You are on page 1of 35

የሶሻል ሚዲያ ለልማትና ዴሞክራሲ

ስርዓት ግንባታችን ያለው ፋይዳና


የምንከተለው
ስትራቴጂ

ጥር 2007
የገለጻው ይዘት
1. አስፈላጊነት
2. መነሻ ሁኔታዎች
3. ጥንካሬዎች፣ ድክመቶች፣ መልካም
አጋጣሚዎችና ስጋቶች
4. ራእይ፣ አላማ፣ ግቦች
5. ስትራቴጂዎች
6. ክትትልና ድጋፍ
መግቢያ
 ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን በሰዎች የእለት ተእለት ህይወት ወሳኝ ሚና
ይጫወታል
 በዘመነ ግሎባላይዜሽን አለምን ወደ አንድ መንደር ተቀይራለች ካስባሏት
ምክንያቶች ውስጡ አንዱ የኢንፎርሜሽን ከሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ነው
 ታሪካዊ አመጣጡን ስንመለከት

 የተለምዶ ሚዲያው (Traditinal media) ጋዜጣ በ17ኛው ከፍለ ዘመን፣


ሬዲዮ በ20ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ፣ ቴሌቪዥን በ1930ዎቹ
 ዘመናዊ ሚዲያ ኢንተርኔት በ1980ዎቹ ተጀመረ

 አሁን ደግሞ ኢንተርኔት ዌብ 2.0 ወደ ሁለተኛ ምእራፍ በመሸጋገር

 ፈጣንና ቀልጣፋ የመረጃ ልውውጥ

 የፈለጉት መረጃ ብቻ መርጦ መውሰድ

 ሰዎች መረጃ ተቀባይ ብቻ ሳይሆኑ መረጃ አቀባይም ሆነዋል

 ይህም የማህበዊ ሚዲያዎች እንዲፈጠሩ አደረገ


ሶሻል ሚዲያ ለድርጅታችን ያለው ፋይዳ
 የድርጅታችን መስመሮች፣ ፖሊሲዎች
ስትራቴጂዎችና ስኬቶቻችን ለማስተዋወቅ
 የድርጅታችንን ታሪክና ህዝባዊ እሴቶች ለማስተዋወቅ
 በተለይ ወጣቱ በቂ መረጃ እንዲያገኝ በማድረግ
ለሃገራችን ልማት፣ ዴሞክራሲና ሰላም የበኩሉን
አስተዋጽኦ እንዲያደርግ ማድረግ፣
 የጽንፈኛ ተቃዋሚውን እንቅስቃሴ በመከታተል
በብቃት ለመመከት
 ለምርጫ ስራችን
የስትራቴጂው መነሻ ሁኔታዎች
የሶሻል ሚዲያ ሃያልነትና ተቀባይነት እየጨመረ
መምጣቱ እንደ መነሻ
 ሶሻል ሚዲያ ሰዎች በህይወታቸው ስለሚያጋጥሟቸው የእለት
ተእለት ጉዳዮች በፎቶ፤ በፅሁፍ፤ በድምፅ፤ በተንቀሳቃሽ ምስል ወይም
እነዚህን ባጣመረ መልኩ መረጃን በነፃነት የሚቀያየሩበትና የሚጋሩበት
በኢንተርኔት አገልግሎት ላይ የተመሰረተ የሚዲያ አይነት ነው
 ይህም በተለይ የወጣቶች ቀልብ የሳበ ሚዲያ ሆኗል

 አሁን ባለው መረጃ 1.61 ቢሊዮን ዜጎች የሶሻል ሚዲያ ተጠቃሚዎች


ናቸው
 መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ሶሻል ሚዲያ የሚጠቀሙ ዜጎች
በአንድ ወር ውስጥ በአማካኝ 6 ሰዓት ከ45 ደቂቃውን የሚያሳልፉት
ፌስቡክ ላይ ነው
የቀጠለ…..የሶሻል ሚዲያ ሃያልነት
 መረጃዎች እንደሚያሳዩት በ2005 በሀገራችን 1ሚሊዮን
የሚሆን የፌስቡክ ተጠቃሚዎች ነበሩ
 በአለን የማህበራዊ ትስስር ምክኒያት የሶሻል ሚዲያ መረጃ
በሰው ለሰው ኮሙዩኒኬሽን (Interpersonal
Communication) አማካኝነት በስፋት ይሰራጫል
 የሶሻል ሚዲያ አይነቶች እየተበራከቱ ይገኛል፡፡ ዋና ዋናዎቹ
ፌስቡክ፣ ቲዊተር፣ ብሎግ፣ ዩቲዩብ፣ ማይስፔስ፣ ጎግል
ፕላስ፣ ሊኒክዲን
 በአለም አቀፍ ደረጃ ከሶሻል ሚዲያ አይነቶች ሁሉ ንቁ
ተሳትፎ የሚደረግበት የሚዲያ አይነት ፌስቡክ ሲሆን
ቲዊተር ይከተላል
 የሶሻል ሚዲያ አካውንት ካላቸው ግለሰቦች መካከል ከፌስቡክ
62 በመቶ ያክሉ ንቁ ተሳታፊ ሲሆኑ ከቲዊተር ባለ
የቀጠለ…..የሶሻል ሚዲያ ሃያልነት
 ሶሻል ሚዲያ ለፖለቲካ ሞብላይዜሽንና ለምርጫ ቅስቀሳ በስፋት እየዋለ
ይገኛል
 የፖለቲካ ፓርቲዎችና መሪዎች ይህን አዲስ ሚዲያ ይዞት የመጣውን ፈተና
ለመቋቋም የሚያደረጉትን ጥረት ያክል የሚሰጣቸውን እድሎች አሟጠው
ለመጠቀም ስልቶችን ነድፋው በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛሉ
 ከተለምዶ ሚዲያው እየራቀ ላለው ወጣት ሃይል የፖለቲካ ስራዎች
ቅስቀሳንና በተለይም በምርጫ ወቅት የምረጡኝ ቅስቀሳን ለማስተላለፍ
ሶሻል ሚዲያውን በስፋት መጠቀም ነው
 ሶሻል ሚዲያ በምርጫ ወቅት ትልቅ አቅም መሆኑ የተረጋገጠው ከ2008ቱ
የአሜሪካ ምርጫ ወቅት ጀምሮ ነው
 በዚህ ቅስቀሳ ወቅት የባራክ ኦባማ የቅስቀሳ ቡድን ፌስቡክ፤ ማይስፔስ፤
ዩቲዩብና ሌሎች ገፆችን ይጠቀም ነበር
 በሌሎች አገሮችም እንደዚሁ

 በአፍሪካ በዚህ ረገድ የሚጠቀሰው ባለፈው አመት በኬንያ የተካሄደው


ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ
የቲዊተር ተጠቃሚ የሀገር መሪዎች ቁጥር እድገት
ጽንፈኛ ተቃዋሚው ዋና ስትራቴጂ
እያደረገው መገኘቱ እንደመነሻ
 በየወቅቱ የተለያዩ አጀንዳዎችን በመቅረፅ
መነጋገሪያ ያደርጋሉ
 ቴክኖሎጂውን በስፋት በመጠቀም ፈጣንና
በስፋት ተደራሽ ናቸው
 እርስ በርሳቸው ጥብቅ ትስስር አላቸው
 በሀገር ውስጥ ባሉትና በውጭ ባሉት ገፆች
 በሶሻል ሚዲያውና በሌሎቹ ሚዲያዎች
 በሚያራምዱት አጀንዳ
በዋነኛነት የሚያነሷቸው አጀንዳዎች
 በውሳኔዎችና ህጎች ዙሪያ የሚነሱ ርዕዮተ አለማዊ ተቃውሞዎች፤

 የመንግስት ግልበጣና የአመፅ ቅስቀሳዎች

 ከአፈፃፀም ጋር በተገናኘ የሚነሱ ከሃይማኖትና ከብሄር ጋር


የተያያዙ ቅሬታዎች

 መንግስትንና ፓርቲውን በሰብዓዊ መብት የሚከሱ አቀንቃኞች


ክሶች

 የመንግስት ባለስልጣናትን በሙስናና በብልሹ አስተዳደር የሚከሱ


ወቀሳዎች

 ከስርዓቱ ጋር መልካም ግንኙነት ያላቸውን ታዋቂ ግለሰቦችና


ሶሻል ሚዲያውን በስፋት የሚገለገሉት
 የድርጅትና የመንግስትን ስኬቶች ለማጥላላት
 የፓርቲና የመንግስት የስራ ሃላፊዎችን ስም በሃሰት
ለመወንጀል
 ስርዓቱን የሚደግፉትን ከምህዳሩ ለማስገለልና ተስፋ
ለማስቆረጥ
 በግንባሩ አባል ፓርቲዎች መካከል ግጭት ያለ አስመስሎ
ለመሳል
 በፌዴራል ስርዓቱ የአንድ ብሄር የበላይነት የነገሰ ለማስመሰል
የአካውንቶች ተጠቃሚ ቁጥር ንፅፅር

Account owened by Accounts owned by Pro


extremists Facebook Twitter government
Account Fb likes

Finote Netsanet + Millions 56,000  --- ERTA/EBC 49,500


Voice for Freedom

Blue Party 52,000 187 FBC 146,000

ECADEF 204,000 7117 WIC 8,254


Nazret Tube  --- 2871 GCAO 1,472
ESAT 310,000 8518 ENA 1,276
Ze habesha 346,000 1569 Press Agency 806
Ethiopian Review 27,000  ---- EPRDF 13,000
የሶሻል ሚዲያ አጠቃቀማችን እንደ መነሻ
 ድርጅታችን ከትጥቅ ትግሉ ጀምሮ በህዝብ ግንኙነት
ስራዎች ላይ የዳበረ ልምድ አለው
 ህዝብን ሞብላይዝ የማድረግ ልምድና ብቃት ያለው
ድርጅት ነው
 የተለምዶ ሚዲያን በመጠቀምም ጥሩ ልምድ አለው

 ቢሆንም ያስመዘገባቸውን ሁሉንም ስኬቶች በተጠናከረ


የህዝብ ግንኙነት ስራዎች ከማጀብ አንፃር ክፍተቶች
አሉበት
የቀጠለ… የሶሻል ሚዲያ አጠቃቀማችን
 ዋናው ትኩረታችን የተለምዶ ሚዲያው /conventional
media/ ሆኖ ቆይቷል
 የግሉ ሚዲያ በተለይም የግሉ የህትመት ሚዲያ ከአፈጣጠሩ
ጀምሮ ከኢህአዴግ በተቃራኒ ጎራ የተሰለፈ ነው
 የህዝብና የመንግስት ሚዲያው የአፈፃፀም ጉድለቶችን ነቅሶ
በማውጣት እንዲታረሙ ከማድረግ አንፃር ክፍተቶች
አሉበት ወጣቱን በሚፈለገው ደረጃ ይዞ የሚዘልቅ አይደለም
የቀጠለ…..ሶሻል ሚዲያ አጠቃቀማችን
 ሰፊ ቁጥር ያለው አባል ቢኖረንም ሶሻል ሚዲያ ተጠቃሚው
አናሳ ነው
 የተወሰኑ አባላት በግላቸው የሚያደርጉት ጥረት አለ

 አብዛኛዎቹም ሶሻል ሚዲያ የሚጠቀሙትም ቢሆኑ


ማህበራዊ ፋይዳው ላይ ያተኩራሉ
 አመራሩም ለሶሻል ሚዲያ ትኩረት ሲሰጥ አይስተዋል

 አሉታዊ ጎኖቹን በመምዘዝ ጎጂ ነው ብሎ የማሰብ


አመለካከትም ይታያል
 ድርጅታችን የማህበራዊ ሚዲያ ገጾችም የሉትም
ውስጣዊ ጥንካሬዎቻችን
 የቀየስናቸው መስመሮች፣ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ተጨባጭ

ስኬቶች ማስመዝገባቸዉ

 በርካታ የተማሩ ወጣት አባላትና ደጋፊዎችን ማፍራታችን

 በለውጥ ሰራዊት መልኩ ህዝብን የማነቃነቅ አቅም መገንባታችን

 በየደረጃው ተልእኮ መፈጸም የሚችል አመራር፣ ፈጻሚ አካልና

አደረጃጀት መገንባታችን
ውስጣዊ ድክመቶቻችን
 ሶሻል ሚዲያ የመጠቀምና የመምራት አቅማችንና
ልምዳችን ውስን መሆኑ
 መረጃዎችን ቀድሞ በመስጠት አጀንዳ በመቅረፅ ረገድ
ያለን አቅም አናሳ መሆን
 የአዲሱ ሚዲያን ኃያልነት በአግባቡ ተገንዝበን ወደ
ተጨባጭ ተግባር አለመግባታችን
 በዋናዋና ሀገራዊ አጀንዳዎች ዙሪያ አሁንም ብሔራዊ
መግባባት አለመፍጠራችን
ውጫዊ መልካም አጋጣሚዎች
 ኢህአዴግ ልማትን ማረጋገጥ የሚችል ድርጅት መሆኑ የጋራ

መግባባት እየተፈጠረበት መምጣቱ

 ህዝባችን ለድርጅታችን ያለው ድጋፍና እምነት እየተጠናከረ

መምጣቱ

 መልእክት በስፋት ለማስተላለፍ የሚያስችል ቴክኖሎጂ መስፋፋቱ

 የሚዲያ ነፃነት የተረጋገጠበት ህገ መንግስታዊ ስርዓት መኖሩ

 የተማረ የሰው ሃይል በስፋት መፍጠራችን


ውጫዊ ስጋቶች
 የኒዮሊበራል ዘመቻው አሁንም ቢሆን ያልበረደልን መሆኑ
 የኪራይ ሰብሳቢነት የፖለቲካል ኢኮኖሚ በከተሞች
የበላይነቱን የያዘ መሆኑ
 ፅንፈኛና አክራሪ ኃይሎች በእያንዳንዷ ስኬታችን
የሚያካሂዱት የማጥላላት ዘመቻ እንደቀጠለ መሆኑ
 በአገራችን ሚዲያ ያሉ ችግሮች
 የሶሻል ሚዲያው ትክክለኛና ትክክለኛ ያልሆነ መረጃ
በስፋት የሚሰራጭበት መሆኑ
ትኩረት የሚሹ መሰረታዊ ጉዳዮች (Critical Issues)
 ከአመለካከት አኳያ በሶሻል ሚዲያ አስፈላጊነትና ጠቀሜታ ላይ
አመራሩና አባሉ የሚሰጠው ትኩረት አናሳ መሆኑ
 በሃሳብ ትግሉ የአጀንዳ ፈጣሪነትና የመሪነት ሚናችን አናሳ መሆን
 በሶሻል ሚዲያው ውጤታማ የሚያደርገን አስፈላጊው
አደረጃጀትና አሰራር ያለመኖር
 ቴክኖሎጂውን በሚፈለገው ደረጃ ጥቅም ላይ ለማዋል የክህሎት
ችግር መኖሩ
የስትራቴጂው ራዕይ

በሶሻል ሚዲያ ምህዳሩ


የልማታዊና ዴሞክራሲያዊ
አስተሳሰቦቻችን
የበላይነት ተረጋግጦ ማየት
አላማዎች
የልማታዊና ዴሞክራሲያዊ አስተሳሰቦች የበላይነት
ማረጋገጥ የሚችል የሶሻል ሚዲያ ሰራዊት መገንባት

በኢህአዴግ መስመሮች፣ ፖሊሲዎች፣ ስኬቶችና


እሴቶች ላይ የጋራ ግንዛቤ እንዲያዝባቸው ማድረግ

የጽንፈኛ ተቃዋሚውን አፍራሽ እንቅስቃሴ


ማጋለጥና መመከት
ስትራቴጂ አንድ:- የሶሻል ሚዲያ ሰራዊት መገንባት
ግቦች
 የተቀናጀና የተሳሰረ አደረጃጀትና አሰራርና መፍጠርና በቀጣይነት
ማጠናከር
 ቀጣይነት ያለው የአቅም ግንባታ ስራ በመስራት ብቃት ያለው
የሶሻል ሚዲያ ሰራዊት መገንባት

የስትራቴጂው አቅጣጫዎች
 በወጣቶች ላይ ትኩረት አድርጎ መስራት

 በማእከላዊ ኮማንድ ፖስት የሚመራ አደረጃጀት መከተል

 ቀጣይነት ያለው የአቅም ግንባታ ስራ መስራት

 መልካም ልምዶችን የመቀመርና የማስፋት አቅጣጫ መከተል


ስትራቴጂ ሁለት፡- የተለያዩ የሶሻል ሚዲያ ቴክኖሎጅዎችን ለአላማ ማስፈፀሚያ
ግብ ጥቅም ላይ ማዋል

 በተለያዩ ስሞች በርካታ ገፆችን በመክፈት በሶሻል ሚዲያ


ተደራሽነታችንና ተቀባይነታችን ማስፋት
የስትራቴጂው አቅጣጫዎች
 ብዙ ተጠቃሚዎች ላሉት የሶሻል ሚዲያ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ
መስራት፣
 ከሶሻል ሚዲያ ጋር የተያያዙ አዳዲስ ቴክኖሎጅዎችንና ስልቶችን
እየተከታተሉ ጥቅም ላይ ማዋል፣
 በድርጅቱ የሚከፈቱ የሶሻል ሚዲያ ገጾች እርስ በእርሳቸው
እንዲሁም ከድረገጻችን ጋር ተሳስረው ጥቅም ላይ የሚውሉበትን
አቅጣጫ መከተል፣
ለጊዜው ትኩረት አድርገን የምንሰራው በፌስቡክ ፣ በቲዊተር፣
ዩቲዩብ እና ብሎግ ላይ ይሆናል
ስትራቴጂ ሶስት፡- መልእክትን መሰረት ያደረገ ቀጣይነት
ያለው መረጃ
ግቦች
 ተከታታይና ቀጣይነት ያለው መልእክቶችን በማሰራጨት
የድርጅታችን መስመሮች፣ ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች እንዲሁም
ስኬቶቻችን በስፋት ማስተዋወቅ፣
 የኢህአዴግ ታሪካዊ ጉዞና በሂደት ያዳበራቸው ህዝባዊ እሴቶች
በቀጣይነት ማስተዋወቅ
የስትራቴጂው አቅጣጫዎች
 በታቀደና በተደራጀ ሁኔታ መልእክቶች በመቅረጽ እንደየሶሻል
ሚዲያው ሁኔታ የተለያዩ ፎርማቶችን በመጠቀም ማሰራጨት፣
 መረጃዎችን ወቅታዊ የማድረግና በየጊዜው አዳዲስ መረጃዎችን
በስፋት ማሰራጨት፣
 በተሰራጩ መልእክቶችና መረጃዎች ግብረ መልስ የማሰበሳብና
ለቀጣይ ስራ እንደ ግብአት መጠቀም፣
ስትራቴጂ አራት፡- የጽንፈኛ ተቃዋሚውን አፍራሽ እንቅስቃሴ ማጋለጥና በብቃት
መመከት
ግብ
 በአገር ውስጥና በውጭ የሚገኙ ድረ-ገፅና ሶሻል ሚዲያ በንቃት
በመከታተል ድርጅታችን ላይ የሚያቀርቧቸው ዘገባዎች ላይ ትንተና
በማካሄድ አወንታዊ መልዕክቶችን ማጉላትና አሉታዊ መረጃዎችን
መመከት
የስትራቴጂው አቅጣጫዎች
 ሁሉንም የጽንፈኛ ተቃዋሚው አሉባልታ የማስተባበልና የማጋለጥ
ስራ እንስራ ማለት የማይቻልና ፋይዳ የሌለው በመሆኑ በዋና ዋና
ጉዳዮች ላይ ብቻ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ያስፈልጋል፣
 የአላማ ትስስር ሳይኖራቸው ኢህአዴግን ለማጥላላት ብለው
የሚወዳጁትን አካላት ድርጊታቸውን የማጋለጥ እቅጣጫ መከተል
ያስፈልጋል፣
 የሚያናፍሱትን አሉባልታ በበቂ መረጃ በማፍረስ ማንነታቸውን
የማጋለጥ አቅጣጫ መከተል ይኖርብናል፡፡
የኢሕአዴግ የሶሻል ሚዲያ
የአሰራር ስነ ምግባር
እንደ መርህ የምንከተላቸው

 ከድርጅታችን መስመርና ፖሊሲ የተጣጣመ ሃሳብ


ማራመድ
 በትክክለኛ መረጃ ላይ የተመሰረተ የሃሳብ ትግል ማድረግ
 አሳታፊ የሃሳብ ትግልና የመረጃ ልውውጥ ማድረግ
 የተሳሳተም ሃሳብ ቢሆን ተገቢውን ክብር መስጠት
 የተደራጀ መልእክት መሰረት ያደረገ የሃሳብ ትግል
 በዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ትኩረት መስጠት
እሴቶች

ተደራሽነት ተጠያቂነት ትክክለኛነት

ዝግጁነት ጥንቃቄ ቁርጠኝነት

ተወዳዳሪነት ትብብር ታማኝነት

እውቅና የአላማ
DO’S

 የሚለዋወጡ ሁነቶችን ታሳቢ በማድረግም መረጃን ማዳበር

 መረጃዎች ላይ እሴት ጨምሮ ማቅረብ

 ከባለድርሻዎች ጋር በጥብቅ መቆራኘት

 ባለን አቅምና ግብዓት ተልዕኮን መፈፀም

 ወጥ የሆነና በቀላሉ የሚታወቅ የአቀራረብ ስልት መከተል

 አንድን ይዘት በተለያዩ የመልዕክት ማስተላለፊያ አግባቦች ማስተላለፍ ጥረት

 አንባቢዎችንና ተመልካቾችን ማክበር

 ስህተት ከፈጠርን ከማንም በፊት ቀድምን ራሳችን ማስተካከል

 የገፆቻችንን ደህንነት መጠበቅ


DO NOT’S

ድርጅታዊም / መንግስታዊ ሚስጥራዊ መረጃ ለሶሻል ሚዲያ አገልግሎት

ያለማዋል

ፖለቲካዊ ፋይዳ በሌላቸው / ፋይዳቸው ዝቅተኛ በሆነ ክርክሮች ጊዜን

ያለማባከን

ከፀያፍና አስነዋሪ መልክቶች መታቀብ

ከስነምግባር የወጡ አስተያየቶችን ማስወገድ

ዘርን፤ ብሄርን ወይም ሃይማኖትን መሰረት አድርገው ለግጭት የሚያነሳሱ

ወይም የሚያነሳሱ ተደርገው ሊወሰዱ የሚችሉ መልዕክቶችን

ከማስተላለፍ መቆጠብ
የድጋፍና ክትትል ስርዓት
የድጋፍ አግባብ

የእለት ተዕለት ስራን ማዕከል አድርጎ በተልዕኮ ማብቃት

መልካም ተሞክሮዎችን ለሁሉም ማዳረስና የተሻለ አፈፃፀም ላላቸው


እውቅና መስጠት

በአደረጃጀቶች መካከል ፈጣንና የማይቆራረጥ የመረጃ ልውውጥ


ማድረግ

በስራ ላይና ከስራ ውጭ በሚሰጡ ስልጠናዎች አቅምን በቀጣይነት


መገንባት
የክትትል አግባብ

የኢሕአዴግ ም/ቤት ፅ/ቤት የሶሻል ሚዲያ ሰራዊቱን እንቅስቃሴ


በበላይነት ያስተባብራል

ሁሉም አደረጃጀቶች እንደራሳቸው ተጨባጭ ሁኔታ ቋሚ


የሪፖርትና የግምገማ ጊዜዎችን ይወስናሉ

በሂስና ግለ ሂስ መድረኮች የአባላት መገምገሚያ ነጥብ ይሆናል

የሶሻል ሚዲያውን ሰራዊትና ኮር አመራሩን የሚያሳትፍ ጠቅላላ


ውይይት በ6 ወር አንድ ግዜ ይካሄዳል
አመሰግናለሁ!

You might also like