You are on page 1of 29

የፌዴራል ፐብሊክ ሰርቪስ የለውጥ ሰራዊት ግንባታ የአደረጃጀትና

የአሰራር ሥርዓት ማኑዋል

የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ሚኒስቴር


መጋቢት 2009
አዲስ አበባ
ማውጫ

ክፍል አንድ

ጠቅላላ

1.1 መግቢያ 3

1.2 አጭር ርዕስ.............................................................................................................................................4

1.3 ትርጓሜ..................................................................................................................................................5

1.4 የማኑዋሉ ዓላማ......................................................................................................................................7

1.5 የማኑዋሉ አስፈላጊነት፣............................................................................................................................7

ክፍል ሁለት

የፐብሊክ ሰርቪስ የለውጥ ሰራዊት ግንባታ ምንነት፣ አስፈላጊነት፣ መርሆዎችና ባህሪያት

2.1 የፐብሊክ ሰርቪሱ የለውጥ ሰራዊት ግንባታ ምንነት፣....................................................................................9

2.2 የፐብሊክ ሰርቪሱ የለውጥ ሰራዊት ግንባታ አስፈላጊነትና ፋይዳው.........................................................................10

2.3 የፐብሊክ ሰርቪሱ የለውጥ ሰራዊት የሚመራባቸው መርሆዎች..............................................................................12

2.4 የፐብሊክ ሰርቪስ የለውጥ ሰራዊት መለያ ባህሪያት....................................................................................12

ክፍል ሶስት

የፐብሊክ ሰርቪሱ የለውጥ ሰራዊት ክንፎችና አካላት

3.1 የለውጥ ሰራዊቱ የመንግስት ክንፍና አካላት......................................................................................................13

3.2 የለውጥ ሰራዊቱ የህዝብ ክንፍና አካላት...........................................................................................................18

3.2.1. የብዙሀንና ሙያ ማህበራት አደረጃጀቶች፣................................................................................................18

3.2.2. አጋር የህዝብ ክንፍ አደረጃጀቶች...........................................................................................................20

3.3 የለውጥ ሰራዊቱ የህዝብ ክንፍ አካላት ልየታ፣...................................................................................................20

3.4 ሌሎች ተገልጋዮች.....................................................................................................................................23

ክፍል አራት

የፐብሊክ ሰርቪስ የለውጥ ሰራዊት አደረጃጀትና አሰራር


1
4.1 የመንግስት ክንፍ አካላት አደረጃጀትና አሰራር...................................................................................................24

4.2 የመንግስት እና የሕዝብ ክንፎች ትስስርና የግንኙነት አሰራር..................................................................................26

4.2.2.1 መድረኮቹን ዋና ተቋማትና ተጠሪ ተቋማት በቅንጅት ማካሄድ፣........................................................28

4.2.2.2 ተመጋጋቢ ተልዕኮ ያላቸው ተቋማት በቅንጅት ማካሄድ፣...........................................................................28

ክፍል አምስት

የፐብሊክ ሰርቪሱ የለውጥ ሰራዊት ግንባታ አቅጣጫዎች

5.1 ሶስቱን የአመራር ኡደቶች በተመጋጋቢነት የመፈጸም አቅጣጫን መከተል፣................................................................29

5.2 የለውጥ ሰራዊት ግንባታውን ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ አስተሳሰብን ይበልጥ በሚያጎለብት አግባብ መፈጸም፣..30

5.3 በተደራጀ አግባብ የመንቀሳቀስ አቅጣጫን መከተል፣...................................................................................31

5.4 የሠራዊቱን የማስፈፀም አቅም በሚገነባ መልኩ የመፈፀም አቅጣጫን መከተል፣...........................................31

5.5 ሁሉንም የለውጥ መሣሪያዎች አቀናጅቶ የመተግበር አቅጣጫን መከተል፣................................................................32

5.6 በስራ አፈጻጸም ውጤት ምዘና ላይ ተመስርቶ የማበረታታትና ተጠያቂ የማድረግ አቅጣጫን መከተል፣...........32

ክፍል ስድስት

የለውጥ ሰራዊት ግንባታ ክትትልና ድጋፍ ስርዓት

6.1. የጋራ ግምገማና ግብረመልስ ስርዓት..............................................................................................................33

6.2 የሪፖርትና ግብረመልስ ሥርዓት.............................................................................................................34

6.3 የሱፐርቪዥንና ግብረመልስ ስርዓት.........................................................................................................34

ክፍል አንድ
ጠቅላላ
1.1 መግቢያ

2
በአገራችን እየተገነባ ባለው ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መንግስት ቁልፍ ሚና አለው፡፡ በተመረጠ
ሁኔታ የገበያ ጉድለትን የመሙላትና የኪራይ ሰብሳቢነት ፖለቲካዊ ኢኮኖሚን በልማታዊ ፖለቲካዊ
ኢኮኖሚ የመተካት ተልዕኮ በአገራችን እየተገነባ ያለው ልማታዊና ዲሞክራሲያዊ መንግሥት ካሉት
ተልዕኮዎች ውስጥ በቀዳሚነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ መንግስት ይህንን ተልዕኮ በብቃትና በውጤታማነት
መወጣት የሚችለው ፐብሊክ ሰርቫንቱ፣ መላው ህዝብና የግሉ ሴክተር የመንግስትን የልማት፣ የመልካም
አስተዳደርና የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎችን በተሟላ መልኩ ተገንዝቦና የራሱ
አድርጎ ዕለት ተዕለት በብቃት ሲፈጽመው ብቻ ነው፡፡ ፐብሊክ ሰርቪሱ ይህንን ብቃት መጎናፀፍ
የሚችለው በአመለካከት፣ በዕውቀት፣ በክህሎት፣ በአደረጃጀትና በአሠራር አስፈላጊውን አቅርቦት
የተሰጠውን ተልዕኮ ለመፈጸም በሚመጥን ደረጃ ሲታጠቀው ነው፡፡

ከዚህ አኳያ ሲታይ የፐብሊክ ሰርቪስ የለውጥ ሠራዊት ግንባታ በመንግስት መዋቅሩ፣ በህዝቡና በግሉ
ሴክተር የሚታዩትን የአመለካከት፣ የዕውቀት፣ የክህሎትና የአቅርቦት ችግሮችን የሚፈታ እና መንግስት
በልማትና ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ወሳኝ የማስፈፀም ሚናውን በአግባቡ እንዲወጣ በማስቻል
የህዝብን ተጠቃሚነትና ተሳትፎ ለማረጋገጥ የሚያግዝ ቁልፍ መሳሪያ ነው፡፡

ይህንኑ ታሳቢ በማድረግ ባለፉት ዓመታት በፐብሊክ ሰርቪስ ተቋማትም የለውጥ ሰራዊት ግንባታውን
አቅጣጫ፣ አደረጃጀትና አሠራር የሚያመላክት ማኑዋል ተዘጋጅቶ ማሻሻያ እየተደረገበት ተግባራዊ
ሲደረግ ቆይቷል፡፡ በዚህም በየተቋማቱ የሚታየው የሰራዊት ግንባታ አፈጻጸም ከጊዜ ወደ ጊዜ
መሻሻሎች እያሳየ በመምጣት ላይ ይገኛል፡፡ ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ በሰራዊቱ አካላት የሚታዩት የኪራይ
ሰብሳቢነት አመለካከትና ተግባር የሆኑት ትምክህት፣ ጠባብነት፣ የሃይማኖት አክራርነት፣ ሙስና እና
የብቃት ማነስ ችግሮች የለውጥ ሰራዊት ግንባታ ሂደቱን በእጅጉ እየተፈታተኑት ይገኛሉ፡፡ ይህ ፈታኝ
ሁኔታ የልማታዊ ዴሞክራሲዊ መንግስትን ዓላማዎችና ፖሊሲዎች በብቃት መፈጸም የሚችል
ተአማኒነት ያለው፣ በግልጽነትና በተጠያቂነት መርሆዎች ላይ ተመስርቶ ሀገርን፣ ህዝብንና ዜጋን
የሚያገለግል ጠንካራና ውጤታማ ፐብሊክ ሰርቪስ የመፍጠር ተልዕኮን ለማሳካት የሚደረገው ጥረት
በሚፈለገው ፍጥነትና ውጤታማነት እንዳይፈጽም ማነቆ ሆኗል፡፡

በመሆኑም በየጊዜው ከምንደርስበት የዕድገት ደረጃ ጋር ተያይዘው የሚመጡና የሰራዊት ግንባታ ሂደቱን
የሚያስተጓጉሉ መሰል ችግሮችን ለመፍታት አዳዲስ አሰራሮችን እየጨመሩና ማኑዋሉን እያዳበሩ እንዲሁም
ወቅታዊነቱን እየጠበቁ መሄድ ተገቢና አስፈላጊ ነው፡፡ በዚሁ መሰረትም አስፈላጊ ማስተካከያዎችና
የማበልፀጊያ ሀሳቦችን በማካተት ይህ የፐብሊክ ስርቪስ የለውጥ ሰራዊት ግንባታ ማኑዋል ተሻሽሎ
ተዘጋጅቷል፡፡

3
ማኑዋሉ ስድስት ክፍሎችን ይዟል፡፡ የመጀመሪያው ክፍል አጠቃላይ ሁኔታን የሚያመለክት ሲሆን ክፍል
ሁለት ደግሞ የለውጥ ሰራዊት ግንባታ ምንነትን ፣ አስፈላጊነትን ፣ የሰራዊቱ መርሆዎችን እና ባህሪያትን
ያብራራል፡፡ ክፍል ሶስትና አራት እንደቅደም ተከተላቸው የለውጥ ሰራዊት ክንፎችና አካላት እና የለውጥ
ሰራዊት አደረጃጀትና አሰራርን በዝርዝር አቅርበዋል፡፡ ክፍል አምስት ደግሞ የለውጥ ሰራዊት ግንባታ
አቅጣጫን የያዘ ሲሆን የመጨረሻው ክፍል የለውጥ ሰራዊት ግንባታ የክትትልና ድጋፍ አግባብን በስፋት
ይዳስሳል፡፡

1.2 አጭር ርዕስ

ይህ ማኑዋል “በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የፌዴራል ፐብሊክ ሰርቪስ የለውጥ


ሰራዊት ግንባታ የአደረጃጀትና የአሰራር ሥርዓት ማኑዋል” ተብሎ ይጠራል፡፡

1.3 ትርጓሜ

የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ ማኑዋል፡-

1. “የለውጥ ሰራዊት” በልማታዊና ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ውስጥ ተለይቶ የተሰጠውን አገራዊ ተልዕኮ
ለማሳካት የሚያስችለውን የጋራ ዓላማና አሰራር እንዲሁም አመላካከት፣ ክህሎትና
ዕውቀትን በመያዝ በተደራጀና በተቀናጀ መንገድ ለለውጥ በቁርጠኝነት የተነሳ የመንግሥትና
የህዝብ የተደራጀ ኃይል ማለት ነው፡፡

2. “የለውጥ ሰራዊት ግንባታ” ማለት በሁሉም የፐብሊክ ሰርቪሱ የለውጥ ሰራዊት አካላት ዘንድ እንደየ አካሉ
የአመለካከት፣ የዕውቀት፣ የክህሎት፣ የተግባር፣ የአሰራርና የአደረጃጀት ተቀራራቢነትን
አዳብሮ አገራዊ ራዕይን ለማሳካት በጋራ የሚዘምት ኃይል መፍጠር ማለት ነው፡፡

3. “የለውጥ ሰራዊት ክንፎች” ማለት የልማት ዕቅድ ነዳፊውና አስፈጻሚው የመንግስትንና የዜጋውን
ጥቅም ለማስጠበቅ ህዝብን ወክሎ ከተቋማት ጋራ የሚሰራ የልማቱ ዋነኛ ባለቤትና ተጠቃሚ
የህዝብ አደረጃጀት ማለት ነው፡፡

4
4. “የመንግስት ክንፍ” ማለት በማንኛውም ደረጃ በተቋቋመ የመንግስት መስሪያ ቤት ውስጥ የሚገኙና የተቋሙ
የሠራዊት አካል ሆነው ከከፍተኛ አመራር እስከ ሰራተኞች እንደ አንድ አካል
የሚዋሃዱበትና የተቋም ተልዕኮን በጋራ ለማሳካት የሚንቀሳቀሱበት አደረጃጀት
ማለት ነው፡፡

5. “የመንግስት ክንፍ አካላት” ማለት በማንኛውም ደረጃ በተቋቋመ የመንግስት መስሪያ ቤት ውስጥ የሚገኙ
የተቋሙ የበላይ አመራሮችንና ፣መካከለኛ አመራርን ፣ የስራ ቡድን መሪንና መላው ፐብሊክ ሰርቫንትን
የሚያጠቃልል ነው፡፡

6. “የህዝብ ክንፍ” ማለት የዜጋውን ጥቅም ለማስጠበቅ ህዝብን ወክሎ ከተቋማት ጋራ የሚሰራ በተለያየ
መልኩ የተደራጀ የህዝብ አካል ማለት ነው፣

7. “የህዝብ ክንፍ አካላት” የሲቪክ ማህበራትን ማለትም የብዙሃንና የሙያ ማህበራት፣ ሌሎች የጋራ
ፍላጎቶቻቸውን፣ ሙያቸውንና የተሰማሩበትን ሥራ መሰረት አድርገው በማህበር የተደራጁ
የሕዝብ አደረጃጀቶችንና ልማታዊ የግል ሴክተሩን የሚያጠቃልል ነው፡፡

8. “ግንባር ቀደም” በመንግስት ተቋም አደረጃጀቶች ውስጥ ካሉ የሰራዊቱ አካላት ውስጥ በአመለካከቱ፣
በክህሎቱ፣ በዕውቀቱ፣ በሥነምግባሩ፣ በሥራ አፈፃፀሙ፣ በፀረ ኪራይ ሰብሳቢነት አቋሙና
ትግሉ፣ በተባባሪነቱ በሥራ ተነሳሽነቱ ወዘተ. በተግባር ወጤቱ ጎላ ብሎ በአርአያነት የሚታይ
የለውጥ ሰራዊት አባል ነው፡፡
9. “አንድ ለአምስት የለውጥ ቡድን አደረጃጀት” ማለት በስራ ሂደት ወይም ከዚያ በታች ባሉት የመንግስት
ተቋም አደረጃጀቶች ውስጥ የሚገኙ ከ 3-7 ፈጻሚዎች በተመሳሳይ ወይም በተዛማጅ
ተግባራት ዙሪያ የሚደራጁበትና በግንባር ቀደም ወይም በአንድ የተሻለ ፈጻሚ አስተባባሪነት
የሚመራ የጋራ ተልዕኮ ያለው አደረጃጀት ነው፡፡

10. “የተቋም የበላይ አመራር” የመንግስት ተቋማትን የሚመሩ ሚኒስትሮችን፣


ሚኒስትር ዴኤታዎችን፣ የጽ/ቤት ኃላፊዎችን፣ ኮሚሸነሮችን፣ ም/ኮሚሸነሮችን ዋና
ዳሬክተሮችን እና ምክትሎቻቸውን እንዲሁም በእነዚህ ደረጃ ያሉ ተሿሚዎችን
ያጠቃልላል፡፡

5
11. “የተቋም መካከለኛ አመራር” ማለት በመንግስት ተቋማት የስልጣን ተዋረድ መሠረት ከበላይ አመራር ቀጥሎ
ባለው አደረጃጀት ውስጥ በሙያው አመራር የሚሰጥ በሜሪት የተመደበ ሙያተኛ
አመራር ነው፣

12. “የተቋም የቡድን መሪ በመንግስት ተቋማት አደረጃጀት የስልጣን ተዋረድ ከስራ ሂደት ቀጥሎ ያለውን
አደረጃጀት የሚመራ በሜሪት የተመደበ ታችኛው አመራር ነው፡፡

13. “መላ ፐብሊክ ሰርቫንት” ማለት በመንግስት ተቋማት በሙያው ህዝብን ለማገልገል የተቀጠረውን መላ ሰራተኛ
ያጠቃልላል::

14. “ሌሎች ተገልጋዮች” የሚባሉት የህዝብ ክንፍ ያልሆኑ ነገር ግን ከመንግስት ተቋማት አገልግሎት
የሚያገኙ ግለሰቦች፣ የግል እና የመንግስት ተቋማት ናቸው፡፡

1.4 የማኑዋሉ ዓላማ

የዚህ ማኑዋል ዓላማ የፐብሊክ ስርቪስ የለውጥ ሰራዊት ግንባታ ዝርዝር የተግባር አፈጻጸም ሂደትን
በሚመለከት ግልጽነትን በመፍጠር ወጥነት ያለው የለውጥ ሰራዊት አሰራር፣ አደረጃጀትና ግንባታ
በሁሉም የፐብሊክ ስርቪስ ተቋማት ዕውን ማድረግ ነው፡፡

1.5 የማኑዋሉ አስፈላጊነት፣

ባለፉት ዓመታት የፐብሊክ ሰርቪሱን ተልዕኮና ራዕይ ለማሳካትና የመንግስት ፖሊሲዎች፣


ስትራቴጂዎችና ዕቅዶች ለማስፈጸም ዋነኛ መሳሪያ በፐብሊክ ሰርቪሱ የለውጥ ሠራዊት ማደራጀትና
መገንባት መሆኑን በማስቀመጥ የተለያዩ ተግባራት ተከናውነዋል፡፡ በፐብሊክ ሰርቪሱ ሁለቱንም የለውጥ
ሠራዊት አቅሞች በማጠናከርና በማቀናጀት የተቋማት ተልዕኮዎችን ለማሳካት ጥረቶች ተደርገዋል፡፡
የሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ከለውጥ ሰራዊቱ ጋር ውይይት ተደርጎ የጋራ መግባባት
ከተፈጠረ በኋላ ወደ ተግባር ተገብቷል፡፡ ዕቅዱን ለማሳካት በተደረገው ርብርብም በለውጥ ሰራዊቱ
ውስጥ የይቻላል መንፈስ መፍጠር የተቻለ ሲሆን በተወሰኑ መስኮች የለውጥ ሰራዊቱን በተደራጀ መልክ
በማንቀሳቀስ ውጤታማ ስራ መታየት ጀምሯል፡፡

ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ አሁንም ፐብሊክ ሰርቪሱ የልማታዊ ዲሞክራሲያዊ መንግስትን ተልዕኮዎች


በብቃት መወጣት የሚያስችለውን ስብዕና አልተላበሰም፡፡ የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና ተግባር ዋነኛ

6
ምንጭ ሆኑት ጠባብነት፣ ትምክህት፣ የሃይማኖት አክራርነትና ሙስና ፐብሊክ ሰርቪሱ ተልዕኮውን
በብቃት እንዳይወጣ ማነቆ ከሆኑ ችግሮች መካከል ዋንኞቹ ሲሆኑ የክህሎት፣ የአቅርቦት፣ የአደረጃጀትና
የአሰራር ክፍተቶችን የየራሳቸው አሉታዊ ድርሻ እንዳላቸው መረዳት ይቻላል፡፡ በእነዚህና እነዚህን
በመሳሰሉት የፐብሊክ ሰርቪሱ ማነቆዎች ምክንያት በኢኮኖሚ ልማት፣ በመንግሥታዊ አገልግሎት
አሰጣጥና በመሰረተ-ልማት አቅርቦት ዙሪያ ግልፅነትንና ተጠያቂነትን ከማስፈንና ውጤታማ የህዝብ
ተሳትፎን ከማረጋጋጥ አንጻር የሚፈለገው ውጤት አልተገኘም፡፡

ይህም ባለፈው ዓመት በአገራችን በተለያዩ አካባቢዎች ለተከሰተው ፈርጀ-ብዙ የህዝብ ቅሬታ አንዱና
ዋነኛ ምክንያት ሆኗል፡፡ ጠንካራ የመፈፀም አቅም ያለውና በሥነ-ምግባሩ የተመሰገነ ፐብሊክ ሰርቪስ
ለመፍጠር በ 2012 ያስቀመጥነውን ራዕይ ለማሳካት በፐብሊክ ሰርቪሱ የለውጥ ሰራዊት ክንፎች
በተጨባጭ የሚታዩትን ማነቆዎች በአግባቡ ለይቶ፣ ፈትሾና ተገቢውን መፍትሔ አስቀምጦ ስራ ላይ
ማዋል ያስፈልጋል፡፡ ይህ ሊሳካ የሚችለው ደግሞ በሁሉም የመንግስት ተቋማት የተግባርና የአመለካከት
አንድነትን በመፍጠር ነው፡፡

በመሆኑም የፐብሊክ ሰርቪሱ የለውጥ ሰራዊት ግንባታ ሂደት በሁሉም የፌዴራል የመንግስት ተቋማት
ወጥ በሆነ የአደረጃጀትና የአሰራር ማዕቀፍ እንዲመራ በማድረግና በሰራዊቱ የሚታዩትን ማነቆዎች
በተደራጀ አግባብ በመፍታት የልማታዊ ዲሞክራሲያዊ መንግስት ተልዕኮዎችን በውጤታማነት
ለመፈጸም እንዲያግዝ ይህንን ማኑዋል ማዘጋጀት አስፈልጓል፡፡

ክፍል ሁለት

የፐብሊክ ሰርቪስ የለውጥ ሰራዊት ግንባታ ምንነት፣ አስፈላጊነት፣ መርሆዎችና ባህሪያት

2.1 የፐብሊክ ሰርቪሱ የለውጥ ሰራዊት ግንባታ ምንነት፣

የፐብሊክ ሰርቪሱ የለውጥ ሰራዊት በተለያዩ ክንፎችና እርከኖች የተዋቀሩ የመንግስትና የህዝብ አካላትን
የመገንባት ጉዳይ ነው፡፡ ዋነኛ ይዘቱም በአመለካከት፣ በአሰራርና አደረጃጀት እንዲሁም በክህሎትና
በዕውቀት ደረጃ ተቀራራቢነትና ከሞላ ጎደል ወጥነት ያለው የለውጥ ሰራዊት ኃይል መፍጠርን
7
የሚመለከት ነው፡፡ የአመለካከት መዘበራረቅ ከኖረ የለውጥ ሰራዊት ተፈጥሯል ሊባል አይችልም፡፡
የአሰራርና የአደረጃጀት መዝረክረክ ባለበት ሁኔታም የሀሳብና የተግባር አንድነቱ የተረጋገጠ የለውጥ
ሰራዊት ኃይል ይኖራል ተብሎ አይታሰብም፡፡ በክህሎትና በዕውቀት ደረጃም ተቀራራቢነት ከሌለ ፈጻሚ
አካላቱ አሁንም በተራራቀ የውጤታማነት ደረጃ ላይ የሚገኙበት ሁኔታ መፈጠሩ አይቀርም፡፡

የልማታዊ ዴሞክራሲያዊ አመለካከት ልዕልናን ያዳበረ፣ በአሰራር፣ በአደረጃጀት፣ በክህሎቱና በዕውቀቱ


ተቀራራቢና ውጤታማ የሆነ የለውጥ ሰራዊት የመገንባት ጉዳይ ሲነሳ አብሮ መታወስ ያለበት ሌላው
ጉዳይ የለውጥ ሰራዊቱ በአንድ ተግባርና በአንድ ንዑስ ምዕራፍ ወይም አብይ ምዕራፍ ተግባራት ብቻ
የማይገነባ መሆኑ ነው፡፡ አንድ መደበኛ ሰራዊት በአንድ ታክቲካዊ ግጥሚያ ብቻ እንደማይገነባ ሁሉ
የለውጥ ሰራዊት ግንባታም በተለያዩ ወቅቶች የሚፈጸሙ ተከታታይነት ያላቸው ተግባራትን በታቀደ
አኳኋን በማዘጋጀትና በመፈጸም ብቻ ይፈጠራል፡፡ ምንም እንኳን የመጀመሪያው ተግባር በከፍተኛ
ውጤታማነት እስከተሰራ ድረስ የለውጥ ሰራዊት ለመፍጠር የሚያስችል መሰረት መጣል ቢቻልም አንድና
ያለቀለት የሰራዊት መገንቢያ ተግባር እንደማይሆን ግን መገንዘብ ያስፈልጋል፡፡ የለውጥ ሰራዊቱ በአንድ
ወይም በጥቂት ተግባራት አፈጻጸም ሂደት ተፈጥሮ ግንባታው ግን በተከታታይ ተግባራት እየጎለበተና
ቀጣይነቱ እየተረጋገጠ የሚሄድ ነው፡፡

ስለሆነም በፐብሊክ ሰርቪሱ የለውጥ ሰራዊት መፈጠር ሲጀምርም ሆነ በቀጣይነት ሲገነባ በርግጥም
የለውጥ ሰራዊት የሚያሰኙትን ጉዳዮች በውል መለየት ያስፈልጋል፡፡ በዚህ ረገድ ወሳኙ የአመለካከትና
የተግባር አንድነትን የመፍጠር ጉዳይ ነው፡፡ የለውጥ ሰራዊት ከሀሳብና ከተግባር አንድነት ውጭ ፈጽሞ
ሊኖር አይችልም፡፡ በአመለካከት ደረጃ ኪራይ ሰብሳቢነትና ልማታዊነት በተደበላለቁበት ሁኔታ የለውጥ
ሰራዊት ብሎ ነገር ሊኖር አይችልም፡፡ ስለሆነም በእያንዳንዱ መሰረታዊ ጉዳይ ላይ ሁሉም ፈጻሚ ኃይሎች
አንድ ዓይነት የጋራ አስተሳሰብ መያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ኪራይ ሰብሳቢነት በየወቅቱ መልኩን እያቀያየረ
የሚያመጣቸውን የተሳሳቱ አስተሳሰቦች መጸየፍ፣ አምርሮ መታገልና ማጋለጥም ይጠበቅባቸዋል፡፡

በተመሳሳይ ሁኔታ የለውጥ ሰራዊት የሚኖረው በተመሳሳይ የተግባር ስምሪት ነው፡፡ አንዱ ቁልፍና አበይት
ተግባራትን ለመፈፀም ሲረባረብ፣ ሌላው በሚያደናቅፍበት ወይም ግዴለሽ በሆነበት ሁኔታ የለውጥ
ሰራዊት ሊኖር አይችልም፡፡ ስለሆነም በፐብሊክ ሰርቪሱ የለውጥ ሰራዊት እንዲገነባ ሁሉም የሰራዊቱ
አካላት በወቅቱ በተያዙት ቁልፍና አበይት ተግባራት ላይ ድርሻ ድርሻቸውን ይዘው በውጤታማነት
የሚረባረቡበት ሁኔታ ሲኖር ነው፡፡ በአጠቃላይ በፐብሊክ ሰርቪሱ የለውጥ ሰራዊት የመገንባት ጉዳይ
በሁሉም ፈጻሚዎች ዘንድ የአስተሳሰብ፣ የተግባር፣ የአሰራር፣ የአደረጃጀትና እንደየአካሉ የክህሎት
ተቀራራቢነትን አዳብሮ በድህነት ላይ በጋራ የሚዘምት ኃይል የመፍጠር ጉዳይ ነው፡፡
8
2.2 የፐብሊክ ሰርቪሱ የለውጥ ሰራዊት ግንባታ አስፈላጊነትና ፋይዳው

የአገራችንን ፐብሊክ ሰርቪስ ብቃትና ውጤታማነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ የተለያዩ የለውጥ


መሳሪያዎች ሲተገበሩ ቆይተዋል፡፡ እነዚህ የለውጥ መሳሪያዎች ተቋማዊ ለውጥን በማረጋገጥና ተልዕኮን
በውጤታማነት በመፈጸም የህዝብ እርካታን ለማስመዝገብ ያላቸው ጠቀሜታ ከፍተኛ ነው፡፡ በመሆኑም
የተቋማዊ ለውጥ ትግበራውን የበለጠ ለማጎልበት እነዚህን የለውጥ መሳሪያዎች ተጠቅሞ ውጤት
እያስመዘገበ፣ በታዩ ውጤቶችና የወደፊት ተስፋ ህዝቡን እየነሸጠና እየኮረኮረ ወደ ጸረ ድህነት ትግል
የሚያስገባና በገባበትም ትግል ጸንቶ እንዲቀጥል የሚያስችል ትግልን አጀንዳ አድርጎ የሚጓዝ የፐብሊክ
ሰርቪስ የለውጥ ሰራዊት ማደራጀትና ወደ ስራ ማስገባት ግድ ይላል፡፡ በዚህ ረገድ በሌሎች ሴክተሮች
የልማት ሰራዊትን በማደራጀት በተገኙ መልካም ውጤቶች መነሻነት የመንግስት ፖሊሲዎችና
ስትራቴጂዎች አስፈጻሚና ዋነኛ መሳሪያ በሆነው በፐብሊክ ስርቪሱ ውስጥም ተግባራዊ በማድረግ
የተጀማመሩትን ተስፋ ሰጪ ውጤቶች እያሰፉ መሄድ ተገቢ ነው፡፡ ከዚህ እውነታ በመነሳት የተጀመረውን
የለውጥ ስራ እያጠናከሩ ለመሄድ መንግስት እና ዜጋው በመተባበር፣ በመቀናጀትና ለውጡን መሰረት
በማድረግ የልማት፣ የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታና የመልካም አስተዳደር እቅዶችን በቅልጥፍናና
በውጤታማነት ለመፈጸምና የህዝብን ተጠቃሚነትና ተሳትፎ ለማረጋገጥ የሚያስችል የፐብሊክ ስርቪስ
የለውጥ ሰራዊት መገንባት አስፈላጊ ሆኗል፡፡

የለውጥ ሰራዊት ገንብቶ መንቀሳቀስ ከሚኖረው ፋይዳ ውስጥ በተቋማዊ ለውጡ አማካኝነት የተፈጠረውን
አደረጃጀትና አሰራር በመጠቀም ውጤት እንዲያመጣ የሚፈለገው የሰው ኃይል ድህነት ዋነኛ የጋራ ጠላት እንደሆነና
በጋራ ሊዘመትበት እንደሚገባ ተረድቶ በአመለካከቱ አዎንታዊ ለውጥ በማምጣት ፈጣን ልማታችን ቀጣይነት
እንዲኖረው እንደሰራዊት በመዝመት ተኪ የለሽ ድርሻውን እንዲወጣ ማድረግ አንዱና ዋነኛ ነው፡፡ መልካም አስተዳደርን
ለማስፈን በሚደረገው ጥረት ውስጥ ህዝቡን ወይም ተገልጋዩን ከዕቅድ ዝግጅት እስከ አፈጻጸም ባለው ሂደት ውስጥ
ድርሻውን በባለቤትነት እንዲወጣ በማነቃነቅና በማሳተፍ ተጠቃሚነቱን ማረጋገጥ የሰራዊት ግንባታ ሌላው ፋይዳ ነው፡፡

በተመሳሳይ ሁኔታ በፐብሊክ ሰርቪሱ የለውጥ ሰራዊትን መገንባት የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና ተግባር መንስዔ
የሆኑና ከዕርሱ የሚመነጩ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በማዳከም ብሎም በማክሰም በምትኩ የልማታዊ ፖለቲካዊ
ኢኮኖሚ አስተሳሰብ እንዲጎለብት የማድረግ ከፍተኛ ጠቀሜታ አለው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በፐብሊክ ሰርቪሱ የለውጥ
ሰራዊት መገንባት በየደረጃው በሚገኙት የሰራዊት ክንፎችና አካላት መካከል የአመለካከትና የተግባር አንድነት
እንዲፈጠር ለማድረግ፣ የቡድን መንፈስን ለማዳበር፣ የሰራዊቱን አቅም ለማመጣጠን፣ ምርጥ
ተሞክሮዎችን በፍጥነት ለማስፋትና የፐብሊክ ሰርቪሱን የእርስ በርስ መማማር ቀጣይነት ባለው ሁኔታ
ለመገንባት ተኪ የሌለው ሚና ይጫወታል፡፡

9
2.3 የፐብሊክ ሰርቪሱ የለውጥ ሰራዊት የሚመራባቸው መርሆዎች

የፐብሊክ ሰርቪሱ የለውጥ ሰራዊት ተቋማዊም ሆነ አገራዊ ተልኮውን በሰራዊት የንቅናቄ ማዕቀፍ ውስጥ
በተሟላ መልኩ ለማሳካት ቀደም ሲል ተቀርጸው ስራ ላይ ያሉ የፐብሊክ ሰርቪሱ የስነምግባር እና
ከሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ተግባራዊ እየተደረጉ ያሉ የመልካም አስተዳደር መርሆዎች እንደተጠበቁ
ሆነው ሰራዊቱ ሊመራባቸው የሚገቡ መሰረታዊ መርሆዎች፡-
ሀ. የሕግ የበላይነት
ለ. ቀልጣፋነትና ውጤታማነት
ሐ. ለጋራ ስኬት በጋራ መረባረብ
መ. ተሳትፏአዊነት
ሠ. የጋራ መግባባት
ረ. ግልጽነት
ሰ. ተጠያቂነት
ሸ. የህዝብን ጥቅም ማስቀደም
ቀ. ሴኩላሪዝም
በ. በሥራ አፈጻጸም ውጤት ብቻ መመዘን ናቸው፡፡

2.4 የፐብሊክ ሰርቪስ የለውጥ ሰራዊት መለያ ባህሪያት


ሀ. የራሱ የሆነ የጋራ ራዕይና ተልዕኮ ያለው፣ ዕቅድን በጋራ የሚያቅድ፣
ለ. የየዕለት ተግባሩን ከስትራቴጂያዊ ዕቅድ ጋር በማስተሳሰር የሚተገብርና
የሚገመግም፣
ሐ. ጠባቂነትን ያስወገደ እና በራስ ተነሳሽነት የሚሰራ፣
መ. ለለውጥ ሰራዊት ግንባታ መርሆዎች ተገዥ የሆነ፣
ሠ. አፈፃፀምን መሰረት ያደረገ ምዘናን ተግባራዊ የሚያደርግ፣
ረ. ለተገልጋይ ተገቢውን ክብር የሚሰጥ፣ ቀልጣፋና ፍትሃዊ ውሳኔ የሚሰጥ፣
ሰ. የኪራይ ሰብሳቢነትን አመለካከትና ተግባር በስራው ላይ የሚጠላና የሚታገል፣
ሸ. ያለውን ዕውቀት፣ ክህሎትና መልካም ልምድ ለሌሎቹ የሚያካፍል የሚሏቸው
የሠራዊቱ መለያ ባህርያት ናቸው፡፡

ክፍል ሶስት

የፐብሊክ ሰርቪሱ የለውጥ ሰራዊት ክንፎችና አካላት

10
የፐብሊክ ሰርቪሱ የለውጥ ሰራዊት ሁለት ክንፎች አሉት፡፡ እነዚህም የመንግስት ክንፍና የህዝብ ክንፍ ናቸው፡፡
እያንዳንዱ ክንፍ የተለያዩ አካላት አሉት፡፡ የመንግስት ክንፍ በየደረጃው የተዋቀሩ የመንግስት አደረጃጀቶችን
ያቀፈ ሲሆን የህዝብ ክንፉ ደግሞ የተለያዩ የህዝብ አደረጃጀቶችንና ዜጋውን የሚመለከት ነው፡፡ በዚሁ
መሰረትም የፐብሊክ ሰርቪሱ የለውጥ ሰራዊት ክንፎችና የእያንዳንዱ ክንፍ አካላት ዝርዝር የሚከተለው ነው፡፡

3.1 የለውጥ ሰራዊቱ የመንግሥት ክንፍና አካላት

በማንኛውም ደረጃ በተቋቋመ የመንግስት መስሪያ ቤት ውስጥ ያለው የተቋሙ አመራርና መላው ሰራተኛ አንድ
የሰራዊት ክንፍ ሆኖ እንደ ተቋሙ ተጨባጭ ሁኔታ አምስት እርከን አሊያም ከስራ ሂደት በታች ቡድን ከሌለ በአራት
እርከን ይደራጃል፡፡ ስለዚህ የመንግስት መዋቅር አንድ የሰራዊቱ ክንፍ ሆኖ የአምስት ወይም የአራት እርከኖች
ውህድ ሆኖ ይደራጃል፡፡

እነዚህም አካላት፡-

ሀ. የተቋሙ የበላይ አመራር


ለ. መካከለኛ አመራር፣
ሐ. የስራ ቡድን
መ. ግንባር ቀደም1 እና
ሠ. መላው ፐብሊክ ሰርቫንት
ሲሆኑ አካላቱም የሚከተሉት ተልዕኮዎች ይኖራቸዋል፡፡

3.1.1. የበላይ አመራር

የተቋም የበላይ አመራር ዋና ተልዕኮ ፐብሊክ ሰርቫንቱን በልማታዊ እና ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብ በመገንባት
ተልኳቸውን በብቃት እንዲወጡ ማስቻል ሆኖ የሚከተሉትን ተግባራት ይፈጽማል፡፡

ሀ. የተቋሙ መካከለኛ አመራርና ፈጻሚ በልማታዊ መንግስት ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ዙሪያ በቂ ግንዛቤ
እንዲፈጥር ማድረግ፣
ለ. የተቋሙን ዕቅድ በሰራዊቱ ሙሉ ተሳትፎ ጥራቱን ጠብቆ በማዘጋጀት ፈጻሚን ለተልዕኮው ዝግጁ

1
ግንባር ቀደም የመንግስት መዋቅር አደረጃጀት አካል ባይሆንም ለለውጥ ሰራዊት ግንባታ ካለው ሚና አንጻር የተቀመጠ ነው፡፡
11
ማድረግ፣
ሐ. የለውጥ ሠራዊቱን የአመለካከት፣ የክህሎት፣ የዕውቀት፣ የአቅርቦት፣ የአደረጃጀትና የአሰራር
ክፍተቶችን በመለየት የአቅም ግንባታ ስራዎችን ማቀድና አፈጻጸማቸውን መምራት፣
መ. በየደረጃው ያለውን መካከለኛ አመራርና ፐብሊክ ሰርቫንቱን ማብቃት፣ መገንባት እንዲሁም ስምሪት
መስጠት፡፡
ሠ. በለውጥ ሰራዊት ምንነት፣ አስፈላጊነት፣ አደረጃጀትና ግንባታ ላይ ለተቋሙ ሠራተኞች በቀጣይነት ግንዛቤ
የመፍጠርና የማሳደግ ስራ መስራት፣
ረ. የለውጥ አመራር ዑደትን ተከትሎ ተቋማዊ ለውጡ ውጤታማና ዘላቂ እንዲሆን ማስቻል፣
ሰ. ከለውጥ ሠራዊቱ ጋር በቋሚ የውይይት መድረክ ማለትም በየአስራ አምስት ቀን ከመካከለኛ አመራሩ እና
በየወሩ ከመላው ሠራተኛ ጋር በመገናኘት አጠቃላይ የለውጡን እንቅስቃሴ መገምገምና አቅጣጫ
ማስቀመጥ፣
ሸ. ከተቋሙ የህዝብ ክንፍ ጋር በየሶስት ወሩ በመገናኘት የለውጥና የመልካም አስተዳደር እቅዶችን
መገምገም፣ ክፍተቶችን መለየትና የመፍትሄ አቅጣጫ ማስቀመጥ፣
ቀ. ወቅታዊ የለውጥና መልካም አስተዳደር አፈጻጸም ሪፖርት በማዘጋጀት ለፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት
ልማት ሚኒስቴር ማቅረብ፣
በ. ምርጥ ልምድ መለየት፣ መቀመር፣ ማቀድና መተግበር፣

3.1.2. የተቋም መካከለኛ አመራር

የዚህ አካል ዋና ዋና ተልዕኮዎች የሚከተሉት ይሆናሉ፡፡

ሀ. ከተቋም እቅድ የተቀዳ ጥራት ያለው ዝርዝር እቅድ በማዘጋጀት እና ለፈጻሚዎች በዝርዝር በማስጨበጥ
በአሳታፊነትና በባለቤትነት ስሜት መስራትና ማሰራት፣
ለ. በስሩ የተደራጀው የለውጥ ሠራዊት ግንባር ቀደም ሚናውን እንዳይወጣ እንቅፋት የሚሆኑ የአመለካከት፣
የክህሎት፣ የዕውቀት እና የአቅርቦት እጥረቶችን እለት በእለት እየተከታተለ መፍታት፣
ሐ. ለሚመራው አካላት በሁለንተናዊ የሥራ እንቅስቃሴው እና መልካም ስብዕናው አብነታዊ ሆኖ መገኘትና
ራሱን ከአድርባይነትና ከጥገኛ አስተሳሰብ፣ ፍላጎትና ተግባር አጽድቶ ሌሎችም አርአያነቱን እንዲከተሉ
መንቀሳቀስ፣
መ. በሚመራው የሥራ ክፍል የሥነ ምግባር ችግሮችን፣ ድክመቶችንና
ጉድለቶችን ፈጥኖ በመለየትና በማስተካከል የመሪነት ሚናውን በቁርጠኝነት መወጣት፣
ሠ. በሚመራው የሥራ ክፍል ያሉ ፈጻሚዎች የተቋሙን ብሎም ሀገራዊውን ራዕይ ለማሳካት የሚያስችል
ውጤታማ አፈጻጸም እንዲኖራቸው ማስተባበር፣ ማማከር፣ ማሰልጠን፣ ማብቃትና የመገምገም ባህልን
12
ማሳደግ፣
ረ. ከዜጎች/ከተገልጋዮች የሚነሱ አቤቱታዎችና ቅሬታዎችን ምንጭና አዝማሚያ እያጠና መፍትሄ መስጠት፣
ሰ. በለውጥ ሰራዊቱ የግንኙነት መርሃ ግብር መሰረት በሰራዊት አግባብ የተገመገመ የአፈጻጸም ሪፖርት
ማቅረብ፤ የሚሰጠውን ግብረ-መልስም ወስዶ ሥራ ላይ ማዋል፣
ሸ. ሰራዊቱ በየዕለቱ የሚወያይባቸውን አጀንዳዎች በየጊዜው እየቀረጸ በመስጠት ተግባራዊነታቸውን
መከታተል፣
ቀ. የአንድ ለአምስት የለውጥ ሰራዊት ቡድንን በስራ አፈጻጸም ውጤታቸው መሰረት በጋራ መመዘን፣
በአፈጻጸማቸው ወደፊት የወጡትን ማበረታታት፣ የደከሙትን የተሻለ አፈጻጸም ካላቸው እንዲማሩ
ማድረግ፣
በ. ግንባር ቀደሞች እንዲፈጠሩ መከታተል፣ መደገፍ፣ ማብቃትና መለየት፣
ተ. በከፍተኛ አመራሩ የሚቀመጡትን አቅጣጫዎች በሥሩ ለሚገኙ አደረጃጀቶችና ሰራተኞች በወቅቱ
ማሳወቅ፣
ቸ. ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ መስጠት፣ በእሱ ደረጃ በቂ ምላሽ ያላገኙ አ. ጥያቄዎችን ደግሞ ለበላይ
አመራሩ በወቅቱ ማሳወቅና መፍትሄ ማስገኘት፣
ምርጥ ልምድ መለየት፣ መቀመር፣ ማቀድና ማስፋት፣

3.1.3. የስራ ቡድን መሪ

በመንግስት ተቋማት አደረጃጀት ከመካከለኛ አመራሩ ቀጥሎ ባለው እርከን በአንዳንድ ተቋማት የስራ
ቡድን የሚደራጅበት ሁኔታ አለ፡፡ የስራ ቡድን መሪው ከሚኖረው ተግባራት ውስጥ ዋና ዋናዎቹ
የሚከተሉት ናቸው፡፡

ሀ. በቡድኑ ስር ያሉ የሰራዊቱ አባላት በአመለካከት፣ በዕውቀት፣ በክህሎት፣ በአቅርቦት የሚታይባቸውን


ማነቆዎች ለይቶ ማወቅና መፍታት
ለ. አፈጻጸማቸውን በየዕለቱ መከታተልና በየሳምንቱ በቋሚ ግንኙነት ፕሮግራም በተልዕኳቸው ዙሪያ
ያላቸውን አፈጻጻም መገምገምና ክፍተቶች ሳይሰፉ የሚደፈኑበትን አግባብ በመቀየስ ስራ ላይ ማዋል፣
ሐ. ግንባር ቀደሞችን ለማብዛት ጠንካራ ክትትልና ድጋፍ መስጠት፣
መ. ከዜጎች/ከተገልጋዮች የሚነሱ አቤቱታዎችና ቅሬታዎችን ምንጭና አዝማሚያ እያጠና መፍትሄ መስጠት፣
ሠ. የሰራዊት መንፈስ እንዲጎለብት ትኩረት ሰጥቶ መስራት፣
ረ. አስፈላጊውን መረጃ መያዝና የአፈጻፀም ሪፖርት ለስራ ሂደቱ መሪ በየሳምንቱ ማቅረብ፣
ሰ. ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ መስጠት፣ በእሱ ደረጃ በቂ ምላሽ ያላገኙ ጥያቄዎችን ደግሞ ለመካከለኛ አመራሩ

13
በወቅቱ ማሳወቅና መፍትሄ ማስገኘት፣

3.1.4 ግንባር ቀደም


ግንባር ቀደም ከለውጥ ሰራዊት አባላት መካከል ሁሉንም የለውጥ መሳሪያዎች አስተሳስሮ
ከመፈጸምና አርአያ ሆኖ ከመገኘት አንጻር የሚመረጥ ሲሆን የሚከተሉትን ዋና ዋና ተግባራት ያከናውናል፡፡

ሀ. የራሱን ተልዕኮ በብቃት መፈፀምና የተቀመጠውን ግብ ማሳካት፣


ለ. ሌሎች ሰራተኞችን ራሱ በደረሰበት የአመለካከት እና የአፈጻፀም ደረጃ እንዲደርሱ ማገዝ፣
ሐ. ልምዱን በማካፈል ሌሎች በአመለካከት፣ በክህሎትና በዕውቀት ያለባቸውን ክፍተት ለመሙላት ትኩረት
ሰጥቶ መስራት
መ. ለላቀ ውጤት የሚያበቁ የራስ አቅም ማጎልበቻ ተግባራትን ማከናወን፣
ሠ. ለውጥ የሚያመጡ አዳዲስ አሰራሮችን ማመንጨትና ለሌሎችም ምሳሌ መሆን፣
ረ. ከአቻ ግንባር ቀደሞች ጋር በመመካከር የተቋሙ ተልዕኮ በቅልጥፍናና በውጤታማነት ስለሚሳካበት ሁኔታ
ለአመራሩ ሀሳብ ማቅረብ፣
ሰ. በመርህ ላይ ተመስርቶ በመተባበርና በመተጋገዝ መስራት፣
ሸ. መልካም ስነ-ምግባር ያለው፣ ታታሪ እና ስራ ወዳድ መሆን፣

3.1.5 መላው ፐብሊክ ሰርቫንት


መላ ፐብሊክ ሰርቫንት የሚባለው ከስራ ሂደት መሪዎች እና ቡድን መሪዎች ቀጥሎ በመንግስት ተቋማት
በሙያው ህዝብን ለማገልገል የተቀጠረውን መላ ሰራተኛ የሚያጠቃልል ነው:: መላው ፐብሊክ ሰርቫንት
የሚደራጀው በዋነኛነት የስራ ሂደትን መሰረት አድርጎ ይሆናል፡፡ የስራ ሂደቱ ባለው የሰራተኛ ብዛት ላይ በመመስረት
በአንድ የስራ ሂደት ውስጥ አንድ የአንድ ለአምስት ቡድን ወይም ከዚያ በላይ ይደራጃል፡፡ እያንዳንዱ ሰራተኛ ቀጥሎ
ያሉትን ዋና ዋና ተግባራትን ያከናውናል፡፡

ሀ. ፈጻሚው እንደ ቡድን የዕለትና የሳምንት እቅድ በትክክል ለተቋሙ ተልዕኮ ማሳካት ያለውን ፋይዳ
በማረጋገጥ አቅዶ ይፈጽማል፣
ለ. ዜጋን/ተገልጋይን በታማኝነትና በቅንነት ማገልገል ፣
ሐ. የጋራ ተልዕኮን ለማሳካት የመተጋገዝና የእርስ በርስ መማማሪያ መድረኮችን ከዕለት ተዕለት ስራ ጋር አዋህዶ
መፈጸም፣
መ. አገልግሎቶችን በዜጎች ቻርተር በተቀመጠው ስታንዳርድ መሰረት መስጠት፣
ሠ. በዕለት ተዕለት የተግባር አፈጻጸም ከሌሎች የሰራዊቱ አባላት ጋር የምርጥ ተመክሮ ልውውጥ ማድረግ፣
ረ. ከዜጎች/ተገልጋይ የሚነሱ አቤቱታዎችና ቅሬታዎች ላይ በወቅቱ የእርምት እርምጃ መውሰድና

14
ለሚመለከተው ማሳወቅ፡፡
ሰ. የሚቀርቡ ቅሬታዎችን በጊዜ፣ በጭብጥ፣ በአቅራቢውና በተቋሙ ለይቶና መረጃ ይዞ ለስራ ሂደት መሪው
ወይም ለቡድን መሪው ማቅረብ፣
ሸ. የውጤት ተኮር ስርዓትን ተከትሎ የወረደለትን ተግባራት በየቀኑ፣ በየሳምንቱና በየወሩ ከፋፍሎ በጥራት፣
በመጠንና በጊዜ በማቀድ ስለአፈፃፀሙ በየሳምንቱ ለሂደት/ለቡድን መሪው ሪፖርት ማቅረብ ፣

3.2 የለውጥ ሰራዊቱ የህዝብ ክንፍና አካላት

የለውጥ ሰራዊቱ የህዝብ ክንፍ የለውጥ ሰራዊቱ ሁለተኛ ክንፍና ዋነኛ የለውጡ ባለቤትና ተጠቃሚም ነው፡፡ ህዝቡ
በተደራጀ መልኩ የሰራዊቱ አካል መሆን እንዳለበት ይታወቃል፡፡ በመሆኑም የህዝብ የተደራጁ አካላት በተለይም
የብዙሃንና የሙያ ማህበራት የአባላቶቻቸውን መብትና ጥቅም ለማስጠበቅና የልማትና የመልካም አስተዳደር
ፍላጎቶቻቸው እንዲሟላላቸው ሚናቸውን ለመጫወት ዋነኛ የለውጡ ፈፃሚ ሃይሎች ሆነው መገንባት አለባቸው፡፡
እነዚህ አደረጃጀቶች የለውጡ ባለቤትና ፈፃሚ ብቻ ሳይሆኑ ዋነኛ የህዝቡ የዴሞክራሲ ትምህርት ቤቶች ጭምር
በመሆናቸው ህዝቡ በነዚህ አደረጃጀቶች አማካኝነት ሊሣተፍ ይገባል፡፡ ከዚህ አንጻር የተለዩ የሕዝብ ክንፍ አካላት
የሚከተሉት ናቸው፡፡

3.2.1. የብዙሀንና ሙያ ማህበራት አደረጃጀቶች፣

ብዙሃን ማህበራት የሚባሉት የተደራጁ የህብረተሰብ ክፍሎችን የሚይዙ ሲሆኑ እነዚህም የተደራጁ የፆታ፣ የእድሜ
ወይም የሙያ ማህበራት እንደ ሴቶችና ወጣቶች፣ መምህራን፤ ሰራተኛ ወ.ዘ.ተ ያሉትን የሚያጠቃልሉ ናቸው።
እነዚህ አደረጃጀቶች ነጻ ማህበራት ስለሆኑ ነፃነታቸውን በማክበርና በመጠበቅ በአጋርነት መርህ በጋራ መስራት
አስፈላጊ ነው። ተሳትፎአቸውን በማጎልበት የህዝብ ክንፍ ሚናቸውን በአግባቡ መወጣት እንዲችሉ አቅማቸውን
ቀጣይነት ባለው መልኩ መገንባት ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፡፡

በነዚህ መሰረታዊ ጉዳዮች ዙሪያ የማህበራቱን አቅም ለመገንባት በሁለት መንገዶች መስራት ይጠበቃል።
በመጀመሪያ ደረጃ በየስራ መስካቸው በተደራጀ የህዝብ እንቅስቃሴ እንዲሳተፉና በዚህ ሂደት ተጠናክረው
እንዲወጡ መደረግ አለበት። ስለሆነም በዋና ዋና የመንግስት ዕቅዶችና ፖሊሲዎች ዙሪያ በሚመለከታቸው የሥራ
ዘርፎች ውይይቶችን በማድረግ የጋራ አመለካከትና ዕቅድ ይዞ መነሳት ያስፈልጋል፡፡ በነዚህ መድረኮች ማህበራቱ
የአባሎቻቸውን መብትና ጥቅም በማስመልከት ለሚያነሷቸው ጥያቄዎች በበቂ ዝግጅት ላይ ተመስርቶ ተገቢው
ምላሽ ሊሰጥ ይገባል፡፡ የሚነሱ ሀሳቦችንም እንደጠቀሜታቸው በመመዘን ግብዓት አድርጎ መውሰድ ብቻ ሳይሆን
የዕቅዱ አካል አድርጎ መተግበርና አፈጻጸሙንም መከታተል ያስፈልጋል፡፡ ከዚህ ውጪ የሚመጡ ኪራይ
ሰብሳቢነትን መሰረት ያደረጉ ጥያቄዎች ሲያጋጥሙ ደግሞ በዴሞክራሲያዊ የሃሳብ ትግል ማረምና ማስተካከል

15
ይገባል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ በጋራ መግባባት በተደረሰባቸው ነጥቦች ምን፣ መቼና እንዴት እንደሚሰራ በመግባባት
ወደስራ መግባትና በየጊዜው አፈፃጸሙን እየገመገሙና እያስተካከሉ መሄድ ያስፈልጋል።

ሁለተኛው የፐብሊክ ሰርቪሱ የለውጥ ሠራዊት እንቅስቃሴ በሚፈለገው ደረጃ ሊሳካ የሚችለውና ለውጡ ወደኋላ
ሊመለስ የማይችልበት ደረጃ ላይ ሊደርስ የሚችለው በለውጥ ሂደቱ ውስጥ ህዝቡ የተደራጀ ግንባር ቀደም ተሳታፊና
ተጠቃሚ እንዲሁም የለውጡ ባለቤት መሆን ከቻለ ብቻ ነው፡፡ ህዝቡ በዚህ ደረጃ ሊሳተፍ የሚችለው ደግሞ
ሥራው እንደ ተደራቢ ሥራ ታይቶ ጊዜ ሲገኝ ወይም ሁኔታዎች ሲያመቹ በሚፈጠሩ መድረኮች የሚፈጸም ሳይሆን
ታስቦባቸውና በቂ የዕቅድ ዝግጅት ተደርጎባቸው በሚካሄዱ መድረኮችና በሚዘረጉ አደረጃጀቶችና አሠራሮች
አማካይነት ብቻ ነው፡፡ መድረኮቹ፣ አሠራሮቹና አደረጃጀቶቹ መፈጠራቸው አንድ መሠረታዊ ጉዳይ ሆኖ
የመድረኮቹን አደረጃጀትና አሠራሮች ተግባራዊነት የሚከታተልና የሚመራ ባለቤት እያንዳንዱ ተቋም መመደብም
ይገባዋል፡፡

3.2.2. አጋር የህዝብ ክንፍ አደረጃጀቶች

በዚህ ደረጃ የሚታዩት በአብዛኛው የግል ልማታዊ ባለሃብት አደረጃጀቶች ናቸው። ባለሃብቱ በነፃ ገበያ ኢኮኖሚ
ማዕቀፍ እየተገነባ ላለው ስርዓት ሞተር ነው፡፡ ስለሆነም ፈጣን ልማትን ለማረጋገጥ ይህንን ኃይል በልማታዊ
መንገድ በሰፊው ማሳተፍና በሂደትም በቁጥርና በአቅሙ በከፍተኛ ደረጃ እንዲጠናከር ማድረግ ይገባል፡፡ ይህንኑ
ለማድረግ ባለሃብቱ መብቶቹንና ጥቅሞቹን በህጋዊ መንገድ ለማስጠበቅ የሚያስችሉ አደረጃጀቶች እንዲፈጠሩና
እንዲጠናከሩ የመንግስት ክንፉ ድርሻውን መወጣት አለበት፡፡ ከባለሃብቱ ጋር በሚኖረው መስተጋብር በዋናነት
እነዚህን የባለሃብቱን አደረጃጀቶች በመጠቀም ሊፈጸም ይገባል፡፡ የተፈጠሩት አደረጃጀቶች ለባለሃብቱ በልማታዊ
መንገድ ያልተቆጠበ ድጋፍ የሚሰጥባቸውና ተግባቦት የሚፈጠርባቸው መድረኮች መሆን አለባቸው፡፡ በተጨማሪም
ማህበራቱ ባለሃብቱ ወደ ኪራይ ሰብሳቢነት መንገድ ሲገባ በዴሞክራሲያዊ አኳኋን ከተሳሳተው መንገድ እንዲወጣ
ትግል የሚደረግባቸውና ልምድ የሚቀሰምባቸው መድረኮች ሊሆኑ ይገባል፡፡ መንግስትና ባለሃብቱ የየራሳቸውን
ነፃነት ጠብቀው ነገር ግን በአጋርነት ለጋራ ሀገራዊ ስኬት የሚሰሩባቸው መድረኮች መሆን አለባቸው፡፡ የባለሃብቱ
መድረኮች ይህንን የትግልና የአጋርነት ግንኙነት በቀጣይነትና በዴሞክራሲያዊ አኳኋን ለመፈፀም የሚያስችሉ
በመሆናቸው መድረኮቹን ከመቼውም ጊዜ በላቀ ሁኔታ ማጠናከርና መጠቀም ይገባል፡፡

3.3 የለውጥ ሰራዊቱ የህዝብ ክንፍ አካላት ልየታ፣

አብዛኞቹ የመንግሥት ተቋማት መጠኑና ስፋቱ ይለያይ እንጂ የሚሰጡትን የመንግስት አገልግሎት በቀጥታ የሚጠቀም
የህብረተሰብ ክፍል ወይም የህዝብ ክንፍ አላቸው፡፡ ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ በጣም ውስን የመንግስት ተቋማት
የሚሰጡትን አገልግሎት በቀጥታ ሳይሆን በተዘዋዋሪ የሚጠቀም የህብረተሰብ ክፍል ወይም የህዝብ ክንፍ
እንዳላቸው ይታወቃል፡፡ በመሆኑም የህዝብ ክንፍ የመለየቱ ጉዳይ እንደ ተቋሙ ተልዕኮና የተለየ ባህሪይ እንዲሁም
16
የአገልግሎት አይነት ስለሚለያይ እያንዳንዱ የመንግስት መ/ቤት ከራሱ ሴክተር ጋር ተያያዥነት ባላቸው አጀንዳዎችና
ተቋሙ በሚሰጠው አገልግሎት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተጠቃሚ የሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን ፍላጎቶች መሠረት
አድርገው የሚፈጠሩ የብዙሃንና የሙያ ማህበራትን፣ አጋር የህዝብ ክንፍ አካላትን እንዲሁም ሌሎች ተገልጋዮችን በተገቢ
መረጃና ጥናት ላይ በተመሠረተ አግባብ መለየት ይኖርበታል፡፡ በዚሁ መሰረት የተቋማትን ተልዕኮና ልዩ ባህሪይ መሰረት
ያደረጉና ተቋማት የህዝብ ክንፋቸውን ሲለዩ ግምት ውስጥ ሊያስገቡአቸው የሚገቡ መሰረታዊ ነጥቦች የሚከተሉት
ናቸው፡፡

3.3.1 የሚሰጡትን አገልግሎት በቀጥታ የሚጠቀም የህብረተሰብ ክፍል ወይም የህዝብ ክንፍ ያላቸው
የመንግስት ተቋማት፣

ሀ. እያንዳንዱ ተቋም የህዝብ ክንፉን በሚለይበት ጊዜ ግምት ውስጥ መግባት ካለባቸው መሰረታዊ ጉዳዮች
መካከል አንዱና ዋነኛው ነጥብ ከተቋሙ አገልግሎት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ የሚመለከታቸውን የሙያ
ማህበራት፣ የብዙሃን ማህበራት እና አጋሮችን እንዲሁም ልዩ ልዩ ተገልጋዮችን በዝርዝር የመለየት ጉዳይ
ነው።
ለ. የሚለየው የህዝብ ክንፍ የተደራጀ ተቋማዊ ህልውና ያለው መሆን ይኖርበታል፡፡ ይሁንና ወደ ተደራጀ
ንቅናቄ ሲገባ የህዝብ አደረጃጀቶች በሚፈለገው አይነት፣ ብዛትና ጥንካሬ ተፈጥረው ሊኖሩ እንደማይችሉ
ታሳቢ በማድረግ አደረጃጀት ባልተፈጠረባቸው አካባቢዎች በተበተነ መልኩም ቢሆን ያሉትን በየተቋሙ
የሚሰጠውን አገልግሎት ሁኔታ በዝርዝር በመለየት የሠራዊት ክንፍ አድርጎ ማንቀሳቀስ ይገባል፡፡ በሂደትም
ይህን አካል የበለጠ ተሰሚነትና አቅም እንዲኖረውና ወደ ተደራጀ ኃይል ደረጃ እንዲሸጋገር አስፈላጊውን
ድጋፍ ሁሉ መስጠት ይገባል፡፡
ሐ. የአንዳንድ ተቋማት ሰራተኞች በልዩ የሥራ ባህሪያቸው ምክንያት በተናጠል እንደ ግለሰብ ሲሰማሩ ፈጻሚ
የመንግሥት ክንፍ (ፐብሊክ ሰርቫንት) ሲሆኑ በሌላ በኩል ደግሞ እንደሙያቸው በማህበር ተደራጅተው
ሲመጡ እንደ ህዝብ ክንፍ የሚወሰዱ ሊሆኑ ይችላሉ። ለምሳሌ መምህራንና የመምህራን ማህበር፣ ነርሶችና
የነርሶች ማህበር ወ.ዘ.ተ. ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡
መ. በህዝብ ክንፍ ልየታ ሂደት ትኩረት ሊሰጠው የሚገባው ሌላው መሠረታዊ ጉዳይ እያንዳንዱ ተቋም
የየራሱን የህዝብ ክንፍ በከፍተኛ አመራር፣ በመካከለኛ አመራሮችና በመላው ሠራተኛ ስምምነት
በተደረሰበት መልኩ በመለየት ወደ ተግባር እንቅስቃሴ መግባት ያለበት መሆኑ ነው፡፡

3.3.2 የሚሰጡትን አገልግሎት በተዘዋዋሪ የሚጠቀም የህብረተሰብ ክፍል ወይም የህዝብ ክንፍ ያላቸው
የመንግስት መ/ቤቶች፣

ከተሰጣቸው ተልዕኮና ካላቸው ልዩ ባህርይ አንጻር በውስጥ አገልግሎት ላይ የታጠሩና ከውጭ ተገልጋይ ጋር ፊት
ለፊት የሚያገናኝ አሰራር የሌላቸው ነገር ግን አገልግሎታቸውን በተዘዋዋሪ የሚጠቀም የህብረተሰብ ክፍል ወይም

17
የህዝብ ክንፍ ያላቸው፣ የፖሊሲና የሌሎች አስፈጻሚ አካላትን የስራ ክንውኖች የመከታተልና ከተቋማቱ በየጊዜው
የሚቀርቡ ሪፖርቶችን የመገምገም ሃላፊነት የተሰጣቸው ተቋማትን በተመለከተ፡-
ሀ. ለአብዛኞቹ አስፈጻሚ አካላት የጋራ የህዝብ ክንፍ ሆነው የሚያገለግሉ አደረጃጀቶችን በጥንቃቄ
በመለየት በተዘዋዋሪ የራሳቸው የህዝብ ክንፍ አድርገው ይጠቀማሉ፡፡
ለ. የመድረኮችን ድግግሞሽ ለመቀነስ ሲባል መደበኛ የግንኙነት መድረክ በየስድስት ወሩ ይካሄዳል፡፡

ከላይ የቀረቡት የህዝብ ክንፍ ልየታ አማራጮች እንደተጠበቁ ሆነው ከተሰጠው ተልዕኮና ካለው ልዩ የስራ ባህርይ
አንጻር ከውጭ ተገልጋይ ጋር ፊት ለፊት የሚያገናኝ አሰራር የሌለው እንዲሁም የሌሎች አስፈጻሚ አካላትን ክንውን
የመከታተልና የመደገፍ ሃላፊነት ያልተሰጠው የመንግስት ተቋም በህዝብ ክንፍነት የሚያሳትፋቸውን የህብረተሰብ
ክፍሎች ወይም አደረጃጀቶች ከመለየት አንጻር ችግር ካጋጠመው ጉዳዩን ለፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት
ሚኒስቴር አቅርቦ የጋራ መፍትሄ አቅጣጫ የሚቀመጥ ይሆናል፡፡

3.4 ሌሎች ተገልጋዮች

ሌሎች ተገልጋዮች የሚባሉት ከላይ በህዝብ ክንፍ ከተጠቀሱት ውጭ የሆኑ ነገር ግን ከመንግስት ተቋማት
አገልግሎት የሚያገኙ ግለሰቦች ወይም ሌሎች የመንግስት ተቋማት ናቸው፡፡ ለምሳሌ ከገንዘብና ኢኮኖሚ
ልማት ትብብር ሚኒስቴር በበጀት ጉዳይ ላይ አገልግሎት የሚያገኙ የመንግስት ተቋማት “ሌሎች
ተገልጋዮች’’ በሚለው የሰራዊቱ ምድብ ውስጥ ይሆናሉ፡፡ በሰራተኛው አስተዳደር አገልግሎት ወይም
በሪፎርም ዕገዛ በኩል ከፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ሚኒስቴር አገልግሎት የሚያገኙ ተቋማትና
ግለሰቦችም እንደዚሁ “ሌሎች ተገልጋዮች” በሚለው ምድብ ውስጥ ይሆናሉ:: ተቋማት እነዚህን
ተገልጋዮች ለህዝብ ክንፍ እንደሚደረገው የራሳቸውን መድረክ በቡድን፣ በስራ ሂደት ወይም በተቋም ደረጃ
በማመቻቸት እንደሰራዊት የድርሻቸውን እንዲወጡ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

18
ክፍል አራት

የፐብሊክ ሰርቪስ የለውጥ ሰራዊት አደረጃጀትና አሰራር

4.1 የመንግስት ክንፍ አካላት አደረጃጀትና አሰራር

በፐብሊክ ሰርቪሱ በተካሄደው የመሰረታዊ የስራ ሂደት ለውጥ መሰረት የስራ ሂደትን የተከተሉ
አደረጃጀቶች መፈጠራቸው ይታወቃል፡፡ ስለሆነም ሌላ አደረጃጀት መፍጠር ሳያስፈልግ የፐብሊክ
ሰርቪሱ የለውጥ ሰራዊት ባለው የመንግስት አደረጃጀት ሊሰራና ሊያሰራ የሚችል የለውጥ ሰራዊት
ይፈጠራል ማለት ነው፡፡ በየተቋሙ የእርከኖቹ ደረጃና መጠሪያቸው የተወሰነ ልዩነት ቢኖረውም
በመንግስት መዋቅር ከለውጥ ስራው ጋር በተዛመደ ከላይ ወደ ታች በአጠቃላይ ቀጥሎ የቀረቡት
ደረጃዎች አሉት፡፡

4.1.1 የተቋሙ የበላይ አመራር

የተቋም የበላይ አመራር የመንግስት ተቋማትን የሚመሩ ሚኒስትሮች፣ ሚኒስትር ዴኤታዎች፣


ጽ/ቤት ሀላፊዎች፣ ኮሚሸነሮች፣ ም/ኮሚሸነሮች ዋና ዳሬክተሮች እና ምክትሎቻቸውን እንዲሁም
በነዚህ ደረጃ ያሉ ተሿሚዎችን የሚያጠቃልል ነው፡፡ የተቋሙ የበላይ አመራር የውይይት መድረክ
በሁለት ሳምንት አንድ ጊዜ ይካሄዳል፡፡

4.1.2 የተቋሙ የስራ አመራር/ማኔጅመንት መድረክ

የተቋሙ የስራ አመራር/ማኔጅመንት የተቋሙን የበላይ አመራሮች እና መካከለኛ አመራሮችን


የሚያጠቃልል ነው፡፡ ይህ መድረክ ቢያንስ በወር አንድ ጊዜ የሚካሄድ ሲሆን በዋናነት የተቋሙን ወርሃዊ
የውጤት ተኮር ዕቅድ አፈጻጸም በመገምገም ቀጣይ አቅጣጫን ያስቀምጣል፡፡ ተጠሪ ተቋማት ያላቸው
ሚኒስቴር መ/ቤቶች የተጠሪ ተቋማት ሃላፊዎች የሚገኙበት ተጨማሪ አደረጃጀትና የግንኙነት ጊዜ
ሊኖራቸው ይችላል፡፡ ይህ ማለት የየተቋሙ የበላይ እና መካከለኛ አመራር በወር አንድ ጊዜ የሚኖራቸው
19
መድረክ እንደተጠበቀ ሆኖ የተቋሙ የበላይ አመራሮችና የተጠሪ ተቋማት የበላይ አመራሮች የጋራ
መድረክም በየወሩ የሚካሄድ ይሆናል፡፡

4.1.3 የዘርፍ ሃላፊዎችና የመካከለኛ አመራሮች መድረክ

በፌዴራል ተቋማት ሚኒስትር ዴኤታዎች፣ ምክትል ዳይሬክቶሬቶች ወይም በእነሱ ደረጃ የሚመደቡ
ሃላፊዎች የሚመሩአቸው ዘርፎች አሏቸው፡፡ የዘርፎቹ የበላይ አመራሮች በየዘርፉ ከሚገኙ መካከለኛ
አመራሮች ጋር በየአስራ አምስት ቀኑ የጋራ መድረክ ይኖራቸዋል፡፡ በዚህ መድረክ የዘርፉና በዘርፉ ስር
የሚገኙ የስራ ሂደቶች የቁልፍ ተግባርና የአበይት ተግባራት አፈጻጸም ይገመገማል፤ አፈጻጸም የታዩ
ጥንካሬዎችና ክፍተቶች ተለይተው ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ይቀመጣሉ፡፡

4.1.4 የስራ ሂደት መሪና የሰራተኞች መድረክ

ይህ መድረክ በስራ ሂደቱ የሚገኙ አጠቃላይ ሰራተኞች ከስራ ሂደት መሪው ጋር የሚያካሂዱት ሲሆን መድረኩም
በየሳምንቱ የሚካሄድና ከስራ ሂደቱ ዕቅድ በሳምንቱ የሚተገበሩ ስራዎች የሚለዩበትና አፈጻጸሙ የሚገመገምበት
ይሆናል፡፡ በስራ ሂደት ስር ያሉ የቡድን አደረጃጀቶች በሳምንት ሁለት ጊዜ የግንኙነት መድረክ ይኖራቸዋል፡፡

4.1.5 የ 1 ለ 5 የለውጥ ቡድን መድረክ

ይህ መድረክ በስራ ሂደት ወይም በስራ ቡድን ውስጥ አንድ ግንባር ቀደም/የተሻለ ፈጻሚ የሚያስተባብራቸውን ከ 3-7
(በአማካይ 5) ፈጻሚዎችን የያዘ የ 1 ለ 5 የለውጥ ሰራዊት ቡድን መድረክ ነው፡፡ የ 1 ለ 5 የለውጥ ሰራዊት አደረጃጀት
ከተቋም ተልዕኮ ተመንዝረው የሚወርዱ ስራዎችን የሚፈጽሙ ሰራተኞችን ያቀፈ በመሆኑ የሰራዊት ግንባታን
ከማጠናከር አንጻር ቁልፍ ሚና ያለው ነው፡፡ በመሆኑም መድረኩ የቡድኑ አባላት ዕለታዊ የውጤት ተኮር ዕቅድ
አፈጻጸማቸውን በየቀኑ የሚገመግሙበት፣ በመማማሪ አቅማቸውን የሚያጎብቱበት፣ በአፈጻጸም ሂደት ያጋጠማቸውን
ችግር የሚለዩበትና ለቀጣይ የተግባር ምዕራፍ የሚዘጋጁበት ነው፡፡

4.2 የመንግስት እና የሕዝብ ክንፎች ትስስርና የግንኙነት አሰራር

4.2.1 የግንኙነት አሰራርና የውይይት አጀንዳዎች፣

20
የመንግስት ክንፉና የህዝብ ክንፉ ሀገራዊ ተልእኮንና ግብን ለማሳካት በቅንጅትና በጋራ መንቀሳቀስ አለባቸው፡፡
ለዚሁም እነዚህን ሁለት ክንፎች በማስተሳስር ለጋራ ውጤትና ስኬት በጋራ የሚሰሩበትን አግባብ ማመቻቸት
ያስፈልጋል፡፡ በዚሁ መሰረት የመንግስት ክንፍ ከህዝብ ክንፍ አካላት ጋር ቢያንስ በየሶስት ወሩ በመገናኘት ውይይት
ያደርጋሉ፡፡

የለውጥ ሠራዊቱ የህዝብ ክንፍ አካላት ተሳትፏቸውን በውጤታማነት ማሳካት ይችሉ ዘንድ በለውጥ ሠራዊት
አግባብ መንቀሳቀስና በሠራዊቱ ውስጥ የሚኖራቸውን ሚና ጠንቅቀው በማወቅ ስትራቴጂያዊ በሆነ አኳኋን
መወጣት ይጠበቅባቸዋል፡፡ የመንግስት ክንፉም የህዝብ ክንፍ መድረኮች ለተግባሮቻቸው መሳካት ትልቅ አቅም
መሆናቸውን ተገንዝበው ተልዕኮአቸውን በተደራጀ አግባብ መፈጸም የሚችሉበትን ምቹ ሁኔታ መፍጠር
አለባቸው፡፡ በአጠቃላይ በፐብሊክ ሰርቪሱ የለውጥ ሰራዊት ግንባታ ተግባርን በውጤታማነት ለመፈጸም
በሚደረገው ርብርብ የህዝብ ክንፉና የመንግስት ክንፉ የጋራ የውይይት አጀንዳ ከሚያተኩርባቸው ጉዳዮች ውስጥ
ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡

ሀ. የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አፈፃፀም፣

ለ. በየዓመቱ የሚታቀዱ የለውጥ ሰራዊት ግንባታ፣ የሪፎርምና የመልካም አስተዳደር እንዲሁም የልማት
ተግባራት ዕቅድ ዝግጅትና አፈፃፀም ግምገማ፣

ሐ. በመንግስት ክንፉ በሚዘጋጁ የአሰራርና የአደረጃጀት ማሻሻያ ስራዎች፣

መ. የመንግስት ተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ በዜጎች ቻርተር ላይ በተቀመጡ የአገልግሎት አሰጣጥ


ስታንዳርዶች መሰረት መሆኑን የመገምገም፣

ሠ. በመንግስት ክንፉ አካላትም ሆነ በህዝብ ክንፉ አካላት ውስጥ በሚታዩ የኪራይ ሰብሳቢነትና አስተሳሰብና
ተግባር የሚታዩ ችግሮች፣

ረ. የመንግስት ክንፉ በሚያመቻቸው መድረክ በመገኘት ተልዕኮን በጋራ ለማሳካት የሚደረገው ጥረት
እንደተጠበቀ ሆኖ የህዝብ ክንፉ የራሱን አጀንዳ ቀርጾ ተቋማትን ሱፐርቫይዝ የማድረግና በሱፐርቪዥኑ
ግኝት ላይ ተመስርቶ ከተቋማት ጋር መወያየትና ቀጣይ አቅጣጫንም ማስቀመጥ ይጠበቅበታል፣

4.2.2 የመንግስትና የህዝብ ክንፎች የጋራ የውይይት መድረክ አካሄድ

አንዳንድ የሕዝብ ክንፍ አካላት ከተለያዩ መንግስታዊ ተቋማት አገልግሎት የሚፈልጉና ከተልዕኳቸው አንፃርም
ከተለያዩ የመንግስት ክንፍ አካላት ጋር የሚያስተሳስሯቸው አጀንዳዎች ስለሚኖሯቸው ከአንድ በሚበልጡ
የመንግሥት ተቋማት እንደ ሰራዊት ክንፍ በጋራ የሚንቀሳቀሱበት ሁኔታ ይኖራል፡፡ ለምሳሌ የሴቶችን፣ የወጣቶችን፣
የአካል ጉዳተኞችን እንዲሁም የሙያ ማህበራትን ፍላጎቶች ማዕከል አድርገው የሚደራጁ የህዝብ ክንፍ አካላት
21
ከአንድ በላይ የመንግሥት ተቋማት ጋር ግንኙነት የሚኖራቸውና የተለያዩ መንግሥታዊ አገልግሎቶችን
የሚያገኙባቸው ሁኔታዎች ስለሚኖሩ ከአንድ በላይ የመንግሥት ተቋማት ጋር በህዝብ ክንፍነት ታቅፈው
ሊንቀሳቀሱ ይችላሉ፡፡

አንድ የህዝብ ክንፍ አካል ከአንድ በላይ የመንግስት ክንፍ አካል ጋር ግንኙነት እንደሚኖረው የሚጠበቅ ቢሆንም
አንድ አደረጃጀት በብዙ ተቋማት በአንድ ጊዜ እንዲሳተፍ መደረጉ የፕሮግራም መደራረብን ከማስከተሉም በላይ
በተሳትፎ ውጤታማነት ላይ አሉታዊ ጫና ሊኖረው ይችላል፡፡ በመሆኑም የህዝብ ክንፉ ከእሱ የሚጠበቀውን
ተልዕኮ በአግባቡ እንዲወጣ የመድረኮችን ድግግሞሽ የሚቀንስ አሰራር መከተል አስፈላጊ ይሆናል፡፡ ከዚህ አኳያ
ሁለቱም የለውጥ ሰራዊት ክንፎች በጋራ ተወያይተው የሚቀይሱት መፍትሄ እንደተጠበቀ ሆኖ እያንዳንዱ ተቋም
የራሱን ተጨባጭ ሁኔታ ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ከዚህ በታች ከቀረቡት አማራጮች እንደአመቺነታቸው አንዱን
ወይም ሁለቱንም በጣምራ በመጠቀም ችግሩን መፍታት ይገባዋል፡፡

4.2.2.1 መድረኮቹን ዋና ተቋማትና ተጠሪ ተቋማት በቅንጅት ማካሄድ፣

ዋና መ/ቤቶች እና ተጠሪ ተቋማት የህዝብ ክንፍ የውይይት መድረኮችን በተናጠል ከማካሄድ ይልቅ በአንድ ላይ
በማቀናጀት እንዲካሄድ ማድረግን እንደ አንድ አማራጭ በመጠቀም የመድረኮች ድግግሞሽን መቀነስ
ይጠበቅባቸዋል፡፡

4.2.2.2 ተመጋጋቢ ተልዕኮ ያላቸው ተቋማት በቅንጅት ማካሄድ፣

በሁለተኛ አማራጭነት መወሰድ ያለበት ተመጋጋቢ የስራ ባህሪ ያላቸው የመንግስት ተቋማት የህዝብ ክንፍ
መድረኮቻቸውን በጋራ እንዲያካሂዱ ማድረግ ነው፡፡ እያንዳንዱ ተቋም የራሱ ተልዕኮ ያለው ቢሆንም ደረጃው
ይለያይ እንጂ ከሌሎች ተቋማት ጋር የእርስ በርስ የስራ ግንኙነት አለው፡፡ ይሁንና በአንዳንድ ተቋማት የግንኙት
ደረጃው የጠበቀና የአንዱ የስራ ክንውን ለሌላኛው ቀጣይ ወይም ደጋፊ ስራ በመሆን ሀገራዊ አጀንዳን የሚያሳኩበት
አግባብ አለ፡፡ የየተቋማቱ የህዝብ ክንፎችም በአብዛኛው ተመሳሳይነት ይኖራቸዋል፡፡ በመሆኑም እነኚህ ተቋማት
የጋራ ዕቅድ በማወጣትና የውይይት አጀንዳዎቻቸውን እንደ ሴክተር በማቀናጀት ከህዝብ ክንፉ አካላት ጋር የጋራ
መድረክ በማመቻቸት ከመድረኮች ድግግሞሽ ጋር ተያይዞ ሊፈጠሩ የሚችሉ ችግሮችን ለመቀነስ የሚቻልበትን
አሰራር ተግባራዊ ማድረግ ይችላሉ፡፡

22
ክፍል አምስት

የፐብሊክ ሰርቪሱ የለውጥ ሰራዊት ግንባታ አቅጣጫዎች

የፐብሊክ ሰርቪሱ የለውጥ ሠራዊት የመንግስት ፖሊሲዎችን በውጤታማነት ለመፈጸምና ተልዕኮን ለማሳካት
እንቅፋት የሚሆኑበትን የአደረጃጀት፣ የአሰራር፣ የአመለካከት፣ የግንዛቤ፣ የክህሎትና የአቅርቦት ማነቆዎች
እየተፈቱለት የዓላማ ግልጽነትን ፈጥሮና እንደ አንድ አካል ከላይ እስከ ታች ተደራጅቶ ድህነትን በማሸነፍ
የኢትዮጵያን ሕዳሴ እውን ለማድረግ የሚረባረብ የለውጥ ኃይል ነው፡፡ የለውጥ ሰራዊቱን የመገንባት ጉዳይ በዘፈቀደ
የሚፈጸም ሳይሆን ግልጽ አቅጣጫን አስቀምጦ በታቀደና የተደራጀ ተግባራዊ እንቅስቃሴን በጥብቅ ዲሲፕሊን
በመፈፀም የሚከናወን ነው፡፡ ከዚህ አንጻር የፐብሊክ ሰርቪስ የለውጥ ሰራዊት ግንባታ ስራዎች ሲፈጸሙ መከተል
ከሚያስፈልጉ አቅጣጫዎች መካከል ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው፡፡

5.1 ሶስቱን የአመራር ኡደቶች በተመጋጋቢነት የመፈጸም አቅጣጫን መከተል፣

የፐብሊክ ሰርቪሱ የለውጥ ሰራዊት ሊገነባ የሚችለው በዋናነት ሶስቱን የአመራር ኡደቶች ወይም ምዕራፎች (የዝግጅት፣
የተግባርና የማጠቃለያ) በተመጋጋቢነት በመፈጸም ነው፡፡ በመሆኑም በዝግጅት፣ በተግባርና በማጠቃለያ ምዕራፍ
ተግባራት እንቅስቃሴ ውስጥ የለውጥ ሠራዊቱ አቅም እየተገነባ መሆኑን በትክክል እየለዩ የመሄድ አቅጣጫን መከተል
ይገባል፡፡

የዝግጅት ምዕራፍ የሚባለው አመራሩ መላውን ፈጻሚ አካላት ይዞ ወደተግባር ስምሪት ከመገባቱ በፊት ሁሉም የዕቅድ
ዝግጅት ስራዎች የሚከናወኑበት የመጀመሪያው የአመራር ኡደት ነው፡፡ ይህ ምዕራፍ በትክክልና በጽኑ ቁርጠኝነት
ከተፈጸመ የተግባር ምዕራፍን ስኬታማ ለማድረግ ወሳኝ ሚና ይጫወታል፡፡ አብዛኛውን ጊዜ የዝግጅት ምዕራፍ አራት
መሰረታዊ ጉዳዮች ማከናወንን የግድ ይላል፡፡ እነዚህም ጥራት ያለው የተሟላ ዕቅድ ማዘጋጀት፣ በዕቅዱ መሰረት
ፈጻሚዎችን ማዘጋጀት፣ ፈጻሚዎችን በአግባቡ አደራጅቶ በጠራ የስራ ክፍፍል መመደብና ለአፈጻጸም የሚያግዙ
ተጨማሪ ዝግጅቶችን ማካሄድና ግብዓቶችን ማቅረብ ናቸው፡፡
23
የዝግጅት ምዕራፍ በበቂ ሁኔታ ከተከናወነ በኋላ የሚቀጥለውና ዋናው የስራ ርብርብ የሚካሄድበት ምዕራፍ ደግሞ
የተግባር ምዕራፍ ነው፡፡ በዚህ ምዕራፍ አስፈጻሚውና ባለድርሻ አካላት የተቀመጡትን ግቦች ለማሳካት ቁልፍና አበይት
ተግባራትን በስራ ክፍፍላቸው መሰረት ያከናውናሉ፡፡ ተግባራትን በለውጥ ሰራዊት አማካኝነት በሚካሄድ ሰፊ የህዝብ
ንቅናቄ የማስፈጸም አቅጣጫ በተጨባጭ ተፈጻሚ የሚሆነው በዚህ ምዕራፍ ውስጥ ነው፡፡ ይህ ምዕራፍ የሰውን
አስተሳሰብ በመለወጥ፣ አካላዊ እንቅስቃሴውን በማስፋፋትና ግብዓቶችን በአግባቡ በመጠቀም ተግባራትን የመፈጸምና
ግቦችን የማሳካት የዕለት ተዕለት የተግባር እንቅስቃሴ የሚካሄድበት ነው፡፡

የማጠቃለያ ምዕራፍ የሚባለው በዝግጅት ምዕራፍ መሰረት የተከናወነው የተግባር ምዕራፍ በሚጠናቀቅበት ወቅት
የሚጀምር የዕቅድ ማሳረጊያ ምዕራፍ ነው፡፡ በዚህ ምዕራፍ በዋነኛነት ካለፈው ሰፊ ተግባር የሚወሰዱ ትምህርቶች
ይቀሰማሉ፡፡ ለቀጣዩ አዲስ ተግባር አስፈላጊ የሆኑ መሰረቶችም ይጣላሉ፡፡ለግምገማውም ሆነ ለቀጣዩ አዲስ ዕቅድ
በግብዓትነት የሚያገለግሉ ጉዳዮች ተለይተው የሚያዙበት ምዕራፍ በመሆኑ ባለፈውና በወደፊቱ መካከል መስተጋብር
መኖሩ የሚረጋገጥበት ምዕራፍ ነው፡፡ በማጠቃለያ ምዕራፍ ከሚከናወኑ ተግባራት መካከል የማጠቃለያ ግምገማ
ማካሄድ፣ የአፈጻጸም ደረጃ ማውጣትና ወጤቱን በማጽደቅ ለቀጣይ ዕቅድ አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን ለይቶ ማዘጋጀት
ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

5.2 የለውጥ ሰራዊት ግንባታውን ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ አስተሳሰብን ይበልጥ በሚያጎለብት


አግባብ መፈጸም፣

ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ ፐብሊክ ሰርቪስ እንዳይገነባ እንቅፋት የሆኑ አመለካከቶችን ማለትም የኪራይ
ሰብሳቢነት አመለካከት፣ ትምክህት፣ ጠባብነት፣ ኃይማኖትን ሽፋን ያደረገ አክራሪነት ወዘተ የመሳሰሉትን
በዕለት ተዕለት የለውጥ ሠራዊት ግንባታ እንቅስቃሴ ውስጥ እየፈተሹ የማዳከም አቅጣጫን መከተል
ይገባል፡፡ በምትኩም ልማታዊ አስተሳሰብን፣ የህዝብ አገልጋይነት፣ ታታሪነትን፣ የስራ ፍቅርን፣ ህዝባዊ
ወገንተኝነትን፣ ለህዝብ ጥቅም መቆምን፣ ህዝቡ ሲጠቀም እኔም እጠቀማለሁ የሚል አስተሳሰብን፣ ኪራይ
ሰብሳቢነት የሥርዓቱ አደጋ እንደሆነ በሚገባ ተገንዝቦ ለመታገል ዝግጁና ቁርጠኛ መሆን እና የመሳሰሉትን
ማጠናከርና ማጎልበት ያስፈልጋል፡፡

5.3 በተደራጀ አግባብ የመንቀሳቀስ አቅጣጫን መከተል፣

ፐብሊክ ሰርቪሱ ሀገራዊውን ራዕይ በተሟላ ሁኔታ የተገነዘበና የተጋራ፣ ይህንኑ ራዕይ ለማሳካት የወጡትን
የመንግሥት ፖሊሲዎችንና ስትራቴጂዎችን የተረዳና እነዚሁኑ ለመተግበርም የሚያስችል ግንዛቤና
ክህሎት ያለው መሆን ይጠበቅበታል፡፡ የመንግሥት ተልዕኮ የነበረውን ኋላቀር ሥርዓት የማስቀጠል ሳይሆን
ልማታዊና ዴሞክራሲያዊ መንግሥት ለመፍጠር ለስርነቀል ለውጥና ትራንስፎርሜሽን በመረባረብ

24
መሥራት በመሆኑ ፐብሊክ ሰርቪሱ ይህንኑ በውጤታማነት ዕውን ማድረግ የሚችለው በተበታተነ ሁኔታ
ሳይሆን ከላይ እስከ ታች ተደራጅቶ እንደ አንድ አካል መንቀሳቀስ ሲችል ብቻ ነው፡፡

በመሆኑም የፐብሊክ ሰርቪሱ የለውጥ ሰራዊት በተሰማራበት የስራ መስክ ሀገራዊ ተልዕኮውንና ሃላፊነቱን
በተሟላ መልኩ በመገንዘብ በተደራጀ አግባብ፣ በብቃት፣ በታማኝነትና በጠንካራ ዲሲፕሊን በመፈፀም
በድህነት ላይ መረባረብ ይገባዋል፡፡

5.4 የሠራዊቱን የማስፈፀም አቅም በሚገነባ መልኩ የመፈፀም አቅጣጫን መከተል፣


እንደሚታወቀው ሁሉ የማስፈፀም አቅም የሚባለው የሰው ሀብት፣ የአሠራርና የአደረጃጀት ጥምር
ውጤት ነው፡፡ ከሦስቱ የአቅም ምንጮች ወሳኙ ሰው ነው፡፡ አሠራርና አደረጃጀት ግዑዝ ነገሮች ስለሆኑ
በአግባቡ ሊጠቀምባቸው ከሚችል ሰው ውጭ ውጤት ሊያስገኙ አይችሉም፡፡ ዕውቀት፣ ክህሎትና
የአገልጋይነት አመለካከት ያለው ሰው ሲኖር ሌሎቹ ተዳምረው ነው ተጨባጭ የማስፈፀም አቅም
የሚገነባው፡፡ በመሆኑም ወሳኙ የሆነው የሰው ኃይል አቅም የሚገነባው በምልመላና ሥልጠና ብቻ ሳይሆን
በዋነኛነት በዕለት ተዕለት የተግባር እንቅስቃሴ ውስጥ በማስገባት የሰራዊቱን የማስፈጸም አቅም መገንባት
ይገባል፡፡

5.5 ሁሉንም የለውጥ መሣሪያዎች አቀናጅቶ የመተግበር አቅጣጫን መከተል፣


የተቋማትን የማስፈጸም አቅም ለመገንባት የተያዩ የለውጥ መሳሪዎች ተግባራዊ በመደረግ ላይ ናቸው፡፡
ተቋምን የመለወጥ ጉዳይ የማያቋርጥና ከህዝብ ፍላጎትና የልማት ዕድገት ጋር እያደገ የሚሄድ ከመሆኑ ጋር
ተያይዞ ትግበራው የአንድ ወቅት አጀንዳ ሳይሆን እየተጠናከረ እና ስርዓት እየሆነ ሊሄድ የሚገባው ነው፡፡
የለውጥ መሳሪያዎች አንዱ አንዱን የሚተካ ሳይሆን በተሳሰረ አኳኋን የሚተገበር ነው፡፡ በመሆኑም
የለውጥ መሳሪያዎችን በማቀናጀት የመተግበር ጉዳይ በፐብሊክ ሰርቪስ የለውጥ ሰራዊት ግንባታው ውስጥ
እንደ አንድ አቅጣጫ ተይዞ በጥብቅ ዲሲፕሊን ሊተገበር የሚገባው ነው፡፡

5.6 በስራ አፈጻጸም ውጤት ምዘና ላይ ተመስርቶ የማበረታታትና ተጠያቂ የማድረግ


አቅጣጫን መከተል፣

የልማታዊ መንግሥት ፐብሊክ ሰርቪስ ለመፍጠር መላው የመንግሥት ሠራተኛ በተሟሟቀ የለውጥ
ተግባር ውስጥ እንዲገባ ማድረግ ወሳኙና የመጀመሪያው ተግባር ነው፡፡ በለውጥ ሰራዊት ግንባታ ሂደት
የእያንዳንዱን ሠራተኛ የሥራ ብቃትና ውጤት በትክክል መዝኖ በሜሪት ላይ ብቻ በመመስረትና ህግን
ተከትሎ በስራ አፈጻጸም ውጤቱ ማበረታታት፣ ማብቃትና ተጠያቂ ማድረግ ቁልፍ መርሆ ነው፡፡ የፐብሊክ
ሰርቪሱ መመዘኛ መሆን ያለበት የሥራ ብቃት፣ ውጤትና ታታሪነት ብቻ ነው፡፡ ከዚህ በመነሳት በፐብሊክ

25
ሰርቪስ የሰራዊት ግንባታ ውስጥ በስራ አፈጻጸም ውጤት ምዘና ላይ ተመስርቶ ማበረታታትና ተጠያቂ
ማድረግን እንደ አንድ አቅጣጫ መያዝና መተግበር ያስፈልጋል፡፡

26
ክፍል ስድስት

የለውጥ ሰራዊት ግንባታ ክትትልና ድጋፍ ስርዓት

ሁለቱም የለውጥ ሠራዊት ክንፎች ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ከገቡ በኋላ የሚያጋጥማቸውን እንቅፋት
ተከታትሎ ለመለየትና ለመፍታት የሚያስችሉ ወቅታዊ ድጋፎች መሰጠታቸውን እንዲሁም በተግባራዊ
ርብርቡ ሂደት የሚገኙ ምርጥ ልምዶችን ተከታትሎ በመለየትና በመቀመር ለማስፋፋት የሚያስችል የክትትል፣
የድጋፍና የግምገማ ሥራ በቀጣይነት እየተሠራ መሆኑን ማረጋገጥ የሠራዊት ግንባታውን እውን ከማድረግ
አኳያ ሊታለፍና ቸል ሊባል የሚገባው አይደለም፡፡ ከዚህ አኳያ ሦስት ዋና ዋና የክትትል እና የድጋፍ
መስተጋብሮች ተግባራዊ ይደረጋሉ፡፡

6.1. የጋራ ግምገማና ግብረመልስ ስርዓት

ሀ. መደበኛ የሚኒስትሮች የጋራ መድረክ በየወሩ ይካሄዳል፡፡ ከየተቋማቱ ለፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት
ልማት ሚኒስቴር ተልዕኮ በተጨመቀው ሪፖርት ላይ በሚኒስትሮች የጋራ መድረክ ውይይት ተደርጎበት
የጋራ አቅጣጫ ይቀመጣል፣
ለ. በየስድስት ወሩ ከሁሉም የፌደራል ተቋማት የበላይ አመራር ጋር የጋር የግምገማና የምክክር መድረክ
ይካሄዳል፡
ሐ. በየተቋማቱ በየሁለት ሳምንቱ የማኔጅመንት ግምገማ በማድረግ በየደረጃው ባለው የለውጥ ሰራዊት ግንባታ
ስራዎች አፈጻጸም ላይ ውይይት ተደርጎ ግብረመልስ ይሰጥበታል፣
መ. በየሳምንቱ በየስራ ሂደቱ ግምገማ በማድረግ በስራ ሂደት ደረጃ በሂደቱ ካሉት ሰራተኞች ጋር በለውጥ
ሰራዊት አማካኝነት እየተፈጸመ ያለው የመንግስት ስራ አፈጻፀም ይፈትሻል፣
ሠ. እያንዳንዱ ተቋምና ተጠሪ ተቋሞቻቸው እንደአመቺነቱ በጋራ ወይም በተናጠል በየወሩ ከመላው ሰራተኛ
ጋር የግንኙነት መድረክ በመፍጠር በተቋሙ የለውጥ ሰራዊት ግንባታ አፈጻፀም ሪፖርት ላይ ግምገማና
ውይይት ተደርጎ የጋራ ቀጣይ አቅጣጫ ይሰጥበታል፡፡
ረ. በየዕለቱ በ 1 ለ 5 የለውጥ ቡድን አደረጃጀት ደረጃ አጠር ያለ የውሎ ግምገማ ይደረጋል፡፡

6.2 የሪፖርትና ግብረመልስ ሥርዓት

ሀ. ለተቋማዊ ለውጥና መልካም አስተዳደር ውጤታማነት ወሳኝ የሆኑ ጉዳዮች ላይ ብቻ በማተኮር


በተዘጋጀው ቼክሊስት መሠረት ዋና ተቋማት የተጠሪ ተቋሞቻቸውን አፈጻጸም ያካተተ ወርሃዊ ሪፖርት
በማዘጋጀት ለፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ሚኒስቴር ይልካሉ፡፡ ግብረመልስም ተዘጋጅቶ
27
ለተቋማቱ ይላካል፡፡
ለ. ተጠሪ ተቋማት ወርሃዊ የቁልፍ ተግባርና የአበይት ተግባራት አፈጻጸም ሪፖርት በየወሩ ለዋና ተቋሞቻቸው
ይልካሉ፤ ዋና ተቋማትም ሪፖርቱን ገምግመው ለተጠሪ ተቋሞቻቸው ግብረ-መልስ ይሰጣሉ፡

6.3 የሱፐርቪዥንና ግብረመልስ ስርዓት

ሀ. በሪፖርት ከሚደረገው በተጨማሪ የክትትል፣ የድጋፍና የግምገማ ስራው በአካል ምልከታ በተደገፍ
ሱፐርቪዥን ጭምር ይካሄዳል፣
ለ. ሱፐርቪዥኑ እንደየሁኔታው በዓመት ሁለት ጊዜ የሚካሄድ ሆኖ የህዝብ እና የመንግስት ክንፉን ተሳትፎ
ባረጋገጠ መልኩ ይፈጸማል፡
ሐ. የሱፐርቪዥን ግኝቱ በግብረ-መልስነት ለተቋማት ይላካል፤ተቋማትም ግብረ-መልሱን በግብዓትነት
በመጠቀም የዕቅዳቸው አካል ያደርጉታል፡
መ. ከሱፐርቪዥኑ የሚገኙ መልካም ልምዶች ተቀምረው ቀጣይ የሱፐርቪዥን ስራን ለማጎልበት ጥቅም ላይ
እንዲውሉ ይደረጋል፡፡
ሠ. ዋና ተቋማት የተጠሪ ተቋሞቻቸውን የለውጥ ሰራዊት ግንባታ፣ የሪፎርምና የመልካም አስተዳደር ስራዎች
አፈጻጸም ሱፐርቫይዝ ያደርጋሉ፣ ግብረ-መልስም ይሰጣሉ፣

28

You might also like