You are on page 1of 35

በኢፊዲሪ ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር

የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ

የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋም

አመራር ምልመላ፣ ምደባ እና ጥቅማጥቅም

ማስፈጸሚያ መመሪያ

(ዜሮ ድረፍት)

ጥር 29, 2013

አዳማ
ይዘት

1. መግቢያ

2. ክፍል አንድ (አጠቃላይ ድንጋጌ) 6 አንቀፅ

3. ክፍል ሁለት (ለአመራርነት ውድድር የሚያበቁ የመመልመያ መስፈርት) 3

4. ክፍል ሦስት

የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና የተቋም አመራር የጥቅማጥቅም

5. ክፍል አራት

የጥቅማጥቅም ዓይነቶች፣ የጥቅማጥቅም አፈጻጸም፣ ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች

የመሸጋገሪያ ጊዜ

6. ከፍል አምስት

አንቀጽ 15. የመመሪያው ተግባራዊነት


1. መግቢያ
• ዘርፍ ለሀገራችን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እድገት የሚጠበቅበትን አስተዋጽኦ የሚያበረክት ብቁ፣ ተወዳዳሪ፣

በራሱ የሚተማመን እና ራሱን ከለውጥ ጋር የሚያስማማ ዜጋ በማፍራት ቀጣይነት ባለው መንገድ ድህነትን

ለመቀነስ በሚደረገው ትግል ተቀዳሚ ተልኮውን መወጣት የሚያስችል የአመራር ስርዓት መዘርጋት በማስፈለጉ፣

• የቴ/ሙያ/ት/ ስ/ ተቋም አመራር ምልመላ እና ምደባ በችሎታ ላይ የተመሰረተ ግልጽና አሳታፊ የውድድር

ስርዓትን የተከተለ እንዲሆን ለማድረግ መንግስት ከፍተኛ ፍላጎት ያለው በመሆኑ፣

• ከዚህ በፊት የነበረው የአመራር ምልመላ፣ ምደባ እና ጥቅማጥቅም አፈጻጸም ከክልል ክልል እንዲሁም ከተቋም

ተቋም የተለያየ በመሆኑ ፤

• ተደጋጋሚ የቅሬታ ምንጭ እየሆነ በመምጣቱ፤

• ጠንካራ ኢንስትራክተርን /ባለሙያን/ ወደ አመራር ለማምጣት በሚደረገው ጥረት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ

እያሳደረ በመሆኑ ኤጀንሲው

• በአዋጅ ቁጥር 954/2008 አንቀጽ 43 ንዑስ ቁጥር 3 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ይህን የአመራር የምልመላ ፣

ምደባ እና ጥቅማጥቅም መመሪያ አውጥቷል፡፡


ክፍል አንድ (አጠቃላይ ድንጋጌ)

1. አንቀጽ 1፡ አጭር ርዕስ

2. አንቀጽ 2፡ ትርጉም

3. አንቀጽ 3፡ ዓላማዎች

4. አንቀጽ4፡ የመመሪያው አስፈላጊነት

5. አንቀጽ 5፡ የተፈጻሚነት ወሰን

6. አንቀጽ 6፡ አጠቃላይ መርሆዎች


ክፍል አንድ፡- አጠቃላይ ድንጋጌ

አንቀጽ 1፡ አጭር ርዕስ

• ይህ መመሪያ የመንግስት ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋም የአመራር ምልመላ ፣ ምደባ

እና ጥቅማ ጥቅም ማስፈፃሚያ መመሪያ ቁጥር ----- ተብሎ ሊጠራ ይችላል፡፡

አንቀጽ 2፡ ትርጉም

• “ሚኒስቴር ወይም ሚኒስትር” ማለት እንደ ቅደም ተከተሉ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት

ሚኒስቴር ወይም ሚኒስትር ነው፤

• “ኤጀንሲ” ማለት በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 194/2003 የተቋቋመው የቴክኒክና

ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ ነው፤

• “የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ/ኤጀንሲ” ማለት በክልል ወይም በከተማ አስተዳደሩ

ህጋዊ እውቅና አግኝቶ የተቋቋመ የቴክኒክና ሙ ትምህርትና ስልጠናን በበላይነት

የሚያስተባብርና የሚመራ አካል ነው፤


ትርጉም የቀጠለ…

• “ባለሙያ” ማለት በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ዘርፍ ስልጠና በሚሰጥባቸው

ሙያዎች የሰለጠነ ሆኖ በሰለጠነበት ሙያ ብቃቱ የተረጋገጠ እና በማሰልጠን ስነ ዘዴ

የበቃ እና በኢንዱስትሪ ስራ ላይ የተሰማራ ሰው ነው፤

• “ኢንስትራክተር” ማለት በማሰልጠኛ ተቋም ውስጥ በ ቢ፣ በ ኤ ወይም ከዛ በላይ

ባለው ደረጃ በማሰልጠን ሥራ ላይ የተሰማራ ሰው ነው፤

• “ማሰልጠኛ ተቋም” ማለት የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና በመስጠት ላይ

የተሰማራ የመንግስት ተቋም ነው፤

• “ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ” ማለት የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋም ሆኖ አስከ

ደረጃ 5 በማሰልጠን ስራ ላይ የተሰማራ ነው፣


ትርጉም የቀጠለ…

• “ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጅ” ማለት የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና

ስልጠና ተቋም ሆኖ እስከ ደረጃ 4 በማሰልጠን ስራ ላይ የተሰማራ ነው፣

• “ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋም” ማለት የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና

ስልጠና ተቋም ሆኖ እስከ ደረጃ 2 በማሰልጠን ስራ ላይ የተሰማራ ነው፤

• “ዲን” ማለት ብቃቱ በሙያ ምዘና የተረጋገጠ የመንግስትን ፖሊሲና እስትራቴጅ

ለመተግበር ብቃትና ተነሳሽነት ያለው የቢ-ደረጃ ፣ የ ኤ-ደረጃ ወይም ከዚያ በላይ

ከሆኑ ኢንስትራክተሮች /ባለሙያዎች/ መካከል ተወዳድሮ የሚመደብ የቴክኒክና

ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋምን በበላይነት የሚመራ ሃላፊ ነው፡


ትርጉም የቀጠለ…

• “ምክትል ዲን” ማለት ብቃቱ በሙያ ምዘና የተረጋገጠ የመንግስትን ፖሊሲና እስትራቴጅ

ለመተግበር ብቃትና ተነሳሽነት ያለው የ ቢ-ደረጃ ፣ የ ኤ-ደረጃ ወይም ከዚያ በላይ ከሆኑ

ኢንስትራክተሮች /ባለሙያዎች/ መካከል ተወዳድሮ የሚመደብ የቴክኒክና ሙያ ውጤት ተኮር

ስልጠና የስራ ሂደትን ፣ ኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽንና የቴክኖሎጂ ሽግግር አገልግሎት የስራ ሂደትን

ወይም እንደ አስፈላጊነቱ በተቋም ተወዳድሮ በምክትል ዲንነት ደረጃ የሚመደብ ኃላፊ ነው፣

• “የትምህርትና ስልጠና ክፍል ተጠሪ” ማለት በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋም ውስጥ

የሚሰጡ ሙያዎችን በውጤት ተኮር ስልጠና የሚመራና የሚያስተባብር ተጠሪ ነው፣

• “የተቋም አመራር” ማለት በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋም የሚሰራ ማለትም ዲን፣

ምክትል ዲን እና የትምህርትና ስልጠና ክፍል ተጠሪ ነው፡

• “ጥቅማጥቅም” ማለት ለዲን ፣ ለምክትል ዲን እና ለትምህርትና ስልጠና ክፍል ተጠሪ

ለሃላፊነት የሚከፈል ገንዘብ ነው፣


አንቀጽ 3፡ ዓላማ

• የአመራር ቦታዎችን ለመመደብ የሚፈልግ ብቃት፣ ክህሎት፣ ልምድ እና


መልካም ስነ ምግባር ያለው እና ተወዳዳሪ የሆነ አመራርን ማግኘት
እንዲያስችል፣

• የአመራር ምልመላ እና ምደባ በሙያ ብቃት በውድድር ላይ የተመሰረተ


መሆኑን ለማረጋገጥ ፣

• የተቋም አመራር የምልመላ፣ የምደባ እና የጥቅማጥቅም አፈጻጸም


ልዩነት በማጥበብ ተነሳሽነት በመጨመር ተቋሙን በብቃት ለመምራትና
የጥራት ማኔጅመንት ስረዓትን ውጤታማነት ማሳደግ እንዲያስችላቸው፣
አንቀጽ4፡ የመመሪያው አስፈላጊነት
• የአመራር ምልመላ ፣ ምደባ እና ጥቅማጥቅም አፈጻጸም ወጥነት ያለው እንዲሆን በማድረግ፡-

• የውድድር መንፈስን በመጨመር ሙያዊ ስነ ምግባርን ለማሳደግ፣

• ወቅቱ ከሚጠይቀው ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፍላጎት ጋር ራሱን የሚያስማማና አዳዲስ

ሀሳብ ማፍልቅ የሚችል አመራር ለመፍጠር

• በአመራር ምልመላ ፣ ምደባ እና ጥቅማጥቅም አፈጻጸም ላይ የሚነሱ ቅሬታዎችን በመቀነስ

ተነሳሽነትን ለመጨመር

አንቀጽ 5፡ የተፈጻሚነት ወሰን

• ይህ መመሪያ በመንግስት የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋም እና በቴክኒክና ሙያ

ትምህርትና ስልጠና ዘርፍ አስፈጻሚ አካለት ላይ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡

አንቀጽ 6፡ አጠቃላይ መርሆዎች

• የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ስርዓት መርሆችን መሰረት ያደረገ ይሆናል


ክፍል ሁለት
አንቀጽ 7፡ ለአመራርነት ውድድር የሚያበቁ የመመልመያ መስፈርት

ለፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ለዲንና ለምክትል ዲን እጩ ተወዳዳሪ


 በትኩረት ዘርፎች ስልጠና ከሚሰጥባቸው ሙያዎች በአንዱ ወይም በቴክኒክና ሙያ አመራር (TVET Leader

Ship) በኤ ደረጃ ኢንስትራክተር ወይም ከዚያ በላይ የደረሰ፣

 በሰለጠነበት የሙያ ዘርፍ ደረጃ በደረጃ IV/V ተመዝኖ ብቃቱ የተረጋገጠ፣

 በማሰልጠን ስነ ዘዴ ስልጠና ብቁ የሆነ፣

 ተቋሙን ወደ ላቀ ደረጃ ማድረስ የሚያስችል ስትራቴጅክ እቅድ አዘጋጅቶ ማቅረብ የሚችል፣

 የመንግስትን ፖሊሲና ስትራቴጅ ለመፈጸምና ለማስፈጸም ዝግጁ የሆነ፣

 ተቋሙን ውጤታማ ለማድረግ ተጨማሪ ክህሎት ያለው እና ብዝሀነትን የሚያክብር እና ልዩ ድጋፍ

ለሚያስፈልጋቸው አካላት ድጋፍ የሚያደርግ፣

 ተባብሮ የመስራትና የመምራት ብቃት ያለው እና በውሳኔ አሰጣጥ ሂደት ልምድ ያለው፣

 ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር መስራት የሚችል፣


ክፍል ሁለት
አንቀጽ 7፡ ለአመራርነት ውድድር የሚያበቁ የመመልመያ መስፈርት

ለፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ለዲንና ለምክትል ዲን እጩ ተወዳዳሪ


 ከኢንዱስትሪው ተወዳዳሪ ሆነው ለሚቀርቡ በቴ/ሙ/ት/ ስልጠና ስልጠና በሚሰጥባቸው ሙያዎች በአንዱ በኤ

ደረጃ እና ከዚያ በላይ የትምህርት ዝግጅት ያለውና 5 ዓመት እና በላይ የስራ ልምድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፤

 በሰለጠነበት የሙያ ዘርፍ ደረጃ በደረጃ IV/V ተመዝኖ ብቃቱ የተረጋገጠ እና

 በማሰልጠን ስነ ዘዴ ስልጠና ብቁ የሆነ፣

 ተቋሙን ወደ ላቀ ደረጃ ማድረስ የሚያስችል ስትራቴጅክ እቅድ አዘጋጅቶ ማቅረብ የሚችል፣

 የመንግስትን ፖሊሲና ስትራቴጅ ለመፈጸምና ለማስፈጸም ዝግጁ የሆነ፣

 ተቋሙን ውጤታማ ለማድረግ ተጨማሪ ክህሎት ያለው እና ብዝሀነትን የሚያክብር እና ልዩ ድጋፍ

ለሚያስፈልጋቸው አካላት ድጋፍ የሚያደርግ፣

 ተባብሮ የመስራትና የመምራት ብቃት ያለው እና በውሳኔ አሰጣጥ ሂደት ልምድ ያለው፣

 ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር መስራት የሚችል፣


ለቴ.ሙ.ት.ስ. ኮሌጅ እና ተቋም ዲንና ምክትል ዲን እጩ ተወዳዳሪ
• የተቃም ውስጥ አሰልጠኞች

• በትኩረት ዘርፎች ስልጠና ከሚሰጥባቸው ሙያዎች በአንዱ በ ቢ ደረጃ ከፍተኛ ኢንስትራክተር፤ በቴክኒክና

ሙያ አመራር (TVET Leader Ship) በኤ ደረጃ ኢንስትራክተር ወይም ከዚያ በላይ የደረሰ፣

• በሰለጠነበት የሙያ ዘርፍ ደረጃ IV/V ተመዝኖ ብቃቱ የተረጋገጠ ;

• በማሰልጠን ስነ ዘዴ ስልጠና ብቁ የሆነ፣

• ተቋሙን ወደ ላቀ ደረጃ ማድረስ የሚያስችል መሪ የልማት እቅድ አዘጋጅቶ ማቅረብ የሚችል፣

• የመንግስትን ፖሊሲና ስትራቴጅ ለመፈጸምና ለማስፈጸም ዝግጁ የሆነ፣

• ተቋሙን ውጤታማ ለማድረግ ተጨማሪ ክህሎት ያለው እና ብዝሀነትን የሚያክብር እና ልዩ ድጋፍ

ለሚያስፈልጋቸው አካላት ድጋፍ የሚያደርግ፣

• ተባብሮ የመስራትና የመምራት ብቃት ያለው እና በውሳኔ አሰጣጥ ሂደት ልምድ ያለው፣

• ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር መስራት የሚችል፣


ለቴ/ ሙ/ት/ስ/ ኮሌጅ እና ተቋም ዲንና ምክትል ዲን እጩ ተወዳዳሪ
• ከኢንዱስትሪው ተወዳዳሪ ሆነው ለሚቀርቡ

 በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ስልጠና በሚሰጥባቸው ሙያዎች በቢ ደረጃ ከፍተኛ

ኢንስትራክተር፤ በኤ ደረጃ እና ከዚያ በላይ የትምህርት ዝግጅት ያለውና 7 ዓመትና በላይ የስራ ልምድ

ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፤

 በሰለጠነበት የሙያ ዘርፍ ደረጃ IV/V ተመዝኖ ብቃቱ የተረጋገጠ ;

 በማሰልጠን ስነ ዘዴ ስልጠና ብቁ የሆነ፣

 ተቋሙን ወደ ላቀ ደረጃ ማድረስ የሚያስችል መሪ የልማት እቅድ አዘጋጅቶ ማቅረብ የሚችል፣

 የመንግስትን ፖሊሲና ስትራቴጅ ለመፈጸምና ለማስፈጸም ዝግጁ የሆነ፣

 ተቋሙን ውጤታማ ለማድረግ ተጨማሪ ክህሎት ያለው እና ብዝሀነትን የሚያክብር እና ልዩ ድጋፍ

ለሚያስፈልጋቸው አካላት ድጋፍ የሚያደርግ፣

 ተባብሮ የመስራትና የመምራት ብቃት ያለው እና በውሳኔ አሰጣጥ ሂደት ልምድ ያለው፣

 ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በትብብር መስራት የሚችል፣


ለትምህርትና ስልጠና ክፍል ዕጩ ተወዳዳሪ (Department Head)

• በተቋሙ ውስጥ ስልጠና በሚሰጥበት የሙያ መስክ በቢ ወይም በኤ ደረጃ ኢንስትራክተር ወይም ከዚያ

በላይ ፣

• የትምህርት ክፍሉን ወደ ላቀ ደረጃ ማድረስ የሚያስችል መሪ የልማት እቅድ አዘጋጅቶ ማቅረብ የሚችል፣

• በሰለጠነበት የሙያ ዘርፍ ደረጃ በደረጃ IV/V ተመዝኖ ብቃቱ የተረጋገጠ እና

• በማሰልጠን ስነ ዘዴ ስልጠና ብቁ የሆነ፣

• በኢንስትራክተርነት ቆይታው ከፍተኛ የስራ አፈጻጸም ያለው እና በመልካም ስነ ምግባሩ ምስጉን የሆነ፣

• የመንግስትን ፖሊሲና ስትራቴጅ ለመፈጸምና ለማስፈጸም ዝግጁ የሆነ፣

• የትምህርት ክፍሉን ውጤታማ ለማድረግ ተጨማሪ ክህሎት ያለው እና ብዝሀነትን የሚያክብር እና ልዩ

ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው አካላት ድጋፍ የሚያደርግ፣

• በቡድን የመስራትና የመምራት ብቃት ያለው እና በውሳኔ አሰጣጥ ሂደት ልምድ ያለው፣

• ከሌሎች ትምህርትና ስልጠና ክፍሎች ጋር በትብብር መስራት የሚችል፣


አንቀጽ 8፡ የተቋም አመራር የመመልመያ መስፈርት የነጥብ አሰጣጥ

ለዲኖች እና ምክትል ዲኖች (100 %)

 የትምህርት ደረጃ 10%


 የስራ ልምድ (አገልግሎት) 10%
 የቃል ፈተና 10%
 የተዘጋጀ የተቋሙ ስትራቴጅክ እቀድ 50 %
 በተቋሙ ትምህርትና ስልጠና ቦርድ የሚሞላ 10%
 በክልሉ/ ከተማ አስተዳደሩ ቴ/ሙ/ት/ስ/ኤጀንሲ/ቢሮ ወይም
ክልሉ/ከተማ አስተዳደሩ ውክልና በሚሰጠው አካል የሚሞላ 10%
የነጥብ አሰጣጥ የቀጠለ….

የትምህርት ደረጃ 10%


– ለመጀመሪያ ዲግሪ 8% ፣

– ለሁለተኛ ዲግሪ 9% እና

– ለሶስተኛ ዲግሪ 10% ይሆናል፡፡

የስራ ልምድ(አገልግሎት) 10%

• ለዲንና ምክትል ዲን ለመወዳደር ዝቅተኛ አገልግሎት ከ 5-7 ዓመት ሆኖ ለያንዳንዱ

ተወዳዳሪ የሚሰጠው የስራ ልምድ ውጤት እንደ አገልግሎቱ መጠን ከ 5 ዓመት

እስከ 10 ዓመት አገልግሎት ያለው 5-10% የሚያገኝ ይሆናል፣ 10 ዓመትና በላይ

የስራ ልምድ/አገልግሎት/ያለው በተመሳሳይ 10% የሚያገኝ ይሆናል፡፡


ትምህርትና ስልጠና ክፍል ተጠሪ (Department Head) የነጥብ አሰጣጥ

 የትምህርት ደረጃ 10%


 የስራ ልምድ (አገልግሎት) 10%

 የ 18 ወራት የስራ አፈጻጸም 30%


 የጽሁፍ ወይም የቃል ፈተና 15%
 የትምህርት ክፍል ስትራቴጅክ እቀድ 15 %

 በትምህርት ክፍሉ ባሉ አሰልጣኞች እና ኢንስትራክተር የሚሞላ 10%


 በተቋሙ ማኔጅመንት የሚሞላ 10%
ትምህርትና ስልጠና ክፍል ተጠሪ (Department Head) የነጥብ አሰጣጥ

 የትምህርት ደረጃ 10%


 ለመጀመሪያ ዲግሪ 8% ፣

 ለሁለተኛ ዲግሪ 9% እና

 ለሶስተኛ ዲግሪ 10% ይሆናል፡፡

 የስራ ልምድ(አገልግሎት) 10%


• ለትምህርትና ስልጠና ክፍል ተጠሪ ለመወዳደር ዝቅተኛ አገልግሎት እንደ ተቋሙ ተጨባጭ ሁኔታ ከ

2-5 ዓመት ሆኖ ለያንዳንዱ ተወዳዳሪ የሚሰጠው የስራ ልምድ ውጤት እንደ አገልግሎቱ መጠን ከ 2

ዓመት እስከ 10 ዓመት አገልግሎት ያለው 2-10% የሚያገኝ ይሆናል፣ ከ 10 ዓመትና በላይ የስራ

ልምድ/አገልግሎት/ያለው በተመሳሳይ 10% የሚያገኝ ይሆናል፡፡


አንቀጽ 9፡ መልማይ ኮሚቴ

• ለዋና ዲንና ለምክትል ዲኖች


 የተቋሙ ትምህርትና ስልጠና ቦርድ የሚወክለው አንድ አባል-------ሰብሳቢ

 የተቋሙ የሴቶች ተወካይ---------------------------------------------------አባል

 የተቋሙ መሰረታዊ መምህራን ማህበር ተወካይ----------------------አባል

 የተቋሙ የሰልጣኞች ተወካይ----------------------------------------------አባል

 የተቋሙ የሰው ኃብት ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር--------አባል እና ጸሀፊ


•  
መልማይ ኮሚቴ

ለትምህርትና ስልጠና ክፍል ተጠሪ (Department Head)

• የተቋሙ ውጤት ተኮር ትምህርትና ስልጠና ም/ዲን -----------------ሰብሳቢ

• የተቋሙ ኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ም/ዲን --------------------------አባል

• የተቋሙ የሴቶች ተወካይ-------------------------------------------አባል

• የተቋሙ መሰረታዊ መምህራን ማህበር ተወካይ------------------------አባል

• የተቋሙ የሰልጣኞች ተወካይ----------------------------------------አባል

• የተቋሙ የሰው ኃብት ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር---------አባልእና ጸሀፊ


አንቀጽ 10፡ የመልማይ ኮሚቴው ተግባርና ኃላፊነት

የኮሚቴው ሰብሳቢ እና የተቋሙ የሰው ኃብት ልማት ዳይሬክቶሬት

ዳይሬክተር፣

• ዝርዝር የጊዜ ሰሌዳ እና የምልመላ ማስፈጸሚያ ዕቀድ ያዘጋጃሉ፣

• ክፍት የአመራር ቦታን የነባሩ አመራር የስራ ዘመን ከመጠናቀቁ ከ 2

ወር በፊት ተደራሽነት ባላቸው የመገናኛ ስልቶች ያሳውቃሉ፣

• ማስታወቂያ ለወጣበት ክፍት የአመራርነት ቦታ በተወዳዳሪዎች

የሚቀርቡ ማስረጃዎችን መቀበል፣ መመዝገብ ፣ አደራጅቶ መያዝ እና

ለውድድር ብቁ የሆኑትን መለየት፣


የመልማይ ኮሚቴው ተግባርና ኃላፊነት የቀጠለ…

• ተወዳዳሪዎች ከተመዘገቡበት ቀን ጀምሮ በ 1 ወር ውስጥ የተቋሙን

ስትራቴጅክ ዕቅድ ማቅርብ እንዲችሉ ጊዜ ይሰጣል፣

• በተወዳዳሪዎች የሚቀርብን የተቋም ስትራቴጅክ ዕቅድ ከሶስት ያላነሱ

ገምጋሚ አካላት ከዩኒቨርስቲ ወይም በአካባቢ ከሚገኙ ተቋማት በመጋበዝ

የመልማይ ኮሚቴው አባላት በተገኙበት የስትራቴጅክ ዕቅዱን በማስገምገም

ውጤት ማስሞላት፣

• የቃል ፈተናን በማዘጋጀት የአመራርነት ክህሎትን መለየት፣

• ውጤቶችን በማሰባሰብ በቃለ-ጉባኤ በማስደገፍ ለአጽዳቂ አካል ማቅረብ፣

• የበላይ አካል ውጤቱን ካጸደቀው በኋላ ለአሸናፊው በጽሁፍ ማሳወቅ፣


ክፍል ሦስት
የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና የተቋም አመራር የጥቅማጥቅም

የጥቅማ ጥቅም ዓይነቶች


1. አንዋላይዜሽን/ኢልቭናይዜሽን
2. የቤት አበል
3. የኃላፊነት ክፍያ
4. የትራንስፖርት ክፍያ
5. የሞባይል እና ሲዲኤመኤ ካርድ ክፍያ
የጥቅማ ጥቅም አፈጻጸም
አንዋላይዝኤሽን/ኢለቭናይዜሽን

• ለዋና ዲኖች የአንዋላይዜሽን አበል የደመወዛቸው 20 በመቶ በየወሩ

በደመወዛቸው ላይ ተጨምሮ እንዲከፈላቸው ይደረጋል፡፡

• ለምክትል ዲኖች የአንዋላይዜሽን አበል የደመወዛቸው 15 በመቶ

በየወሩ በደመወዛቸው ላይ ተጨምሮ እንዲከፈላቸው ይደረጋል ፡፡

• ለትምህርትና ስልጠና ክፍል ተጠሪ/Department Head/

የኢለቭናይዜሽን አበል የደመወዛቸው 10 በመቶ በየወሩ

በደመወዛቸው ላይ ተጨምሮ እንዲከፈላቸው ይደረጋል፡፡


የቤት አበል
ተቋማት በሚያሰለጥኑት የስልጠና ደረጃ በሚገኙበት ቦታ ማለትም ክልል፣ ከተማ
አስተዳደር ፣ ዞን እና ወረዳ የተለያዩ በመሆናቸው ይህን ግምት ውስጥ በማስገባት የቤት
አበል ክፍያ በሚከተለው ሰንጠረዥ መሰረት ተዘርዝሯል፡፡

ተ.ቁ
ቴ/ሙ/ት/ ስልጠና ቴ/ሙ/ት/ ስልጠና
ኃላፊነት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
ኮሌጅ ተቋም

1 ዋና ዲን
1500.00 ብር 1100.00 ብር 850.00 ብር
2 ምክትል ዲን 1200.00 ብር 900.00 ብር 500.00 ብር

3 የትምህርትና ስልጠና ክፍል 350.00 ብር 250.00 ብር 200.00 ብር


ተጠሪ
የኃላፊነት ክፍያ
• ተቃማት በሚያሰለጥኑት የስልጠና ደረጃ ያለባቸውን የስራ ጫና እና
ኃላፊነት ልክ በተዋረድ የኃላፊነት ክፍያ በሚከተለው ሰንጠረዥ
መሰረት ተዘርዝሯል፡፡

ተ.

ቴ/ሙ/ት/ ስልጠና ቴ/ሙ/ት/
ኃላፊነት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
ኮሌጅ ስልጠና ተቋም

1 ዋና ዲን
1500.00 ብር 1000.00 ብር 650.00 ብር

2 ምክትል ዲን 1300.00 ብር 800.00 ብር 500.00 ብር

3 የትምህርትና ስልጠና ክፍል 500.00 ብር 400.00 ብር 250.00ብር


ተጠሪ
የትራንስፖርት ክፍያ

ለዋና ዲን በየወሩ 800.00 ብር

ለምክትል ዲን በየወሩ 700.00 ብር

ለትምህርትና ስልጠና ክፍል ተጠሪ 300 ብር


 
የሞባይል እና የሲዲኤምኤ ካርድ ክፍያ

ተ.
ቁ ፖሊ ቴክኒክ ቴ/ሙ/ት/ ቴ/ሙ/ት/
ኃላፊነት
ኮሌጅ ስልጠና ኮሌጅ ስልጠና ተቋም

1 ዋና ዲን
800.00 ብር 500.00 ብር 300.00 ብር

2 ምክትል ዲን 500.00 ብር 300.00 ብር 200.00 ብር

3 የትምህርትና ስልጠና 200.00 ብር 150.00 ብር 100.00ብር


ክፍል ተጠሪ
አንቀጽ 13፡ ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች
• የዲኖችና የም/ዲኖች የቆይታ ጊዜ 5 ዓመት ይሆናል፤ ሆኖም ግን በቆይታቸው ከፍተኛ
አፈጻጸም ካስመዘገቡ ለቀጣዩ ዙር መወዳደር ይችላሉ፣ ነገር ግን ከሁለት ዙር በላይ መወዳደር
አይችሉም፣

• በ አንቀጽ 13 ንኡስ አንቀጽ 13.1 የተጠቀሰው እንደ ተጠበቀ ሆኖ በቆይታ ጊዜው ተገቢውን
አገልግሎት ካልሰጠ ወይም ዝቅተኛ አፈጻጸም ካስመዘገበ ተገምግሞ ከኃላፊነት የሚነሳ ይሆናል፣

• አንቀጽ 13.2 የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ በስራ ድክመት ወይም በራስ ፍላጎት ወይም በጤና
ችግር ምክንያት ከኃላፊነት የተነሳ ዲን ወይም ምክትል ዲን በውድድር እስኪተካ የክልሉ/ከተማ
አስተዳደሩ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ/ኤጀንሲ ወይም ውክልና በሚሰጠው አካል
ቦታው በውክልና ተሸፍኖ ይቆያል፣

• የትምህርትና ስልጠና ክፍል ተጠሪ የቆይታ ጊዜ 2 ዓመት ሆኖ በቆይታው ከፍተኛ አፈጻጸም


ካስመዘገብ ዳግም ሊወዳደር ይችላል፣
ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች

• የዲኖችና ምክትል ዲኖች መልማይ ኮሚቴ የአገልግሎት ዘመን 2 ዓመት ሆኖ እንደ አስፈላጊነቱ
የሚራዘም ይሆናል፣

• የዲኖች እና ምክትል ዲኖች መልማይ ኮሚቴ ተጠሪነቱ ለተቋሙ ትምህርትና ስልጠና ቦርድ
ይሆናል፣

• የዲኖችና ምክትል ዲኖች ምደባ በክልል/ከተማ አስተዳደር ቴ/ሙ/ት/ስ/ቢሮ/ኤጀንሲ


የሚጸድቅ ይሆናል፣

• የትምህርትና ስልጠና ክፍል ተጠሪዎች መልማይ ኮሚቴ ተጠሪነቱ ለተቋሙ ዲን ይሆናል፣

• የትምህርትና ስልጠና ክፍል ተጠሪዎች መልማይ ኮሚቴ የቆይታ ጊዜ 2 ዓመት ሆኖ እንደ


አስፈላጊነቱ የሚራዘም ይሆናል፣

• የትምህርትና ስልጠና ክፍል ተጠሪዎች ምደባ በተቋሙ ዲን የሚጸድቅ ይሆናል፣

• በአንቀጽ 12 ንኡስ አንቀጽ 12.1 የተቀመጡ ዝርዝር ጥቅማጥቅሞች ኃላፊዎች ከኃላፊነት


በሚነሱበት ጊዜ ሲያገኟቸው የነበሩት ጥቅማጥቅሞች የሚቋረጡ ይሆናል፡፡
ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች

• በአንቀጽ 12 ንኡስ አንቀጽ 12.1. ቁጥር 12.3. 2 የተቀመጠው እንደተጠበቀ ሆኖ የትራንስፖርት


ክፍያ አበል የተሸከርካሪ አቅርቦት የተሟላላቸው ኃላፊዎችን አይመለከትም፡፡

• ጥቅማጥቅሞች የሚመለከታቸው የፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆች ፣ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና


ስልጠና ኮሌጆች እና የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋም ዲኖች ፣ ምክትል ዲኖች እና
ትምህርትና ስልጠና ክፍል ተጠሪዎች ብቻ ናቸው፡፡

• በአንድ የስራ ኃላፊነት ላይ ያለ አመራር ከአንድ በላይ በሆነ መንግድ የጥቅማጥቅም ተከፋይ
አይሆንም፡፡

• አንድ አመራር በዓመት እረፍት ፣ በትምህርት እና በሌሎች ምክንያቶች ከ አንድ ወር በላይ


በመደበኛ ስራው ላይ የማይገኝ ከሆነ የትራንስፖርት የሞባይል እና ስዲኤሚኤ ካርድ ክፍያ
የማይከፈለው ይሆናል፡፡

• ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች የራሳቸውን ነባራዊ ሁኔታ መነሻ በማድረግ ይህን መመሪያ
መሰረት አድርገው የራሳቸውን መመሪያ ማውጣት ይችላሉ
ክፍል አራት
አንቀጽ 14፡ የመሸጋገሪያ ጊዜ

• ከዚህ ቀደም በዲን ወይም በምክትል ዲን ቦታ ተመድቦ


በመስራት ላይ የሚገኝ አመራር ቆይታ በአንቀጽ 13 ንዑስ
አንቀጽ 13.1 የተቀመጠው እንደተጠበቀ ሆኖ ከተመደበ 5
አመት እና በላይ ከሆነው ለቦታው የውድድር ማስታወቂያ
ይወጣል፤
ከፍል አምስት
አንቀጽ 15. የመመሪያው ተግባራዊነት

• ይህ መመሪያ ተግባራዊ የሚሆነው መመሪያው ከወጣበት


ከዛሬ----------ቀን----- ዓም ጀምሮ ይሆናል፡፡

• መመሪያው ከጸናበት ቀን ጀምሮ ከዚህ በፊት በፖሊ ቴክኒክ ኮሌጆች፣


በቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጆች እና በቴክኒክና ሙያ
ትምህርትና ስልጠና ተቋም ሲተገበር የነበረው የአመራር ምልመላ፣
ምደባ እና ጥቅማጥቅም ማስፈጸሚያ ሰነድ በዚህ መመሪያ ተሸሯል፡፡

ሳሙኤል ዑርቃቶ (ዶ/ር)


የሳይንስና የከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር
አመሰግናለሁ!!

You might also like