Professional Documents
Culture Documents
የጠለሃ መስጂድ ወጣቶች ጀመዓ ሹራ
የጠለሃ መስጂድ ወጣቶች ጀመዓ ሹራ
አሰላሙ ዓለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካትሁ ውድና የተከበራችሁ የጠለሃ መስጂድ ወጣቶች ጀመዓ ቋሚ አባላት በሙሉ
ዛሬ በነበረን ሹራ ላይ 12 አባላት የተገኙ ሲሆን ከሹራው ያለ በቂ ምክንያት ሰምተው የቀሩ ከሆኑ ይህ የቋሚ አባል፣
የጀመዓው ክንፍ የሆነ፣ እንዲሁም የጀመዓው መቋቋም እና መጠናከር ከሚያሳስበው አካል ፈፅሞ የሚጠበቅ አልነበረም፡፡
ይህ ተግባር ሃላፍትናን ከመዘንጋትና ለጉዳዩ ተትኩረት ባለመስጠት ስለሆነ ለቀጣይ ይህ እንዳይፈጠር መንቀቅ
ይኖርብናል፡፡ በከባድ ሀጃ ተወጥረውና ሀጃዎት ከሹራው በላይ አሳሳቢ ሆኖብዎት ባለመመቸት አልያም ሳይሰሙ ቀርተው
ከሆነ አላህ ባሰባችሁት(በኒያችሁ) ኸይር ምንዳችሁን ይከፍላችኋል፡፡ በእኛ ዘንድም ምንም ቅሬታ አይኖረንም፡፡
የዛሬው ሹራ የሚያጠነጥነው ጀመዓው በሁለት እግሩ የመቆም ህልውና ጋር የተያያዘ ሲሆን በቅድሚያ ለጀመዓው
የተጠናከረ መዋቅር እንዲኖረው በሹራው ላይ የተገኙት ሁሉም አባላት በአንድ ድምፅ በመስማማታቸው
መዋቅሩን በትቂቱ ለመንደፍ ተሞክሯል፡፡ በሹራው ለይ የተለያዩ ሀሳቦችን በማመንጨትና በማጤን መዋቅሩ እጅግ
የተጠናከረና ስር መሰረት ያለው እንዲሆን ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት ተደርጓል፡፡
ሆኖም 7 ዘርፎችን በማፅደቅ የእነርሱን የውስጥ ህግና ደንብ አብራርተው እንዲያቀርቡ ብቻ 7 ቡድኖች
ተዋቅረዋል፡፡ አንዱ ቡድን ላይም 2 ሰው ተመድቧል፡፡ በአጠቃላይ የተመደቡት 14 ሰዎች ናቸው እያንዳንዳቸው
ቡድኖች ይዘውት የሚመጡት የዘርፍ ህግጋት ማብራሪያ በፍላጎታቸው መሰረት ተሰጥቷቸዋል፡፡ ቀጣይ ቅዳሜ
ድረስ የጊዜ ገደብ የተሰጣቸው ሲሆን ቀጣይ ቅዳሜ ከዓሱር በኋላ በሚኖረው ሹራ ላይ ህግና ደንቡን ይዘው
እንዲቀርቡና ማብራሪያ ተሰጥቶበት የሚጨመረው ተጨምሮ የሚቀነሰውም ተቀንሶ መዋቅሩ እንዲጠናከር
በሚል ተጠናቋል፡፡ የተሰጣቸው የስራ ዘርፍና ተጠሪዎቹ እነዚህ ይሆናሉ፡-
አካዳሚክ ዘርፍ
- የጥናት ክፍል
- ምክር ሰጪ ክፍል
- የኮርስ ፕሮግራሞች አዘጋጅ ክፍል
የስፖርት ዘርፍ
- የጨዋታ ክፍል
- የሰውነት ማጠናከሪያ ክፍል
የንብረት ዘርፍ
- ቤተ-መፅሐፍት
- የዕቃ ግዢ ክፍል
- የሽያጭ ክፍል
- የግዢ ክፍል
መረዳጃ ዘርፍ
- የዚያራ ፕሮግራም
- የድጋፍ ዘርፍ
(ሚዕራጅ እና ዑመር)
የዳዕዋ ዘርፍ
- ቂርዓት ክፍል
- ሙሀደራ ክፍል
- ጽህፈት ቤት