Professional Documents
Culture Documents
2015 . . . 10
2015 . . . 10
ግንቦት/2015 ዓ.ም
ወራቤ
0
መግቢያ
ፓርቲያችን ብልጽግና ባለፉት የለውጥ ዓመታት የኢትዮጵያን ከፍታ ለማሳደግና ብልጽግናን ለማረጋገጥ በኢኮኖሚያዊ፣
በማህበራዊና በፓለቲካዊ ጉዳዮች በርካታ ተግባራትን ማከናወን የቻለ ፓርቲ ነው፡፡ የሀገራችን ወቅታዊ ሁኔታ
እንደሚታወቀው በውጫዊና ውስጣዊ ተግዳሮቶች ውስጥ ሆነን ፓርቲው ለቀጣይ ሥራችን መሠረት የሚሆኑ ስኬቶችን
ማስመዝገብ ተችሏል፡፡
የፓርቲያችንን ጉባኤ ተከትሎ በየደረጃው ህዝቡ ያነሳቸውን የመልማት፣ የመልካም አስተዳደር፣ የሰላምና ደህንነት፣ ሥራ አጥነትና
ኑሮ ውድነት እንዲሁም በአግልግሎት አሰጣጥ ያሉ ጉድለቶችን ለማረምና የህዝብ እርካታ ከፍ ለማድረግ የተነሱ ጉዳዮች
በአጭር፣ በመካከለኛና በረጅም ጊዜ ምላሽ እንዲያገኙ ለማድረግ ትግል እየተደረገ ይገኛል፡፡ በዋናነት ፓርቲን የማጠናከርና
ተቋማዊ አሰራርን መትከል አንኳር ተደርጎ ተወስዷል፡፡
ያለፈውን ዓመት የፓርቲና የመንግስት ዋና ዋና ግቦች አፈፃፀም ግምገማ እንደ መነሻ በመውሰድ የ 2015 ዓ/ም ዕቅድ በማቀድ
ከዞን እስከ ታችኛው መዋቅር ፈፃሚን የማዘጋጀት ስራ ተሰርቶ ወደ ተግባር ተገብቷል፡፡ የፓርቲ አመራርና አባላት
የማጥራት፣ የበቅቶ ማብቃት፣ ጠንካራ ተቋማዊ አደረጃጀት በመፍጠርና በማጠናከር ላይ ትኩረት ያደረገ እቅድ በማቀድ በሁሉም
ተቋማት ደረጃ አደረጃጀቶችን እየፈተሹና እያጠናከሩ ወደ ተግባር ማስገባት፣ፓርቲውን ወደ ፊት ሊያራምዱ የሚችሉ
ወይም ለፓርቲው እሴት የሚጨምሩ ወጣቶች፣ ሴቶችና ምሁራን ላይ ትኩረት በማድረግ አዳዲስ አባላት ምልመላ አሰራርን
በጠበቀ መልኩ መተግበር፤ የፓርቲ ተግባራት በህገ ደንቡ መሰረት እንዲፈጸም ትግል በማድረግ፣ ወደ መረጃ ቋት ያልገቡ አባላትን
ወደ መረጃ ቋት የማስገባት ተግባራት ሁሉንም ተግባራት በጊዜ የለንም መንፈስ የመፈፀም ተግባር ተጠናክሮ እንዲቀጥል
ጠንካራ ክትትልና ድጋፍ ተደርጓል፡፡
በንቅናቄ መፈፀም ያለባቸውን ተግባራት ለይቶ ርብርብ በማድረግ አመራራችንና አባሉ በፓርቲ የሚቀመጡ አቅጣጫዎችን
በመቀበል ዘርፈ ብዙ ስኬቶችን ጠብቆ በማስቀጠልና ጉድለቶችን ያለምህረት በማረም በህዝብ የተነሱ አንገብጋቢ ጥያቄዎችን
መመለስ በሚያስችል ሁኔታ ጠንካራ የፓርቲ አደረጃጀት በመፍጠር የአስተሳሰብና የተግባር አንድነትን በመገንባት ተግባራት
የመፈጸም አቅማችን በማሳደግ ብልፅግናችንን እውን ለማድረግ ከመቼውም ጊዜ በላይ ወሳኝ ወቅት ላይ እንገኛለን፡፡
በዚህ ዓመት እንደ ሀገር የተጋረጡብንን ፈተናዎች በጽናትና በብስለት ተቋቁመን በአዲስ መልክ በፓርቲያችን እየመነጩ
የሚቀርቡና የህዝቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ሊያረጋግጡ የሚችሉ አዳዲስ እሳቤዎችን አረንገዴ አሻራ፣ የሌማት
ትሩፋት፣‹‹በደም የተከበረ በላብ የታሰረ›› ወዘተ ከፍተኛ ሀገራዊ ንቅናቄዎች የመምራት፤ የዞናችን ህዝብ የጠየቀውን የአደረጃጀት
ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት በዲሲፕሊን በመምራት ውጤታማ ለማድረግና ተቆጥሮ በተሰጠው ተግባር ልክ በአዲሱ የአመራር ምዘና
መመርያ መሰረት የመመዘን ስራ ያለ ጠንካራ ፓርቲና ተቋማዊ አሰራር ሊሳካ የማይቻል በመሆኑ በየደረጃው ያለውን የፓርቲ
መዋቅር በሱፐርቪዥን የማጠናከር ተግባራት ተከናውኗል፡፡
1
በሂደቱ በየደረጃው ተጨባጭ ውጤቶች የታዩ ቢሆንም ከተግባር ተግባር እና ከመዋቅር መዋቅር የአፈፃፀም ልዩነቶች
ተስተውሏል፡፡ በመሆኑም ያለፈው የዘጠኝ ወራት የዕቅድ አፈፃፀም እና የፈዴራል እና የዞን ሱፐርቪዥን ቡድን ምልከታ ሪፖርት
በማመጋገብ ጥንካሬዎችን ይበልጥ በማጠናከር እና ጉድለቶችን ፈጥኖ በማረም ፓርቲን በየደረጃው ለመትከል በሚያስችል
በጥንካሬ
ከፍተኛ አመራሩ የተግባርና የአስተሳሰብ አንድነቱ ይበልጥ ተጠናክሮ በመሔዱ በሀገራዊ፣በክልላዊና በዞናዊ የተለያዩ
አጀንዳዎች ላይ የጋራ አቋም በመያዝ በቀላሉ እያሳካን የመጣንበት
በየደረጀው የሚገኘውን የአመራራችን ጤናማነት ነባራዊ ሁኔታ በየወቅቱ እገመገሙ በመሄድና በተለዩ ጉድለቶች
የተመሰረተ የተሻለ ድጋፍ ለታችኛው መዋቅር የተደረገበት
በየደረጃው የፓርቲና የመንግስት ሥራዎች ተቀናጅተው እንዲመሩ በማድረግ በተለያዩ የማታገያ አጀንዳዎች
በተለይም በመደበኛና በበጋ መስኖ ስንዴ፣በሌማት ቱርፋት፣በምርት አሰባሰብ፣በመከላከያ ሠራዊት ድጋፍ፣ በስራ ዕድል
ፈጠራ፣ በገቢ አሰባሰብ፣ በትምህርት ሥራዎች፣ በከተማ ንቅናቄ ሥራዎች፣ በአደረጃጀት እና በሌሎች ተግባራትም
እያደረገ ያለው ጥረት፣
የህዝባችንን የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ የገጠሩንና የከተማውን ህዝባችንን በማነቃነቅ
በትምህርት፣ በጤና፣ በመንገድ፣ በውሀ፣ በማብራት፣ በሀገር-ህልውና፣ በስፖርትና በሌሎችም መስኮች በበርካታ መዋቅርች
ለተሞክሮ የሚሆኑ ስራዎች የተሰራበትና ተግባሩን በቅርብ ርቀት ድጋፍ የተደረገበት
በበጀት ዓመቱ መጀመሪያ አጠቃላይ የፓርቲና የመንግስት ዋና ዋና ተግባራት ዕቅድ አፈፃፀም በመገምገምና በ2015 በጀት
ዓመት መከናወን ያለባቸውን የፓርቲና የመንግስት ዋና ዋና አቅጣጫዎችን በተደራጀና በተቀናጀ መልኩ የፈጻሚ ዝግጅት
መድረኮች እስከታችኛው መዋቅር ድረስ በትግል ማሳካት የተቻለበት፣
በጉድለት
በየወቅቱ በተለያየ መንገድ የሚነሱ ጉድለቶችን ለአብነት የገጠመንን ሀገራዊ የግብዓት እጥረት፣ በሸገር
2
ከተማ የቤቶች መፍረስ ዙሪያ እና የዞኑ ሚና፣ የፕሮጀክቶች አፈፃፀም እና እየገጠመን ያለው ሀገራዊ
ሁኔታ አለማቀፋዊ ይዘት ያለው የኑሮ ውድነት ችግር ወዘተ… ሰነድ እያዘጋጁ በየደረጃው ካለው
አመራር፣ አባል እና ሕዝብ እየተግባቡ የመሄድ ውስንነት መኖሩ፤
ለስራ አጥ ወጣቱ ፋይናንስ ለማቅረብ ምንጭ የሆነውን ቁጠባና ብድር የማስመለስ ስራው ላይ
እንደመሪ በመራነው ያክል የሚፈለገውን ለውጥ ማምጣት አለመቻሉን
ሁሉ-አቀፍ ድጋፍ ከመስጠትና ፈጣንና ቀልጠፋ አገልግሎት ከመስጠት አንፃር መሻሻሎች ያሉ ቢሆንም አሁንም
አመራሩ ከችግር ሙሉ በሙሉ ያልወጣ መሆኑን፣
የሴክተርና የንቅናቄ ተግባራትን እንዲሁም ወቅታዊና መደበኛ የፓርቲና የመንግስት ስራዎችን አደራጅቶና አቀናጅቶ
ከመምራት ይልቅ አሁንም በወቅታዊ ተግባራት ላይ ብቻ የመንጠልጠል ድክመት፣
አመራሩ ባለቤት ሆኖ ሌብነትን እና ብልሹ አሰራርን ከመታገል አንፃር በከተማ መሬት፣በገጠር የወል
መሬት፣ በተለያዩ መዋጮዎች በደረሰኝ አሰባሰብ፣ በገቢ ፣በፋይናንስ ግዢ እና ኮን/ት አስተዳደር እና
በአገልግሎት አሰጣጥ ጉድለት ወዘተ እየተስተዋሉ ያሉ ጉድለቶች መታየታቸው፣/ሁሉም መዋቅር
ከስነ ምግባር አንፃር በሶሻል ሚዲያ በዩቲዩብ እና ቲክቶክ በተደራጁና አፍራሽ ኃይሎች በፓርቲያችን
በሚነዙት ፕሮፖጋንዳ እና በሚራገቡ አሉባልታዎች ላይ ብዥታ ውስጥ የመግባት፣ ስልክ የመዝጋት፣
ከማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም አንፃር ቀጣይነት ያለው ጠንካራ የማጥቃትና የመመከት ሥራ አሁንም የቤት ሥራ
ሆኖ መቆየቱ፣ሁሉም መዋቅር
የተጀማመሩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ሥራዎች በተለይም ገበያን ለማረጋጋት በሁሉም ከተሞች
የተጀመረውን የቅዳሜ፣የእህድ፣የሰኞ በሁሉም መዋቅር ተመሳሳይ ደረጃ አለማድረስና ከማጠናከር አንፃር
አሁንም ጉድለት ያለ መሆኑ፣
ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ከመስጠትና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በቋሚነት የሚታዩ ችግሮችን እየፈቱ
የመሄድ እጥረቶች መኖር፤
3
በጥንካሬ
ከላይ በሚወርድ ዕቅድና አቅጣጫ መሠረት መከናወን ያለባቸውን አንኳር የፓርቲና የመንግስት ተግባራትን በመለየት
አቅዶ ለማሳካት መካከለኛ አመራሩ እያደረገ ያለው ጥረት፣
በዋና ዋና የፓርቲና ንቅናቄ ተግባራት በተለይም በመደበኛና በበጋ መስኖ ስንዴ፣በሌማት ቱርፋት፣በተቀነጀ
ተፋሰስ ልማት፣ በሥራ ዕድል ፈጠራ፣ በገቢ አሰባሰብ፣ በጤናና ትምህርት ሥራዎች እንዲሁም በከተማ ንቅናቄ
ሥራዎች እና በሌሎች ተግባራት የመካከለኛ አመራሩ ሚና ከፍተኛ የሆነበት፣
በአጠቃላይ ሲታይ ግን የታቀዱ የመንግስትና የፓርቲ ሥራዎችን ለማሳካት የሚደረገው የአመራሩ ዝግጁነት ከጊዜ ወደ
ጊዜ እየተሻሻለና እያደገ የመጣበት ሁኔታ መኖሩ፣
በጉድለት
ቁጥሩ ቀላል ያልሆነ አመራር አሁንም የልምድና የተሞክሮ እንዲሁም የውጤታማነት እጥረት የሚታይበት መሆኑ፣
የፓርቲውን መርሆዎችና እሴቶች በሚገባ ጨብጦ ዕለት ተለት ለተግባራዊነቱ ርብርብ በማድረግ የተዛቡ
አመለካከቶችን ታግሎ ከማስተካከል አንፃር አሁንም የተጠናከረ የግንባታ ሥራ የሚያስፈልገው መሆኑ፣
የሴክተርና የዘመቻ ሥራን አቀናጅቶ ውጤታማ አድርጎ ከመምራትም አንፃር ጉድለት ያለበት መሆኑ፣
የሚመራዉን መዋቅር ነባራዊ ሁኔታ በዝርዝር ገምግሞ የተደራጀና የተገመገመ ሪፖርት በወቅቱ ከማቅረብ አንፃር
ውስንነት ያለበት መሆኑ፣
4
በየተቋማቱ ያለውን የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለይቶ በአጭር፣ በመካከለኛና በረዥም ጊዜ አቅዶ በለውጥ
አመራር ማዕቀፍ ውስጥ በመሆን ለላቀ ውጤታማነት ተቀናጅቶ ከመስራት አንፃርም ጉድለት እንዳለበት
ተገምግሟል፡፡
ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት ከመስጠት አንፃር አሁንም የሚፈለገውን ቁመና በሚገባ ያለመላበስ፣ በትንሽ ውጤት
የመርካት፣
ሐ/ የመሠረታዊ ድርጅትና የህዋስ አመራር ሁኔታ
በጥንካሬ
አብዛኛው መሠረታዊ ድርጅት በተቀመጠዉ የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ዉይይት እያደረገ መሆኑ፣
በጉድለት
የታችኛው አመራራችን የትምህርትና የግንዛቤ ደረጃዉ ከሌላዉ የአመራር እርከን በአንፃራዊነት ዝቅተኛ ከመሆኑ ጋር
ተያይዞ ወቅታዊ መረጃዎችን በሚገባ አደራጅቶ መዋቅሩን በሚገባው ልክ ከማንቀሳቀስ አንፃር ጉድለት መታየቱ፣
በአንዳንድ በከተሞች ሆነ በወረዳዎች የሚስተዋለውን የህገ-ወጥ ግንባታና መሬት ወረራ ከመከላከል ይልቅ
የጉዳዩ ተባባሪ ሆኖ የመገኘት፣/በአብዘኛው መዋቅሮች/
5
የልማትና መልካም አስተዳደር ጥያቄዎች ሙሉ በሙሉ በላይኛው መዋቅር ብቻ እንደሚፈታ መጠበቅ፣አልፎ አልፎ
ከህዝበኝነት አባዜ ያለመላቀቅ ሁኔታ መታየት፣
በመደበኛነት መሠረታዊ ድርጅቶችና ህዋሳት በተግባር አፈፃፀም መነሻ ለመሠረታዊ ድርጅትና ህዋስ አመራሮች
እንዲሁም ለአባላት የደረጃ ምዘና በየወቅቱ እየሰጡ አለመሄድና የማሳወቅ ድክመት፣
መ/ የአባላችን ሁኔታ
በጥንካሬ
በፓርቲና መንግስት የሚወርዱና የሚቀመጡ ዕቅዶችንና አቅጣጫዎችን መሬት ለማውረድ የሚያደርገው ጥረት ጠንካራ
መሆኑ፣
እንደ ሀገር የገጠመንን የሠላም፣ የፅንፈኝነት፣ የአክራሪነት፣ የኑሮ ውድነትና የገበያ አለመረጋጋት ፈተናዎች ተቋቁሞ
ከፓርቲና መንግስት ጎን ሆኖ አሁንም በተለያየ መንገድ እያደረገ ያለው ድጋፍ፣
በ 2015 በጀት ዓመት የታቀዱ የፓርቲና የመንግስት ሥራዎችን ለመፈፀም በፈፃሚ ማዘጋጃ መድረኮች ላይ ባሳዩት
ቁርጠኝነት ልክ እየተንቀሳቀሱ መሆኑ፣
በሠላም፣ በልማት፣ በመልካም አስተዳደርና በዴሞክራሲ ግንባታ እና በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ በሚፈጠሩ መድረኮች
ቀድሞ ተሳታፊ በመሆን እና ገንቢ ሀሳቦችን በመስጠት ለመድረክ ስኬት አዎንታዊ ሚና እያበረከተ መሆኑ፣
የክልል አደረጃጀት ጥያቄን ፓርቲና መንግስት ምላሽ ለመስጠት እያደረገ ያለውን ጥረት በመደገፍ የቆመበት
አግባብ የተሻላ መሆኑ፣
በጉድለት
ጥቂት የማይባል አባላችን ድርጅታዊ፣ መንግስታዊና ህዝባዊ ዉይይቶች ላይ ወጥነት ባለው መልኩ በግንባር
ቀደምትነት የመሳተፍ ድክመት፣
6
እርስ በእርስ ከመተጋገል ይልቅ በአመራር ጉድለት ላይ ብቻ ማነጣጠር፣
ጥቂት የማይባል የፐብሊክ ሰርቫንት አባል ትክክለኛ የአባል ስብዕና ተላብሶ ለብልፅግና ዕሳቤና ግብ ከመታገል
አንፃር ጉድለት ያለበት መሆኑ፣
ዉይይቶች ላይ ወጥነት ባለው መልኩ አለመሳተፍ፣ የአቋም መዋዥቅና የጥራት ችግር መስተዋሉ፣
ከኑሮ ውድነትና ከአንዳንድ የመልካም አስተዳደር እጦት ጋር ተያይዞ አልፎ አልፎ በፓርቲና
በመንግስት ላይ የምሬት ድምፆችን ማስተጋባት፣
በተሰማራበት ቦታ የህዝብ አገልጋይነት መንፈስ ተላብሶ ባለጉዳይን ከማስተናገድ አኳያ ግንባር ቀደም ያለመሆኑ፣
ሠ/ የህዝብ
በጥንካሬ
እንደ ሀገር የገጠመንን የሠላም፣ የፅንፈኝነት፣ የአክራሪነት፣ የኑሮ ውድነትና የገበያ አለመረጋጋት ፈተናዎችን ተቋቁሞ
ከፓርቲና መንግስት ጎን ሆኖ አቋሙን ሳያሸራርፍ አሁንም በተለያየ መንገድ እያደረገ ያለው ድጋፍ የሚደነቅ መሆኑ፣
በ 2015 በጀት ዓመት የታቀዱ የፓርቲና የመንግስት ሥራዎችን ለመፈፀም የሚያደርጉት እንቅስቃሴ፣በፓርቲና መንግስት
የሚቀመጡ ዕቅዶችንና አቅጣጫዎችን መሬት ለማውረድ የሚያደርገው ጥረት፣
በየወቅቱ በሚፈጠሩ መንግስታዊና ህዝባዊ መድረኮች ላይ የገጠሩ ማህበረሰብ እያደረገ ያለው ተሳትፎና ትግል፣
በሠላም፣ በልማት፣ በመልካም አስተዳደርና በዴሞክራሲ ግንባታ የላቀ ሚና መጫወታቸው
የክልል አደረጃጀት ጥያቄን ፓርቲና መንግስት ምላሽ ለመስጠት እያደረገ ያለውን ጥረት በመደገፍ ያሳዩት ቁርጠኝነት፣
በጉድለት
አ/አደሩ ራሱ የሚያመርተውን ምርት በውድ ዋጋ እየሸጠ ባለበት ሂደት የማደበሪያ ዋጋ የሚቀመስ አልሆነም የማለት፣
አለምዐቀፍ ሁኔታ የወለደው የማደበሪያ ዋጋ መናርና የአቅርቦት ዕጥረቱን እንደመልካም አስተዳደር እጦት ጋር ተያይዞ
የምሬት ድምፆችን ማሰማት፣
ለኑሮ-ውድነት በስፋት የመንግስት ችግር ብቻ አድርጎ የመመልከትና የሚዛናዊነት ችግር የሚታይ መሆኑ፣
7
ረ/ የከተማ ነዋሪ ሁኔታ
በጥንካሬ
የከተማው ማህበረሰብ የፅንፈኛ ፖለቲከኞች ሰለባ የመሆን እድል ያለው ቢሆንም መንግስት የሚያደርጋቸውን
የፖለቲካና የልማት እንቅስቃሴዎች እየደገፈ መሆኑ፣
አቋሙን ሳያሸራርፍ ከአመራር ጎን በመሆን በየወቅቱ እያጋጠመን ያለው አስቸጋሪ ሁኔታ እንዲቀየር
እያደረገ ያለው ድጋፍ፣
መንግስታዊና ህዝባዊ የውይይት መድረኮች ላይ እያደረገ ያለው ተሳትፎና እየሰጠ ያለው ገንቢ አስተያየት፣የልማትና
የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ፊት ለፊት የመታገልበት ሁኔታ፣
የፀረ-ሠላምና ፀረ-ልማት ኃይሎችን ከማጋለጥ፣ ከመታገልና ከማክሸፍ አንፃር የበኩሉን ሚና በግንባር ቀደምትነት
እየተወጣ መሆኑ፣
ህዝባዊ አደረጃጀትን በማጠናከር የማታ ሮንድ ጥበቃ ላይ በመሳተፍ የአካባቢ ሠላምንና ፀጥታን ለማረጋገጥ
እያደረጉት ያለው እንቅስቃሴ የተሸለ መሆኑ፣
እስካሁን በከተሞች የተከማቹና ሲንከባለሉ የቆዩ የልማትና መልካም አስተዳደር ችግሮች ሁሉም በአንዴ መንግስት
እንዲፈታለት የመጠበቅ ዝንባሌ፣
የተለያዩ የአካባቢ መሠረተ ልማቶች እንዲሰሩ የተወሰኑ አካላት በመንግስትና ፓርቲ ላይ ጫና ለማሳደር መሞከር፣
ባልተመለሱ የልማትና የመልካም መልካም አስተዳደር ችግሮች ምክንያት በተለይም ከገበያ አለመረጋጋት ጋር ተያይዞ
ተስፋ የመቁረጥና በፓርቲና መንግስት ላይ የማማረር ሁኔታ፤
ጥቂት የማይባል የከተማ ነዋሪ መንግስታዊና ህዝባዊ ዉይይቶች ላይ የመሳተፍ ፍላጎት ዝቅተኛ መሆን፣
ሸ/ የወጣቶች ሁኔታ
በጥንካሬ
ወጣት ከፀጥታ አካላት ጎን ሆኖ የአካባቢውን ሠላም ለማስጠበቅ በየአካባቢው እያደረገ ያለው ተሳትፎና
እንቅስቃሴ የተሻላ መሆኑ፣
በክረምትና በበጋ በጎ ፈቃድ ሥራዎች ላይ አብዛኛው ወጣት ያደረገው ተሳትፎና እንቅስቃሴም እጅግ የተሻለና ተስፋ
8
ሰጪ መሆኑ፣
በየወቅቱ የሚያደርገውን ሀገራዊ ጥሪ ተቀብሎ አዎንታዊ ምላሽ በመስጠት ረገድ የወጣት አደረጃጀቶችና አጠቃላይ
ወጣቶች እያሳዩት ያለው እንቅስቃሴ፣
በየወቅቱ በሚፈጠሩ ሀገራዊ፣ ክልላዊና ካባቢያዊ መድረኮች በተለይም በፀጥታ፣ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች፣ በተለያዩ
የፓርቲና መንግስት የንቅናቄ መድረኮች፣ በበጎ ተግባራት እና በሌሎችም ወቅታዊ መድረኮች ወጣቶች በንቃትና በስፋት
በመሳተፍ ከፓርቲና መንግስት የሚወርዱ አቅጣጫዎችንና ተልዕኮዎችን ተቀብሎ ለተግባራዊነቱም እያሳዩት ያለው
አዎንታዊ ምላሽ፣
በጉድለት
አጋጣሚ ቢያገኙ በፀረ-ሠላም ቡድኖች ተታለው በአፍራሽ ተልዕኮ ዉስጥ ለመሰለፍ ወደ ኋላ የማይሉ ወጣቶች
መኖራቸው፣
ከሥራ ዕድል አለመፈጠርና ኑሮ ውድነት ጋር ተያይዞ ባሉ ጉዳዮች በማማረር መርህ ላይ ቆሞ ከመታገል ይልቅ ጭፍን
ከሥራ ዕድል ፈጠራ አንፃር መንግስት በሚያመቻቸዉ ማንኛዉም የሥራ አማራጭ ተደራጅቶ ከመስራት ይልቅ ሥራ
ማማረጥና የተቀጣሪነት አዝማሚያ መታየቱ፣
በሥራ-አጥነት ችግር ሳቢያ ቁጥሩ ቀላል ያልሆነ ወጣት የተሟላ ሥነ-ምግባር ይዞ በአገር ወዳድ ስሜት ምክንያታዊ ትወልድ ሆኖ
በተለያዩ ኢሞራላዊ ድርጊቶች ውስጥ መዘፈቅ፣ በተለያዩ ሱሶች መጠመድ እና በመሳሰሉት ችግሮች ሰለባ የሆነ ወጣት
የጠባቂነትና የሥራ ባህል አለማሻሻል፣ሁሉንም ነገር መንግስት እንዲፈታ የመፈለግ ዝንባሌ አሁንም ያለ መሆኑ፣
ቀ/ የሴቶች ሁኔታ
በጥንካሬ
ሴቶች በአደረጃጀቶቻቸው በመጠርነፍ የሚሰጣቸውን ተልዕኮ ከራሳቸው ሁኔታ ጋር አጣጥመው እቅድ በማውጣት፣
በወጣው እቅድ ላይ በመግባባትና በጋራ በማቀድ የሚያደርጉት እንቅስቃሴና እያስመዘገቡት ያለው ተጨባጭ ውጤት፣
ቁልፍ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ ሴቶችን ለመተካትና ለማብቃት እየተደረገ ያለው ጥረት በሴቶች ዘንድ ከፍተኛ
መነሳሳት የፈጠረ መሆኑ፣
9
በሠላሙ፣ በልማቱና መልካም አስተዳደር ሥራዎች ላይ ሴቶች እያበረከቱ ያሉት እንቅስቃሴ የተሻላ መሆኑ
በጉድለት
በየደረጃው አጠቃላይ ሴቶችን በጋራ ዓላማ ዙሪያ በማነቃነቅ ህብረተሰባዊ ለውጡን በማፋጠን ሴቶች በፖለቲካዊ፣
ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዘርፉ ያላቸውን ተሳታፊነትና ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚደረገው ትግል አሁንም ሰፊ ጉድለት
የሚታይበት ነው፡
በታችኛዉ መዋቅር አሁንም የሴቶች ተዋፅዖ የሚፈለገውን ያህል አለመሆን፣ በተለይ በትምህርት ዘርፍ አመራርነት ማለትም
በርዕሰ-መምህርነትና በሱፐርቫይዘር ደረጃ ላይ የሴቶች ቁጥር ማነሱ መስተካከል ያለበት እንደሆነ ተገምግሟል፡፡
በጥንካሬ
አሁን ባለው ሁኔታ አብዛኞቹ የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ወሳኝ በሆኑ አገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ የተቀራረበና
ተመሳሳይ ሀሳብና አዎንታዊ አቋም ያላቸው መሆኑ፣
እንደዞን የጋራ ም/ቤቱን በየወቅቱ በተለያዩ ሀገራዊና ክልላዊ አጀንዳዎች በመወያየት የጋራ ም/ቤቱ አዎንታዊ
ሚና እንዲጫወት መደረጉ፣
ለአንድ ለተፎካካሪ ም/ቤት አባላት በዳሎቻ ከተማ አስተዳዳርና በዞን ታርቲ ድጋፍ በማድረግ ቤት እንዲሰራ
የተደረገበት፣
ጦርነቱ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ድቀት በማስከተሉ መንግስት የኢትዮጵያን ጥቅም በሚያረጋግጥ
መልኩ ድርድር ማድረጉ እና ከድርድሩ በኋላም መንግስት በፍጥነት እያደረጋቸው ያለውን ሥራዎች በተለይም መልሶ
የማደራጀት ሥራዎችን አብዛኞቹ የተፎካካሪ አባላት ማድነቃቸው፣
የኢትዮጵያን ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ አቅም ለማዳከም ከተለያዩ አቅጣጫዎች ብዙ ጫናዎች እንዲደርስ ታቅዶ እየተሰራ
ቢቆይም ያንን በመቋቋም ሉዓላዊነቷ ተረጋግጦ እንዲቀጥል መንግስት እያደረገ ያለው መሪነት እጅግ የሚያስመሰግን
መሆኑን መናገራቸው፣
በጉድለት
ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተበራከተ የመጣውን የሥራ-አጥነት ችግር፣ የገበያ አለመረጋጋትና የዋጋ ግሽበት በወለደው የኑሮ
10
ውድነት፤በሸገር ሲቲ ስለተፈናቀሉ ዜጎቻችን፣በዞናችን እየተሰሩ ባሉ የልማት ፕሮጀክቶች ዲሊያንስ፣በስልጤ የልማት
ማህባር፣በክልል አደረጃጀት ጉዳዮች ላይ ወዘተ...የማስጮህ ሁኔታ መኖራቸው፣
ዓላማቸውን ለማስፈፀም ደግሞ ወጣቶችን የመጠቀም ፍላጎት፣ በተላይም በወጣቶች የበጎ ስራዎች አመካይነት ወጣቱን
ለመያዝ የመፈለግ ፍላጎት የሚታይ አዝማሚያ መታየቱ፣
ከአልቾ ዊሪሮ ወረዳ ውጪ ሌሎቹ አምስቱ የተፎካካሪ ታርቲዎች የጋራ ም/ቤት ወቅታቸውን ጠብቀው መወያየት
አለመቻለቸው፣
በጥንካሬ
የብልጽግና ፓርቲ የሚያቅዳቸው እቅዶች የሚያማልሉ ናቸው የመደመር ፍልስፍና የሰው ተኮር መሆኑ
ህብረተሰቡ በነጻነት የመናገር እና የህብረተሰቡ ተሳትፎ ስራዎች እንዲጠናከሩ የማድረግ ስራ ሊቀጥል
እንደሚገባ/ሁሉም መዋቅር/
ብልጽግና ማለት ከስሙም መሊቅ/እድገት ማለት ነው ይህን እድገት አሁን ላይ በአጭር ግዜ ማየት
ያልቻልነው በሃገሪቷ ውስጥ ከውጭም ከውስጥ ጠላቶች በመብዛታቸው የህዝቡ ሁለንተናዊ ልማቱ
እንዳይረጋገጥ በመሆኑ ነው እንጂ ከብልጽግና ዓላው አንጻር ወደ ፊት ጥሩ ነገር ይመጣል የሚል ተስፋና
እንደ ዓለም ገበያ ከተማ ከተማ አ/ሩ ራሱ የብልጽግና ውጤት መሆኑ ብልጽግና እንደፈለግን የመናገርና
የሃሳብ በነጻነት ማራመድ፣ እኩልነት የሰጠ ፓርቲ ነው የቀድሞው አፈናና ውሽት ቀርቷል፡/ሳንኩራ
፣ዓለምገበያ
ህዝቡ ከለውጡ በኃላ የመጡ ለውጦችና በሂደቱ የገጠሙ ችግሮችን የሚፈታበት አግባብ በጥንካሬ
የሚያነሳ ሲሆን በተለይም የህዳሴ ግድብ ለማጠናቀቅ የተደረገውን ጥረት ፣የሠላም ስምምነት፣
11
የህዝብ ድጋፍና ቁርጠኝነት፣ ገበታ ለሀገር፣ አረንጓዴ አሻራና የሌማት ትሩፋት፣
የተነሳበት/ሁሉም ጋ/
ወረዳ ላይ የህግ የበላይነት እየተከበረ አይደለም፤ ለአብነት ሌባ ታስሮ ያለአግባብ ይለቀቃል፤
ቢኖር ተፎካካሪ ፓርቲ አያሸንፍም ነበር ወይ በሚል የሚያነሱበት ምዕ/አዘ/በ የሌራ ከተማ
12
ከተማው ላይ ሌብነት/ስርቆት የሞተር፣ባጃጅ፣ ስልክ፣ሱቅ …..ወዘተ እንደሚሰረቅ በቀጣይ የከተማ
ፓሊስ የተለከየ ትኩረት ሰጥቶ ማ/ቡን አሳትፎ በጋራ መሰራት እንዳለበትና በሌቦቹም ላይ ተገቢው
ተጠይቆ ምላሽ አላገኘንም፣የወረዳው መቀመጫ ትሆናለች ተብሎ ነበር በሚል የተሳሳተ ትርክት
በበጀት ዓመቱ መጀመሪያ ዞናል በስልጢ ወረዳ በተዘጋጀው መድረክ በየዘርፉ የተከናወኑትን ተግባራት
በመገምገም፣የነበሩ ጥንካሬዎች እና ጉድለቶች በተገቢው ተለይተው በጥንካሬው ልምድ በመውሰድ፣ የነበሩ ጉድለቶች
የዞን ቅድመ-ዝግጅት ተከትሎ የወረዳ/ በከተማ አስተዳደር፣ የቀበሌ፤ የመሰረታዊ ድርጅት ፤ የህዋስ እንዲሁም
በግለሰብ ደረጃ እቅድ በማዘጋጀት እና ተገቢውን ተግባቦት በመፍጠር ወደ ትግበራ መገባቱ፣
በየደረጃው የታቀዱ እቅዶችን ከራሳቸው አካባቢያዊ ነባራዊ ሁኔታ ጋር በማጣጣም ተዘጋጅቶ ከፈጻሚ
አካላት/አመራርና አባላት/ ጋር በቂ ተግባቦት የተፈጠረ ሲሆን ሁሉም እንደየ ማህበራዊ መሰረቱ በዕቅዱ አፈፃጸም ዙርያ
የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ተደርጓል፡፡
በየደረጃው የሚታቀደው እቅድ ከዋናው እቅድ የተናበበ እንዲሆን ጥራት ያለው እቅድ ለማቀድ ጥረቶች ተደርጓል፡፡
ከዞን ጀምሮ እስከ ታችኛው መዋቅር ድረስ አደረጃጀቶች የሚወያዩበት ወጥ አሰራር በማዘጋጀት ወደ ውይይት
የተገባ መሆኑ፣
13
በጉድለት
አንዳንድ መዋቅሮች እቅድ ያላጠናቀቁ መሰረታዊ ድርጅትና ህዋሳትና መዋቅሮች መኖራቸው በ 9 ወር አፈጻጸም
በጉድለት ተገምግሞ የተቀለሰ እቅድ በማቀድ ሁሉም በእቅድ እንዲመሩ የማድረግ ስራ ቢሠራም ተግባሩ
አለመጠናቀቁ ፡፡
በየደረጃው የታቀዱ እቅዶች የእቅድ ጥራት ውስንነቶች የሚታይባቸው፣የነባራዊ ሁኔታ ግምገማ የሌለው፣ኮፒ-
ፔስት፣የተሟላ ዕቅድ ያልያዘ በተለይም እንደፓርቲ የሚሰሩ ስራዎችን ያልያዘ ዕቅድ
የተገኘበት/ቅበት፣ጦራ፣አልቾዊሪሮ፣ምዕ/አዘ/በ፣ሳንኩራ፣ዳሎቻ
የዓመቱ የፓርቲ ዕቅዶች እስከ ግለሰብ ድረስ ስለመታቀዱ እንዲሁም ሁሉም አደረጃጀቶችና አባላት በዕቅድ
በጥንካሬ
የ 2015 ዓ.ም የፈጻሚ ማዘጋጃ መድረኮች በአብዛኛው መዋቅሮች በቂ ቅድመ ዝግጅት በማድረግ በተገቢው
መፈጸማቸው፤
ከጥቂት መዋቅሮች ውጪ በመ/ድርጅትና በህዋሳት ደረጃ ዕቅድ እንዲኖራቸው መደረጉና በአሰራርና አደረጃጀት
ዕቅዶች በፎርማቱ መሰረት የተዘጋጁ መሆኑ፣ በተዘጋጀው እቅድ ላይ ውይይት የተደረገበት መሆኑና
ሞደል የአደረጃጀቶችና የግለሰብ ዕቅድ በአብዛኛው ተደራሽ መደረጉ አንዲሁም እስከ ግለሰብ ድረስ የታቀዱ ዕቅዶች
መኖራቸው፤ በአብዛኛው መዋቅር መ/ድርጅትና ህዋስ አደረጃጀቶች የአባልነት መዋጮ ዕቅድ በአግባቡ ተካትቶ የታቀደ
መሆኑ፣
በጉድለት፡-
የህዋስና መሰረታዊ ድርጅት ዕቅድ ዝግጅት በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት ተግባራዊ ከማድረግ አንጻር ሰፊ ጉድለት
መኖሩ፤
የዕቅድ ዝግጅት የጥራትና ይዘት ጉድለት ያለበት (ነባራዊ ሁኔታ የማይተነትን፣ የድርጊት መርሃ ግብር የሌለው፣ የዕቅድ
መጠን የማይገልጽ፣ የአባላት መዋጭ ፣አባላት ምልመላ አደረጃጀቶች በአብዛኛው የመዋጮ ዕቅድ የሌላቸው
መሆኑ፣
ነባራዊ ሁኔታ የተነተነና አደረጃጀቶቹን የሚመሰል ዕቅድ አለማቀድ፤ የወረዳውን መነሻ ዕቅድን እንደ ራስ ዕቅድ
14
ወስደው ከራስ ተጨባጭ ዕቅድ ያላቀዱ መ/ድርጅቶች፣ ህዋሳት መኖራቸው፣
የመሰረታዊ ድርጅት ንዑሳን ኮሚቴዎች ዕቅድ ተዘጋጅቶላቸው ያለመመራቱ፣
የአባላት የግል ዕቅድ የተንጠባጠና በአግባቡ ያልታቀደ መሆኑ፣በስተቀር የአባላት የግል እቅድ አለመኖሩ፡፡
አባላት በውይይት ወቅት የግል ዕቅድ እንዳላቸው በቃል ደረጃ የተናገሩ ቢሆንም በተደረገው የዶክመንት
ግብር፣የአባላት የመዋጮ ፣የግንኙነት አግባብ የማይገልጽ መሆኑ) የሁሉም ህዋሳት ዓመታዊ ዕቅድ
የወቅታዊ የፖለቲካ፣ የልማት፣ የፀጥታና የመልካም አስተዳደር የሁኔታ ግምገማ ሰነዶችን በማዘጋጀት በየደረጃው
ከሚገኘው አመራር ጋር በተገቢው በመግባባት፣ በተዋረድ ለመላው አባላት እና ደጋፊዎች በማውረድ የተግባር
እንቅስቃሴ መደረጉ፣
በየደረጃው በተለያዩ ወቅታዊ ሀገራዊና ዞናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ማለትም
ከወጣቶች፣ ሴቶች፣ ምሁራን፣ የሀይማኖት መሪዎች፣ አ/አደሮች፣ የከተማ ነዋሪዎች ጋር ገንቢ ውይይቶች
መደረጋቸው፣
የ2015 በጀት ዓመት የፓርቲና የመንግስት ሥራዎች አፈፃፀም መነሻ ያደረገ የአመራርና አባል የማጥራት መድረክን
እንደ ቁልፍ መገንቢያ መሣሪያ አድርጎ በመውሰድ በየደረጃው የሚገኝ የአመራሩንና አባሉን አቅም ለማጎልበት ታቅዶ
መሰራቱ፣
የአባላት ፖለቲካዊ አቅም ለመገንባት እንዲሁም የተግባርና አስተሳሰብ አንድነት ለመፍጠር የመሠረታዊ ድርጅትና
የሕዋስ ውይይቶች የማይተካ ሚና ያላቸው ሲሆን ሰፊ የፖለቲካ ሥራዎች በመስራትና ያሉንን አባላት በማጥራት
በአዲስ መልክ እንዲደራጁ በማድረግ ለአቅም ግንባታና ተልዕኮ ሥምሪት የተሻለ ሁኔታ ለመፍጠር ተችሏል።
አሁን ባለው ሁኔታ ፓርቲን ለማጠናከር በየማህበራዊ መሠረት የሕዋሳት ውይይቶች በየ 15 ቀናት እየተደረገ ይገኛል፡፡
የተግባር አንድነት ለማረጋገጥ በያንዳንዱ ተልዕኮ አፈፃፀም ሂደት የሚፈጠሩ ግድፈቶችንና የተዛቡ አስተሳሰቦችን ጊዜ
ሳይሰጠዉ ከማረም አንፃርም በርካታ መሻሻሎች ተመዝግበዋል፡፡
“የልሳነ ብልፅግና” መፅሄት ቅፅ 1 ቁጥር 3 ፈጥኖ ለአባላት ተደራሽ በማድረግ በመ/ድርጅትና በህዋስ ውይይት በማድረግ
15
ለፓርቲው አመራርና አባላት አቅም መገንብያ እንዲሆን መደረጉ፣
ሁሉም መሠረታዊ ድርጅቶች የግማሽ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት፣ የቀጣይ ዕቅድ እና የፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ
ላይ ተጨማሪ ግንዛቤ እንድይዙ ወጥ በሆነ ሁኔታ አቅም የመገንባት ሥራ መሰራቱ፣
የአመራር እና አባላት ማጥራት መድረክ /በወቅታዊ የፖለቲካ ፤ የሰላም እና የልማት ተግባራት ሁኔታ ግምገማ
ሰነድ፣
ዐቅምን በውጤት፤ ፈተናን በስኬት በሚል ለብልጽግና አመራርና አባላት የተዘጋጀ የስልጠና ሠነድ፣
ለፀረ ሙስና ቀን በዓል አከባበር ፓናል ዉይይት የቀረበ ክልላዊ መነሻ ሰነድ፣
በቅርቡ በፓርቲው በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት ድሎችን ጠብቆ ሳናሳንስና ሳናንኳስስ በመቀበል
ወቅታዊ ፈተናዎችን በብቃት መመከት የሚያስችል አቅም መገንቢያ መድረክ እና ሌሎችም የውይይት
ሰነዶች ላይ አባሉ ውይይት አድርጎባቸዋል፡፡
በየወቅቱ ከማዕከል በሚወርዱ ሰነዶች የአመራርና የአባለት ሰልጠና መድረክ የተመራበት አግባብ ‹‹በደም የተከበረ በላብ
የታሰረ››፤ ‹‹ዐቅምን በውጤት፤ ፈተናን በስኬት››፤ ከፈተና ወደ ልዕልና፤ የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ወዘተ አፈፃፀም
በሱፐርቪዥን ምልከታ ግኝቶች፡-
በጥንካሬ
በየወቅቱ አባላት እንዲወያዩባቸው የወረዱ ወቅታዊ አጀንዳዎች በቂ ቅድመ ዝግጅት ተደርጎ የተፈጠሩ መሆኑን
የተገኘባቸው መዋቅሮችና የሱፐርቭዥን ቡድኑ በገባባቸው ህዋሳትና መሰረታዊ ድርጅቶች ዘንድ ማየት መቻሉ፣
በስልጠናው መድረኮችም የተፈጠረው ቁጭትና መነሳሳት ወደ ተግባር እየተለወጡ መሆኑ መልካም እንደሆነ፣
16
በመድረኩም በየመዋቅሩ በስልጠናው ማለፍ ያለባቸው አመራሮች፣ አባላትና ደጋፊዎች መሳተፋቸውን ማረጋገጥ
መቻሉን፣
ከውስን አካላት በስተቀር በስልጠናው መድረክ ማለፍ ያለባቸው አመራሮች፣ አባላትና ደጋፊዎች የስልጠናዎቹን
መድረክ ያለፉ መሆኑ፤
በጉድለት
የስልጠናም ሆነ የውይይት መድረኮች ወደ ታች እየወረዱ በሄዱ ቁጥር የተሟላ ቅድመ ዝግጅት
ግድፈት የሚታይበት፣የተበታተና የአባላት ተሳትፎ የሚታይበት፣
በሰነዶቹ ይዘትና መሰረታዊ ጭብጥ አባላት በተገቢው እንዲጨብጡ እየተደረገ ያለበት አግባብ መሠረታዊ ጉድለት
መታየቱ፣ሰለጠኑ/ተወያይረተዋል የተባሉ አባላት አብዘኛው ሲጠየቅ መናገር የማይችልበት ሁኔታ በሁሉም መዋቅር
ያጋጠመ መሆኑ፣
በአባላት ዘንድ ውይይት የተደረገባቸውን ርዕሰ-ጉዳዮች እና መሰረታዊ ጭብጦችን ያለማስታወስ ሁኔታ በስፋት
መኖሩን፣የመድረኮቹ ጥራት ችግር እንደሆነ ምልከታ በተደረገባቸው አደረጃጀቶች በሙሉ መታየቱ፣
ሰነዶቹ የተደራጁበትን ሁኔታ ምልከታ ሲደረግ ከውስን ሰነዶች በስተቀር ብዙሃኑን ማግኘት
አለመቻሉን፣በአብዛኛው መዋቅር
2.5 የአስተሳሰብና የተግባር አንድነትን ለማጠናክር እየተሰራ ያለው የፖለቲካ ስራ አፈፃፀም ያለበትን ደረጃ
በጥንካሬ
የአመራሩ የአስተሳሰብና የተግባር አንድነት ያለ በመሆኑ ከክልል አደረጃጀት ጋር ተያያዥ በነበሩ አጀንዳዎች
በቀላሉ እየተግባቡ የጋራ አቋም የተያዘበት፣እንደዞን ደማቅ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ማድረግ የተቻለበት፣
በሁሉም መዋቅር
በየደረጃው ተግባርን ማእከል ያደረገ የፖለቲካና የአደረጃጀት ተግባራት እንቀስቃሴ ለማሳካት ከሚደረገው ጥረት መነሻ
የፓርቲው አመራር የአስተሳሰብና የተግባር አንድነት በአብዛኛው መዋቅር መኖሩን መመልከት መቻሉ፣
የአመራርና አባላት ማጥራት መድረኮችንና ሌሎች የግንባታ መድረኮች በመጠቀም በተከታታይ የማረም ሥራዎችን
እየሰሩ መሆናቸው፣
የአ/አደር መሰረታዊ ድርጅትና ህዋሳት በወቅታዊ የግብርና ልማትና የመልካም አስተዳደር አጀንዳዎች ላይ
እንደሚወያዩና ከሞላ ጎደል በአብዛኛው መዋቅር ተመሳሳይ ግንዛቤ መኖሩ መረጋገጡ፣
በየደረጃው ጤናማ መተማመንና መናበብ እንዳለ በውይይት በተነሱ ሀሳቦችና በተግባር የተሰሩ ስራዎች
ያስረዳሉ፣ምስራቅ ስልጢ ወረዳ አመራሩ
17
በአመራሩ የአስተሳሰብና የተግባር አንድነት በመኖሩ ሁሉንም የህበረተስብ ክፍል በተደራጀ አግባብ ወደ ልማት
ምስ/ስልጢ፣ሁልባራግ፣ስልጢ፣ምስ/አዘ፣
በጉድለት
የተሟላና ወጥ ቁመና ያለው የፓርቲ አመራርና አባላት ከመፍጠር አንጻር ጉድለት መኖሩ፤ የፐ/ሰርቫንት
ከወረዳ/ከተማ ከጠቅላላ አመራሩ እስከ አባል ድረስ የአስተሳሰብና የተግባር አንድነት ለማጠናክር የሚሰራው የፖለቲካ
ስራ አሁንም ብዙ መስራት የሚጠይቅ መሆኑን፣
በመሠ/ድርጅትና በህዋስ አመራሩ በሁሉም አካባቢ ወጥና ተቀራራቢ የሆነ የአመራር የአስተሳሰብና የተግባር
አንድነት ያለመፈጠሩ፣
ለህበረተሰብ ጥያቄዎች ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ሰበቦችን የማብዛት፣የህዝብ መድረኮች የመሸሽ አዝማሚያዎች
ህብረተሰቡ የሚያነሳቸውን የመልካም አስተዳደር ጉድለቶች ፈጥኖ ያለማረም፣የተሳሳተ ሪፖርትና እይታ እንዲኖር
በአፍራሽ አጀንዳዎች የመጠለፍ አዝማሚያ መታየቱ (በሸገር ሲቲ ጋር የተፈጠረ አጀንዳን በፓርቲው ስርዓት
ከሚያገኘው መረጃ ይልቅ የማህበራዊ ሚዲያን የመረጃ ምንጭ አድርጎ
ሁሉም አመራር በእኩል ደረጃ የተግባር ተሳትፎ ከማድረግ አንጻር ውስንነት መኖሩ፤የተጀመሩ ውይይቶች ጥሩ
ቢሆኑም እስከ ታች ድረስ ባለመውረዱ የተነሳ አሁንም ልዪነቶች በስፋት የሚንጸባረቁ መሆኑን፣
በጥንካሬ
የፓርቲያችን አመራርና አባላት የማጥራት ስራ ከዞን ማዕከል እስከ ታች ቀበሌ ድረስ ሳይጠባጠብ መከናወኑ፣
በመድረኮቹ በስራ አፈጻጸም ድክመት፣ በስነ-ምግባር ብልሽት እንዲሁም በአመለካከት ጥራት ግድፈት የሚታይባቸው
18
አመራርና አባላትን በሚገባ በመለየት የማረምና የመገንባት ሥራ መሰራቱ፣በሁሉም መዋቅር
በማጥራት መድረኮች የየደረጃው አመራር እና አባላት ሁኔታ ግምገማ ሰነድ ላይ የበሰለ ውይይት በማድረግ ተገቢ
ግንዛቤ መያዙ፣ በአካል ግምገማ ነጥሮ የውጡ ጉዳዮች በሂስ ግለ ሂስ እና በማጥራት መድረክ ባለቤት
ማግኘታቸው፣
በሂስ ግለ ሂስ ሂደቱ በአመራርና አባላት መካከል ተገቢ መማማር የተፈጠረበት፤ ክፍተቶች በትግል እንዲታረሙ
መልካም ዕድል የተፈጠረበት፣ የማጥራት ሂደት በጣም አስተማሪ የነበረበት፣
የፓርቲያችንን ውስጠ ዴሞክራሲ የሚያጠናክር፣ አመራርና አባላትን ለቀጣይ ተልዕኮ ያነሳሳ እና የውስጥ አቅም
የሚፈጥር እንደሆነ
በአጠቃላይ በየማህበራዊ መሰረቱ የተፈጠሩ የማጥራት መድረኮች የተሻለ ግንዛቤ የተፈጠረበት፣ ተሳታፊው ሃሳቡን
በዴሞክራሲያዊነት፣ በነፃነት እና በግልፅኝነት ያራመደበት፣ ብዥታ የሚፈጥሩ ጉዳዮች ላይ በግልፅ በመነጋገር እና
በመከራከር የተሻለ ተግባቦት የተፈጠረበት እና ለቀጣይ ተግባር ተነሳሽነትን የጫረ መድረክ እንደነበር የሁሉም መዋቅር
ሪፖርት ያሳያል፣
የማጥራት መድረኮችን ተከትሎ በፓርቲው ውስጥ የገዘፈ ችግር የሚታይባቸው አመራርና አባላት ላይ ተገቢው
ፓለቲካል እርምጃ መወሰዱ፣
በአመራር ምዘና መመሪያ ላይ በሁሉም ደረጃ ላለው አመራር ግንዛቤ እንዲይዝ ከተደረገ በኋላ የግማሽ ኣመት አፈፃፀም
መነሻ ባደረገ ሁኔታ ሁሉም የፓርቲ አመራሮች እንዲመዘኑ የተደረገበት፣
በጉድለት
በቀበሌያት ለአ/ አደር አባላት የሚሰጠው የምዘና ውጤት አባላት እምብዛም የማይታወቅ መሆኑ፤
በአንዳንድ አመራሮችና አባላት በማጥራት መድረኩ የተወሰደው እርምጃ አስተማሪ አለመሆኑ ግምገማዉ
የአደርባይነት ችግሮች የሚታይበት መሆኑ፣ከመጠን በላይ የማስታመም ሁኔታ መኖሩንና አባሉ ግን ከችግር
የማይጠራበት፣
ቀበሌ መ/ድርጅትና ህዋስ በዝቅተኛ ደረጃ የተፈረጁ አመራርን በግንባር ቀደም የመተካት ሥራው
የ ጥ ራ ት ጉድለት ሚታይበት መሆኑ፤
19
ቅሬታ አለመፍታት፣
1.1. በ 2014 ዓ.ም በጀት ዓመት ሳይከናወኑ የቀሩ ስራዎችን የ 2015 ዕቅድ ከማዘጋጀት አኳየ (ዕቅድ
ዝግጅት)
በጥንካሬ
እንደዞናችን በ 2014 በጉድለት የተለዩ እና በ 2015 የእቅድ ዘመን የትኩረት አቅጣጫ የነበሩ ዋና ዋና
ጉዳዮች፡-
በመሆኑም የ 2015 ዓ.ም ዕቅድ በ 2014 የልተሳኩ፤በከፊል የተሳኩና ዝቅተኛ ክንዉን የላቸዉ
ከዞን እስከ ህዋስ የዕቅዶቻችን ይዘት ከላይ የ10 አመት ስትራቴጂክ/ጠቋሚ አቅታጫ/ ከታች የ2014
ግምገማ መነሻ መድረግ እንዳለብን ተግባብተናል፤ሞዴል እቅድ ለሁሉም ማህ/መሠረት መሠ/ድና ህዋሳት
አዉርደናል፡፡
እስከ 10ኛ ወር ሪፖርት የመሠ/ድ 100%፤የህዋሳት 100%ና የግለሰብ ዕቅድ (85 - 95%) ፤በሩብ አመት
የመስክ ምልከተ የን/ኮ ዕቅድ እና የግለሰብ ዕቅዶች እንዲሟሉ አቅጣጫ ተቀመጠ የተህሳስ ቀጥሎ
ይቀርበል፡፡
የወረዳ/ከተማ አስተዳደሮች ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ደረጃ ሁሉም መዋቅሮች የዘርፍ ዕቅዶችን
ጨምሮ ከወትሮ በተሸለ ጥራት አዘጋጅተዉ ወደ ተግባር ምዕራፍ መገባቱን የኢንስፔክስን ቡድኑ
20
በመሠ/ድና ህዋስ ደረጃ በሁሉም መዋቅር የሚገኙ መሠረታዊ ድርጅቶችና ህዋሳት ዕቅድ እንዳላቸው
ከአባላት እቅድ አንፃር፦ በየደረጃው የዕቅድ መረጃዎች በተህሳስም ሆነ በዚህ ዙር የመስክ ምልከተ
ተረጋግጧል ሆኖም ግን አብዛኛዉ የአመራርና አባላት እቅድ የጥራት ችግር ያለበት ነዉ፡፡
የመሠ/ድና ህዋስ ዕቅዶች የጥራት ችግር፤ከወረዳ/ከ/አስተዳደር የተላኩ ሞዴል እቅድ ኮፒ፤ ሁሉም
ያለገናዘበ ፣ ሊመዘን የማይችል፤እና ዉስን መዋቅር ቢሆንም ዕቅድ የሌላቸዉ አደረጃጀት እንዳሉ
የን/ኮሚቴዎችና የግል እቅድ ፦ ከነጥራት ችግሩም በየደረጃው የግል ዕቅድ የዘጋጁ አመራሮችና አባለት
21
በየደረጃዉ ፈፃሚ አካላት ማለትም አመራርና አባላት በተጀጋጀዉ እቅድ ላይ ተከታተይ መድረኮችን
3.1. የፓርቲ አደረጃጀቶች በአደረጃጀት መመሪያ መሠረት መደራጀት፤ በግንባር ቀደም አመራር መመራት፣
ሁሉም አባላት አሰራር መመሪያዉን፤ፕሮግራም፤ህገደንቦች ስለመገንዘባቸዉ በጥንካሬና በጉድለት፡-
በጥንካሬ፡-
በ 2015 ሁሉም የፓርቲ አደረጃጀቶች የአደረጃጀት አሰራር መሰረት እንዲደራጁ በማድረግ ክፍተት
የአደረጃጀት ክፍተቶች ለማረጥበብ የሞከረዋል፡፡
የ 135869 አባለት መረጃ በኦርኔል ተደራጅቶ በመሠ/ድና ህዋስ በመዝገብ፤ወረዳ/ከተማ በኤከስ
ኤልና ፎቶ፤ በዞን በመረጃ ቋት ለማደራጀት አቅደን በመጃ ቋት 99%፤ ፎቶ 90% ተፈፅሟል፡፡
በአድሱ አደረጃጀት መሠ/ድርጅት 105 በመጨመር ከ 635 ወደ 740 ሲሆኑ 514 ህዋስ
በጉድለት፡-
የኢንስፔክሽን የተለዩ፡
የፌድራል ሱፐርቪዢን ቡድን የማዕከል ፐብሊክ ሰርቪስ አባላት ወይይት ወቅት 300 አባል በአንድ
22
ሚያዝያ 2015 በ 9 ወረዳና 4 ከ/አስተዳደሮች በተደረገ ኢንስፔክሺን የተዩ ጉድለቶች፡-
አባላት በፓርቲው የአሰራርና አደረጃጀት መመሪያ መሰረት ከማደራጀት አንፃር አብዛኛዉ መዋቅር የመ/ድ
ና ህዋስ አመራሮች ሰፊ የግንዛቤ ክፍተት በመኖሩ መሠ/ደ ከ 210 በላይ ህዋስ ከ 35 በላይ አባላት
በጥንካሬ
በወረዳ/ከተማ አስተዳደር ደረጃ ፤ሁሉም መዋቅር ሊባል በሚችል ደረጃ የአስተባባሪ ኮሚቴ፤ የፓርቲ
ለዉጥ የለዉ ቢሆንም ሂደቱን ወደ ዉጤት የቀየሩ መዋቅሮች ቁጥር ዉስን መሆናቸዉን መየት ተችሏል፡፡
በተለይም አመራሩ ዕቅዱንና አሰራር ግንዘቤ አስጨብጦ ወደ ተገባር ከማስገባት አንፀር የተሸሉ
፤ሁልባራግ፤-ም/ስልጢ ፤ስልጢ ሲሆን ከነበረባቸዉ ጉድለት የወጡ ቅበት ከተማ ፤ምዕራብ ተጠቀሽ
ናቸዉ፡፡ በአንድ ወይም ሁለት ዘርፍ የሚገለፅ ጥንካሬ የላቸዉ አ/ገበያ፤ምስራቅ አዘርነት፤ላንፉሮ
፤ምዕራብ አዘርነት፤ አሊቾ ፤ዳሎቻ ወረዳ የሚጠቀሱ ናቸዉ
በጉድለት
23
መሠ/ድርጅትና ህዋሳት ወቅቱን ጠብቆ የፓርቲና የመንግስት ተግባራትን በመደበኛነት
ጦራና ቅበት ከ/አስ ት/ት ግንባር እንዲሁም አ/ገበያ ከ/አስ ኢንተርፕራይዝ መሠ/ድ
ናቸዉ፡፡
ምክኒያት የላቸዉም፡፡
መጥቀስ ይቻላል፡፡
በቀበሌ ከአንድ በላይ መሠ/ድ በሚገኝባቸዉ ቀበሌዎች የቀበሌ የመሠ/ድርጅት አስተባባሪ ኮሚቴ ሁሉም
ተግባራዊ አልሆነም፡፡
በጥንካሬ
24
በሦስቱም ዙር በቂ የቅድመ ዝግጅት ተደርጎ ኮንፈረንስ ተካሄዷል፡፡ በክልል፤ በዞን ፤ወረዳ/ከ/አስደረጃ
በኮንፈረንሶች መድረከሎች የአሰራር መመሪየዉ ስልጠና የተሰጠ ቢሆንም አመራሩ የግነዛቤ ጉድለቶች
የስራ ድርሻ አለማወቅ፤የምዘና ደረጃ፤ የግንኙነት አግባብ ፤የዕቅድ ግልፅ አለመሆንና የጥራት ችግር
፤የሪፖርት ግዜ ፤የአባላት ተሰትፎ ክፍተት በተለይም የተሳተፉ አመራሮችና አባላት አጀንዳዉን በአግባቡ
መሠ/ድ፤ምዕራብ አዘርነት የኗሪ ግንባር ፤ላንፉሮ አለም ጨፌ 01 ፤ዓለም ገበያ የኗሪ ግንባር፤ሳንኩራ
በጥንካሬ፡-
በጉድለት፡-
አብዛኛዉ መዋቅር የአደረጃጀቶችንም ሆና የአባላት ምዘና በቁጥር ከመግለፅ ባለፈ ምዘናዉ የስገኛዉን
ፈይዳ የለመግለፅ ችግር መኖሩ፤
በተለያየ ወቅት በታየ የመስክ ምልከተ አደረጃጀቶች ተመዝነዉ የተፈረጁበትን ደረጃ የለመወቅ ችግር፤
በጥንካሬ
ተግባሩ በ 2015 የትኩረት አቅጣጨ ተይዞበት የሚሰራ ሲሆን እንደ ዞን ካሉን 740 መሰረታዊ ድርጅቶች
26
ከፅ/ቤት አኳ መዋቅሮችን ስንመለከት አሊቾ ከ 104 ለ 104 ፤ኡልባራግ ከ 44 ለ 44፤ ቅበት ከ 24
ከ 4795 ህዋሳት ዉስጥ በተለየ አማራጭ የመወያያ ቦታ ያላቸው ህዋሳት ብዛት 1806 ሲሆኑ ቀሪዎቹ
በሂደት ላይ ናቸዉ፡፡
5. በሁሉም ተቋማት ደረጃ ተግባራትን በአደረጃጀት ከመፈፀም አንፃር፡-
በጥንካሬ፤
ከዞን እስከ ቀበሌ መሠ/ድርጅትና ህዋሳት ድረስ ተግባራት በፓርቲ አደረጀጀት መሠረት በተገበዉ
እየተከናወነ ያለ መሆኑ፡፡
ከመሠረታዊ ድርጅት ፣ህዋሳ ፣አባል ግለሰብ ድረስ በፓርቲ አሠራርንና አደረጃጅት መመሪያ በተከተለ
መልኩ ተደርጀቷል፡፡
በፓርቲያችን አሠራርንና ሥራዓት ዙሪያ አባላት ጋር ወይይት ተደርጎ ወደ ተግባር በመግባት በፓርቲያችን
የሚከናዉኑ ተግባራት በሙሉ አሠራር ተጠብቶ ይተገበራል፡፡ ተቋማዊ
መዋቅሮችን ስንመለከት
ሁሉም የዞናችን መዋቅሮች እንደ አግሮኢኮሎጂያቸዉ ተጨባጭ የማህ/ሰቡን ኢኮኖሚያዊ ብልፅግና
ለማረጋገጥ አመራሩንና አባሉን በዋና ዋና የልማትና የመ/አስተዳደር አጀንዳዎች በማሳተፍ እስከ ግለሰብ
እየመዘነ ይገኛል፡
ለአብነት የበጋ መስኖ ስንዴ ልማት ፤ የሙዝና ፍራፍሬ ክላስተር በመፍጠር፤ በሌማት ትሩፋት የወተት ልማት
፤ዶሮ ልማት ፤የማር ሀብት ልማት ፤በክርምትና በጋ የበጎ ፈቀድ ስራዎች ፤ የት/ቤቶችን ስታንደርድ
በማሻሸል፡ በከተማ ልማት ስራዎች ወዘተ አደረጃጀቶችና አባላት በደረጃ እየተፈረጁ ይገኛሉ፡፡
በጉድለት
27
ሁሉንም ተግባር በዘመቻ ለመፈጸም የመፈለግና ሁልግዜ ጉትጎታን የመጠበቅ ችግሮች ያለባቸው
አደረጃጀቶች መኖራቸዉን በአባላት ፎቶ አሰባሰብ፤
የመሠ/ድ አመራር አጀንዳዎችን ለህዋሳት አከፋፍሎ በመስጠት ህዋሳትን ተከፋፍለው ድጋፍ የለ ችግር፡፡
በጥንካሬ፡-
በነሀሴ ወር የአመራር ና የአባል ማጥራት ግምገማ መድረኮችን ተከትሎ በተለያየ ምክኒያት የልተሟሉ
የአደረጃጀት አመራሮችን ጨምሮ የተግባር አፈፃፀም ችግር የተየባቸዉ በርካታ ቁጥር ያላቸዉ አመርሮችን
በግምባር ቀደሞች የመተካት ስራ ተሰርቷል፡፡
ግ/ቀደም አመራሮች የሚመሩ ቢሆንም የግንዘቤ ክፍተቶች ሰፊ ናቸዉ
በአባለት መረጃ ማዘመን ተግባር ጎን ለጎን በርካተ ጉድለት የነበረባቸውን የአደረጃጀት አመራሮችን
28
6. ተግባራት በህገ -ደንብ መሰረት እየተመራ ስለመሆኑ
በአሰራር መመሪያዉ በተለየየ ወቅት ለአባለት የአጫጭር ግዜ ስልጠናዎች ተሰጥተዋል፡፡
በወረዳ/ከተማ አስተዳደር ደረጃ ፤ሁሉም መዋቅር ሊባል በሚችል ደረጃ የአስተባባሪ ኮሚቴ፤ የፓርቲ
አመራር ኮሚቴ አሰራሩን ጠብቆ በመደበኛነት ተግባር መገምገም፤ግ/መልስ መስጠት፤አረጃጀቶችን ጠጋ
ብሎ የሚደግፉበት ሂደት በአብዛኛዉ መዋቅሮች የተሸለ እንደሆነ ተወስዷል፡
በመሠ/ድርጅትና ህዋሳት ደረጃ፤ ወቅቱን ጠብቆ የፓርቲና የመንግስት ተግባራትን በመደበኛነት
የመገምገም፤ግ/መልስ የመስጠት፤አረጃጀቶችን በተግባር መፈረጅ በአብዛኛዉ መዋቅር ከግዜ ወደ ግዜ
ለዉጥ የለዉ ቢሆንም ሂደቱን ወደ ዉጤት የቀየሩ መዋቅሮች ቁጥር ዉስን መሆናቸዉን መየት ተችሏል፡፡
በ 2015 ሁሉም የፓርቲ አደረጃጀቶች የአደረጃጀት አሰራር መሰረት እንዲደራጁ በማድረግ ክፍተት
የአደረጃጀት ክፍተቶች ለማረጥበብ የሞከረዋል፡፡
የ 135869 አባለት መረጃ በኦርኔል ተደራጅቶ በመሠ/ድና ህዋስ በመዝገብ፤ወረዳ/ከተማ
በጥንካሬ
ትኩረት በተሰጣቸው ማህበራዊ መሰረቶች ማለትም ሴቶች ፣ ወጣቶች፣ ምሁራን፣ ላይ ትኩረተረ የደረገ
ስራ ለመስራት ተችሏል፡፡
እንደ ዞን በ 2014 ዓ.ም. መጨረሸ ከነበረን 135604 አባል ዉስጥ 10%(13560) ለመመልመል ተቅዶ
29
የአድስ አባል ምልመላችን በፓርቲው አሰራር መሠረት መመልከቻ አስገብቶ፤በፕሮግራሙ አሰልጥኖ፤በቂ
ድጋፍ እየገኛ 6 ወር የዕጩነት ግዜ አጠናቆ በኮንፈረንስ የፀደቀበት መረጀ በአግባቡ አለማደረት ጉድለት፡፡
የአዳድስ አባላት ቁጥር መጨመር ከመዋጮ ጋር በማስተሳሰር ብዙ ዕጩዎች እያሉ ግዜየቸዉ አልፎም
የለማፅደቅ ችግር፡፡
በመሠ/ድርጅትና ህዋሳት ደረጃ በ 2015 ወደ ሙሉ አባልነት የመጡትና በዕጩነት ደረጃ የሉትን መረጃ
በስም ዝርዝር ፈይል የለማድግ ችግር፡፡
ኮር አመራር ማለት በቁጥር ጥቂት ሆኖ በአመራር ልምድና ብስለት፣ ስትራቴጂክ ጉዳዮችን በቁልፍነት
ለይቶ አመራር ከመስጠትና ከፍ ያለ ሀሳብ በማፍለቅ አመራር የሚሰጥ ሀይል ሲሆን አብዛኛዉ መዋቅር ኮር
አመራር የአስተባበሪ ኮሚቴ አካትን መረጀ ብቻ የደረጃሉ፡
ተተኪ አመራር ማለት አሁን በየመዋቅሩ ያለውን ፑል አመራር እና ግንባር ቀደም አባላትን ያካተተ ስለሆነ
ከህዋስ ጀምሮ ከቁጥር መረጃ ባለፈ በስም ተለይቶ ድጋፍ የመደገፍና የማብቀት እና በየግዜዉ ብቃቱንም
እየመዘኑ የለመሄድ ጉደለት ይተየል፡፡
11.መረጃና ዶክመንቴሽን በተመለከተ
ሁሉንም አይነት መረጃዎችና ዶከመንቶች ዘመናዊ በሆነ መልኩ(soft and hard copy) ከማደራጀት
በጥንካሬ የተለዩ፡-
30
በዞን፤ወረዳ/ከ/አስተዳደር ፓርቲ ፅ/ቤቶች ደረጃ በሁሉም ዘርፎች ሁሉም አይነት መረጃዎች በሶፍት
ኮፒ ዶክመንት ኖራቸዉን ማረጋገጥ የተቻለ ሲሆን ዉስን መረጃዎችን በሀርድ ኮፒ የላደረጁ መዋቅሮች
የመረጃ አደረጃጀት ለማዘመን በ 2015 ዓ.ም ከሌላው ግዜ በተለየ መልኩ ትኩረት በመስጠት የአባላትና
በአጠቀለይ ወ 692 ሴ 110 ድ 802 አመራሮችን በተሻሻለው ኤክስ ኤል ፎርማት ለማደራጀት ተቅዶ
ድ 134770 (99%) አባላትን በማደራጀት ወደ መረጃ ቋት መስገባት የተቸለ ሲሆን ከዚህ ዉስጥ ወ
ከአባላት ማጥራት ስራዉ ተየያዥ መረጃዎች ከህዋስ ጀምሮ በኦርኔል የተደደረጀበት መንገድ የተሸለ
በመሠ/ድርጅትና ህዋሳት ደረጀ የመረጃ ና ዶክመነቴሺን ስራአቱ በተሸለ ሁኔታ ማደረጀት የተቸለ
መረጃዎች መኖራቸዉን ማየት የተቸለ ቢሆንም ቁጥራቸዉ ቀላል የልሆኑ አደረጃጀቶች የተጓደለና
የጥራት ችግር የለዉ መሆኑ ፤ አንዳንዶቹ ደግሞ ምንም አይነት መረጃ የሌላቸዉ መሆኑን በመስከ
ክፍል ሁለት ሀብት ልማት እና አስተዳደር ዘርፍ የአስር ወራት የዕቅድ አፈፃፀም እና የሱፐርቪዥን ሪፖርት
31
1. የመዋጮ አቆራረጥ መመሪያዉን ተግባራዊ ከማድረግ አንጻር
እየተገበሩ ያሉ ስልጢ ወረዳ፣ቅበትና ላንፍሮ ሲሆኑ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ያላደረጉ ዳሎቻ ወረዳ ፣ሚቶ
ደረሰኝ በወቅቱ ከመስጠት አንጻር እስከ መጋቢት ወር ድረስ ደረሰኝ የሰጡ ዳሎቻና ምስ/ስልጢ ወረዳ፤ እስከ
የካቲት ወር የሰጡ ጦራ ከተማ፣ወራቤ ከተማና ሁለባራግ፤ እስከ ጥር ወር የሰጡ ዳሎቻ ከተማ ና ሳንኩራ፤
እስከ ታህሳስ ወር የሰጡ ስልጢ ወረዳ ና ቅበት ከተማ እስከ ጥቅምት ወር የሰጡ ሚቶና ላንፉሮ ወረዳ በዘጠኝ
ደረሰኝ ቆርጠው ለህዋስ አመራ ወይም ለሰውሃብት እያስፈረሙ የሚሰጡ ዳሎቻ ወረዳ፣ጦራ
በ 2013/14 ዓ.ም ለቀበሌ ተሰራጭተው ያልተመለሱ ደረሰኞች ያላስመለሱ መዋቅሮችን ስንመለከት ዳሎች
ወረዳ 6 ደረሰኝ፣ ሚቶ 2 ደረሰኝ፣ ላንፉሮ ወረዳ 7 ደረሰኝ፣ ምዕ/አዘርነት 1 ደረሰኝ፣ ምስ/አዘርነት 3 ደረሰኝ
4. የ 10 ወር የገቢ አሰባሰብ
32
አስተዳደር ገቢ ዕቅድ ዕቅድ የገቢ አፈፃጸም በፐረሰንት
1 ስልጢ 870,282 725,235 745,000 103%
2 አልቾ 734,868 612,390 607,989 99%
3 ሁልባራግ 604,797 503,997 607,017 120%
4 ሳንኩራ 600,180 500,150 566,925 113%
5 ወራቤ 545,138 454,281 409,569 90%
6 ምዕ/አዘርነት 480,744 400,620 289,622 72%
7 ላንፍሮ 470,404 392,003 411,555 105%
8 ዳሎቻ ወረዳ 456,315 380,262 386,077 102%
9 ምስ/አዘርነት 433,413 361,177 336,548 93%
10 ሚቶ 328,356 273,630 269,287 98%
11 ምስ/ስልጢ 305,535 254,612 217,025 85%
12 ቅበት 297,481 247,900 224,401 91%
13 ጦራ 297,362 247,801 239,645 97%
14 አለምገበያ 170,928 142,440 193,831 136%
15 ዳሎቻ ከተማ 175,816 146,513 146,071 100%
16 ዞን ማዕከል 460,000 383,333 349,500 91%
ድምር 7,083,754 5,903,128 5,898,379 99.9%
5. የልሳነ-በልጽግና መጽሔት ዕዳ
የመጽሔት ስቀየር
ብዛት
1 ስልጢ 400 4,000 4,000 0
2 አልቾ 400 4,000 4,000 0
33
3 ሁልባራግ 350 3,500 3,500 0
4 ሳንኩራ 350 3,500 3,500 0
5 ወራቤ 300 3,000 3,000 0
6 ምዕ/አዘርነት 350 3,500 3,500 0
7 ላንፍሮ 300 3,000 3,000 0
8 ዳሎቻ ወረዳ 350 3,500 3,500 0
9 ምስ/አዘርነት 300 3,000 3,000 0
10 ሚቶ 300 3,000 3,000 0
11 ምስ/ስልጢ 300 3,000 3,000 0
12 ቅበት 300 3,000 3,000 0
13 ጦራ 300 3,000 3,000 0
14 አለምገበያ 200 2,000 2,000 0
15 ዳሎቻ ከተማ 200 2,000 2,000 0
16 ዞን ማዕከል 300 3,000 3,000 0
ድምር 5,000 50,000 50,000 0
የመጽሔት ስቀየር
ብዛት
1 ስልጢ 400 8,000 0 8,000
2 አልቾ 400 8,000 0 8,000
3 ሁልባራግ 350 7,000 7,000 0
34
4 ሳንኩራ 350 7,000 7,000 0
5 ወራቤ 300 6,000 6,000 0
6 ምዕ/አዘርነት 350 7,000 0 7,000
7 ላንፍሮ 300 6,000 0 6,000
8 ዳሎቻ ወረዳ 350 7,000 0 7,000
9 ምስ/አዘርነት 300 6,000 3,000 3,000
10 ሚቶ 300 6,000 0 6,000
11 ምስ/ስልጢ 300 6,000 0 6,000
12 ቅበት 300 6,000 0 6,000
13 ጦራ 300 6,000 0 6,000
14 አለምገበያ 200 4,000 0 4,000
15 ዳሎቻ ከተማ 200 4,000 0 4,000
16 ዞን ማዕከል 300 6,000 6,000 0
ድምር 5,000 100,000 29,000 71,000
35
የሱፐር ቪዥኑ አካሄድ
የፌደራሉን መነሻ ያደረገ እና ዞናዊ ጉዳዮችን ያካተተ ቼክ ሊስት ተዘጋጅቶ ዝርዝር ኦረንቴዬሽን ተሰጥቱዋል።
ከመረጃ ፍተሸ በተጨማሪ በያንዳንዱ መዋቅር 6 መድረኮች ተፈጥሩዋል የፓርቲ ኮሚቴ፤የህዋስ እና መ/ድርጅት
አመራር፤ የቀበሌ አመራር ፤የተመረጠች ህዋስ አባላት፤ የተውጣጣ የህዝብ ክፍል እስከ 30 የሚደርስ እና አስተባባሪ
ኮሚቴ፤የፓርቲ ኮሚቴ እና የካብኔ አባላት መድረክ ተፈጥሩዋል፡
በማዕከልም የተቋም አመራር የህዋስ እና የመ/ድርጅት አመራር እና አጠቃላይ አባላት ጋር ውይይት ተደርጉዋል፡፡
ሆስፒታሎች በሚገኙበት ከተማ /ወረዳ ፓርቲ ይታያሉ ይላል አስታንዳርድ አልተቀመጠም በቀጣይ ፈትሸን ማረም
ማብራሪያም መጠየቅ ያስፈልጋል፡፡
እያንዳንዱ መዋቅር ሁለት ቀን የፈጀ ፍተሸ እና ምልከታ ተደርጎ ሶስት ቀን የሪፖርት ዝግጅት በመስጠት ሁለት ቀን
የፈጀ ዝርዝር ግምገማ ከሱፐር ቪዥን ቲሙ ጋር አድርገናል፡፡
ሁሉም መዋቅር በቀጣይ 60 ቀናት ትኩረት ሰጥቶ ሊሰራባቸው እና ሊፈትሻቸው የሚገቡ ጉዳዮች
በመመሪያው መሰረት አደረጃጀቶችን ከማደራጀት አንፃር ጉድለቶች ታይተዋል። መ/ድርጅት አባላት ከ 22 እስከ
210 መሆን እንዳለበት ያስቀምጣል ይህ ችግር አሁንም አልተፈታም በአንድ መሰረታዊ ድርጅት ከተባለው በላይ
አባል እና የ ታቀፉ ህዋሳት መኖራቸውን አይተናል ። ህዋሳት ብዛት ትንሹ 2 ትልቁ 6 መሆን እያለበት በዚያ መንገድ
አይደለም፤ የህዋስ አባልም ከ 11 እስከ 35 ቢልም ከተቀመጠው ቁጥር በላይ እስከ 47 የተደራጀበት ሁኔታ
አይተናል።
የቀበሌ አስተባባሪ ኮሚቴ የቀበሌ አደረጃጀቱ ላይ ያለ የግልፀኝነት ችግር መፈታት ይኖርበታል።
ውይይት በአደረጃጀትና አሰራር መመሪያው መሰረት እየሄደ አይደለም።
የሪፖርት ቅብብሎሹ ችግር ያለበት ነው ህዋስ ለመ/ድርጅት መ/ድርጅት ለፓርቲ ጽ/ቤት
የግ/መልስ፤ የደረጃ አሰጣጥ፤ የኮንፍረንስ አካሄድ፤ አባል ማድረግ ሂደቱ ወዘተ ችግር ያለበት ነው። ቀጣይ ፈትሾ
ማረም ያስፈልጋል።
ሶስቱ ንኡስ ኮሚቴዎችን አደራጅቶ ወደ ስራ ከማስገባት አንፃር ጉድለት ያለበት ነው።
36 | P a g e
መሰረታዊ የሆነ የዕቅድ ችግር ዕቅዱ ኮፒ ነው፤ የግለሰብ ዕቅድ የለም፤ ዕቅዱ የፓርቲ ስራወችን በተገቢው
አልያዘም፤ ዕቅዱን አባሉ አያውቀውም፤ ዕቅዱ የድርጊት መርሃ ግብር የለውም ፤ ጭራሽ ዕቅድ የሌለበትም አለ
በሁሉም ማህበራዊ መሰረት ያሉ አደረጃጀቶችን እኩል ያለመደገፍ፣ ያለ ማደራጀት፣ ያለ መከታተል፣ የሚቀለው
ቦታ የማዘንበል ችግሮች የታዩ ሲሆን በተለየ መንገድ የት/ት ግንባር እና የእንተርፕራይዝ ግንባር የተተወ ነው።
የከተማ ነዋሪ አደረጃትም በቂ ትኩረት አላገኘም።
የመረጃ አደረጃጀት እና ዶክመንቴሽን በአብዛኛው በማዕከል ጽ/ቤት ደረጃ በተሸለ መንገድ ያለ ቢሆንም በህዋስ እና
መ/ድርጅት ደረጃ ችግር ያለበት ነው። የተለያዩ መ/ደርጅቶች በአንድ መዝገብ በአንድ ፋይል አመራራቸውን ያለ
ማወቅ መመሪያዎች ያለ መኖር ዕቅዶች ሪፖርቶች ቼክ ሊስቶ ሚዘና የአመራር ባንክ ወዘተ ፋይል ተሟልቶ እና
ተደረጅቶ አልተያዘም።
2 የፖለቲካ ስራ ላይ
የውይይት አጀንዳ ያለመቅረጽ፤ ተጨማሪ ሰነድ ያለማዘጋጀት፤ የተዘጋጁ የፓርቲ ዕሳቤ ላይ፤ የአደራጃጀት እና
የአሰራር መመሪያ፤ ፕሮግራም ላይ፤ ልሳነ ብልጽግና፤ በየ ወቅቱ የሚወርዱ አጀንዳዎች ላይ በወቅታዊ የንቅናቄ
አጀንዳ እና በተቋም ስራ ላይ በወጥነት ውይይት እየተካሄደ አይደለም።
የፖለቲካ ስርፀት ስራችን ከችግር የተላቀቀ አይደለም አሁንም ቀላል የማይባል አመራር በፖርቲው የነገበውን
አላማ፣ ለማሳካት የወጠናቸው ግቦችን፣ የፖርቲው ዕሴት፣ ስለ ፖርቲው ፕሮግራም ፣ መተዳደሪያ ደንብ፣ ስለ
አደረጃጀት እና አሰራር መመሪያ፣ ዋናዋና ጉዳዮችን እና ሜጀር ሺፍቶችን ከማወቅ እና ከመተንተን አንፃር ጉድለት
አለ።
ህዋስ እና መ/ድርጅት የነባራዊ ሁኔታ ምንጭ እና የአመለካከት ቀረፃ እና የተግባር ማሳለጫ ቱልስ እየሆኑ
አይደሉም።
ተገቢ የሆነ ምዘና የመመዘን እና ምዘናውን መነሻ ያደረገ የፖለቲካ የቅጣት ውሳኔ ያለ ማሳረፍ፣ የአመራር እና
የአባላት የግናባታ እና የአያዝ እንዲሁም እርምጃ አወሳሰድ ስራችን ችግር ያለበት እና በመረጃ የተደገፈ
አይደለም።
ኮር አመራር የማፍራት አመራር ሊሆኑ የሚችሉ አባላትን ለይቶ የአመራር ባንክ የለ ማዘጋጀት ወዘተ ችግር አለ።
በየ ወቅቱ የሚፈጠሩ አጀንዳዎችን ምንጭ ፤መንስኤ እና አሁናዊ ነባራዊ ሁኔታን ተረድቶ እና ተንትኖ እሱን
የሚመጥን ሰነድ አዘጋጅቶ የፖለቲካ ስራ ከመስራት አንፃር የጠባቂነት እና የአላካኪነት ችግር ይስተዋላል። ለምሳሌ
እንደ ዞናችን በሱፐር ቪዥኑ የተለዩ እና በስፍት የሚነሱ አጀንዳዎች
2 የኑሮ ውድነት
5 ሀገራዊ፤ክልላዊ፤ዞናዊ፣ ወረዳዊ እና ከተማ አስተዳደራዊ ነባራዊ ሁኔታ ላይ በየ ደረጃው ካለው አመራር ፤ አባል እና
ህዝቡ ጋር የምናደርገው ውይይት ጥራት ያለው እና የተግባባንበት ነው ብሎ መውሰድ አይቻልም።
37 | P a g e
3 ከሰው ሀብት እና የፋይናንስ አስተዳደር ስራችን
የመዋጮ አቆራረጡ መመሪያነ ደንቡን ተከትለው የማይቆርጡ 4 መዋቅሮች ዳሎቻ ወረዳ፣ሚቶ ወረዳ፣አልቾ ወረዳ
እና ወራቤ ከተማ አስተዳደር ሲሆኑ አቆራረጥ ላይ የወጥነት ችግር ያለባቸው እና ቡራቡሬ መዋቅሮች ስልጢ፣ ቅበት
እና ላንፉር ሲሆኑ ሌሎች ቀሪ 8 መዋቅሮች በአሰራሩ መሰረት የሚቆርጡ ናቸው። ሁሉም መዋቅር መፈተሽ እና
ማጥራት ያለበት በየ ግዜው አብዴት እየተደረገ እየተስተካከለ አለመሆኑን በአባላት ቅሬታም ይነሳል የኛ ምልከታም
ተመሳሳይ ደሞዝ ኖሮት 75 ብር 16 ብር የሚቆረጥበት ሁኔታ ማየት ተችሉዋል።
አልቾ ደግሞ ከ ግሮስ ነው የሚቆረጠው
ለአባላት ደረሰኝ እንዲደርስ ከማድረግ አንፃር ከመዋቅር መዋቅር የሚለያይ ቢሆንም ችግር ውስጥ ያሉ እና 1 ብቻ
የሰጡ ምዕራብ አዘርነት እና አለም ገበያ ናቸው
የተቆረጠ ገንዘብ በየ ወሩ ተቆርጦ ከመላክ አንፃር የ 9 ኝ ወሩን ስናይ የ 5 ወር ባለ ማስገባት መሪው ምዕራብ አዘርነት
ሲሆን ሚቶ የ 3 ወር ባለ ማስገባት ይከተላል ሳንኩራ የ 2 ወር አላስገባም የአንድ ወር ያላስገቡ አልቾ፣ ጦራ፣
ላንፉሮ፣አለም ገበያ እና ዳሎቻ ከተማ ናቸው።
የአምና ካርኒ ያላስመለሱ መዋቅሮች ዳሎቻ ወረዳ 6 ሚቶ 2 ላንፉሮ 7 ምስ/አዘርነት 3 ምዕ/አዘርነት 1 እና አልቾ
1 ናቸው።
የልሳነ ብልጽግና መጽሄት ሁለተኛ ዙር ገንዘብ ሙሉ በሙሉ ገቢ ያደረጉ ሶስት መዋቅሮች ሁልባራግ፣ሳንኩራ እና
ወራቤ ሲሆኑ ምስ /አዘርነት ግማሽ ገንዘብ አስገብተዋል ሌላው መዋቅር በሙሉ ያላስገቡ ናቸው።
4 የፓርቲ ስራዎች ላይ ያለ የድጋፍና ክትትል ስራን በተመለከተ
ወጥ በሆነ መንገድ ፓርቲ ተክሎ አንድም አባል እና አደረጃጀት ከዕቅድ፤ ከውይይት ፤ ከሪፖርት ፤ከግ/መልስ ፤
ከደረጃ፤ ከመዋጮ መቁረጥ ፤ ከአባላት ማፍራት እና ከኮንፍረንስ ውጪ መሆን የለበትም ብሎ ተተክሎ ከመስራት
አንጻር ጉድለት ያለበት ነው
ሶስቱን መስተጋብሮችን ዕቅድና ሪፖርት፤ ግምገማ እና ግ/መልስ፤ ምዘና እና ደረጃን ተክሎ ያለመሄድ ጉድለት አለ
የፓርቲ የበላይነት እና መሪነትን ያለ ማረጋገጥ ተግባራትን በአደረጃጀት ያለ መምራት የሚሰሩ ሁሉም የልማት
ስራዎች ከፓርቲያችን ዕሳቤ አንጻር ምን ማለት እንደሆነ ያለመረዳት እና ከዕሳቤያችን አስተሳስሮ ያለ ማንሳት
አንዳንድ መዋቀሮች የፓርቲን ስራ በሙሉ ወደ ጎን በመተው የመንግስት ስራዎች ላይ ስምጥ ብሎ የመግባት እና
በድጋፍና ክትትል ያለ ማውጣት ችግር
ጠንካራ የኮ/ፖስት ስርአት ያለመትከል
የውሸት ሪፖርት ቀምሞ የመስጠት እና እሄን በድጋፍና ክትትል ያለ ማጋለጥ
በመምሪያና ጽ/ቤት
38 | P a g e
ችግሮችን ውጫዊ የማድረግ፤ ፓርቲውን የመተቸት፤ አልቻለም ይልቀቅ የኑሮ ውድነት ተረኝነት አለ ጦርነቱ ትክክል
አልነበረም ኤሄ ሁሉ ሰው አልቆ ለምን በዚህ መንገድ ተፈታ፤የኑሮ ውድነት እያለ እንዴት ላወያይ ወዘተ
ዝቅተኛ፡- ሚቶ
ከመምሪ እና ጽ/ቤት
ት/ት
ቴክኒክና ሞያ
ውሃ እና ሚሊሻ ሲሆኑ
መሀከለኛ ያሉ
አስተዳደር እና እንቨስትመንት
የተሸሉ ህዋሳት
ፋይናንስ እና
ንግድ ናቸው
39 | P a g e