You are on page 1of 4

4.

1 ኢንተርፕራይዞቹከሌሎች ክፍሎችጋር ያላቸው ግንኙነት


በጅማ ዩኒቨርሲቲ
ከመንግስት ድርጅቶች ጋርየስራ ውል በመፈራረም የገበያ ተደራሽነት ማስፋፋት፣በጫረታ በመሳተፍ
የተለያዩ የመንግስት ድርጅቶች ፍላጎት የሚፈልጉትን ምርት አምርቶ በማቅረብ በትብብር መስራት
እና አክሲዮን ከግል ድርጅቶችና ባንኮች በመግዛት በጋራ ይሰራል፡፡ የዋስትና ሽፋን
አገልግሎትንበተመለከተ ኢንተርፕራይዞቹ ከተለያዩ ኢንሹራንስ አግልግሎት ከሚሰጡ ድርጅቶችየዋስትና
ሽፋን ገዝተዋል፡፡ኢንተርፕራዙ የህግ አማካሪ የዩኒቨርሲቲውን የህግ አገልግሎት ይተቀማል፡፡

4.2 ያጋጠሙ ችግሮችና መፍትሄዎቻቸው


በጅማ ዩኒቨርሲቲ
ኢንተርፕራይዞቹን ለማቋቋምና ከተቋቋሙ በኋላ ያጋጠሙት ችግሮች፡ ሳይቋቋም በፊት ህጋዊ ሰዉነት
ለማግኘት ያጋጠመዉ ችግርና ከታክስ ጋር በተያያዘ ከገቢዎችና ጉምሩክጋር የነበረዉ አለመግባባት
ሲሆን ከተቋቋመ በኋላ ዩኒቨርሲቲዉ በጨረታ የሚያሰራቸዉ ስራዎች ከግል ነጋዴዎች ጋር እንዲወዳደሩ
መደረጉና የኢንተርፕራይዝ ማናጀር፣ የብረታብረት እናእንጨት ስራ ኢንተርፕራይዝ የባለሙያዎች
ፍልሰት ዋና ችግሮች ናቸው፡፡ ከዚህ በላይ ላጋጠማቸው ችግሮች የተወሰደዉ መፍትሄ ጥራት ያለዉ
ምርት ማምረትና ከግል ነጋዴዎችጋር ተፎካካሪ ለመሆን ልምድ ያላቸዉን ባለሙያዎችን
በኢንተርፕራይዙ ዉስጥ ለማቆየት የደሞዝ ስኬል ማሻሻልና የተለያዩ ጥቅማጥቅሞችን በመስጠት
ለማቆየት መታሰቡ እንዲሁም አዳዲስ ፕሮጀክቶችን በማዘጋጀት ትርፋማነትን ለማሳደግ እየተሰራ
መሆኑን ነው፡፡

በወለጋ ዩኒቨርሲቲ
ኢንተርፕራይዞቹን ለማቋቋም የነበረው ችግር ህጋዊ ሰውነት ለማግኘት ፍቃድ በገቢዎች ፅ/ቤት ሲሰጥ
ባለሙያዎቹሁኔታዎች ያለመረዳት ላይ የነበረው ችግር ሲሆን በተደጋጋሚ በማስረዳትና የዞኑ
አስተዳደርን በመጠቀም መፍትሄ ተገኝቷል፡፡ ኢንተርፕራይዞች ከተቋቋሙ በኋላ ልምድ ያላቸው
ሠራተኞች በጥቅማጥቅምና በደሞዝ ማነስ ምክንያት ስራ መልቀቅ ሲሆን ለዚህምየቅጥር ሁኔታና
የጥቅማጥቅም አይነቶችና መጠን በመለየት ማጽደቅ እንደመፍትሄ ተወስደዋል፡፡ ኢንተርፕራይዞች
በሰው ሃይል፣ በአስተዳደር እና በፋይናስ እራሳቸውን ችለው ሙሉ በሙሉ አለመንቀሳቀስቸው
ስራዎችን እንደሚፈለገው ለመስራትና ትርፋማ ለመሆን እንዲሁም ትርፍን ለማስላት አስቸጋሪ
በመሆኑ ኢንተርፕራይዞች የራሳቸውን ሰራተኞች ቀጥረው እራሳቸውን ሙሉ በሙሉ ለማስተዳደር
አሰራሮችን መዘርጋት እንደመፍትሄ ተወስዷል፡፡

1
1. ለመደወላቡ ዩኒቨርሲቲ ጠቃሚ የሆኑ ተሞክሮዎች
1. ዩኒቨርሲቲው የአከባቢውና የፌደራል ባለስልጣናትን በመጠቀም ለዩኒቨርሲቲው ማስፋፊያ፣
ለልማት ስራዎች እና ለቴክኖሎጂ መስፋፊያ መሬት ጠይቆ በመረከብ እንተርፕራይዞችን
እንዲቋቋሙ ማድረግ ላይየዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንቶች መጫወት ያለባቸው ሚና ከፍተኛ መሆን
አለበት፡፡ አለበለዚያ ዩኒቨርሲቲው የሚያቋቁማቸው እንተርፕራይዞች ወደፊት ደካማና ትርፍ
አልባ ሊሆኑ እንደሚችሉ ነው፡፡
2. ለመማር ማስተማር፣ ለምርምርና ማህበረሰባዊ አገልግሎት የሚቋቋሙ ማእከላት ተጓዳኝ የገቢ
ምንጭ መሆናቸውን በመረዳት ጣምራ አላማዎችን እንዲያሳኩ አድርጎ መመስረት
እንዳለባቸው ነው፡፡
3. እስከ አሁን ከተገኘው ተሞክሮና ዩኒቨርሲቲው ካለው ተጨማሪ ሁኔታ አንፃር እንደ መደወላቡ
ዩኒቨርሲቲ ለመጀመሪያ ጊዜ በግብርና ልማት ዘርፍ ኢንተርፕራይዝ፤ በብረታብረትና እንጨት
ስራ ምርትና ጥገና ዘርፍ ኢንተርፕራዝ አስፈላጊው የአዋጭነት ጥናት ተደርጎና ፕሮጀክት
ተቀርጾለት ቢቋቋም የሚል ሃሳብ ኮሚቴው እስካሁን ከሰበሰበው ልምድ አንፃር አስቀምጠዋል፡፡
4. ዩኒቨርሲቲው እንተርፕራይዞችን በበላይ ሆኖ የሚያስተዳድር ቦርድ ማቋቋም እንዳለበት ነው፡፡
ኮሚቴው የተሻለ ብሎ የመረጠው የጅማ ዩኒቨርሲቲን ነው፡፡
5. ኢንተርፕራዞች የሚቋቋሙት የፍላጎት ጥናት ላይ ተመርኩዘው ትርፋማነታቸው በባለሙያዎች
ተጠንቶ ሲረጋገጥ መሆን እንዳለበት ነው፡፡
6. የገቢ ማመንጫ ዳይሬክቶሬት ስራን የሚመራ ቢያንስ ሁለተኛ ዲግሪ ያለው፣ ተነሳሽነት፣
ትእግስተኛ እና እልኸኛየሆነ እና ኢንተርፕራይዞችን ለማቋቋምልምድና ብቃት ያለው ባለሙያ
መሆን እንዳለበትነው፡፡ ይህ ካልሆነ ኢንተርፕራይዝ የማቋቋም ስራው አስቸጋሪመሆኑን ነው፡፡
7. እያንዳንዱን ኢንተርፕራይዝ የሚያስተዳድሩ ማናጀሮች በሚቋቋሙ እንተርፕራይዞች
መስክየመጀመሪያ ዲግሪና ከዚያ በላይ ያላቸው፣ፕሮጄክት የማዘጋጀት ልምድና ተነሳሽነት
ያላቸው ባለሙያዎች መሆን እንዳለባቸው ነው፡፡
8. በኢንተርፕራይዞች ለሚሰሩ ስራዎች የሚቀጠሩ ሰራተኞች አስፈላጊ ባለሙያዎችና የጉልበት
ሰራተኞች ብቻ መሆን እንዳለባቸውና ቅጥራቸው በኮንትራት ቢሆን የተሻለ መሆኑን ነው፡፡
አለበለዚያ እንተርፕራይዞቹ ላይ ኪሳራ ያመጣል፡፡
9. በዩኒቨርሲቲው የሚቋቋሙ ኢንተርፕራይዞች የራሳቸው መተዳደሪያ ደንብ፣ የራሳቸው
የፋይናንስ መመሪያና አስፈላጊ ሰነዶች ተዘጋጅቶላቸው የራሳቸውን አስተዳደር፣ ግዢ፣ ሽያጭና
ፋይናስ ኖሯቸው እንዲቀሳቀሱ ካልተደረገ ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት ስለማይችሉ
ተወዳዳሪና ትርፋማ መሆን እንደማይችሉነው፡፡
2
10. የልማትና ገቢ ማመንጫ ዳሬክቶሬት መሰረታዊ የአሰራር ሂደት ለውጥ ጥናት መሰራት
እንዳለበት ጥናቱ ካልተሰራ አሁን ያሉት ፋይዳ ቢስ አሰራሮች አይወገዱም እንዲሁም ሂደቱን
ያለበትን የአሰራር ክፍተት ማስተካከል እንደማይቻል ነው፡፡
11. በኢንተርፕራይዙ ያለው የሰው ሃይል ለኢንተርፕራይዙ ገቢ የሚያስገኙ ስራዎችን እንዲሰራ
ማነሳሳትና ጠንካራ ሰራተኞችን ሞራል በማበረታቻ መገንባት እንዳለበት ነው፡፡
12. ኢንተርፕራይዞች ሲቋቋሙ አከባቢው የሚገኙ ግብአቶች ከግንዛቤ ውስጥ ማስግባት
እንዳለባቸው ነው፡፡

3
2. ኢንተርፕራይዝ ምስረታ ላይ የሚሰሩ ስራዎችና የሚዘጋጁ ሰነዶች
ተቁ የሚሰሩ ስራዎች የሚከናወንበት ጊዜ የሚያከናውነው አካል
1 የልማትና ገቢ ማመንጫ የስራ ሂደት ጥናት ማካሄድ ህዳር ወር ኮሚቴው
2 የሂደቱን ጥናት ማፅደቅ የህዳር ወር መጨረሻ ሳምንት የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ካውን
3 የኢንተርፕራይዞች ቦርድ ማቋቋሚያ ሰነድ ማፅደቅ ህዳር ወር የዩኒቨርሲቲዉ አስተዳደር ካዉን
4 የኢንተርፕራይዞች ቦርድ ማቋቋሚያ ሰነድ ማፅደቅ ህዳር ወር ሶስተኛ ሳምንት የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ካውን
5 ቦርዱን ማቋቋም ሀዳር ወር አራተኛ ሳምንት ፕሬዝዳንቱ
6 አዋጭ የሆኑ እንተርፕራይዞች ጥናት ማካሄድና ዶክመንት ከህዳር 15-ታህሳሰ 27 ኮሚቴዉ
ማዘጋጀት
7 አዋጭ የሆኑ ኢንተርፕራይዞችን ማፅደቅ ታህሳስ ወር መጨረሻ ሳምንት ፕሬዝዳንቱ
8 የኢንተርፕራይዞች መተዳደሪያ ደንብ ማዘጋጀት ታህሳስ ወር ሶስተኛ ሳምንት የልማትና ገቢ ማመንጫ ዳይሬክ
9 የኢንተርፕራይዞች መተዳደሪያ ደንብ ማፅደቅ ታህሳስ የመጨረሻሳምንት ሳምንት ቦርዱ
10 ለሚቋቋሙ ኢንተርፕራይዞቹን የየራሳቸውን ስራስኪያጅ መመደብ ታህሳስ 30 ቦርዱ
11 ለኢንተርፕራይዞቹ ስራስኪያጆች ደብዳቤ መፃፍ ጥር 2 ፕሬዝዳንቱ
12 የግዢ እና የሽያጭ መመሪያ ማዘጋጀት ከታህሳስ 16- 25 ኮሚቴው
13 የፋይናንሰ አስተዳደር መመሪያ ማዘጋጀት ከታህሳስ 16- 25 ኮሚቴው
14 የሂሳብ ሰነዶች ቅፅ ማዘጋጀት ከታህሳስ 16- 25 ኮሚቴው
15 የተዘጋጁ መመሪያዎችን ማፅደቅ ታህሳስ 28 ቦርዱ
16 የሂሳብ ሰነዶች ማሳተም ጥር 5-15 የልማትና ገቢ ማመንጫ ዳይሬክ
17 የንብረት ቁጥር ሰነዶችን ማሳተም ጥር 5-15 የልማትና ገቢ ማመንጫ ዳይሬክ
18 የንግድ ፈቃድ ማውጣት ጥር 5-20 የልማትና ገቢ ማመንጫ ዳይሬክ
19 ቲን ቁጥር ማውጣት ጥር 20 -25 የልማትና ገቢ ማመንጫ ዳይሬክ
20 መነሻ ካፒታል መመደብ ጥር 28 ቦርዱ
21 ኢንተርፕራይዞችን በግብአት፣ በመሳሪያዎችና በሰው ሃይል እስከ ጥር 30 የልማትና ገቢ ማመንጫ ዳይሬክ
ማሟላት

You might also like