You are on page 1of 24

የወጣቶች የንቅናቄና የተሳትፎ ኮንፈረንስ 2010 ዓም

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት


ወጣቶችና ስፖርት ጉዳይ ቢሮ

የወጣቶች የንቅናቄና ተሳትፎ ኮንፈረንስን አስመልክቶ የተዘጋጀ ማስፈጸሚያ እቅድ

ሚያዝያ/2010 ዓ.ም
ደሴ
1. መግቢያ
አገራችን ከግብርና ወደ ኢንዱሰትሪ ለማሸጋገር የሚያስችል የኢኮኖሚ ፖሊሲ እና

ስትራቴጂዎችን በመንደፍ ፈጣን፣ ተከታታይና የህዝቡን የላቀ ተጠቃሚነት

ያረጋገጠ ዕድገት በማስመዝገብ መካከለኛ ገቢ ካለቸው ሀገሮች ተርታ ለመሰለፍ

ከፍተኛ ርብርብ በማድረግ ላይ ትገኛለች፡፡

በዚህ የኢኮኖሚ ልማት እንቅስቃሴ ውስጥ ከጠቅላላው የሀገራችን ህዝብ 30%

ገደማ የሚሸፍነውን አምራች ወጣት የህብረተሰብ ክፍል የእድገቱ ተሳታፊ እና

ተጠቃሚ መሆኑን ለማረጋገጥ ራሱን የቻለ የወጣቶች ፖሊሲ እና የልማትና

ለውጥ ፓኬጅ ተዘጋጅቶ ተግባራዊ ሲደረግ ቆይቷል፡፡


በዚህም ባለፉት አመታት የገጠር ወጣቶች ልማትና የዕድገት ፓኬጅን መሰረት በማድረግ የአገራችንም

ሆነ የክልላችን ወጣቶች ግብርናን ባማከሉ የሰብል ልማት፣ የእንስሳት እርባታ፣ የአትክልት እና ፍራፍሬ

ልማት፣ የተፈጥሮ ሀብት ልማት እና ጥበቃ እና ግብርና ነክ ባልሆኑ የስራ ዘርፎች በርካታ የስራ

እድሎችን በመፍጠር ኢኮኖሚያዊ አቅማቸውን ለማሳደግ ጥረት ተደርጓል፡፡

በከተማም ወጣቱ በጥቃቅንና አነስተኛ፣ በከተሞች ቤቶች ልማት ፕሮግራም፣ በከተማ ማስዋብ፣

በኢንዱስትሪና ንግድ ዘርፎች፣ በግል ክፍለ ኢኮኖሚ መስኮች በመሰማራት ተሳታፊና ተጠቃሚ

እንዲሆኑ አበረታች ስራዎች በመሰራታቸው የማይናቅ ቁጥር ያላቸው የከተማ ወጣቶች የራሳቸውን

ሃብትና ጥሪት ማፍራት ችለዋል፡፡

በማህበራዊና በፖለቲካ መስክም ከኢኮኖሚው መስክ ባልተናነሰ መልኩ አመርቂ ድሎች ተመዝግበዋል፡፡

ባለፈው አመትም ወጣቶችን ይበልጥ ተጠቃሚ ለማድረግ በፓኬጁ ተቀምጠው ተግባራዊ ያለሆኑና

ያልተካተቱ ጉዳዮችን አካቶ የወጣቶች ፖሊሲ፤ ስትራቴጅና የልማትና ለውጥ ፓኬጅ ተሸሽሎ

እንዲወጣ ተደርጓል፡፡
ይሁን እንጅ mNGST z¤¯cÜN blW_ ¯Ä lmM‰T ÆdrgW ytúµ _rT

wÈtÜM t«Ý¸ mçN XNdjmr ÆYµDM የወጣቱን ዘርፈ ብዙ ችግሮች፣ ፍላጎቶችና

ጥያቄዎችን ለመመለስ bmNGST çn bHBrtsB dr© ytkÂwnW S‰ በሚጠበቀው

መጠን አይደለም”

ይህም bwÈtÜ zND የ¸¬†ትን zRf Bzù CGéC ለመፍታት wÈtÜN ên¾ CGR fC

¦YL xDR¯ b¥NqúqS rgD yts‰W S‰ ym§ýN wÈT XRµ¬N çrUg«

ባለmçnù Ælፉት አመታት የተፈጠረው አለመረጋጋት ለአብነት የሚጠቀስ ነው””

SlçnM wÈtÜ xgR trµbþ S‰ wÄD z¤U XNÄþçN bS‰ f«‰ MNnT\

በሰላምና ሰላም አስፈላጊነት፤ በምክንያት ማመንና በምክንያት በመቃወም ዙርያ እንዲሁም

በልማትና በዲሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ እና ከመልካም ዜጋ ምን ይጠበቃል b¸lù gùÄ×C

GN²b¤ lmF«R ÃSCL zND YH XQD lþzUJ C§*L””


2. የእቅዱ መነሻ ሁኔታ
2.1. በክልላችን የንቅናቄ ኮንፈረንሱ አስፈላጊነት
አገራችን ኢትዮጵያ በመጀመሪያው ሚሌኒየምና እስከ ሁለተኛው ሚሌኒየም አጋማሽ ድረስ

በነበረችበት የስልጣኔ ደረጀ በአይነቷ ስሟ ገኖ ትታወቅ የነበረ ሲሆን በመጨረሻዎቹ 500 አመታት

ግን ለውድቀት ተዳርጋለች፡፡

አለም ረስቷት፣ እሷም አለምን ረስታ በድህነትና ኋላቀርነት የምትማቅቅ አገር ሆናለች፡፡

በስልጣኔ ወደኋላ የነበሩ አገሮች ቀድመዋት ሲሰለጥኑና ሲበለፅጉ ኢትዮጵያ ግን በአለም ያሉ

አገሮች ሁሉ ጭራ ሆና ድህነትና ኋላቀርነት መታወቂያዋ የሆነበት ደረጃ ላይ ደርሳ ነበር፡፡

አገሪቱ በኢኮኖሚያዊ ውድቀትና በዴሞክራሲ እጦት የመበታተንና እንደ አገር ያለመኖር

የመጨረሻው ደረጃ ላይ የደረሰችበት ሁኔታ ተፈጥሮ እንደነበር ይታወቃል፡፡

በዚህ ወቅትም ወጣቶች የሚፈለጉት ለልማት ስራ ሳይሆን ለጦርነትና ለገዥዎች አገልጋይነት


የደርግ መንግስት በዚያኞቹ ግፍና በደል ሲደርስባቸው በነበሩት ወጣቶች ትግል ከወደቀ በኋላ ባለፉት

ሁለት አስርት አመታት ግን አገሪቱ ከውድቀት አፋፍ ተመልሳ ወደ ዕድገት ማምራት ጀምራለች፡፡

የመበታተኑ ስጋት ተወግዶ ጠንካራ አንድነት በመገንባት ላይ ትገኛለች፡፡

ቀደምት ስልጣኔዋንና ገናና ስሟን የቀየረው ድህንትና ኋላቀርነት ቁራኛ ከበላይዋ እንዲላቀቅ

የሚያደርገው ምስ ተገኝቶለት መፈወስ ጀምራለች፡፡

ረስቷትና ረስታው ወደኖረችው የዕድገትና የስልጣኔ አለም ለመቀላቀል በሚያስችላት ጎዳና ገበታ ጉዞ

ጀምራለች፡፡

በአንድ ቃል የህዳሴ ጉዞ ጀምራለች፡፡

የተቀበልነው አዲሱ ሚሌኒየም በርግጥም የኢትዮጵያ ህዳሴ እውን የሚሆንበት፣ በመጀመሪያው

ሚሌኒየም እንደነበረው ሁሉ በአለም የተከበረችና በመልካም ስም የምትታወቅበት እንደሚሆን

ይታመናል፡፡
በተመሳሳይም ክልላችን የምትገኝበት ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ሁኔታዎችን ስናይ

በከፍተኛ ለውጥ ውስጥ ነን፡፡

በመሰረተ ልማት እንቅስቃሴ፤ በትምህርት፤ በጤና ከፍተኛ ለውጥ አስመዝግበናል ፡፡

በተለይ በስራ እድል ፈጠራም አያሌ ወጣቶች ከምንም ተነስተው በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ

ማፍራት ችለዋል፡፡

ይህ ደግሞ እንደ ሀገር ብሎም እንደ ክልል እየተመዘገበ ያለው ለውጥ አንድ አካል ነው፡፡

ይህ ለውጥ ደግሞ እየተመዘገበ የመጣው በልማታዊ ዲሞክራሲ መስመር ነው፡፡

በዚህም እኛ ወጣቶች ያደረግነው እልህ አስጨራሽ የልማትና የዲሞክራሲ ትግል ውጤት ነው፡፡

በዚህ ውጤትም ተጠቃሚወቹ እኛ ወጣቶች ነን፡፡

ባለፈው አመት ጀምሮም ከመቸውም ጊዜ በተለየ መልኩ የወጣቶችን ተጠቃሚነት እውን

ለማድረግ በየደረጃው በጀት ተመድቦ፤ የአሰራር መመሪያዎች ወጥተው ወደ ተግባር ገብተናል፡፡


ይሁን እንጅ በተለያዩ የጥፋት ሀይሎች ጠንሳሽነት ከ2008 አመት ጀምሮ የተቀጣጠለው አመጽ ሲጀምር አማራ

ተጨቆነ፤ ተበደለ፤ ተደፈረ ፤መሬቱን ተቀማ በሚል የተቀነባበረ ዜማ እንደ አረብ አገራት ብጥብጥ በመፍጠር

ህዝብንና መንግስትን፤አንዱን ሀይማኖት ከሌላው ሀይማኖት፤ አንዱን ብሄር ከሌላው ብሄር ጋር ሲያጋጩን ቆይተዋል፡፡

በዚህም የወጣቱንና የሀገራችንን እድገት ከመግታት ባሻገር የንጹሀን ወንድሞቻችን ህይወት አልፏል፤ አያሌ ንብረቶች

ጠፍተዋል፡፡

አያሌ ወጣቶችም ከስራ ገበታቸው ተፈናቅለው ይገኛሉ፡፡

አንዱ ክልል ወደ ሌላኛው ክልል በነጻነት የማይንቀሳቀስበት፤ ዘር እየተቆጠረ የሚጨፈጨፍበትና ሰላም ዉሎ ለማደር

የሚናፍቅበት ወቅት ማሳለፋችን የማይረሳ ነው፡፡

ስለሆነም ይህ እንቅስቃሴ አገራችን ድሮ ወደነበረችበት የጨለማና የድንቁርና ጉዞ እንድትመለስ የሚያመላከት

ቢሆንም መንግስት ከሀገራችን ህዝቦችና በተለይ ደግሞ ከወጣቱ የህብረተሰብ ክፍል ጋር በመሆን የአገራችን እድገት

ወደ ማይቀለበስበት ጎዳና እንዲያድግ አልሞ እየሰራ ነው፡፡

ለዚህ አላማ እውን ይሆን ዘንድ ወጣቶችን በሰላምና ሰላም አስፈላጊነት፤በምክንያት ማመንና በምክንያት በመቃወም

ዙርያ እንዲሁም በልማትና በዲሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ እና ከመልካም ዜጋ ምን ይጠበቃል በሚሉ ርእሰ ጉዳዮች

ዙርያ ለማወያየት ይህ እንደመነሻ ሁኔታ ተቀምጧል፡፡


2.2 የወጣቶች የሰላም፤ የልማት፤ የዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታና ምክንያታዊነት ያለበት ሁኔታ
ወጣቶች በሰላምና በዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ያላቸውን ተሳትፎ ለማሳደግ በተከናወኑት ተግባራት

በህገ-መንግስቱ የተቀመጠውን በነፃ የመደራጀት መርህን መሰረት በማድረግ የአገሪቱ ወጣቶች

በሚፈልጉት አደረጃጀት ጥላ ስር በመሆን


 ዲሞክራሲያዊ አመለካከቶቻቸውን እንዲያንፀባርቁ፣

 መብትና ጥቅማቸውን ህገ-መንግስቱ ባስቀመጠላቸው አግባብ መሰረት እንዲጠይቁ፣

 የወጣት አደረጃጀቶች እንዲፈጠሩና በወጣት አደረጃጀት ስር ታቅፈው የሚገኙ ወጣቶች መብትና

ጥቅማቸውን ለማስከበር በተቀናጀ አካኋን ጥያቄያቸውን እንዲያቀርቡና

 በአገሪቱ ከተፈጠረው የዲሞክራሲ ስርዓት ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚያግዙ የግንዛቤ ማስጨበጫ

ስራዎች በመሰራታቸው

 ለመብቱና ለጥቅሞቹ መሟገት የጀመረ፤ በሰላምና በኢትዮጵያዊ አንድነት የማይደራደር፤ በምክንያት

በማመንና በምክንያት በመቃወም ዙርያ የሚያምን ወጣት የህብረተሰብ ክፍል መፍጠር ተችሏል፡፡
የዲሞክራሲና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን በማከናወን ረገድ
o ወጣቶች ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብና አመለካከት እንዲኖራቸው

o በአገሪቱ በሚከናወኑ አገራዊ ምርጫዎች ውስጥ በአስመራጭነት፣ በመራጭነትና በታዛቢነት በመሳተፍ

o አልፎም በፌድራልና በክልል ደረጃ ባሉ ምክር ቤቶች ውስጥ በድምፅና ያለ ድምፅ በመሳተፍ የዲሞክራሲ መብቶቻቸውን

መጠቀም መጀመራቸውን በምርጥ ተሞክሮነት መውሰድ ይቻላል፡፡

ይሁን እንጂ የወጣት አደረጃጀቶችን ስንመለከት


 አባሎቻቸውን አደራጅተው በመብትና ጥቅሞቻቸው ዙሪያ በማንቀሳቀስ ረገድ ጥንካሬ አልባ መሆናቸው፤

 ባለድርሻ አካላትም የሚያደርጉላቸው ድጋፍ ውስን መሆን አደረጃጀቶቹ የሚፈለገውን ውጤት እንዳያስመዘግቡ መንስኤ

ሆኗል፡፡

 ይህም በመሆኑ ወጣት አደረጃጀቶች በመንግስት ላይ ጥገኛ እንዲሆኑ አልፎም አብዛኛውን ወጣት በአደረጃጀቶች እንዲታቀፉ

ማድረግ እንዳይችሉ ከማድረጉም በላይ

 በወጣት አደረጃጀቶችና በመንግሰት መካከል ያለው ቅንጅታዊ አሰራር ደካማ እንዲሆንና

 በአደረጃጀቶቹ በኩል የሚከናወኑ ተግባራት በሚፈለገውና በሚጠበቀው ደረጃ እንደይሆኑ ምክንያት ሆኗል፡፡
ይህ በመሆኑ ፡-

 የክላላችን ወጣቶች ተከታታይና ቀጣይነት ባለው ሁናቴ በሰላም፤ በልማት፤ በምክንያታዊነት፤

በዲሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ ዙርያ በአደረጃጀታቸውም ሆነ በመንግስት በኩል ቀጣይነት ያለው

ውይይት ስለማይደረግ የግልጽነት መጓደል ይስተዋላል፡

 በዚህም የተነሳ ወጣቶች ባለፉት ሁለት አመታት ለሁከትና ብጥብጥ ተዳርገዋል፤ለህይወት መጥፋትና

ለአካል ጉዳተኝነት ተጋልጠዋል፤ ለንብረት መውደምና የሀገራችን ገጽታ ጥላሸት ላይ ወድቋል፡፡

 በሌላ በኩል ወጣቶች ስለራሳቸው መብትና ግዴታ ማሰብና ማሰላሰል ያለባቸው ራሳቸው መሆኑ

እየታወቀ አንዳንዶቹ በበሬ ወለደ ወሬ መታለልና መተራመስ፤ በሰለም ሰርቶ ከመኖር ለሁከትና

ብጥብጥ መዳረግ፤ ሰርቶ ከማደግ ይልቅ አንጋጦ የመጠበቅ ፤

 በምክንያት ከመደገፍና ከመቃወም በጭፍን የመቃወምና የመደገፍ ሁኔታዎች ስላሉ በቀጣይ ልዩ

ትኩረት ሰተን ልንሰራቸው ይገባል፡፡


3. የእቅዱ አላማ፤-
በየደረጃው ያለውን መዋቅራችን፤ የወጣቶች አደረጃጀትና መላ ወጣቶችን በሰላምና ሰላም አስፈላጊነት፤

በምክንያት ማመንና በምክንያት በመቃወም ዙርያ እንዲሁም በልማትና በዲሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ

እና ከመልካም ዜጋ ምን ይጠበቃል በሚሉ አጀንዳዎች ዙርያ መግባባት ላይ መድረስ፤

4.የእቅዱ ግቦች፤
የክልላችን የወጣቶች አደረጃጀት አመራርና አባላትን እንዲሁም መላ ወጣቶችን በሰላምና ሰላም

አስፈላጊነት፤ በምክንያት ማመንና በምክንያት በመቃወም ዙርያ ግንዛቤ በመፍጠር የወጣቶችን ስብእና

መገንባት፤

በልማትና በዲሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ ዙርያ በመግባባት ከወጣቱ ወይም ከመልካም ዜጋ

የሚጠበቀውን አስተዋጽኦ ለራሳቸው፤ ለማህበረሰቡና ለክልላቸው ማበርከት እንዲችሉ የተሟላ ግንዛቤ

መፍጠር ፤
5. አበይት ተግባራት

ወጣቶችን
በሰላምና ሰላም አስፈላጊነት፤

በምክንያት ማመንና በምክንያት በመቃወም ዙርያ

እንዲሁም በልማትና በዲሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ እና ከመልካም ዜጋ

ምን ይጠበቃል በሚሉ አጀንዳዎች ዙርያ በዞንና በሜትሮፖሊታንት ከተሞች

ደረጃ አቅማቸውን ሊገነባ የሚችል የንቅናቄ ኮንፈረንስ ማካሄድ፣


6. የሚከናወኑ ዝርዝር ተግባራት

6.1 ኮንፈረንስ ማካሄድ

6.1.1 በክልል ደረጃ የወጣቶችን አቅም ሊገነባ የሚችል የንቅናቄ ኮንፈረንስ ማካሄድ
 በክልል ደረጃ በግንቦት ወር አጋማሽ የወጣቶች የንቅናቄ ኮንፈረንስ በባህርዳር ከተማ ይካሄዳል፡፡

 በውይይቱም ከሁሉም ዞኖች፤ ከተማ አስተዳደሮችና ወረዳዎች የተውጣጡ 1000 ወጣቶችን ያሳትፋል፡፡

 የውይይቱ ጊዜ 2 ቀናት የሚወስድ ሲሆን

 በመጀመርያው ቀን ጠዋት ወጣቶችን በሰላምና ሰላም አስፈላጊነት፤በምክንያት ማመንና በምክንያት በመቃወም

ዙርያ እንዲሁም በልማትና በዲሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ እና ከመልካም ዜጋ ምን ይጠበቃል በሚሉ

አጀንዳዎች ሰነድ ይቀርባል፡፡ ከሰአት በኋላ በቀረበው ሰነድ ላይ ውይይት የሚካሄድ ይሆናል፡፡

 በሁለተኛው ቀን ከሰአት በፊት ከተሳታፊዎች ለክቡር ርእሰ መስተዳድሩ የሚነሱ ጥያቄዎች ቀርበው ምላሽ

እንዲሰጥ ይደረጋል፡፡ ከሰአት በኋላ በአጀንዳዎቹ ዙርያ የሞዴል ወጣቶች ተሞክሮ ለተሳታፊው እንዲቀርብ

ይደረጋል፡፡ለተሳታፊዎች የአበልና የትራንስፖርት የሚሸፈነውን ወጭ የመስተዳድሩ ምክር ቤት የሚሸፍን


6.1.2 በሁሉም ዞንና በሜትሮፖሊታንት ከተሞች ደረጃ የወጣቶችን አቅም ሊገነባ የሚችል የንቅናቄ ኮንፈረንስ
ማካሄድ
ወጣቶችን

 በሰላምና ሰላም አስፈላጊነት፤

 በምክንያት ማመንና በምክንያት በመቃወም ዙርያ

 እንዲሁም በልማትና በዲሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ እና ከመልካም ዜጋ ምን ይጠበቃልና

 የስራ እድል ፈጠራ በሚሉ ርእሰ ጉዳይ በዋናነት በ3ቱ ሜትሮፖሊታንት ከተሞችና በ12 ዞኖች

ኮንፈረንስ በማካሄድ የወጣቶችን የኢኮኖሚ ተጠቃሚነትና የፖለቲካ ግንዛቤያቸውን

ማሳደግና ማዳበር ይገባናል፡፡

 ስለሆነም በክልላችን የስራ ፈላጊዎችን ችግር ለመፍታት መመርያ እስከማውጣትና

የወጣቶችን ተጠቃሚነት ለማጎልበት የተሰራውን ስራ በማሳወቅ በነሲብ ስራ የሌላቸው


 በመጨረሻም ይህ ኮንፈረንስ በሜትሮፖሊታንት ከተሞችም ሆነ በዞን ደረጃ ከሁሉም

ወረዳወችና ቀበሌወች የተወጣጡ እስከ 1 ሽህ የሚሆኑ

 የወጣቶች አደረጃጀት አመራርና አባላት፤

 ግንባር ቀደምና ሀብት የፈጠሩ ወጣቶች፤

 ተጽእኖ ፈጣሪ ወጣቶችና

 ስራ ፈላጊ ወጣቶችን የሚያካት ሆኖ ይካሄዳል፡፡

 በዞን ደረጃ የሚካሄደው ኮንፈረንስ ለሁለት ቀን ብቻ የሚቆይ ይሆናል፡፡

 ሌላው ጉዳይ ስልጠናው/መድረኩ በክልሉና ዞኑ ከፍተኛ አመራሮች የሚሰጥ ስለሆነ ልዩ

ትኩረት አድርገን መንቀሳቀስ ይኖርብናል፡፡

 እንደተለመደው ለስልጠናው/ለመድረኩ የሚያስፈልጉትን ማንኛውንም ወጭዎች የዞንና


7.የአፈጻጸም አቅጣጫዎች

7.1. የማወያያ ፅሁፍ ዝግጅት


 የኮንፈረንሱ አጀንዳ በዋናነት ወጣቶችን በሰላምና ሰላም አስፈላጊነት፤በምክንያት ማመንና በምክንያት

በመቃወም ዙርያ፤ በልማትና በዲሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ፤ የስራ እድል ፈጠራና በመልካም ዜጋ

ምንነት /What is Good Citizen/ በሚል ርእስ ይሆናል፡፡

 ስለሆነም የስልጠናው ሰነዱ በክልሉ ወጣቶችና ስፖርት ጉዳይ ቢሮ አማካኝነት ተዘጋጅቶ የሚቀርብ ሲሆን

በዋናነት በ3ቱ ከተሞችና በዞን ደረጃ ለሚካሄዱ ውይይቶች ይውላል፡፡

7.2 ኮንፈረንሱን የሚያስተባብር ኮሚቴ ማደራጀት


 ይህ ተግባር ሊፈፀም ከሆነ ሥራው በተደራጀ መንገድ በዕቅድ ሊመራ ይገባዋል፡፡

 በዚህም መሠረት ኮንፈረንሱን የሚመራ ኮሚቴ በየደረጃው ያለው የብአዴን ጽ/ቤት፤ ከወጣቶችና

ስፖርት ጉዳይ መዋቅርና ከወጣቶች አደረጃጀት የሠው ሃይል ተመድቦ ማስተባበር

ይጠበቅበታል፡፡
7.3 የመድረክ መሪና የተሳታፊ ምልመላ ስራን በተመለከተ

ከላይ እንደተገለፀው ፡-

 ይህ ኮንፈረንስ የሚሠጠው ለወጣቶች አደረጃጀት አመራርና አባላት፤ ሀብት ለፈጠሩ ወጣቶች፤

ተጽእኖ ፈጣሪና ስራፈላጊ ወጣቶች ሲሆን በኮንፈረንሱ የተሻለ የአመለካከት ሥርዓት አግኝተው

ለቀጣይ ተልዕኮ የሚዘጋጁበት ነው፡፡

 ስለሆነም በየደረጃው ለሚካሂደው ኮንፈረንስ ብቁ ዝግጅት አድርገው ሥልጠናው የሚፈለግበትን

ውጤት እንዲያመጣ የሚመሩ አመራሮች መመልመል ይጠበቅብናል፡፡

 በዋናነት በዩኒቨርስቲ ምሁራንና በከፍተኛ ሀላፊዎች የሚቀርብ ይሆናል፡፡

 በተጨማሪም በኮንፈረንሱ የሚሣተፉ ወጣቶችን በአግባቡና በጥንቃቄ ምልመላ በማካሄድ

በሥልጠናው ተሣትፈው የሚሠጣቸውን ተልዕኮ የሚወጡትን በመመልመል ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራ

ይገባዋል፡፡
7.4 የሚያጋጥሙ ችግሮችና ሊወሰዱ የሚገባ የመፍትሄ ሃሳቦች፣

7.4.1. ችግሮች፡
 ይህን ተግባር አሳንሶ በመመልከት የተለመደ የግብር ይውጣ ስምሪት የሚካሄድ ችግር

ሊያጋጥም ይችላል፣
 ብቁ የሰው ሃይል መድቦ ተግባሩን ያለመከታተልና

 ስራውን ወጣቶችና ስፖርት አመራሮችና አስተባባሪዎች ብቻ እንዲከታተሉ አሳልፎ

መስጠት ችግር ሊያጋጥም ይችላል፣


 የፋይናንስና ለኮንፈረንሱ የሚያስፈልግ ሎጀስቲክስ እጥረት ሊያጋጥም ችላል፣

 የስራ መደራረብ ችግር ተግበሩን በተቀመጠለት ጊዜ እንዳይፈጸም አስተዋጽኦ ሊኖረው

ይችላል፣
7.4.2. የመፍትሄ ሃሣቦች
 ይህ ተግባር አብዛኛውን የህበረተሰብ ክፍል የምናንቀሳቅስበት ትልቅ ተግባር ነው፣

 ከዚህም በተጨማሪ ድርጅታችን የሚያካሂዳቸው የልማትና የመልካም አስተዳደር ሊሳኩ የሚችሉት አበዛኛውን

የህዝብ ቁጥር የያዙት ወጣቶችና ሴቶችን ተጠቃሚነት እስከ አረጋገጡ ደረስ ነው፡፡

 ስለሆንም የሚያሰራ እቅድ በማዘጋጀት ለተግባሩ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ መንቀሳቀስ በየደረጃው ካለው አመራር

ከፍተኛ ሃለፊነት ይጠበቃል፡፡

 ከላይ እንደተገለጸው ወጣቶችን በአግባቡ አንቀሳቅሶ ልማት ማምጣት የሃገራችንን የወደፊት እድል ይወስናል፡፡

 ለዚህ ደግሞ አብዮታዊ ዲሞከራሲያዊ መስመራችን ታሪካዊ ሃላፊንቱን በመውሰድ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡

 ይህም የሚሳካው ወጣቶችን በሰላምና በምክንያታዊነት ዙርያ በግንባር ቀደም መሪነት ማንቀሳቀስ ሲቻል ነዉ፤

 ስለሆነም በዚሀ አመት በወጣቶች ደረጃ የምንፈጥረው መድረክ መላ ወጣቶችን በማነቃነቅ ቀሪ ጊዜያት የእድገትና

ትራንስፎረሜሽን ዕቅዳችን ከማሳካት አንጻር መታየት አለበት፡፡


 ስለሆነም በዚህ መድረክ በቁ አመራር ተመድቦ ንቅናቄውን መምራት እንደሚገባ በጥብቅ ልንገነዘብ

ይገባል፤

 የፋይናንስና የሎጀስቲክስ እጥረት ይህን ስልጠና በተለይም በክልል ደረጃ የሚካሄደውን መድረክ

ለመፈጸም እንደ ችግር የሚታይ ቢሆንም የክልሉ አመራር ተግባሩ የክልላችን ልማት ከማፋጠንና መላ

ህዝቡን ከማንቀሳቀስ አንጻር ባለዉ ፋይዳ በጀት አንደሚመድብ ይጠበቃል፡፡

 ከዚህም በተጨማሪ ልዩ ልዩ የስፖንሰር-ሽፕ የድጋፍ አማራጮችን ማስብና መጠቀም ይገባል፡፡

 በዞን ደረጃ ለሚካሄዱ መድረኮችም አመራሩ አማራጮችን በማፈላለግ እንደሚፈጽማቸው ይጠበቃል፤

 በያዝነው አመት በርካታ የድርጅትና መንግስት ትግባራት የሚፈጸሙበት እንደሆነ ይታወቃል፡፤

 ስለሆነም ወጣቶችን በሰላም አስፈላጊነትና ምክንያታዊነት ዙርያ ያለንን አቅም ውጤታማ በሆነ

መንገድ ለመጠቀም አቅዶና የስራ ክፍፍል በማድረግ ውጤት የሚያመጣ በመሆኑ ጠንካራ የክትትልና

ድጋፍ ስርአት ዘርግቶ ስራዎችን በተልዕኮ ክፍፍል ላይ ተመስርቶ መፈጸም ይገባል፡፡


8. የኮንፈረንሱ የጊዜ ሰሌዳ
በክልል ደረጃ ……ግንቦት ወር መጨረሻ ባሉት ጊዜያት

በዞን ደረጃ…………ከሚያዝያ ወር መጀመርያ - ግንቦት ወር


አጋማሽ ባሉት ጊዜያት
# በወጣቶች የነቃ ተሳትፎና ተጠቃሚነት የክልላችን
ልማት ዕውን ይሆናል!! ;

አመሰግናለሁ !!

You might also like