You are on page 1of 1

‫جمعية الشباب المسجد طلحا في علم بانك‬

Teleha masjid’s Youth Jemaah of Alem bank


ቀን…………………

ቁጥር……………...

ለጠለሃ መስጂድ ቋሚ ኮሚቴ


አዲስ አበባ

ጉዳዩ፡- በጠለሃ መስጂድ ላይ የዳዕዋ ፕሮግራም ለማካሄድ ፍቃድ ስለመጠየቅ

እንደሚታወቀው የጠለሃ መስጂድ ወጣቶች ጀመዓ ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ ለ 13 አመታት እንደየ አመራሮቹ ለጀመዓው ጠቃሚ
የሆኑ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን ሲያከነናውን ቆይቷል፡፡ እንደ ፓምፕሌት፣ መፅሔት፣ የአዝካር ባነሮች፣ መፅሐፍቶች፣ የዚያራ ፕሮግራም፣
አቅመ ደካሞችን ማገዝ…ወ.ዘ.ተ ከመስጂዳችን የኺድማ እንቅስቃሴ አንፃርም ከመስጂድ ግቢ ፅዳት አንስቶ፣ ስፒከር ማስተካከል፣
የማብራት ስራዎችን ማከናወን፣ ምንጣፎችን ማጠብ… ለአብነት ያክል ተጠቃሽ ናቸው፡፡ በእነዚህም ተግባራት አንድም አኼራችንን
እየሸመትን አንድም ደግሞ የመስጂዳችንን ገፅታ እየቀየርን፣ ለጀመዓችን የዲን ግንዛቤን እያስጨበጥን በርካታ ወጣቶችን ወደ መስጂድ
ልንጠራ ችለናል፡፡

ስለሆነም ፕሮግራም ይዘን በተለይ ደግሞ ወጣቱን ለመገሰፅ በማሰብ ከበፊት ጀምሮ እሁድ ከዒሻ ሶላት በኋላ ያለውን 20 ደቂቃ
ለመጠቀም ፍላጎት ነበረን ያም ሆኖ ሳለ የመስጂድ ግንባታ፣ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትና መሰል እንከኖች ይዘውን ሀሳቡን ለመግፋት አዳጋች
ሆኖብን ቆይቷል፡፡ አሁን ግን መስጂዳችን በመገባደዱ፣ ጀመዓችንም ይበልጥ በመሰባሰቡና ወደ ቀድሞ እንቅስቃሴ በመገባቱ ይህንን ሰዓት
በዳዕዋ ለመጠቀም አስበናል ሰዓቱ ከየትኛውም ጀመዓ ፕሮግራም ጋር ቁርኝት የሌለው በመሆኑ ፍፁም ሰላማዊና ተደራሽ ያደርገዋል፡፡
ሰዓቱን አልፎ አልፎ የመስጂዳችን ኮሚቴ በሚፈልግበት ሰዓት የምንፈቅድ መሆኑንም ከወዲሁ ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡ ፕሮግራሙ ላይ
እንከኖች እንዳይፈጠሩ በመስጋት ከወዲሁ ያስቀመጥናቸው እና የምንከተላቸው ቅድመ አሰራር ህግጋትና መስፈርቶች አዘጋጅተናል፡፡
እነርሱም፡-

 በየሳምንቱ ለማህበረሰቡ እንዳይደጋገምና ሁሌም አዲስ ይሆን ዘንድ ዳዒዎቹ(ዓሊሞቹ) ይቀያየራሉ፡፡


 ዳዒዎቹ(ዓሎሞቹ) የሚመጡት አብዘሀኞቹ ከእኛው ሰፈር ካሉትና ከምናውቃቸው ዑስታዞች ብቻ ይሆናል፡፡ ይህም እንዲሆን
የመረጥነው ስህተት ሲኖር ለማረምም ሆነ ለመግባባት ቅርብ ስለሚሆን ነው
 የሚያቀርበው ርዕስ እኛ የሰጠነውን ብቻ ሲሆን የሚመጣው ዳዒ በኺላፍ እና አንጃ ከመፍጠር የፀዳ ይሆናል
 ርዕሶቹ ከኺላፍ፣ ከፖለቲካና ከመሰል ዘርፎች የፀዱ ሆነው ይዘጋጃሉ፡፡

ለአብነት ያክል ይህንን የጠቀስን ሲሆን በቢሮ ደረጃ ህግና ስርዓቱን ይበልጥ አጠናክረን እንቀርፀዋለን፡፡ በመሆኑም የመስጂዳችን
ኮሚቴ ለዳዕዋ ያለንን ተነሳሽነትና የዚህችን ሰዓት ነፃ መሆን ከግምት ውስጥ በማስገባት ይፈቀድልን ዘንድ በታላቁ አላህ (ሱ.ወ) ስም
ለመጠየቅ እንወዳለን፡፡

ለሚደረግልን ትብብር ሁሉ ምስጋናችን ላቅ ያለ ነው፡፡

ከሰላምታ ጋር
የጠለሃ መስጂድ ወጣቶች ጀመዓ

Tel:- 0949442792 / 0985342500 / 0919802716 Telegram Group:- የጠለሃ መስጂድ ወጣቶች ጀመዓ
Address:- ayer tena - Alembank teleha masjid Email:- Telehayouth14@gmail.com

You might also like