቀርብ

የሚያስችል ሥርዓት መዘርጋት፡፡

• ምርቶቹ በሕገወጥ መንገድ ከሀገር የሚወጡበትን መንገድ በመቆጣጠርና የተሻለ የግዥ ሥርዓት በመዘርጋት

እንዲቆም ማድረግ። እና

ረቂቅ የማዕድን ሀብት ልማት ፖሊሲ 23


• ባህላዊ የማዕድን ሥራዎች በሚካሄዱባቸው አካባቢዎች አማራጭ ኢኮኖሚያዊ ተግባራት እንዲፈጠሩ

በመርዳት በመስኩ የተሰማሩ ሰዎች ሥራው ሲያበቃ ወይም ሥራቸውን መለወጥ ሲፈልጉ ሊሰማሩ

የሚችሉበት የሥራ እድል ማመቻቸት።

4.8. ስለአካባቢ ጥበቃ፣ ማኅበራዊ ጉዳዮችና ዘላቂ ልማት

4.8.1. ስለአካባቢ ጥበቃ

4.7.1.1 የፖሊሲ ዓላማ

የኢትዮጵያ የማዕድን ሀብት ልማት በዘላቂ የልማት መርሆዎች እና አግባብ ባለው የአካባቢ ጥበቃ መርሖዎች፣ ሥርዓቶች እና

ደረጃዎች መሰረት እንዲካሄድ ይደረጋል።

4.7.1.2 የማስፈጸሚያ ሥልት

• ማንኛውም የማዕድን ልማት ሥራ ከምርመራ ጀምሮ ልማት፣ ማምረትና መዝጋት ድረስ ተገቢና ደረጃውን

የጠበቀ የአካባቢ እና የማኅበራዊ ተጽእኖ ግምገማ ሥርዓቶችን እንዲያልፍ ይደረጋል።

• ማንኛውም የአካባቢና የማኅበራዊ ተጽእኖ ግምገማ ይህንኑ በግምገማው ላይ የተመለከተውን ተጽእኖ

ለማስወገድ፣ ለማቃለል፣ መልሶ ለማቅናትና ለማልማት እንዲሁም ወደፊት ሊደርስ የሚችለውን

ማናቸውንም ጉዳት ለመከታተል፤ ለመቀነስና ለማስወገድ የሚያስችል የአካባቢና የማኅበራዊ ማናጅመንት

እቅድ እንዲኖረው ይደረጋል።

• የአካባቢ እና የማኅበራዊ ጥበቃ ማናጅመንት እቅዶችን የሚገመግም፣ የሚያጸድቅና በሥራ ላይ መዋላቸውን

የሚከታተልና የሚያስፈጽም አካል በተሟላ ሁኔታ እንዲደራጅና እንዲጠናከር ይደረጋል።

• ለአካባቢ እና ማኅበራዊ ተጽእኖ ግምገማ፣ የአካባቢ እና የማኅበራዊ ጥበቃ ማናጅመንት እቅዶችን አዘገጃጀት፣

ግምገማና አፈጻጸም ሞያ በቂ እውቀትና ችሎታ ያላቸውን ባለሙያዎች የማሰልጠን ሥራ በቀጣይነት

ተጠናክሮ እንዲካሄድ ሥርዓት ይዘረጋል።

• ከማዕድኑ ኢንዱስትሪ የሚወጣውን የቆሻሻ መጠን የመቀነስ፣ ወደ ጠቃሚ ምርት የመለወጥና መልሶ

የመጠቀም አሠራር እንዲስፋፋ የሚያስችል ጥናትና ምርምሮችን የሚያበረታታና በሥራ ላይ እንዲውሉ

የሚያስችል ሥርዓት ይዘረጋል።

ረቂቅ የማዕድን ሀብት ልማት ፖሊሲ 24


4.8.2. የማዕድን ልማት ለዘላቂ ማኅበራዊ ልማት

4.8.2.1. የፖሊሲ ዓላማ

በዚህ ጉዳይ ዙሪይ የፖሊሲው ዋና ዓላማ የማዕድን ልማት ሥራዎች ከሠራተኞቻቸው እና ከአካባቢው ኅብረተሰብ ጋር

መልካም ግንኙነት ያላቸው፣ ከአካባቢው እድገት እና ልማት ጋር ዘላቂ መተሳሰር የፈጠሩ የኅብረተሰቡ አካል እንዲሆኑ፣ እና

የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ እንዲሆኑ ማስቻል ነው።

4.8.2.2. የማስፈጸሚያ ሥልቶች

• የማዕድን አምራቾች የማዕድን ሥራ ለሚያካሂዱበት አካባቢ ልማት የሚውል ገንዘብ የሚመድቡበት እና

የተመደበው ገንዘብ በተገቢው መንገድ ለአካበቢው ልማት እንዲውል የሚያስችል ሥልት ይዘረጋል።

• መንግሥት ከማዕድን ልማት በተለያዩ የአስተዳደር እርከኖች በሮያሊቲ፣ በገቢና ትርፍ ግብር፣ እንዲሁም

የመሬት መጠቀሚያኪራይ መልክ የሚሰበስበውንገንዝብ ለማሕበረሰቡ ግልጽ በማድረግ የማዕድን ልማት

ለሚካሄድባቸው አካባቢዎች ማኅበራዊ ልማት የተለየ ድጋፍ ይደረጋል።

• የማዕድን አልሚዎችና አምራቾች ከአካባቢው ነዋሪ ጋር የሰመረ ግንኙት እንዲኖራቸው የሚያስችል

ተከታታይ እና ዘላቂ የሆነ የምክክር ሥርዓት ይዘረጋል።

• መንግሥት የማዕድን ልማት ከሚካሄድበት አካባቢ ከማዕድን ልማቱ የሚያገኘውን ገቢ በከፊል በመጠቀም

ቢቻል ማዕድኑን እንደ ግብአት የሚጠቀሙ ፋብሪካዎችን ማቋቋም የሚያስችል ሁኔታ ወይም በአማራጩ

ሌሎች ወደፊት የማዕድን ሥራው ቢያልቅ ያለማቋረጥ ሊቀጥሉ የሚችሉ ፋብሪካዎችን/ኢንዱስትሪዎችን

እንዲስፋፉ የሚያስችል ሌሎች የሥራ መስኮች እንዲፈጠሩ ያመመቻቻል።

• ከማዕድን ዘርፉ ገቢ የተወሰነውን እጅ በመቀነስ በዘላቂነት የሚሠራ፣ ለወደፊቱ ትውልድ ጥቅም የሚውል

ብሔራዊ የገንዘብ ቁጠባ ቋት ይቋቋማል።

ረቂቅ የማዕድን ሀብት ልማት ፖሊሲ 25


4.9. የማዕድን ኢንቨስትመንትና ገበያ

4.9.1. የማዕድን ኢንቨስትመንት

ለኢኮኖሚው ወሳኝ ሚና የሚጫወቱ የማዕድን ዓይነቶችና አጠቃላይ የዘርፉ ቁልፍ የልማት አቅጣጫ ከተመላከተ በኋላ

ትኩረት የሚጠይቀው ጉዳይ ኢንቨስትመንት ነው። የኢትዮጵያ የማዕድን ኢንቨስትመንት ፖሊሲ ከአጠቃላይ የማዕድን ልማት

ፖሊሲ የሚመነጭና የዘርፉን ልዩ ባሕሪይ ከግምት ያስገባ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ አጠቃላይ አቅጣጫው ከሀገሪቱ

የኢንቨስትመንት ፖሊሲ ጋር የተጣጣመ ይሆናል። የኢትዮጵያ የማዕድን ልማት ፖሊሲ የአገሪቱን የመዋቅራዊ ሽግግር

በሚያፋጥን መልኩ የተቃኘ በመሆኑ በዘርፉ የሚደረገው ኢንቨስትመንትም ከዚህ ጋር የተጣጣመ ይሆናል።

ኢትዮጵያ ኢንዱስትሪያላዊነትን መሠረት ያደረገ የመዋቅራዊ ሽግግር እንዲሰፍን በተለይም የአምራች ኢንዱስትሪ እና የግብርና

ዝመና ሂደቶች እንዲፋጠኑ የማዕድን ሀብት ወሳኝ ሚና አላቸው። በሀገር ውስጥ መኖራቸው የተረጋገጠ ለልማት አጋዥ የሆኑ

ማዕድናት በልማት ውስጥ በሚኖራቸው የተፈላጊነት ደረጃ በሀገር ውስጥ ባለሀብቶች፣ በውጭ ባለሀብቶች፣ በመንግሥት፣

በመንግሥትና በባለሀብቶች ሽርክና ሊለሙ ይችላሉ። የማዕድናት ቁልፈ ሚናም ለአምራች ኢንዱስትሪ ልማት፣ ለግብርና

ዝመና፣ ለአጠቃላይ የዘርፎች ትስስር፣ እንዲሁም የውጭ ምንዛሪ ለማስገኘት ባላቸው አስተዋፅኦ ይወሰናል።

የዘርፉ ኢንቨስትመንት በውጭ ሀገር ኩባንያዎች ፍላጎት፣ በአገር ውስጥ ባለሀብቶች ፍላጎትና አቅም፣ እንዲሁም በመንግሥት

አቅም ይወሰናል። የመንግሥትና የአገር ውስጥ ባለሀብቶች አቅምም በፋይናንስ፣ በሰው ኃይልና በቴክኖሎጂ ደረጃ ይገለጻል።

ከዚህ አንጻር ከፍተኛ የቴክኖሎጂ ልምድና የፋይናንስ አቅሞችን የሚጠይቁትንና በውጭ ኩባንያዎች የማልማት ፍላጎት ውስጥ

የገቡትን የማዕድን ዓይነቶች የዓለም አቀፍ አልሚዎች እንዲሳተፉባቸው ማበረታታት ይገባል። ለኢኮኖሚ ዕድገት ወሳኝ

የሆኑና በሀገር ውስጥ አቅም ሊለሙ በሚችሉ የማዕድን ዓይነቶች የአገር ውስጥ የግሉ ዘርፍ፣ እና መንግሥት በተናጠልና

በሽርክና ሊያለሟቸው ይችላሉ። ለኢኮኖሚ ዕድገትና ለታቀደው የመዋቅራዊ ሽግግር ዳር መድረስ ምትክ የሌላቸው፣ ከፍተኛ

የፋይናንስና የቴክኖሎጂ አቅም የሚጠይቁ፣ ነገር ግን ዓለም አቀፍ ኢንቨስትመንት መሳብ ያልቻሉ ማዕድናትን በመንግሥትና

በግሉ ዘርፍ ልዩ ትብብርና ጥረት እንዲሁም ከልማት አጋር ሀገሮች ጋር በመተባበር ማልማት ሊታሰብ ይችላል።

4.9.1.1. የፖሊሲ ዓላማ

በማዕድኑ ዘርፍ በቂ ኢንቨስትመንት ለመሳብ ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንድትሆን የሚያስችሉ ሥርዓቶችን

እና ዘዴዎችን በሥራ ላይ ማዋል።

ረቂቅ የማዕድን ሀብት ልማት ፖሊሲ 26


4.9.1.2. ማስፈጸሚያ ሥልቶች

• የኢንቨስትመንት ማነቆ የሆኑ ሕጎችን፣ ደንቦችን፣ መመሪያዎችን፣አሰራሮችን መለየት ናማሻሻል፣

• የውጭም ሆነ የሀገር ውስጥ ባለሀብቶች በማዕድን ልማቱ ዘርፍ በስፋት እንዲሰማሩ ተገቢውን ድጋፍና

ማበረታቻ መስጠት፣

• የፈቃድ አሰጣጥ ሥርዓቱን ማቀላጠፍ፣ በዋናነት ፈቃዶችን በአመጣጥ ቅደም ተከተሎቻቸው መመዝገብና

ማስተናገድ፣ በቂ ምክንያት ሲኖርና በጣም በተወሰነ ሁኔታ ፈቃዶችን በጨረታም ሆነ በሌላ ዘዴ

በማወዳደር የሚሰጥበት ሥርዓት መዘረጋት።

• ከማዕድን ሥራ ጋር የተያያዙና የተገናኙ አገልግሎቶችንና መሰረተልማቶችን የሚያቀርቡ የመንግሥት

መሥሪያ ቤቶች ተቀናጅተው የሚሰሩበትን ሥርዓት መዘርጋት።

• በማዕድን ሥራ አስተዳደር፣ክትትልና ቁጥጥር እና የተያያዙ ሥራዎች የተመደቡ ባለሞያዎች በቂ ቁጥርና

ስብጥር እንዲኖራቸው ማድረግ፣ አስፈላጊው ሥልጠና ልምድ እንዲኖራቸውና በያዙትሥራ ላይም

በፍቃዳቸው እንዲቆዩ የሚያስችል ሥርዓት መዘርጋት።

• ኢትዮጵያውያን ባለሀብቶች በቀጥታም ሆነ ከውጭ ባለሀብቶች ጋር በመቀናጀት በሀገሪቱ የማዕድን ሀብት

ልማት ላይ የሚሳተፉበትን መንገድ ማመቻቸት።

• የባንክ አሰራሮችና የውጭ ምንዛሪ ሕጎች፣ ደንቦችና መመሪያዎች የማዕድን ዘርፉን ልማት ሊያፋጥኑ

በሚችሉበት መልክ ማስተካከል።

• የማዕድን ዘርፉን የግብር ሥርዓት ኢንቨስትመንት ለመሳብ የሚያስችል የተረጋጋ፣ግልጽነት ያለው፣ በጋራ

ተጠቃሚነት መርህ ላይ የተመሰረተና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆነ የግብር ሥርዓት እንዲሆን

ማድረግ።

4.9.2. የማዕድን ገበያ

ለመዋቅራዊ ሽግግር በሚተጋ ሀገር ዋነኛው የማዕድን ዘርፍ ገበያ የሀገር ውስጥ የኢንዱስትሪ ልማት፣ የግብርና ዝመና ፍላጎቶች

ናቸው። እነዚህ ፍላጎቶች የሚዳብሩት በረጅም ጊዜ በመሆኑ የማዕድን ዘርፍ የአጭር ጊዜ ገበያ የውጭ አገር ገበያ ሲሆን ከዚህ

ጥረት ጎን ለጎን ለሀገር ውስጥ የልማት ፍላጎት የሚውሉ ማዕድናትን ማልማት አስፈላጊ ነው። ኢትዮጵያ በዘመናዊም ሆነ

ረቂቅ የማዕድን ሀብት ልማት ፖሊሲ 27


በባህላዊ መንገድ ለዘመናት በምታለማው የወርቅ ማዕድን ዙሪያ ከውጭ ገበያዎች በተጨማሪ ወርቅን ከጌጥነት ባለፈ አንድ

ትልቅ የሀብት መያዥያ መሆኑን በማጉላትና ለዚህም የብሔራዊ ባንክን ጨምሮ በአገሪቱ ያሉ የፋይናንስ ተቋማት የተሻለ

ዕውቅና እንዲሰጡ በማድረግ ለዘርፉ የተሻለ ገበያ መፍጠር ይቻላል።

4.9.2.1. የፖሊሲው ዓላማ

የፖሊሲው ዋና ዓላማ ለከበሩና፣ ሀገሪቷ ለሀገር ውስጥ ኢንዱስትሪዎች በግብአትነት ለማትፈልጋቸው ወይም ትርፍ ማዕድናት

አስተማማኝ ዓለም አቀፍ ገበያ ከማፈላለግ ጎን ለጎን የኢትዮጵያን የማዕድን ሀብት በአግባቡ ተጠቅሞ ለኢኮኖሚው እመርታን

የሚጨምር የሀገር ውስጥ ገበያ መፍጠር ነው።

4.9.2.2. የማስፈጸሚያ ሥልቶች

• ዘመናዊ የማስታወቂያ ሥርዓት እንዲገነባ ማገዝ፣

• ዓለም አቀፍ የመረጃ ሥርዓትና የደንበኛ ትስስር መፍጠር፣

• ማዕድናትንና የማዕድን ውጤቶችን የሚጠቀሙ ኢንዱስትሪዎችን እና የማዕድን ዘርፍ አልሚዎችን ትብብር

በማጎልበት የማዕድን ግብአቶችን በአስተማማኝነትና በዘላቂነት ለማቅረብ እንዲቻል ማድረግ፣

• የማዕድናትንና የማዕድን ውጤቶችን ጥራት ለመጠበቅ፣ የማዕድን ገበያን ለማዘመን ዘርፉን በጥናትና ምርምር

ማገዝ።

4.10. ተወዳዳሪ የማዕድን ዘርፍ ስለመፍጠር

ተወዳዳሪ የማዕድን ዘርፍ መፈጠር በዚህ የፖሊሲ ሰነድ ውስጥ የተመለከቱት ዝርዝር የፖሊሲ ዓላማዎች በተሳካ ሁኔታ ወደ

ተግባር የመለወጣቸው ድምር ውጤት ነው። ስለሆነም ተወዳዳሪነት ብቻውን ተነጥሎ መታየት አይገባውም። ይህ አስተሳሰብ

እንደተጠበቀ ሆኖ፣ በዚህ ክፍል ውስጥ በሌሎች ምዕራፎች ባልተጠቀሱ ዓላማዎችና ሥልቶች ላይ ትኩረት ይደረጋል።

4.10.1. የፖሊሲ ዓላማዎች

የሀገራችን የማዕድን ልማት ዘርፍ ከዓለም አቀፉ የማዕድን ልማት እንቅስቃሴ ጋር የተጣጣመ፣ተወዳዳሪና በቂ ኢንቨስትመንት

መሳብ የሚችል እና ለሀገር ዘላቂ ልማት ተገቢውን አስተዋጽኦ የሚያበረክት ጠንካራ ዘርፍ እንዲሆን ማስቻል።

ረቂቅ የማዕድን ሀብት ልማት ፖሊሲ 28


4.10.2. የአፈጻጸም ሥልቶች

• ለሀገሪቱ ሥነምድር ጥናትና ምርምር፣ ለማዕድን ልማት ፍላጎትና አስተዳደር አግባብ ያለውና ብቃት ያላቸው

ባለሞያዎችና ቴክኒሽያኖችን ማሰልጠን የሚቻልበት ሥርዓት ይዘረጋል።

• ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በማዕድን ሀብት ልማት የተለያዩ ዘርፎችና የሥነምድር ጥናትና ምርምር

እንዲዳብርና እንዲስፋፋ ማድረግ እንዲችሉ አስፈላጊው ድጋፍ እና እገዛ ይደረግላቸዋል።

• የቴክኖሎጂ ሽግግርንና የሰው ኃይል ልማትን ለማስፋፋት በመንግሥት፣ በማዕድን ኢንዱስትሪውና በከፍተኛ

ትምህርት ተቋማት መካከል የሚገኙ የተለያዩ መገልገያዎችን በጋራ የመጠቀምና የጋራ የምርምር ሥራዎችን

ለማካሄድ የሚያስችል የትብብር ሥርዓት ይዘረጋል።

• የማዕድን ምርመራ፣ ማምረት፣ የማዘጋጀት (ፕሮሰስ የማድረግ)፣ ግብይት፣ ፍብረካን እና የአካባቢ ጥበቃን

የሚደግፉ በተገልጋዮችና በባለድርሻዎች ፍላጎት ላይ የተመሰረቱ የጥናትና የምርምር ተቋሞች ይደራጃሉ።

• በምርምር የተገኙ ውጤቶች ወደ ተለያዩ ኢንዱስትሪዎች እንዲሸጋገሩ እና አገልግሎት ላይ እንዲውሉ

ለማድረግ አስፈላጊ ማበረታቻና ድጋፍ ይደረጋል።

• ለማዕድን ሠራተኞች፣ ለማዕድን አምራቾችና ለቴክኒሻኖች የሚሰጥ የሙያ ሥልጠና ወጥ ደረጃዎች

እንዲኖሩት ሥርዓት ይዘረጋል፤

• ለማዕድን ዘርፍ ልማት ወሳኝ የሆኑ እንደ ትራንስፖርት፣ የውሃ አቅርቦት፣ የኃይል አቅርቦት፣ የመገናኛ

አውታሮችን የመሳሰሉ መሰረተ ልማቶች አቅም በፈቀደ መጠንእንዲስፋፉ ይደረጋል።

• ከአፍሪካና ከሌሎች የዓለም ሀገራት ጋር በጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረተ በማዕድናት እና በማዕድን ሥራዎች

ላይ ያተኮረ ትብብር እንዲፈጠር ይደረጋል።

• በሀገራችንና በአፍሪካ ሀገሮች መካከል ትብብርና ቅንጅት በመፍጠር የላቀ የአቅም አጠቃቀም እንዲኖር ወሰን

ተሻጋሪና አካባቢያዊ ትስስርን (regional integration) ለማጠናከር በሚያስችል መልኩ የማዕድናትን

እሴት ከፍ የማድረግ ማዕድን የማበልጸግ፣ የማቅለጥና የፍብረካ ሥራዎች እንዲዳብሩ የሚረዳ ሥርዓት

ይዘረጋል፣ እንዲሁም

ረቂቅ የማዕድን ሀብት ልማት ፖሊሲ 29


• የማዕድን ዘርፍ የሣይንስና ቴክኖሎጂ እውቀትና ዘዴዎች እንዲስፋፉና በሥራ ላይ እንዲውሉ ለማድረግ

የሚያስቸል ሥርዓት ይዘረጋል።

4.11. የማዕድን ልማት ሕግና አስተዳደር

እስካሁን በሥራ ላይ የዋሉት የማዕድን ልማት ሕጎች ከጊዜ ወደ ጊዜ በዘመናዊ አስተሳሰብና በይዘታቸው እየተሻሻሉ የመጡ

ቢሆንም ከልዩ ልዩ የማዕድናት ባሕርይ ይልቅ በአጠቃላይ የማዕድኑ ዘርፍ የጋራ ባሕርያት ላይ ያተኮሩና በዚሁ ቅኝት

የተዘጋጁ ናቸው። ሆኖም ማዕድናት በርካታ ዘርፍና የተለያየ ባሕሪይ ያላቸው፣ ለተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች ግብአት ሊሆኑ

የሚችሉ፣ ኢንቨስትመንታቸውና የአመራረት ዘዴአቸውም በጣም የተለያዩ ናቸው። በአንጻሩ፣ ሕጎቹ የተለያዩ የማዕድን ንዑስ

ዘርፎችን ልዩ ባሕርያት ያላገናዘቡ በመሆናቸው ምክንያት ለየንዑስ ዘርፎቹ መሰጠት ያለበትን ልዩ ትኩረት፣እገዛና ማበረታቻ

ሊሰጡ አልቻሉም።

በሥራ ላይ የዋሉት ሕጎች ለተለያዩ የንዑስ ዘርፎች የትኩረት አቅጣጫ ያለመስጠታቸው እንዳለ ሆኖ የወጡትን ሕጎች በሥራ

ላይ ለማዋል ኃላፊነት የተሰጣቸው አካላት በሚፈለገው ደረጃ ባለመጠናከራቸውና የሰው ኃይላቸውም በቂ ባለመሆኑ፣

የተቋማቱ በብቃትና በተቀላጠፈ መንገድ ሕጎቹን ለማስፈጸም የሚታየው ክፍተት በዘርፉ ሊኖር የሚችለውን ኢንቨስትመንት

ሙሉ በሙሉ ለመቀበልና ለማስተናገድ ችግሮች እንዳሉ ያመላክታል።

ምንም እንኳን በተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀም ላይ ሕግ የማውጣትና በሥራ ላይ የሚውልበትን ሁኔታ የመምራትና የማስተዳደር

ሥልጣን የተሰጠው የፌደራል መንግሥቱ ቢሆንም በፌደራል መንግሥትና በክልል መንግስታት የማዕድን ሕግ አስፈጻሚ

አካላት መካከል በበቂ ደረጃ የሰመረ የመተባበርና የመደጋገፍ አሠራር ባለመፈጠሩ፣ የዚህ በአግባቡ የመናበብ እና የመተባበር

ጉድለት የማዕድን ልማቱን ለማፋጠን የራሱ አሉታዊ አስተዋጽኦ ይኖረዋል።

4.11.1. ዋና ዋና ችግሮች

• ሕጎቹ ለየማዕድን ልማቱ ንዑስ ዘርፎች በቂ ትኩረት ባለመስጠታቸው ለሀገር ልማት አስፈላጊ የሆኑት

የማዕድን ልማት ንዑስ ዘርፎች በበቂ ትኩረት ያለመመራታቸው፣

• የማዕድን ሕጎቹን በአግባቡ ለማስፈጸም በቂና ቀልጣፋ ተቋማዊ ዝግጅት ጉድለት መኖሩ፣

• የማዕድን ሕጎቹን ለማስፈጸም ቀጣይነት ያለው የሰለጠነና ልምድ ያለው የሰው ኃይል በበቂ መጠንና ጥራት

ያለመኖር፣ እና

ረቂቅ የማዕድን ሀብት ልማት ፖሊሲ 30


• በበቂና በአስፈላጊ መጠን ለሥራው አግባብ የሆነ የሰው ኃይል ሥልጠና ያለመኖርና የሰለጠኑ ባለሞያዎችንም

በያዙት ሥራ ላይ ለማቆየት ያለመቻል ናቸው።

4.11.2. የፖሊሲ ዓላማ

• የማዕድን ልማት ፖሊሲውን ለማስፈጸም የሚችል የማዕድን ልማት አስተዳደር ሥርዓትና ሕግ አዘጋጅቶ

በሥራ ላይ ማዋል።

• ከሀገር አቀፍ ደረጃዎች ጋር የተጣጣመ የአስተዳደር፣ የክትትልና የድጋፍ አሰጣጥ ሥርዓት መዘርጋትና

በሥራ ላይ ማዋል።

4.11.3. የማሥፈጸሚያ ሥልት - ሕጎችን በተመለከተ

• በሥራ ላይ ያሉ አሰራሮችንና ሕጎችን መመርመርና ተገቢውን ማሻሻያ ማድረግ፤ አስፈላጊ የሆኑ አዳዲስ

ሥርዓቶችን መዘረጋትና ሕጎችን ማውጣት።

• የማዕድን ሕጎች በዋናነት በግሉ የኢኮኖሚ ዘርፍ መሪነት ላይ ያተኮሩ፣ ተገማችና ዘላቂነት ያላቸው፣ በሥራው

ላይ ለሚሰማሩ ሰዎች በቂ ጥበቃና ዋስትና የሚሰጡ፣ የማዕድን ፈቃዶችን ያለችግር ወደሚቀጥለው ደረጃ

ማሸጋገር የሚያስችሉ፣ የማዕድን መብቶችን በዋስትና የማስያዝ፣ ለሌላ የማስተላለፍን መብት የሚያስከብሩ፣

ሌሎች አስፈላጊና ወሳኝ ዝርዝር ጉዳዮችን የሚይዙ፣ ቀልጣፋ አገልግሎት፣ አስፈላጊውን ድጋፍና ማበረታቻ

የሚሰጡ ይሆናሉ።

• ሕጎቹ መንግሥትና የግሉ ዘርፍ በማዕድን ልማት ሥራዎች ውስጥ ስለሚኖራቸው ተሳትፎ ዝርዝር

ድንጋጌዎች ይኖራቸዋል።

• ሕጎቹ ለኢንዱስትሪ፣ ለግብርና ግብዓት፣ ለኮንስትራክሽንና ለጌጣጌጥ ማዕድናት ፍለጋና ምርት ልዩ ትኩረት

በመስጠት ለኢንዱስትሪ ልማት ግብአት እንዲሆኑ ለማስቻል አስፈላጊው ድጋፍና ማበረታቻ የሚደረግበት

ሥርዓት ይዘረጋል።

• የከበሩ፣ ቤዝ ሜታልስና ብረት ነክ ማዕድናት ፍለጋ እንዲፋጠን እንዲስፋፋ እንዲለማና እንዲመረት ተገቢው

ትኩረትና ማበረታቻ ይደረጋል።

ረቂቅ የማዕድን ሀብት ልማት ፖሊሲ 31


• የማዕድን ኢንዱስትሪ ሥራ ግልጽነት እና ተጠያቂነትን የተላበሰና ለሕዝባዊ ውይይት ክፍት እንዲሆን

በማድረግ በኢንዱስትሪው ውስጥ መልካም የተፈጥሮ ሀብት አስተዳደር እንዲሰፍን ለማስቻል አስፈላጊው

ሥርዓት ይዘረጋል።

• በፌደራልና የማዕድን ልማቱ በሚካሄድባቸው የክልል መንግሥታት መካከል ፍትሐዊ የማዕድን ገቢ ክፍፍል

ሥርዓት ይዘረጋል።

4.11.4. የማሥፈጸሚያ ሥልት - የአስተዳደርና የምርምር ተቋማትን በተመለከተ

• የማዕድን ዘርፉን አስተዳደር በጥልቀት መመርመርና የማዕድን ዘርፉን በብቃት ማስተዳደር፣ ፈቃድ መስጠት፣

ማበረታታት፣ ድጋፍ መስጠት፣ መከታተልና መቆጣጠር እንዲሁም አግባብ የሆኑ እርምጃዎች ለመውሰድ

በሚያስችል መልክ እንዲጠናከር ሆኖ እንደገና ይደራጃል።

• ዘርፉን ለመምራት፣ ለማስተዳደር፣ ለመከታተልና ለመቆጣጠር አስፈላጊ የሆኑ ቁሳዊ ፍላጎቶች አቅም በፈቀደ

መጠን እንዲሟሉ ይደረጋል።

• የተሟላ መረጃ ማግኘት የሚያስችል ዘመናዊና ሀገር አቀፍ የማዕድን ካዳስተር ሥርዓት በመዘርጋት በተግባር

ላይ እንዲውል ይደረጋል።

• የማዕድን ሀብት አስተዳደርና አመራርን በተመለከተ በመንግሥት መሥሪያ ቤቶች እንዲሁም ከክልል

መንግሥታትና ተያያዥነትና ተደጋጋፊነት ባላቸው አካላት መካከል ዘላቂ የማዕድን ልማትን ማምጣትና

ማፋጠን በሚቻልበት ሁኔታ ምክክር፣ ትብብርና መደጋገፍ እንዲፈጠር የሚያስችል ሥርዓት ይዘረጋል።

• በማዕድኑ ዘርፍ አስተዳደር ውስጥ ግልጽነት፣ ሚዛናዊነት እና ፍትሐዊነት እንዲሰፍን ለማስቻል

የባለድርሻዎችን አመለካከት፣ ሐሳብና ፍላጎት ለማዳመጥና ምክክር ለማድረግ የሚያስችል ሥርዓት

ይዘረጋል።

• የማዕድን ዘርፉን ልማት በተመለከተ ስትራቴጂያዊ አቅጣጫዎችን የሚያመላክት፣ ምክር የሚሰጥ፣ ችግሮች

ሲኖሩ የመፍትሔ ሀሳብ የሚያቀርብ ከባለድርሻ አካላት የተውጣጣ አማካሪ ጉባኤ ይደራጃል።

ረቂቅ የማዕድን ሀብት ልማት ፖሊሲ 32


• የጂኦሎጂካል ሰርቬይ የተጠናከረ፣ የተሟላና ዘመናዊ ተቋም እንዲሆን ተደርጎ የጂኦሳይንስ መረጃውዎችን

የሚሰበሰብ፣ በየጊዜው የሚያሻሽልና በዘመናዊ መልክ የሚያደራጅ ለተጠቃሚዎችም የሚያቀርብ የማዕድኑ

ዘርፍ የጂኦሳይንስ ዕውቀትና ተፈላጊ መረጃ ምንጭ እንዲሆን ይደረጋል።

• የማዕድኑን ዘርፍ ለማስተዳደር፣ ለማልማት ከኢንዱስትሪ፣ ከግብርና፣ ከኮንስትራክሽን፣ ከጌጣጌጥ ሥራዎች

እና ሌሎች የአገልግሎት ዘርፎች ጋር ዘርፉ ሊኖረው የሚገባውን ግንኙነትና መደጋገፍ ሊያጠናክር

የሚያስችል ቀጣይነት ያለው የአቅም ግንባታ ሥራ ይካሄዳል።

4.11.5. የሰው ኃይል ሥልጠና እና አስተዳደር

• የዘርፉን ልማት በብቃት እንዲሁም በኃላፊነትና ተጠያቂነት ለማስተዳደር የሚያስችል ቀጣይነት ያለው የሰው

ኃይል አቅም ግንባታ ሥራ ይካሄዳል።

• የዘርፉ ባለሞያዎች በያዙት ሥራ ላይ እንዲቆዩ ለማስቻል ተገቢ የሆነ የማበረታቻ ሥርዓት ይዘረጋል።

• በተለያዩ የማዕድን ንዑስ ዘርፎች (የኢንዱስትሪ፣ ለግብርና፣ የኮንስትራክሽን፣ የጌጣጌጥ ማዕድናት፣ የከበሩ

ብረት ማዕድናት የቤዝ ሜታልሰ፣ እና ሌሎች የብረት ነክ ማዕድናትን) ለፍብረካና ማዕድናቱን በጥቅም ላይ

ለማዋል የሚያስችሉ የቴክኒክና የቴክኖሎጂ ክህሎቶችን፣ ጥናትና ምርምሮችን ማዳበርና በሥራ ላይ ማዋል

የሚችል የሰለጠነ የሰው ኃይል ለማልማት የሚያስችል የአጭርና የረጅም ጊዜ ሥልጠናዎች በትምሕርት

ካሪኩለም/ሥርዓት ውስጥ እንዲገቡ ይደረጋል።

4.12. ዘርፈ-ብዙ ጉዳዮች

4.12.1. ስለሴቶች መብትና ስለሥርዓተ-ጾታ

4.12.1.1. የፖሊሲ ዓላማ

የማዕድን ኢንዱስትሪው የሴቶች መብቶችና እኩልነት የሚከበርበት እንዲሆን ማድረግ እና የማዕድን ሥራ አካባቢዎች ለሴቶች

የተመቻቹ አንዲሆኑ ማስቻል።

4.12.1.2. የአፈጻጸም ሥልቶች

• ለእኩል ሥራ እኩል ደመወዝ በሥራ ላይ እንዲውል ይደረጋል።

ረቂቅ የማዕድን ሀብት ልማት ፖሊሲ 33


• ሴቶች በማዕድን ዘርፉ ውስጥ እኩል የሥራ፣ የትምህርት እና የተሳትፎ ዕድል እንዲኖራቸው ይደረጋል።

• ለሴቶች የተፈጥሮ፣ አካላዊ እና የጤና ፍላጎቶች አትኩሮት በመስጠት የማዕድን ሥራ አካባቢዎች ለሴቶች

የተመቻቹ እንዲሆኑ ይደረጋል።

• ከማዕድን ልማት ጋር የተያያዙ ማናቸውም ምክክሮችና ውሳኔዎች የሥርዓተ-ጾታ ምልከታዎችን ከግምት

ውስጥ እንዲያስገቡ ይደረጋል።

• በማዕድን ዘርፉ ውስጥ ሊያጋጥሙ የሚችሉ የሥርዓተ-ጾታ ችግሮችን በተለይም ጾታዊ ትንኮሳን ጨምሮ

ጾታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶችን መከላከል እና የጥቃት ድርጊቶች በሚፈጸሙበት ጊዜም በኃላፊነት

እርምጃዎችን ለመውሰድ የሚያስችል ሥርዓት ይዘረጋል።

4.12.2. የሠራተኞች መብትና አያያዝ

በማናቸውም የማዕድን ሥራዎች አካባቢ በዓለም አቀፍ መልካም የአሠራር ልምድ መሰረት የሠራተኞችን መብት አኗኗር፣

ጤንነትና ደህንነትን የሚያስጠብቅ ሥርዓት እንዲኖር ይደረጋል።

4.12.3. የሕፃናት ጥበቃ

ሕጻናትን ከጉልበት ብዝበዛና ከማዕድን ሥራ አሉታዊ ተጽዕኖዎች እንዲጠበቁ አስፈላጊው ሥርዓት ይዘረጋል።

4.12.4. የአካል ጉዳተኞች መብት

የማዕድን የሥራ ቦታዎች የአካል ጉዳት ያለባቸውን ሰዎች ከግምት ውስጥ በማስገባት ለሥራ አመቺ ሆነው እንዲደራጁ

ይደረጋል።

4.12.5. ተላላፊ በሽታዎችና ወረረሽኝ

ኤች አይቪ ኤድስ እና ማናቸውም አይነት ወረርሽኞችና የጤና ችግሮች የማዕድን ሥራዎች በሚካሄዱባቸው አካባቢዎች

ሊያደርሱ የሚችሉትን ጉዳት ለመከላከልና ለማስወገድ የሚያስችል ሁሉን አቀፍ የሆነ ሥርዓት ይዘረጋል።

5. የፖሊሲ አፈጻጸም ማዕቀፍ

ለዚህ ፖሊሲ ውጤታማ አፈጻጸም እንዲያመች የፖሊሲ አፈጻጸም ማዕቀፉን መወሰን አስፈላጊ ነው። ይህም

የሚመለከታቸውን አካላትለማስተባበር፣ ለማቀናጀት፣ ለመምራትና የአፈጻጸም ደረጃውን ለመከታተል ይረዳል። በተጨማሪም

ረቂቅ የማዕድን ሀብት ልማት ፖሊሲ 34


ፖሊሲውን ለማስፈጸም የሚያስፈልጉ ማናቸውንም ድጋፍና ዕርዳታን ለማስተባበር እና ተገቢውን ድጋፍ በተገቢው ጊዜ

ለመስጠት የሚያስችል በቂ አቅም ለመፍጠርም ይረዳል። የዚህ ፖሊሲ የአፈጻጸም ማዕቀፍ የፖሊሲውን የተፈጻሚነት ወሰን፣

ፖሊሲውን የማስፈጸም ኃላፊነት ያለበትን ተቋም እና ልዩ ልዩ ባለድርሻ አካላትን ከነሚናቸው ይዘረዝራል።

6. የፖሊሲው የተፈጻሚነት ወሰን

• ይህ ፖሊሲ በማዕድን ልማትና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ተፈፃሚ ይሆናል።

• ተያያዥ ጉዳዮች ማለት ከማዕድን ሀብቱ ልማት እና ፓሊሲው እንዲያሳካ የሚታሰበውን መዋቅራዊ ሽግግር ብሎም

ዘላቂ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ልማት ለማምጣት እንዲቻል ማዕድናት ለኢንዱስትሪ፣ ለግብርና፣

ለኮንስትራክሽን/ግንባታ፣ ጌጣጌጥ ሥራ እና ሌሎችም አገልግሎቶች በግብአትነት እንዲያገግሉ ተሳሳሪነታቸውንና

ተደጋጋፊነታውን ለመፍጠር እንዲሁም የውጭ ምንዛሪ ማስገኘት እንዲችሉ አስፈላጊ የሆነውን ተግባርና እንቅስቃሴ

ሁሉ ይጨምራል።

7. ፖሊሲውን የማስፈጸም ኃላፊነት ያለበት ተቋም

ይህንን ፖሊሲ ለማስፈጸም የመሪነቱ ሚና የኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት ሲሆን በፌደራል መንግሥቱ ሥር በዋናነት

ኃላፊነቱን ወስዶ የሚሠራው፣ የሚከታተለውና የሚያስፈጽመው አካል ስያሜው እንደሁኔታው ሊለዋወጥ የሚችል ቢሆንም

በዋናነት የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር (ሚኒስቴር) ነው።

8. የባለድርሻ አካላት እና ሚናቸው

8.1. ይህን ፖሊሲ ለማስፈጸም በርካታ ባለድርሻ አካላት ይኖራሉ። ባለድርሻ አካላት የሚለው አገላለጽ፡-

8.1.1. መንግሥት በሚኒስቴሩ በኩል የመሪነቱ ሚና ቢኖረውም ባለድርሻ አካላት ከጉዳዩ ጋርተያያዥነት

ያላቸው አንደ የአካባቢ ጥበቃ፣ የገንዘብ፣ የንግድና የኢንዱስትሪ፣ የግብርና እና የሳይንስና ቴክኖሎጂ

የመሳሰሉትን ዘርፎች የሚመሩ እና ሌሎችም ከሥራው ጋር ግንኙነት ያላቸው የመንግሥት አካላትን፤

8.1.2. በማዕድን ልማቱ ላይ የተሰማሩ ድርጅቶችን፣

8.1.3. የማዕድን ልማቱ የሚካሄድበት ክልል መንግሥትና በቀጥታ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የክልል

መንግሥታት የሥራ ክፍሎች ፣

ረቂቅ የማዕድን ሀብት ልማት ፖሊሲ 35


8.1.4. የማዕድን ሥራው የሚካሄድበት አካባቢ ነዋሪዎች፣

8.1.5. በተፈጥሮ ሀብት ጉዳዮች በተለይም በማዕድን ልማት፣ በአካባቢ ጉዳዮች፣ በማኅበራዊ ልማት ላይ

ትኩረት ሰጥተው የሚሰሩ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ የሙያ ድርጅቶች፣ የማኅበረሰብ ድርጅቶች፣

የሲቪክ ማኅበራት እና የመሳሰሉት፣ እና

8.1.6. በጉዳዮ ላይ ያገባናል የሚሉ ዜጎች በተለይም ደግሞ በዘርፉ የተሰማሩ የዘርፉ ሙያ፣ እውቀትና ልምድ

ያላቸው ዜጎች ይጨምራል።

8.2. ባለድርሻ አካላት ይህን ፖሊሲ በሥራ ላይ ለማዋል አስፈላጊ በሆነው ተግባር ላይ በሙሉ ይሳተፋሉ።

በተለይም፡-

8.2.1. የማዕድን ዘርፉና በኢንዱስትሪው፣ በግብርና፣ በግንባታ፣ በጌጣጌጥ ሥራ ዘርፎች መካከል ትስስር

ለመፍጠርና ለማዳበር እንዲሁም በዘርፉ ኢንቨስትመንት እንዲስፋፋ፣ ከዘርፉ መገኘት ስላበት የውጭ

ምንዛሪ እና ማዕድናትን ማበልጸግና፣ እሴት መጨመርን በተመለከተ ስለሚደረጉ ጥናቶች በሚቋቋሙ

አማካሪና ስትራቴጂያዊ አመራር በሚሰጡ ጉባኤዎች ላይ በንቃት የመሳተፍ፣

8.2.2. የማዕድን ዘርፉንና ኢንዱስትሪው፣ በግብርናው፣ በኮንስትራክሽን/በግንባታ፣ በጌጣጌጥ ሥራ እና

በሌሎችም አገልግሎት ዘርፎች ጋር እንዲፈጠር የሚፈለገውን ትስስር፤ ማዕድናትን ማበልጸግና እሴት

መጨመርን በተመለከተ በየዘርፉ የሚደረጉ ምርመርና ጥናቶችን በተናጠልም ሆነ በቅንጅት ማድረግ፣

መደገፍ፣ ማበረታታና ሁኔታዎችን ማመቻቸት፣

8.2.3. በማዕድን ዘርፉ የሥራ ሂደት፤ ግልጽነት፣ ተጠያቂነትና ሕዝባዊ ውይይት እንዲስፋፋ በማድረግ

መልካም የማዕድን ሀብት አስተዳደር እንዲሰፍን በሚደረገው ጥረት ውስጥ የነቃ ተሳትፎ የማድረግ።

ረቂቅ የማዕድን ሀብት ልማት ፖሊሲ 36


9. የፖሊሲ ክትትል፣ የግምገማ እና የክለሳ ስርዓት

9.1. ሚኒስቴሩ በዋናነት ይህንን ፖሊሲ የማስፈጸም፣ አፈጻጸሙን የመከታተል፣ ግምገማ የማድረግ፣

በግምገማው ላይ ተመስርቶ የክለሳ ሀሳብ የማዘጋጀትና የማቅረብ ኃላፊነት አለበት።

9.2. ሚኒስቴሩ በየዓመቱ የፖሊሲውን አተገባበር ሁኔታዎች እየገመገመ ሪፖርት ያቀርባል።ሪፖርቱ የፖሊሲውን

አፈጻጸም፣ ያጋጠሙ ችግሮችን፣ ለተሻለ አፈጻጸም መወሰድ ስላለባቸው እርምጃዎች፣ ስለሚያስፈልጉ የማሻሻያና

የክለሳ ሀሳቦችን እና ሌሎችም አስፈላጊ ናቸው የሚባሉ ጉዳዮችን መያዝ አለበት።

9.3. የማሻሻያ/የክለሳ ሀሳቦች በምክረሀሳብ ደረጃ ከመቅረባቸው በፊት በባለድርሻ አካላት ውይይት

ሊደረግባቸው ይገባል።

9.4. የክለሳና የማሻሻያ ሀሳቦች በግልጽ ተለይተው አስፈላጊነታቸውን ከሚያብራራ መግለጫ ጋር ለሚኒስትሮች

ምክር ቤት በሸኚ ደብዳቤ መቅረብ አለባቸው።

9.5. የሚኒስትሮች ምክር ቤት የቀረበውን የማሻሻያ ሀሳብ ከተቀበለው አጽድቆ ለአፈጻጸምና ክትትል

ለሚኒስቴሩ ይመልሰዋል።

10. የፖሊሲው ስርጭት

ይህ ፖሊሲ በማናቸውም የሕዝብ መገናኛ ዘዴ እንዲሰራጭና ሕዝብ እንዲያውቀው ይደረጋል። በተጨማሪም በሚስቴሩ ድረ

ገጽ ላይ በቋሚነት እንዲሰፍር ይደረጋል።

11. ፖሊሲው ተፈጻሚ የሚሆንበት ጊዜ

በየጊዜው የሚደረጉ ክለሳዎችና ማሻሻያዎች እንደተጠበቁ ሆነው ይህ ፖሊሲ ከጸደቀበት ቀን ጀምሮ ለሃያ (20) ዓመታት

(እስከ 2032 ዓ.ም) በሥራ ላይ ይቆያል።

12. የቃላት መፍቻ

12.1. “ማዕድን” ማለት ለዚህ ፖሊሲ አፈጻጸም በተፈጥሮ ሥነምድራዊ ሂደት የተፈጠረና ኢኮኖሚያዊ ዋጋ ያለው

በምድር ላይ ወይም በከርሰ ምድር ወይም በውሀ ውስጥ የሚገኝ ማናቸውም ሀብት ማለት ነው።

ረቂቅ የማዕድን ሀብት ልማት ፖሊሲ 37


12.2. “የማዕድን ሥራ” ማለት በጥቅሉ የማዕድን ቅኝት፣ፍለጋ፣ ምርመራ፣ ልማት ወይም የማዕድን

ማምረት/ማውጣት ሥራ ማለት ሲሆን በነጠላ አንዱን የሥራ አይነትም ያመለክታል፡፡

12.3. “የማዕድን ልማት ሥራ” ማለት ማዕድኑን ለማምረት ወይም ለማውጣት ወደማዕድን አዘል አካሉ ለመድረስ

ለመክፈት ማዕድኑን ለማውጣትና ለማዘጋጀት ለማጓጓዝ የሚያስቸሉ እና የማዕድን ሥራውን ለማካሄድ

በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ የሚያገለግሉ መሰረተልማቶችን መሥራትን ይጨምራል።

12.4. “የማዕድን ልማት” ወይም “የማዕድን ዘርፍ ልማት” እንደቃሉ አገባብ አጠቃላይ ማዕድን በኢኮሚው ውስጥ

የሚሰጠውን የእድገት፣ የመስፋት፣ የመበልጸግ ሁኔታዎች ማለት ነው።

12.5. “የኢንዱስትሪ ማዕድናት” ማለት ለኢንዱስትሪ ግብአትነት የሚውሉ እንደ ካኦሊን፣ ቤንቶናይት፣

ፊልድስፓር፣ ፖታሽ፣ ሲሊካ ሳንድ፣ የመሳሰሉ ብረት ያልሆኑ ማዕድናት ማለት ነው።

12.6. “የግብርና ግብዓት ማዕድናት” ማለት የኢንዱስትሪ ማዕድናት ሆነው በቀጥታም ሆነ በፍብረካ ሂደት አልፈው

ለግብርና ግብአትነት የሚውሉ እንደ ፓታሽ፣ ፎስፌት፣ ላይም ስቶን፣ የመሳሰሉ ማዕድናትን ይጨምራል።

12.7. “የኮንስትራክሽን/ የግንባታና የገጥ/ ማጋጌጫ (dimension stones) ማዕድናት” ማለት ለተለያዩ የግንባታ

ሥራዎች የሚውሉ ድንጋዮችን፣ እንደ እምነበረድ፣ ግራናይት፣ ባሳልት ያሉ ድንጋዮችንና አሸዋን ይጨምራል።

12.8. “የጌጣጌጥ ድንጋዮች/ማዕድናት”፣ ማለት ለተለያዩ ጌጣጌጥነት የሚውሉ እንደ አልማዝ፣ ዕንቁ፣ አኳማሪን፣

ሩቢ፣ ኤምራልድ፣ ሳፋየር፣ ጋርኔት፣ ኦፓል፣ ኦሊቪን የመሳሰሉ ድንጋዮችን ይጨምራል።

12.9. “የከበሩ ማዕድናት” ማለት እንደ ወርቅ፣ፕላቲነምና ተዛማጅ ማዕድናት እና ብር፣ ያሉ ማዕድናት ማለት ነው።

12.10. “ሚስቴር” ማለት የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር ነው።

12.11. “የአካባቢና ማኅበራዊ ተጽእኖ ግምገማ” ማለት ፕሮጀክቱ/ሥራው በአካባቢና በአካባቢው ማኅበረሰብ ላይ

አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ላይ መሰረት በማድረግ ሥራው ተግባራዊ ሲሆን የሚያስከትለውን ገንቢም

ሆነ አፍራሽ ውጤት ለይቶ በማወቅና በመመዘን የተዘጋጀ ሪፖርት ማለት ነው።

12.12. “የአካባቢና ማኅበራዊ ተጽእኖ ማናጅመንት እቅድ” ማለት በአካባቢና ማኅበራዊ ተጽኖ ግምገማ ሪፖርቱ

ውስጥ የሰፈሩትን ጉዳቶች፣ ለማቃለል፣ለማቅናት፣ መልሶ ለማልማት፣ ለማከም፣ ክትትል ለማድረግና ጉዳት

ረቂቅ የማዕድን ሀብት ልማት ፖሊሲ 38


እንዳያደርሱ ወይም ሊያደርሱ የሚችሉትን ጉዳት ተቀባይ በሚሆንበት ደረጃ ለማድረስ የሚደረጉ

እርምጃዎችን የያዘ ለአፈጻጸሙም ግልጽ መመሪያዎችን የያዘ ተፈጻሚ መሆን ያለበት እቅድ ነው።

ረቂቅ የማዕድን ሀብት ልማት ፖሊሲ 39

You might also like