You are on page 1of 2

አንበሳ የከተማ አዉቶቡስ አገልግሎት ድርጅት

አዲስ አበባ

የቢሮ ማስታወሻ

ለዴፖዎች ጥ/ም/ክ/ድ/ን/ስ ሂደት

ከቴ/ም/አገ/ዋ/ስራ ሂደት

ቀን 15/3/14

ጉዳዩ ፡ የአውቶብሶችን ባትሪ ይመለከታል፡፡

እንደሚታወቀው በርካታ አውቶብሶች በባትሪ ምክንያት እንደቆሙብን ይታወቃል፡፡ በመሆኑም አውቶብሶቹ


ላይ ተገጥሞ የመጣው ባትሪ ወይም የምንጠቀመው ባትሪ 12 ቮልት ከ 195 እሰከ 200 አምፔር (12 volt, 195-
200 amph) ሲሆን ይህን ባትሪ ለመግዛት የ 2013 ዓ.ም. ፍላጎት የጠየቅን ሲሆን በበጀት እጥረት ምክንያት ሂደቱ
በመጓተቱ እስከ አሁን ድረስ ባትሪ ማግኘት አልተቻለም፡፡ በአሁኑ ሰዓት አውቶብሶቹ ላይ የተገጠመው ባትሪ
አውቶብሶቹ ወደ ድርጅቱ እንደገቡበት ወቅት ተራ በተራ እየሞተ እንዲሚገኝ ታይቷል፡፡ ስለዚህ መጀመሪያ
አካባቢ የገቡት ሁሉም አውቶብሶች ባትሪ የሚፈልጉ በመሆኑ በተደጋጋሚ ግዢ ጠይቀናል፡፡

በመሆኑም ከገበያ ላይ የተገኙት ባትሪዎች በመጠን (size) አንዳንዱ ከእኛ ባትሪ ማስቀመጫ ያነሰ እና አንዳንዱ
ደግሞ ከማስቀመጫው ቦታ በላይ መጠን ያለው ስለሆነ ሊግጠም አልቻለም፡፡ ለምሳሌ የመንግስት ተቋም
ከሆነው ከእርሻ መሣሪያ አቅራቢ ድርጅት የተገኘው ባትሪ 12 ቮልት 200 አምፔር (12 volt, 200 amph)
ከአውቶብሶቻችን የባትሪ የማስቀመጫ ቦታ በላይ ከፍ ያለ በመሆኑ መግጠም አልተቻለም፡፡ እንደዚሁም ከዚሁ
ድርጅት የተገኘ 12 ቮልት 180 አምፔር (12 volt, 180 amph) ባትሪ ከአውቶብሶቻችን የባተሪ ማስቀመጫ ጋር
የተወሰነ የሚያንስ ሲሆን እንዲሁም የሚያሰፈልገው የባትሪ አምፔር ከቀዲሞ ከምንጠቀመው አንጻር ያነሰ
ሆኖ ለአውቶብሶቻችን የሚያስፈልገው የባትሪ አምፔር አንጻር ያነሰ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ 180 አምፔር ባትሪ
የአገልግሎት እድሜው እንደ 195 አምፔር ካለው በትሪ ጋር ሲነጻጸር 180 አምፔር የተወሰነ ያነሰ እድሜ
እድሜ ይኖረዋል፡፡

ነገር ግን አሁን ካለብን ችግር አንጻር ከስልጠና ዳፍ ( DAF) አውቶብሶቻችን ላይ 12 ቮልት 170 አምፔር (12v,
170 amph) የሆነ ባትሪ ወስደን ለመደበኛ አውቶብሶች እየተጠቀምን ሲሆን ምንም እንኳን ከ 195 አምፔር
ባትሪ ያነሠ ከረንት (current) ያለው ባትሪ ቢሆንም አገልግሎት እየሠጠ ስለሚገኝ እና አሁን ከእርሻ
መሣሪያዎች አቅራቢ ድርጅት የተገኘው ሲልድ (maintenance free 12v,180 amph) የሆነ ባትሪ ስለተገኘ እና
ለስልጠና አውቶብሶች ከተጠቅምነው ባትሪ አንጻር ይህ ባትሪ አሁን ካለብን የባትሪ ችግር አንፃር
ልንጠቀምበት እነደምንችል በድርጅቱ ባለሙያዎች ይሆናል ስለተባለ ግዢ ቢፈጸምልን እና ከተማችን አሁን
ካለችበት ሁኔታ አንጻር ከፍተኛ ትራንስፖርት ችግር ከመፍታት እና አውቶቡሶቻችን ወደ ስራ ከማስገባት
አንፃር ከፍተኛ ሚና የኖረዋል የሚል አስተያየት አለን ::
ከሰላምታ ጋር

You might also like