You are on page 1of 40

ስለ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ

ምንነት

ጥቅምት 2009 ዓ/ም


አዲስ አበባ

1
መግቢያ
 በሀገራችን ልማታዊና ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ለመገንባት በተደረገ
ጥረት

 የልማት፣ የሰላም፣ የዴሞክራሲና የመልካም አስተዳደር ስኬቶች


ተመዝግበዋል።

 ፈጣንና ቀጣይነት ያለው እድገትን ማረጋገጥ ከቻሉ፣ ጥቂት


የአለማችን አገራት ተርታ እንድትሰለፍ አስችሏታል።

 የብሔር ብሔረሰቦችንና ህዝቦችን መብት ያረጋገጠ፣ ፌዴራላዊ


ስርዓቱ መገንባት የተቻለ ሲሆን፣

 በቀጣዮቹ ሁለት አስርት አመታት አገራችንን መካከለኛ ገቢ ካላቸው


አገራት ተርታ ለማሰለፍ የተሰነቀው ራዕይ፣ ለማሳካት የሚያስችል
ተስፋ ሰጪ ውጤት እየተመዘገበ ይገኛል።
2
መግቢያ የቀጠለ…

 በዲፕሎማሲውም ረገድም አገራችን ተደማጭነቷ ከጊዜ ወደጊዜ እያደገ


በመምጣቱ፣
 የአለማችን ሰላምና መረጋጋትን በማስፈን ተግባር፣ ቀዳሚ ከሚባሉ አገራት ጎን
እንድትሰለፍ አድርጓታል።
 ይሁንና በተቃራኒው የጀመርነውን ተስፋ ሰጪ እድገትና ለውጥ የሚፈታተኑ
ተግዳሮቶች እያጋጠሙን ይገኛል።
 ከፈጣን እድገታችን ከመነጨ የህዝብ ፍላጎት መጨመር፣ ቀላል የማይባል ቁጥር
ያለው ወጣት ስራ አጥ መሆኑ፣
 በየደረጃው ለህዝብ ጥያቄ ፈጣን ምላሽ የሚሰጥ አመራር በሚፈለገው መልኩ
አለመኖር፣
 የስርዓታችን ቁልፍና አደጋ መሸሸጊያ የሆኑት የትምክህተኝነት፣ የጠባብነት፣
የአክራሪነትና የሽብርተኝነት አስተሳሰቦችን ተግባሮች እየተስፋፉ መሄድና
 የህዝባችን የመልካም አስተዳደር ችግሮች በበቂ ሁኔታ ያልተፈቱ መሆናቸው
 የፈጣን ልማታችንና የዲሞከራሲያዊ ስርዓታችን ፈተናዎች እንዲሆኑ
አድርጓቸዋል። 3
መግቢያ የቀጠለ…
 መንግስታችን ችግሩን በጥልቀት በመገምገም፣ ራሱን ለማደስ
እየተንቀሳቀሰ በሚገኝበት በአሁኑ ወቅት፣
 መንግስታችንን ለማዳከም የኒዮሌበራል ሀይሎች፣
 እንዲሁም ልማታችንና እድገታችን የማይፈልጉ እንደ ግብጽና የኤርትራ
መንግስት የመሣሠሉ የውጭ ሀይሎች፣
 ከሀገር ውስጥ ፀረ-ሰላም ሀይሎች ጋር በመቀናጀትና ከኪራይ ሰብሳቢ
ጥገኛ ሀይሎች ጋር ትስስር በመፍጠር፣
 በህዝባችን ውስጥ ያለውን የመልካም አስተዳደር ቅሬታዎች በመጠቀም፣
 ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን በሀይል ለማፈራረስና ልማታችንን ለማደናቀፍ
 ያለ የሌለ ሀይላቸውን በማረባረብ፣ የጥፋት ተግባራቸውን በግላጭ
በመፈጸም ላይ ይገኛሉ።

4
መግቢያ የቀጠለ…

 ካለፈው አመት ጀምሮ በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች በማህበራዊ


ሚዲያዎች፣
 በተለያዩ ድህረገፆች፣ ኢሳት፣ የአሜሪካና የጀርመን በመሣሠሉ
የቴሌቪዥንና የሬዲዮ ጣቢያዎች በመታገዝ፣
 በብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች መካከል መቃቃርና ጥላቻ እንዲፈጠር
ለማድረግ ያደረጉት ጥረትን በመቀጠል፣
 በየጊዜው በመጠን፣ በአይነትና በደረጃው እያደገ የመጣ፣ የአመጽና የሁከት
ድርጊቶችን በመፈጸም፣
 የሰላማዊ ዜጎችና የፀጥታ ሀይሎች ህይወት መጥፋት፣ የህዝብ፣
የግለሰቦችና የመንግስት ንብረቶችን ጨምሮ፣
 የአገር ውስጥና የውጪ ዜጎች የኢንቨስትመንት ተቋማት እንዲዘረፉ፣
እንዲቃጠሉና እንዲወድሙ ምክንያት ሆነዋል።
5
መግቢያ የቀጠለ…

 የተወሰነን ብሔር በጠላትነት በመፈረጅ፣ በህዝቦች መካከል የነበረው ታሪካዊና ስነ-ልቦናዊ


ትስስር በማደብዘዝ፣መቃቃር እንዲፈጠር በሰፊው ተንቀሳቅሰዋል።

 ይህ የጥፋት ሀይሎች ድርጊት፣ የአገሪቱን ህገ-መንግስታዊ ስርዓትና የህዝቡን ደህንነት ለአደጋ


በማጋለጥ፣

 የሀገራችንን ህልውና በእጅጉ እየተፈታተነ የሚገኝ የብሔራዊ ደህንነት ስጋት እየሆነ በመሄድ ላይ
ይገኛል።

 ስለሆነም የብሔራዊ ደህንነት አደጋ ከመሰረቱ ለመግታትና የተረጋጋ ሰላም በማስፈን፣


የልማታችንን ቀጣይነት ለማረጋገጥ፣

 ከተጋረጠብን የደህንነት ስጋት ጋር የሚመጣጠንና አደጋውን በአፋጣኝ መመከት የሚያስችል


 አወቃቀር፣ የሰው ሀይል ስምሪትና የሪሶርስ አቅም በመፍጠር፣ አደጋውን በብቃት መከላከልና

 በዘላቂነትም ማስወገድ የሚያስችል የህግ ማዕቀፍ ወይም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ታውጇል።

 በመሆኑም የህግ አስከባሪ አካላት አዋጁን ሲፈጽሙ፣ የአዋጁን ድንጋጌዎች በተሟላ መልኩ
ተገንዝበው የህግ ጥሰት ሳይፈፅሙ፣

 አዋጁ ተግባራዊ ለማድረግ እንዲቻል፣ በአዋጁ እና ተዛማጅ ጉዳዮች ዙሪያ ኦረንቴሽን ለመስጠት
የተዘጋጀ ሰነድ ነው።
6
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ትርጉምና ምንነት
 የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማለት
 አንደኛው ቁልፍ ጉዳይ፣ ያጋጠመው አደጋ ቀላል ያልሆነ ከባድ ተጽዕኖ
ያለው ሲሆን ፣
 ሁለተኛው ደግሞ አደጋው ጊዜ የማይሰጥና በአጭር ርብርብ አፋጣኝ ምላሽ
እና መፍትሔ የሚሻ ሲሆን፣
 ይህም አደጋ በተለመደው ህጋዊና አስተዳደራዊ አካሄድ ለመቆጣጠር
የሚያስችል ሁኔታ በማይኖርበት ጊዜ ከተለመደው አካሄድ ወጣ ያለ
 ፈጣንና ብቃት ያለው ውጤት ለማምጣት የሚያስችል ህጋዊ ድንጋጌ ነው።
 የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መንግስት የተፈጠረውን ችግርና አደጋ
 በአፋጣኝ መፍትሔ እንዲያገኝ የሚያስችለው ህጋዊና ሌሎች አቅሞች
እንዲኖረው ያደርጋል።
7
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ትርጉምና ምንነት
የቀጠለ…
 ይህ አቅም ከልዩ ሁኔታው በመነጨ ምክንያት የሚያገኘው ስለሆነ፣
በአጣዳፊው ክስተት ወቅት ብቻ የሚያገለግል ተጨማሪ ሀይል ሆኖ
ያገለግላል።
 የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አላማ፣
 ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱንና ህገ-መንግስቱን ለመጠበቅ፣
 በዲሞክራሲና ሰብዓዊ መብቶች ላይ የተጋረጠ አደጋን በመከላከል ህግና
ስርዓት እንዲረጋገጥ ማድረግ ነው።
 የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በአለማችን ብዙ አገሮች አስቸኳይ መፍትሔ የሚሹ
ሰው ሰራሽ ወይም የተፈጥሮ አደጋ ሲያጋጥማቸው ይጠቀሙበታል።
 በቅርቡ በአሜሪካ፣ የከተማው ከንቲባ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጀዋል።
 ሄርከን ማቴው የባህር አውሎነፋስ፣ በፍሎሪዳ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ
ታውጇል።
8
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ትርጉምና ምንነት
የቀጠለ…
 ግብፅ እኤአ ከ1967 እስከ 2012 በአረብና እስራኤል ጦርነት ሰበብና
ምክንያት በአስቸኳይ ጊዜያዊ አዋጅ ስር ቆይታለች።

 ፈረንሳይም እስከ 2017 የሚቆይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ደንግጋለች።

 ቱርክ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጀ አውጃለች። አሁንም በዚህ አዋጅ ስር ነች።


 አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጅ የመንግስታትን ድክመትና ጥንካሬ የሚያሳይ
ሳይሆን፣

 አደጋውን በፍጥነት በመቀልበስ በአገራቸው ሰላምና መረጋጋት በማስፈን


 ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ እድገታቸውን ለማስቀጠለ የሚያስችል መሣሪያ
በመሆኑ ነው።

 ይልቁኑ ደካማ መንግስታት ፈታኝ ሁኔታ ሲያጋጥማቸው ህገ-መንግስታዊ


ሰርዓቱን ለድርድር በማቅረብ፣ የበለጠ ሁኔታዎች እንዲባባሱ ምክንያት
ሆነው ይታያሉ።
9
የተደነገጉ ድንጋጌዎች

 በአገራችንም አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሚታወጀው


 በአገራችን ላይ ወረራ ሲያጋጥም፣
 ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን አደጋ ላይ የሚጥል ሁኔታ ሲፈጠር፣
 የተለመደው የህግ ማስከበር ስርዓት መፈጸም ሳይቻል ሲቀር፣

 የተፈጥሮ አደጋና የህዝብን ጤንነት አደጋ ላይ የሚጥል በሽታ ሲያጋጥም እንደሆነ በህገ-
መንግስታችን በአንቀጽ 93 ተደንግጓል።

 የህገ-መንግስታችን ድንጋጌ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ


 የማወጅ ስልጣን የማን እንደሆነ፣
 ስልጣን የተሰጠው አካል አዋጁን ለማወጅ የሚከተላቸውን ስነ-ስርዓቶች፣

 አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የሚገድባቸውና የማይገድባችው የዜጎችና የህዝቦች ዲሞክራሲያዊ


መብቶችን፣

 የአዋጁን አፈጻጸም የሚመረምር ቦርድ፣ እንዴት እንደሚቋቋምና ስልጣንና ሃላፊነቶቹ ምን


እንደሆኑ በዝርዝር ተደንግጓል።

10
የህገ-መንግስታችን ድንጋጌዎች የቀጠለ …

 የጸጥታና የፍትህ አካላት


 የድንጋጌዎቹን ይዘት በሚገባ አውቀው፣ አዋጁን ተግባራዊ ሲያደርጉ
ድንጋጌዎቹን ተከትሎ በመፈጸም፣

 የህገ-መንግስታዊ ድንጋጌዎች በተሟላ መልኩ ተግባራዊ


እንዲያደርጉና

 በአፈጻጸሙም ሒደት ከድንጋጌዎቹ ውጪ የተለያዩ የህግ ጥሰቶች


እንዳይፈጸሙ እንደሚረዳ ይታመናል።

 በመሆኑም በህገ-መንግስታችን አንቀጽ 93 ላይ ስለአስቸኳይ ጊዜ


አዋጅ የተደነገጉ ድንጋጌዎች፣

 በስድስት ንዑስ አንቀጾች ተከፋፍለው የቀረቡ ሲሆን፣ በእያንዳንዱ


ንዑስ አንቀጽ ስር የተደነገጉት ድንጋጌዎች የሚከተሉት ናቸው።
11
የህገ-መንግስታችን ድንጋጌዎች የቀጥለ …
ንዑስ አንቀጽ አንድ፣

ሀ. የውጭ ወረራ ሲያጋጥም ወይም ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን አደጋ


ላይ የሚጥል ሁኔታ ሲከሰትና በተለመደው የህግ ማስከበር ስርዓት
ለመቋቋም የማይቻል ሲሆን፣ ማንኛውም የተፈጥሮ አደጋ
ሲያጋጥም ወይም የህዝብ ጤንነት አደጋ ላይ የሚጥል በሽታ
ሲከሰት፣ የፌዴራሉ መንግስት የሚኒስትሮች ምክር ቤት የአስቸኳይ
ጊዜ አዋጅ የመደንገግ ስልጣን አለው።

ለ. የተፈጥሮ አደጋ ሲያጋጥም ወይም የህዝብ ጤንነት አደጋ ላይ


የሚጥል በሽታ ሲከሰት፣ የክልል መስተዳደሮች በክልላቸው
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሊያውጁ ይችላሉ። ዝርዝሩ ክልሎች ይህን ህገ-
መንግስት መሠረት በማድረግ በሚያወጧቸው ህገ-መንግስቶች
ይወሰናል።

12
የህገ-መንግስታችን ድንጋጌዎች የቀጠለ …
ንዑስ አንቀጽ ሁለት

በዚህ ንዑስ አንቀጽ አንድ (ሀ) መሠረት የሚታወጅ


የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ።
ሀ. የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በስራ ላይ ባለ ጊዜ የታወጀ ከሆነ፣
በታወጀ በአርባ ስምንት ሰዓታት ውስጥ ለህዝብ ተወካዮች ምክር
ቤት መቅረብ አለበት። አዋጁ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሁለት
ሦስተኛ ድምጽ ተቀባይነትን ካላገኘ ወዲያውኑ ይሻራል።

ለ. ከላይ በንዑስ አንቀጽ (ሀ) ስር የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ፣


የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት በስራ ላይ በሌለበት ወቅት የሚታወጅ
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ፣ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቅረብ
ያለበት አዋጁ በታወጀ በአስራ አምስት ቀናት ውስጥ ነው።

13
የህገ-መንግስታችን ድንጋጌዎች የቀጠለ …
ንዑስ አንቀጽ ሦስት

 በሚኒስትሮች ምክርቤት የተደነገገው በምክር ቤቱ ተቀባይነት ካገኘ በኋላ


ሊቆይ የሚችለው እስከ ስድስት ወራት ነው። የህዝብ ተወካዮች ምክር
ቤት በሁለት ሦስተኛ ድምጽ አንድን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በየአራት ወሩ
በተደጋጋሚ እንዲታደስ ሊያደርግ ይችላል።

ንዑስ አንቀጽ አራት

ሀ. ይ ጊዜ አዋጅ በሚታወጅበት ጊዜ የሚኒስትሮች ምክርቤት በሚያወጣቸው


ደንቦች መየአስቸኳሰረት፣ የሀገርን ሰላምና ህልውና የህዝብን ደህንነት፣
ህግና ስርዓትን የማስከበር ስልጣን ይኖረዋል።

ለ. የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስልጣን በህገ መንግስቱ የተቀመጡትን


መሰረታዊ የፖለቲካና የዲሞክራሲ መብቶችን፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን
ለማወጅ ምክንያት የሆነውን ጉዳይ ለማስወገድ ተፈላጊ ሆኖ በተገኘው
ደረጃ እስከ ማገድ ሊደርስ የሚችል ነው።
14
የህገ-መንግስታችን ድንጋጌዎች የቀጠለ …
ሐ. የሚኒሰትሮች ምክር ቤት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስር
የሚያወጣቸውን ድንጋጌዎችና የሚወስዳቸው እርምጃዎች፣
በማንኛውም ረገድ በዚህ ህገ-መንግስት አንቀጽ 1፣ 18 , 25 እ 39
ንዑስ አንቀጽ (1) እና (2) የተቀመጡትን መብቶች የሚገድቡ ሊሆኑ
አይችልም።

ንዑስ አንቀጽ አምስት

 በሀገሪቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በሚታወጅበት ወቅት የህዝብ


ተወካዮች ምክር ቤት ከአባላቱና ከህግ ባለሙያዎች መርጦ
የሚመድባቸው ሰባት አባላት ያሉት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም
መርማሪ ቦርድ ያቋቁማል። ቦርዱ አዋጁ በህዝብ ተወካዮች
ምክርቤት በሚፀድቅበት ጊዜ ይቋቋማል።

15
የህገ-መንግስታችን ድንጋጌዎች የቀጠለ …
ንዑስ አንቀጽ ስድስት

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ የሚከተሉት ስልጣንና


ሀላፊነቶች አሉት።

ሀ. በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ምክንያት የታሰሩትን ግለሰቦች ስም፣ በአንድ ወር ጊዜ


ውስጥ ይፋ ማድረግና የታሰሩበትን ምክንያት መግለጽ፣

ለ. በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ወቅት የሚወሰዱት እርምጃዎች በማናቸውም ረገድ ኢ-


ሰብዓዊ አለመሆናቸውን መቆጣጠርና መከታተል፣

ሐ. ማናቸውም የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እርምጃ ኢ-ሰብዓዊ መሆናቸውን ሲያምንበት፣


ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወይም የሚኒስትሮች ምክር ቤት እርምጃውን እንዲያስተካክል
ሀሳብ መስጠት፣

መ. በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እርምጃዎች ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት የሚፈጽሙትን ሁሉ


ለፍርድ እንዲያቀርቡ ማድረግ፣

ሠ. የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲቀጥል ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጥያቄ ሲቀርብ፣


ያለውን አስተያየት ለምክር ቤቱ ማቅረብ የሚሉ ናቸው። “ምንጭ የኢፌድሪ ህገ
መንግስት”
16
3. በሀገራችን በአሁኑ ወቅት የአስቸኳይ ጊዜ
አዋጅ እንዲታወጅ ያደረጉ ምክንያቶች
 በአገራችን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲታወጅ ከሚያደርጉ ምክንያቶች መካከል አንዱ፣

 ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱ አደጋ ላይ የሚጥል ሁኔታ ሲፈጠርና የተለመደው የህግ ማስከበር


ስርዓትን መፈጸም ሳይቻል ሲቀር እንደሆነ በህገ-መንግስቱ ተደንግጓል።

 በአሁኑ ወቅት በሀገራችን አንዳንድ አካባቢዎች ግጭቶች እየተበራከቱ በመምጣታቸውና


 ህግና ስርዓት እየተጣሱ፣ ስርዓት አልበኝነት እያደገ የመጣበት ሁኔታ ይታያል።

 በዚህም የህዘቡ የዕለት ተዕለት የኑሮ እንቅስቃሴ እየታወከ ይገኛል።

 የልማት አውታሮች እየተዘረፉና እየተቃጠሉ በአገሪቱ ኢኮኖሚያዊ እድገት አሉታዊ ተፅዕኖ


እያሳደረ ይገኛል።

 በህዝቦችና በሀይማኖት መካከል የቆየው የመቻቻልና የመተሳሰብ እሴቶች በመሸርሸር፣ አንድን


ሀይማኖት ከሌላው ሀይማኖት፣

 አንድን ህዝብ ከሌላው ህዝብ ላይ በማነሳሳት መልኩ የሚገለጽ ግጭት እንዲሆን የሚያደርግ
ዝንባሌዎች በመታየት ላይ ናቸው።

 በድምሩ እነዚህ ድርጊቶች ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን አደጋ ውስጥ የሚከቱ ሆነው በመገኘታቸው
አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲታወጅ ተደርጓል።
17
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲታወጅ ያደረጉ ምክንያቶች
የቀጠለ…
3.1 የተቀሰቀሰው ሁከት ወደመላው ሀገሪቱ እየተስፋፋ በመሆኑና የሁከቱ ባህሪ እየተቀየረ
በመምጣቱ፣

 በአለፈው አመት በኦሮሚያ የተለየዩ ዞኖች እና በአማራ ክልል፣ በተለይም በሰሜን ጎንደር ፀረ-
ሰላም ሀይሎች የቀሰቀሱት ሁከት፣ አሁንም በተሟላ ሁኔታ በቁጥጥር ስር የዋለ አይደለም።

 በቅርቡም በቢሸፍቱ ሀይቅ በተካሄደው የኤሬቻ በዓል ፀረ-ሰላም ሀይሎች በፈጠሩት ግርግር፣

 በሰላማዊ ዜጎች የህይወትና የአካል ጉዳት መድረስ ተከትሎ፣ በተለያዩ የኦሮሚያ ዞኖች ግጭቶች
እየተስፋፉ ይገኛሉ።

 በቅርቡም በደቡብ በዲላ ከተማ ግጭቶች ተፈጥረው በሰው ህይወትና ንብረት ላይ ጉዳት
ደርሷል።

 እነዚህም ሁከቶችና ግርግሮች ወደሌሎች የሀገሪቱ አካባቢዎች እየተዛመቱና ስፋቱ እየጨመረ


መምጣቱ የሚያመላክቱ ናቸው።

 ሁከቱ ሲጀመር በመንግስት በኩል ህዝቡ ይጎድላል ያለውን ጥያቄ ያቀላቀለ የነበረ ቢሆንም፣
አሁን ግን ባህሪውን ቀይሮ

 ጠቅላላ ስርዓት ለመቀየር አላማ ያደረገና በህዝብ እና በኢኮኖሚ ያነጣጠረ ሁከትና ብጥብጥ
በመሆኑ፣ ከፍተኛ ኪሳራና ጉዳት እያስከተለ መሆኑ ነው።

18
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲታወጅ ያደረጉ ምክንያቶች
የቀጠለ…
3.2 ሁከቱ በህዝቦችና በሀይማኖቶች መካከል መቃቃር እንዲፈጠር የሚያደርግ እየሆነ
መምጣቱ፣

 ሁከቱ በህዝቦች እና በሀይማኖት መካከል መቃቃር እንዲኖር የሚያደርግ ግጭት እየሆነ


መጥቷል።

 በእነዚህ ክልሎች የተነሱ ግጭቶች የተወሰነ የህብረተሰብ ክፍልን በጠላትነት በመፈረጅ


 በህዝቦች መካከል መቃቃር እንዲፈጠር ለማድረግ ተንቀሳቅሰዋል። ንብረታቸውን
ዘርፈዋል፣ የሰው ህይወትም ጠፍቷል።

 የእምነት ቦታዎችን በማቃጠልና በመዝረፍ፣ በሀይማኖት መካከል መቃቃር በመፍጠር፣


ግጭቱን ሀይማኖታዊ መልክ እንዲይዝ ለማድረግ ሞክረዋል።

 ለአብነትም

 በምዕራብ አርሲና በባሌ አካባቢ በተፈጠሩ ሁከቶች አክራሪ የዋህቢይ ሼኮችና


ተከታዮችም ተሳትፈውበት ግጭቱን የአላማቸው ማስፈጸሚያ ለማድረግ ሲጥሩ
ታይተዋል።

 ከውርጃ የተባለው ሌላው የእስልምና አክራሪ ፈለግ ተከታዮች በምዕራብ ሐረርጌ


ቤተክርስቲያን ያቃጠሉበት ሁኔታ ተከስቷል። ሌሎች ሀይማኖቶችም ….
19
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲታወጅ ያደረጉ ምክንያቶች
የቀጠለ…
3.3 ግጭቶቹ በጦር መሣሪያ የተደገፉና ከጸጥታ ሀይሎች ጋር ውጊያ
የሚደረግበት ሁኔታ እየጨመረ በመምጣቱ፣

 በአማራ፣ በኦሮሚያ የተለያዩ ዞኖች የተካሄዱ ህገ-ወጥ ሰልፎች


በአብዛኛው መሣሪያ የያዙ አካላት የተሳተፉባቸው ነበሩ።
 በአንዳንድ አካባቢ ወንጀለኞችን አደራጅተው በማስታጠቅ፣ የግልና
የመንግስት ተቋማትና ንብረቶች ዘርፈዋል፣ አቃጥለዋል፣
 መንገድ በመዝጋት ትራንስፖርት እንቅስቃሴ እንዲቋረጥ አድርገዋል፣
 የሰላማዊ ዜጎችና የጸጥታ ሀይሎች ህይወት እንዲጠፋ አድርገዋል።
 በአንዳንድ አካባቢዎች ከመከላከያ ሰራዊት፣ ከፌደራል ፖሊስ እና
ከክልል ፖሊስ ጋር በተደራጀ መልኩ ውጊያ የማድረግ ሁኔታዎች
አጋጥመዋል።
20
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲታወጅ ያደረጉ ምክንያቶች
የቀጠለ…
3.4 አመጹን ለማካሄድ የሚጠቀሙበት ስልት ተለዋዋጭ እየሆነ
በመምጣቱ፣

 በአንድ በኩል አመጹን ወደትላልቅ ከተሞች (አዲስ አበባ፣ አዳማ፣


አዋሳ) ለማስፋፋት ጥረት የማድረግ፣

 በሌላ በኩል ደግሞ አነስተኛ የሆኑ ቡድኖችን በማቋቋም፣


ግለሰቦችንም በመጠቀምና ወደተለያዩ ቦታዎች በማንቀሳቀስ

 ጨለማን ተገን በማድረግ ቁልፍ ተቋማት ላይ አደጋ በማድረስ፣


ስርዓት አልበኝነት እንዲሰፍን የማድረግ፣

 ከዚህም አልፈው በተመረጡ ግለሰቦችና የመንግስት ባለስልጣናት


ላይ ግድያ ለመፈጸም ፍላጎት እያሳዩ በመምጣታቸው ነው።

21
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲታወጅ ያደረጉ ምክንያቶች
የቀጠለ…
3.5 ኢንቨስትመንትን አላማ ያደረገ ጥቃት እየሆነ በመምጣቱ፣
 የውጭ ኢንቨስተሮች የኢንቨስትመንት ተቋም እየተዘረፉ፣ እየተቃጠሉ ይገኛሉ።
 ፋብሪካዎች፣ የእርሻና የአበባ ልማቶች ላይ፤ እንዲሁም በግልና በመንግስት
የልማት ተቋማት ላይ ቀላል የማይባል ጉዳት አድርሰዋል።
 በሀገራችን ኢኮኖሚ ስራ ከመፍጠር አኳያ ብቻ የማይታይ፣ ምርቶቻቸውን
ወደውጭ ኤክስፖርት በማድረግ
 ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ የሚያስገኙ የነበሩ ፋብሪካዎችና እርሻዎች ወድመዋል።
 ይህ በቀጣይ የሀገራችን እድገት በውጭ ምንዛሬ እየገነባቸው ባሉት ትላልቅ
ፕሮጀክቶች ላይ የራሱ ከፍተኛ ተፅዕኖ የሚያሳድር ነው።
 ይህ አይነት ተግባር እየቀጠለ ከሄደ የአገራችን ገጽታ በማበላሸት፣
 በቀጣይ በአገራችን የኢኮኖሚ እድገትና ኢንቨስትመንት ለመሳብ እየተደረገ ባለው
በጎ ጅምር ላይ አሉታዊ ሁኔታ የሚፈጥር ስለሆነ ነው።

22
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲታወጅ ያደረጉ ምክንያቶች
የቀጠለ…
3.6 መንግስት ሰላማችንን የሚያረጋግጡ አስቸኳይ እርምጃ
እንዲወሰድ የሚጠይቅ የህዝብ ግፊት እያጨመረ መምጣቱ፣

 ህዝቡ፣ ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱ አደጋ ላይ እየወደቀ ነው፣


 ሰላማችን እየደፈረሰ ችግሩ የእያንዳንዳችን ቤት የሚያንኳኳ እየሆነ
ነው፣

 መንግስት የህዝቡን ሰላምና ደህንነት በአስተማማኝ ደረጃ


ለማረጋገጥ የሚያስችል

 እርምጃ ለምን አይወስድም የሚል ጥያቄ እያቀረበ ግለቱም


እየጨመረ በመሄዱ ነው።

23
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲታወጅ ያደረጉ ምክንያቶች
የቀጠለ…
3.7 ሁከቱ ከሚገባው ጊዜ በላይ በመቆየቱ ትዕግስት አስጨራሽ
ሁኔታ እያስከተለ በመምጣቱ፣

 በአጠቃለይ ሁከትና አመጹ ከተጀመረ ከ6ወር እስከ 9ወር የዘለቀ


ስለሆነ፣ እስከ አሁን ድረስ እልባት ባለማግኘቱ፣

 የጸጥታ ሀይሉ ሁከቱን ለመቆጣጠር የሚያደርገው ጥረት አድካሚና


ትዕግስት የሚፈታተን እየሆነበት መጥቷል።

 ሁከቱን በዘላቂነት ለማስወገድ የሚያስችል መፍትሔና ለውጥ


ለማምጣት

 በመንግስት በኩል የተፈጠረውን ችግር በአፋጣኝ መልክ ማስያዝ


አስፈላጊ በመሆኑ ነው።

24
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲታወጅ ያደረጉ ምክንያቶች
የቀጠለ…
3.8 የውጭና የአገር ውስጥ ፀረ-ሰላም ሀይሎች በህዝቡ የተነሱ
የመልካም አስተዳደር ቅሬታዎች ጠልፈው በመውሰድ
ስርዓቱን በሀይል የማፍረስ ግብ ይዘው ተቀናጅተው
እየተንቀሳቀሱ በመሆኑ፣

 መንግስት የኪራይ ሰብሳቢነት አደጋን ለመዋጋት እና የመልካም


አስተዳደር ችግሮችን ለመፈታት ረጅም ጊዜ የፈጀበት መሆኑን
በመገንዘብ፣

 በአንዳንድ አካባቢ ህዝቡ ቅሬታውን ለመግለጽ ህጋዊ ባልሆነ


መንገድ ያደረጋቸውን እንቅስቃሴዎች

 የውጭና የአገር ውስጥ ፀረ-ሰላም ሀይሎች በመጥለፍ በመውሰድ፣


ለራሳቸው ዓላማ ማስፈጸሚያ ለማድረግ

 ሁከትና ብጥብጡ እንዲቀጥል ተቀናጅተው እየሰሩ ይገኛል። 25


የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲታወጅ ያደረጉ ምክንያቶች
የቀጠለ…
 የአለም አቀፉ ኒዮሌበራል ሀይል፣ ግብጽና የኤርትራ መንግስት የአገር
ውስጥና የውጭ ፀረ-ሰላም ሀይሎች በገንዘብ በመደገፍ፣
 ፀረ-ሰላም ሀይሎችን በቡድን አደራጀቶ በማንቀሳቀስ፣ የመንግስትና
የግል ተቋማት እንዲቃጠሉ፣ እንዲዘረፉ
 እንዲሁም በሀይማኖትና በህዝቦች መካከል መቃቃር የሚፈጥር
ግጭት እየፈጠሩ ይገኛሉ
 እነዚህ ሀይሎች አመጹን በማቀጣጠል፣ መንግስት የሚይዘውና
የሚጨብጠውን በማሳጣት
 በአገሪቱ ስርዓት አልበኝነት በማስፈን የህዝቦችና የአገራችን ሉዓላዊነት
አደጋ ውስጥ እንዲገባ በማድረግ
 ህገ-መንግስታዊ ስርዓቱን በሀይል ማፍረስ ይቻላል የሚል ግብ ይዘው
ሌት ተቀን እየሰሩ ስለሆነ
 የወጠኑትን ሴራ በአጭሩ ማክሸፍ አስፈላጊ ሆኖ ስለተገኘ ነው።

26
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ቁጥር /2009 ማብራሪያና
ዝርዝር ይዘት

4.1. የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ማብራሪያ


1. ርዕስና መግቢያ
 የአዋጁ ርእስ የህዝብን ሰላምና ፀጥታ ለማስጠበቅ የወጣ የአስቸኳይ ጊዜ
አዋጅ የሚል ሲሆን
 በተለይም "የህዝብን ሰላምና ፀጥታ ለማስጠበቅ" የሚለው ሀረግ
የሚያመለክተው
 ህገ-መንግስታዊ ስርአቱን አደጋ ላይ የሚጥል ሁኔታ የተከሰተ መሆኑ
 ይህም ዋንኛ መገለጫው የህዝብ ሰላምና ፀጥታ መናጋት መሆኑን
ለማመልከት ነው፡፡
 ስለዚህ የዚህ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ርእስ በግልፅ የሚያመለክተው
 ህገ-መንግስታዊ ስርአቱ አደጋ ላይ በመውደቁ ምክንያት የታወጀ
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መሆኑን ነው፡፡
27
4. የአዋጁ ማብራሪያና ዝርዝር ይዘት የቀጠለ …

 በመግቢያው ላይ በአሁኑ ሰአት በሀገሪቱ ውስጥ ህገመንግስታዊ ስርአቱን


ሊያናጋ የሚችል ሁኔታ መከሰቱን፣
 የህዝብን ሰላምና ፀጥታ አደጋ ላይ የሚጥል፣ የዜጎችን ህይወትና አካል
የሚጎዳ፣
 የኢንቨስትመንትና የልማት እንቅስቃሴን በማዳከም ላይ ያነጣጠረ
በውጭ ሀይሎች ተሳትፎ ጭምር የተፈፀሙ ህገወጥ ተግባራት
 ለበርካታ ሰዎች ህይወት መጥፋት፣ አካል መጉደል፣ ለተቋማት እና መሰረተ
ልማቶች መውደም ፣ለብጥብጥና ስርአት አልበኝነት ምክንያት እየሆኑ
መሆኑን፣
 በመደበኛው የህግ ማስከበር ስርአትም እነዚህን ችግሮች ለመፍታት
አለመቻሉ ተመልክቷል፡፡
 እንዲህ አይነቱን ሁኔታ ለመቆጣጠር እና ህገመንግስታዊ ስርአቱን
ለመጠበቅ
 ልዩ ህጋዊ እርምጃዎችን ለመውሰድ የሚያስችል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ
ማውጣት አስፈላጊ በመሆኑ የአዋጁ መግቢያ ይህን ያመለክታል፡፡
28
4. የአዋጁ ማብራሪያና ዝርዝር ይዘት የቀጠለ …

2. ትርጓሜ
 የህግ አስከባሪ አካል ማለት
 የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር፣ የብሔራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት፣
የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን፣ የክልል ፖሊስ እና ሌሎች የፀጥታ አካላት ማለት
እንደሆ ተመልክቷል፡፡
 ሌሎች የፀጥታ አካላት ማለት
 የክልል ልዩ ሀይል ፖሊስ፣ ሚሊሻ፣ ተጠባባቂ ጦር እና የተቋማት ጥበቃ
ያካትታል፡፡
 የመከላከያ ሰራዊት በህገመንግስቱ አንቀፅ 86/3/ ላይ ከመደበኛ የሀገር
ሉአላዊነት የማስከበር ስራው በተጨማሪ
 በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተፈፃሚነት ወቅት የሚሰጡትን ተግባራት
እንደሚያከናውን በተመለተከው መሰረት የተካተተ ነው፡፡
 በአጠቃላይ በህግ አስከባሪነት የተመለከቱት አካላት በጋራና በአንድ እዝ
በአስቸኳይ ጊዜ ኮማንድ ፖስት ስር ተቀናጅተው እንዲፈፅሙ ለማስቻል
ታስቦ ነው፡፡ 29
4. የአዋጁ ማብራሪያና ዝርዝር ይዘት የቀጠለ …

3. የተፈፃሚነት ወሰን
 የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ተፈፃሚነት ወሰን “በመላ ሀገሪቱ አካባቢ” መሆኑ
በአዋጁ ተመልክቷል፡፡
 ይህም ማለት በሀገሪቱ በሙሉ ተግባራዊ የሚደረግና አዋጁን ለማስፈፀም
 በጠቅላይ ሚኒስትሩ በሚመራው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስት
እርምጃዎች እንደሚወሰዱ የሚያመለክት ነው፡፡
 የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስት በሚወስነው መሰረት ተፈፃሚ
ሊሆንባቸው የሚገቡ አካባቢዎችና ጊዜ ይወሰናል፣
 የሚወሰዱ እርምጃዎች አይነት በኮማንድ ፖስቱ ይመረጣል፡፡
 አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ቀሪ ሊያደርግና ሊያስቆም ይችላል፡፡
 በዚህም እርምጃዎቹ ተፈፃሚ የሚሆኑባቸው ቦታዎችንም ሊገድብ ወይም
ቀሪ ሊያደርግ ይችላል፡፡

30
4. የአዋጁ ማብራሪያና ዝርዝር ይዘት የቀጠለ …

4. በአስቸኳይ ጊዜ የሚወሰዱ እርምጃዎች

 አዋጁ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስት ሊወስዳቸው


ስለሚችላቸው እርምጃዎች ተመልክቷል፡፡

 እነዚህ እርምጃዎች ሊወሰዱ የሚችሉት ህገ መንግስታዊ ስርአቱን


ለማስከበርና

 የህዝብንና የዜጎች ሰላምና ፀጥታ ለማስጠበቅ አስፈላጊ በሆነው ልክ


ብቻ ነው፡፡

 በዚህም መሰረት በአዋጁ አንቀፅ 4(1-12) የተጠቀሱት እርምጃዎች


ሲወሰዱ የአንቀፁን መንደርደሪያ መሰረት በማድረግ መሆን አለበት፡፡

31
4. የአዋጁ ማብራሪያና ዝርዝር ይዘት የቀጠለ …

 በዚሁ መሰረት ከሚወሰዱት እርምጃዎች መካከል


 “ማንኛውም ሁከት፣ ብጥብጥና በህዝቦች መካከል መጠራጠርና መቃቃር
የሚፈጥር ይፋዊ ሆነ የድብቅ ቅስቀሳ ማድረግ፣
 ፅሁፍ ማዘጋጀት፣ ማተምና ማሰራጨት፣ ትእይንት ማሳየት፣ በምልክት
መግለፅ ወይም መልእክትን በማናቸውም ሌላ መንገድ ለህዝብ ይፋ
ማድረግ፣” የሚለው የሚገኝበት ሲሆን፣
 ይህ ማለት ማንኛውም ሰው ሀሳብን የመግለፅ መብትን አላግባብ
ተጠቅሞ ህገ መንግስታዊ ስርአቱን አደጋ ላይ የሚጥልና
 የህዝብና የዜጎች ሰላምና ፀጥታ የሚያደፈርስ ተግባር እንዳይፈፅም
የሚያግድ አንቀፅ ነው፡፡
 ድንጋጌው ኮማንድ ፖስቱ ከላይ የተገለጹ ተግባራት የሚፈጸሙ መሆኑን
ካወቀ ተግባራዊ እንዳይደረጉ ለመከልከል ስልጣን ይሰጣቸዋል፡፡

32
4. የአዋጁ ማብራሪያና ዝርዝር ይዘት የቀጠለ …

 በሌሌ በኩል ማናቸውም የመገናኛ ዘዴ ለምሳሌ ስልክ፣ ኢንተርኔት፣


ድረገጽ፣ ማኅበራዊ ሚድያ እንዲዘጋ ወይም እንዲቋረጥ ሊያደርግ
ይችላል፡፡
 የህዝብና የዜጎች ሰላምና ፀጥታ ለማስጠበቅ ሲባል ስብሰባና ሰልፍ
ማድረግ፣ መደራጀት፣ በቡድን ሆኖ መንቀሳቀስ ሊከለከል ይችላል፡፡
 በዚህም በየትኛውም ቦታ ማናቸውም ዓይነት ሰልፍና ስብሰባ
የተከለከለ ሣይሆን
 ኮማንድ ፖስቱ ችግር የሚያስከትሉ ስብሰባዎችን ወይም በሰዎች
ላይ ችግር ሊፈጥር የሚችሉ ሆኖ ከተገኘ ብቻ የሚታገዱ ናቸው፡፡
 የህዝብን ሰላምና ፀጥታ በማደፍረስ ተግባር ላይ ተሳትፏል ተብሎ
የሚጠረጠር ማናቸውም ሰው
 ያለፍርድ ቤት ትእዛዝ በቁጥጥር ስር ሊደረግ፣ ተጣርቶ ትምህርት
ተሰጥቶት ወይም እንዲሁ ሊለቀቅ ይችላል፡፡
33
4. የአዋጁ ማብራሪያና ዝርዝር ይዘት የቀጠለ …

 በሌላ በኩል የህግ አስከባሪ አካላት ረብሻና ሁከት ፈጣሪዎችን ይዞ


ለማቆየት ወይም በመደበኛ ህግ ተጠያቂ እንዲሆኑ ለማድረግ
ይችላል፡፡

 ይህ ማለት ከ48 ሰአት በላይ እና ይህ አዋጅ ተፈፃሚ በሆነበት ጊዜ


ገደብ ውስጥ ፍርድ ቤት ሳይቀርቡ ተይዘው ሊቆዩ ይችላሉ ማለት
ነው፡፡

 በሌላ በኩል ወንጀል የተፈፀመባቸውን ወይም ሊፈፀምባቸው


የሚችሉ እቃዎችን ለመያዝ ሲባል

 ማናቸውንም ቤት፣ ቦታ፣ መጓጓዣ ለመበርበርና እንዲሁም


ማናቸውንም ሰው ለማስቆም፣ ማንነቱን ለመጠየቅ፣ ለመፈተሽ
ይችላል፤

 በብርበራ ወይም በፍተሻ የተያዙ እቃዎችን በማስረጃነት ለፍርድ


34
ቤት መቅረባቸው እንደተጠበቀ ሆኖ ተጣርተው ለባለመብቱ
4. የአዋጁ ማብራሪያና ዝርዝር ይዘት የቀጠለ …

 የሰአት እላፊ ተፈፃሚ የሚሆንበትን ሁኔታ ይወስናል፤ ለተወሰነ ጊዜ


አንድን መንገድ፣ አገልግሎት መስጫ ተቋም ለመዝጋት

 እንዲሁም ሰዎች ለጊዜው በተወሰነ ቦታ እንዲቆዩ፣ ወደ ተወሰነ


አካባቢ እንዳይገቡ ወይም ከተወሰነ ቦታ እንዲለቁ ለማዘዝ ይችላል፣

 የተቋማትና የመሰረተ ልማቶች ጥበቃ ሁኔታን ይወስናል፣


 የህዝብና የዜጎች ሰላምና ፀጥታ ለማስጠበቅ ሲባል የጦር መሳሪያ፣
ስለት ወይም እሳት የሚያስነሱ ነገሮችን ይዞ መንቀሳቀስ
የማይቻልባቸውን ቦታዎች ለይቶ ሊወስን ይችላል፣

 በሰላም መደፍረስ ምክንያት የፈረሱ የተለያዩ የአስተዳደር እርከኖች


ከክልሉ እና ከአካባቢው ህብረተሰብ ጋር በመተባበር መልሶ
እንዲቋቋሙ ያደርጋል፣

35
4. የአዋጁ ማብራሪያና ዝርዝር ይዘት የቀጠለ …

 በህግ አስከባሪ አካል ሳይታዘዝ ህዝብ የሚጠቀምባቸውን ፈቃድ


የወጣባቸው የንግድ ስራዎች ወይም
 የመንግስት ተቋማት ክፍት እንዲደረጉ፣ አገልግሎት እንዲሰጥ ወይም የስራ
ማቆም እንዳይደረግ ሊያዝ ይችላል፣
 በዚህ አዋጅ የተመለከቱ የአስቸኳይ ጊዜ እርምጃዎችን ለማስፈፀም
አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ተመጣጣኝ ሀይል መጠቀም ይችላል፡፡
5. የማይፈቀዱ ተግባራት
 አዋጁ ለህግ አስከባሪ አካላትና አባላት በአስቸኳይ ጊዜም ቢሆን
ሊፈፅሟቸው ወይም ሊጥሷቸው የማይችሉዋቸው ተግባራት ወይም
መብቶች
 በህገመንግስታችን አንቀፅ 93/4/ሐ/ በተመለከተው መሰረት በአዋጁም
እነዚህ የማይገደቡ መብቶች የተጠበቁ መሆናቸው።
 ይህ ማለት እነዚህ መብቶች በምንም አይነት ሁኔታ ሊጣሱ እንደማይችሉ
ተመልክቷል፡፡
36
4. የአዋጁ ማብራሪያና ዝርዝር ይዘት የቀጠለ …

6. የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስት

 የአስቸኳይ ጊዜ እርምጃዎችን የሚያስፈፅምና የህግ አስከባሪ


አካላትን የሚያስተባብር የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስት
ተቋቁሟል፡፡

 ኮማንድ ፖስቱ የተቋቋመው ስራው ኦፕሬሽነል ስለሆነ ነው፡፡


 ኮማንድ ፖስቱ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመራ ሆኖ
የሚመለከታቸውን የህግ አስከባሪና የፀጥታ ሀይሎች ጠቅላይ
ሚኒስትሩ እየመረጠ በአባልነት የሚሳተፉበት አካል ነው፡፡

 የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስቱ በቁጥጥር ስር ያደረጋቸውን


ሰዎች እና በቁጥጥር ስር ሆነው የሚቆዩበትን ቦታ ለአስቸኳይ ጊዜ
አፈፃፀም መርማሪ ቦርድ የማስታወቅ ግዴታ አለበት፡፡

37
4. የአዋጁ ማብራሪያና ዝርዝር ይዘት የቀጠለ …

7. የአስቸኳይ ጊዜ አፈፃፀም መርማሪ ቦርድ


 በሕገ መንግስቱ አንቀፅ 93/5/ መሰረት እንደሚደራጅ በተመለከተው
መሰረት ይህ ቦርድ እንደሚኖር አዋጁ እውቅና ይሰጣል፡፡
 መርማሪ ቦርዱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስት የሚወስዳቸውን
እርምጃዎች
 ህጋዊነት፣ ኢሰብአዊ አለመሆን ይከታተላል ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት
ሪፖርት ያደርጋል፡፡
 የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኮማንድ ፖስት በተጨማሪም አጥፊዎች ካሉ
እንዲጠየቁ እንደሚያደርግ ተመልክቷል፡፡
 8. የመተባበር ግዴታ
 ይህ ግዴታ የህግ አስከባሪ አካላት በኮማንድ ፖስቱ እየተመሩ ስራቸውን
በሚያከናዉኑበት ጊዜ ከፌዴራል እስከ ክልል፣ ከመንግስታዊ አካላት ጀምሮ
እስከ ግለሰቦች ድረስ የመተባበር ግዴታ አለባቸው፡፡

38
4. የአዋጁ ማብራሪያና ዝርዝር ይዘት የቀጠለ …

9. የወንጀል ተጠያቂነት

 በአዋጁ የተመለከተውን የመተባበር ግዴታ አለመወጣት ወንጀል


የተደረገ ሲሆን

 በሌላ በኩል ደግሞ በአዋጁ የተመለከቱ ግዴታዎችን ማለትም ሰአት


እላፊን መተላለፍ፣ ህገወጥ ሰልፍና ስብሰባ

 በተከለከለባቸው አካባቢዎችና ጊዜ ማድረግ የመሣሠሉት ድርጊት


መፈፀም እስከ አምስት አመት የሚያስቀጣ መሆኑ ተመልክቷል፡፡

 ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ ማናቸውም ሰው የሽብር ወንጀል፣ በንብረት


ላይ ጉዳት ማድረስ፣ በሰው አካልና ህይወት ላይ ጉዳት ማድረስ

 በመደበኛው የወንጀል ህግ መሰረት በተደራራቢ ወንጀልነት


የሚያስጠይቅ ይሆናል፡፡
39
7
5. አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አፈጻጸም ስኬታማነት የሚያረጋግጡ
ቁልፍ ጉዳዮች
 ብቃት ያለው ዝግጅት ብቃት ያለው አመራርና አፈጻጸም በማረጋገጥ አዋጁ በህግና
በጥንቃቄ እንዲፈጸምና በተቀናጀ ሁኔታ ተግባራዊ እንዲሆን ማድረግ።
 አዋጁን በታላቅ ህዝባዊነት መፈጸም፣ ታክስ ከፋይ የሆነውን ህዝብ ሰላም
ማረጋገጥና ሰላሙን ከሚያሳጡ ጉዳዮች እንድንከላከል ህግ ያስገድደናል።
 በመሆኑም አፈጻጸማችን ህዝቡን በማሳተፍ የሚፈጸም እና መለኪያውም ህዝቡ
ምን ያህል ተሳትፎበታል የሚለው መሆኑን ማረጋገጥ።
 ህግ አስከባሪው አዋጁን ሲፈጽም ውግናውን ለህዝብና ለህግ ብቻ በማድረግ
ኋላቀር አመለካከት ከሆኑ የትምክህት፣ የጠባብነት፣ የአክራሪነት ዝንባሌዎች ራሱን
ማፅዳትና
 በህዝቦችና በእምነቶች መካከል ያለውን መቻቻልና መከባበር በመጠበቅ ግዳጁን
ያለአድልዎ መፈጸም።
 በቁጥጥር ስር የሚውሉ ግለሰቦችን ህገ-መንግስቱ በሚፈቅደው መሠረት
አያያዛችን ሰብአዊ ርህራሄ የተሞላበት ማድረግ፣ (ምግብና፣ ውሃ መከልከል፣
ማሰቃየት፣ ክብራቸውን ማዋረድ ወዘተ የመሳሰሉ ኢ-ሰብአዊ ድርጊቶች ከመፈጸም
መቆጠብ) ህግና ህግን ብቻ ተከትለን ስራዎች መስራት።
40

You might also like