You are on page 1of 5

የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ

I. አጠቃላይ መግለጫ
የመሥሪያ ቤቱ ስም የሥራ መደቡ መጠሪያ የሥራ ዘርፍ/የሥራ ሂደት
ጤና ጥበቃ ሚ/ር የጤና አገልግሎት ጥራት ማጠናከር የጤና አገልግሎት ጥራት
ባለሙያ ІV

የቅርብ ኃላፊ የሥራ መደብ በሲቪል ሰርቪስ ሚኒስቴር/ቢሮ ብቻ የሚሞላ


/ተጠሪነት
የሥራው ደረጃ የሥራው ኮድ
ለቡድን መሪ
መሥሪያ ቤቱ የሚገኝበት ቦታ

II. የሥራ መደቡ ዋና ዓላማ፣ ውጤቶችና ተግባራት


2.1. የሥራ መደቡ ዓላማ፡-
 የአሠራር ማኑዋል፣የማጣቀሻ መጻሕፍት በማዘጋጀት፤ ጥናትና ምርምር በማካሄድ፣የሪፎርምትግበራ
ላይድጋፍና ክትትል በማድረግ እና የስልጠና ክፍተትን ለይቶ ስልጠና በመስጠት በጤና ተቋማት
የአገልገግሎት አሰጣጥ ጥራትና ቅልጥፍና እንዲኖር ማድረግ ነው፡፡

ውጤት 1፡መመሪያ፣የአሠራር ማኑዋል፣የማጣቀሻ መጻሕፍት ማዘጋጀት እና ጥናት ማካሄድ


 ያለፈውን በጀት ዓመት የሥራ አፈፃፀም በመተንተን በቀጣይ የሚሠሩትን አንኳር ሥራዎች በመለየት
ረቂቅ እቅድ ያዘጋጃል፣
 ፖሊሲዎች፣ እስትራቴጂዎች፣ ፕሮጀክቶች እና ፕሮገራሞች መንደፍ እና መቅረጽ፡፡
 በመንግስት የጤና ተቋማት ሥር የግል ሕክምና አገልግሎት መላስተግበር የሚያስችል መመሪያ
ማዘጋጀት፣
 የኦዲቴብል ፋርማሲ በሁሉም ሆስፒታሎች ለመተግበር የሚያስችል የህግ ማዕቀፍ ብሎም የአሰራር
መመሪያ ማዘጋጀት እና መተግበር፣
 የአካል ንቅለ ተከላ በሀገራችን የጤና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ እንዲካተቱ ለማድረግ የሚያስችል
የህግ ማዕቀፍ ማዘጋጀት፣ አስፈላጊነቱንና አዋጭነቱን ለማየት የሚያስችል ጥናት ማድረግ፣
የሚተገበርባቸው ጤና ተቋማት መምረጥ እና አገልግሎቱን ማስጀመር፡፡
 የድንገተኛ ህክምና እና የህሙማ ቅብብሎሽ ስራዓት ለማስተግበር የሚያስችሉ የህግ ማዕቀፎችን
ማዘጋጀትና ማሻሻል
 የጤና አገልግሎትን የዋጋ እና የአካል ጉዳት ትመና መመሪያ ማዘጋጀት፣ ማሻሻልና ማፀደቅ
 የፕሮጄክት መነሻ ፁሁፍ በማዘጋጀት በውይይት እንዲተች ያደርጋል፣በተገኘው ግብአት ሰነዱን
ያዳብራል፣የፕሮጄክት ረቂቅ ሰነድ ያዘጋጃል
 የጤና አገልግሎትን ለማሻሻል ለተመረጡ ፕሮጄክቶችን በበላይነት የሚያማክር የቴክኒክ ኮሚቴ
ያቋቁማል፣ ለኮሚቴው ቢጋር ያዘጋጃል፣ኮሚቴውን ይመራል
 ሀገራዊና አለም አቀፍ ምርጥ ተሞክሮዎችን በመቀመር እንዲተገበሩ ለተቋማት ያሰራጫል
ተግባራዊነቱንም ይከታተላል፡፡
 በጤና ተቋማት የዳሰሳ ጥናት የሚያስፈልጋቸውን ይለያል፣ለጥናቱ አጋዥ የሆኑ መጠይቆችን በማዘጋጀት
ያስተቻል ለጥናቱ መረጃ የሚሰበስቡ ባለሙያዎችን ይለያል ተሰባስበው የቀረቡለትን መረጃዎች
ያጠናቅራል ይተነትናል፣ ጥናቱን ያካሂዳል
 የጥናቱንግኝት ከመፍትሄ ሃሳብ ጋር ሪፖርት ያቀርባል፣ ሲፀድቅ ተግባራዊ እንዲሆን ያደርጋል
 የቅድመ-ሆስፒታል የድንገተኛ ሕክምና አገልግሎትን ለማስፈፀም የሚረዳ መመሪያና ማኑዋሎችን
እንዲሁም የአቡላንስ አገልግሎት ደንብ ያዘጋጃል
 የድንገተኛ ሕክምና አገልግሎትን ለመደግፍ የሚያስችሉ የማጣቀሻ መፃህፍትን ያዘጋጃል
 በነርሲንግ፣ በጥራት ቁጥጥር፣ በፋርማሲ፣ በላቦራቶሪ፣ ዲያግኖስቲክ፣ በወሊድ አገልግሎት፣ በህጻናት
ህክምና፣ በሆስፒታሎች ትስስር ለጥራት፣ በድንገተኛ ህክምና እንዲሁም በህክምና መሳሪዎች
ለመተግበር እና ለመከታተል የሚያስችል የአሰራር መመሪያ ማዘጋጀት
 የእስፔሻሊቲ አገልግሎቶች ቅድመ-ትኩረት ለመለየት ጥናት ማካሄድ፣ የሚተገበርባቸው ጤና
ተቋማት መምረጥ እና አገልግሎቶችን ማስጀመር፡፡
 ከተለያዩ አጋር ድርጅቶች ጋር አብሮ ይሰራል ፕሮግራሞች እና ፕሮጀክቶች ለሚመለከታቸው
መንግስታዊ እና መንግስታዊ ላልሆኑ አካላት ያስተዋውቃል፡፡

ውጤት 2፡የአገልግሎትአሰጣጥመለኪያዎችንበማዘጋጀት፣በመሰብሰብ፣በመተንተንየድጋፋናክትትልየትኩረትአቅጣጫ
በመለየት ቀጣይነት ያለው እና ሁሉን አቀፍ የሆነ ድጋፍና ክትትል ማካሄድ
 ጤና ተቋማት የሚያስፈልጋቸው ድጋፍ ለመለየት የሚያስችል የዳሰሳ ጥናት ያካሄዳል በግኝቱ
መሰረት ጠንካራ እና ደካማ ጎኖች በመለየት ድጋፍ ያደርጋል
 የጤና አገልግሎትን ለማሻሻል የተመረጠውን ፕሮግራም/ፕሮጀክት አተገባበር ለመከታተል የሚረዳ
የክትትልና ግምገማ ቅፅ ያዘጋጃል፣
 በክትትልናግምገማቅፅተሞልቶ የመጣውን መረጃ ይተነትናል፣ ክፍተቶችንም ይለያል፣በተለዩ ክፍተቶች
ላይ ከቴክኒካል ኮሚቴ ጋር ተከታታይ ውይይት በማካሄድ የማስተካከያ ዕርምጃ ይወስዳል፣
 የጤና አገልግሎትን ለማሻሻል የተመረጠው ፕሮጄክትሲፀድቅዝርዝርመርሃግብር በማዘጋጀት ተግባራዊ
እንዲሆን ያደርጋል፣
 የጤና አገልግሎት ለማሻሻል የተቀረፀው ፕሮጄክት ያለበትን የአፈፃፀም ደረጃ የሚያሳይ የማጠቃለያ
ሪፖርት ያቀርባል፣
 የአገልግሎት አፈጻጸም መለኪያዎችንበመተንተንየድጋፋናክትትልየትኩረትአቅጣጫ ይለያል
 የየተቋማት የጤና አገልግሎት ሪፎርም አፈፃፀም ግምገማዊ ስብሰባ ለማድረግ የተቋማቱን ሪፖርት
ትንተና ያካሂዳል በግምገማዊ ስብሰባ ወቅት ለተሳታፊ ጤና ተቋማት ቴክኒካል ግብረ መልስ ይሰጣል

ውጤት 3፡ በጤናተቋማት የስልጠና ክፍተትን በመለየት መሰረታዊና የአሰልጣኞች ስልጠና መስጠትና


ስለጠናውያመጠውንፋይዳ መገምገም፣
 በጤናተቋማትያለውንየባለሙያዎች የስልጠና ክፍተት ይለያል፣መሰረታዊና የአሰልጣኞች ስልጠና
ይሰጣል ስለጠናውያመጠውንፋይዳ ይገመግማል፣
 ለጤናተቋማትየቦርድአባላት የስልጠና ማቴሪያሎችን አዘጋጅቶ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ይሰጣል
 ለጤናተቋማትየቦርድአባላትበጤናአገልግሎትገቢማስገኛሪፎርምእናየአመራርክህሎትማሻሻያላይግንዛቤበማስጨበ
ጥትበራውን ይከታተላል
 ለሆስፒታልባለሙያዎችበድገተኛሕክምናየመሰረታዊናአደቫስድ የህይወት አድን ስልጠና መስጫ ማኑዋችን
ያዘጋጃል ስልጠናም ይሰጣል
III. የሥራው ባህሪ መግለጫዎች
3.1. የሥራ ውስብስብነት
 ያለፈውን የበጀት ዓመት የሥራ አፈፃፀም በመተንተንን ረቂቅ እቅድ ማዘጋጀት፣ በመንግስት የጤና
ተቋማት ሥር የግል ሕክምና መስጫ ክፍልን ስራ ለመምራት፣ የቅድመ-ሆስፒታል የድንገተኛ ሕክምና
አገልግሎትን ለማስፈፀም የሚረዳ እና የጤና አገልግሎትን የዋጋ ትመና ለማደረግ የአቡላንስ
አገልግሎት ደንብ፣ መመሪያ፣ ማንዎል ማዘጋጀት፣ ማሻሻል እና ማፀደቅ፣የፕሮጄክት መነሻ ፁሁፍ
ማዘጋጀት፣ ሀገራዊናአለምአቀፍምርጥተሞክሮዎችንመቀመርንና ማስፋፋትን፣አጋዥ የማጣቀሻ መፅሃፍትን
እና መጠይቆችን/ቅፆችንማዘጋጀት፣ በክትትልናግምገማ ወቅት በቅፆች ተሞልቶ የመጣውን መረጃ
መተንተን፣ የጤና አገልግሎትን ለማሻሻል የተመረጠው ፕሮጄክትሲፀድቅ ተግባራዊ እንዲሆን ማድረግ፣
የሪፎርምአፈጻጸምመለኪያዎችንበመተንተንየድጋፋናክትትልየትኩረትአቅጣጫ ማዘጋጀት፣ የጤና አገልግሎት
ሪፎርም አፈፃፀም ግምገማዊ ስብሰባ ለማድረግ የተቋማቱን ሪፖርት ትንተና ያካሂዳል ቴክኒካል
ግብረ መልስ መስጠት፣ የስልጠና ክፍተት መለየት፣ የአሰልጣኞች ስልጠና መስጠት፣
ስለጠናውያመጠውንፋይዳ መገምገም፣ ለጤናተቋማትየቦርድአባላት የስልጠና ማቴሪያሎችን ማዘጋጀት፣
ለሆስፒታልባለሙያዎችበድገተኛሕክምናየመሰረታዊናአደቫስድ የህይወት አድን ስልጠና መስጫ ማኑዋችን
ማዘጋጀት ሲሆን
 በስራ ሂደትም ወቅታዊ፣ የተሟላና ጥራት ያለው መረጃ አለማግኘት፣ የተዘጋጁ ደንቦች
መመሪያዎች የአሰራር ማንዋሎች ከሁሉም የጤና ተቋማት ነባራዊ ሁኔታ ጋር አለመጣጣም፣
ለውሳኔ የሚቀርቡ ጉዳዩች በበላይ አካላት ቶሎ ተቀባይነት አለማግኘት፣ ምርጥ ተሞክሮዎች
በሚሰበሰቡበት ወቅት የምርጥ ተሞክሮዎችን አይነትና ትርጓሜያቸውን ለመረዳት አስቸጋሪ
መሆን፣ ሰልጣኞች የተለያየ የግንዛቤ ደረጃ ላይ መሆን የሚያጋጥም ሲሆን
 የተሟላና ወጥ የሆን የመረጃ አሰባሰብ ስርአትን በመዘረጋትና ክትትል በማድረግ፣ በሁሉም ደረጃ
ተግባራዊ የሚሆኑ ሰነዶች ለማዘጋጀት የዳሰሳጥናት በማካሄድ እና ውይይት በማድረግ፣ ስራዉን
እንዲረዱት ለበላይ አካላት ማብራሪያ በመስጠት፣ የምርጥ ተሞክሮ አይነቶችን እና
ጥርጓሜያቸውን ለመለየት የሚስችል መስፍርቶችን በማዘጋጀትና የሰልጣኞችን አይነትና ደረጃ
ለይቶ ለሁሉም በሚመጥን መልኩ ተዘጋጅቶ በማሰልጠን መፍታትን ይጠይቃል፡፡
3.2. ራስንችሎመስራት
3.2.1. ሥራው የሚከናወንበት አግባብ
 ሥራው ከኃላፊ በሚሰጥ አጠቃላይ መመሪያ፣ ደንብ እና የፕሮጄክት እቅዶች መሰረት በማድረግ
የሚሰራ ነው
3.2.2. ሥራው የሚጠይቀው የክትትልና ድጋፍ ደረጃ
 ሥራው ከኃላፊ በተሰጠው አጠቃላይ መመሪያ፣ ደንብ እና የፕሮጄክት እቅዶች መሰረት አጠቃላይ
የፕሮግራሞችን አላማ ከማሳካት አንፃር በመጨረሻ ይገመገማል፡፡
3.3.ተጠያቂነት
3.3.1. ተጠያቂነት ለሥራ ውጤት /
 ያለፈውን የበጀት ዓመት የሥራ አፈፃፀም ተንትኖ ረቂቅ እቅድ ባያዘጋጅ፣ የጤና አገልግሎት ጥራትና
ቅልጥፍናን ለማሻሻል የሚረዱ ደንብ፣ መመሪያ፣ የስራና ስልጠና ማንዎል ባያዘጋጅ፣ ባያሻሽል እና
ባያፀድቅ፣የፕሮጄክት መነሻ ፁሁፍ ባያዘጋጅ፣ ሀገራዊናአለምአቀፍምርጥተሞክሮዎችንባይቀምርና
ባያስፋፋ፣አጋዥ የማጣቀሻ መፅሃፍትን እና መጠይቆችን/ቅፆችንባያዘጋጅ፣ በክትትልናግምገማ ወቅት
በቅፆች ተሞልቶ የመጣውን መረጃ ባይተነትን፣
የሪፎርምአፈጻጸምመለኪያዎችንባይተነትንናየድጋፋናክትትልየትኩረትአቅጣጫባያዘጋጅ፣ የጤና አገልግሎት
ሪፎርም አፈፃፀም ግምገማዊ ስብሰባ ለማድረግ የተቋማቱን ሪፖርት ትንተና በማካሄድ ቴክኒካል
ግብረ መልስ ባይሰጥ፣ የስልጠና ክፍተት ባይለይና የአሰልጣኞች ስልጠና ባይሰጥ እና
ስለጠናውያመጠውንፋይዳ ባይገመግም የተቋማት የጤና አገልግሎት አሰጣጥ ጥራትና ቅልጥፍና ደረጃ
ይወርዳል ይህም የመሥሪቤቱን የእቅድ አፈፃጸም ላይ አሉታዊ ተፅህኖ ይፈጥራል ፡፡
3.3.2. ተጠያቂነት ለምስጢራዊ መረጃ
 በረቂቅ ደረጃ ያሉና በበላይ አካላት ውሳኔን ያላገኙ የህግ ማህቀፎችን እና መሪሆስፒታል
በሚመረጡበት ሂደት መረጃዎችን በጥንቃቄ መያዝን የሚጠይቅ ሲሆን የህግ ማእቀፎች ሳይፀድቁ
እና ምርጫው ሳይጠናቀቅ መረጃው ለሶስተኛ ወገን ተላልፎ የማወዳደር ሂደቱን ሊያስተጓጉል
ይችላል በመስሪያቤቱ ላይም አመኔታ ያሳጣል፡
3.4. ፈጠራ
 የጤና አገልግሎት ሪፎርም አፈፃፀም ትግበራን ለማሻሻል አዳዲስ የአሰራር ስልቶችን በመንደፍ፣
የፕሮጀክት ሃሳቦችን በማፍለቅ፣ ጥልቅ ምርምሮችና ትንተናዎችን በማድረግ፣ በአገር ውስጥና
ከአገር ዉጪ የሚገኙ ምርጥ ተሞክሮዎችን ቀምሮ ከአገራዊ ነባራዊ ሁኔታ ጋር ማጣጣምን
ይጠይቃል፡፡
3.5. የሥራግንኙነት
3.5.1. የግንኙነቱ ዓይነትና ደረጃ
 ሥራውከውስጥከቅርብኃላፊው፣ከስራክፍሉ ባለሙያዎች፣ ከሌሎች የስራ ክፍል ኃላፊዎችና
ባለሙያዎች፣ ከጤና ተቋማት ኃላፊዎች እና ባለሙያዎች፣ መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ካልሆኑ
ተቋማት ጋር የሥራ ግንኙነት ያደርጋል፡፡
3.5.2. የግንኙነቱ ዓላማ/አስፈላጊነት
 የሥራትዕዛዝለመቀበል፣ሪፖርት ለመስጠት፣ መረጃ ለመቀበልና ለመስጠት፣ ተቀናጅቶ ለመሥራት፣
የድጋፍ እና ክትትል ሥራዎችን ለመሥራት፣ ስልጠና እና ግብረ መልስ ለመስጠት ግንኙነት
ያድረጋል፡፡
3.5.3. የግንኙነቱ ድግግሞሽ
 ሥራው የሥራ ግንኙነት ያለው ሲሆን ከስራ ጊዜውም እስከ 30% ያህል ይሆናል፣
3.6. ኃላፊነት
3.6.1. ኃላፊነት ለሰው ሀብት
 የለውም፡፡
3.6.1.1 በኃላፊነት የሚመራቸው ሠራተኞች ብዛት
 የለውም
3.6.1.2. የኃላፊነት ዓይነትና ደረጃ
 የለበትም
3.6.2. ኃላፊነት ለንዋይ
 የለበትም
3.6.3. ኃላፊነት ለንብረት
 ሥራውን ለማከናወን የሚጠቀምባቸውን የቢሮ እቃዎች ማለትም እንደ ዲስክ ቶፕ ኮምፒዩተር፣
ላፕቶፕ ኮምፒዩተር፣ ሲዲኤምኤ፣ ፕሪንተር፣ ወንበር ጠረጴዛ፣ ሸልፍ የመያዝ ሃላፊነት ያለበት ሲሆን
ይህም እስከ 50000 ብር/ ሃምሳ ሽህ ብር/ ይደርሳል፡፡
3.7. ጥረት
3.7.1 የአዕምሮ ጥረት
 ሥራው ያለፈውን የበጀት ዓመት የሥራ አፈፃፀም መተንተንና ረቂቅ እቅድ ማዘጋጀት፣ የጤና
አገልግሎት ጥራትና ቅልጥፍናን ለማሻሻል የሚረዱ ደንብ፣ መመሪያ፣ ማንዎል ማዘጋጀት፣የፕሮጄክት
መነሻ ፁሁፍ ማዘጋጀት፣ ሀገራዊናአለምአቀፍምርጥተሞክሮዎችንመቀመርንና ማስፋፋትን፣አጋዥ የማጣቀሻ
መፅሃፍትን እና መጠይቆችን/ቅፆችንማዘጋጀት፣ በክትትልናግምገማ ወቅት በቅፆች ተሞልቶ የመጣውን
መረጃ መተንተን፣ የሪፎርምአፈጻጸምመለኪያዎችንበመተንተንየድጋፋናክትትልየትኩረትአቅጣጫ ማዘጋጀት፣
የጤና አገልግሎት ሪፎርም አፈፃፀም ግምገማዊ ስብሰባ ለማድረግ የተቋማቱን ሪፖርት ትንተና
በማካሄድ ቴክኒካል ግብረ መልስ መስጠት፣ የስልጠና ክፍተት በጥናት መለየት፣ የአሰልጣኞች ስልጠና
መስጠት፣ ስለጠናውያመጠውንፋይዳ መገምገም የአእምሮ ጥረትን የሚጠይቅ ሲሆን ይህም ከስራ
ጊዜው እስከ 70 በመቶ ይወስዳል፡፡
3.7.2. ስነልቦናዊ ጥረት
 የጤና ተቋማት የአገልግሎት አሰጣጥ ሪፎርሞችን ለማስተግበር በሚደረግ ድጋፍና ክትትል
እንዲሁም ጤና ተቋማትን አወዳድሮ ለመሻሻለምና እውቅና ለመስጠት ሥራዎች በሚሰሩበት
ወቅት የሚነሱ የተለያዩ ትችቶችን እና ክሶችን ተቋቁሞ ስራውን ውጤታማ ለማድረግ የስነልቦና
ዝግጁነትና ቁርጠኝነት ይጠይቃል፡፡
3.7.3 የዕይታ ጥረት፣
 ሥራው በኮምፒውተር ላይ የተለያዩ ጽሁፎችን ማንበብን እና መፃፍን፣ የቪዲሆ ኮንፈረንስ
ማድረግን የሚጠይቅ ሲሆን ይህም ከስራ ጊዜው እስከ 51% ያህል ይሆናል፡፡

3.7.4. የአካል ጥረት


 ስራው 85 በመቶበመቀመጥ፣ 15 በመቶበመቆም ይከናወናል፡፡

3.8.የሥራ አካባቢ ሁኔታ


3.8.1. ሥጋትና አደጋ፣
 የለበትም
3.8.2. የሥራ አካባቢ ሁኔታ
ሥራው ምቹ በሆነ አካባቢ የሚካናወን ነው

3.9.1. የትምህርት
የትምህርት ደረጃ የትምህርት አይነት
የመጀመሪያ /ቢ. ኤስ ሲ/ ዲግሪ በሕብረተሰብ ጤና፣በሕክምና፣በነርሲንግ በሌሎች ተዛማጅ
ወይም የማስተርስ ዲግሪ ወይም የጤና የሳይንስ መስኮች
የህክምና ዶክትሬት ዲግሪ
3.9.2 ሥራውን ለመጀመር የሚያስፈልግ የሥራ ልምድ
የሥራ ልምዱ ለማግኘት የሚጠይቀው ጊዜ ልምዱ የሚገኝበት የሥራ ዓይነት
6/4/2

የሥራ ዝርዝሩን ያዘጋጀው ባለሙያ ሥም ፊርማ ቀን

የሥራ ዝርዝሩን ያጸደቀው የሥራ መደቡ መጠሪያ ፊርማ ቀን


የኃላፊው ሥም

You might also like