You are on page 1of 8

የቤ/ጉ/ክ/ቴ/ሙ/ኢ/ል/ቢሮ የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ

የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ


I. አጠቃላይ መግለጫ
የመስሪያ ቤቱ ስም የሥራ መደቡ መጠሪያ የሥራ ዘርፍ/የሥራ ሂደት
የቤ/ጉ/ክ/መ/ቴ/ሙ ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ የስራ ዕድል ፈጠራና የስራ ዕድል ፈጠራ ዳይሬክቶሬት
ኢንተርፕራይዞች ልማት ዳይሬክተር

የቅርብ ኃላፊ የሥራ መደብ /ተጠሪነት የሥራው ደረጃ የሥራው ኮድ


ቢሮ ኃላፊ XVII

መስሪያ ቤቱ የሚገኝበት ቦታ
አሶሳ
II. የሥራ መደቡ ዋና ዓላማ፣ከሥራ መደቡ የሚጠበቁ ውጤቶችና ተግባራት
2.1. የሥራ መደቡ ዓላማ፡-
የዳይሬክቶራቱ ሥራ በማቀድ፣ በመምራት፣ በመከታተልና በመገምገም እንዲሁም የህግ ማዕቀፍ፣ የስትራቴጂዎች፣ የፖሊሲዎች
የመመሪያና የደንብ ዝግጅት፣ የጥናትና ምርምር፣ የትብብርና ግኙነት፣ የሥራ ዕድል አማራጮችንና የሥልጠና ሥራዎችን በመምራት
በመከታተልና በመገምገም የሥራ ዕድል በመፍጠር ድህነትን ለመቀነስ እንዲያስችል የኢንዱስትሪው ዘርፍ ለሀገር የሚያሰገኘው
እኮኖሚያዊና ማህበራዊ ጠቀሜታ ማሳደግ ነው፡፡
2.2. ከሥራ መደቡ የሚጠበቁ ውጤቶችና ተግባራት
ውጤት 1፡ የዳይሬክቶራቱ ሥራ ማቀድ፣ መምራት፣ መከታተልና መገምገም
 የሥራ ክፍሉን እቅድ ያዘጋጃል፣ ያስተባብራል፣ ይመራል፣ ይተገብራል፣ ተግባራዊነቱን ይከታተላል፣ ይገመግማል፣ የአፈጻጸ
ሪፖርት ለሚመለከተው ያቀርባል፣
 የሥራ ክፍሉን ባለሙያዎች የአቅም ክፍተት በመለየት አቅማቸው የሚገነባበትን ሁኔታ ያመቻቻል፣
 የሥራ ክፍሉን ባለሙያዎች የውጤት ተኮር ዕቅድ ያዘጋጃል፣ ይከታተላል፣ ይገመግማል፣ የሥራ አፈፃፀም ውጤታቸውን ይሞላል
 በስራ ሂደት ውስጥ የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን ይፈታል፣ ሙያተኞች በስራ ላይ የሚያጋጥማቸውን አለመግባባት የሚፈቱበት
መንገድ ይቀይሳል።
 የተቀመሩ ምርጥ ተሞክሮ ለበላይ ኃላፊ ወይም ለማኔጅመንት አባላት በማቅረብ ያስገመግማል፣
 የዳይሬክቶሬቱን ስራ ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እንዲሰራ ያደርጋል፣
 ለሥራ ክፍሉ የሚያስፈልጉ ግብአቶች እንዲሟሉ ያደርጋል፣ ለታለመለት ዓላማ በአግባቡ መዋሉን ይከታተላል፣
 በስራ ሂደት ውስጥ የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን ይፈታል፣ ባለሙያዎች በስራ ላይ የሚያጋጥማቸውን አለመግባባ
የሚፈቱበትን መንገድ ይቀይሳል።
ውጤት 2፡ በዘርፉ የስራ እድል ፈጠራና ተወዳዳሪነት ላይ ግብአት ሊጨምሩ የሚችሉ ጥናቶች እና የአሰራር መመሪያዎች
እንዲዘጋጁ ያደርጋል ፣ይገመግማል፣ያረጋግጣል
 በኢንተርፕራይዞች ልማት ተወዳዳሪነት ላይ እንቅፋት የሆኑ ጉዳዮችን በመለየት ጥናቶች እንዲካሄዱ ያደርጋ
የጥናቶቹን ውጤት ገመግማል፣ያረጋግጣል፣
 በሥራ እድል ፈጠራ ላይ አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎች እንዲሰበሰቡ ያስተባብራል፣ እንዲተነተን፣ እንጠናቀርና እንዲደራጅ
እንዲሁም ለተጠቃሚዎች እንዲሠራጭ የአሠራር ስልት ይቀይሳል፡፡
 የእሴት ሰንሰለት ጥናት መርሃ ግብር እንዲዘጋጅ ያደርጋል ፣አጥኚ ቡድኑን ያዋቅራል ሂደቱንም ይከታተላል ፤ያረጋግጣል
 በየደረጃው ያሉ የአሰራር ክፍተቶች ጥናትን መሰረት በማድረግ የተለያዩ ስልቶችን ይነድፋል፣ መመሪያዎች

1
የቤ/ጉ/ክ/ቴ/ሙ/ኢ/ል/ቢሮ የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ

ማኑዋሎች ያዘጋጃል፣ እንዲጸድቁ ያደርጋል፣


 በውጭ ባለሙያ ለሚጠኑ ጥናቶች ቢጋርና የውል ሰነድ እንዲዘጋጁ ያደርጋል፣ጥናቱን ይከታተላል፣ የጥናት ሰነዱ የተሟ
መሆኑን ያረጋግጣል፣

 በየደረጃው ያሉ የአሰራር ክፍተቶች ጥናትን መሰረት በማድረግ የተለያዩ ስልቶች እንዲነደፉ ያደርጋል መመሪያዎች
ማኑዋሎች እንዲዘጋጁ ያደርጋል፣ የተዘጋጁትንም እንዲጸድቁ ያደርል፤
 ጊዜያዊ ስራ ዕድል ወደ ቋሚ ለመቀየር የሚያስችሉ ጥናቶች እንዲጠኑ ያደርጋል ፣ውጤቱንም ያረጋግጣል፣

ውጤት 3 ኢንተርፕራይዞችን ለማጠናከር የሚረዱ የተለያዩ ረቂቅ ሰነዶች እንዲዘጋጁ ያደርጋል ፣ይገመግማል
 የጨርቃ ጨርቅ፤ ቆዳና የቆዳ፤እንጨትና ብረታ ብረት፣የከተማ ግብርናና አግሮ ፕረሰሲግ ውጤቶች የዕድገት ደረጃን
ታሳቢ ያደረጉ ለድጋፍ ማዕቀፎች ዝግጅት የሚረዱ መረጃዎችን በመጠቀም ረቂቅ ሰነዶች እንዲዘጋጁ
ያደርጋል፣ይገመግማል፣
 የዘርፉን ዝርዝር የፕሮጀክት ፕሮፋይል ሀሳቦችን በማፍለቅ የትንተና ሥራ እንዲከናወን ያደርጋል፣

 ከሃገር ውስጥና ከውጭ ሀገር ምርጥ ተሞክሮዎችን ይቀምራል፣ እንዲቀመሩ እና እንዲስፋፉ ያደርጋል፣ስራውንም
ይገመግማል፣
 በኢንተርፕራይዞች የተለዩ የቴክኖሎጂ ችግሮች እና ምርት ሊጨምሩ የሚችሉ አዳዲስ ሃሳቦችን በማፍለቅ በከፍተኛ
ትምህርት ተቋማት እና በዘርፍ ኢንስቲትዮቶች እንዲፈቱ ያደርጋል፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲኖርም በቅርበት
ይከታተላል፣

ውጤት 3 የጨርቃ ጨርቅ፤ ቆዳና የቆዳ፤እንጨትና ብረታ ብረት እና የከተማ ግብርናና አግሮ ፕረሰሲግ ውጤቶች ዘር
ተወዳዳሪና ቀጣይነት ያለው እድገት እንዲያመጣ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር መስራት፡፡

 ስታንዳርድ ያልወጣላቸው ምርቶች በመለየት ስታንዳርድ እንዲወጣላቸው ያስተባብራል፣

 ኢንተርፕራይዞች በገበያ ውስጥ ተወዳዳሪ እንዳይሆኑ የሚያደርጋቸውን የተለያዩ ተግዳሮቶች ከሚመለከተው አካል ጋር በመሆ
ይፈታል፣
 ሞዴል ኢንተርፕራይዞች ተለይተው አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያገኙ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ተገቢውን ክትትል ያደርጋል
 የጨርቃ ጨርቅ፤ ቆዳና የቆዳ ውጤቶች ዘርፍ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ከተለያዩ ቦታዎች የሚገኙ የማምረ
መሣሪያዎችንና ምርቶች የሚፈበረኩበትን የቴክኖሎጂ አቅርቦት ተለይተው እንዲቀቡ ያስተባብራል፣

ውጤት 4 ኢንተርፕራይዞች ቀጣይነት ያለው እድገት እንዲያመጡ ተከታታይና ችግር ፈቺ የሆነ የድግፍና ክትትል ስራዎች
በመገምገምና፣በማረጋገጥ ውሳኔ መስጠት

 ኢንተርፕራይዞች የመሣሪያ ሊዝ ብድር ተጠቃሚ እንዲሆኑ የማምረቻ መሣሪያ ዓይነቶችን ዝርዝር መግለጫና ብዛ
በየጊዜው እንዲዘጋጁ በማድረግ፣ የመሳሪያዎቹን ምርታማነት ሁኔታ የክትትል ስራዎችን ይገመግማል፣

 በድጋፍ ማዕቀፍ አተገባበር ላይ ስልጠናዎች እንዲሰጡ ያደርጋል፣ አፈፃፀሙንም ይከታተላል፣ ውጤቱ


2
የቤ/ጉ/ክ/ቴ/ሙ/ኢ/ል/ቢሮ የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ

ይገመግማል፣ያረጋግጣል፣

 ስታንዳርድ ያልወጣላቸው ምርቶች በመለየት ስታንዳርድ እንዲወጣላቸው ያስተባብራል፣

 ሞዴል ኢንተርፕራይዞች ተለይተው አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያገኙ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ተገቢውን ክትትል ያደርጋል
 ዘርፉ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ከተለያዩ ቦታዎች የሚገኙ የማምረቻ መሣሪያዎችንና ምርቶች የሚፈበረኩበት
የቴክኖሎጂ አቅርቦት ተለይተው እንዲቀቡ ያስተባብራል፣
 ኢንተርፕራይዞች በገበያ ውስጥ ተወዳዳሪ እንዳይሆኑ የሚያደርጋቸውን የተለያዩ ተግዳሮቶች ከሚመለከተው አካል ጋር በመሆ
ይፈታል፣

 በዘርፉ የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ከመካከለኛና ከፍተኛ ኢንዱስትሪዎች ጋር የግብአትና የምርት ትስስር እንዲኖራቸው አቅጣጫ ያስቀምጣል፣ ይከታተላ
ይገመግማል

 ከኢንተርፕራይዞች የሚመጡ የተለያዩ የፈጠራ ስራዎችን ተግባራዊ እንዲሆኑ ያደርጋል፣

 ከፈጻሚ አካላት ጋር በመሆን በየደረጃው ለሚገኙ አደረጃጀቶች ድጋፍና ክትትል ስራዎችን ይገመግማል፤

 ከግብዓት እስከ ተጠቃሚ ድረስ ያለውን የምርት ሂደት የእሴት ሰንሰለት ተመጋግበው መፈጸሙን ይከታተላል፣ያረጋግጣል፣

 በብሄራዊ ደረጃ የፀደቁ ስታንዳርዶችን ኢንተርፕራይዞች መጠቀማቸውን ይከታተላል ፣አፈጻጸሙንም ይገመግማል፣

 ኢንተርፕራይዞች የፋይናንስ፣ የቴክኖሎጂ ማስተዋወቅና የምክር አገልግሎት ከአስፈፃሚ ተቋማት ማግኘታቸው


ይከታተላል፣
 ከሚመለከታቸዉ ተቋማትና የስራ ክፍሎች ጋር በመተባበር የስራዎችን አፈጻጸም እና ውጤታማነት ለመመዘ
የሚካሄዱ የክትትል እና ግምገማ ሂደቶችን ይቀይሣል፣ ይመራል፣ ያስተባብራል፤
 በጨርቃ ጨርቅ፤ ቆዳና የቆዳ፣በእንጨትና ብረታ ብረት እና በከተማ ግብርናና አግሮፕሮሰሲግ ውጤቶች ላይ የተሰማ
አንቀሳቃሾች ምዘናን ይከታተላል፣ይገመግማል ፣ያረጋግጣል

ከቴክኒክና ሙያ ተቋማት፣ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና ከምርምር ተቋማት ጋር በመተባበር ኢንተርፕራይዞች የአዳዲ
ቴክኖሎጂዎች ተጠቃሚ የሚሆኑበት ሁኔታ እንዲመቻችያደርጋል፣ ያስተባብራል፣ አፈጻጸሙን ይከታተላል፡፡
ውጤት 5፡ የጥናትና ምርምር ሥራዎችን መከታተልና መገምገም

 የኢንተርፕራይዞች የማምረቻ መሣሪያና የምርት ጥራት ደረጃን ማሻሻል የሚችሉ ችግር ፈቺ ጥናቶችን ያጠና
እንዲጠኑ ያስተባብራል፣
 በሥራ ዘርፉ የተጠኑ ጥናቶችን ይመራል ይገመግማል፣ አስተያየት ይሰጣል፣ የተመረጡት ስራዎች በተለያዩ አገር አቀፍ
አህጉር አቀፍ መድረኮች እንዲቀርቡ በታዋቂ አለም አቀፍ ጆርናሎች ላይ እንዲታተሙ ያደርጋል፣
 በየጊዜው እየተጠኑ የሚቀርቡ ጥናቶች ወደ ተግባር የሚለወጡበትን መንገድ አቅጣጫ ይቀይሳል።
 በሥራ እድል ፈጠራ ላይ እንደ ሀገር የተጠኑ ጥናቶችን ተግባራዊ እንዲሆኑ ያስተባብራል፣ የጥናት ውጤቶ
ለተጠቃሚዎች እንዲሠራጭ ያደርጋል፣
 በኢንተርፕራይዞች የተለዩ የቴክኖሎጂ ችግሮች እና ምርት ሊጨምሩ የሚችሉ አዳዲስ ሃሳቦችን በማፍለቅ በከፍተ
ትምህርት ተቋማት እና በዘርፍ ኢንስቲትዮቶች እንዲፈቱ ያደርጋል፣ ያስተባብራል፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲኖር
በቅርበት እንዲሰራ ይከታተላል ይመራል፡፡

3
የቤ/ጉ/ክ/ቴ/ሙ/ኢ/ል/ቢሮ የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ


በአግሮፕሮሰሲንግና በከተማ ግብርና ዘርፎች በውጭ ባለሙያ የሚጠኑ ጥናቶችን ያስተባብራል ምቹ ሁኔታ እንዲፈጠ
ያመቻቻል፣
ከውጭ ሀገር የሚገቡ ምርቶችን የሚተኩና ወጪ ምርቶችን ለማምረት የሚያስችሉ የፕሮጀክት ፕሮፖዛሎችን ከሚመለከታቸው ጋ
በመሆን እንዲዘጋጅ ያደርጋል፣
ውጤት 6፡ የሥራ ዕድል አማራጮችን፣ የሥልጠና ሥራዎችን መምራት፣ መከታተልና መገምገም

 በተለያዩ የዘርፉ ልማት ተሰማርተው ለሚሰሩ ኢንተርፕራይዞች የሚሆን የሥራ እድል አማራጮች እንዲ
ያስተባብራል፣ የሥራ እድል ፈጠራ ሥራን በኃላፊነት ይመራል፣
 በማኑፋከቸሪግ፣ኮንሰትራክሽን፣አገልግሎትና ንግድ፣በአግሮፕሮሰሲንግና በከተማ ግብርና ዘርፍ ተከታታይ ትምህርት
ሰልጠናዎች እንዲሰጡ ያደርጋል፣ ሂደታቸውንም ይቆጣጠራል።
 የማኑፋከቸሪግ፣ኮንሰትራክሽን፣አገልግሎትና ንግድ፣አግሮፕሮሰሲንግና ከተማ ግብርና ዘርፍ ስልጠናዎችን በየደረጃ
በወጣው መመሪያ እና ደንብ መሰረት ተፈጸጻሚ መሆኑቸውን ይከታተላል ያስፈጽማል ይመራል።
 የእሴት ሰንሰለትን መሠረት በማድረግ በማኑፋከቸሪግ፣ በኮንሰትራክሽን በአግሮፕሮስሲግና በከተማ ግብርና ሥራዎች ላ
ለተሰማሩ ኢንተርፐራይዞች በፍላጐታቸው ላይ የተመሠረተ የሥልጠና፣ የፋይናንስ የቴክኖሎጂና የምክር አገልግሎ
ከድጋፍ ሰጪ ተቋማት እንዲያገኙ ያስተባብራል ይከታተላል፡፡
 በአግሮፕሮሰሲንግና በከተማ ግብርና ዘርፍ የተሠማሩ ባለሀብቶችና አገልግሎት ሰጪዎችን ክህሎቶቻቸውን እንዲያዳብ
በሥራ አመራርና በፈጠራ ሥራዎች ሥልጠና የሚያገኙበትን ሁኔታ ያመቻቻል፡፡
 ኢንተርፕራይዞች በገበያ ውስጥ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የሚያስችላቸው ደረጃም ከሚመለከተው አካል ጋር በመሆ
እንዲዘጋጁ ያስተባበራል፣ የተዘጋጁ ደረጃዎችንም እንዲጠቀሙና በደረጃዎቹ ላይ እና በጥራት ላይ ኢንተርፕራይዞ
ግንዛቤ እንዲኖራቸው ያስተባብራል፡፡

III. የሥራው ባህሪ መግለጫዎች


3.1 የሥራ ውስብስብነት
 ስራው የሥራ ክፍሉን ሥራ ማቀድ፣ መምራትና ማስተባበር፣በስራ ሂደት ውስጥ የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን መፍታት፣
በጨርቃ ጨርቅ፤ ቆዳና የቆዳ፣ ኮንስትራክሽን እንጨትና ብረታ ብረት፣ከተማ ግብርናና አግሮ ፕሮሰሲግ ውጤቶች ዘር
እንቅፋት የሆኑ ጉዳዮችን በመለየት ጥናቶች እንዲካሄዱ ማድረግና የጥናት ሰነዱ የተሟላ መሆኑን የማረጋገጥ፣
በየደረጃው ያሉ የአሰራር ክፍተቶች ጥናትን መሰረት በማድረግ የተለያዩ ስልቶች እንዲነደፉ የማድረግና የመገምገም፣
መመሪያዎችና ማኑዋሎች እንዲዘጋጁ የማድረግና ሰነዱ የተሟላ መሆኑን የማረጋገጥ፣ከሀገር ውስጥና በውጪ ከሚገኙ
ተቋማት ጋር በቅንጅት የሚሰራበትን መንገድ ማመቻቸት፣ ከመንግስት ግዙፍ ፕሮጀክቶችና ከመካከለኛና ከከፍተኛ ኢንዱስትሪዎች
ጋር ኢንተርፕራይዞች የግብዓትና የምርት ትስስር እንዲኖራቸው ማስተባበር፣ መምራት፣ ከቴክኒክና ሙያ፣ ከከፍተኛ ትምህርትና
ከምርምር ተቋማት ጋር በመተባበር ኢንተርፕራይዞች የአዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ተጠቃሚ የሚሆኑበት ሁኔታ እንዲመቻች፣
ችግሮች እንዲፈቱና ቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲካሄድ ማስተባበር፣ ጊዜያዊ ስራ ዕድል ወደ ቋሚ ለመቀየር የሚያስችሉ ጥናቶ
እንዲጠኑ የማድረግና የትናት ውጤቱን የማረጋገጥ፣ ከሃገር ውስጥና ከውጭ ሀገር ምርጥ ተሞክሮዎችን የመቀመር፣
እንዲቀመሩ እና እንዲስፋፉ የማድረግ፣ በኢንተርፕራይዞች የተለዩ የቴክኖሎጂ ችግሮች እና ምርት ሊጨምሩ የሚችሉ
አዳዲስ ሃሳቦችን የማፍለቅ፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲኖርም በቅርበት የመከታተል፣ ኢንተርፕራይዞች በገበያ ውስጥ
ተወዳዳሪ እንዳይሆኑ የሚያደርጋቸውን የተለያዩ ተግዳሮቶች ከሚመለከተው አካል ጋር በመሆን የመፍታት፣ የመሳሪያዎቹን

4
የቤ/ጉ/ክ/ቴ/ሙ/ኢ/ል/ቢሮ የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ

ምርታማነት ሁኔታ የመከታተል፣ ኢንተርፕራይዞች ከመካከለኛና ከፍተኛ ኢንዱስትሪዎች ጋር የግብአትና የምርት ትስስር እንዲኖራቸው አቅጣጫ
የማስቀመጥና የመከታተል፣ ከግብዓት እስከ ተጠቃሚ ድረስ ያለውን የምርት ሂደት የእሴት ሰንሰለት ተመጋግበው መፈጸሙን የመከታተል ፣ተግባራ

ያሉበት ሲሆን
 uY^ ¡”¨<” ¨pƒ ¾T>ÁÒØS< ‹Óa‹ በቂ መረጃ አለመኖር፣ የግንዛቤ እጥረት መኖሩ እና የኢንተርፕራይዞች የቁጠባ
ባህል አነስተኛ መሆኑ፣ የማኑፋክቸሪንግ ቴክኖሎጅ ዘርፍ በጅምር ላይ ያለ መሆኑ፣ ኢንተርፕራይዞች የእሴት ሰንሰለቱ
ጠብቀው ባለማምረታቸው፣ የተቀመሩ ምርጥ ተሞክሮዎችን ተቋማዊ ለማድረግ ወጥ የሆነ የመተግበሪያ ስታንዳርድ
አለመኖር፣ የመሣሪያ ሊዝ ብድር አክሲዮን ማህበሮች በአዲስ እየተቋቋሙ መሆናቸው፣ ኢንዱስትሪዎች
በኢንተርፕራይዞች ላይ ያላቸው እምነት አነስተኛ መሆኑ ፣በስራ ሂደትም የተዳራጀ መረጃ አለመኖር፤ ሪፖርቶች በወቅቱና
በአግባቡ አለመቅረብ፤ የቡድን ስሜት አለመኖር፤ በፖሊሲ ዝግጅት ወቅት የሀገሪቱ ማህበራዊ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎች
ተጽዕኖ መፍጠር፣ ሙያተኞች አስተያየቶችንና ግብአቶችን በተፈለገው መጠንና ሁኔታ ያለማካተት፣ ጥናቶች በተገቢው ጊዜ እ
ደረጃ አለመሰራት፣ ተግባራዊ አለመሆን፣ የትብብር እና የስምምነት ተፈፃሚነት የሁሉንም ባለድርሻ አካላት እኩል ትኩረት
አለማግኘት፣ በዘርፉ ያሉ ባለ ድርሻ አካላት በሚፈለገው ደረጃ ተቀናጅተው አለመሥራት፣ የውውይይትና የቅንጅት መድረኮች
በሚፈለገው መጠን አለመኖር ሲሆኑ
 እነዚህን ችግሮች ለመፍታትም፣ ለህብረተሰብ ለአጋር አካላት እና ለአስፈጻሚ አካላት እንዲሁም ለኢንተርፕራይዞች ሰፊ
ተከታታይነት ያለው ግንዛቤ እንዲፈጠር በማድረግ የአመለካከት ክፍተቶች እንዲሞሉ በማስቻል፣ ለስራው ግብዓ
የሚሆኑ የተለያዩ የመረጃ ምንጮችን መጠቀም፣ ሪፖርቶች በወቅቱና በአግባቡ የሚቀርቡበትን ስርዓት በመዘርጋት፤ የተለ
አስተዳደራዊ ዘዴዎችን በመጠቀም የቡድን ስሜት በመፍጠር ፣ በፖሊሲ ዝግጅት ወቅት የሀገሪቱ ማህበራዊ ፖለቲካዊ
ኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎች ጋር እንዲጣጣም በማድረግ፣ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ሀገራዊ ጥቅምን ባስጠበቀ መልኩ በቅንጅ
በመስራት፣ የሚሰበሰቡ ግብዓቶች እና የሚጠኑ ጥናቶች በተገቢው መንገድ ጥቅም ላይ እንዲውሉ ክትትልና ድጋፍ በማድረ
የትብብር፣ የውይይት እና የቅንጅት መድረኮች በመፍጠርና ተከታታይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎችን በመስራት፣ ጠንካ
የክትትል እና ድጋፍ ስርዓት መዘርጋት፣ የተሟላ እና ወጥ የሆነ የመረጃ ማሰባሰቢያ ስልቶችን በመዘርጋት እና እንዲዘረ
በማስተባበር፣ የተለያዩ ጥናቶችን በማጥናት፣ኢንተርፕራይዞች የቁጠባ ባህል እንዲያሳድጉ በማስተባበ
ለማኑፋክቸሪንግ ቴክኖሎጅው ዘርፍ እድገት ምቹ ሁኔታወችን በመፍጠር፣ በተሞክሮ ቅመራ ላይ ወጥ የሆ
ስታንዳርድ በማዘጋጀት፣ የእሴት ሰንሰለቱን ጠብቀው ማምረት እንዲችሉ ተገቢው ድጋፍ እንዲሰጥ በማስተባበ
የመሣሪያ ሊዝ ብድር አክሲዮን ማህበሮች እንዲስፋፉ የተለያዩ ስልቶችን በመቀየስ፣ ለኢንዱስትሪዎ
ኢንተርፕራይዞች በተግባር ጥራት ያለው ምርት አምርተው እንዲያሳዩ በማድረግ እና በማቀናጀት ችግሮቹ የሚፈ
ናቸው፡፡
3.2.1 ሥራው የሚከናወንበት አግባብ
 ስራው ፖሊሲዎችን፣ አዋጆችን፣ ደንቦችን፣ ስትራቴጅዎችን፣ ፕሮጀክቶችን፣ አቅጣጫዎችን፣ ዕቅዶችንና ¾e^ pÅ
}Ÿ}KA‹ን መሰረት በማድረግ የሚከናወን ይሆናል፡፡
3.2.2 ሥራው የሚጠይቀው የክትትልና ድጋፍ ደረጃ
 የዳይሬክቶሬቱን ግቦችን ከማሳካት አንጻር በሚያቀርበው ሪፖርት መሰረት የመጨረሻ አጠቃላይ ግምገ

5
የቤ/ጉ/ክ/ቴ/ሙ/ኢ/ል/ቢሮ የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ

ይደረግበታል፡፡

3.3 ተጠያቂነት
3.3.1 ተጠያቂነት ለሥራ ውጤት /Responsibility for Impact/፣
 የዳይሬክቶሬቱን የስራ ዕቅድ የማዘጋጀት፣ ጥናቶች እንዲካሄዱ የማድረግ፣ የጥናቱን ውጤታማነት የማረጋገጥ፤ የእሴ
ሰንሰለት ጥናት መርሃ ግብር እንዲዘጋጅ የማድረግና የመገምግም፣ የጥናት ሰነዱ የተሟላ መሆኑን የማረጋገጥ
መመሪያዎች፣ ማኑዋሎችና ረቂቅ ሰነዶች እንዲዘጋጁ የማድረግ፣ ከሃገር ውስጥና ከውጭ ሀገር ምርጥ ተሞክሮዎች
የመቀመርና እንዲስፋፉ የማድረግ፣ የተለዩ የቴክኖሎጂ ችግሮች እና ምርት ሊጨምሩ የሚችሉ አዳዲስ ሃሳቦች
የማፍለቅ፣ ኢንተርፕራይዞች የሚያጋጥማቸውን የተለያዩ ተግዳሮቶች ከሚመለከተው አካል ጋር በመሆን የመፍታ
የመሣሪያ ሊዝ ብድር ተጠቃሚ እንዲሆኑ የማምረቻ መሣሪያ ዓይነቶችን ዝርዝር መግለጫና ብዛት በየጊዜ
እንዲዘጋጁ የማድረግ፣ የመሳሪያዎቹን ምርታማነት ሁኔታ የመከታተል፣ ኢንተርፕራይዞች ከመካከለኛና ከፍተኛ ኢንዱስትሪዎች
የግብአትና የምርት ትስስር እንዲኖራቸው የስራ አቅጣጫ የማስቀመጥና የመከታተል፣በኮንስትራክሽን፣አግልግሎት፣ንግድ፣በማኑፋክቸሪግ፣ በከተማ ግብር

አግሮ ፕሮሰሲግ፣ በጨርቃ ጨርቅ፤ ቆዳና የቆዳ ውጤቶች ዘርፍ የተሰማሩ አንቀሳቃሾች ምዘናን የመከታተል እና የስራ አፈጻጸም ሪፖ
ለሀላፊው የማቅረብ፣ የቡድን መሪዎችን የሥራ አፈጻጸም የመገምገም ተግባራት የማከናወን ሃላፊነት ያሉበት ሲሆን እነዚህ ተግባራ
የጥራት ደረጃቸውን ጠብቀው በአግባቡ ባይከናወኑ በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ዕድገት፣ በስራ ዕድል ፈጠራ እና በኢንዱስትሪ
ልማት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ይፈጥራል፣ በዳይርክቶሬቱ እና በተቋሙም ዕቅድ አፈጻጸም ላይ ከፍተኛ ችግር ያስከትላል፡፡
3.2.2 ተጠያቂነት ለሚስጥራዊ መረጃ፣
 የፕሮጀክት ፕሮፖዛሎች በሚስጢር መያዝ ያለበት ሲሆን ፕሮፖዛሉ በሚመለከተው አካል ውሳኔ ተሰጥቶት ይፋ ከመደረጉ በፊ
ለማይመለከተው አካል ተላልፎ ቢሰጥ በፕሮጀክቱ ተጠቃሚ መሆን የሚችሉትን ማህበረሰቦች ይጎዳል፣ በተቋሙ እና በህብረተሰቡ መካከ
አለመግባባትን እና በዳይሬክቶሬቱ ባለሙያዎች መካከል አለመተማመንን ሊያስከትል ይችላል፡፡ በማኑፋቸቱሪንግ ዘርፍ በሚከናወ
ስራዎች ላይ የኢንተርፕራይዞች የፈጠራ ስራዎች በአእምሮ ንብረት አስተዳደር የባለቤትነት መብት ሳያገኝ ለሌላ አካል አሳል
ቢሰጥ በፈጠራ ባለቤቱ እና በተቋሙ አመራሮች መካከል አለመግባባትን፣ አለመተማመንን ከማስከተሉም በላይ በፈጠራ ባለቤ
ጥቅም ላይ አሉታዊ ተጽኖ ይኖረዋል፡፡
3.4 ፈጠራ
 በማኑፋክቸሪግ፣ኮንስትራክሽን፣ከተማ ግብርናና አግሮ ፕሮሰሲግ፣አገልግሎትና ንግድ ዘርፍ የተለያዩ የቴክኖሎጂ ችግሮ
እና ምርት ሊጨምሩ የሚችሉ አዳዲስ ሃሳቦች ማፍለቅን፣ የቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲኖር የተለያዩ ሃሳቦች ማመንጨት
በዘርፉ ስራ ላይ የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች የአጠቃቀም ስልትን መቀየስንና ልዩ ልዩ ተሞክሮዎችን ማፈላለግ ና የተሸለው
የመጠቀም፣የተለያዩ ጥናቶችን በማድረግ አዳዲስ የአሰራር ስልቶች መንደፍን ይጠይቃል፡፡
3.5. የሥራ ግንኙነት /Work Communication/
3.5.1 የግንኙነት ደረጃ
 ከውስጥ ከቅርብ ኃላፊው፣ ከሚያስተባብራቸው ቡድን መሪዎች፣ ከተለያዩ ስራ ክፍል ዳይረክቶሬቶች ከው
በየደረጃው ካሉ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ መዋቅሮች፣ በዘርፉ ተጠቃሚ ከሚሆኑ እና ጉዳ

6
የቤ/ጉ/ክ/ቴ/ሙ/ኢ/ል/ቢሮ የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ

ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ግንኙነት ያደርጋል፡፡


3.5.2 የግንኙነቱ ዓላማ
 አቅጣጫ ለመቀበል፣ መመሪያ ለመስጠት፣ መረጃ ለመለዋወጥ የስራ ግብአቶችን ለማሟላት፣ ለመወያየት፣ መረ
ለመስጠትና ለመቀበል፣ ድጋፍ ለመስጠት ከውጭ ካሉት በጋራ የተያዙ ግቦችን ለማከናወን፤ ድጋፍና ክትትል ለማደረ
ጥናት ለማካሄድ፣ ስልጠና ለማስተባበር፣ ምርጥ ተሞክሮዎችን ለመቀመር፣ ለማማከርና ሪፖርት ለማድረግ ነው፣ ፡፡
3.5.3 የግንኙነቱ ድግግሞሽ
 ሥራው ከፍተኛ የሥራ ግንኙነት ማድረግን የሚጠይቅ ሲሆን ከሥራ ጊዜው 85 በመቶ ይሆናል፡
3.6 ኃላፊነት
3.6.1 ኃላፊነት ለሰው ሀብት
 አለበት
3.6.1.1 በኃላፊነት የሚመራቸው ሠራተኞች ብዛት
 ሁለት ቡድን መሪዎች፣8 ባለሙያዎችና 1 ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች የመምራት ሀላፊነት አለበት
3.6.1.2 የኃላፊነት አይነትና ደረጃ
 ስራን ማከፋፈል፣ ግብረመልስ ፣ ብቃታቸውን እንዲያሳድጉ ማድረግ፣ ክትትል እና ግምገማ ማድረግ፣ መረጃዎቸ
በወቅቱ እንዲያገኙ ማድረግ፣ ማስተባበር፣ መምራት
3.6.2 ኃላፊነት ለንዋይ
 የለበትም
3.6.3 ኃላፊነት ለንብረት
 ኮምፒዩተር፣ ጠረጴዛ፣ ወንበር፣ ሼልፍ፣ ፕሪንተር፣ ላፕቶፕ፣ ፎቶ ኮፒ፣ ፕሮጄክተር፣ ስካነር፣ ለሥራ ስለሚያስፈልገው
በአግባቡ የመያዝና የመጠቀም ኃላፊነት አለበት ግምቱም እስከ 50,000 ብር ይደርሳል፡፡
3.7. ጥረት
3.7.1 የአዕምሮ ጥረት
 ስራው የዳይሬክቶሬቱን የስራ ዕቅድ የማዘጋጀት፤ እንቅፋት የሆኑ ጉዳዮችን በመለየት ጥናቶች እንዲካሄዱ የማድረ
፤የጥናት ሰነዱ የተሟላ መሆኑን የማረጋገጥ፤ መመሪያዎችና ማኑዋሎች እንዲዘጋጁ የማድረግ፤ ረቂቅ ሰነዶ
እንዲዘጋጁ የማስተባበር፤ የፕሮጀክት ፕሮፋይል ሀሳቦችን የማፍለቅ፤ከሃገር ውስጥና ከውጭ ሀገር ምርጥ ተሞክሮዎች
የመቀመር፤ የተለያዩ ተግዳሮቶች ከሚመለከተው አካል ጋር በመሆን የመፍታት፤ ኢንተርፕራይዞች ከመንግስት ግዙፍ ፕሮጀክቶ
ከመካከለኛና ከፍተኛ ኢንዱስትሪዎች ጋር የግብአትና የምርት ትስስር እንዲኖራቸው አቅጣጫ የማስቀመጥ፣ ድጋፍና ክትትል የማድረግ፤ በስሩ ያ
ባለሙያዎችን የማስተባበር ስራዎች ያሉበት ሲሆን ከቀን የስራ ጊዜው እስከ 85% ይወስዳል፡፡

3.7.2.ስነልቦናዊ ጥረት
 አልፎ አልፎ ከቅርብ ሃላፊ፣ ከሚያስተባብራቸው ቡድን አስተባባዎች፣ በተቋሙ ካሉ ዳይርክቶሬት ዳይሬክተሮች
ከባለ ድርሻ አካላትና ከአስፈጻሚ አካላቶች ጋር ጭቅጭቆች ክርክሮች እና አለመግባባቶች የሚፈጠሩ ሲሆን ይህ
ተቋቁሞ ስራን በትዕግስት እና በተረጋጋ መንፈስ ማከናወንን ይጠይቃል፡፡
7
የቤ/ጉ/ክ/ቴ/ሙ/ኢ/ል/ቢሮ የሥራ ዝርዝር መግለጫ ቅጽ

3.7.3 የዕይታ ጥረት፣


 ሥራው የተለያዩ የቴክኖሎጅ ዲዛይኖችን የማረጋገጥ፣ ጥናቶችን፣ መመሪያዎችና ማንዋሎችን የመገምገም እ
የማረም፣ የሕግ ማቀፎችን፣ ግብረ መልሶችን በኮምፒውተር የማንበብና የመጻፍ ተግባራት ያሉበት ሲሆን ከቀ
የስራ ጊዜው 70% ይሆናል፡፡
3.7.4 የአካል ጥረት
 ስራው በመቀመጥ 70%፣ በእግር በመጓዝ 20%፣ በመቆም 10% ይከናወናል፡፡
3.8. የሥራ ሁኔታ
3.8.1. ሥጋትና አደጋ
 የለበትም
3.8.2. የሥራ አካባቢ ሁኔታ

 የለበትም

3.9. እውቀትና ክህሎት፣


3.9.1. ትምህርት
የትምህርት ደረጃ የትምህርት ዓይነት
የመጀመሪያ ዲግሪ ቴክስታይል ኢነጅነሪግ፤ቴክስታይል ኢዱኬሽን፤
ቴክስታይል/ሌዜር/ ቴክኖሎጂ፤ኢንዱስትሪያል/ኬሚካል/ ኢንጅነሪንግ፤
ማኒፋክቸሪንግ ቴክኖሎጂ፤ የእንስሳት ሳይንስ፣
በዕፅዋት ሳይንስ፣ በአግሮ ኢኮኖሚክስ እና በአግሪካልቸራል ኢንጅነሪንግ፣
በሆርቲካልቸር፣ሜካኒካል፣ ኢንደስትሪያል ኢንጅነር፣

3.9.2 ሥራውን ለመጀመር የሚያስፈልግ የሥራ ልምድ


የሥራ ልምዱ ለማግኘት የሚጠይቀው ጊዜ ልምዱ የሚገኝበት የሥራ ዓይነት
አስር ዓመት ከስራ መደቡ ጋር አግባብ ያለው የስራ ልምድ

የሥራ ትንተና ባለሙያ ሥም ፊርማ ቀን

የሥራ ዝርዝሩን ያጸደቀው የኃላፊው ሥም የሥራ መደቡ መጠሪያ ፊርማ ቀን

You might also like