Professional Documents
Culture Documents
ሰኔ 2009 ዓ.ም
የትምህርትና ሥልጠና የአንድን ተቋም የማስፈጸም አቅም ግንባታ መሳሪያዎች አካል ከመሆናቸውም በላይ በተቋሙ ውስጥ የሚታየውን የሥራ
አፈጻጸም ችግር ለመፍታት የሚጠቀሙበት መሳሪያ ነው። ሰራተኞች ሙያዊ ዕውቀታቸውንና ክህሎታቸውን በመገንባት የሚጠበቅባቸውን ሃላፊነት
ለመወጣት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው። በፈጣን የዕድገት ጉዞ ላይ ከሚገኘው ሳይንስና ቴክኖሎጂ ጋር ተጣጥሞ ለመጓዝና በዘርፉ ዕድገት የሙያተኛውን
ዕውቀትና ችሎታ በትምህርትና ስልጠና በመገንባት ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ አስተዋጽኦው ትልቅ ነው።
ትምህርትና ስልጠና የሰውን ልጅ የእውቀት፣ የክህሎት፣ የባህርይና የአመለካከት ደረጃ ለማሳደግ እንደ ትልቅ መሳሪያ የሚያገለግል ስለሆነ በተቋሙ
ውስጥ በየደረጃው የሚገኙ የስራ ሃላፊዎች፣ ባለሙያዎችና ሌሎች ሰራተኞች የተጣለባቸውን ተግባርና ሃላፊነት በአግባቡ እንዲወጡ ለማስቻል
ከወቅቱ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ዕድገት ጋር እንዲራመዱ እና የመ/ቤታቸውን አላማና ግብ በአግባቡ ተረድተው ወጤታማ በሆነ መልኩ እንዲያሳኩ
ለማድረግ የትምህርትና ሥልጠና ዕድል ማግኘት አለባቸው።
በፌደራል የመንግስት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 515/1999 አንቀጽ 12/2 ላይ “ማንኛውም የመንግስት መ/ቤት ስትራቴጂክ እቅዱን መሰረት በማድረግ
የአጭር፣ የመካከለኛና የረጅም ጊዜ የሰው ሀይል ዕቅዱን አጥንቶ ተግባራዊ ማድረግ አለበት።” ይላል። አንቀጽ 58 ንዑስ አንቀጽ 1 ላይም “እያንዳንዱ
የመንግስት መ/ቤት ለመ/ቤቱና ለሰራተኛው የሚያሰፈልገውን ሥልጠና በማጥናት፣ ዕቅድ በማውጣትና በጀት በማስፈቀድ ሰራተኞቹ አስፈላጊውን
ሥልጠና እንዲያገኙ የማድረግና ለፌደራል የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ሚ/ር የማሳወቅ ሃላፊነት አለበት።” በማለት በመንግስት መ/ቤቶች
ላይ ሃላፊነት ጥሏል።
ከዚህ ሌላ የመግስት ኮሙየኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት የጥናት፣ ምርምርና አቅም ግንባታ ጄኔራል ዳይሬክቶሬት ተግባርና ሃላፊነት አስመልክቶ ሰኔ 27/2006
ዓ.ም በቁጥር ኮ/ሠሀ-19/9098 ባስተላለፈው ሰርኩላር “1 ኛ).ተቋሙን በማገልገል ያለውን የሰው ሃብት አቅም ለማሳደግ የሚያስችሉ የአገር ውስጥና
የውጭ አገር የትምህርትና ስልጠና ዕድሎችን በማፈላለግ ተግበራዊ ያደርጋል፣ 2 ኛ). በፌዴራል እና በክልል ያሉ ኮሙዩኬተሮችንና በተቋሙ ውስጥ
የሚገኘውን የሰው ሃብት አቅም ክፍተት ፍላጎት ዳሰሳ በማድረግ እንዲለይ ያደርጋል፣ የአቅም ክፍተቶች የሚሞሉበትን የትምህርትና ስልጠና
ፕሮግራሞች በመቅረጽ ተግባራዊ ያደርጋል፣ ከስልጠና በኋላ የተገኘውን የስራ ላይ ለውጥ በመገምገም ከሙያዊ ትንተና ጋር ተዘጋጅቶ እንዲቀርብ
ያደርጋል፣ 3 ኛ).ስልጠናዎች የሚመሩበትን ዝክረ ተግባር ተዘጋጅቶ እንዲቀርብ ያደርጋል፣ የስልጠና ርዕሰ ጉዳዮችንም በመለየትና በማፅደቅ ሞጅሎች
እንዲዘጋጁና ተፈፃሚ እንዲሆኑ ይሠራል፣ 4 ኛ). በኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን፣ በማህበረሰብ ሚዲያ እና በህዝብ ግንኙነት የስራ መስክ ተሰማርተው
እየሰሩ ያሉና አዲስ የሚቀጠሩ ባለሙያዎችን አቅም ለመገንባት /ለማብቃት/ የሚያስችል የስልጠና ማዕከል እንዲደራጅ ያደርጋል፣ ስራውን በባለቤትነት
ይመራል” የሚባሉ ተግባርና ሃላፊነቶች ግምት ውስጥ በማስገባት የትምህርትና ስልጠና መመሪያው አሻሽሎ ማዘጋጀቱ ታምኖበታል።
የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት የትምህርትና ስልጠና የውስጥ መመሪያ Page 2
በዚሁ መሰረት የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት በተቋቋመበት አዋጅ፣ በተሰጠው ስልጣንና ሃላፊነት መሰረት በኮሙዩኒኬሽን፣ ኢንፎርሜሽንና
በሚዲያ ልማት ዘርፍ ሁለገብ አቅም መገንባት እንዲሁም ህዝቡ በዋና ዋና አገራዊ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት እንዲፈጠር በዘርፉ ስትራቴጂካዊ
የመሪነት ሚና መጫወት እንዲችል እንዲሁም በጽ/ቤቱ ማቋቋሚያ ደንብ ቁጥር 158/2001 በ 5.3 ላይ የፌደራል የመንግስት መ/ቤቶችን የህዝብ
ግንኙነት ሰራተኞች አቅም ያለበትን ደረጃ እያጠናና እየፈተሸ አቅማቸውን የመገንባት ተግባራትን ከወቅቱ ሁኔታ ጋር እያጣጣመ የመንግስትን ተልዕኮ
እና አላማውን ለማሳካት በሚየስችል መልኩ የፌደራልና የክልል ኮሙዩኒኬተሮች በብቃትና በጥራት አሟልቶ የሰው ሃይሉን የሚፈለገውን ውጤት
ማምጣት እንዲቻል በትኩረት መሰራትን ዘመኑ ከሚጠይቀው የሚዲያ፣ ኮሙዩኒኬሽንና ኢንፎርሜሽን አንጻር በትምህርትና ስልጠና እንዲገነባ ማድረግ
ጊዜ የማይሰጠው ጉዳይ ነው።
በመሆኑም ይህ መመሪያ የፌደራል መንግስት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 515/1999 ክፍል ስድስት አንቀጽ 58 ፣የመንግስት ሠራተኞችን የማሰልጠን
ኃላፊነትን አስመልክቶ በንዑስ አንቀፅ 1 እና 2 የተገለጸውን መነሻ በማድረግና ቀደም ሲል በነበረው የጽ/ቤቱ የትምህርትና ስልጠና መመሪያ ላይ የታየውን
ክፍተት ሊሞላ በሚችል መልኩ አስተካክሎና መተግበር በሚያስችል ሁኔታ እንደገና ማሻሻያ በማድረግ ተዘጋጅቷል።
ስለሆነም የሰው ሃብት አቅምን ለመገንባት በአገር ውስጥና በውጭ አገር የሚሰጥ የትምህርትና ሥልጠና መመሪያ ማዘጋጀት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ
በቀድሞው የሥልጠና መመሪያ ላይ በአፈጻጸም የተከሰቱ ክፍተቶችን መዝጋት በሚያስችል መልኩ ማሻሻያ የተደረገበት ይህ የትምህርትና ሥልጠና
መመሪያ ተሻሽሎ እንዲወጣ ተደርጓል።
ክፍል አንድ
ጠቅላላ
1.1) አጭር ርዕስ “ይህ መመሪያ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት የትምህርትና ሥልጠና መመሪያ ቁጥር ---/2008” ተብሎ ሊጠቀስ
ይችላል።
1.2) ትርጓሜ
የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በሰተቀር በዚህ መመሪያ ውስጥ:-
1.2.1. “ጽ/ቤት” ማለት በሚኒስትሮች ም/ቤት ማቋቋሚያ ደንብ ቁጥር 158/2001 የተቋቋመ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው።
1.2.2. “የበላይ ሃላፊ” ማለት ጽ/ቤቱን በበላይነት የሚመራ ሚኒስትር ወይም ሚኒስትር ዴኤታ ማለት ነው።
1.2.3. “ትምህርት” ማለት የመ/ቤቱ ሰራተኞች በስራ ላይ እንዳሉ ወይም ለተወሰነ ጊዜ ስራቸውን አቋርጠው ደረጃቸውን ከፍ ለማድረግ በአገር ውስጥ
ወይም በውጭ አገር ዕውቀት የሚቀስሙበት ሥርዓት ነው።
1.5.4. ባህርያት
1.5.4.1. በቀጥታ ለጽ/ቤቱ የሚደለደሉ እድሎች:- መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶችና ተቋማት በቀጥታ ለጽ/ቤቱ ተወስነው የሚደለደሉ
ሲሆኑ የሀገር ውስጥ ወይም የውጪ ሀገር ትምህርትና ስልጠና ዕድሎችን ሊያካትቱ ይችላሉ፡፡
1.5.4.2. ተጨማሪ የውድድር ጠባይ ያላቸው እድሎች:- መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶችና ተቋማት በሚገኙ ዕድሎች የጽ/ቤቱ እጩ
ተወዳዳሪዎች
1.5.4.3. ከሌሎች መስሪያ ቤቶች፤ድርጅቶችና ሀገሮች ዕጩ ተወዳዳሪዎች ጋር የሚወዳደሩበት የትምህርትና ስልጠና ዕድሎችን ሊያካትቱ ይችላሉ፡፡
በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገር በሚሰጡ የአጭር፣ የመካከለኛና የረዥም ጊዜ የትምህርትና የሥልጠና ዕድሎች የሚወዳደሩ ሰራተኞች:-
2.1.1. በጽ/ቤቱ ቋሚ ሰራተኞች የሆነ፣ በጽ/ቤቱ ወይም በማንኛውም የመንግስት ተቋም ቢያንስ ሁለት አመት ያገለገለ፣
2.1.2. ዕድሉን በሰጠው አካል የተቀመጡ መስፈርቶችን የሚያሟሉ፣
2.1.3. በሌሎች የትምህርትና ስልጠና እድሎች ተመዝግበውና ተወዳድረው ያልተመረጡ፣
2.1.4. ቀደም ሲል በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገር የአጭር፣ የመካከለኛና የረዥም ጊዜ ትምህርትና ሥልጠናዎች ላይ የተሳተፉ ከሆነ ለሌላ
የትምህርት ወይም የስልጠና ዕድል ለመወዳደር ቀድሞ የገቡትን የውል ግዴታ ያጠናቀቁ መሆን አለባቸው፣
2.1.5. የከፍተኛ ትምህርት ዕድል ተጠቃሚ የሆነ ሠራተኛ ትምህርቱ ለሚወስደው ጊዜ እጥፍ አመት አገልግሎት ለመስጠት ተመጣጣኝ ዋስትና
ማቅረብ አለበት፣
2.1.6. ለጽ/ቤቱ በቀጥታ የተደለደሉ የስልጠና ዕድሎች የተወዳደረ ዕጩ በውድድሩ ማለፉ እስካልተረጋገጠ ድረስ በሌላ ትምህርት/ስልጠና መወዳደር
አይችልም።
2.1.7. ማንኛውም እጩ ተወዳዳሪ በአገር ውስጥ ወይም በውጭ አገር በማንኛውም የትምህርት/ስልጠና ፕሮግራም ላይ ያለ መሆን የለበትም፣
2.1.8. ከአገር ውስጥና ከውጭ አገር በሚገኙ የትምህርት ዕድሎች በተመሳሳይ የትምህርት ደረጃ በድጋሚ መወዳደር አይችልም፣
2.1.9. የስራ አፈጻጸም ምዘና የሁለት ጊዜ አማካኝ ነጥብ 60% እና ከዚያ በላይ የስራ አፈጻጸም ደረጃ ያገኘ መሆን አለበት፣
2.1.10. ለሁለተኛ እና ለሶስተኛ ዲግሪ የትምህርት ዕድል ለመወዳደር ለወንድ 50 ለሴት 52 መብለጥ የለበትም።
2.1.11. የትምህርት ደረጃቸው ከመጀመሪያ ዲግሪ በታች ያሉ ሠራተኞች በጽ/ቤቱ የበላይ ሃላፊ በልዩ ሁኔታ ሲፈቀድ ብቻ እንዲማሩ ይደረጋል።
2.1.12. ለአጫጭር ጊዜ ስልጠናዎች የሚቀርቡ ዕጩዎች እድሜ እድሉን በሰጡ ወገኖች መስፈርት መሰረት ሊፈፀም ይችላል።
2.2. ልዩ ትኩረት የሚሹ ዕጩዎች አመራረጥ፣
የስራ አፈጻጸም ምዘና ውጤት በተቋሙ በሚመለከተው የስራ ሂደት መሪ ተሰጥቶ በበላይ ሃላፊ /በተወካዩ የተረጋገጠ መሆን ይኖርበታል፣
ለማወዳደር እንዲያመች ከ 100% የተገኘውን የቅርብ ጊዜ ሁለት የውጤት ተኮር የስራ አፈጻጸም ውጤታቸው ወደ 70% በማስላት ይቀየራል።
በተለያዩ ምክንያቶች የስራ አፈጻጸም በተከታታይ ያልተሞላ ከሆነ በ 2 ተከታታይ የስራ አፈጻጸም ውጤት ማወዳደር ይቻላል። ይህም ካልተሟላ
እና በቂ ምክንያት ያለው ከሆነ በአንድ ጊዜ የስራ አፈጻጸም መወዳደር ይቻላል፣
ቀጥታ አግባብነት ያለው የትምህርት ደረጃ 10%፣በተዘዋዋሪ ግኑኙነት ያለው የትምህርት ደረጃ 5% እና ግኑኙነት የሌለው የትምህርት ደረጃ 2.5%
የሚሰጥ ይሆናል።
የማህደር ጥራት አንዱ የማወዳደሪያ መስፈርት ሲሆን ውድድር ከመደረጉ ቀደም ብሎ ቀላል የዲሲፕሊን ቅጣት እስከ 2 አመት፣ ከባድ የዲሲፕሊን
ቅጣት እስከ 5 አመት በሪከርድነት በሰራተኛው ማህደር ውስጥ የሚያዝ በመሆኑ የሥነ-ምግባር ችግሮች ያሉበትን ሰራተኛ ተጠቃሚ የመሆን መብት
ከቅጣት ዘመኑ በፊት እንዳይጠቀምበት ለማድረግ የማህደር ጥራት ያላቸውን ሰራተኞች ለማበረታታት ለማህደር ጥራት የሚሰጠው አጠቃላይ ነጥብም
10% ሆኖ ዝርዝር የነጥብ አሰጣጡም እንደሚከተለው ይሆናል።
ተ.ቁ የማህደር ጥራት የሚቀነስ ነጥብ የሚሰጥ ነጥብ
1 አንድ ወር ደመወዝና በላይ ቅጣት 4 6
2 የሁለት ጊዜ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ 3 7
3 የመጀመሪያ የጽሁፍ ማስጠንቀቂያ 2 8
ክፍል ሦስት
3. በአገር ውስጥና በውጭ አገር ሥልጠና/ትምህርት ስለሚከፈል ደመወዝ እና ድጋፍ፦
ሀ) ሠራተኛው የተላከበትን ወይም ሠራተኛው እንዲሰለጥን ከተላከበት ደረጃ በላይ ለመቀጠል የሚያስችል ዕድል ቢያገኝ በቅድሚያ የጽ/ቤቱን ኃላፊ
ስምምነት እስካላገኘ ድረስ ያገኘውን ዕድል መቀጠል አይችልም። ሆኖም ሠልጣኙ ለስልጠና የተላከበትን የሙያ መስክ ያለጽ/ቤቱ ፍቃድ ቢለውጥ
ወይም ያልተፈቀደለትን የትምህርት ደረጃ ቢማር፤
ለ) በውጭ ሃገር ስልጠና እንዲከታተል የተመረጠ ሠራተኛ ለጤና ምርመራ፣ ለክትባት፣ ለኮቴ፣ ለፓስፖርት፣ ለቢዛና ለመሳሰሉት የሚያስፈልገው ወጪ
በጽ/ቤቱ የሚሸፈን ይሆናል።
ሐ) ትምህርት ወይም ስልጠና በመከታተል ላይ የሚገኝ ሠራተኛ በስራ ላይ ሊያገኝ ይችል የነበረውን ለተመሳሳይ የስራ መደብ ባልደረቦቹ የተሰጠ
ጥቅም በመመሪያ የተከለከለ እስካልሆነ ድረሰ በውጭ አገር ትምህርት ወይም ሥልጠና በመከታተል ላይ በመሆኑ ምክንያት የሚሰጠው ጥቅም
አይነፈግም። ሆኖም በስራ ፀባይ ምክንያት ለስራ ማከናወኛ ተብሎ ይከፈል የነበረው የትራንስፖርት የኃላፊነትና ሌሎች አበሎች አይሰጡም።
መ). በውጭ ሃገር ነፃ የትምህርት ዕድል አግኝተው ለሚሄዱ የጽ/ቤቱ ሠራተኞች ለትምህርት ላይ ለሚቆዩበት ሙሉ ጊዜ ግመሽ ደመወዝ
ይከፈላቸዋል።
ጉዳዩ የሚመለከተው የቀረበለትን የማራዘም ጥያቄ በስልጠና ኮሚቴው ማስረጃዎች እንዲታዩ እና ኮሚቴው የደረሰበትን የውሳኔ ሃሳብ በበላይ ኃላፊ
ተቀባይነት ሲያገኝ ሊፈቀድ ይችላል፣
ክፍል አራት
4. የትምህርትና ስልጠና ኮሚቴ ስለመቋቋም
ሐ) ተወዳዳሪዎች የትምህርትና ስልጠና እድሉን አስመልክተው እንዲያውቁና ያላቀረቧቸውን ማስረጃዎች በወቅቱ ለማቅረብ እንዲችሉ ለማድረግ፣
1) የጊዜ መጣበብ ከሌለ በስተቀር ማስታወቂያው ለአምስት/5/ ተከታታይ የስራ ቀናት በማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ ተለጥፎ የሚቆይ ሲሆን በዚሁ ጊዜ
ውስጥ የተወዳዳሪዎች ምዝገባ ጎን ለጎን በሰው ሃብትና ሪከርድ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት አማካኝነት ይካሄዳል። ሆኖም የስልጠናው እድል ውድድር በጣም
አስቸኳይና የተጣበበ ጊዜ ያለው ከሆነ የተገኘው እድል እንዳይመክን ማስታወቂያው አምስት የስራ ቀናትን ላይጠብቅ ይችላል።
ለ) ለአጭርም ሆነ ለረዥም ጊዜ ከውጭ አገር የተገኘ ስኮላርሺፕ ማስታወቂያውና ምዝገባው የሚቆይበት ጊዜ በሚለው መመሪያ ቁጥር 2.2.3 “1”
መሰረት መፈፀም የማይቻል ከሆነና ቀነ ገደቡ በማጠሩ ምክንያት ማሰታወቂያ አውጥቶ ዕጩዎች ተመዝግበው ውድድር ተካሂዶ ዕጩ ለመምረጥ
የማይቻል ሆኖ ሲገኝ በበላይ አካል ውሳኔ የመጣውን መስፈርት አሟልቶ የተገኘ ሰራተኛ በዕድሉ እንዲጠቀም ይደረጋል።
ክፍል ስድስት
6. ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች
6.1. የቅሬታ አቀራረብና ውሳኔ አሰጣጥ
6.1.1. በዚህ መመሪያ መሰረት በሚከናወን የዕጪዎች ምዝገባ፣ ውድድርና መረጣ እንድሁም በሌሎች አፈጻጸሞች ላይ ቅሬታ ያላቸው ሠራተኞች
ለበላይ ኃላፊው አቤቱታቸውን ማቅረብ ይችላሉ፣
6.1.2. የመ/ቤቱ ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ ቅሬታው በደረሰው ከ 5(በአምስት) ቀናት ባልበለጠ ጊዜ ምላሽ መስጠት አለበት፣
6.1.3. ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴው የደረሰበትን የውሳኔ ሃሳብ/አስተያየት ወዲያውኑ ለበላይ ሃላፊው ያቀርባል፣
6.1.4. የጽ/ቤቱ የበላይ ሃላፊ ቅሬታው በቀረበ በሦስት ቀን ጊዜ ውስጥ ተገቢውን ውሳኔ ለአቤቱታ አቅራቢው ያሳውቃል፣
6.1.5. የበላይ ሃላፊው ውሳኔ የመጨረሻ ይሆናል፣
6.2. በመመሪያው ያልተሸፈኑ ጉዳዮች
ይህ የስምምነት ውል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት (ከዚህ በኋላ ውል ሰጪ እየተባለ በሚጠራው) አድራሻ፦ አዲስ አበባ ቂርቆስ ክ/ከተማ
ወረዳ፦….የቤት ቁጥር፦..……..ስልክ ቁጥር፦……….የፖስታ ሳጥን ቀጥር፦ …………..ፖስታ ሣጥን እና
አንቀፅ 1
የውሉ አላማ
የዚህ ውል ዓላማ የመ/ቤቱን ቋሚ ሠራተኞች የትምህርት ወይም የስልጠና ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችል መብትና ግዴታን በውል ሰጪ እና
በውል ተቀባይ መካከል ለመፈፀም ነው።
አንቀፅ 2
የትምህርት ወይም ስልጠና ዕድሉ በተሰጠበት ወቅት ውል ተቀባይ በ………ዳይሬክቶሬት ተመድቦ ይሰራ የነበረ ሲሆን፦
አንቀጽ 3
ስለትምህርቱ/ ሥልጠናው
የቆይታው ጊዜ፦………………………………………..
የስልጠናው ዘርፍ፦……………………………………
የፈቀደው ኋላፊ፦………………………………………..
አንቀፅ 4
የውል ተቀ ባይ ግዴታ
ውል ተቀባይ
በገባው ግዴታ መሠረት ሣይፈጽም ቢቀር እሱን ተክቶ ሃላፊነቱን የሚወስድ ዋስ የመጥራት፣
የተላከበትን ትምህርት ወይም ስልጠና በአግባቡ የመከታተልና ውጤት የማስገኘት ፣
በቅድሚያ ለውል ሰጪ አስታውቆ ካልተፈቀደለት በስተቀር የተላከበትን የትምህርት/የስልጠና መስክ ያለመለወጥ፣
ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት ካላጋጠመ በስተቀር ትምህርቱን/ስልጠናውን ለማቋረጥ ቢገደድ አመች በሆነ የመገናኛ ዘዴ ተጠቅሞ ለውል ሠጪ
ማሳወቅ፣
ከነዚህም በተጨማሪ
አንቀጽ 6
ውሉ ስለሚቆዩበት ጊዜ
አንቀፅ 7
ውሉ ስለሚቋረጥበት ሁኔታ
እንደውሉ ሲፈፀም፣
አንቀጽ 8
የዋስ ግዴታ
አንቀጽ 9
ስለውል ሰጪ ውል ተቀባይ
ስም…………………………… ስም……………………………
ፊርማ………………………… ፊርማ……………………………
ቀን……………………………… ቀን……………………………
የውል ተቀይ ባለቤት
ስም………………………
ፊርማ…………………………
ቀን…………………………
ዋስ የዋስ ባለቤት
ስም……………………… ስም…………………….
ፊርማ……………………… ፊርማ…………………..
ቀን………………………… ቀን…………………………
ምስክሮች
ስም ፊርማ ቀን
1………………………….. ……………….. ………………….
2…………………………… ………………... ………………….
3…………………………… ………………… ………………….
4…………………………… ………………… …………………..
ይህ ስምምነት ………………ቀን…………………ወር……….ዓ.ም. ተፈርሟል።
የሚፈጀው ጊዜ …………………………
ከዚህ ጋር ተያይዞ በሚገኘው የእጩዎች ማወዳደሪያ ቅፅ ላይ በስም የተጠቀሱትን ካወዳደረ በኋላ አቶ/ወ/ሮ/ወ/ሪት………………………ን መርጦ
አቅርቧል።
………………………………………………………………………………………………………………………………………………
……………………………………………………………………………………………………
በምርጫው ያልተስማማ አባል ቢኖር በሃሳብ የተለየበት ምክንያት…
………………………………………………………………………………………………………………
በምርጫው ያልተስማማው አባል ስም ……………………..ፊርማ……………………………
ኮሚቴው የውሳኔ አስተያየቱን ያቀረበበት ቀን……………ወር……………ዓ.ም…………….
የኮሚቴው ሰብሳቢና የአባላት ስም
ስም ፊርማ
……………………………….. ………………………..
………………………………. ………………………..
……………………………… …………………………
………………………………. ……………………………
የመ/ቤቱ የበላይ ኃላፊ ውሳኔ
ተ.ቁ የተወዳዳሪ ስም የትውልድ የት/ት አመካይ የስራ ልምድ 10% ለውጤት ተኮር የማህደር ጥራት 10% ጠቅላላ የነጥብ ደረጃ መግለጫ
1. …………………………………………
2. ………………………………………..
3. …………………………………………
4. ………………………………………..
5. ………………………………………..
6. ……………………………………….