You are on page 1of 4

3.

10 የኦዲት ጥራትን ማረጋገጥ


የኦዲት ውጤት ሪፖርት በኋላፊ ተፈርሞ ለግብር ከፋዮች
እንዲደርስ ከመደረጉ በፊት በተወጣጣ ቡድን /Virtual
Team/ አማካኝነት በቅድሚያ እንዲረጋገጥ ይደረጋል፡፡
ይህም የኦዲት ጥራት ደረጃን ያሻሽላል፡፡ የቀረበው ኦዲት
ከአድሎና ከኪራይ ስብሳቢነት አስተሳሰብና ድርጊት የፀዳ
መሆኑን ማረጋገጥ ያስችላል፡፡ ኦዲተሮች በኋላፊነትና
በተጠያቂነት መንፈስ ተግባራቸውን እንዲወጡ ያስችላል፡፡
3.10.1 የኦዲት ጥራት ሲረጋገጥ የሚተኮርባቸው ጉዳዮች
ድርጅቱ የሚጠቀምባቸው ደረሰኞች በተቋሙ የተፈቀዱና
የክትትላቸው አግባብ በተገቢው መንገድ መሆኑንና የኦዲት
ሪፖርት በደረሰኝ አጠቃቀም ዙሪያ በቂ መረጃ መቅረቡን፣
ስለ ካሽ ሪጅስተር አጠቃቀምና ሪፖርት አቀራረብ በቂ
መግለጫ ተብራርቶ መቅረቡን፣
የግብር ከፋዩ የሂሣብ መዝገብና ደጋፊ ሠነዶች አያያዝ
ተቀባይነት ማግኘታቸው ወይም ተቀባይነት ላለማግኘታቸው
የተጠቀሱ ነጥቦች አጠቃላይ ተቀባይነት ያገኙ የሂሣብ አያያዝ
መርህና የግብር እና ታክስ ህግን መሠረት አድርጎ የተገለፀ
መሆኑን፣
የግብር ከፋዩ የባንክ እንቅስቃሴ ከሂሣብ መዝገብ ጋር ያለው
ግንኙነት በበቂ ደረጃ መብራራቱንና ገላጭ መሆኑን፣
የባንክ ብድርና ተመላሽ ከንግድ ሥራው ጋር ያለው ግንኙነትና
ልዩነተ ተብራርቶ መግለፁን፣
ግብር ከፋዩ በተጨማሪ የንግድ ሥራ/ገቢ ሊያስገኝ የሚችል ሁኔታ
ተጠቃሎ በሪፖርት የተገለፀ መሆኑ፣
ከግብር ከፋዩ ጋር የቅርብ ግንኙነት ያላቸው/ዘመዶች/
በሚያካሄዱት የንግድ ሥራ በግብር ከፋይነት ወይም ለተ.እሴት
ታክስ መመዝገባቸው ተብራርቶ መገለጹን፣
የግብር ወይም የታክስ ውሣኔው በ3ኛው ወገን የግዥ ወይም
የሽያጭ መረጃን መሠረት አድርጎ የተሠራ ከሆነ የመረጃው ጥራትና
ተገቢነት ትክክለኛ በደጋፊ ሠነድ ላይ የተመሠረት መሆኑን፣
ግብርን ወይም ታክስ ለመወሰን የሚያስችል ዓመታዊ
የሽያጭ መጠን ትክክለኛ ህጋዊ መሠረት ያለው መሆኑ፣
በሂሣብ ስሌት የተወሰነ ግብር ወይም መቶ መተመኛ
እና የመጣኔ አጠቃቀም፣ የተርን ኦቨር ታክስ ወይም
የተ.እሴት ታክስ ልክ በአግባቡ የተሠላ መሆኑ፣
በቅድሚያ የተከፈለ ግብርን እና ታክስን በደረሰኝ
የተረጋገጠ መሆኑ፣
አስተዳደራዊ መቀጫና ወለድ በህጉ መሠረት የተሰላ
መሆኑ፣

You might also like