You are on page 1of 70

የትምህርት ልማት ሰራዊት

ግንባታ እና የማስፋት ስትራቴጅ


ለሁሉም የዩኒቨርስቲ አመራሮችና አስተባባሪዎች
የሚጠቅም መወያያ ሰነድ
የካቲት 2007
ባህር ዳር
የትምህርት ልማት ሰራዊት ምንነት
2
የትምህርት ልማት ሰራዊት ስንል የጋራ ዓላማ እና ግብ ያላቸው
አካላት የተሰጣቸውን ተልዕኮ በውጤታማነት ለመፈጸም
ተደራጅተው የሚንቀሳቀሱበት ጥበብ ነው::
የጋራ ዓላማ እና ግብ የምንለው ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በ2017 ከአፍሪካ
ምርጥ 10 የምርምር ዩኒቨርሲቲዎች ተርታ ለማሰለፍ የምናደርገው
ርብርብ ማለት ነው፡፡
ግባችንን በአጭር ጊዜ እና አነስተኛ ወጭ ለማሳካት ደግሞ ከዚህ በፊት
መሰል ድርጅቶች የተከተሉትን ምርጥ አሰራር እና ልምድ በመቀመር
እና ከራስ ተጨባጭ ሁኔታ ጋር አጣጥሞ መተግበር እና አሰራሮችን
በማስፋፋት የስራ ባህላችን ማድረግ ይጠይቀናል ማለት ነው፡፡
ምርጥ ልምዶችን ለማስፋፋት እና ለመተግበር የድርጅቱን ሰራተኛ
እንደ ስራው ተዛማጅነት ማድራጀት እና በጠራ እቅድእንዲመራ
ማድረግ
የትምህርት ልማት ሰራዊት ግንባታ አተገባበር የለበት
ሁኔታ
3
መምህራን በኮርስ ቲም
አስተዳደር ሰራተኛው በ 1 ለ 5
ተማሪዎች በ 1 ለ 5 ተደራጅተው እቅድ አውጥተው በመንቀሳቀስ ላይ
ናቸው፡፡ የሁሉም አደረጃጀቶች ዕቅድ ሲፈተሽ መምህሩ እና የአስተዳደር
ሰራተኛው መደበኛ ስራውን እንዴት እነደሚሰራ ተማሪው ደግሞ የቤት
ስራ እንዴት እንደሚሰራ እና መቸ እንደሚገናኙ ከመተንተን ባሻገር ሌላ
ነገር የለውም፡፡
ነገር ግን የልማት ሰራዊቱ መደራጀት ዋነኛ አላማው ከላይ የተጠቀሱት
ተግባራት እንደተጠበቁ ሆነው ዋናው አላማው ግን የማስፋት
ስትራቴጅውን ለመተግበር ነው፡፡ ለማስፋት ደግሞ የሚሰፋው ነገር ተለይቶ
እና ተቀምሮ በየአደረጃጀቱ ዕቅድ መካተት አለበት ማለት ነው፡፡ ስለዚህ
የእስከ አሁኑ ጉዞአችን የጎደለው ነገር ምርጥ ልምድ መቀመር ነው፡፡ ይህ
ደግሞ ዋናውን ነገር የረሳነው መሆኑን ያስረዳናል፡፡
የትምህርት ልማት ሰራዊት ግንባታ አስፈላጊነት
4

በትምህርት ስራወቻችን ዙርያ ምርጥ ልምዶችን ወይም


ተሞክሮዎችን በመቀመር የማስፋት ስትራቴጅን በመጠቀም
የተቀመሩ ምርጥ ልምዶችን ለሁሉም ፈፃሚ አካላት
በማዳረስ የትምህርት ጥራትን ማረጋገጥ ነው፡፡
ምርጥ ተሞክሮዎችን ለማስፋፋት እና ውጤታማ
ለማድረግ ከተፈለገ ደግሞ ፈፃሚ አካላት መደራጀት ብቻም
ሳይሆን ከመደራጀት ባሻገር በጠራ የጋራ ዕቅድ አቅደው
መንቀሳቀስ ያስፈልጋል፡
በአጠቃላይ ሲታይ የልማት ሰራዊት መገንባት የሚያስፈልገው
የማስፋት ስትራቴጅውን ተግባራዊ ለማድረግ ነው፡፡
5

ማስፋፋት ሲባል………..
የማስፋፋት ምንነት…….
ማስፋፋት ስንል ምርጥነታቸው በተወሰነ
አካባቢና አካላት ደረጃ ተፈትሸው የተረጋገጡ
አሠራሮችን ወደ ሰፊ መልክዓ ምድራዊ አካባቢ
በመውሰድ በአጭር ጊዜ፣ በአስተማማኝ
ሁኔታና በዘለቄታዊነት አብዛኛውን
የህብረተሰብ ክፍል ተጠቃሚ ለማድረግ
የሚያስችል ልማታዊ መሰረት ማስያዝ
ማለታችን ነው፡፡
6
ማስፋፋት፣ በሕብረተሰቡ ዘንድ አዎንታዊ ተጽእኖ
የሚኖራቸውን ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች
በመተግበር ውጤታማና ስኬታማ ከሆኑ ተቋማት
የተገኙ ምርጥ ልምዶችን እቅድና ፕሮግራም
በመንደፍ በሁሉም አካባቢዎች ሥራ ላይ
እንዲውሉ ማድረግ ነው፡፡

7
በጥቅሉ በተቋማት ምርጥ ልምዶችን
ማስፋፋት ሲባል ከቁጥርና ከቦታ ስፋት ባሻገር
በለውጥ ትግበራ ሂደት ውስጥ በአንድ ተቋም
የታዩ ስኬታማና ሞዴል ተግባራትን በመቀመር
ከሌሎች ተቋማት ነባራዊ ሁኔታ ጋር
በማጣጣም ተግባራዊ ማድረግ ነው፡፡
8
ማስፋፋት ለምን አስፈለገ?

በአሁኑ ወቅት የማስፋፋት ስትራቴጅን መተግበር


የተመረጠበት ዋናው መሰረታዊ ጉዳይ ከድህነት የመውጣት
ጉዳይ የህልውና ጉዳይ በመሆኑ ነው፡፡
ድህነትን ለመዋጋት እና ማምለጫው መንገድ ደግሞ
እውቀት ነው፡፡
እውቀት ደግሞ የሚገኘው በትምህርት ቤቶች ነው፡፡
9
የቀጠለ…….
10

ስለዚህ ተማሪዎቻችን መምህራን የአስተዳደር


ሰራተኛው ድህነትን ማስወገድ የሚችል እውቀት
ሊገበይ ይገባል፡፡ ይህም የሚሳካው ምርጥ ልምዶችን
በመቀመር እና ለሁሉም በማዳረስ ይሆናል ማለት ነው፡፡
ለእንደኛ አይነት ታዳጊ አገር ውጤታማና ተስማሚ
ተግባራትን በመቀመር እንደማስፋፋት አዋጭ የሆነ
ነገር የለም፡፡ በአጠቃላይ የማስፋት ስትራቴጅን
መተግበር የሚከተሉት ጠቀሜታዎች ይኖሩታል፡፡
ሀ. ከኢኮኖሚ ጠቀሜታ አንጻር

ቴክኖሎጂን በፍጥነትና ተከታታይነት ባለው አኳኋን


ከአገር ውስጥም ሆነ ከውጭ በመኮረጅ ላለንበት
የእድገት ደረጃ ተስማሚ የሆነውን ቴክኖሎጅ
በጥንቃቄ መምረጥ ተገቢ ይሆናል፡፡ ይህም በአጭር
ጊዜና ባነሰ ወጪ ወደ ዩኒቨርሲቲያችን አምጥቶ
በማስፋፋትና ውጤታማነትን በላቀ ደረጃ
በማረጋገጥ፣ በጥራትና በዋጋ ተወዳዳሪ መሆን
ያስችላል፡፡
11
ለ. ከማህበራዊ ጠቀሜታ አንጻር

ለዩኒቨርሲቲው ህብረተሰብ አዳዲስ አሰራሮችን


በማቅረብና በፍጥነት በማስተዋወቅ በማህበራዊ
ዘርፎች የሚታዩ ሰፊ ጉድለቶችን ለመሙላት ፡፡
ማለትም ስራው በቡድንና በቅንጅት የሚሰራ
በመሆኑ የእርስ በእርስ ግንኙነትን እና መረዳዳትን
ያጠናክራል፡፡

12
ሐ. ከመልካም አስተዳደር አንጻር
መልካም አስተዳደርን በማስፈንና የዲሞክራሲ
ስርአትን በመገንባት ሂደት የሚደረገውን ጥረት
ለማፋጠን እና የህዝቡን እኩል ተጠቃሚነት
ለማረጋገጥ፣ እንዲሁም አገልግሎት አሰጣጡን
ቀልጣፋና ውጤታማ በማድረግ የህዝቡን የደህንነት
ዋስትና ለማረጋገጥ ምርጥ ልምዶችን በማስፋፋት
መጠቀም ወሳኝ ከመሆኑም ባሻገር ለሀገሪቱ ደንቃራ
የሆነውን የኪራይ ሰብሳቢነት አባዜ ለመዋጋት ፈር
ቀያሽ ይሆናል፡፡
13
የማስፋፋት መርሆዎች (Principles of Scaling
up)
እንደ William Easterly አቀራረብ የሚከተሉት
ይጠቀሳሉ፡-
• ስኬታማ የሆኑ ልምዶችን ማስፋፋት (Scale
up success not failure)
(ያልተለመዱና ውጤታቸው ያልታወቀ
ተሞክሮዎችን ማስፋፋት ውድቀትን ሊያመጣ
ይችላል)፡፡
14
. እጅግ አስፈላጊና ጠቃሚ ነው ብለን
ያሰብነውን ሳይሆን በተሻለ ሊሰራ
የሚቻለውን መምረጥ
(Don’t scale up what you think is
most important, scale up what you
do best)
15
. ከፍተኛ ወጪና በቀላሉ ሊገኝ የማይችል
ግብዓት የሚጠይቀውን ሳይሆን ዝቅተኛ ወጪ
የሚጠይቀውንና አስተማማኝ ግብዓት
ያለውን መምረጥ

(you can scale up only what requires


cheap, abundant inputs; you cannot
scale up something that depends on
expensive, scarce inputs)

16
• ባለው የሰው ሀይልና ማቴሪያል
በቀላሉ የማስፋፋት መርህን መከተል
(Things that you make routine
are among the easiest to scale up)

17
• ምርጥ ልምዱን በማስፋት ከተጠቀምን
በኋላ ሂደቱ ውጤታማ መሆኑን መገምገም፤

(Evaluate whether you are


successful after scaling up)

18
ምርጥ ልምድን የማስፋፊያ ዘዴዎችና ሊፈጠር
የሚችል አደረጃጀት

የማስፋፋት ዘዴዎችና አደረጃጀቶች እንደ


ተቋሞቹ ባህርይና ቴክኖሎጂ ይዘት የሚለያይ
ቢሆንም የጋራ ሊሆኑ ከሚችሉት ውስጥ
የተወሰኑት እንደሚከተለው ቀርበዋል፡፡
19
ሀ. አደረጃጀት

. የአመራርና አስተባባሪ ግብረ ሀይል


ማቋቋም (Establish the
Leadership and Coordinating
Committee )
. የባለሙያ ቡድን ማቋቋም (Establish
Expert Group)

20
ለ. የአተገባበር ስልት
. ምርጥ ልምድ ያላቸውን ተቋማት ወይም
ግለሰቦች በመምረጥ ተመሳሳይ ዓላማና ሙያ
ያላቸውን ተቋማት ወይም ግለሰቦች
አቻ ለአቻ ትምህርት እንዲሰጡ ማድረግ
(አንድ ለብዙ ወይም ብዙ ለብዙ
ተሞክሮዎችን ማስተላለፍ)
21
• የተቀመሩ ልምዶችን በዩኒቨርሲቲው
በተቀናጀና በተደራጀ ሁኔታ ወደ ሥራ
ለማስገባት የሚያስችል ኮንፈረንስ ማካሄድ፡፡

22
• የልምዱ ተጠቃሚዎችን ባሳተፈ መልኩ
ኤግዚቢሽን በህዝብ አደባባይ ወይም ምቹ
በሆነ ቦታ በማዘጋጀት በፎቶ ግራፍ፣
በግራፍ፣ ወዘተ. አስደግፎ ለእይታ በማብቃት
የህዝብ ንቅናቄ መፍጠር፤
(Exhibition Presentation)

23
• ተሞክሮዎችን በጥልቀት መምረጥና
መረዳት (Understand the Full Scale
Intended)
• የሚሰፋፉባቸውን ቦታዎች በማስተዋል
መምረጥ (Select Participating Sites)
24
• አስፈላጊ ፋሲሊቲዎችን ማሟላት
(Organize and Equip the Team) 1 ለ 5

• መተግበርና ተከታታይ ድጋፍና ክትትል


ማድረግ (Implementation and Close
Follow up)

• ሞዴል መጠቀም (Use the Model)

25
• አፈጻጸሙን መቀመርና እንደገና ማሻሻል
(Document Progress and Updating)

• ተሻሽሎ የተቀመረውን ሥራ ላይ በማዋል


ተገቢውን ክትትልና ድጋፍ ማድረግ እንዲሁም
መገምገም

26
• በትግበራው ሂደት ልምድ ካለውና ድጋፍ
ከሚሰጠው አካል ጋር የቅርብ ግንኙነት
በማድረግ አፈፃፀሙን እያሻሻሉ መሄድ

27
ምርጥ ልምድን ለማስፋፋት መሟላት ያለባቸዉ
ቅድመ ሁኔታዎች

ምርጥ ልምዶችን ለማስፋፋት


የሚከተሉትን ቅድመ ሁኔታዎች ስራ ላይ
ማዋል ይገባል፡፡
28
• አስቀድሞ በብቃት የተነደፈ እቅድ
(Adequate planning)

• የፖሊሲ ድጋፍ (Policy Support)

• የአመራር ቁርጠኝነት
(Leadership Commitment)

• ጠንካራ የግንኙነት መረብ


(Strong & Networked
29
relationship)
በአጠቃላይ የማስፋፋት ስራ ከላይ የተመለከቱትን
አቅጣጫዎች በድምር ወይም በተናጠል በመጠቀም
የተያዘውን እቅድ ወደ ላቀ ደረጃ በማድረስ በአጭር ጊዜ
በሁሉም አካባቢዎች ከፍተኛ ለውጥ የመፍጠር እንቅስቃሴን
ዕውን ማድረግ ይቻላል፡፡

በተለይም የለውጥ ትግበራን ምርጥ ልምዶች በማስፋፋት


ሂደት የተለያዩ ተለዋዋጭና ልዩ ባህርያትን ማገናዘብ ተገቢ
ይሆናል፡፡ በዚህም ውስጣዊና ውጫዊ ሁኔታዎችን በትኩረት
በማጥናትና በማጣጣም ማስኬድና የስኬታማነቱን ዘለቄታ
ማረጋገጥ ከበሳል አመራርና ባለሙያ ይጠበቃል፡፡

30
31

ለማስፋት የሚሰፋ ነገር መኖር አለበት


የሚሰፋ ነገር ደግሞ ምርጥ ልምድ ምርጥ አሰራር እንጅ ምርጥ
ውጤት አይደለም፡፡ ምክንያቱም ምርጥ ውጤት 4 ቢሆን ሁሉንም
ተማሪ 4 እንዲያመጣ ማድረግ አይቻልም፡፡ ነገር ግን ምርጥ ውጤት
ያመጣ ተማሪ ምን መንገድ ተከትሎ ነው የሚለውን ምርጥ አሰራር
በመቀመር እና ሁሉም ተማሪ እንዲተገብረው በማድረግ ተማሪዎችን
ከስነ ምግባር ጀምሮ የተሸለ እውቀት እነዲገበዩ ማድረግ ይቻላል፡፡
Peer learning is not scaling up.
በአስተዳደር ሰራተኛም ሆነ በመምህራን ዘንድ የሚሰፋ ምርጥ
ልምድ/አሰራር ሊቀመር እና ሊስፋፋ ይገባል፡፡
.

ለመሆኑ ምርጥ ልምድ ምንድን

ነው?

32
በተለያየ ወቅት ስለ ምርጥ ልምድ የፃፉ ምሁራን የተለያየ
ብያኔ አስቀምጠዋል፡፡

. ተቋማት በሥራ አፈፃፀማቸው ከሌሎች ተቋማት ጋር


ሲነፃፀሩ ለየት ብሎ የወጣ በጥናት፣ በምርምርና
በልምድ ላይ ተመስርቶ ወደ ተፈለገው ውጤት
በአስተማማኝ ሁኔታ መመራትን የሚያረጋግጥ ሥነ-
ዘዴ ነው፡፡

. የላቀ አፈፃፀም፣ የአሠራር ሂደት፣ ድርጊትና ፍፃሜ


ማለትም ነው፡፡

33
በሌላ አባባል ምርጥ ልምድ እጅግ በጣም
አነስተኛ በሆነ ወጪና ጥረት እንዲሁም
ወጥ በሆነ የአሠራር ቅደም ተከተል የላቀ
ውጤታማነት የሚመጣበት ዘዴ ነው፡፡

34
በምርጥ ልምድ ጽንሰ-ሐሳብ መሠረት ምርጥ
የሚለው ቃል የጥራት ደረጃን ብቻ የሚወክል
ሳይሆን ችግሮችን ለመፍታትና ስኬትን ለማምጣት
ጥቅም ላይ የሚውል ቴክኒካዊ የአሠራር ቅደም
ተከተልም ነው፡፡
ተከስተው የነበሩ ስህተቶች እንዳይደገሙ ማድረግ
የሚቻልበትም ስልት ነው፡፡
35
ከላይ አንደተባለዉ በርካታ ፀሐፍት ምርጥ
ልምድን በተለያየ መንገድ ገልፀውታል፡፡
ስለምንነቱ ከተጻፉት ዉስጥ ለአብነት ያህል
የተወሰኑትን እንመልከት፡-

36
Best practices are planning or
operational practices that have proven
successful in particular circumstances
and which are "used to demonstrate
what works and what does not and to
accumulate and apply knowledge about
how and why they work in different
situations and contexts" UNFPA/United Nations Population
Fund/ cited in Torres (8: 2005)

37
The achievement of best practice
refers to the way in which leading-
edge organizations are able to
manage and organize their
operations to deliver world-class
standard of performance in areas
such as cost, quality and timeliness.
Australian Government Department of Infrastructure, Transport, Regional Development and Local
Government Annual Report 2000-2001

38
“ … a specific action or set of actions
exhibiting quantitative and qualitative
evidence of success together with the
ability to be replicated and the potential
to be adapted and transferred. Best
practices represent the "Gold Standard"
of activities and tools that can be
implemented to support program
objectives."Tores(8: 2005).

39
Best Practice is a superior method or
innovative practice that contributes to the
improved performance of an organization,
usually recognized as "best" by other peer
organizations. It implies accumulating and
applying knowledge about what is working
and not working in different situations and
contexts, including lessons learned and the
continuing process of learning, feedback,
reflection and analysis (what works, how and
why). Thiyagarajan Word press፡ /Visited on March 27, 2010/
40
ጽንሰ-ሐሳቡ በተለያየ መልኩ ቢገለፅም ሁሉም
የሚያመላክቱት ምርጥ ልምድ ማለት በአፈፃፀም የላቀ
ውጤት ያስመዘገቡ ተግባራት ስብስብ ወይም
የአፈፃፀም ሂደት ነው።
ምርጥ ልምድ/ተሞክሮ ማለት ምርጥ ውጤት ማልት
አይደለም፡፡ ምርጥ አሰራር እንጅ፡፡

41
የለውጥ ፕሮግራም ምርጥ ልምድ ተብሎ
የሚፈረጅ (አመለካከት፣ ዕዉቀት፣ ክህሎት፣
አሰራር፣ አደረጃጀት፣ ወዘተ.) በአንድ ወይም ከአንድ
በበለጡ የመንግሥት ተቋማት ውስጥ ተከናውኖ
ውጤት ያመጣና ወደ ሌላ ተቋም ሲስፋፋ ምንም
ዓይነት ተጨማሪ ሃብት መጠቀም ሳያስፈልግ
ተመሳሳይ ወይም ተቀራራቢ ወደሆኑ ተቋማት
በመውሰድ ካለው ተጨባጭ ሁኔታ ጋር አጣጥሞ
በመጠቀም ከፍተኛ ስኬት ማምጣት የሚያስችል
ልምድ ነዉ፡፡
42
በአጠቃላይ ምርጥ ልምድ ሲባል የቴክኖሎጂ
ግኝት፣ አዳዲስ የሃብት አጠቃቀም እና የአሠራር
ዘዴ ድምር እንደመሆኑ መጠን ለውጡን በአንድ
ጊዜ በሁሉም ሥፍራ ለመተግበር እንደ ግብዓት
ከመሆን ባሻገር ለዜጎች አዎንታዊ ውጤት
ሊያመጣ የሚችል የለውጥ መሣሪያ ነው፡፡

43
ምርጥ ልምድ በአካባቢ እና በጊዜ አግባብነት
ላይ የተመሠረተ በመሆኑ አንፃራዊ እንጂ
ፍፁም ነው ማለት አይቻልም፤ እንዲሆንም
አይጠበቅም፡፡ ምክንያቱም በየትኛዉም ጊዜና
ቦታ ፍፁም የሆነ ምርጥ ልምድ የለምና ነው፡፡
ነገር ግን እንደ ምርጥ ልምድ የተወሰደው
የተግባራት ስብስብ በአግባቡ በሌላ አካባቢ
ከተተገበረ በወቅቱ ላሉት ችግሮች መፍትሔ
ሊሆን እንደሚችል በእርግጠኝነት መናገር
ይቻላል፡፡
44
ምርጥ ልምድ ከከፍተኛ ትምህርት አንፃር
45

ምርጥ ልምድ ከዩኒቨርሲቲዎች አንፃር ከሶስት አቅጣቻወች ሊታይ


ይገባል፡፡
1. መምህራንን ውጤታማ ከማድረግ አንፃር
2. የአስተዳደር ሰራተኞችን ውጤታማ ከማድረግ አንፃር
3. ተማሪዎችን ውጤታማ ከማድረግ አንፃር
በተጨማሪም ውጤታማነት እንዴት ሊለካ ይችላል የሚለውን ጉዳይ
አስቀድሞ መልሶ መግባት በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ስለሆነም፡-
የመምህራን ውጤት
46

ዩኒቨርሲቲውን የምርምር ዩኒቨርሲቲ ከማድረግ አንጻር የተሄደ ጉዞ


እና የመጣ ለውጥ
የምርምር ውጤቶች ለአካባቢ ልማት ያበረከቱት አስተዋፅኦ
የተማሪዎች ውጤት ስነ ምግባር የባህሪ ለውጥ እና ተወዳዳሪነት
በዩኒቨርሲቲው ፐብሊሽ የተድርገ የምርምር ጆርናል ብዛት
ዩኒቨርሲቲው የሚሰጠው የማህበረሰብ አገልግሎት መጠን እና
ብዛት እና በመሳሰሉት የሚሊካ ሆኖ ምርጥ ልምዶችንም
ስንቀምር ከላይ ባስቀመጥናቸው መስፈርቶች የተሳካላቸውን
ዩኒቭረሲቲዎችን መርጠን ያስመዘገቡት ውጤት በምን መንገድ
ተጉዘው እነደሆን በጥንቃቄ በመመረመር ይሆናል ማለት ነው፡፡ To
scale up we have to bench mark.
ከተማሪዎች ውጤት አንፃር
የተማሪዎች ውጤት በሚያስመዘግቡት
47 ውጤት/ግሬድ እና ባምጡት

የባህሪ ለውጥ ወይም ስነ ምግባር ሊሆን ይችላል፡፡


ሁሉም ተማሪ 4 ነጥብ ሊያመጣ አይችልም ነገር ግን ተቀራራቢ ዉጤት
እንዲኖረው ማድረግ ይቻላል፡፡ ስለዚህ ምርጥ ልምድ ስንቀምር
የውጤታማ ተማሪዎችን ጥሩ ውጤት ሊያስመዘግቡ ያስቻላቸውን
ልምድ ማለትም
የአጠናን ስልት/
የጊዜ አጠቃቀም
ሪፈረንስ አጠቃቀም
መረጃ አያያዝ እና የመሳሰሉትን ማዕከል አድርገን ልንቀምር እንችላለን፡፡
ከአስተዳደር ሰራተኞች ውጤት አንፃር
48

የአስተዳደር ሰራተኛው ውጤታማነት በሁለት ዋና ነገሮች መለካት


ይቻላል፡፡ አንደኛው የመማር ማስተማር ምረምር እና ማህበረሰብ
አገለግሎት የመስጠት ተግባሩ እንዳይደናቀፍ ሙሉ ድጋፍ
ለመምህራን ማድረግ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ እንከን የለሽ
የተማሪ አገልግሎት በመስጠት በዩኒቨርሲቲው ሰላማዊ የመማር
ማስተማር ሂደት በማስፈን ልንለካው እንችላለን፡፡
ስለሆነም ምርጥ ልምድ ስንቀምር አገልግሎት አሰጣጥ፤ በጀት
ክትል እና አጠቃቀም፤ የግዥ አፈፃፀም፤ እና በአጠቃላይ ቀልጣፋ
አሰራርን ከማስፍን አንፃር ውጤታማ የሆኑ ዩኒቨርሲቲዎችን
አሰራር በመፈተሸ እና ተስማሚውን በመምረጥ ይሆናል ፡፡
የምርጥ ልምድ መምረጫ መርሆዎች

ምርጥ ተሞክሮን የማላመድና የማስፋፋት ሥራ


ሲሰራ ከግምት ውስጥ ሊገቡ የሚገባቸው
ጉዳዮችን ስናነሳ የመምረጫ መርሆዎችን
ማስቀመጥ የግድ ስለሚል እንደሚከተለው
ቀርበዋል፡- 49
1. . ይሰራል ተብሎ በተቀመጠለት ጊዜ
ውስጥ ስኬታማ የመሆን መርህ፤
2. በተገልጋዩ ዘንድ አዎንታዊ ምላሽ
የማግኘት/ተገልጋይ ዜጋውን የማርካት መርህ፤
3. በመጠንና በጥራት ውጤት የማምጣት
መርህ፤
50
4. የፈጠራ ጥበብ የመጨመር መርህ፤

5. በቀላሉ መባዛት የሚችል አድርጎ


የማስማማት መርህ፤

6. ለማጓጓዝ ቀላልና ከማስተካከያው ወይም


ከማጣጣሚያዉ ጋር ወደ ሌሎች ሊሸጋገር የሚችል
መሆኑ እና
51
7. የአፈጻጸም ደረጃው ለተጠቃሚዎች
ትርጉም እንዲሰጥ የማድረግ መርህ የሚሉት
በዋናነት ይጠቀሳሉ፤
ይህን መሰረት በማድረግም ምርጥ
የተባሉ ልምዶችን መምረጥ ይቻላል፡፡

52
የምርጥ ልምድ መገለጫ ባህርያት
መገለጫ ባህርያቱ በተለያየ ወቅት የተለያየ
መስፈርት ሲቀመጥላቸው እንደቆየ ማየት ይቻላል፡፡
አንዳንድ ጸሐፍት የምርጥ ልምድ መገለጫ
ባህርያትን ሲያስቀምጡ በሚከተለዉ መልኩ
ይገልጹታል፡-
53
• ልምዱ በቀላሉ የሚሰራና የሚለካ፣ ውጤት
ሊያመጣ የሚችል፣ አግባብ ባለው ሃብትና ጊዜ
የሚከናወን መሆኑ፤
• ስራ ላይ ከሚውልበት የስራ ሁኔታ ጋር
ተስማሚ መሆኑ፤
• በሚተገበርበት አካባቢ ካለው ህብረተሰብ ባህልና
እሴት ጋር በቀላሉ የሚላመድ መሆኑ፤
54
• በማንኛውም ቦታ የመስፋፋት እድል
ያለው መሆኑ፤

• ከያገባኛል ባዮች ጋር ውጤታማ ትብብር


መፍጠር ማስቻሉና

• ልምዱ ከብሔራዊ እስከ ከባቢያዊ


መስተዳድር ያሉ አመራሮችን ድጋፍ
ማግኘት የሚያስችል መሆኑ ናቸዉ፡፡
55
ይህን በሚመለከት UNESCO (2003)
ያስቀመጣቸዉን የምርጥ ልምድ ባህርያት
እንደሚከተለው ማየት ይቻላል፡-

56
Best practices have four common characterstics:
they:-

are innovative. A Best Practice has


developed new and creative solutions to
common problems of poverty and social
exclusion.

make a difference. A Best Practice


demonstrates a positive and tangible impact on
the living conditions, quality of life or
environment of the individuals, groups or
communities concerned.57
have a sustainable effect. A Best
Practice contributes to sustained eradication
of poverty or social exclusion, especially by
the involvement of participants.

have the potential for replication. A


Best Practice serves as a model for generating
policies and initiatives elsewhere.

58
ሌሎች ጸሃፍት ደግሞ የምርጥ ልምድ ባህርያትን
በሚከተለው መልኩ ይገልጹታል።
1. የለውጡ አድማስ ሠፊ መሆኑ፤

2. ከፍተኛ የጥራት ደረጃ ያለው መሆኑ፤

3. በአቅማችን ልንገዛውና ደጋግመን


ለመጠቀም ተጨማሪ ወጪ የማያስወጣን
ሊሆን የሚገባው መሆኑ፤
59
4. ከጊዜ አኳያ ፈጣን እና ስርነቀል ለውጥ
ሊያመጣ የሚችል መሆኑ፤

5. ተፅእኖው ወይም የግብ ስኬቱ ሊቀለበስ


የማይችል እና ለረዥም ጊዜያት የሚቆይ
መሆኑ፤
60
ከላይ የተዘረዘሩት የምርጥ ልምድ መገለጫ
ባህርያት እንደሚከተለው ተብራርተው
ሊገለፁ ይችላሉ።

61
1. የለውጡ ተጽዕኖ አድማስ ሠፊ መሆን፣
የለውጡ አድማስ ሠፊ የሆነ ሲባል ለውጡ በሁለት፣
በሶስት፣ በአራት፣….. እጥፍ የሚንፀባረቅ፣
የሚጨበጥና የሚዳሠስ፤ በተወሰኑ ቦታዎች ወይም
ጥቂት የህብረተሰብ ክፍሎች ላይ ብቻ ሳይሆን ሠፋ
ወዳለ አካባቢ እና የህብረተሰብ ክፍል ሊዳረስ
የሚችል ለውጥ ማለት ነው፡፡
62
2. ከፍተኛ የጥራት ደረጃ ያለው መሆኑ፤

አንድ ውጤታማ አፈፃፀም በምርጥ ልምድነት


ሊወሰድ ከሆነ ቢያንስ ከተቋማት መካከል
ከፍተኛ የአፈፃፀም ለውጥ ያመጣ ሊሆን
ይገባዋል፡፡

63
3. በአቅማችን ልንገዛውና ደጋግመን ለመጠቀም
ተጨማሪ ወጪ የማያስወጣን መሆኑ

ምርጥ ልምድ በመጠቀም ስርነቀል ለውጥ በዘላቂነት


ማምጣት የሚቻለው አቅምን ያገናዘበ
(affordable) እና ቀጣይነት ያለው (Sustainable)
ሆኖ ከተገኘ ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ ምርጥ ልምዶችን
ለማስፋት ከወጪ አንፃር አዋጭና የተቋማትን
አቅም ያገናዘበ መሆኑን መፈተሽ ተገቢ ይሆናል፡፡
64
4. ፈጣንና ስር-ነቀል ለውጥ ሊያመጣ
የሚችል መሆኑ፣

የምርጥ ልምድ ሌላው ባህርይ ፈጣንና የማይታመን


የሚመስል ለውጥ በአጭር ጊዜ ማስመዝገብ ማስቻሉ
ነው፤ ይኸውም ዓመት የሚፈጀው በወራት፣ በቀናት፣
በሰዓታት፣ ወዘተ. ውስጥ ማረጋገጥ ማስቻሉ ነው፡፡

65
5. የግብ ስኬቱ ሊቀለበስ የማይችልና
ለረዥም ጊዜያት የሚቆይ መሆኑ፣
ከሁሉም የላቀ ለውጥ ያመጣ ምርጥ ልምድ ሲባል
ለአጭር ጊዜያት ቆይቶ ውጤት የሚያሳፍስ እና
በማግስቱ የሚፈራርስ ወይም የሚተን ማለት
አይደለም፡፡ ይልቁንም በፅኑ መሰረት ላይ የተገነባና
ለረዥም ጊዜ የሚቆይ ፋይዳ ያለው ለውጥ ማለት
ነው፡፡ 66
ምርጥ ልምዶችን ከማስፋታችን በፊት ከዚህ
በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች በጽሞና
መመልከትና በእርግጥ ተሞክሮ መሆናቸውን
መመዘን ይጠይቃል፡-

67
• ብዙ ተጠቃሚወችና ባለድርሻዎች
የረኩበትና ማረጋገጫ የሰጡት መሆኑ
• የስራው ባለቤቶች/ ባለሙያዎች ሥራው
ምርጥ መሆኑን የተስማሙበትና
ያመኑበት መሆኑ፤
• ያመጣው ለውጥ ሲመዘን ቀልጣፋና
ውጤታማ አሰራር በመፍጠር በግንባር
ቀደምትነት የሚጠቀስ መሆኑ፤
68
• የሚወሰደው ልምድ ከተመሳሳይ ተቋማት ጋር
ሲነፃፀር በተጨባጭ ብልጫ ያሳየ ስለመሆኑ
የተመሰከረለት መሆኑ እና
• ዘመኑ ከወለደው ቴክኖሎጅ ጋር አጣጥሞ
መጠቀም የሚቻል መሆኑ ልብ ሊባል ይገባል፡፡

ይሁንና ከዚህ በላይ የተጠቀሱትን ሁኔታዎች


በቅድሚያ ማረጋገጥ ሳይቻል የተገኘን ልምድ
ለማስፋፋት መሞከር ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ
ሊያመዝን ይችላል፡፡
69
70

ከዚህ በመነሳት የዩኒቨርስቲ አመራር ምርጥ ተሞክሮዎችን ቀምሮ


ለማሰፋፋት በሁሉም ዘርፍ የተደራጀ የልማት ሰረዊት መገንባት
ይጠበቅበታል ማለት ነው፡፡
የተደራጀ የልማት ሰራዊት ስንል ከ3ቱ የዩኒቨርሲቲ ተልዕኮዎች
በመነሳት ሊታይ ይገባዋል፡፡
1. መማር /ተማሪው የአስተዳደር ሰራተኛው
2. መመራመር /መምህራን ለተማሪው እና
ለመምህሩ
3. ማህበረሰብ አገልግሎት /መምህራን አገልግሎት በመስጠት
ሰራዊት መፍጠር መቻል አለበት፡፡

You might also like