You are on page 1of 1

ፕሬስቲጂየስ ዩዝ አካዳሚ

የፕሪፓራቶሪ የአማርኛ መልመጃ


አቤል
አቤል ጎበዝ ተማሪ ነው፡፡ ትምህርቱን በደንብ

ያጠናል፤ አስተማሪ ሲያስተምር በደንብ ያዳምጣል፤

ታላላቆቹን ያከብራል ለወላጆቹም ይታዘዛል፤ ጓደኞቹንም

ይወዳቸዋል፡፡ አቤል በእረፍት ቀናቶች ትምህርቱን አጥንቶ

ሲጨርስ ከጓደኞቹ ጋር ይጫወታል፡፡ ሁሉም አስተማሪዎቹ

እና ጓደኞቹ አቤልን በጣም ይወዱታል፡፡ ስለዚህ ልጆች

ሁላችሁም ጎበዝ ተማሪ መሆን አለባችሁ፡፡

ሀ. በምንባቡ መሰረት “እውነት” ወይም “ሐሰት” በማለት መልሱ፡፡


1. አቤል ታላላቆቹን ያከብራል፡፡

2. ጎበዝ ተማሪ ለመሆን ማጥናት አያስፈልግም፡፡

3. ሁሉም ልጆች ጎበዝ ተማሪ መሆን አለባቸው፡፡

4. አቤል ለወላጆቹ አይታዘዝም፡፡

5. አቤልን አስማሪዎቹ እና ጓደኞቹ ይወዱታል፡፡

You might also like