You are on page 1of 26

የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ

ሰላም ፎሪም 2011 ዓ.ም


የስራ- አፈፃፀም ሪፓሪት

ሰኔ 2011 ዓ.ም

አምዩ
ይዘት

• መግቢያ
• የፎረሙ አመሰራረት
• የፎረሙ አላማ
• የፎረሙ እሴት
• የፎረሙ ግብ
• የዓመት የስራ ክንውን ሪፖርት
• ያጋጠሙን ችግሮች
መግቢያ
• አንድ ተቋም የተቋቋመበትን ዓላማ ለማሳካት ግልጽና ሊሳካ
የሚችል አስራርና ዉጤታማ የሆነዉ ተቋማዊ እሴቶች
ማጎልበት ይኖርበታል፡፡ ከነዚህ ተቋማዊ እሴቶች አንዱ
የሰላም እሴት ሲሆን ትርጉሙም መልካም ባህሪና
አመለካከትን በማስረፅ ተቋሙን ከሁከትና አመፅ ነፃ
በማድረግ የትምህርት መርሃ ግብሩን አስተማማኝ ሰላም
በተረጋገጠበት ሁኔታ ማስኬድ ማለት ነዉ፡፡ለዚህ ግብ
ስኬታማነት የሚረዱ በዩኒቨርሲቲዉ ዉስጥ የተለያዩ
ተግባራት ተግባራዊ በመሆን ላይ ናቸዉ፡፡ ከነዚህም
መካከል አንድ የሰላም ፎረም መመስረት ነዉ፡፡አርባ
ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የሰላም ፎረምን በፌዴራል ጉዳዮች
ሚኒስቴር የተላከዉን መመረያ መሰረያ መሠረት በማድረግ
ከዚህ ቀደም የነበረውን የሰላም ክበብ (peace club )
በመተካት 2003 ዓ.ም ተመሰረተ፡፡
የቀጠለ............

• አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ በአሁኑ ሰዓት ስድስት ካምፓሶች ያሉት ሲሆን


በተለያ የትምህርት 20,000 የሚበልጡ ተማሪዎች በተለያየ የትምህርት
አይነትና በተለያየ የትምህርት ደረጃ ተቀብሎ እያስተናገደ የሚገኝ ሲሆን
ካላው የተማሪው ብዛትና የቋንቋና የባህል ብዛሃነት አኳያ ሰላም ላይ
የተመሰረተና የተፈለገው ጥራት ያለው ትምህርት እንዲረጋገጥ ሰላም
ፎረም ያለው ሚና ከፍተኛ ነው፡፡ ፎረሙም የተለያዩ ተግባራቶችን
በማከናወን ሁከትና ብጥብጥ ተከስቶ ጥፋት ከማድረሱ በፊትም ሆነ
በኃላ የማረጋጋትና የማርገብ ስራዎችን በማከናወን ሰላም ወዳድ ዜጋ
ለመፍጠር የሰላም እሴት ግንባታን በህብረተሰቡ መሀል የማስፋፋት ስራ
እንደዋነኛ ተግባር አድርጎ እየተንቀሳቀሰ ያገኛል፡፡የአርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ
ሰላም ፎረም በስድስቱም ግቢ በዋናው ግቢ 13 በአባያ ካምፓስ 13
በጫሞ ካምፓስ 13 በነጭ ሳር ካምፓስ 13 በኩልፎ ካምፓስ 13
በሳውላ ካምፓስ 13 በአጠቃለይ 78 ስራ አስፈጻሚወችን የያዘ ነው
የፎረሙ አመሰራረት

• በፌደራል ጉዳዮች ሚኒስተር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት


የሰላም ፎረም ማቋቋሚያ መመሪያ መሰረት በተማሪዉ
ዉስጥ የሰላም ባህል ግንዛቤን ለማስረፅ የሰላም እሴቶችን
ለማጎልበት ከመምህራንና ከሌሎች ሰራተኞች እንዲሁም
ከአካባቢዉ ማህበረሰብ ጋር የሚኖረዉን መልካም ግንኙነት
ለማዳበር የአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ የሰላም ፎረም
በ2006ዓ.ም የተቋቋመ ሲሆን በ2004 እና 2005 የሰላም
ክበብ ተብሎ ስራውን ሲሰራ ቆይተዋል
• ሰላም ፎረም በተማሪዉ መካከል ያለዉን ህብረ ብሄራዊ
አንድነት ፤ የትምህርት እና ማህበራዊ መስተጋብሮችን
ማዋሀድ ሰላማዊ የመማርና የምርምር ምቹ ሁኔታዎችን
እንዲፈጠሩ በትጋት የሚሰራ ፎረም ነው
የቀጠለ............

• አርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ 6 ካምፓሶች እና 8 ኮሌጆች ያሉት ሲሆን


እነሱም፡-
• ቴክኖሎጅ ኢኒስቲቲዩት
• ወተር ቴክኖሎጅ
• የተፈጥሮ ሳይንስ ኮሌጅ
• ግብርና ሳይንስ ኮሌጅ
• የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ
• የህግ ት/ት ቤት
• የህክምና ሳይንስ ኮሌጅ
• የስነ-ሰብና ማህበረሰብ ናቸው፡፡
የቀጠለ............

• በመሆኑም በቀንና በማታው ፕሮግራም 32630


ተማሪዎችን ተቀብሎ በማስተማር ላይ የሚገኝ
ዩኒቨርሲቲ ነው፡፡
የፎረሙ አለማዎች

• በዩኒቨርስቲው የአጥፊ ሀይሎች ሁከት እና አመፀን


የማነሳሳት ሙከራወች በሰላምዊ መንገድ በመፈታት
እና ተማሪወች የአፈራሽ ተልእኮ ማስፈፀሚያ መሳሪያ
እንደይሆኑ ግንዛቤ በማስጨበጥ የ2011 ትምህርት
መርሀ ግብርን አስተማማኝ ሰላም በተረጋጋበት ሁኔታ
በተቀመጠለት እቅድ መሰረት እንዲጠናቀቅ ማድረግ
የቀጠለ............

• በተማሪወች መካከል መልካም የእርስ በእርስ ግንኙነት


እንዲኖር ማድረግ ፡፡
• እንዲሁም ከዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ ጋር የሚኖራቸው
ግንኙነት መልካም እንዲሆን ማስቻል ፡፡
• በተማሪወች መካከል እንዲሁም በተማሪወች እና
በሌሎች የዩኒቨርሰቲው አካለት መካከል አለመግባባት
ሲፈጠር በግልፅ በመወያየትና በመከባበር ችግሮች
እንዲፈቱ ማስቻል ፡፡
• በዩኒቨርስቲው ውስጥ የሰላም ባህል የሚያጎለብቱ
አወንታዊ አመለካከቶች እንዲዳብሩ ማስቻል
የፎረሙ እሴቶች

• ለሰላም ዘብ መቆም
• እኩልነት
• አርያ መሆን
• መቻቻል
• መከባበር
• አሳታፊነት
• ፍታሀዊነት
• ተቆርቋሪነት
ግብ

የትምህርት ዘመኑ መማር ማስተማር እና የዩኒቨርስቲው


የለውጥ እቅዶችን ያለምንም ሁከት ማሳከት
የአ.ም.ዩ ሰላም ፎረም የዓመት
የስራ ክንውን ሪፖርት

• የአዲስ ገቢ ተማሪዎች ቅበላ በሰላም ፎረም ተ/ፖሊስ ተደርጉዋል፡፡


• በተጓደሉ የሰላም ፎረም እና ተ/ፖሊስ አባላት የሟሟያ ምርጫ
አድርገናል፡፡
• ሰላም ፎረም በ 13 ንዑሳን ኮሚቴ ተዋቅረን እየሰራን እንገኛለን
• በተለያዩ ባአላቶች ከሌሎች አደርጃጅቶች ጋር በመሆን የበኩላችንን
ድርሻ አበርክተናል
• የግቢዉ ተማሪዎች ስለፎረሙ የላቸዉን አመለካከቶች የሚያጎሉበትን
መድረኮች ፍጠረናል እንዲሁም የአባለቶቻችንን ቁጥር ወደ 9770
አጠቃልይ ድምር ሲሆን ሴት 1500 ወንድ 8270 አድርሰናል፡፡
የቀጠለ............

• ለፎረሙ አበላት የመታወቂያ ካርድ አዘጋጅተናል


• በግቢያችን ውስጥ ተማሪዎች ስለ-ሰላም ፎረም
መረጃና እውቀት እንዲኖራቸው ለማድረግ በተወሰኑ
ካምፓሶች በራሪ ወረቀቶች በየብሎክ መኝታ ቤት
ተቆጣጣሪዎች ቢሮ ላይ በመለጠፍ ተማሪዎች
የፎረሙን እንቅስቃሴ እንዲውቁ ተደርጓዋል፡፡
• በግቢ ውስጥ ሊከሰቱ የሚችሉ ችግሮች ለመከላከል
በተለይም ማታ ማታ ከግቢው የደህንነት ሀይል ጋር
በመቀናጀት ግቢውን ፓትሮል አርገናል
የቀጠለ............

ተማሪዎች የማንኛውም አገልግሎት አሰጣጥ ችግርና አስቸኳይ


መፍትሄ የሚያስፈልጋቸው ችግሮችና አስቸኳይ መፍትሄ
የሚያስፈልጋቸው ችግሮች ሲያጋጥማቸው እንዲያሳውቁንና
አስቸኳይ መፍትሄ ለመስጠት በግቢያችን ውስጥ ተማሪዎች
በሚኖሩባቸው 11 ብሎክ ላይ የተረኛ ፕሮክተር ስምና ስልክ
የግቢውን የደህንነት ሃላፊዎች ስምና ስልክ፣ የፕሮክተሮች
ሀላፊና የፈረቃ አስተባባሪ ስምና ስልክ፣ የካምፓሱ ሰላም
ፎረም ፕሬዘዳንት ስምና ስልክ፣ የካምፓሱ ተ/ህ/ፕሬዘዳንት
ስምና ስልክ እንዲሁም የካምፓሱ መብራት ፣ ውሀና፣ሌሎች
ጥገናዎች ሀላፊ ስምና ስልክ ቁጥር በመለጠፍና የተማሪዎችን
ቅሬታ በማዳመጥ ለሚከሰቱ ችግሮች በአስቸኳይ ለመፍትሄ
በማቅረብ በአገልግሎት ችግር ምክንያት ይከሰታሉ የሚታሰቡ
ችግሮች ቅድመ መከላከል ስራ ተሰርቷል
የቀጠለ............

• ግቢያችን ውስጥ በተማሪዎች መካከል የሚከሰቱ


ግጭቶችና አለመግባባቶችን በፎረሙ ንዑስ ኮሚቴ
ማለትም በዲሲፕልን ኮሚቴ ጉዳዩን በማየት ተማሪዎች
እንዲታረቁ ለማድረግ ችለናል፡፡
• የአገልግሎት ችግሮች በሚያጋጥሙ ግዜ በአስቸኳ
ይሪፖርት በማድረግ አስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጣቸው
ማድረግ ችለናል፡፡ ለምሳሌ የDSTV ካርድ ማለቅ
በአስቸኳይ ሪፖርት በማድረጋችን በአስቸኳይ መፍትሄ
ተሰቶታል፡፡
• ሰላማዊና ኢ ሰላማዊ ተግባራትን በተመለከተ የሚዘክሩ
በራሪ ወረቀቶችን አዘጋጅተናል በተዎሰኑ ካምፓሶች
• የፎረሙን አላማ ለዪኒቭርሰቲው ማብርሰብ ማሳወቅና የውዪዪት
መድረኮችን አዘጋጅተናል
• ከተለያዩ ዪኒቨርስቲዎች ከሚገኙ ተመሳሳይ አደረጀጀቶች ጋር
የልምድ ልውውጥ አድረገናል
• የሰላም ፎረም እና የተ/ፖሊስ ስራ አስፈፃሚዎች በካፈቴሪያና
ፓትሮል ተመድበን ሰርተናል፡፡
• በካፍቴሪያ አካባቢ ይነሱ የነበሩ ጥያቄወች ከምገብ ቤት ሀላፊወች
ጋር በቅርበት በመስራታችን አሁን ላይ ሙሉ በመሉ ባንልም
አብዘሀኘው ችግሮችን ለመቅረፍ ችለናል
የቀጠለ............

• ፀረ-ጥላቻ ንግግርን በመቃወም ከተ/ህ እና ከ


ቲክቫህ.ዔች አባላት ጋር በመሆን ወደ-አቻ ዩኒቨርሲቲዎች
በመዘዋወር ስራዎችን ሰርተናል በካንፓሶቻችን
መድረኮችን ፈጥረናል።
• ከዞኑ አስተዳደር ፀጥታና ግጭት መካለከል የስራ ሂደት
አስተባሪ በጋራ በመሆን ተመራቂ ተማሪወች ውጭ ላይ
ለሚያከብሩት ፕሮግራም ደህንነታቸው ተጠብቆ ወደ
ግቢ እንዲገብ በማድረግና የሰላም ባህልን ከማጎልበት
አንፃር የጋራ የሆነ ስብሰባ አዘጋጅተናል፡፡
• የተማሪዎች ስልጠና ወቅት ለስልጠናው የሚያስፈልጉ
ቁሳቁሶች ለተማሪወች ማቅረብ እና በስልጠናው ወቅት
የቀጠለ............

• ለመሳሌ ውሃ ማሰራጨት
• ለስልጠናው የተዘጋጁትን ሞጅል መበተን
• የሰልጣኝ ተማሪወችን ቦታ ማዘጋጀት
• የዶርምተሪ ተጠሪ የፈሎር እና የብሎክ ማስተሮችን
በመምረጥ ችግሮች ከመፈጠራቸው በፊት እንዲደርሱን
አድርገናል
• በግቢው ውስጥ አንዳንድ ተማሪዎች አደንዛዥ ዕፅ
ሲጠቀሙ የመከታተል ከጊቢያችን ባሉ አደረጃጀቶች
ማለትም ከተ/ህብረት እና ከደህንነት አካል ጋር ተናበን
በመስራት ተመክሮ እንዲመለሱ ያደረግናቸውም አሉ
የቀጠለ............

• በተወሰኑ ካምፓሶች ውስጥ በግለሰቦች መካከል


የተፈጠረውን አለመግባባትና ግጭት የሰላም ፎረም
ስራ አስፈፃሚ ሆነው በሚሰሩ ተማሪዎች ጋር
በመወያየትና ችግሮቻቸውን ተወያይተው እንዲፈቱ
በማድረግ ወደሌሎች ግቢዎች ሊዛመት የነበረውን
ግጭት ማስቀረት ችለናል፡፡ ከዚህ አፈንግተው ሌላ
ችግር ለመፍጠር የሞከሩትን ደግሞ ካምፓስ
ደህንነቶች ጋር በመወያየት አፋጣኝና ህጋዊ እርምጃ
ተወስዷል፡፡
የቀጠለ............

• የፎረሙን ተግባርና ስራ የሚቆጣጠሩ ማለትም የግቢው


ዲኖች ፣ ከፎረሙ ጋር በጋራ አብረው የሚሰሩ ማለትም
የግቢው ደህንነት እና ጸጥታ ፣ የካምፓሱ ተ/አገ/ማስ/ጽ/ት
እና ከአገልግሎት ሰጪ ሴክተሮች ማለትም የቤተ መፃህፍት
አገልግሎት፣ ጤና አገልግሎት ፣መኝታ አገልግሎት ፣ እና
መብራትና ሌሎች ጥገናዎችን ከሚያስተባብሩ ሀላፊዎችና
አካላትጋር የነበረን ቁርጠኝነትና በጋራ የተከናወኑ ተግባራት
በጥንካሬ ተነስተው ወደ ፊትም ይበል የሚያሰኙ ናቸው፡፡
• ለ2011 በስራ አስፈፃሚነት የሚያገለግሉ ተማሪወችን
መርጠናል፡፡
• ለፎረሙ አባላትና የባለድርሻ አካላት የሽኝት እና የምስክር
ወረቅት አሰጣጥ ፕሮግራም አዘጋጅተን ሰተናል
የአጋጠሙን ችግሮች

• የሰላም ፎረም ስራ አስፈፃሚዎች በቁርጠኝነትና በስነ-ምግባር


አለመስራታቸው እና ለአንድ ወይ ለሁለት ሰው ሀላፊነት ሰጥቶ
ቁጭ ማለት
• የፎረሙን እንቅስቃሴዎች የምናደርገው ከትምህርት ሰዓት
ውጪ በመሆኑ በሚያጋጥመን የትምህርት ጫና ስራውን
በሙሉ አቅማችን እንዳንሰራ አድርጎናል
• የጊዜ እጥረት
• የአባላት መተካካት በዲስፕሊንና በሌሎች ጥፋቶች የተተኩ
አባላትን በአስቸኳይ ይዘን መቀጠል አልተቻለም ፡፡ ምክንያቱም
አብዘኛው ሥራ አስፈፃም ለዲስፒሊን ጥሰት እየተጋለጠ ስለሆነ
ጥቅት አባላት ቁርጠኝነት ችግር ነበረባቸው
የቀጠለ............

• ቢሮና የቢሮ ቁሳቁሶች በአስቸኳይ ባለመማላታቸዉ


ጫና ተፈጥሮብናል ፡፡
የመፍትሔ አቅጣጫ
• በአንዳንድ የጊቢያችን ቦታዎች የመብራት ችግር በመንገዶች ላይ
ይስተዋሉ ነበር ይህንን ችግር ለመቅረፍ ከሚመለከተው አካል ጋር
በመሆን በሚያስፈልጋቸው ቦታዎች የማብራት(ፓውዛ) ተከላ
ተደርጉዋል፡፡
• ይህ በንዲ እንዳለ የተማሪውን ደህንነት ለመከላከል በጊቢው ውሰጥ
በሚደረገው እንቅስቃሴ ላይ በዋነኛነት አስፈላጊ የሆነው የእጅ ባትሪ
ለሰላም ፎረም እና ተ/ፖሊስ ማዳረስ ተችሉዋል፡፡
• በተጨማሪም የቢሮ እና የቢሮ ቁሳቁሶችን ማግኘት ተችሉዋል፡፡
• የፎረሙን ቢሮና ቁሳቁሶች ማደራጀት/ሟሟላት፡፡
• ለ2011 አዲስ ገቢ ተማሪዎች አቀባበል ማድረግና በግቢ ዉስጥ
ለሚያጋጥማቸዉ ችግሮች መፍትሄ ማግኘት የሚችሉባቸዉን ሂደቶች
ላይ መረጃ መስጠታችን፡፡
የቀጠለ............

• የግቢዉ ተማሪዎች ስለፎረሙ የላቸዉን አመለካከቶች


የሚያጎሉበት መድረኮች መፍጠር፡፡
• በዩኒቨርሲቲያችን ሰላማዊና መልካም የመማር ማስተማር
ሂደቶች እንድጎለብቱ ማድረግ፡፡
• ለግጭት የምዳሪጉ ቦታዎችን እና የአገልግሎት መጓደሎችን
መለየትና ልዩ ትኩረት አድሪጎ መንቀሳቀስ፡፡
• ለዩኒቨርሲቲያችን ብሎም ለካምፓስሳችን መኀበረሰብ
በሰላም እሴት ግንባታ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ
መፍጠር፡፡
• ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት የ2012 ዕቅዳችንን
በተሳካ ሁኔታ መተግበር፡፡
ምስጋና…

• በመጨረሻም ለጠየቅነዉ ጥያቄ ሁሉ በቅንነት


ለሚያስተናግዱን ለአርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ
ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት
• ለደ/ብ/ብ/ሕ/ ከልል ጸጥታና አስተዳደር ቢሮ
• የጋሞ ጎፋ ዞን ጸጥታና አስተዳደር ጽ/ቤት
• በስራችን ሁሉ ከጎናችን በመሆን ለደገፉን ለ አቶ
አስፈው ደምሴ፤ አቶ ያሊሾ ለሌሎችም የአርባ ምንጭ
ዩኒቨርስቲ የሰላም አምባሰደሮችን ላደረጋችሁልን
ድጋፍ ልባዊ ምስጋናችንን እንገልፃለን፡፡
ሰለም በራሱ ሽልማታችን ነው!!!
ሰላማችሁን ያብዛላችሁ..........

You might also like