Professional Documents
Culture Documents
ጥር/2015 ዓ.ም
ጎንደር
ምስጋና
ይህን ተሞክሮ እንዲደራጅ በርካታ ግለሰቦች ድጋፍ አድርገዋል፡፡ በቅድሚያ ደከምኝ ሰለችኝ ሳይሉ በጽሁፍ እና በአርትኦት ትልቅ ድጋፍ
ለዳረጉልን ወ/ሮ ሙሉቀን አጣናውና አቶ ደርሶልኝ አበበ በቀጠል ኮሚቴው ውን በመላላክ እንዲሁም ሪፍሬሽመነት በማቅረብ ለተባበሩን
ወ/ሮ አበበች፣ ከቦታ ቦታ በሚደረገው እንቅስቃሴ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይል ያመላለስን ሹፌራችን አቶ ዘውዱ አድማሱ፣ በቃለ መጠይቅን
እና የቡድን ውይይት የተሳተፉ የቁሳቋም፣ የደብረብርሐን ስላሴ እና የተጠዳ እንግዚአብሔር አብ ኗሪዎች፣ የክ /ከተማና ቀበሌ
አስተዳደሮች ከልብ የመነጨ ምስጋናችን ይድረሳችሁ! ያለ እናንተ ድጋፍ የትም አይደርሰም ነበር እና!
ማውጫ
01. መግቢያ.....................................................................................................................................................1
03. ዓላማ........................................................................................................................................................3
04. ወሰን........................................................................................................................................................3
05. ዘዴዎች.....................................................................................................................................................4
06. አስፈላጊነት.................................................................................................................................................4
4. የአጋር አካት ተሳትፎ ተሳትፎን ለማሳደግ የራስ ግንብ ሙዚየምን መልሶ የማልማት የተሰሩ ዝርዝር ተግባራት......................10
7. የነበሩ ጥንካራ፣ ደካማ ጎኖች፣ መልካም እድሎች እንዲሁም ተግዳሮቶች ትንተና (SWOC)............................................14
9. ማጠቃለያ.............................................................................................................................................15
አጠቃሎ
በቱሪዘም ገቢያ ተወደዳሪ በመሆን ከፍተኛ ጎብኝ ለመሳብ ዘርፈ ብዙ ስራዎችን መስራት ይጠበቃል፡፡ ከእነዚህም የመዳረሻ
ልማት ስራዎች እና የቅርስ እንክብካቤ እና ጥገና ቅድሚያ የሚሰጣቸው ናቸው፡፡ እነዚህ ተግባራት በአንዴ ተጀምረው አንዴ
የሚያልቁ ስራዎች ሳይሆነ የመዳረሻ ባለቤት የሆኑ አገራት ወይም መንግስታት ሁልጊዜ የሚሰሯቸው ተግራት ናቸው፡፡ ካለው
የዋጋ ግሽበት እንዲሁም ካላቸው ኢኮኖሚ አቅም አኳያ በተለይ በማድግ ላይ ያሉ አገራት ይህ ተግባር በብቃት
አያካነውኑትም፡፡ ይህን ጉድለት ለመሙላት የተለያዩ ዘዴዎች ይቀየሳሉ፡፡ በዚህ ወረቀት የጎንደር ከተማ አስተዳደር ባህልና
ቱሪዝም መምሪያ ያለበተን የፋይና አቅም ውስንነት በማህረሰብ ድጋፍና አጋር አካለት አስተዋጽኦ እንዲሸፍን ሰፊ የህዝብ
ንቅናቄ ስራዎችን ሰርቷል፡፡ በመሆሙም በቅርስ ጥበቃ እንክብካቤ ስራ ያመጣውን ለውጥ፣ ለለውጡ መምጣት የተካናወኑ
ዝርዝር ተግበራት እንዲሁም ማን ምን ፈጸመ የሚሉ ዝርዝር ጉዳዮችን አደራጅቶ እንደ ምርጥ ተመክሮ አደራጅቷል፣
አሰራጭቷል፡፡
1
01. መግቢያ
የባህልና የቱሪዝም ስራዎች ከፍተኛ ኢንቨስትመንት የሚጠይቁ ሁለት የተለያዩ ሴክተሮች ናቸው፡፡ (Luodolf, 1991)
የባህል ዘርፍ ውሰጥ የፈጠራ ስራን ለማጉልበት በብዙ ሚሊየኖች የሚቆጠር ከፍተኛ ካፒታል ይጠይቃል፡፡ በተለያዩ አለም
ሀገራት ያለዉ የፈጠራ ኢንዱስትሪ ወስደን ብንመለከት የአገርን ኢኮኖሚን ግንባታ ከፍተኛ ሚና እዲኖረው ለማድረግ
መንግስት ከፍተኛ በጀት በመመደቡ ዘርፉን ሲያንቀሳቅስው ይሰተዋላል (Kadile, 2012)፡፡ ለምሳሌ ከአሜሪካ ሆሊውድ
የደቡብ አፍርካ የፊልም ኢንዱስትሪ እና ናይጀሪያ “ኖሊ ውድ” የፊልም ኢንዱስትሪ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ መንግስት በዉጭ
ከፍተኛ ድርሻዉን ወሰዶ ሲያንቀሳቅሰው ዘርፍ በራሱ ገቢ ማመንጨት ይጀምራል፡፡ ከዚህ አኳያ ዘርፍ በሙሉ አቅም
እንዲያድግ በማድረግ ረገድ የመንግስት ተሳትፎ በእጅጉ ሲታከልበት ውጤታማና ለኢኮኖሚ የሚያደርገው አስተዋጽኦም
ከፍተኛ ይሆናል (Kin, 2014)፡፡ ነገር ግን በማደግ ላይ ያሉ አገራት ግን ከፋይናስ አኳያ የመንግስት አሰተዋጽኦ እድግ ደካማ
ነዉ፡፡ በመሆኑም ዘርፍ እምብዛም አድጎ ለኢኮኖሚ ያለዉ አበረክቶ ጎልቶ አይታይም፡፡
በባህል ዘርፍ ይህን ለማሳያ ካልን በቱሪዝም ዘርፍ በተመሳሳይ ገቢያ ውስጥ ተወዳዳሪ ለመሆን ግብዓት የሚሆኑ በርከታ
ጉዳዮች ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ይጠይቃል፡፡ ለአብነት ፕሮሞሽን, የማህበረሰቡ ህሴቶችን መጠበቅ (Authenticty)
አካባቢን ወይም (environement) ማልማት ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡
መዳራሻ ስፍራ ልማቶችንና አቅርቦቶች የማልማት ጉዳይ በገቢያ ተዋዳዳሪ ከሚያደርጉና ከፍተኛ ካፒታል ከሚጠይቁ
ጉዳች የሚመከደብ ነው፡፡ ይህ ሲባል አንድ መዳረሻ በተሟላበት ሁኔታ ምንም የተፈጥሮ እና ሰዉስራሽ ሀብቶች ቢኖሩም
የቱሪዝም ገቢያ ዉስጥ ገብተዉ በብቃት ለማሸነፍ ስለማይችል ተጨማሪ የመዳረሻ ልማት ስራዎች መስራት እና
አቅርቦቶችን ሟሟላት ይጠይቃል ማለት ነው፡፡ ይህን ኃላፊነት ደግሞ በአብዛኛው የሚወስደው መንግስት ነው፡፡ ስለሆነም
መንግስት መዳረሻዎች በቱሪዝም ገቢያ እንዲቀርቡ ለማድረግ ከፍተኛ መዋለ ንዋይን ወደ ልማት ስራ መርጨት ይኖርበታል
(Luodolf, 1991)፡፡ ይህን ማድረግ የቻሉ አገራት ከፍተኛ የገቢያ ድርሻ ይዘው ይሰዋላል፡፡ በዚህ ረገድ ቀዳሚዉን ቻይና
ከፍተኛ ስፋራን እየተቆናጠጠች ትገኛለች (ben, 2014) ለቱሪዝም ኢንዱስትሪ ማድረግ የቻይና መንግስት የሚዉስደዉ
ድርሻ ከፍተኛ ነዉ፡፡ የደቡብ አሜሪካዋ ብራዚልም ይህን በሁለተኛነት ተግባራዊ ስታደርገ ይታያል፡፡ ከአህጉራችን ሞሮኮ እና
አልጀሪያ የልማት ስራዎች ላይ መንግስት ደርሻ ከማንም በላይ ነው፡፡ በታዳጊ አገራት በተለይም ዝቅተኛ የኢኮኖሚ እድገት
ያለዉ አገራት ከገቢያዉ ተጠቃሚ ሲሆን አይስተዋልም ምንም የመስህብ ሀብት ሞልቶ ቢተረፈረፍባቸወም (Luodolf,
1991)፡፡ ለዚህም ቻድ እንደ ምሳሌ ትጠቀሳለች፡፡ በዋናነት ከድህነት ጋር ወይም ከፋይናስ አቅም ማነስ ጋር በቀጥታ
የሚያያዝ ሲሆን አገራዊ ፖለቲካዊ ሁኔታ ሌላው ምክኒያት ሊሆን እንደሚችል ይታወቃል፡፡
እንደ ቻድ ያሉ አገራት በርከታ ሲሆኑ ባለሙያዎች የሚያሰጡት ምክር የገቢያ ጉድለ ትሸፍኖ የቱሪዝም ገቢያውን ለማሸነፍ
የፋይናስ አቅም የሌላቸው አገራት ከፍተኛ የገቢ ማመነጫ ዘዴዎች ቀይሰው መንቀሳቀስ እንደሚገባቸው ነው፡፡
በየትኛውም ጉዳይ ላይ የሚፈጠር የፋይናንስ ጉድለት (financial short fall) መሙላት ብዙ ገቢ ማመንጫ ዘዴዎች
እንዳሉ ይታወቃል፡፡ በአብዛኛዉ አጋር አካላትን አካቶ መስራት በሁሉም አካባቢዎች የተለመደ ተግባር ( (Dawning,
2015)፡፡ የከፍ ሲል የጠቀስናቸው የአፍሪካ አገራት ሞሮኮ አን ቱኒዚያ አብዛኛውን በቱሪዝም ልማት ስራዎች የአየር መንገድ፣
ባንኮች እና ፕራይቬት ቱሪስት ሳይት ኦነሮች ጋር ተቀራርቦ መስራት የበጀት ምንጭ ሆኖ እንደገዛቸው ይጠቅሳሉ (Sales
@exploring moroco travel, 2023)
2
ይህም ስልት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአገራችንም በስፋት ጥቅም ላይ ሲዉል ይስተዋላል የኮይሻ፣ የሃላላ ኬላ እና የጎርጎራ
ፕሮጅክቶች ጥቂት ማሳያዎች ናቸዉ፡፡ በከተማችንም የመንግስት ያለበትን የፋይናስ ጉድል ሞልቶ በቂ የመሰረተ ልማት
አቅርቦት ያለበት የቱሪዝም ኢንዱስትሪ ለመገንባት ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ ይህ የስራ ድርሻ የወሰደዉ ደግሞ የከተማ
አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ነዉ ፡፡
ሴክተሩ መንግስት ያለበትን የገንዘብ ጉድለት እንዲሟላ ለማድረግ የተለያዩ ተግባራት እያከናወነ ይገኛል፡፡ ከዚህ በመነሳት
ከፍተኛ የመሰረተ ልማት ለማዳረሻዎች ማሟላት ተችሏል ይህን አስመልክቶ ዉጤቶች፣ ለዉጤቶች ምክንያት የሆኑ
የተቀናጁ ስራዎች እና ተግባራትን ለመቀመር ኮሚቴ ተደራጅተዉ ወደ ስራ ገብቷል ነበር፡፡ ከተደረገ መለስተኛ የማህበራዊና
ኢከኮኖሚያዊ እዲሁም አሰራር ወይም አተጋበር ልምዶች ጥናት በኋላ የገኘውን ተሞክሮ በሚከተለው መንገድ ተቀምሯል፡፡
ስለሆነም ይህ ተሞክሮ ሰነድ ተዘጋጅቷል፡፡
03. ዓላማ
የአጋር አካላት ተሳትፎ በማሳደግ የቱሪዝም መዳረሻ የሆነዉን ሀብቶችን ለመጠገን፣ ለመንከባከብና ለማስተዋወቅ
የሚጠየቀዉ ከፍተኛ ገንዘብ በመሸፈን የቱሪዝም ገቢያ የተሟላ ምርትን ለማቅረብ እንዲሁም ይህን አሰራር ቀምሮ ለሌሎች
እንዲዳረስ ማድረግ ዋናዉ ዓላማ፡፡
3
04. ወሰን
የጎንደር ከተማና አካባቢዋ ባሉ 11 ገጠር ቀበሌዎች ክልል ዉስጥ ነዉ የመንግስት የቱሪስት መዳረሻ አካባቢዎችን
ለመንከባከብና ለማልማት ያለበትን የገንዘብ እጥረት ለመቅረፍ የአጋር አካላትን አካቶ በመስራት እና ልዩ ልዩ ገቢ መሰብሰቢያ
ስልቶችን ተቀይሶ ተግባራዊ በማድረግ የመጣዉን ዉጤት፣ ለውጤቱ መገኘት የተከናወኑ ተግበራንት የሚዳስስ ሰነድ ነዉ፡፡
በዋናነት በሶሰት ጉዳዮች ያተኩራል እነዚህም፡-
የወዳደቁ ቁሳቁሶችን ምልሶ ጥቅም ላይ ማዋልና አቅርቦ ልማት (Facilities development) ናቸው፡፡
05. ዘዴዎች
ይህን ተሞክሮ ለመቀመር የተጠቀምንባቸው ዘዴዎች እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡
06. አስፈላጊነት
በጎንደርከተማ ተከስቶ የቆየውን የኢኮኖሚ ማሽቆልቆልና ማህበራዊ መስተጋብርን ለማነቃቃት ስላገዘ
ተደራሽ ያልሆኑ የቱሪስት መዳረሻዎች መሰረተ-ልማት እንዲሟላላቸው በማድረግ ተደራሽ እንዲሆኑ ስላስቻለ
ግለሰቦችና ድርጅቶች እንዲማሩባቸው ለፖሊሲና ስትራቴጅ አዘጋጆች (ግብዓት) መነሻ ሆነው እንዲያገለግሉና
እንዲሰፋ ለማድረግ ተሞክሮውን መቀመር አስፈላጊ ሆኗል፡፡
4
1. አጠቃላይ ተግባራት እና ውጤት
የደብረጸሀይ ቁስቋ ቤተክርስቲያ የተገነባችው በእቴጌ ምንትዋብ በ 1878 ዓ.ም አካበቢ እንደሆነ ይነገራል፡፡ በ 1979 ዓ.ም
በተባበሩት መንግስታት በትምህርት፣ በሳይንስ እና ባህል ተቋም በሰው ልጆች ወካይ ቅርስነት ከተመዘገቡ የጎንደር ቅርሶች
ውስጥ ትካተታለች፡፡ ሆኖም በተለያዩ ጊዜያት በተፈጥሮ እና ሰውሳራሽ ችግሮች የመፈራረስ ኣዳጋ ተጋርጦባት ቆይቷል፡፡
በመሆኑ ጣራው እንዲሁም ግድግዳና ፈራርሶ የነበረበት ሁኔታ ይስተዋል ነበር፡፡ በተለይም የአዋፍት ኩስ፣ አልጌና ሌሎች በካይ
ቁሶች በህንጻው ላይ የነበሩ በመሆኑ ጉዳቱን ይበልጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደግ መጥቶ ነበር፡፡ በመሆኑም የማህበረሰቡ የቅሬታ
ምንጭ ሆኖ የይጠገንልን ጥያቄ በተደጋጋሚ የሚቀርበብት ታሪካዊ ቅርስ እና ስፍራ ነበር፡፡
5
2.1.2. ለ ውጤት አንድ. ደብረ ፀሀይ ቁስቋምን በህ/ሰብ ተሳትፎን ለማጠገን የተሰሩ ዝርዝር ተግባራት
ዝርዝር የአተገባበር ሂደትን የሚያሳይ ፕሮጀክቶች ፕሮፖዛል ተቀርጻል
አ
ሰ
ል
ጣ
ኞ
ች
በኮሚቴ የተደራጁ አካላት ከምንግሰት፣ ከታዋቂ ግለሰቦች፣ ሽማገሌዎች፣ ምሁራን እንዲሁም ነጋዴዎችና የቤተ
ክርስቲያኗ መሪዎች የተውጣጣ እንዲሆን ተደርጓል፡፡
የጎንደር ከተማ ዓማቀፍ ቅርስ አስተዳደር ዋና ስበሳቢ
6
የቤተ ክርሰቲያኗ አስተዳዳረ ምክትል ሰብሳቢና የሰበካ ጉባኤ ተወካይ ጸሐፊ በውስጡ 25 አባላት ያሉት ዓብይ
ኮሚቴ ተቋቋመ በስሩ
3 ንዑሳት ኮሚቴዎች አደረጃጀት
1 ኛ. ገንዘብ አሠባስብ ኮሚቴ
2 ኛ. የህዝብ ግንኙነት ኮሚቴ
3 ኛ. የስትሪንግ ኮሚቴ
ተደራጀቶ በየዘርፍ በተናጠል እና በቡድን ከፍተኛ ርብርብ ተደርጓል
መሰረት ከማህበረሰቡ በአንድ ጊዜ ብቻ 2.6 ሚሊዬን ብር ለስራ ማስጀመሪያ ተብስቦ ወደ ስራ ተገብቷል፡፡
በሂደት 6.5 ሚሊዬን ብር ወጭ የተደረገበት የደብረ ፀሀይ ቁስቋም ቤቱ ክርስቲያን ጥገና ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ
ጥር 6/2015 ዓ.ም ተመርቆ ወደ ስራ ገብቷል፡፡
7
የቁስቋምን መርሐ ግብር ተከትለን የተፈፀመ ሲሆን በዚህ
በደ/ብርሃን ስላሴ ቤተክርስቲያን ጥገና ላይ ተመሳሳይ ተግባርት
በመፈጽም ከፍተኛ ውጤት ተገኝቷል፡፡
በመጀመሪያው አካባቢያ በተደረገ ጥረት 124 ሺ ሰዎችን ላይ
በተፈጠረሰ ግንዛቤ ስራ እና ከግንዘቤ ፈጠራ በኋላ በተደረገው ገቢ
ማሰባሰቢያ ስልት መሰረት ከማህበረሰቡ 2.8 ሚሊዮን ብር ተሰብሰብ
ወደስራ የተገባ ሲሆን ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ወደስራ ገብቷል፡፡
የቁስቋምንና የደብረብርሐን ስላሴን ተሞክሮ በተመሳሳይ ወስደን ለዚህ ጥናታ በተክርስቲያን ጥገና ተግበራዊ
አድርገነዋል፡፡ በመሆኑ በመጀመሪያው አካበቢያ በተደረገ ጥረት ከግንዘቤ ፈጠራ በኋላ በተደረገው ገቢ ማሰባሰቢያ
ስልት መሰረት ከማህበረሰቡ 3 ሚሊዮን ብር እንዲሁም ፕሮጅቱ ለቅርስ ጥበቃ በላስልጣን ቀርቦ 3.8 ሚሊዮን
ብር ድጋፍ እንዲያገኝ ተደርጓል፡፡ በድመሩ 6.8 ሚሊዮን ብር ተሰብሰቦ ወደስራ የተገባ ሲሆን አሁን ሰዓት
ጥገናው ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ወደስራ ገብቷል፡፡
4. የአጋር አካት ተሳትፎ ተሳትፎን ለማሳደግ የራስ ግንብ ሙዚየምን መልሶ የማልማት የተሰሩ ዝርዝር
ተግባራት
4.1. የማልማት ስራ ከመሰራቱ በፊት
ራስ ግንብ በአጼ ፋሲል ዘመነ መንስት ከተገነቡ ቀደምት ታዊካዊ ህንጻች አንዱ ሲሆን አጼ ፋሲል ለጦር አበጋዛቸው
ለራስ ወልደ ጊዎርጊ መኖሪያ ቤት ይሆን ዘንድ የተገነባ ህንጻ ነው፡፡ ይህ ህንጻ ምንም ዓይነት ጥገና ተደርጎለት
የማያውቅ ከመሆኑም በላይ በተለያዩ ጊዜያት አላስፈላጊ ሚበሉ ጣልቃ ገብነቶች ሲዳርጉበት የቆየና ትኩረት ተነፍጎ
የኖረ ታሪካ ሐብት ነው፡፡ በመሆኑም በስመንቶ የተለጠፈ፣
በአልጌ የተወረረ፣ በወፎች ኩስ ተወረራ እና በስጥቆች
የተሸሞነሞነ የነበ ህንጻ ነው፡፡ ቅጥር ግቢውም በአረሞ
እንዲሁም በተለያ አላፋስላጊ ህጻዎች ግንባታ ይዘቱ
የተረበሸ ግቢ ነው የነበረው፡፡ ልዕየታ ያመይስብ ነው
የነበረው፡፡
4.2. የመጣ ለውጥ
ገጽ ምድር የማስዋብ ስራ
የመዝናኛ፣ የባህል ምግብ በመጠጥ ማቅረቢያ ጎጆ
ቤት ስራ ተከናውኗል፡፡
9
በዚህ ስራ ከ 4 ሚሊዮን ገደማ የሚገመት ወጭ የጠየቀን ሲሆን ይህም የተሰበሰበው
ፕሮፖዛል በመቅረጽ በዚህ ላይ ከሀበሻ ቢራ ጋር መግባባት ላይ በመድረስ የተቻለ ሲሆን ታላቅ የሙዚቃ
ኮንስርት በማዘጋጀት ወደ 780,000 ብር ተገኝቷል፡፡
ከተቋማት ድጋፍ 2 ሚሊዮን የሚገመት ብር በዓይነት ድጋፍ ተገኝቷል፡፡
ከዚህ ውጭ ያሉ ቀረ የወዳደቁ ንብረቶችን በቅርስ ጥገባ ፕሮጅክት ተገዝተው የተጣሉንት በቅጥር ግቢያችን በማስበሳሰቡ
ጥቅም ላይ እንዲውሉ በማደረግ ነው፡፡
እነዚህን ግብአቶች በልሶ ጠቅም ላይ በመዋል ወደ 820,000 ብር የሚገመት ግብዓት እንዲሆኑን በማስቻል በፋሲል
አብያተ መንግስትና በራስ ግንብ ሙዚየም 2 ደረጃቸውን የጠበቁ ሽንት ቤቶች ተግንብተው ለጎብኝ አገልግሎት
እንዲሰጡ ተደርጓል
የደረቁ የኖራ ግግሮች የራስ ግንብ ሙዚም የእግር ምገድ እና ከርብ ስቶን ስራ እንዲሰራ ተደርጓል
10
ከወዳደቁ ብረቶች ለጎብኝው መረጃ ሚሰጡ ከ 220 በላይ ፓኔሎች
በዚህ ምክኒያት ተልከስክሰው አካበቢን ያበላሹ የነበሩ አላፋለጊ ቁሳቁሶች ጥቅም ላይ እንዲወሉ ተድርጎ ወጭን
ከመቀነስ በላይ የአካበቢው ውበት እንዲጠበቅ በማድረግ ከፍተኛ ጠቅም አስገኝቷል፡፡
11
7 ከወዳደቁ ቁሳቀሱች በገንዘብ የሚገመት በብር 820,000
ግብዓት
8 ጠቅላላ ድምር በብር 23,120,000
በዚህ ሰንጠረዥ እንደሚታየው 23,120,000 ብር መንግስት ለጥገና የጎደለውን ከአጋር አካለት እንዲም ከማሀብረሰቡ
በማሰባሰብ ጉድለቱን በብቃት መልቶ ሊሰሩ የሚችሉትን የጥገናና እንክብካቤ ስራ በቅሶቻችን ላይ መስራት መቻላት ትልቅ
አቅም በገቢየ ላይ ልንፈጥር ከሚያስችሉን አንዱን እና ዋነኛው ደረጃ አሟልተና ተበሎ ይገመታል፡፡
በቅርስ ባለቤትነት እና የኔ ባይነት ስሜት በማህበረሰቡ ዘንድ ስር እንዲሰድ ትልቅ ፋይዳ መኖሩ
ተረጋግጧል
በመንግሰት እና ማህበረሰቡ እንዲሁም በማህረሰቡ መካከል ከፍተኛ መቀራረብን የፈጠረ ተግባራ
መሆኑ ተረጋጧል
ቅርሶች እንዲሁም ሌሎች አካባቢያችን ጸጋዎች በማህበረሰቡ ዘንድ ተለይተው እንዲታወቁ የማደረግ
እድልን በመፍጠር የጋራ ግንዘቤ ያደገበት ሁኔታ ፈጥሯል፡፡
በራስ የሚተማመን ማህረሰብ በመፍጠር ረገድ ከፍተኛ ሚና እደነበረው ተረጋግጧል፡፡
7. የነበሩ ጥንካራ፣ ደካማ ጎኖች፣ መልካም እድሎች እንዲሁም ተግዳሮቶች ትንተና (SWOC)
7.1. ጠንካራ ጎን
በመምሪያው ያሉ ባሙያዎች ከፍተኛ የእውቅት እና ክህሎት ያላቸው መሆኑና ችግሩን ተረድቶ ወጭ ቆጣቢ በመሆነ
መንገድ ተግባራትን ለመፈጽም ያለው ዝግጁነት
12
ከሁኔታው ጋር የሚሄዱ ፕሮጅከት ፕሮዛሎችን በጥራት ቅረጽና ተግባዊ ላድረግ ያለው ጥረት
7.2. ደካማ ጎን
የኮረና ወረርሽኝ
የፖለቲካ አለመረጋጋት
በሰነድ ደረጃ ተዘጋጅቶ ቢታትም እና ለአንባቢያን በመረጃ መስጫ ማዕከላት በቤተ-መጻሀፍት እንዲቀመጥ ቢደረግ
ለአስተዋጽኦ ላደረጉ አጋር አካለት ቢሰራጭ
በኢንተርኔት ወይም በዌብ ሳይት ለሁለም ተደራሽ እንዲሆን ቢለቀቅ መልካም ነው
13
9. ማጠቃለያ
የገንዘብ እጥረት በመንግስት ተቋማት የመግጠሙ ሁኔታ ዛሬም እንዲሁም ለቀጣይ አመታት ሊቀጥል
የሚችል ችግር በመሆኑ ይህን ጉድለት ሊሞላ የሚችል ደግሞ የማህረሰቡ ተሳትፎ መሆኑን ያየናቸው
ድርሳናት ያስረዳሉ፡፡ ስለሆነም ከአጋር አካለት ጋር ተቀራርቦ መስራት፣ ኪነ ጥበብን መስረት ያደረገ የገቢ
ማሰባሰቢያ ስልቶችን ተግራበዊ ማድረግና ማህረሰቡን ግንዛቤ በማሳደግ ለማኝኛውም አይነት ልማት ስራ
ተጨማሪ ሀብትን ፈጥሮ ተግባራዊ በማድረግ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግርች መፍታት ይቻላል፡፡
የጎንደር ከተማ ባህልና ቱሪዝም መምሪያ በመንግስት በጀት የማይሸፈኑ የቅርስ ጥገና ጉዳዮችን የከወነው በዚህ
መንገድ እንደሆነ ይህ ተሞከሮ ያስረዳል፡፡ በተለይም ፕሮጅክቶችን በመቅረጽ፣ ከማህበረሰቡ ጋር በአደረጃጀት
ውይይት በማድረግ፣ አጋር አካላትን ጋር በተመረጡ ስራዎች ላይ አብሮ ለመስራት ሰምምነት ላይ በመድረስና
የኪነ ጥበብ ስራዎን ለገቢ ማመንጫነት አደርጎ በመጠቀም እንደሆነ ተመላክቷል፡፡ ሰለሆነም ይህን ተሞክሮ
ሊያሰፋ የሚፈልግ አካል እዚህ ላይ አተኮሮ እንደ አካባቢው ነባራዊ ሁኔታ ቃኝቶ ተግራባዊ ቢያደርግ መሰል
ውጤቶችን በአካባቢው ሊያጣ እንዲችል እሙን ነው፡፡
14
ማጣቀሻ
ben, M. (2014, sept 24). wolrdtourism. Retrieved ju ne 02, 2023, from www.wto.com:
hh://www.wto.com
Dawning, A. (2015). information. Retrieved june 07, 2023, from Newsights:
www.newsight.com
Kadile. (2012). in creative world: who shoulder the role. Abuja: Abjua publishing.
Kin, L. (2014, july 06). creative world. Retrieved june 08, 2023, from cinima Host:
http://www.cinimahost.com
Luodolf, S. (1991). effectiive community based tourism Development . London: London
pulishing.
Peterson, A. (2015). community based ecotourism. Easian Tourism , 78-81.
Sales @exploring moroco travel. (2023). home. Retrieved from Exploring morocco travel:
Exploringmoroccotravel.com
15