Professional Documents
Culture Documents
ቴክኒክና
ሙያ
ኮሌጅ
የ 2015
ዓ.ም
የሚያዚያ
ወር የስራ
ሪፖርት የሚያዚያ 2015 ዓ/ም
አ/አበባ
መግቢያ
የኢት/ፌደራል ፖሊስ ከዚህ በፊት በተበታተነ መልኩ በየዘርፎች ይሰጡ የነበሩ የተለያዩ ስልጠናዎችን ወደ ኢት/ያ
ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ እንዲካተቱ በመደረጋቸው ዩኒቨርቲውም ወጥነት ባለው መልኩ ስልጠና መስጠት በሚያስችል መልኩ
መዋቅራዊ አደረጃት በመስራት እንዲካተቱ ተደርጓል፡፡ ስለሆነም በዩኒቨርሰቲው የስልጠና ም/ፕሬዝዳንት ስር 5 የስልጠና
ማዕከላት አካቶ እንዲይዝ ተደርጓል፡፡
በስልጠና ዘርፉ የፖሊስ ቴክኒክና ሞያ (TVET) ኮሌጅ በተለያዩ ዲፓርትመንቶችን በማደራጀት የፌደራል
ፖሊስንም ሆነ የአገራችንን ፖሊስ አቅም የሚያጎለብት የፖሊስ ሞያና ቴክኒክ ስልጠናዎችን፣ ለሁሉም የት/ትና ስልጠና
ተሳታፊዎች በብቃት ለመስጠት በሚያስችል መልኩ እዲደራጅ በማድረግ ተቻይነት ያላቸውን ዋና ዋና ተግባራትን በመለየት
ከ 2013-2022 ዓ.ም ድረስ የሚቆይ ስትራቴጂክ እቅድ በማዘጋጀት ወደ ተግባር ተገብቶ የስትራቴጂክ ዘመኑን እቅድ ስኬትና
ክንውን ለመፈጸም እየሰራ ይገኛል፡፡
ስለሆነም በ 2015 ዓ/ም የሚያዚያ ወር ውስጥ የተከናወኑትንና ያልተከናወኑትን በመለየት የስራ ሪፖርት
እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡
የተከናወኑ ተግባራት
በኮሌጅ ለማሰልጠን በተያዘው የስልጠና ፕሮግራም መሠረት ስልጠናዎችን በተሳካ ሁኔታ በመስጠት የተቋሙ የሰለጠነ
የሰው ሃይል ፍላጎት በመሟላትና የሰልጣኙን የስልጠና ፍላጎት በማሳካት የተገልጋይ አመኔታ ማሳደግ ተችሏል፡፡
የሰልጣኞችን ዕለታዊ እንቅስቃሴ ክትትል በማድረግ ግምገማዎችን በማከናወን በክፍል ት/ት፣ በመስክ ስልጠና የዕርስ
በዕርስ ግንኙነት ላይ አስተያየት እንዲሰጡ በማድረግ ቅሬታዎችን እንዲፈቱ ተደርጓል፡፡
እያንዳንዱ መምህራን በሚያስተማሯቸው ት/ቶች በሰልጣኞችን ሃፒ ሽት በማስሞላት ያላባቸውን ክፍቶች
እንዲያስተካክሉ የማድረግ ስራ ተሰርቷል፡፡
በኮሌጅ ለማሰልጠን በተያዘው የስልጠና ፕሮግራም መሠረት ስልጠናዎችን በተሳካ ሁኔታ በመስጠት የተቋሙ
የሰለጠነ የሰው ሃይል ፍላጎት በመሟላትና የሰልጣኙን የስልጠና ፍላጎት በማሳካት የተገልጋይ አመኔታ ማሳደግ
ተችሏል፡፡
በምንሰጠው ስልጠና ውስጥ የስልጠናው ፕሮግራም መሰረት በማድረግ ከትምህርቱ ጋር ቀጥታ ግንኙነት ያላቸውን እና
ልምድ ያላቸውን መምህራኖችን በመጋበዝ በተሻለ መልኩ ትምህርታቸውን እንዲማሩ እየተደረገ ይገኛል፡፡
የቤተ-መጽሀፍትን አገልግሎት በተመለከተ 2182 አንባቢዎች በቤተ-መጽሀፍት ውስጥ የራሳቸውን ደብተሮችና የተለያዩ
መጽሀፍቶችን ያነበቡ ሲሆን 219 መጽሀፍ በትውስት የወሰዱ አሉ ከዚህም ውስጥ 197 ተመላሽ ሲያደርጉ ቀሪው 22
መጽሀፍ በአንባቢ እጅ ላይ ይገኛል፡፡
በሁሉም የት/ትና የስልጠና ፕሮግራም የሚሳተፉ ሴቶችን ስልጠናውን በብቃት እንዲወጡ በሴት አሰልጣኝ አማካኝነት
ያላባቸውን ችግር እንዲገልፁ የማድረግ ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡
በወር በአውቶ መካኒክና አሽከርካሪዎች ስልጠና ዲፓርትመንት የተሰጡ የመንጃ ፍቃድ ዓይነቶች፡-
ተ.ቁ የፁሑፍ ፈተና
በምትክ
የተሰጠ
ሜድካ
እድሳት
እድሳት
መንጃ
የተስራ
የተሰራ
የተወሰ
የተወሰ
አጋር
አዲስ በድጋሚ
አዲስ
አዲስ
ል
ፆታ 11 ወ ሴ ወ ሴ ወ ሴ ወ ሴ ወ ሴ ወ ሴ ወ ሴ 4 ሴ ወ ሴ ወ ሴ
- - 7 - 18 - 4 - 4 1 - -
የተለያዩ ፎርሞች ደብዳቤዎች፣ የተለያዩ ፈተናዎች፣ የተማሪዎች ሞጁል የተለያዩ ጽሁፎችን በመጻፍና የኮፒ
አገልግሎት ለ 1,450 አገልግሎት ተሰጥቷል፡፡
ከሆስፒታል እና ከኢት/ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ በየወሩ የሚመጣውን መድሃኒት በወቅቱና በሰዓቱ ገቢ በማድረግ ለተገልጋዮች
አገልግሎት እንዲውሉ ተደርጓል፡፡
በምንሰጠው ስልጠና ውስጥ የስልጠናው ፕሮግራም መሰረት በማድረግ ከትምህርቱ ጋር ቀጥታ ግንኙነት
ያላቸውን እና ልምድ ያላቸውን መምህራኖችን በመጋበዝ በተሻለ መልኩ ትምህርታቸውን እንዲማሩ እየተደረገ
ይገኛል፡፡
የመስክ ስልጠናው አቅም የፈጠራና የጥዋት ማንቂያ ስፖርት የሰልጣኞችን የጤና ሁኔታና አቅምን ያገናዘበ
ሰልጠና ተሰጥቷል፡፡
በአሁኑ ሰዓት በ TVT ደረጃ እየተሰጡ ያሉ ስልጠናዎች፡-
ተ.ቁ የስልጠናው ዓይነት Lvel ስልጠና የገቡበት ቀን ወ ሴ ድምር ምርመራ
1. አውቶ ሞቲቭ ኤሌክትሪክ II 18/03/2015 ዓ/ም 18 - 18 በት/ት ላይ
2. አካውንቲንግ እና ፋይናንስ II 18/03/2015 ዓ/ም 08 08 16 በት/ት ላይ
3. የማርች ባንድ ሰልጣኖች I 20/06/2015 ዓ/ም 26 7 33 በስልጠና ላይ
ጠቅላላ ድምር 52 15 67
አጫጭር ስልጠናዎች
2.1.1የ 1 ኛ ዙር የአካውንቲግ እና ፋይናንስ ደረጃ ተማሪዎች (lavel) እየወሰዱት ያለው ትምህርት ዓይነቶች ፡-
TVET Institution
training Cooperative Total
R.no Unit competency
Theory Practical training hours
የተከናወኑ ተግባራት
ከአዲስ አበባ ፖሊስ አከዳሚ ከሞጁል እና ካሪኩለም በተመለከተ የተለያዩ ጠቃሚ ግንኙነቶችን በማድረግ የተሻለ
የመማር ማስተማር ሁኔታዎችን መፍጠር ተችሏል፡፡
ከፖሊስ ዩኒቨርስቲ ጋር ከተለያዩ የስራ ክፍሎች የአካውንቲግና ፋይናንስ እና የአውቶ ሞቲብ ተማሪዎችን በማሰልጠን
ላይ እንገኛለን፡፡
ከኮሌጁ አመራሮችና አባላት ጋር በየሩብ ዓመቱ ግልፅ የውይይት መድረኮችን በመፍጠር የስራ አፈፃፀምን ማሳደግ፣
የኮሌጁን አመራሮችና አባላት የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመለየትና ለችግሮቹ ባለቤት ሰጥቶ 100% እንዲፈቱ
ሞልቶ ማስቀመጥ፣
የተከናወኑ ተግባራት
የሪከርድና ማህደር ክፍል 303 ገቢ እና 1,400 ወጪ በድምሩ 1,703 (አንድ ሺህ ሰባት መቶ ሶስት) ደብዳቤዎች
በቅልጥፍና እና ሚስጥራዊነት በመጠበቅ የተገልጋዮችን አቀባበል በማሻሻል ቀልጣፋ አገልግሎት ተሰጥቷል፡፡
04 ኮምፒውተሮችን ፎርማት እና የማስተካከል ስራ እንዲሁም 02 ፕሪንተር በመስራት ለተገልጋይ ቀልጣፋ
አገልግሎት እየተሰጠ ይገኛል፡፡
በኮሌጁ ስር ላሉ አገልግሎት ፈልገው ለሚመጡ አመራርና አባሎች 143 የድጋፍ ደብዳቤ፣
በስልጠና ፕሮግራሙ የሚሳተፉ ሴቶችን ስልጠናውን በብቃት እንዲወጡ ለማስቻል ሀንድአውት በግላቸው
እንዲሰጠቸው እና በሴት አሰልጣኛቸው አማካኝነት ያለባቸውን ችግር እንዲፈቱ እየተደረገ ይገኛል፡፡
ካርድ ክፍል ተመድባ ስትሰራ የቆየችው አንድ አባል የጤና ትምህርት ተምራ የሙያ ፍቃድ እንዲታወጣ ይረዳት ዘንድ
በፖሊስ ሆስፒታል ልምምድ እያደረገች ትገኛለች፡፡
በማሰልጠኛዉ በስልጠና ላይ የሚገኙ ሴቶችን በትምህርት ውጤታቸው እርስ በእርስ እንዲደጋገፉ እየተደረገ ይገኛል፡፡
የሰው ሀይላችን ወቅታዊ ከማድረግ አንጻር እስታስቲክስ በብሔር፣ በት/ት በቅጥር፣ በትውልድና በኃላፊነት በየጊዜው
የሚመደቡልን አባላት በማካተት በየወሩ ሪፖርት እየተደረገ ይገኛል፡፡
02 በጡረታ እና 11 በከጂ ከሰው ሀይል እንዲቀነሱ በደብዳቤ ብናሳውቅም እስካሁን ድረስ የሰው ሀይል መቀነሻ
ደብዳቤ አልተላከልንም፡፡
ሰርተፍኬት
1 ኛ ደረጃ
2 ኛ ደረጃ
ማስተርስ
ሌቭል 5
ሌቭል 4
ሌቭል 3
ሌቭል 2
ሌቭል 1
በፖ በአካዳ
መ/2 ኛ
ድምር
መረጃ
ዲግሪ
ደረጃ
ጠ/ድምር
ሊስ ሚ
ወ ሴ ወ ሴ ወ ሴ ወ ሴ ወ ሴ ወ ሴ ወ ሴ ወ ሴ ወ ሴ ወ ሴ ወ ሴ ወ ሴ ወ ሴ ወ ሴ ወ ሴ
1 - 3 1 3 - 1 1 3 1 2 3 1 1 - - 1 - 1 3 1 1 5 1 1 1 - - 8 7 16
0 1 4 9 5 5 4 0 4 2 5 7
በኮሌጁ የሚሰጡ ስልጠናዎችንና የማህበረሰብ አገልግሎቶችን የተቋሙን ሚዲዎችና ሶሻል ሚዲዎችን በመጠቀም ማስተዋወቅ፣
የስልጠና መስጫ ቦታን፣ መመሪያ ክፍሎችንና የስልጠና አካባቢዎችን ለስልጠና ምቹ ማድረግና በተገቢ የስልጠና መሳሪያዎች
እንዲሟሉ ማድረግ፣
የተከናወኑ ተግባራት
ሰልጣኞች እና ሰራተኞች በአካባቢ ልማት ተሳትፏቸውን አጠናክሮ ችግኞችን የመኮትኮትና ስራ ተሰርቷል፡፡
የፖሊስ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅን ለእስልምና እምነት ተከታዩች ለ 1444 ኛ የረመዳን ከሪም ዓል ምክንያት በማድረግ የሚዲያ ሽፋን እንዲሰጥ
ተደርጓል፡፡
ከአ/አበባ ዩኒቨርስቲ መምህራን እና ሌሎች መምህራን ጋር በመነጋገር ኢትዮጵያ ለነፃነት ያደረገቸው አስተዋፆ የኔልሰን ማንዴላ ስልጠና
ሲምፖዚየም ለማዘጋጀት ጥናታዊ ጽሁፍ ለማቅረብ ስራ ተሰቷል፡፡
ግብ ሰባት፡- የኮሌጁን ንብረቶችና በጀት ከሙስናና ብልሹ አሰራር በፀዳ ሁኔታ ስራ ላይ ማዋል፣ (የሃትና
በጀት አጠቃቀም)
ዓላማዎች፣
ለስልጠና የሚያስፈልጉ ልዩ ልዩ ግበዓቶች በወቅቱ ተገዝተው እንዲቀርቡ ጥያቄ ማቅረብና አፈፃፀማቸው በቅርበት መከታተል፣
ለኮሌጁ የተገዙ ንብረቶችን መዝግቦ በመያዝ በአግባቡና በቁጠባ በስራ ላይ እንዲውሉ ማድረግ፣
የተበላሹ ንብረቶች በወቅቱ በመለየት ተጠግነው አገልግሎት ላይ እንዲውሉ ማድረግ፣ የማይጠገኑ ንብረቶች እንዲወገዱ
ማድረግ፣
ለኮሌጁ የተፈቀዱ ንብረቶች፣ ፋይናንስና ግበዓቶች ከሙስና በፀዳ መልኩ ስራ እንዲውሉ ማድረግ፣
የተከናወኑ ተግባራት
በፖሊስ ሙያና ቴክኒክ ኮሌጅ ያለው ጄኔሬተር ለቢሮ እና ለምግብ አዳራሽ በቀንና በማታ እንዲሁም ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ መብራት
በጠፋበት ሰዓት ለተለያዩ አገልግሎት ተጠቅመናል፡፡
ለዳቦ ቤት የተፈቀደልን ዘይት በማምጣት አገልግሎት ላይ እንዲውል ተደርጓል፡፡
የሰልጣኙ የቀለብ ግዥን በኮሚቴ በመግዛት ለሰልጣኝ ከወጪ ቀሪ ያለውን ሂሳብ በማወጅ እንዲያውቁት እየተደረገ ይገኛል፡፡
ከመንጃ ፍቃድ የሚሰበሰበው ገንዘብ በህጋዊ ደረሰኝ ገቢ መደረጉን ቁጥጥር እና ክትትል እየተደረገ ይገኛል፡፡
ለሰልጣኞች የውሃ አገልግሎት እንዲያገኙ የተለያዩ የማስፋፊያ ዝርጋታ በማድረግ የዉሀ እጥረት እንዳይከሰት ተደርጎል፡፡
በክሊኒክ አካባቢ መብራት እና ዉሓ ተበላሽቶ ጥገና በማድረግ አገልግሎት እንድሰጥ ተድርጎል፡፡
በቢሮ አካባቢ መብርት ተመበላሸቱ 05 አምፖል 03 እስታርተር እንዲሁም 05 ሶኬት በመስራት አገልግሎት እንድሰጥ ተደርጎል፡፡
በኮሌጁ ውስጥ ላሉ 58 አመራሮች እና ለ 94 አባሎች፣ ጉርድ ጫማ በማምጣት የማደል ስራ ተሰርቷል፡፡
በኮሌጁ ውስጥ ላሉ ስቪል ሰራተኞች፡-
የሰልጣኞችን የስነ-ምግባር መከታተያ ስርዓት በአይቲ እንዲደገፍ ማድረግ፣ በኮሌጁ፣ ከሌሎች ዩኒቨርሲቲው የስራ ዘርፎች፣
ከፌዴራል ፖሊስ የስራ ዘርፎ እና ክልሎች ጋር የሚደረጉ የመልእክትና የመረጃ ልውውጦችን በቴሌግራምና በሌሎች የመልእክት
መለዋወጫ ፕላትፎርሞች በመደገፍ የፈጠነ የስራ ግንኑነት አቅምን ማሳደግ፣
የተከናወኑ ተግባራት
የስታፍ አባላትን እና የሰልጣኞች የግል ማህደር፣ አውቶሜት በማድረግ የመረጃ አያያዝን የማሳደግ ስራ ባለው ms-excel ዳታ
እንዲያዝ ተደርጓል፡፡
ሪፖርቶችንና የተለያየ ፎርማቶችን በኢሜልና በየቴሌግራም ከፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመለዋወጥ ፈጣን የመረጃ ልውውጥ
አድርገናል፡፡
ማጠቃለያ፤
በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የፌደራል ፖሊስ ስር የሚገኘው የፖሊስ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ የተሰጠውን ህገ- መንግስታዊ ስርዓቱን የመጠበቅ
ተልዕኮ ከዳር ለማድረስ የተለያዩ ስልጠናዎችን እየሰጠ ይገኛል፡፡
ስለዚህ የሚያዚያ ወር ውስጥ የተሰሩ ስራዎችን ጠንካራ ጎናቸውን በማጠናከር ያጋጠሙን ችግሮች በማስተካከልና በማረም
ለቀጣይ ሊሰሩ የሚገባቸውን በመለየት የተሰጠውን የ 2015 ዓ/ም ዕቅድ ለማሳካትም ከዩኒቨርሲቲው ስትራቴጂክ ዕቅድ መሰረት
በማድረግ ለ 2015 በጀት ዓመት ለትግበራ በተመረጡ 08 ግቦችና የትኩረት አቅጣጫዎች በመነሳት በእያንዳንዱ ግብ መሰረት
የተከናወኑ እና ያልተከናወኑ በመለየት በነበረው የዕቅድ አፈጻጸም ውስጥ ያጋጠሙ ድክመቶችንና ጥንካሬዎችን የቀረበ ሪፖርት
በመሆኑ በዕቅድ መሰረት ትኩረት በመስጠት የበለጠ በስትራቴጂክ መስራት ያስፈልጋል፡፡