You are on page 1of 21

የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት

ድርጅት
የኮሙኒኬሽን ስትራቴጂ (ረቂቅ)

ማውጫ ገጽ
ክፍል አንድ
1.1 መግቢያ ……………………………………….……………….………

1.2 የኮሙኒኬሽን ስትራቴጂ አስፈላጊነት ……………….……………

1.3 የኮሙኒኬሽንና የህዝብ ግንኙነት ስትራቴጂ ዓላማዎች……………

1.4 የኮሙኒኬሽን ስትራቴጂ ጠቀሜታ ……………….……………….

1.5 የኮሙኒኬሽን ስትራቴጂ ግብ……………….……………….…………


ክፍል ሁለት
2.1 ስትራቴጂክ እቅዱን ለመቅረጽ መነሻ የሆኑ ምክንያቶች……………….…

2.2 ልንከተለው የሚገባ የኮሙኒኬሽን ባህል……………….……………….

2.3 የድርጅቱ ተልዕኮ፣ ርዕይ እና እሴቶች……………….……………….……

2.4 የጠንካራጎን፣ ደካማ ጎን፣መልካም አጋጣሚና ስጋት ትንተና……………….


ክፍል ሦስት
አተገባበር ……………….……………….……………….……………….……

3.1 የኮሙኒኬሽን ዘዴዎች……………….……………….……………….

3.2 የሚዲያ አጠቃቀም እና አስተዳደር……………….……………….……


ክፍል አራት
4.1 ቁሌፍ መልዕክቶች……………….……………….……………….………

4.2 ስትራቴጂያዊ አጋሮች……………….……………….……………….……

4.3 የግንኙነት መርሆዎች……………….……………….……………….……

4.4 የድርጅቱ የውስጥ ኮሙዩኒኬሽን……………….……………….…………

4.5 የውጭ ግንኙነት……………….……………….……………….…………

4.6 የውስጥ ኮሙኒኬሽን ማጠቃለያ……………….……………….……………

4.7 የውጭ ግንኙነት ማጠቃለያ……………….……………….……………….

ክፍል አምስት

5.1 የክትትልና ግምገማ ዕቅድ እና በጀት……………….……………….………


ክፍል አንድ

1.1 መግቢያ

የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት በዋናነት የፖስታ መልዕክቶችን በመቀበል፣ በማስተላለፍ እና በማደል እንዲሁም የገንዘብ
ማስተላለፍ ስራ ላይ የተሰማራ ሲሆን ከነዚህ አገልግሎቶች በተጨማሪ የተለያዩ የኮሚሽንና የውክልና ስራዎችን ያከናውናል፡፡ ድርጅቱ
ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት በመስጠት በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪና ለአገሪቱ ዘላቂ ልማት የላቀ ሚና የሚጫወት መሆን እንዲችል
ደንበኛ ተኮር የአሰራር ስርዓት በመዘርጋት የአስር ዓመቱን ዕቅድ አቅዶ ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል፡፡
የተያዘውን ዕቅድ ለማሳካት ደግሞ በስትራቴጂ የሚመራ የኮሙኒኬሽን ስርዓት መተግበር ከበላይ አመራሩ የሚጠበቅ ወሳኝ ሚና
ነው፡፡
ተቋሙን የሚመለከቱ መረጃዎችን በወቅቱና ቀጣይነት ባለው መልኩ በአግባቡ ለማሰራጨት አስፈላጊ ከሆኑ የኮሙኒኬሽን የአሰራር
ስርዓቶች መካከል አንዱ የኮሙኒኬሽን ስትራቴጂ ነው፡፡ በቀላል አገላለጽ የኮሙኒኬሽን ስትራቴጂ አንድን ጉዳይ ወይም ሁነት የተመለከቱ
መረጃዎችን ወደተለያዩ ተደራሲያን ለማሰራጨት የሚያገለግል የኮሙኒክሽን ዕቅድ ነው፡፡ በሌላ አገላለጽ የኮሙኒኬሽን ስትራቴጂ
ከማህበረሰብ፣ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላትና ተደራሲያን ጋር ለመገናኘት የሚያገለግል ንድፍ ነው ማለት ይቻላል፡፡
ኮሙኒኬሽን ስትራቴጂ፡-

- የኮሚዩኒኬሽን ዓላማዎችን በዝርዝር ማሣየት፣

- ባለድርሻዎችን መለየት፣

- ቁልፍ መልዕክቶችን መለየት፣

- የኮሙኒኬሽን መንገዶችን ማመላከት፣

- በስትራቴጂው ላይ ግብረ መልስ ለማግኘት የሚያስችሉ መንገዶችን ወዘተ ማመላከት አለበት፡፡

ከነዚህ ሐሳቦች በመነሳት የኮሙኒኬሽን ስትራቴጂ ለምን መረጃ ማሰራጨት እንዳለብን ወይም ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ግንኙነት
ማድረግ ያለብን ለምን እንደሆነ ከወዲሁ አውቀን እንድንነሣ ምቹ ሁኔታ ይፈጥርልናል፡፡
ከእነዚህ ሃሳቦች በመነሣት የኮሙኒኬሽን ስትራቴጂ ለምን መረጃ ማሰራጨት እንዳለብን ወይም ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር
ግንኙነት ማድረግ ያለብን ለምን እንደሆነ ከወዲሁ አውቀን እንድንነሣ ምቹ ሁኔታ ይፈጥርልናል፡፡ የኮሙኒኬሽን ስትራቴጂ ኮሙኒኬሽን

ለምን? የሚለውን በግልጽ የሚመልስ ከመሆኑ በተጨማሪ ሊሳኩ የሚታሰቡ ዓላማዎችን በግልጽ በማመላከትም ምቹ የኮሙኒኬሽን
ድባብ ይፈጥራል፡፡

1.2 የኮሙኒዩኬሽን ስትራቴጂ አስፈላጊነት

o የድርጅቱን ርዕይ፣ ዓላማ፣ ተልዕኮና መሪ ዕቅድን ሰራተኛው፣ ተገልጋዩና ባለድርሻ አካላት


እንዲያውቁትና እንዲያምኑበት ለማድረግ እንዲቻል፣
o የኢትዮጵያ ፓስታ አገልግሎት ድርጅት ሰራተኞች በየዲፓርትመንቱ የተፈጠሩትን የመረጃ
ውስንነቶች (communication limitations) ሊያጠብ ወይም ሊቀርፍ የሚችል ከመሆኑም በላይ
ለለውጡ ንቅናቄ ለመፍጠርና ተዋናይ እንዲሆኑ፣
o የድርጅቱ ሰራተኞች ስለ ለውጡና ስለአተገባበሩ ትክክለኛና ወቅታዊ መረጃዎችን እንዲያገኙ
በማድረግ የለውጥ ኃይሎችን ለማፍራትና ለማብዛት፣
o የድርጅቱ ሰራተኞች በለውጡ ሂደት ዙሪያ በየጊዜው የሚኖራቸውን አስተያየት (opinion)፣
አዝማሚያና (attitude) ድርጊት (action) በመከታተልና በመረዳት አሉታዊ ዝንባሌዎችን በመለየት
የመፍትሄ እርምጃ ለመውሰድ፣
o በለውጡ ሂደት የሚገኙ አዎንታዊ ጥንካሬዎችን በየወቅቱ በመከታተል ሰራተኛውና ደንበኛ (ባለድርሻ
አካላት) ለማሳወቅና ለማበረታታት፣
o በየጊዜው ተለዋዋጭ የሆነውን የደንበኞች (ባለድርሻ አካላት) ፍላጎት ለመረዳትና ግብረ መልስ
ለማግኘት፣
o በግልፅ የምንሰራቸውን ስራዎች መሰረት አድርገን የመወያየት፣ ችግሮቻችንን በአስተማሪነታቸው
ለመቀበልና በቀጣይ ለማስተካከል ይረዳን ዘንድ ግብዓት ማግኛ መንገድ ስለሚሆን፤
የሚሉት ናቸው፡፡

1.3 የኮሙዩኒኬሽንና የህዝብ ግንኙነት ስትራቴጂ ዓላማዎች

የኮሙዩኒኬሽንና ህዝብ ግኝኙነት ስትራቴጂው የሚከተሉት ዓላማዎች ይኖሩታል፡፡

 የድርጅቱ ዓላማ፣ ርዕይና ተልዕኮ እንዲሁም ዕቅድች በተገቢው መንገድ እንዲተዋወቁና የባለድርሻ
አካላት ድጋፍ እንዲያገኙ ማድረግ፣
 የኮሙዩኒኬሽን ስራዎች በተቀናጀ መንገድ የድርጅቱ የስራ ማዕከል እንዲሆን ማድረግ ፤
 እንደተቋም ጠንካራና ወጥ የሆነ መልዕክት እንዲተላለፍ ማድረግ ፤

 ድርጅቱ የሚያስተላልፋቸው ቁልፍ መልእክቶች ግልጽና ሚዛናዊ በሆነ መንገድ እንዲተላለፍ ማድረግ ፤

 የድርጅቱን ዓላማ ለማሳካት ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅርበት መስራት፣


 የድርጅቱን እንቅስቃሴዎችና ያስገኛቸውን ውጤቶች በተገቢው መንገድ ማስተዋወቅ፣
 ድርጅቱ ሊደርስበት ያቀደውን ግብ ለማሳካት የሚያስችል የሰራተኛ ንቅናቄ መፍጠርና ድጋፍ ማድረግ፣

 የባለድርሻ አካላት አመለካከትና ባህርይ ለመለወጥና ለድርጅቱ ተልዕኮ ስኬት አጋር እንዲሆኑ ድጋፍ
ማድረግ፣
 ደረጃውን የጠበቀና የተቀናጀ የኮሙዩኒኬሽንና የህዝብ ግኝኙነት ስራ ማከናወን፣
 በኮሙዩኒኬሽን ስራዎች ላይ የምክር ድጋፍ፣ አመራርና የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ በመስራት ተቋማዊ
የገጽታ ግንባታ ስራ ማከናወን፣
1.4 የኮሙኒዩኬሽን ስትራቴጂ ጠቀሜታ

1. በድርጅቱ ላይ የሚነሱ አሉታዊ ገጽታዎች ወደ አዎንታዊ ገጽታ ይለወጣል

2. የሥራ ሀላፊዎች ከሰራተኞች ጋር ያላቸው ግንኙነት የሰመረ እንዲሆን ያደርጋል


3. በድርጅቱ ውስጥ የኢንዱስትሪ ሰላም እንዲሰፍን ያደርጋል
4. ከውስጥ እና ከውጪ ደንበኞች ጋር ያሉትን ችግሮች ይቀርፋል
5. የድርጅቱን አቅም ለማሳደግ ይረዳል
6. በአገልግሎቱ የረካ ደንበኛ እንዲኖር ያደርጋል
1.5 የኮሙኒዩኬሽን ስትራቴጂ ግብ
የኮሙዩኒኬሽን ስትራቴጂ በድርጅቱ የሚተገበረውን ለውጥ ለማሳካትና በድርጅቱ ሰራተኞች ዙሪያ ሰፊ ንቅናቄን
ለመፍጠር የሚያስችል ሶስት ግቦችን መሰረት ያደረገ ይሆናል፡፡ በዚህም መሰረት፡-
1. የማሳወቅ
2. የማሳመን
3. ለተግባር ማነሳሳት የሚሉት ግቦች ይኖሩታል፡፡
ክፍል ሁለት
2.1 ስትራቴጂክ እቅዱን ለመቅረጽ መነሻ የሆኑ ምክንያቶች
2.1.1 ከተቋም አንጻር
ስትራቴጂካዊ እቅዱን ለመቅረጽ ዋነኛ መነሻ ምክንያቶች ከሆኑት ውስጥ የድርጅቱን ሪፎርም አጠናክሮ
ለማስቀጠል የውስጥ እና የውጪ ኮሙኒኬሽኑ ተጠናክሮ መከናወን የሚገባው በመሆኑ እና ያለው የቢዝንስ ፉክክሩ
እየተስፋፋ በመምጣቱ ሰራተኞችንም ሆነ ያገባኛል ባዮችን ስትራቴጂክ በሆነ መልኩ ግንኙነት ማድረግ አስፈላጊ
በመሆኑ ነው፡፡
በዚህም የድርጅቱ የውስጥ እና የውጭ የኮሙኒኬሽኑ ስራው ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ እና ወደፊትም በተጠና
መልኩ ለማስኬድ እንዲያስችለው በተለያዩ መንገዶች ያለበትን ክፍተት ለማየት ሞክሯል፡፡
ለድርጅቱ ሰራተኞች መጠይቆችን በመበተን እንዲሁም በደንበኞች መድረክ እና በዋናው መስሪያቤት ካውንተር
ላይ አገልግሎት ለማግኘት የመጡ ደንበኞችን ቃለ መጠይቅ በማድረግ ክፍተቶቹን ለማየት ተችሏል፡፡
በዚህም የኮሙኒኬሽን ስራው ፊትለፊት መደረግ እንዳለበት፣ ለሚመለከታቸው አካላት ያሉ ችግሮችን በግልጽ
መንገር እንደሚገባ፣ በድርጅቱ ውስጥ አሉባልታዎች እንደሚበዙ፣ መረጃም በአግባቡ ለሰራተኛውም ሆነ
ለደንበኛው የሚደርስበት አሰራር እንዳልተዘረጋ፣ የበላይ አመራሩ የሰራተኛውን እና የደንበኛውን ቅሬታ ለመቀበል
ዝግጁ አለመሆኑ፣ ስራዎችን በተመለከተም በትእዛዝ ሳይሆን በመግባባት የሚሰራ መሆኑ፣ በአስፈጻሚ እና
በፈጻሚ መካከል ያለው ግንኙነትም ሀሳብን በመለዋወጥ ላይ የተመሰረተ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡
በመሆኑም ተከታታይነት ያለው የኮሙኒኬሽን ሥራ መስራት ከተቻለ፣ በመረጃ እጦት ምክንያት የሚፈጠሩ
አሉባልታዎችን ለመቀነስ፣ ከድርጅቱ ባህሪ እና ስራን ቆጥሮ ከመስጠት እና ከመቀበል አኳያ አንዱ የኮሙኒኬሽን
መንገድ በመሆኑ የኮሙኒኬሽን ስራው በስትራቴጂ መመራት አስፈልጓል፡፡
2.1.2 ከኮሙኒኬሽን አኳያ
የድርጅቱን መለያ ከገጽታው አኳያ አጉልቶ ለማውጣት እየተሰራ አለመሆኑ፣ ድርጅቱ ሊደርስበት ከሚያስበው
ጥሩገጽታ እና መልካም ሥም አንጻር ልዩነትን ለማጥበብ የሚያግዙ ስራዎች እየተሰሩ አለመሆናቸው፣ከተግባቦት
ስራ አንጻር ተጠያቂነት ባለው መልኩ የሚመለከታቸው የስራ ሃላፊዎች ተግባርና ሀላፊነት እየተወጡ አለመሆኑ
እና የሥራ ክፍፍል አለመኖሩ፣ የኮሙኒኬሽን ሥራን በተመለከተ ውሳኔ ለመስጠት እንዲያስችል ሥራዎችን
በቅደም ተከተል ለማዘጋጀት የተዘረጋ አሰራር አለመሆኑ፣ የውስጥ እና የውጪ ደንበኞችን ንቅናቄ ፈጥሮ
የድርጅቱን ተልዕኮ ለማሳካት የሚያስችሉ ሥራዎች አለመሰራታቸው፣ መካከል መተማመን ፈጥሮ ከመስራት
አንጻር የድርጅቱ ሰራተኛ ተለይቶ የሚታወቅበትን መለያ ተጠናክሮ እየተሰራ አለመሆኑ፣ ድርጅቱ የያዘውን
ተልዕኮ ለማሳካት ማኔጅመንቱ እና ሰራተኛው ተቀራርቦ መስራት ወሳኝ በመሆኑ ስትራቴጂያዊ ኮሙኒኬሽን
አስፈልጓል፤
2.1.3 ከሚዲያ አኳያ
ከተለያዩ የሚዲያ ተቋማት ጋር ያለው ግንኙነት መልካም ቢሆንም እንደቢዝነስ ተቋም ጠንካራ የሆነ የተለያዩ
የኮሙኒኬሽ ሥራዎች ለመስራት በጀት መድቦ ከመስራት አኳያ ክፍተት ያለ መሆኑ፤

2.2 ልንከተለው የሚገባ የኮሙኒኬሽን ባህል

የተሳካና የተዋጣለት የስራ አፈፃፀም እንዲኖር ለማስቻልና ሁሉን አሳታፊ የሚያደርግ ስርዓት ለመፍጠር
በድርጅቱ የሚታዩ የመረጃ ክፍተት (information gap) ሊያጠቡ የሚችሉ መንገዶችን ማሰብ የግድ የሚል ነው፡፡
በመሆኑም ሁሉም የድርጅቱ ማህበረሰብ እንደ ባህል ሊከተላቸውና ዕለት ተዕለት የህይወቱ መመሪያ
ሊያደርጋቸው የሚገቡ የኮሙኒኬሽን ባህሎች ሊኖሩት ይገባል፡፡
በዚህም መሰረት የተያዘውን ለውጥ የተሳካ ለማድረግ፣ በአመለካከቱ የተቀየረ እና ለለውጥ ዝግጁ የሆነ የሰው
ሀይል ለመፍጠር፣ በቀላሉ ችግሮችን ለመፈተሽና ለመቅረፍ እንዲሁም መልካም አስተዳደርን ለማስፈን
የሚያስችሉ ከታች የተቀመጡትን የኮሙኒኬሽን ባህልና እምነቶችን ለማዳበርና ለማጎልበት ርብርብ ማድረግ
ይገባል፡፡
 ወቅታዊ መረጃዎችን የሚመለከተው ደንበኛ/ሰራተኛ እንዲያውቅ ማድረግ
 መረጃን የማካፈል ልምድን ማዳበር፣
 የተሟላ፣ ግልፅና ተአማኒነት ያለው የመረጃ ልውውጥ ሳይቆራረጥ በተከታታይ መስጠት፣
 በኮሙኒኬሽን ክፍተት ይሁን በሌላ የሚፈጠሩ ያለመጣጣምን በሂሳዊ መንገድ የሚሻሻሉበትን
መንገድ ማመቻቸት፣
 የምንሰጣቸው (የምናስተላልፋቸው) መረጃዎች (ውይይቶች) አዎንታዊ ምላሽን የሚቀሰቅሱ
እንዲሆኑ ማድረግ፣
 ሁልጊዜ በመልዕክት ላይ መሆን የሚለውን መሰረት ያደረጉ የመረጃ ባህሎችና እምነቶች
ማዳበር፣
 ትክክለኛ እና ጥራት ያለው መረጃ ለደንበኛ እና ለሰራተኛ በመስጠት ግንኙነትን ማሻሻል የሚሉ
ናቸው፡፡
2.3 የድርጅቱ ተልዕኮ፣ ርዕይ እና እሴቶች
ተልዕኮ
ጥራቱን በጠበቀ እና ኢኮኖሚያዊ በሆነ የፖስታ አገልግሎት ዜጎች እና ተቋማትን እርስ በእርሳቸውና ከሌላው
ዓለም ጋር ማስተሳሰር
ርዕይ
በ 2022 ዓ.ም በአፍሪካ ተወዳዳሪ የሆነ እና ለሀገራችን ዘላቂ ልማት የላቀ ሚና የሚጫወት የኢትዮጵያ ፖስታ
ተፈጥሮ ማየት
እሴት
 ደንበኛ ተኮር አገልግሎት፤

ደንበኞች የህልውናችን መሰረት መሆናቸውን በማወቅ በአግባቡ ልናስተናግዳቸውና

ልናገለግላቸው ይገባል፤

 ጥራት ያለው አገልግሎት፤

ዘመናዊ አሰራርን በመከተል ፍጥነትንና አስተማማኝነትን መሰረት ያደረገ አገልግሎት

እንሰጣለን፡፡

 ታማኝነት፤

ደንበኞቻችንን በታማኝነት እናገለግላለን፤

 ተጠያቂነት፤

ለምንሰጠው አገልግሎት ኃላፊነት እንወስዳለን

 ፈጠራን ማበረታታት

ሰራተኞች በግላቸውም ይሁን በቡድን ለሚያበረክቱት የአዕምሮ ውጤት ዕውቅና እንሰጣለን፤

2.4 የጠንካራጎን፣ ደካማ ጎን፣ መልካም አጋጣሚና ስጋት ትንተና(SWOT Analysis)


2.4.1 ጠንካራጎን
 በእቅድ የሚመራ አሰራር መከተል :- በተቻለ አቅም ያሉ ስራዎችን በአመታዊ እቅድ ውስጥ በማስገባት

እና በጀት በመመደብ ለመስራት ጥረት መደረጉ

 የሪፎርም ስራው ለሰራተኛው ተደራሽ የሚሆንበትን መንገድ ማመቻቸት ፡- ድርጅቱ አዲስ የጀመረውን
የሪፎርም ስራ ተከታታይነት ባለው መንገድ ለሰራተኛው እና ለደንበኛው ለማሳወቅ ፍላጎት እና ጥረት
መኖሩ
 የፖስታ ክበባት ፡- የፖስታ ክበባትን በመላው ሀገሪቱ ለማጠናከር እና የፊላቴሊ ተግባራት ለተማሪዎች
ለማስተዋወቅ በድርጅቱ ያለው ፍላጎት እየሰፋ መምጣት
 የደንበኞች ዳሰሣዊ ጥናት መሰራቱ፡- በመላው ሀገሪቱ ከደንበኞች ጋር በሚኖሩ መድረኮች ተሳታፊ
ለሚሆኑ ደንበኞች መጠይቆችን በመበተን የደንበኞች ዳሰሳዊ ጥናት መሰራቱ እና የደንበኞችን ፍላጎት
በየጊዜው ለማወቅ ጥረት መደረጉ
 በውስን የሰው ሀይል ስራዎችን ለመስራት ተነሳሽነት መኖሩ፡- የድርጅቱ አመራሮች ከተገልጋዩ
ህብረተሰብ ፊት ለፊት የሚገናኙበት ሁኔታ መፈጠሩ እና የደንበኞችን ችግሮች ለመፍታት የረጅም እና
የአጭር ጊዜ እቅዶች በማስቀመጥ መፍትሄ ለመፈለግ ጥረት መደረጉ
 ከሚዲያዎች ተቀራርቦ ከመስራት አንፃር፡- ሚዲያዎች መረጃ ፈልገው በሚመጡበት ወቅት በፍጥነት
መረጃውን በመስጠት ከሚዲያዎች ጋር ጥሩ ግንኙነት መፍጠር መቻሉ፤ የሚወጡ ዘገባዎች አብዛኛዎቹ

አዎንታዊ እንደሆኑ በሚዲያ ሞኒተሪነግ ማረጋገጥ መቻሉ፡፡ በድርጅቱ የሚዘጋጁ መድረኮችም ለሁሉም
ሚዲያዎች ክፍት በማድረግና በመጋበዝ ተገቢውን የሚዲያ ሽፋን እንዲያገኝ መቻሉ፡፡
 የሰራተኞች የስራ ተነሳሽነት መኖር፡- የዲፓርትመንቱ ሰራተኞች ድርጅቱን ወደተሻለ ደረጃ ለመለወጥ
የሚቀርብላቸውን ስራ በተገቢው መንገድ ለመስራት፣ደንበኞችን በተገቢው መንገድ ለማስተናገድ፣
ትእዛዝን ሳይጠብቁ ስራዎችን ለመስራት ተነሳሽነት መኖር እና ተጠቃሚነታቸውን ለማሳደግ
ተነሳሽነት መኖር፡፡

2.4.2 ደካማ ጎን

 የገጽታ ግንባታ ስራው በተፈለገው መጠን አለመሰራቱ


 ለክፍሉ የተሰጠው ትኩረት አነስተኛ መሆኑ
 በመመሪያ የተደራጀ አሰራር አለመኖሩ
 የድርጅቱ አመራር ለኮሙኒኬሽን ስራዎች ትኩረት አለመስጠቱ፡- ከኮሙኒኬሽን ዲፓርትመንቱ ጋር

በመገናኘት ለሚያጋጥሙ ችግሮች መፍትሄ አለመስጠት እና የትኩረት አቅጣጫ አለመስጠት እና


አለመደገፍ፡፡
 የኮሙኒኬሽንን ስራ ለመስራት የሚያስችል የሰው ኃይል አደረጃጀት አለመኖር፤ ድርጅቱ የተሰጠውን

ተልዕኮ ለመወጣት እንዲያስችለው የሪፎርም ስራዎችን ማከናወን ጀምሯል፡፡ በዚህ መሰረት ሰራተኞች
የትምህርት ዝግጅታቸውና የስራ ልምዳቸው ታይቶ የሚመጥኗቸው ቦታዎች እንዲመደቡ መደረግ
ይገባዋል፡፡ ከዚህ አንፃር የኮሙኒኬሽን እና አለም አቀፍ ግንኙነት ዲፓርትመንት ኮሙኒኬሽን እና አለም
አቀፍ ግኝኙነት በሚሉ ሁለት ቡድኖች ተዋቅሯል፡፡ በእነዚህ ቡድኖች ውስጥ ስራው በሚፈልገው ዕውቀት
እና ክህሎትሰራተኞች አልተሟሉም፡፡
 ለኮሙኒኬሽን ስራ የሚውሉ የግብዓት አቅርቦቶች አለመሻሻል ፡- ለኮሙኒኬሽን ስራ የሚውሉ ግብዓቶች
አቅርቦት በተገቢው መንገድ እየቀረቡ ባለመሆኑ ስራዎች ላይ ጫና እያደረሰ ይገኛል፡፡ በተለይ ከቴክኒካዊ

ስራ ጋር የተያያዙ ስራዎችን ለመስራት የሚያስችሉ ዘመናዊ ቁሳቁሶች አለመኖራቸው የተሟላ የመረጃ

ቋት እንዳይኖር አድርጓል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በዲፓርትመንቱ ለሚሰሩ ስራዎች ከጥራት ይልቅ ለአነስተኛ
ገንዘብ ትኩረት መሰጠቱ ስራው ላይ ከፍተት እንዲፈጠር አድርጓል፡፡
 ከቅርንጫፍ ፖስታ ቤቶች እና ከዲፓርትመንቶች ጋር ያለው የመረጃ ልውውጥ ደካማ መሆን ፡- ከተለያዩ

ዲፓርትመንቶች እና ቅርንጫፍ ፖስታ ቤቶች የሚመነጩ መረጃዎች በፍጥነት ወደ ዲፓርትመንቱ

የሚላኩበት እና መረጃው ተመልሶ ለህዝብ ተደራሽ የሚደረግበት ምቹ ሁኔታ አለመኖር፡፡


 የሚሰራጩ መረጃዎች አዘገጃጀትና አቀራረብ ሳቢነት መጓደል፡- የፖስታው ቢዝነስ ተፎካካሪ እየበዛበት
መምጣቱ እና ደንበኛውም ጥራትን መምረጡ ሁኔታዎች ያሳያሉ፡፡ በዚህም ለዲዛይን ስራዎች ትኩረት
መስጠት፣ በተለያዩ ሚዲያዎች የሚሰራጩ መረጃዎችም ደረጃቸውን የጠበቁ እና ሳቢ እና ወጥ
አለመሆናቸው፡፡ ብቃት ያለው ተንታኝ መረጃዎችን እንዲሰጥ አለመደረግ፤
 የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂዎችን አሟጦ አለመጠቀም፡- በድርጅቱ የፌስቡክ ገጽ የሚሰራጩ መረጃዎች

አነስተኛ መሆን፣ በየዕለቱ አዳዲስ መረጃዎች አለመጫን፤ የገጹ ተከታዮች ቁጥርም አነስተኛ መሆን እና
መረጃዎችንም ቡስት ለማድረግ አለመሞከሩ፡፡ ድረ-ገፁ ሙሉ በሙሉ አለመስራቱ እና ሳቢ አለመሆኑ፣
ዩቲውብ ቻናል እና ትዊተር ገጽ እና ሌሎች የማህበራዊ ድረ-ገጾች ከመጠቀም አንፃር ከፍተኛ ክፍተቶች
መኖራቸው፡፡
 በወቅታዊ ጉዳዮች መጠመድ፡- የተግባቦት ስራዎቻችንን ስትራቴጂክ ከሆኑ ጉዳዮች ይልቅ በወቅታዊ
ጉዳዮች ማተኮር፡፡ ይህም ለከፍተኛ አመራሩ በኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዙሪያ የማማከር ስራ ላይ ትኩረት

እንዳይደረግ አድርጓል፡፡
2.4.3 መልካም አጋጣሚዎች
 አማራጭ የሆኑ የተለያዩ መገናኛ ብዙሃን መገኘታቸው
 የአለም ፖስታ ህብረት ለኮሙኒኬሽን ስራ ትኩረት መስጠት
 የትምህርት ቤት ፖስታ ክበባትን ለማጠናከር በጎ ፈቃደኝነት መኖር
 የገፅታ ገንባታው ሥራው እየተጠናከረ መምጣት
 የማህበራዊ ድረ-ገፅ አጠቃቀም እየተጠናከረ መምጣት ፡- ማህበራዊ ሚዲያዎችን በመጠቀም

መረጃዎችን በአነስተኛ ወጪ ማሰራጨት መጀመሩ እንደ መልካም አጋጣሚ የሚወሰድና ወደፊትም

ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት ነው፡፡ የደንበኞችንና የሰራተኞችን ጥቆማዎች በቀላሉ ማግኘት ማስቻሉ
እንዲሁም በቀላሉ ብዙ ሰዎች መረጃው እንዲደርሳቸው ጥረት መደረጉ እና የተከታዮች ቁጥርም
ጭማሪ እያሳየ መምጣቱ፡፡

2.4.4 ስጋቶች
 አሉታዊ ገጽታ በፍጥነት አለመቀየር ፡- ከዚህ ቀደም ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ ደንበኛው

የነበረው አመለካከት አሉታዊ ጎን የሚያመዝን ነው፡፡ ምንም እንኳን በአሁኑ ወቅት የሪፎርም ስራ

በመስራት በለውጥ ሂደት ላይ የሚገኝ ተቋም ቢሆንም ቀደም ሲል የነበረውን ስም ለመቀየር የራሱ ጊዜ

መወሰዱ የማይቀር ነው፡፡ አመለካከት የረጅም ጊዜ ሂደት በመሆኑ ቀደም ሲል የነበረው የተቋሙ ገጽታ

አሁን የምንሰራው ስራ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እንደሚያሳድር ግልፅ ነው፡፡ ደንበኛ ለውጦችን እያየ

በሂደት ድርጅቱ የሚሰራቸውን አበረታች ስራዎች ይደግፋል የሚል ፅኑ እምነት አለን፡፡ ይህን ዕውን

እንዲሆን ግን ሁሉም የድርጅቱ ሰራተኛ ቁርጠኝነትና ቀጣይነት ያለው ተሳትፎ አስፈላጊ ነው፡፡
 የብልሹ አሰራሮች መኖር፡- በድርጅቱ የተለያዩ ዲፓርትመንቶች ከብልሹ አሰራር ጋር በተያያዘ የሚወጡ
መረጃዎች አሉ፡፡ መሰል ተግባር ላይ የተሰማሩ ህገወጥ ስራቸው እንዳይታወቅባቸው እና የገንዘብ
ምንጫቸው እንዳይደርቅ የተለያዩ ፕሮፓጋንዳዎችን ሊያሰራጩ ይችላሉ፡፡ ለውጡን ለመደገፍ ፍላጎት
ያለውን ሰራተኛ እንዲሁም ደንበኛን አፍራሽ መረጃዎች እያሰራጩ ብዥታ ሊፈጥሩበት ይችላሉ፡፡
 የበጀት እጥረት ፡- ከሚዲያ ተቋማት፣ ከአማካሪ ድርጅቶችና ከሌሎች አጋር ድርጅቶች ጋር በመቀናጀት

ለሚሰሩ የኮሙኒኬሽን ስራዎች የበጀት እጥረት ሊያጋጥም ይችላል የሚል ስጋት አለ፡፡ የሚተላለፉ
መልዕክቶች ተቀባይነት እንዲያገኙ የተመረጡ የተግባቦት ስራዎችን ፕሮፌሽናል በሆኑ ተቋማት

ማሰራት አስፈሊጊ ነው፡፡ ስለሆነም ይህንን ለማሳካት ለስራው በቂ በጀት ይዞ መንቀሳቀስ ያስፈልጋል፡፡
 ለክፍሉ የሚገባውን ትኩረት አለመስጠት፡ - በድርጅቱ የውስጥ እና የውጭ ኮሙኒኬሽን ስራው በጥሩ
ሁኔታ እንዲሰራ መሻት ቢኖርም ክፍሉን ለማጠናከር ፍላጎት አለመኖር፡፡

ክፍል ሦስት
አተገባበር
የኮሙዩኒኬሽንና የህዝብ ግንኙነት ስትራቴጂውን ዕለት ተዕለት የመተግበርና አተገባበሩን የመከታተል
ኃላፊነት የኮሙዩኒኬሽን እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዲፓርትመንት ቺፍ ኦፊሰሩ ነው፡፡ ውጤታማ የሆነ

የኮሙኒኬሽን ስራ ለመስራት እንዲያመች ቁልፍ መልእክቶች ተለይተው በዋና ስራ አስፈፃሚ፣ በምክትል ዋና

ስራ አስፈጻሚዎች፣ በኮሙኒኬሽን ቺፍ ኦፊሰር እና እንደ አስፈላጊነቱ በዲፓርትመንቶች ቺፍ ኦፊሰሮች


ከዚያም ሲያልፍ በሰራተኞች የኮሙኒኬሽን ስራ የሚሰራ ይሆናል፡፡
የኮሙኒኬሽን ስራ የተቀናጀ ጥረት የሚፈልግ በመሆኑ ያሉትን ሃብቶችና የተግባቦት መንገዶች አቀናጅቶ

መንቀሳቀስ ይፈልጋል፡፡ የሚተላለፉ መልእክቶችም ከአንድ ቋት የሚወጡና ተቋማዊ ተልዕኮን የሚያሳኩ

እንዲሆኑ መልዕክቶቹ የሚተላለፉበትን መንገድ መምረጥና መወሰን ተገቢ ይሆናል፡፡ ይህም ስትራቴጂካዊ

አቅጣጫ በማስቀመጥ ግቡ የተለየ፣ትኩረት የሚስብ መልዕክት ማስተላለፍ ያስችላል፡፡

3.1 የኮሙኒኬሽን ዘዴዎች


የተቋመን ተልዕኮ፣ ርዕይ፣ ዓላማ፣ እንቅስቃሴና ተያያዥ ጉዳዮችን ለታላሚ ተደራሲያን ለማስተላለፍ የተለያዩ
የኮሙኒኬሽን ዘዴዎችን መጠቀም ያስፈልጋል፡፡ በዚህ መሠረት ቀጥሎ በተዘረዘሩት የኮሙኒኬሽን ዘዴዎች

በመጠቀም የተቋሙን ቁልፍ መልዕክት ለማስተላለፍ ጥረት ይደረጋል፡፡

3.1.1 የገፅ ለገፅ ግኝኙነት፡-


ይህ የኮሙኒኬሽን ዘዴ ስብሰባዎችን፣ ወርክሾፓችን፣ ገለፃዎችንና ፕረዘንቴሽኖችን ያጠቃልላል፡፡ በዚህ ዘዴ

ከማናጀር ጀምሮ እስከ ዋና ስራ አስፈፃሚ መልዕክቶችን ለማስተላለፍ ሊጠቀሙ ይችላሉ፡፡


3.1.2 የህዝብ ግንኙነት፡-
የተቋሙን ገፅታ በሚገነቡና ስራዎቹን በሚያስተዋውቁ አግባቦች ላይ መሳተፊያ መንገድ ሲሆን፤ ጽሁፎችን

አዘጋጅቶ ለተለያዩ መገናኛ ብዙሃን የመስጠትና የተቋሙን ስራዎች ማስተዋወቅ፣ በስብሰባዎች እና አውደ

ርዕዮች መሳተፍ፣ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በሚሳተፉባቸው መድረኮች ላይ መገኘትን ያካትታል፡፡


3.1.3 ፐብሊሲቲዎች፡-

መረጃ ለመስጠት፣ የተቋሙ ይፋዊ እንቅስቃሴዎች ለማስተዋወቅ፣ ምልመላና መረጣ ለማከናወን፣ ለባለ ድርሻ

አካላት ጥሪ ለማስተላለፍና መረጃ ለመለዋወጥ ተግባራዊ ሊሆን የሚችል የኮሙኒኬሽን ዘዴ ነው፡፡


3.1.4 የህትመት ውጤቶች፡-
የተለያዩ የህትመት ውጤቶችን (መጽሔት፣ጋዜጣ፣ ቡክሌት፣ብሮሸር፣……)በመጠቀም መልዕክት

ለማስተላለፊያነት የሚያገለግል ነው፡፡ ለምሳሌ፡- በየወሩ የሚታተመው ፖስታ ጋዜጣ፣ በዓመት ሁለት ጊዜ
የሚታተመው ዜና ፖስታ መጽሔት፤
3.1.5 ኦን ላየን ሚዲያ/ኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ
ኦን ላየን ሚዲያ ድረ-ገጽ እና ማህበራዊ ሚዲያዎችን የሚያካትት ሲሆን በይነ መረብ /Internet/ በመጠቀም

በተቋሙ ዌብሳይትና ማህበራዊ ሚዲያ አማካይነት መረጃ ለማስተላለፍ ጥቅም ላይ የሚውል ነው፡፡ ከዚህ
በተጨማሪ በብሮድካስት ሚዲያው (ቴሌቪዥንና ሬዲዮ) በአየር ሰዓት ኪራይ እና ተመርጠው ስፓንሰር

በሚደረጉ ፕሮግራሞች ላይ ተቋማዊ መልዕክት የሚተላለፍበት ነው፡፡


3.1.6 የድርጅቱ ሁነቶች፡-
በድርጅቱ የተለያዩ ሁነቶችን በማስተባበርና ከወቅቱ ጋር ሊሄዱ የሚችሉ ሁነቶችን በመቅረጽ በተቋሙ ሊሰሩ
የሚችሉና እንደ አስፈሊጊነቱ ልምድ ባላቸዉ የሁነትና ኮሙዩኒኬሽን ተቋማት በመታገዝ የሚከናወን ነው፡፡

ለምሳሌ፡- የዓለም ፖስታ ቀን፣የአፍሪካ ፖስታ ቀን፣የሰራተኞች ቀን፣ የእግር ጉዞ ፕሮግራሞች፣ወዘተ


3.2 የሚዲያ አጠቃቀም እና አስተዳደር

የድርጅቱን እንቅስቃሴ የተመለከተ ዜና እና መረጃ በተገቢው ሁኔታ ለማስተላለፍ ውጤታማ የሆኑ የዜና
ተቋማት /የመገናኛ ብዙሃን ግንኙነት ሊኖር ይገባል፡፡ ይህ ግንኙነት ከድርጅቱ የኮሙኒኬሽን ቺፍ ኦፊሰር ባሻገር

የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች ሊመሩትና ሲኒየር ባለሙያዎች ሊሳተፉበት ይገባል፡፡ ከዚሁ ጎን ለጎን የድርጅቱ ዋና
ዋና እንቅስቃሴዎች የዜና ሽፋን በሚያገኙበት ጊዜ ሚዲያዎች መረጃዎቹና ባላቸው የዜና ፋይዳ (News

Value) ለይተው ትኩረት ለሚሰጧቸው ጉዳዮች ተገቢውን ትኩረት እንዲሰጡ አዎንታዊ ግፊት ማሳደሩ
አስፈላጊ ይሆናል፡፡
የድርጅቱ ሰራተኞች ለመገናኛ ብዙሃን መረጃ/ቃለመጠይቅ በሚሰጡበት ጊዜ እርስ በእርሱም ሆነ ጉዳዩ

የሚመለከታቸው የስራ ኃላፊዎች ከሰጡት መረጃ ጋር እንዳይጋጭ እና አሉታዊ መልዕክት እንዳያስተላልፉ

ተገቢው ክትትልና ጥንቃቄ መደረግ ይኖርበታል፡፡ ለመረጃ ግልፅነትና ቅልጥፍና መረጃ የሚሰጡ አካላትን

መለየትና ተገቢውን የመገናኛ ብዙሃን አጠቃቀም ስልጠና እንዲያገኙ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ለድርጅቱ

ኃላፊዎችና ባለሙያዎች የሚሰጠው ስልጠና የተቋሙን ተልዕኮና ርዕይ እንዴት ማስተዋወቅ

እንዳለባቸው የሚያሳይ /የሚጠቁም መሆን አለበት፡፡

በሌላ በኩል የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮችና ባለሙያዎች መደበኛ ያልሆኑና ከተቋማዊ ስራዎች ጋር ቀጥተኛ

ግንኙነት የላቸውን ቃለመጠይቆች እንዲያደርጉ በመፍቀድና ሁኔታዎችን በማመቻቸት ድርጅቱን በተለያዩ


መድረኮች የማስተዋወቅ ስራ የሚሰሩበትን እድል መፍጠር ያስፈልጋል፡፡ እንዲህ ዓይነት አሰራር መፈጠሩ

የተቋም ገፅታ ከመገንባት ባሻገር ከመገናኛ ብዙሃን ጋር መልካም ግንኙነት ለመፍጠር ያግዛል፡፡

ክፍል አራት
የኮሙኒኬሽንና የህዝብ ግንኙነት ስትራቴጂ
4.1 ቁልፍ መልዕክቶች
ድርጅቱ በአዋጅ ከተሰጠው ተልዕኮ በመነሳት ማስተለለፍ የሚፈልጋቸው ቁልፍ መልዕክቶች ከተልዕኮው
በመነጩ ምሰሶዎች (Pillars) ላይ የተመሰረቱ እንዲሆኑ ከፍተኛ ጥረት ያደርጋል፡፡ በእነዚህ ምሰሶዎች ላይ
ተመስርቶ የሚቀረፀውን መልዕክት ወጥ በሆነ መንገድ በአግባቡ እንዲተላለፍ ማድረግም መሰረታዊ ጉዳይ

ነው፡፡ ስለሆነም ቀጥሎ የተመለከቱት ቁልፍ መልዕክቶች የተቋሙን ተልዕኮ የሚያሳኩ ናቸው ተብለው

ተለይተዋል፡፡

 ድርጅቱ ለደንበኞቹ የሚሰጠውን አገልግሎት ፈጣንና ዘመናዊ ለማድረግ የሚያስችል የለውጥ


ስራዎችን ዘርግቷል፡፡
 ድርጅቱ የነደፋቸውን ግቦች ለማሳካት ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት ይሰራል፡፡

 በድርጅቱ ቁልፍ ተግባራት ላይ የደንበኞችና ባለድርሻ አካላት ድምፅ እንዲሰማና እንዲሳተፉ ለማድረግ
በትጋት ይሰራል፡፡
 ለድርጅቱ ተልዕኮ ስኬት የተቋሙ ሰራተኞች የጎላ ድርሻ አላቸው፡፡
 በመልካም ስነምግባርና ቅልጥፍና የታገዘ አገልግሎት በመስጠት የድርጅታችንን ስምና ዝና እንገነባለን፡፡
 የድርጅቱን ገቢ ለማሳደግ ትኩረት ሰጥተን መስራት ይኖርብናል፡፡
 የመረጃ አስተዲደር ሰርዓታችንን የሚያሻሽሉ ስራዎች ላይ ትኩረት ሰጥተን እንሰራለን፡፡
 የአገልግሎት አሰጣጥን እና የደንበኛ አገልግሎት አፈጻጸምን ለማሻሻል የሚያግዙ ምቹ ሁኔታዎችን
እንፈጥራለን፡፡
4.2 ስትራቴጂያዊ አጋሮች
 የኮሙኒኬሽን ባለስልጣን
 ኢትዮቴል ኮም
 የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር
 የዓለም ፖስታ ህብረት
 የተለያዩ አየር መንገዶች
 የተለያዩ የየብስ የህዝብ ትራንስፖርት ማህበራት
 የአፍሪካ ፖስታ ህብረት
 ጉሙሩክ ኮሚሽን
 የመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ
 ዲኤች ኤል
 ግብርና ሚኒስቴር
 መድሀኒት ቁጥጥር ባለስልጣን
 የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፓሬሽን

4.3 የግንኙነት መርሆዎች (Communication Principles)


ድርጅቱ ከውስጥ እና ከውጪ ደንበኞች የሚኖረው ግንኙነት የኮሙኒኬሽን አግባብ ቀጥሎ በተዘረዘሩት
መርሆዎች ላይ ይመሰረታል፡፡
 በድርጅቱ ተልዕኮና ግብ ላይ መመስረት፣
 ግልፅነትና ቀናነት የተላበሰ መሆን፣
 አሻሚ ባልሆነ መንገድ መግለፅ፣
 ወቅታዊና በቀላሉ ሊረዱት የሚችሉት መሆን፣
 የተለያዩ የኮሙኒኬሽን መሳሪያዎችን (Communication tools) የሚጠቀም መሆን (የጽሁፍ፣ የቃል፣
የምስልና ኤሌክትሮኒክ ኮሙዩኒኬሽኖችን መጠቀም)
 ከተቋማዊ የለውጥና አሰራር ደረጃዎች (Standards) ጋር አብረው የሚጓዙ መሆን፣
 የአገልግሎት አሰጣጥን የላቀ የሚያደርግ መርሆዎችን ይከተላል፡፡
4.4 የድርጅቱ የውስጥ ኮሙኒኬሽን (Internal Comunication)
ውጤታማ የሆነ የውስጥ /ድርጅታዊ ግንኙነት የድርጅቱን ተልዕኮና ግቦችን ለማሳካት ወሳኝ እንደሆነ
ይታመናል፡፡ በመሆኑም የድርጅቱ ሠራተኞች የድርጅቱን ርዕይ፣ ዓላማና ተልዕኮ በአግባቡ ከተረዱ
የተጣለባቸውን ኃላፊነት በታማኝነት በመወጣት ደንበኞችን የሚያረካ አገልግሎት መስጠት ይችላሉ፡፡ ስለሆነም
ጠንካራ የውስጥ /ተቋማዊ ግንኙነት የሚመሰረትበት ግልፅ አሰራር መዘርጋት ያስፈልጋል፡፡ ለዚህ የሚያስፈልጉት
የግንኙነት/ ኮሙኒኬሽን ስሌቶች ቀጥሎ በዝርዝር ተቀምጠዋል፡፡

4.4.1 የቡድን ግንባታና ገለፃ


በአሰራሮችና አፈፃፀም ላይ የሚታዩ ጥንካሬዎችን የበለጠ የሚያጎለብትና የሚያሰፋ እንዲሁም ድክመቶችን
የሚያርም በተወሰነ ጊዜ ውስጥ የሚከናወን እንደየስራው ባህርይ አመቺ ሰዓት ተመርጦለት የሚከናወን በየ 15
ቀኑ የጠዋት ገለጻ (Morning Briefing) ወይም የምሳ ሰዓት ገለፃ (Lunch Briefing) እንዲኖር ማድረግ
ያስፈልጋል፡፡ የቡድኑ የስራ እንቅስቃሴም እየተገመገመ በየደረጃው ለሚገኙ የስራ ኃላፊዎች በመጨረሻም ለዋና
ስራ አስፈጻሚ ሪፖርት ይደረጋል፡፡

የቡድን ገለፃው መልዕክት ለዲፓርትመንቱ በተሰጠው ዋንኛ ተግባር ላይ የሚተኩር ይሆናል፡፡ የሚመረጠው
መልዕክትም እንደአስፈሊጊነቱ ለዲፓርትመንት መሪዎች በቃል/በስልክ፣ በኢሜይል፣ ወይም በሌላ ተመራጭ
በሆነ አመቺ መንገድ እንዲደርስ እና ለየቡድኖቹ ካስኬድ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ በዚህ መነሻነት መልዕክቱ
በየቡድኑ ገለጻ እና ውይይት የሚደረግበት ነው፡፡
4.4.2 ኮሙዩኒኬተሮችን መጠቀም
በዲፓርትመንቶች የሚከናወኑ ስራዎችን ታሳቢ ያደረጉ መልዕክቶችን ለመቅረፅና በተገቢው መንገድ
ለማስተላለፍ እንዲሁም የኮሙዩኒኬሽን ስትራቴጂውን ለመተግበር ለዲፓርተመንቱ ቋሚ ኮሙዩኒኬተሮችን
(Focal communicator/person) መመደብ አስፈሊጊ ይሆናል፡፡ ይህ አሰራር ኮሙኒኬተሮቹ
የዲፓርትመንቶችን ስራዎች በቅርበት ተረድቶ የሚፈለገውን መልዕክት ለማስተላለፍ ያስችላቸዋል ተብሎ
ይታመናል፡፡ ኮሙዩኒኬተሮቹ በኮሙኒኬሽን እና አለም አቀፍ ግኝኙነት ዲፓርትመንት ውስጥ ሆነው
የተመደቡበትን የስራ ሂደት ስራዎች በአግባቡ እንዲተዋወቁ የሚሰሩ ይሆናል፡፡

4.4.1.1 የኮሙዩኒኬተሮች ሚና ፡-
 በስራ ክፍሎች ውስጥ የኮሙኒኬሽንና የህዝብ ግንኙነት ስትራቴጂውን አፈፃፀምን ማገዝ፣
 ለስራ ክፍልቹ የኮሙዩኒኬሽን ወኪል (Laison) ሆኖ ማገልገል፣
 ስራ ክፍልቹ የኮሙኒኬሽን ፍላጎቶችን በመለየት ለኮሙኒኬሽን እና አለም አቀፍ ግኝኙነት ቺፍ ኦፊሰር
ማቅረብ፣
 የስራ ክፍልቹን መረጃዎችን በመለየት በመገናኛ ብዙሃን ተገቢው ሽፋን የሚያገኙበትን ዘዴ በመቀየስ
የገፅታ ግንባታ ስራ እንዲሰራ ለዲፓርትመንቱ ግብአቶችን አደራጅቶ ማቅረብ፣
 የመገናኛ ብዙሃን ስራ ክፍልቹን የተመለከተ መረጃ ወይም ምላሽ ሲፈልጉ መረጃ ማደራጀት
የኮሙዩኒኬተሮቹ ሚና ይሆናል፡፡
4.4.3 የውስጥ ህትመቶች
በድርጅቱ አሰራሮች ላይ በማተኮር በሚታተመው ፖስታ ጋዜጣ ላይ የተቋሙን ርዕይ፣ ተልዕኮ፣ አፈፃፀም፣
የሞዴል ሠራተኞች/ፈጻሚዎች ድርሻ፣ አርአያነት ያለው ተግባር የፈጸሙ ሰራኞችን በማቅረብ ሌሎች
ሰራተኞችን ለተቋሙ ተልዕኮ ስኬት ለማነሳሳት ሊያግዝ ይችላል፡፡

4.4.4 መልዕክቶች ማስተላለፍ


አገልግሎት አሰጣጥን ቀልጣፋ ለማድረግና የስራ ውድድር ለመፍጠር የሚያግዙ፣ አስተማሪና አዝናኝ
የሆኑ፣ሰራተኞች ሊወያዩባቸው የሚችሉ ጉዳዮችን የያዙ ይዘቶችን በማስታወቂያ ሰሌዳዎች ላይ እንዲለጠፉ፣
በአውትሉክ እንዲተላለፉ በማድረግ የተሻለ አገልግሎት አሰጣጥ መዘርጋት ይቻላል፡፡ ወቅታዊ መረጃዎችን
ተከታትሎ እንዲለጠፍና በሰራተኛው እንዲታወቅ ማድረግ የቺፍ ኦፊሰሩ እና የኮሙዩኒኬተሮች ኃላፊነት
ይሆናል፡፡
ስለድርጅቱ፣ ስለደንበኛ እና ስለመልዕክት አጭር እና ተከታታይነት ያላቸውን መልዕክቶች በመቅረፅ ሰራተኛው
እንዲያውቀው በድርጅቱ አጭር መልዕክት መላኪያ ማሳወቅ፡፡
4.4.5 የሠራተኞች ቀን
በተቋም ደረጃ የሠራተኞች ቀን እንዲከበር በማድረግ መልካም የሆነ የእርስ በእርስ ግንኙነትን ማጠናከርና
ሠራተኞች ለድርጅቱ ተልዕኮ ስኬት በጋራ እንዲሰለፉ ማድረግ ይቻላል፡፡ በዕለቱ እንዲተላለፉ የሚደረጉት
መልዕክቶች ሠራተኛውን በአንድ መንፈስ እንዲያስብ የሚያደርገው እንደሚሆን ይታመናል፡፡ በተጨማሪም
በስራ ክፍሎች መካከል መናበብና ቅንጅት እንዲኖር የሚያግዝም ይሆናል፡፡

N.B. የድርጅቱን ሠራተኞች ቀን በእግር ጉዞ እንዲከበር ማድረግ ይቻላል፡፡


4.4.6 የሰራተኛ መድረክ
በድርጅቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ እና የበላይ አመራሮች አጠቃላይ የድርጅቱን እንቅስቃሴ እና አፈጻጸምን
አስመልክተው በአመት ሁለት ጊዜ ማለትም በጀት ከተዘጋ በኋላ እና ከስድስት ወር ክንውን በኋላ ውይይት
ያደርጋል፡፡ ከተቻለም ከቦርድ ስራ አመራር ጋር ጊዜዎችን በማመቻቸት በመላው ሀገሪቱ ሰራተኞችን
በማግኘት ማወያየት የሚችሉበት ወይም የስራ እንቅስቃሴውን የሚጎበኙበት አሰራር ይፈጠራል፡፡ በዚህም
ከሰራተኛው ጋር በቅርበት ተገናኝቶ መወያየት ስለሚያስችል ችግሮችን መፍታት እና አላማዎችን ማሳወቅ
ይቻላል፡፡
N.B የውስጥ ኮሙኒኬሽን ፖሊሲ ከዚህ ሰነድ ጋር ተያይዞ ቀርቧል፡፡
4.5 የውጭ ግኝኙነት (External Communication/Relation)
4.5.1 ሁነቶች
በኮሙኒኬሽን እና አለም አቀፍ ግንኙነት ዲፓርትመንት በሚዘጋጅ እቅድ ላይ ተመስርቶ በየሩብ ዓመቱ
ከደንበኞች ጋር መገናኘት የሚያስችሉ ኹነቶች ሲሆኑ ኹነቶቹ ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይም ምክትል ዋና ስራ
አስፈጻሚዎች የሚመሯቸውና የሚገኙባቸው ዝግጅቶችን ያካትታል፡፡

4.5.2 የህትመትና የአየር ሰዓት ግዢ ስራዎች


በድርጅቱ የኮሙኒኬሽን ዲፓርትመንት የሚዘጋጁት የህትመት ውጤቶች(ፖስታ ቡለቲን፣ ዜና ፖስታ
መጽሔት) ፣ የሬዲዮና ቴሌቭዥን የአየር ሰዓት ግዢ አማካይነት ስለተቋሙ ተልዕኮና እንቅስቃሴ እንዲሁም
ስለተጀመሩት የለውጥ ስራዎች በስፋት ማስተዋወቅ ይገባል፡፡ የህትመትና የፕሮዳክሽን ስራዎቹ ላይ
የሚወጡት ይዘቶች በመወሰን ሁሉንም ተቋማዊ የለውጥ እንቅስቃሴዎች በፍትሃዊነት የሚዳስሱና ቁልፍ
የድርጅቱን መልእክቶች የሚያስተዋውቁ እንዲሆኑ ጥረት ይደረጋል፡፡ የደንበኞች ፍላጎትና ጥያቄ እንዲሁም
የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ በጥንቃቄ እየተመረጠ የሚካተትበትም ይሆናል፡፡
በህትመት ስራዎቹ ላይ በየጊዜው የይዘት፣ የአቀራረብና የገፀ ዕይታ (Layout) ለውጥ ለማድረግና የህትመቱን
ተቀባይነት ለማሳደግ በጥናት ላይ የተመሰረተ ማሻሻያ ማድረግ ይገባል፡፡ በተመሳሳይም የቴሌቭዥንና የሬዲዮ
ፕሮግራሞችም ለታላሚ ታዲሚዎች የሚሆኑ ይዘትና አቀራረቦችን ይዘው እንዲመጡ ለማድረግ
ፕሮግራሞችን በማጥናት መከለስ ያስፈልጋል፡፡

4.5.3 ድረ-ገፅ እና ሶሻል ሚዲያዎች


የተቋሙ ድረ-ገፅ www.ethiopostal.com ለደንበኞች እና ለመረጃ ፈላጊው ጠቃሚ የሆኑ የድርጅቱን
አገልግሎቶች እና አጠቃቀም ፣ ርዕይና ተልዕኮ አካቶ መገኘት ይኖርበታል፡፡
ድረ-ገፁ በአዲስ መልክ እየተገነባ መሆኑም ለአጠቃቀም አመቺ የሆኑ እና ለእይታ ሳቢ እንዲሆን አድርጎ
ማስተካከል ይቻላል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ከዚህ ቀደም በድረገጹ ያልነበሩ ጉዳዮችን አካቶ ለማቅረብ መንገድ
ይከፍታል፡፡
ሶሻል ሚዲያዎችን በተመለከተም ተከታታይነት ባለው መልኩ በየጊዜው መረጃዎችን መለጠፍ፣ ሳቢ የሆኑ
ዲዛይኖችን መጠቀም፣ ጥራት ያላቸው ፎቶዎችን መለጠፍ እና እነዚህን ተግባራት የሚያከናውን የሰለጠነ ሰው
በበመደብ የኮሙኒኬሽኑ ስራ የተሳለጠ እንዲሆን ማድረግ ይቻላል፡፡

4.5.4 የቃል አቀባይነት ስራ


ከተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ጋር በተመረጡ ርዕሰ ጉዳዮች እና የፖሊሲ ጉዳዮች ላይ በኮሙኒኬሽን እና አለም
አቀፍ ግንኙነት ቺፍ ኦፊሰር ወይም በዋና ስራ አስፈጻሚ በተወከሉ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች አማካይነት በገዕ
ለገዕ ወይም በስልክ የሚሰጥ ገለፃ/ ማብራሪያ ነው፡፡ እንዲህ ዓይነት ማብራሪያ በወር ውስጥ ቢያንስ አንድ ጊዜ
የሚሰጥ ቢሆን ይመረጣል፡፡ ርዕሰ ጉዳዩን የመምረጥ ኃላፊነት የኮሙዩኒኬሽን እና አለም አቀፍ ግኝኙነት ቺፍ
ኦፊሰር ይሆናል፡፡፡
4.5.5 የፕሬስ ኮንፈረንስ / መግለጫ
በዋና ስራ አስፈጻሚ ወይም በሌሎች ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በወሳኝ ተቋማዊ ጉዳዮች ላይ በማተኮር ቢያንስ
በ 3 ወር አንድ ጊዜ የሚሰጥ የፕሬስ መግለጫ ነው፡፡ ይህ መግለጫ የባለድርሻ አካላትና የደንበኞችን ጉዲይ፣
አገልግሎት አሰጣጥ ላይ እንዲሁም የመንግስት የፖሊሲ አቅጣጫዎች ላይ በሚያተኩሩ አንኳር ርዕሰ ጉዳዮች
ላይ የሚያጠነጥን እንዲሆን ይጠበቃል፡፡
4.5.6 ፕሬስ ሪሊዝ
በድርጅቱ ቁልፍ ስራዎች ላይ እንዲሁም ሁነቶችን በማስመልከት ለመገናኛ ብዙሃን በጽሁፍ መረጃ በመላክ
የሚከናወን የኮሙኒኬሽን ተግባር ነው፡፡ ይህም የዜና መረጃና ጥቆማ መላክን ያካትታል፡፡
4.5.7 ማማከር
ለድርጅቱ የሚመጡ ሰነዶች፣ መረጃዎች እና ሌሎች ጉዳዮችን አስመልክቶ ለዋና ስራ አስፈጻሚ ምክር የማቅረብ
እና ፕሮፖዛል የማዘጋጀት ስራ ይሰራል፡፡
4.5.8 ግራፊክስ፣ህትመት ሥራዎች የኮሙኒኬሽንና የህዝብ ግንኙነት ስትራቴጂ የተቀናጀ የኮሙዩኒኬሽን
መሳሪያዎች መጠቀምን ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም የተቋሙን ቁልፍ መልዕክቶችና አዲሱን ሎጎ ለማስተዋወቅ በአንድ
የኮሙዩኒኬሽን ዘዴ ሳይወሰኑ የተለያዩ የኮሙኒኬሽን አግባቦችን በተቀናጀ መልኩ መጠቀም የግድ ይላል፡፡
ስለሆነም በግራፊክ ዲዛይን የታገዘ አዲሱን ሎጎ የማስተዋወቅ፣ የህትመት ስራ፣ የፐብሊሲቲ ስራ መስራት
ይገባል፡፡
4.6 የውስጥ ኮሙኒኬሽን ማጠቃለያ
የተመረጠው
የኮሙኒኬሽን ዘዴ ዝርዝር ተግባራት የጊዜ ሰሌዳ

 የቡድን ገለጻ (Briefing) ስርዓት መዘርጋት፣


 በተመረጡ ዲፓርትመንቶች የገለጻ ስርዓቱን ማስጀመርና ለሁሉም
የቡድን ግንባታ እና ገለጻ ክፍሎች ካስኬድ ማድረግ፣ በየ 15 ቀኑ የሚደረግ
 እያንዳንዱ የስራ ክፍል የራሱን የገለጻ ስርዓት እንዲዘረጋ ማድረግ፣
 አፈፃፀሙን በቅርበት መከታተል፣ መገምገምና ጉድለቶችን ማረም፣
ኮሙዩኒኬተሮችን  ለስራ ክፍሎች ኮሙዩኒኬተሮችን መመደብ፣
መጠቀም  በየዲፓርትመንቱ የኮሙዩኒኬሽን ትኩረት ሚፈልጉ ጉዳዮችን እንዲለዩ በየሳምንቱ
ማድረግና የግንኙነት አግባቡን መወሰን፣

ጋዜጣው በየወሩ፣ መጽሔቱ በአመት ሁለት

የውስጥ ህትመቶች  የጋዜጣና መጽሔት፣ ዜና መጽሔት፣ብሮሸር ህትመት፣ ፍላየር ጊዜ፣ ብሮሸር በአመት ሁለት ጊዜ፣ ፍላየር
በአመት አንድ ጊዜ

 የማስታወቂያ ሰሌዳውን የወቅታዊ መረጃዎች መለዋወጫ ማድረግ፣ የማስታወቂያ ሴሌዳ በየሳምንቱ፣ በየ 15


አጫጭር መልዕክቶች  ሞባይል ኖቲፊኬሽን ቀኑ በሞባይል እና በአውትሉክ መልዕክት
 አውት ሉክን በመጠቀም መረጃዎችን ማስተላለፍ ማስተላለፍ
የሰራተኞች ቀን  የእግር ጉዞ በማድረግ ተቋማዊ ንቅናቄ መፍጠር፣ በአመት አንድ ጊዜ
 በስራ ክፍሎች መካከል መናበብና በጋራ መስራት የሚያስችል

የተቋም/ሰራተኞች ቀን መወሰንና ማክበር፣


የሰራተኞች መድረክ  በአመት ሁለት ጊዜ የሰራተኞች ስብሰባ ነሐሴ እና የካቲት

4.7 የውጭ ግኝኙነት ማጠቃለያ


የተመረጠ የኮሙዩኒኬሽን የጊዜ ሰሌዳ
ዘዴ ዝርዝር ተግባራት
 የሩብ ዓመት የደንብኞች መድረክ በየሩብ አመቱ
ሁነቶች

 ጋዜጣው በየወሩ፣ መጽሔቱ


የህትመትና የአየር ሰዓት
 በህትመት ስራዎች (ፖስታ ጋዜጣ እና ዜና ፖስታ) ላይ የሚወጡ በአመት ሁለት ጊዜ፣ ብሮሸር
ግዢ ስራዎች
በአመት ሁለት ጊዜ፣ ፍላየር
ጽሁፎችን ይዘት፣ የአቀራረብ ስታልይል እና ገፀ - ዕይታ (Layout)
በአመት አንድ ጊዜ
ማሻሻል፣
 በአመት አራት አራት ጊዜ
 የቴሌቭዥንና የሬድዮ አየር ሰዓት ግዢ

 አሁን ያለውን ድረገጽ www.ethiopostal.com ማሻሻል


ድረ-ገፅ እና ሶሻል  በድረ ገፁ ላይ የሚጫኑ ይዘቶችን መከታተል፣
ሚዲያዎች  ፌስቡክ ላይ መረጃ መጫኑን እና ክትትሉን ማሳደግ
 ትዊተር፣ ዩ ቲውብ እና ቴሌግራም ቻናሎችን መክፈት እና መረጃዎችን በየእለቱ የሚከናወን
መጫን
 ማብራሪያ የሚሰጥባቸው ርዕሰ ጉዳዮችን መለየት፣
የቃል አቀባይነት ስራ  የማብራሪያ የሚሰጠውን ኃላፊ መለየትና ከመገናኛ ብዙሃን ጋር ግንኙነት በየ ወሩ / ሚዲያዎች ጥያቄ እንዳቀረቡት
መፍጠር፣ የሚሰጥ
 የፕሬስ ኮንፈረንስ የሚካሄድበትን ርዕሰ ጉዳይ መምረጥ፣ በየሦስት ወሩ

የፕሬስ ኮንፈረንስ  የተመረጠው ርእሰ ጉዳይ መልዕክት በማን መተላለፍ አለበት የሚለውን
መግለጫ መወሰን፣
 መግለጫውን መስጠት
የተቀናጀ የኮሙዩኒኬሽን  በግራፊክስ፣ በህትመት፣ በፐብሊሲቲ እንዲሁም በህዝብ ግንኙነት የሚሰራ
ስራ የገጽታ ግንባታ ስራዎች መለየትና መተግበር፣
የማማከር ስራ  ለድርጅቱ የሚመጡ ሰነዶች፣ መረጃዎች እና ሌሎች ጉዳዮችን በቀረቡ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ
አስመልክቶ ለዋና ስራ አስፈጻሚ ምክር የማቅረብ እና ፕሮፖዛል
የማዘጋጀት ስራ ይሰራል፡፡
የውስጥ ህትመቶች  የጋዜጣና መጽሔት፣ ዜና መጽሔት፣ብሮሸር ህትመት፣ የጊዜ ሰሌዳ

ክፍል አምስት
5.1 የክትትልና ግምገማ ዕቅድ እና በጀት

የኮሙኒኬሽን ሥራችን ያመጣውን ውጤት የምንከታተለበትና የምንለካባት ሥርዓት መፍጠር አስፈላጊ ነው፡፡
ክትትል ምን እየሆነ ነው የሚለውን ሂደት ቀጣይነት ባለው መልኩ የምንከታተልበት ሲሆን፤ ግምገማ አጠቃላይ
የኮሙኒኬሽን ተግባራት ፕሮግራሙን ከማሣካት አኳያ ያላቸውን ሚና የምናይበት ነው፡፡ በዚህ ሂደት የሚከተሉት
ቁልፍ ጉዳዮች ላይ ማተኮር ያስፈልጋል፡፡
 የምንመዝነው ውጤትን እንጂ የተከናወኑ ተግባራትን መሆን የለበትም፤
በዚህም መሠረት በኮሙኒኬሽን ግቦች የተከናወኑ የኮሙኒኬሽን ተግባራት፣ የኮሙኒኬሽን ውጤቶችና
ኮሚዩኒኬሽን የፈጠረው ተፅዕኖ ነው፡፡
 በግቦቹ ላይ የተመሠረቱ የውጤት አመልካቾች መቀመጥ ይኖርባቸዋል፤
 በኮሚዩኒኬሽን ስትራቴጂ ዝግጅት ወቅት ሙሉ የክትትል ዕቅድ ከማውጣት ይልቅ በሂደት ማዘጋጀት የተሻለ
ይሆናል፤
5.2 በጀት

የኮሙኒኬሽን ስትራቴጂ በሚዘጋጅበት ወቅት አንዱ አስፈላጊ የፕሮግራሙ አካል በጀትና የበጀት ምንጭ የመለየት
ሥራ ነው፡፡ በስትራቴጂው የመጀመሪያ ክፍል ላይ የተሰራው ትንታኔ በጀቱ ምን ላይ? በምን ያህል መጠን? መዋል
እንዳለበት ለመለየት ያስችላል፡፡ በኮሙኒኬሽን ስትራቴጂ በጀት የሚመደብላቸው ሰባት ጉዳዮች አሉ፡፡ እነዚህም፦
1. የኮሙኒኬሽን ምርምር
2. ክትትልና ግምገማ
3. የፕሬስ ሥራዎች ዝግጅትና ሕትመት
4. የብሮድካስት ውጤቶች ዝግጅት
5. ልዩ ልዩ ሁነቶች
6. የዕቅድ ዝግጅትና ቅንጅታዊ ትስስር መፍጠሪያ ስብሰባዎች
7. ለውስጥ ኮሙኒኬሽን
ከዚህ ውጭ ዝርዝር የበጀት መጠን በኮሙኒኬሽን ስትራቴጂው ላይ እንዲቀመጥ አይጠበቅም፡፡ ይህም ሆኖ
ስትራቴጂው ፈጽሞ ሊገኝ/ሊሟላ/ የማይችል የበጀት መጠን ታሣቢ ተደርጎ መዘጋጀት የለበትም፡፡
የኮሙኒኬሽን እና አለም አቀፍ ግኝኙነት ዲፓርትመንት የአምስት ዓመት ስትራቴጂክ ዕቅድ በጀት
የጊዜ ሰሌዳ የሀብት ፍላጎት
ተ.ቁ ተግባራት መለኪያ መጠን አስተያየት
2013 2014 2015 2016 2017 ገንዘብ ምንጭ

1 ዜና ፖስታ መጽሔት በቁጥር 9 1 2 2 2 2 450,000 ከድርጅቱ

2 ቡለቲን በቁጥር 60 12 12 12 12 12 540,000 ከድርጅቱ

3 ባነር በቁጥር 75 15 15 15 15 15 52,500 ከድርጅቱ

4 የግድግዳ ካላንደር በቁጥር 15000 3000 3000 3000 3000 3000 2,500,000 ከድርጅቱ

5 የጠረጼዛ ካላንደር በቁጥር 15000 3000 3000 3000 3000 3000 3,000,000 ከድርጅቱ

6 ባዛር ተሳትፎ በቁጥር 10 2 2 2 2 2 220,000 ከድርጅቱ

7 የግድግዳ ዜና በቁጥር 2600 520 520 520 520 520 7,500 ከድርጅቱ

የሬድዮ አየር ሰዓት በመግዛት ተዘጋጅቶ የተላለፈ ከድርጅቱ በተባባሪዎች


8 በቁጥር 17 1 4 4 4 4 960,000
ፕሮግራም በቁጥር የሚዘጋጅ
የቴሌቪዥን አየር ሰዓት በመግዛት ተዘጋጅቶ የተላለፈ ከድርጅቱ በተባባሪዎች
9 በቁጥር 16 4 4 4 4 2,560,000
ፕሮግራም በቁጥር የሚዘጋጅ
10 ብሮሸር በቁጥር 10 2 2 2 2 70,000 ከድርጅቱ

ከድርጅቱ በፖስታ ሳጥን


11 ፍላየር በቁጥር 10 2 2 2 2 700,000
የሚበተን
ከድርጅቱ እንደ የሁኔታው
12 የሰራተኛ ቀን በቁጥር 4 1 1 1 1 1,300,000 በእግር ጉዞ
በውይይት
በድርጅቱ እቅድ ዙሪያ እና የጋራ መግባባቶችን ለመፍጠር ከድርጅቱ
13 በቁጥር 10 2 2 2 2 2 6,000,000
ከሰራተኞች ጋር የውይይት መድረክ ማመቻቸት

ከባለ ድርሻ እና አጋር አካላት ጋር የተደረጉ ቋሚ ከድርጅቱ


14 በቁጥር 20 4 4 4 4 4 4,000,000
ግንኙነቶች በቁጥር
15 የዓለም ፖስታ ቀን በቁጥር 5 1 1 1 1 1 20,000 ከድርጅቱ

16 የአፍሪካ ፖስታ ቀን በቁጥር 5 1 1 1 1 1 15,000 ከድርጅቱ

17 ፖስተር በቁጥር 5 1 1 1 1 35,000 ከድርጅቱ

18 ዓለም አቀፍ የደብዳቤ አጻጻፍ ውድድር በቁጥር 5 1 1 1 1 1 150000 ከድርጅቱ ለአሸናፊዎች


19 ሀገር አቀፍ የደብዳቤ አጻጻፍ ውድድር በቁጥር 5 1 1 1 1 1 150000 ከድርጅቱ ሽልማት

20 የእንኳን አደረሳችሁ ማስታወቂያ በጋዜጣ በቁጥር 120 24 24 24 24 24 2,400,000 ከድርጅቱ

21 የእንኳን አደረሳችሁ ማስታወቂያ በቴሌቪዥን በቁጥር 90 18 18 18 18 18 1,800,000 ከድርጅቱ

በድርጅቱ እቅድ ዙሪያ የጋራ መግባባቶችን ለመፍጠር ከድርጅቱ


22 በቁጥር 20 4 4 4 4 4 20000
ከሰራተኞች ጋር መድረክ ማመቻቸት

You might also like