Professional Documents
Culture Documents
Squad Formation
Squad Formation
ነሀሴ 2001
አዲስ አበባ
የአደጋ መቆጣጠር ቡድን አመሠራረት/
የእሳት ቃጠሎ አደጋ ሲድርስ አደጋዉን በአፋጣኝ በተቀላጠፈና በተቀናጀ መንገድ ለመቆጣጠር
በቅድሚያ የአደጋ ተቆጣጣሪ ሠራተኞች በቡድን መዋቀር ይኖርባቸዋል፡፡የዚህ ትምህርት ዋና
ዓላማዉ እያንዳንዱ ሠራተኛ የሚሰጠዉን የሥራ ድርሻ በሚገባ ተረድቶ ራሱን በአካልና በአእምሮ
በማዘጋጀት በአደጋ ሥራ ላይ የሙያ ግዴታዉን በብቃት ለመወጣት እንድችል ለማድረግ ነዉ፡፡
በዓለም-አቀፍ ደረጃ ለቃጠሎ መቆጣጠር ተግባር ወደ አደጋዉ ሥፍራ የሚሰማራዉ የሰዉ ኃይል
በአንድ የቃጠሎ ማጥፊያ ተሸከረካሪ ላይ የቡድን መሪዉንና አሽከርካሪዉን ጨምሮ 6/ስድስት/
አባላትየሚኖሩት ሲሆን ከቡድኑ አባላት መካከል አራቱ የአደጋ ተቀጣጣሪ ኃይል ፣ አንድ ሾፌር እና
አንድ የቡድን መሪ ናቸዉ፡፡ በዚሁ መሰረት እያንድንዱ አባል የሚከተሉት ሥራ ድርሻ ይኖራቸዋል፡፡
ቁጥር 1 በራንች የሚይዝ
ቁጥር 2 የፓምፕ ኦፕሬተር
ቁጥር 3 ረዳት ብራንች ያዥ
ቁጥር 4 መለዕክት አስተላላፊ/
የቡድን መሪ የሥራ ድርሻ
በአደጋ መቆጣጠሩ ሥራ ላይ የተሰማሩ ሠራተኞችን ይቆጣጠራል፤ሥራዉን ይመራል፡፡
ስለአደጋዉ ሁኔታ መረጃ ያሰባስባል፤
አደጋዉን ለመቆጣጠር ስትራቴጂ ይቀይሳል፤
አደጋዉ ከአቅም በላይ ከሆነ ተጨማሪ ኃይል ይጠይቃል፤
በአደጋዉ የወደመና የዳነ ንብረት ግምት ይይዛል፤
በአደጋዉ የተጎዳና የሞተ ሰዉ ካለ ሪፖርት ይይዛል፤ዕርዳታ እንዲያገኙ ያደርጋል
መጠለያ አልባ የሆኑትን ጊዚያዊ ድጋፍ እንዲያገኙ ለሚመለከተዉ አካል ያሰተላልፋል
በአደጋ ሥራ ላይ የተሳተፉትን ሠራተኞች፤ተሸከርካሪዎች፤አጋር ድርጅቶችን ብዛት
መዝግቦ ይይዛል፤
የተረጨ ዉሀ፤ፎምና የነዳጅ ፍጆታ በሪፖርት መዝግቦ ይይዛል፤
የአደጋዉን መንስኤ ከአካባቢዉ ሕብረተሰብ ያገኘዉን መረጃ ይይዛል
ከላይ በዝርዝር የተመዘገቡትን በወቅቱ ለዳታና ስታቲስቲክስ ክፍል ያስተላልፋል፡፡
የሹፌሩ የሥራ ድርሻ
የአደጋ ተቆጣጣሪ ኃይሉንና የተሟላ የአደጋ ጊዜ መገልገያ
መሣሪያዎችን በመያዝ በተቀላጠፈ ሁኔታ አቋራጭና አማራጭ
መንገዶችን በመምረጥ በፍጥነት ወደ አደጋዉ ሥፍራ መድረስ፤
አደጋዉ ስፍራ እንደደረሰ ተሽከርካሪዉን ለአደጋ መቆጣጠሩ ሥራ
አመቺ በሆነ ቦታ ላይ ያቆማል፤
ከቡድኑ አባላትና ከቡድን መሪዉ የሚሰጡትን ትዕዛዞችን
ይፈጽማል፤
የአደጋ መቆጣጠሩን ሥራ ያግዛል/ኦፕሬተር በመሆን/፤
ከአደጋ መቆጣጠር በኋላ ዉሃ ሞልቶ ወደ ክፍሉ ይመለሳል፡፡
በጓድአመሠራረት ወቅት የምንጠቀማቸዉ
የዕዝ ቃላቶች፤
ከቀኝ በአራት ቁጠር፤ በዚህ ጊዜ በሰልፍ የሚገኙ ሠልጣኞች በትዕዛዙ መሰረት ከቀኝ ወደ
ግራ ከ1-4 ይቆጥራሉ፤ይህም እያንዳንዱ አባል የሥራ ድርሻዉን እንዲያዉቅ ይረዳል፡፡
ጓድ ቁጠር” ይህ ትእዛዝ በሚሰጥበትጊዜ አንዳንድ ቁጥር የጠሩት በሙሉ ተራ በተራ
በመጥራት ስንተኛ ጓድ ዉሰጥ እንዳሉ ጓዳቸዉ የሚገኙበትን ምድብ ይናገራሉ፤
ለሥራ ተዘጋጅ ፤ ሠልጣኞች በሚለማመዱበት መሳሪያ አጠገብ/ጀርባ/ ሄደዉ ለመቆም
ራሳቸዉን አዘጋጅተዉ ተከታዩን ትእዛዙን ይጠባበቃሉ፤
ሥራህን ጀምር ፤ በዝግጅት ላይ ያሉት ጓዶች በተእዛዙ መሰረት ሥራቸዉን ይጀምራሉ፡፡
ሥራህን አብቃ ፤ ሠልጣኝ ጓዶች ሲለመማዱበት የነበረዉን መሳሪያ አስተካክለዉ
በተገቢዉ ቦታ ያስቀምጣሉ፡፡
ፕሬዠር መቀነስ
ፓወር ቴክ-ኦፍ /የዉሃ ማርሽ/እንዲያስወጣ ለሹፌሩ
መልክት ማስተላለፍ
የዉሃ ጋኑን /ታንከሩን /መስመር መዝጋት፤
የዉሃ መርጫ መስመሮችን መዝጋት፤
ሆሱን ከፓምፑ ላይ እንዲሁም ብራንቹን ከሆሱ ላይ
መንቀልና መጠቅለል
ዕቃዎችን መሰብሰብ
8 ከግድብ ወይም ከወንዝ ዉሃ ለመሳብ በቅደም-ተከተል
የሚሠሩ ሥራዎች
ፕሬዠር መቀነስ
ፓወር ቴክ ኦፍ እንዲያወጣ ለሹፌሩ መልክት
ማስተላለፍ፤
ወደ ታንከር የሚያስገባዉን መስመር /ቫልቭ /መዝጋት
የሳክሽን ሆሱን ጫፍ ከዉሀ ዉስጥ ማዉጣትና ፈታቶ
መኪና ላይ መጫን
ፓምፕ ዉሀ እንዳይስበ የሚያደርጉ ሁኔታዎች