You are on page 1of 82

እንን ደህና

መጣችሁ
 
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት

የተሻሻለ የመንግስት ሠራተኞች

የሥራ አፈፃፀም ምዘና መመሪያ


 
 
 

 
 
 
 
መግቢያ

 ተቋማት በስራ አፈፃፀም ምዘና ስርዓት እንዲገቡ ካልተደረገ


የመሻሻል እድላቸው በጣም ዝቅተኛ ነው፡፡ በመሆኑም ተቋማት
የስራ ምዘና አፈጻጸምን በመዘርጋት በጥንካሬም ሆነ በድክመት
የታዩትን አፈጻጸሞችን በመለየት በመለኪዎች አማካኝነት
የሚገባውን ውጤት በመስጠት የተቋማትን ግብ ስኬት
በውጤታማነት ለመፈጸም እንዲሁም ለማሻሻል ይረዳቸዋል ፡፡
በዚህም መሠረት በ2ዐዐ5 ዓ.ም የመንግስት ሠራተኞች የስራ
አፈፃፀም ምዘና መመሪያ ወጥቶ ተግባራዊ መደረጉ
ይታወቃል፡፡
የቀጠለ---
ይሁን እንጅ የስራ አፈፃፀም ምዘና አተገባበር የተቋሙን
የዳሬክቶሬቶች/የቡድኖች፣ የስራ ክፍሎችና ፈፃሚዎች
የሚሰሩትን ከተቋሙ ስትራቴጅ ጋር አስተሳስሮ ያለማቀድ ፣
የተቋሙ የበላይ አመራር ለምዘና ስርዓት ትኩረት
አለመስጠት፣ የሚገባው ውጤት ለሚገባው ፈፃሚ
ያለመስጠት፣ የተጠያቂነት ስርዓት አለመኖር፣
የቀጠለ---
የተቋሙ እቅድ አፈፃፀም ከፈፃሚው የአፈፃፀም ውጤት ጋር
እንዲናበብ ያለማድረግ ፣ የውጤት ግሽበት መኖር ፣ የሰራተኞች
እቅድ ሳይሰጥ መቅረትና ውጤትም ሳይሞላ መቅረት ፣
ሶስቱን መለኪያዎች አሟጦ አለመጠቀምና በተለይም ለጥራት
መለኪያ የተሻለ ክብደት አለመስጠት ፣ ከአሁን በፊት የነበረው
የሠራተኞች የስራ አፈጻጸም ደረጃ በአራት ክፍል ብቻ የተገደበ
መሆን፣
ሰራተኛው እራሱን በተለያየ ደረጃ አስቀምጦ እራሱን እንዲያይ

አለመጋበዝ፣ ከአሁን በፊት በጣም ከፍተኛና ከፍተኛ ለሚገቡ

ሰራተኞች ግልጽ የሆኑ ለመለኪያ ክብደት

የተለዩ ግብ ተኮር ተግባራት አለመቀመጡ እና የማበረታቻ ስርዓት

ተግባራዊ አለመሆን ሲሆኑ በተጨማሪም በተደረጉ ሁለንተናዊ ድጋፍና

ክትትል፣ ምልከታዎችና የአካል ውይይቶች መመሪያው እንዲሻሻል

ከተገልጋዬችና ከአጋር አካላት በመሰጠቱ ምክንያት እነዚህን ክፍተቶች

ለመሙላት መመሪያውን ማሻሻል አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡


ለተቋማት ተልዕኮና ራዕይ መሳካት ከሠራተኞች
የሚጠበቁ ውጤቶችን በማሳወቅ ፤ ሠራተኞች
የተቋማቸውን ስትራቴጂ ከዕለት ዕለት
ሥራቸው ጋር የሚያስተሳስሩበትን አግባብ ለመፍጠር
፤ የመንግስት ሠራተኞችን አፈጻጸም
በተጨባጭ መረጃ ላይ በመመስረት ለመለካትና
ለማሻሻል የሚያስችል የሥራ አፈፃፀም ሥርዓት
በመዘርጋት ቀጣይነት ያለው ተቋማዊ

መማማርን እውን ለማድረግ ፤ ሠራተኞችን ለተሻለ


አፈፃፀም ለማበረታታት ፤ ተገቢ ድጋፍ ለመስጠትና
በአፈፃፀም ሂደት የሚያጋጥሙ ማነቆዎችን ለመፍታት
የሚያስችል የአፈፃፀም ምዘና ሥርዓት ለመዘርጋት፤
ሠራተኛው የሚጠበቅበትን መብትና ግዴታ
ተገንዝቦ ከፍተኛ የአገልጋይነት ባህርይ
እንዲላበስ፣ የመንግስት አገልግሎት በግልፅነት፣
በተጠያቂነትና በውጤታማነት እንዲፈጸም
ኮሚሽኑ በአዋጅ ቁጥር 280/2014 ዓ.ም
የሰራተኛ መመዘኛ ስታንዳርድ በማዘጋጀት
ለክልሉ መስተዳድር አቅርቦ እንዲያፀድቅ
በተሰጠው ስልጣን መሰረት ይህን የአማራ
ብሔራዊ ክልላዊ የመንግስት ሰራተኞች የስራ
አፈፃፀም ምዘና መመሪያ አዘጋጅቷል፡፡
ክፍል አንድ
ጠቅላላ
 አንቀጽ 1
አጭር ርእስ
 
ይህ መመሪያ “የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ
መንግስት የተሻሻለ የመንግስት ሠራተኞች
የስራ አፈፃፀም ምዘና መመሪያ” ተብሎ
ሊጠቀስ ይችላል፡፡
አንቀጽ 2

ትርጓሜ
 
የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው
ካልሆነ በስተቀር በዚህ መመሪያ ውስጥ፡-
“ኮሚሽን” ማለት የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ
መንግስት ሲቪል ሰርቪስ እና የሰው ኃብት
ልማት ኮሚሽን ነው፡፡
“የመንግስት ሰራተኛ” ማለት ሙሉ በሙሉ
ወይም በከፊል በመንግስት በጀት በሚተዳደሩ
የመንግስት መስሪያ ቤቶች ውስጥ በቋሚነት
ወይም በጊዜያዊነት ተቀጥሮ የሚሰራ ሰው
ነው፡፡
ሆኖም ግን በክልሉ በየደረጃው የሚገኙ
የመንግስት ተሿሚዎችን ፣ የም/ቤት
አመራሮችን እና በራሳቸው የምዘና ሥርዓት
ያላቸውን ዐቃቢ ህጎችን ፣ ዳኞችንና የፖሊስ
አባላትን አይጨምርም፡፡
 “የሥራ/ዕቅድ አፈፃፀም” ማለት አንድ
ሠራተኛ የተሰጠውን ዕቅድ አከናውኖ
በመጨረሻ በሚገኝ ውጤት እና ለውጤቱ
መገኘት መንስኤ በሚሆኑ የግብ ተኮርና
የባህርይ መለኪያዎች የሚገለፅ ክንውን ነው፡፡
 “የዕቅድ አፈፃፀም ስምምነት” ማለት

በሠራተኛውና በቅርብ ሃላፊው መካከል


በየስድስት ወሩ የሚደረግ የዕቅድ ውል
ስምምነት ነው፡፡
 “ግብ ተኮር ተግባራት” ማለት ከተቋም ዓመታዊ
ግቦች ተወስደው ለዳይሬክቶሬት ወይም ለቡድን
የተዘጋጁ ግቦችን ለማሳካት በአባሪ 1.1 እና
በአባሪ 2.1 ቅፆች ተካተው ለሠራተኛ፣ ለቡድን
መሪ፣ ለዳይሬክተር ወይም ለሌላ የሥራ ሃላፊ
የሚሰጡ ዋና ዋና ተግባራት ማለት ነው፡፡
“የድርጊት መርሀ ግብር ” ማለት የሰራተኛው የወርና
የቅርብ የስራ ሃላፊው የሩብ አመት ዝርዝር
የሥራ ዕቅድና ዕቅዱ የሚተገበርበት የጊዜ ሰሌዳ
ማመላከቻ ነው
“የሥራ አፈጻጸም ምዘና” ማለት በጊዜ፣ በጥራት፣
በመጠን እና በወጪ የተገኘ የሥራ ክንውን ቀደም
ሲል ከተዘጋጀ ግብ ተኮር ተግባራት መለኪያ
ክብደት እንዲሁም የባህርይ አፈጻጸምን ከተቀመጠ
የባህርይ አመላካች ክብደት ጋር በማነፃፀር የግል
ሥራ አፈጻጸም ውጤትን መለካት ወይም
መመዘን ማለት ነው፡፡
“የአፈጻጸም ደረጃ ” ማለት በየደረጃው ከሚጠበቀው
ውጤት አንጻር የሰራተኛው ወይም የሥራ ኃላፊው
አፈጻጸም ውጤት የሚገለጽበት ደረጃ ነው፡፡
 “ዳይሬክቶሬት/ቡድን/የሥራ ክፍል” ማለት
በአንድ የመንግስት መስሪያ ቤት የሥራ እንቅስቃሴ
ውስጥ ውጤት ለማምጣት አንድ ሠራተኛ ወይም
ሠራተኞች ወይም የሥራ ሃላፊ ደረጃ በደረጃ
 የሚያከናውናቸው ተያያዥነትና ተከታታይነት ያላቸው

ተግባራት ከመነሻ እስከ መድረሻ የሚከናወኑበት የአንድን


ክፍለ-ሥራ ፍሰት የሚያሳይ አደረጃጀት ነው፡፡
 “ብቃት” ማለት ከሰራተኛው ወይም ከሥራ ኃላፊው
የሚጠበቀውን ውጤት ለማግኘት የሚያስፈልገውን እውቀት ፣ ክህሎት እና
አመለካከት የሚመለከት ነው፡፡
 “ባህርይ” ማለት ሰራተኛው የሚያስፈልገውን
ውጤት ለማምጣት ሊኖረው የሚገባውን በዚህ
መመሪያ በአባሪ 1.2 እና በአባሪ 2.2 በባህርይ
ብቃት መስፈርትነት የተቀመጡትን መለኪያዎች
የሚመለከት ነው፡፡
 “የበላይ አመራር/ኃላፊ/ ተወካይ” ማለት

በክልል፣ በዞን፣ በወረዳና በከተማ አስተዳደር ደረጃ


የመንግስት መስሪያ ቤቶችን በበላይነት
ለመምራት በመንግስት የሚሾም ኃላፊ፣ ምክትል
ኃላፊ ወይም በአቻ ደረጃ የሚገኝ አመራርን ነው፡፡
 “አቅም ግንባታ” ማለት የሰራተኛውን የመፈጸም
አቅም ለማሳደግ በኃላፊዎችና ለዚሁ ተግባር
በተመረጡ ባለሙያዎች የሚሰጥ የሥራ ላይ
ስልጠና/ድጋፍ ነው፡፡
 “ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት” ማለት ሠራተኛው

ከህመም፣ ከወሊድ፣ ከእስር፣ ከስልጠና/ከትምህርት፣


ከመደበኛ ስራ ውጭ ከሆነ ተልዕኮ ወይም ከተፈጥሮ
እና ሰው ሰራሽ ክስተቶች ጋር በተያያዘ ሠራተኛው
በሥራው ላይ እንዳይገኝ ያስቻለ ምክንያት ነው፡፡
 ማንኛውም በወንድ ፆታ የተገለጸው ሴትንም ይጨምራል፡፡
አንቀጽ 3
የመመሪያው ዓላማ
ለተቋማት ተልዕኮና ራዕይ
መሳካትከሠራተኞች የሚጠበቁ
ውጤቶችን በማሳወቅ ሠራተኞች
የተቋማቸውን ስትራቴጂ ከየዕለት
ሥራቸው ጋር የሚያስተሳስሩበትን
አግባብ ለመፍጠር፤
 የመንግስት
ሠራተኞችን አፈጻጸም በተጨባጭ መረጃ
ላይ በመመስረት ለመለካትና ለማሻሻል የሚያስችል
የሥራ አፈፃፀም ሥርዓት በመዘርጋት ቀጣይነት
ያለው ተቋማዊ መማማርን እውን ለማድረግ፤

 ሠራተኞችንለተሻለ አፈፃፀም ለማበረታታት ፣


ተገቢ ድጋፍ ለመስጠትና በአፈፃፀም ሂደት
የሚያጋጥሙ ማነቆዎችን ለመፍታት የሚያስችል
የአፈፃፀም ምዘና ሥርዓት ለመዘርጋት፤
12ቱን የስነ-ምግባር መርሆዎች በተሟላ መልኩ
እንዲይዝ በማድረግ ሠራተኛው የሚጠበቅበትን
መብትና ግዴታ ተገንዝቦ ከፍተኛ የአገልጋይነት
ባህርይ እንዲላበስ ለማድረግ፣

የባህርይ መለኪያ የሠራተኛውን አመለካከት


/Attitude/፣ እሴት /Value/ እና ስነ-
ምግባር /Ethics/ በማቀናጀትና ባህርይን በማረቅ
ለደንበኛው የሚያረካ አገልግሎት ለመስጠት ዝርዝር
ዓላማዎች ናቸው፡፡
 

አንቀጽ 4
የመመሪያው ተፈፃሚነት ወሰን
 
ይህ መመሪያ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ
በመንግስት በጀት በሚተዳደሩ በክልሉ በየደረጃው
በሚገኙ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ላይ ተፈፃሚ
ይሆናል፡፡
 
 
አንቀጽ 5
የአፈጻጸም ምዘና መርሆዎች
 የተቋማት ስትራቴጂያዊ ግቦች ከክልላዊ ተልዕኮና ራዕይ
የመነጩ እንዲሆን ይደረጋል፤

 በየደረጃው የሚዘጋጁ ዓመታዊ ግቦች እንዲሁም የግብ ተኮር


ተግባራት ዒላማዎች ጥረትን የሚጠይቁና ሊተገበሩ የሚችሉ
ይሆናሉ፤

- የሰራተኛው የአፈጻጸም እቅድ የሚዘጋጀው ከተቋሙ አመታዊ


ግቦችና ከዳይሬክቶሬቱ ወይም ከቡድኑ እቅድ ጋር በቀጥታ
በሚመጋገብበት (በሚተሳሰርበት) አግባብ ይሆናል፤
በተቋም አመራርና በመላው ሠራተኛ መካከል
ስለተግባርና ሃላፊነት፣የሥራ አፈፃፀም ግምገማ ፣
ምዘና ፣ በቂ ግንዛቤና የጋራ መግባባት ይፈጠራል፤
የሠራተኞች ዕቅድ ዝግጅት ፣ የአፈጻጸም ግምገማና

ምዘና የሚካሄደው አስቀድሞ ከስምምነት


በተደረሰባቸው ግብ ተኮር ተግባራት መለኪያዎችና
ዒላማዎች እንዲሁም ለውጤቱ መገኘት መንስኤ
የሆኑ የባህርይ ብቃት መለኪያዎችን ከተገኙ
ውጤቶች ጋር በማነጻጸር ይሆናል ፣ ለዚህም የዕቅድና
የአፈጻጸም መረጃ በአግባቡ እንዲያዝ ይደረጋል፤
የስራ አፈጻጸም ግምገማና ምዘና በተቋም፣
በዳይሬክቶሬት/ በቡድን ፣ በስራ ክፍል እና በፈጻሚ
ደረጃ በተናበበና ሚዛናዊ በሆነ መልኩ በግልጽነትና
በተጠያቂነት መንፈስ ይከናወናል፤
አፈጻጸምን ለመገምገም፣ ለመለካትና የቡድን

መማማርን ለመፍጠር በለውጥ መሣሪያዎች


አጋዥነት ከዕቅድ ዝግጅት ጀምሮ በትግበራና
ማጠቃለያ ምዕራፍ ቀጣይነት ያለው የክትትልና
ግምገማ ሥርዓት እንዲዘረጋ ተደርጎ ይተገበራል፤
 
 
ክፍል ሁለት
የሠራተኞች አፈጻጸም ዕቅድ ዝግጅት እና
ምዘና ሥርዓት
 
አንቀጽ 6
የአፈጻጸም ዕቅድ ዝግጅት
 
የሠራተኞች ሥራ አፈፃፀም ዕቅድ የሚዘጋጀው
በሚከተለው አግባብ ይሆናል፡-
 በተቋም ተልዕኮ፣ ራዕይ፣ እሴቶችና ስትራቴጂያዊ ግቦች
ላይ ቀጣይነት ባለው ውይይት የጋራ መግባባት ላይ
በመድረስ፤
 በዳይሬክቶሬቱ፣ በቡድኑ ወይም በሥራ ክፍሉ ግቦች፣

መለኪያዎችና ዒላማዎች ላይ የጋራ መግባባት ላይ ደርሶ


ግብ ተኮር ተግባራትን በማመላከት፤
 የሠራተኛውን ተግባርና ኃላፊነት ከዳይሬክቶሬቱ፣

ከቡድኑ ወይም ከሥራ ክፍሉ ግቦች ጋር በማስተሳሰር፤


 የማንኛውም ኃላፊ ፣ ዳይሬክተር ወይም ቡድን መሪ እና

ሠራተኛ የግብ ተኮር ተግባራትን እቅድ ለመለካት


አስቸጋሪ ካልሆነ በስተቀር ከመጠን፣ ከጥራት፣ ከጊዜና
ወጪ አንፃር መለኪያዎችን አሟጦ በመጠቀም ፣
 የዳይሬክቶሬቱን ወይም የቡድኑን የ6 ወር እቅድ ከተግባሩ ፣
ከሃላፊነቱና ከባህርይ ብቃት መለኪያዎች ጋር አስተሳስሮ
በማዘጋጀት፤

 ለግብ ተኮር ተግባራትና ለውጤቱ መገኘት መንስኤ ለሆኑ


የባህርይ ብቃት መገለጫ መለኪያዎች ክብደት በመስጠት፤

 ለማንኛውም የመንግስት ሰራተኛ የሚዘጋጅ የ6ወር ዕቅድ በየወሩ


የተሸነሸነ እቅድ እንዲሰጠው ይደረጋል ፣

 የሰራተኛ ዕቅድ በቅርብ ኃላፊው በማጽደቅ፣ ከስምምነት


መድረስ ካልተቻለ ግን በመስሪያ ቤቱ የበላይ ሃላፊ ውሳኔ
እንዲያገኝ በማድረግ፤
 ለአንድ ወርና ከአንድ ወር ለበለጠ ጊዜ በኮሚቴና በውክልና እንዲሰራ
ሃላፊነት የተሰጠው ሠራተኛ ወይም የሥራ ሃላፊ ተግባሩ ከተሰጠ በኋላ
የዕቅዱ አካል ተደርጎ እንዲወሰድ በማድረግ፤

 የክትትልና ድጋፍ አግባብን እና የሠራተኛ አፈጻጸም መረጃ ማሰባሰቢያ


ስልቶችን አስቀድሞ በመቀየስ፤

 ከፍተኛና በጣም ከፍተኛ የምዘና ውጤት የሚሰጥ የአፈጻጸም እቅድ


ስምምነት እንደ ተቋሙ ተግባርና እንደ የስራ መደቡ የስራ ባህርይና
ተግባር አኳያ የምርምር ፣ የፈጠራ ተግባራት ፣ተሞክሮ በመቀመር
ለሌሎች አርአያ የሚያደርግ ፣ከመደበኛ የስራ ስአት ውጪ አገልግሎት
የሰጠና የደንበኛውን እርካታ ያረጋገጠ ፣ ወጪ ቆጣቢ በሆነ መንገድ
ስራውን የከወነ ወይም ከብክነት የጸዳ አገልግሎት የሰጠ እና
ለተቋሙ ግብ ስኬት ፋይዳ ያለው ተግባር እንዲያከናውን 20%
ክብደት ያለው የግብ ተኮር ተግባር ራሱን አስችሎ የዕቅድ
አካል በማድረግ ለፈጻሚው እቅድ መስጠ

 የስድስት ወር እቅድ በሰራተኛው ንቁ ተሳትፎ ከቅርብ


ኃላፊው ጋር በጋራ የሚዘጋጅ ሆኖ የአፈጻጸም ስምምነቱ
ከሐምሌ 1-15 እና ከጥር 1-15 ባለው ጊዜ ውስጥ ብቻ
በመፈራረም የሚዘጋጅ ይሆናል::
አንቀጽ 7
የአፈጻጸም ስምምነት ሰነድ ይዘት
 

የሚከተሉትን ዝርዝር ሃሳቦች የያዘ የአፈጻጸም ስምምነት ሰነድ ተዘጋጅቶ የስራ


ኃላፊዎች እንደ ተጠሪነታቸው ከመስሪያ ቤቱ የበላይ ኃላፊ ወይም ምክትል ኃላፊ
እና ሠራተኞች ደግሞ ከቅርብ የሥራ ኃላፊዎች ጋር መፈራረም ይኖርባቸዋል፡፡

ሆኖም የአፈጻጸም ስምምነት ማን ከማን ጋር መፈራረም እንዳለበት የሚወሰነው


በየመስሪያ ቤቱ መዋቅር መሰረት ይሆናል፡፡
 የዕቅድ አፈጻጸም ስምምነት ሰነዱ፡-
 የሰራተኛው ሙሉ ስም ፣የስራ መደብ መጠሪያና ደረጃ
 የአፈጻጸም ስምምነት ጊዜውን
 የዳይሬክቶሬቱን፣ የቡድኑን ወይም የስራ ክፍሉን ግቦች
መመገብ የሚችሉ ለሰራተኛ የተሰጡ ግብ ተኮር ተግባራት
እና የባህርይ መገለጫዎች
 የሚጠበቁ የባህርይ ብቃት አፈጻጸም ውጤት መለኪያዎችን
እና
የግብ ተኮር ተግባራት አፈፃፀም ስምምነት
መለኪያን፣ ክብደትን፣ ኢላማን፣
መርሀ-ግብርን፣ የአፈፃፀም ደረጃዎችንና
የክትትልና ድጋፍ አግባብን ማሟላት አለበት፡፡
አንቀጽ 8
የሠራተኛ አፈጻጸም ምዘና ሥርዓት
የሠራተኛው አፈጻጸም ክትትል፣ ግምገማና ምዘና በሚከተለው
አግባብ ይከናወናል፡-
የአፈጻጸም ግምገማና ምዘናም የሚከተሉትን የአፈጻጸም መረጃ
ላይ ተመስርቶ በመገምገም የግለሰብ ምዘናን ማካሄድ፣
የአፈፃፀም ግምገማና ምዘናም የሚከተሉትን የአፈጻጸም የመረጃ
ምንጮች መሰረት ያደረገ ይሆናል፡-
ሀ) የተቋምና የቡድን እቅድ የአፈጻጸም ሪፖርት
ለ) የሠራተኛው የየወሩ እና የቅርብ ሃላፊው የሩብ ዓመት አፈፃፀም
ሪፖርት፣
ሐ) አስቀድሞ የተያዙ ሪፖርቶች፣ ግብረ-
መልሶችና ቃለ-ጉባኤዎች፣
መ) የግብ ተኮር ተግባራትና የባህርይ ብቃት
መገለጫዎች አፈፃፀም፣
 የግለሰብ ዕውቀት ፣ ክህሎትና አመለካከት

ጥንካሬና እጥረትን በመለየት


 በግለሰብ አፈፃፀም የባህርይ ጥንካሬና

ጉድለትን በማሳየት
 ለውጤቱ መገኘት የአመራሩን ድርሻ ለይቶ በማሳየት እና
ሥራዎች ያልተከናወኑበትን ምክንያት በመለየት፣
 በጣም ከፍተኛ፣ ከፍተኛ ፣ አጥጋቢና ዝቅተኛ

አፈጻጸምን በመለየትና ለውጤቱ ባለቤቶች እውቅና


በመስጠት፣
 አፈፃፀሙ በቀጣይነት የሚሻሻልበትን ስልት በማሳየት፣
 የሰራተኛ የስድስት ወራት አፈጻጸም ምዘና ሲካሄድ የግብ

ተኮር ተግባራት አፈፃፀም ውጤት 70% የሚይዝ


ሲሆን፤ ለውጤቱ መገኘት መንስኤ ለሚሆኑ የባህርይ
ብቃት አፈፃፀም ውጤት ደግሞ 30% የሚይዝ ይሆናል፡፡
 የሰራተኛው የስድስት ወራት ግብ ተኮር ተግባራት አፈፃፀም
ውጤት በየ15 ቀኑና በየወሩ በሚካሄድ ግምገማ ላይ ተመስርቶ
በቅርብ የስራ ኃላፊው ይሞላል፤
 ሆኖም በአፈፃፀም ውጤት አሞላሉ ላይ በቅርብ የስራ
ኃላፊውና በፈፃሚው መካከል ልዩነት ካለ የመስሪያ ቤቱ የበላይ
ኃላፊ ውሳኔ ይሰጣል፡፡ የቡድን ወይም ሌላ ለመስሪያ ቤቱ የበላይ
ኃላፊ ተጠሪ ያልሆነ የስራ ኃላፊ በሚሆንበት ጊዜ ከኃላፊው
በፊት የቅርብ ኃላፊው እንዲያየው ይደረጋል፡፡
የሠራተኛው የባህርይ ብቃት አፈፃፀም ምዘና የሚካሄደው ተመዛኙ
በተገኘበት በሥራ ቡድን አባላትና በቅርብ የስራ ኃላፊው ሲሆን
አሰራሩም አሳታፊ፣ ግልፅና ተጠያቂነት የሰፈነበት መሆን አለበት፡፡
በሁለቱ መዛኞች የሚሰጥ የምዘና ውጤት የሚከተለው የነጥብ
ክብደት ክፍፍል ይኖረዋል፡-
ሀ) በቡድን አባላት ለግለሰቡ አፈጻጸም ውጤት የሚሰጥ የነጥብ ክብደት
10%፣
ለ) በቅርብ የስራ ኃላፊው ለግለሰቡ የሚሰጥ አፈጻጸም ውጤት የነጥብ
ክብደት 20% የሚይዝ ይሆናል፤
 ሐ) በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 10/ሀ እና 10/ለ የተጠቀሰው
የዳይሬክተሮች፣ የቡድን መሪዎች ወይም የስራ ክፍል ኃላፊዎችንም
ይመለከታል፡፡
 በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ 10 የተጠቀሰው ቢኖርም በቡድን
ያልተደራጁ ሰራተኞች የባህርይ ብቃት አፈፃፀም ምዘና ውጤት ሙሉ
በሙሉ በቅርብ ኃላፊው ብቻ የሚሞላ ይሆናል፤
 በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ 10 የተጠቀሰው ቢኖርም በልዩ ልዩ
የኮሚቴ ስራዎች ውስጥ ከሁለት ወር በላይ ለሚሰራ ሰራተኛ
የባህርይ ብቃት አፈፃፀም ውጤት 20% በቅርብ ኃላፊው
10% ከኮሚቴው ሪፖርት በመነሳት በዳይሬክቶሬቱ ወይም
በቡድኑ አባላቱ እንዲሞላ ይደረጋል፤
 በኮሚቴ ሥራ የሚሳተፍ ሠራተኛ የግብ ተኮር ተግባራት
አፈፃፀም ምዘና ከኮሚቴው ሪፖርት በመነሳት ከ70%
በቅርብ ሃላፊው የሚሞላ ይሆናል፣
 የግለሰብ የግብ ተኮር ተግባራት የአፈጻጸም ሪፖርት በየወሩ
ለቅርብ የስራ ኃላፊ፣የሥራ ኃላፊው የሩብ ዓመት አፈፃፀም
ሪፖርት ደግሞ እንደ ተጠሪነታቸው ለመስሪያ ቤት የበላይ ኃላፊ
ወይም ምክትል ኃላፊ እየቀረበ ይገመገማል፣ በአምስት
ተከታታይ ቀናት ጊዜ ውስጥ በፅሁፍ ግብረ-መልስ ይሰጣል፤
ሆኖም ለሰራተኛው በየወሩና ለቅርብ ሃላፊው በየሩብ ዓመቱ
ውጤት መሙላት አስፈላጊ አይሆንም፡፡
የፑል አገልግሎት የሚሰጡ የስራ ኃላፊዎች የግብ ተኮር ተግባራት
አፈፃፀም ምዘና ውጤት የተጠቃሚ መስሪያ ቤት ኃላፊዎች
አስተያየቶችን አካቶ በፑል ተጠሪ መስሪያ ቤት ኃላፊው የሚሞላ
ሲሆን፤ የባህርይ ብቃት አፈፃፀም ምዘና 10% ተጠሪ በሆነበት ቡድን
አባላት፣ 20% የፑል ተጠሪ መስሪያ ቤት ሃላፊው ከተጠቃሚ መስሪያ
ቤት ኃላፊዎች ያገኛቸውን አስተያየቶች አካቶ የሚሞላ ይሆናል፡፡
የአፈጻጸም ምዘናና ምዘናውን መሰረት በማድረግ የሚሰጡ ውሳኔዎች
በጽሁፍ የተደራጁ ያፈጻጸም መረጃዎችን መሰረት ያደረገ ይሆናል\
አንቀጽ 9
 የአፈጻጸም ምዘናን ስለማጠቃለል
  የአፈጻጸም ምዘና ማጠቃለያ

ሀ) የተጠቃለለ የአፈጻጸም ምዘና በሠራተኛው በየ 15 ቀኑና በየወሩ የአፈጻጸም


ክትትልማ ግምገማ መረጃዎች ላይ ይመሰረታል
ለ) የስድደስት ወር አፈጻጸም ማጠቃለያ ምዘና ውጤት ላይ በስራ ቡድን አባላትና
በቅርብ የስራ ኃላፊው የአፈጻጸም ግምገማ ውጤቶች መካከል ልዩነት ካለ
መጀመሪያ የቅርብ ሥራ ኃላፊውን ባካተተ የጋራ ውይይት ልዩነቱን ለመፍታት
ይሞከራል
ሆኖም የአፈጻጸም ውጤት አሞላል ልዩነቱ በጋራ ውይይት የማይፈታ ከሆነ በበላይ
ኃላፊው የሚሰጥ ውሳኔ የመጨረሻ ተደርጎ ይወሰዳል፤
ሐ) የሰራተኛው የ6 ወራት አጠቃላይ የአፈፃፀም ውጤት በተቋሙ
ማኔጅመንት ኮሚቴ እንዲፀድቅ ይደረጋል፤
መ) የተጠቃለለ የአፈፃፀም ምዘና ውጤት በሁለት ቅጅዎች ተዘጋጅቶ
አንዱ ቅጅ ለተመዛኙ ሰራተኛ ወይም ዳይሬክተር ወይም ቡድን መሪ
ይሰጣል፣
ሁለተኛው ቅጅ በዳሬክቶሬቱ ወይም በቡድኑ እንዲያዝ ይደረጋል፣ አባሪ
3 ወይም በማጠቃለያ ቅፁ የተሞላው ውጤት ብቻ በየአስተዳደር
እርከኑ ላለው የሰው ሀብት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ወይም ቡድን
በመሸኛ ደብዳቤ ተልኮ በተመዛኙ የግል ማህደር እንዲያዝ ይደረጋል፤
የአፈጻጸም ምዘና ማጠቃለያ ጊዜ 
ሀ) የመጀመሪያው ስድስት ወር ግምገማና የሥራ አፈጻጸም ማጠቃለያ
ምዘና ከጥር 1 እሰከ 15 ከተከናወነ በኋላ በመ/ቤቱ ማኔጅመንት ጸድቆ
ማጠቃለያው እስከ ጥር 30 ለሰው ሃብት አስተዳደር መድረስ አለበት፣
ለ) የሁለተኛው ስድስት ወር የአፈጻጸም ግምገማ የሥራ አፈጻጸም
ማጠቃለያ ምዘና ከሃምሌ1 እስከ 15 ከተከናወነ በኋላ በመ/ቤቱ
ማኔጅመንት ጸድቆ ማጠቃለያው እስከ ሐምሌ 30 ለሰው ሃብት
አስተዳደር መድረስ አለበት፣
ሐ) ከላይ በንዑስ አንቀፅ 2/ሀ እና ለ ላይ የተጠቀሰው እንደ ተጠበቀ ሆኖ
ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት ካልሆነ በስተቀር ከላይ ከተጠቀሱ ቀናት
በኋላ የተካሄደ ምዘና ተቀባይነት አይኖረውም ሆኖም ለመዘግየቱ
ምክንያት የሆነው አካል ተጠያቂ ይሆናል፡፡
መ) የሙከራ ቅጥር ሰራተኛ የስራ አፈፃፀም ምዘና ማጠቃለያ ቅጥር
ከተፈፀመበትና የእቅድ አፈፃፀም ውል ስምምነት ከተያዘበት ጊዜ
ጀምሮ ላሉት ተከታታይ ስድስት ወራት ያለው አፈፃፀም ውጤት
የሚሞላ ሲሆን ቋሚ ሰራተኛነቱ ከተረጋገጠ በኋላ በዓመት ሁለት ጊዜ
ወደ ሚሞላው ስርዓት ለማስገባት
ሶስትና ከሶስት ወር በላይ ቀሪ ጊዜ የሚኖረው ከሆነ ልክ እንደ
ሙሉ ስድስት ወራት ተቆጥሮ የአፈፃፀም ውጤቱ የሚሞላ
ይሆናል፡፡ ሆኖም ቀሪ ጊዜው ከሶስት ወር በታች ከሆነ ከቀጣዩ
ስድስት ወር ጋር ተካቶ የሚመዘን ይሆናል፡፡
ሠ) የአፈጻጸም እቅድ ዝግጅት ክትትል ፣ ድጋፍና ግብረ- መልስ
በየበጀት ዓመቱ ሙሉ ጊዜ (ከሃምሌ 1 እስከ ሰኔ 30)
በተከታታይ ይሰጣል
አንቀጽ 10
የተጠቃለለ የሥራ አፈጻጸም ምዘና ደረጃ
አሰጣጥ
 
ለመንግስት ሰራተኛ በየመንፈቅ ዓመቱ
መጨረሻ የሚሰጥ የተጠቃለለ የሥራ
አፈጻጸም ምዘና ነጥብ ከሚከተሉት አምስት
የአፈጻጸም ደረጃዎች ውስጥ ያርፋል፤
ሀ) ደረጃ አምስት- በጣም ከፍተኛ (Excellent) የአፈጻጸም
ደረጃ ሲሆን ከ95-100% የሚደርስ የተጠቃለለ ምዘና ውጤትን
ያመለክታል፡፡
ለ) ደረጃ አራት- ከፍተኛ(Very Good) የአፈጻጸም ደረጃ ሲሆን፤
ከ80-94.99% የሚደርስ የተጠቃለለ ምዘና ውጤትን
ያመለክታል፡፡
ሐ) ደረጃ ሶስት- መካከለኛ (Good) የአፈጻጸም ደረጃ ሲሆን ከ65-

79.99% የሚደርስ የተጠቃለለ ምዘና ውጤትን ያመለክታል፡፡


መ) ደረጃ ሁለት- አጥጋቢ (Satisfactory) የአፈጻጸም ደረጃ
ሲሆን ከ50-64.99% የሚደርስ የተጠቃለለ ምዘና ውጤትን
ያመለክታል፡፡
ሠ) ደረጃ አንድ - ዝቅተኛ (Poor) የአፈጻጸም ደረጃ ሲሆን
ከ50% በታች የሆነ የተጠቃለለ ምዘና ውጤትን
ያመለክታል፡፡
ለአፈፃፀም ምዘና ደረጃዎች የሚሰጠው ነጥብ ከአንድ እስከ
አምስት ሲሆን ለበጣም ከፍተኛ አፈፃፀም 5፣ ለከፍተኛ 4 ፣
ለመካከለኛ 3 ፣ ለአጥጋቢ 2 እና ለዝቅተኛ 1 ይሆናል፡፡
አንቀጽ 11
የአፈፃፀም ማሻሻያ እርምጃ አወሳሰድ
የተጠቃለለ የአፈጻጸም ምዘና ውጤትን መሰረት በማድረግ
የሚከተሉት ዋና ዋና የማሻሻያ እርምጃዎች መወሰድ
አለባቸው፡-
የሠራተኛውን የአፈጻጸም ውጤት መሰረት በማድረግ
የዕውቀት ፣ የክህሎት እና የአመለካከት የአቅርቦት
እጥረቶችን መለየትና መፍታት፣
 በዳይሬክቶሬቱ፣ በቡድኑ ወይም በስራ ክፍሉ የሚገኙትን ውጤታማ
ሠራተኞች በመለየት ሌሎች ሠራተኞች ውጤታማ ከሆኑት እየተማሩ
አፈፃፀማቸው የበለጠ የሚሻሻልበትንና በብቃት የሚደግፉበትን ስልት
መቀየስ፣
 ዝቅተኛ አፈፃፀም ያላቸውን ሠራተኞች የምክር አገልግሎት
የሚያገኙበትን ሁኔታ በማመቻቸት አቅማቸው እንዲገነባ ማድረግ፣
 የግለሰብ አፈጻጸም በቀጣይነት የሚሻሻልበትንና እርምጃዎችን በጥናት
እየለዩ መውሰድ ፣
 በጣም ከፍተኛና ከፍተኛ የስራ አፈፃፀም ውጤት ያስመዘገበ ሰራተኛ
እንዲበረታታ ማድረግ፣
 ድጋፍና ክትትል እየተደረገለት በተከታታይ ለሦስት ጊዜ
ዝቅተኛ የተጠቃለለ የስራ አፈፃፀም ውጤት ያስመዘገበ
ሰራተኛን ከስራ ማሰናበት፣
 በተራ ቁጥር 6 የተገለጸው ቢኖርም ለተከታታይ አምስት
ዓመታት በጣም ከፍተኛና ከፍተኛ የሥራ አፈጻጸም ምዘና
ውጤት ሲያገኝ የነበረ የመንግሥት ሠራተኛ የሥራ አፈጻጸም
ምዘና ውጤቱ በተከታታይ ለአራት ጊዜ ዝቅተኛ ካልሆነ
በስተቀር ከሥራ አይሰናበትም፡፡
ክፍል ሦስት

የልዩ ልዩ አካላት ተግባርና

ኃላፊነቶች
አንቀጽ 12

በየደረጃው ያሉ የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ፣


መምሪያና ጽ/ቤት ተግባርና ኃላፊነት
 
1.መመሪያውን አግባብነት ላላቸው አካላት ሁሉ ማስተዋወቅና
አስፈላጊውን ሥልጠና መስጠት፣
2. መመሪያውን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያግዝ ተጨማሪ ሥልጠና
እንዲሰጥ ሁኔታዎችን ማመቻቸት፣
3. የመመሪያውን አፈጻጸም መከታተልና መገምገም፣
4. መመሪያውን አስመልክቶ አስፈላጊውን ድጋፍ መስጠት፣
5. አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ መመሪያው እንዲሻሻል በጥናትና ምርምር
የተደገፈ የውሳኔ ሃሳብ ማቅረብ፣
6.በየደረጃው ያሉ መ/ቤቶች ለሠራተኞች የስራ አፈፃፀም
ስምምነት መስጠታቸውን፣ ውጤት መሙላታቸውን እና
የተሞላው ውጤት በተቋሙ ማኔጅመንት ተገምግሞ
መፅደቁን፣ በተሰራው ልክ ያልተሞላ (የተጋነነ) ውጤት ሲኖር
ደግሞ ከመ/ቤቱ የበላይ አመራር ጋር በመነጋገር
እንዲስተካከል ድጋፍና ክትትል ማድረግ፣ ካልተስተካከለ
በአንቀጽ 18 መሠረት ተጠያቂ እንዲሆን ማድረግ፣ ውጤቱ
እስከ ሚስተካከልም ጥቅም ላይ እንዳይውል ማድረግ፣
7. ሰራተኞችን በማብቃትና በአፈጻጸም ሂደት የሚያጋጥሙ
ችግሮችን በመፍታት ወይም እንዲፈቱ ማድረግ
8. የተጠቃለለውን የአፈፃፀም ውጤት መነሻ በማድረግ
ሰራተኞች እንዲበረታቱ የሚያስችል ምቹ ሁኔታ
ይፈጥራሉ፤
አንቀጽ 13
የሰው ኃብት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት /ቡድን
ተግባርና ኃላፊነት
 
 በየመስሪያ ቤቱ የሚገኙ የሥራ ሃላፊዎችና ሠራተኞች
በመንግስት ሠራተኞች ዕቅድ አፈፃፀም ምዘና መመሪያ ላይ በቂ
ዕውቀትና ክህሎት መያዛቸውን ማረጋገጥ፤
 ለሰራተኛው የተሞላው የአፈፃፀም ምዘና ማጠቃለያ ውጤት
በግል ማሕደር ከመታሰሩ በፊት ሠራተኛው የሚሰራበት መ/ቤት
ማኔጅመንት ውሳኔ መስጠቱን ማረጋገጥ፤
 የስራ ሃላፊዎች አፈጻጸምን የመመዘንና የማሻሻል ሃላፊነታቸውን በሚገባ ለመወጣት
የሚያስችላቸውን አስፈላጊውን ድጋፍ መስጠት
 የሰራተኞች አፈጻጸም ምዘና መረጃዎችን በአግባቡ መያዝና ጥቅም ላይ እንዲውሉ
ማድረግ፣
 በተቋሙ ውስጥ ያሉ ሁሉም ሰራተኞች እቅድ መሰጠታቸውንና ውጤት መሞላቱን
ማረጋገጥ፣
 የአፈጻጸም ምዘና መመሪያ አሠራሩ በሚያዝዘው መሠረት የተከናወነ መሆኑን
ማረጋገጥ፤
 በየደረጃቸው ያሉ መ/ቤቶች ለሠራተኞች የሰጡትን የስራ አፈፃፀም ምዘና ውጤት
ከሠራተኛው የግል ማህደር ማሰርና መረጃውን ለሚመለከተው አካል በወቅቱ
ማስተላለፍ፤
አንቀጽ 14
በየደረጃው ያሉ የመንግስት መ/ቤቶች የበላይ
አመራር ወይም ኃላፊ ወይም ተወካይ ተግባርና
ኃላፊነት
 
 የተቋሙን ተልዕኮ፣ ራዕይ፣ ስትራቴጂና እሴቶች በሚገባ መረዳትና
ከፈፃሚዎች ጋር የጋራ ማድረግ፣
 የተቋሙን ስትራቴጂ ማጋራት፤ መመሪያውን ተግባራዊ ለማድረግ
የሚያስችሉ ሁኔታዎችን ማመቻቸት፤
 የስራ ክፍል ኃላፊዎች ለሚያቀርቡት የአፈጻጸም ሪፖርት በአምስት
ቀናት ጊዜ ውስጥ ተገቢውን ግብረ-መልስ በፅሁፍ መስጠት፣
 መካከለኛ አመራሩና የመንግስት ሰራተኛው በእቅድ ዝግጅት በአፈጻጸም
ግምገማና ምዘና እንዲሁም በውጤታማ ግብረ-መልስ አሰጣጥ ዙሪያ
ተገቢውን እውቀት ፣ ክህሎትና አመለካከት መያዛቸውን ማረጋገጥ
 ከመካከለኛ አመራሩ አቅም በላይ የሆኑ የግብዓት አቅርቦት ችግሮችን
መፍታት፣
 የመንግስት ሰራተኞች አፈጻጸም ምዘና ማጠቃለያ ውጤት በየደረጃው
ለሚገኙ የሲቪል ሰርቪስ መስሪያ ቤቶች የምዘና ጊዜው በተጠናቀቀ
በ15 ቀናት ውስጥ ማድረስ፣
 የስራ አፈፃፀም ምዘና መረጃዎች በአግባቡ መያዛቸውንና ጥቅም ላይ
መዋላቸውን ማረጋገጥ፣
 ለመመሪያው ውጤታማነት በየደረጃው ከሚገኙ የሲቪል ሰርቪስ
መስሪያ ቤቶች ማለትም ከሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን፣ መምሪያና ጽህፈት
ቤት ጋር በቅንጅት መስራት፣
 የሠራተኞች አፈጻጸም ምዘና ወቅታዊ፣ ከአድሎ የጸዳና የሥራ ዕቅድን
ማዕከል ያደረገ መሆኑን ማረጋገጥ፣
 ለሠራተኞች የስራ አፈፃፀም ስምምነት በአግባቡ መሰጠቱንና ውጤት
መሞላቱን ማረጋገጥ፣ የተሞላውን ውጤት በማኔጅመንት በጋራ
በመገምገም ማስተካከያ ማድረግ፣
 የተጠቃለለውን የአፈፃፀም ውጤት መነሻ በማድረግ
ሰራተኞች እንዲበረታቱ ማድረግ፤
 የክልል ተቋማት በስራቸው የሚገኙትን የዞንና ቅርንጫፍ
መ/ቤቶችን፣ የዞን ተቋማት ደግሞ በስራቸው የሚገኙ
ወረዳዎችንና ከተማ አስተዳደሮችን የስራ አፈፃፀም ምዘና
በአግባቡ መካሄዱን መከታተልና መደገፍ
አንቀጽ 15
በየደረጃው የሚገኝ ዳይሬክተር ፣ ቡድን መሪ ወይም ሌላ
የስራ ክፍል ኃላፊ ተግባርና ኃላፊነት
 
 የተቋሙን ተልዕኮ ፣ ራዕይ፣ ስትራቴጂና እሴቶች በሚገባ መረዳትና
ሠራተኞችን ለዕቅድ ትግበራ ማዘጋጀት፣
 ከተቋሙ የአመት እቅድ በመነሳት የአመት ፣ የስድስት ወር የሩብ
አመትና የወር እቅድ ማዘጋጀት
 ከስራ ክፍሉ የዓመት ፣ የስድስት ወር ዕቅድና ከሚጠበቅበት ተግባርና
ኃላፊነት በመነሳት የሠራተኞችን እቅድ ውል በመያዝ ሠራተኞችን
ለዕቅድ ትግበራ ማዘጋጀት፣
 በሚጠበቁ የአፈጻጸም ውጤቶችና የምዘና መስፈርቶች ላይ
ከሰራተኛው ጋር ለመወያየት የሚያስችል ዝግጅት ማድረግና
ሠራተኞች የተቋሙን ውጤታማነት እያሰቡ እንዲሰሩ ማገዝ፣
 የፈፃሚዎችን የግብዓት አቅርቦት ማሟላት እና የስራ ክፍሉ
ፈጻጸም የሚሻሻልበትን ስልት መቀየስና ተግባራዊ ማድረግ፣
 የሠራተኞችን የብቃት ክፍተት ለይቶ በማውጣት ዕውቀትን
፣ ክህሎትንና አመለካከትን ማሻሻል እና ለሠራተኞች
አስፈላጊውን ድጋፍና ምክር መስጠት፣
 ከስራ ክፍሉ የአፈጻጸም ምዘና ሂደት ሊነሱ የሚችሉ
አለመግባባቶችን ውጤት በሚያስገኙበት አግባብ መፍታት፣
 የሠራተኞች አፈጻጸም ምዘና ውጤት ወቅታዊ፣ ከአድሎ
የጸዳና የሥራ ዕቅድን ማዕከል ባደረገ መንገድ መሙላትና
የአፈጻጸም ምዘና ማጠቃለያ ማዘጋጀት፣
 የሰራተኞችና የቡድን የስራ አፈፃፀም መረጃዎች በአግባቡ እንዲያዙና
ጥቅም ላይ እንዲውሉ ማድረግ
 ዳይሬክተሮች፣ ቡድን መሪዎች እና ለዚህ ተግባር የተመረጡ የሥራ
ሃላፊዎች በሥራቸው ያሉ ሰራተኞችን በማብቃትና በአፈጻጸም ሂደት
የሚያጋጥሙ ችግሮችን በመፍታት ወይም እንዲፈቱ በማድረግ ላይ
ትኩረት አድርገው ይሰራሉ፤

 
አንቀጽ 16
የማንኛውም ሠራተኛ ተግባርና ኃላፊነት
 
 የተቋሙን ተልዕኮ ፣ራዕይ፣ ስትራቴጂና እሴቶች በሚገባ መረዳትና መተግበር፤
 የዳይሬክቶሬቱን /የቡድኑን ወይም የስራ ክፍሉን የመንፈቅና አመታዊ እቅድ
በሚገባ መረዳት
 ፈጻሚ ሠራተኛው የሚሰራበትን የስራ መደብ የተግባራት ይዘትና ወሰን በሚገባ
መገንዘብ
 የስራ አፈጻጸም ግብ ተኮር ተግባራትና የባህርይ ብቃት መለኪያዎችን
አፈጻፀማቸውን እና የተለያዩ የምዘና ደረጃዎችን የሚኖራቸውን አንድምታ ማወቅ
 የግል አፈጻጸም መረጃን መሰብሰብ፣ መለካትና መተንተን፤
 ከቅርብ የስራ ሃላፊው ከሚሰጠው የስድስት ወር ዕቅድ በመነሳት በየወሩ
የሚፈጽማቸውን ተግባራት በስራ መርሀ - ግብር ለይቶ መተግበርና
በወሩ መጨረሻ የአፈፃፀም ሪፖርት በጽሁፍ ለቅርብ ሃላፊው ማቅረብ፤
 የራስንና የሌሎችን እውቀት፣ ክህሎትና አመለካከት ለማሳደግ
ተገቢውን ጥረት ማድረግ
 ለዳይሬክቶሬቱ /ለቡድኑ ወይም ለስራ አባላት በመረጃ ላይ የተመሰረተ
የአፈጻጸም ግምገማና ምዘና በሚካሄድበት ወቅት ገንቢ አስተያየት
መስጠት
- ማንኛውም የመንግሥት ሠራተኛ በየስራ ቡድኑ ወይም
በየዳይሬክቶሬቱ በሚደረግ የአፈፃፀም ግምገማ በንቃት
በመሳተፍ በመ/ቤቱ ስትራቴጂያዊ ግብ ስኬት ሂደት ሁነኛ
ሚናውን መጫወት ይኖርበታል፤
ክፍል 4 

ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች

 አንቀጽ 17 

ከሠራተኛ አፈጸጸም ምዘና ጋር ተያያዥነት ያላቸው


ጉዳዮች አፈጻጸም
 ሰራተኛው ከአቅም በላይ በሆኑ ምክንያቶች የአፈፃፀም ምዘና ጊዜው ሳይደርስ ከሶስት

ወራት በላይ ተግባሩን ቢያቋርጥ ወይም ሊመዘን የማያስችለው ሁኔታ ቢፈጠር


በወቅቱ የሚደረግለት ምዘና አይኖርም፤ ሆኖም ለተለያዩ ጉዳዮች የሚወሰደው
ውጤት ተግባሩ ከመቋረጡ በፊት የነበረው የ6 ወሩ የምዘና ውጤት ይሆናል፡፡
 ከላይ በተራ ቁጥር 1 የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ ከአቅም በላይ

በሆኑ ምክንያቶች ከ6ወር በላይ የሥራ አፈፃፀም ምዘና ውጤት

የሌለው ከሆነ ሥራ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ዕቅድ ተሰጦት የተገኘ

የሥራ አፈፃፀም ምዘና ውጤት እንዲያዝ ከማድረግ ውጭ ወደኋላ ሄዶ

መያዝ አይቻልም።
አንዲት ሴት የመንግስት ሠራተኛ በሙከራ ቅጥር ላይ ያለች ከሆነና

ከአንድ ወር በላይ በወሊድ ምክንያት ከስራዋ ተለይታ ከቆየች

የወሊድ ፈቃዷን እንደጨረሰች የሙከራ ጊዜዋን እንድታጠናቅቅ

ይደረጋል፤
 እንደ የመስሪያ ቤታቸው የስራ ባህርይ ይህን መመሪያ አሻሽለው
መጠቀም የሚፈልጉ ተቋማት ካሉ መሰረታዊ መርሆዎችን ባልሸራረፈ
ሁኔታ አሻሽለው ለሲቪል ሰርቪስ እና ለሰው ሃብት ልማት ኮሚሽን
እያቀረቡ በማፀደቅ መጠቀም ይችላሉ፤
 እንደ ተቋሙ የሥራ ሁኔታ የባህርይ አመላካቾችንና መለኪያዎችን
መጨመርም ሆነ የክብደታቸውን መጠን ከፍ ወይም ዝቅ ማድረግ
ይቻላል፡፡
 የባህርይ አፈፃፀም በየጊዜው ክትትልና ግብረ-መልስ የሚያስፈልገው
ሲሆን፤ ውጤቱ የሚሞላው በየስድስት ወር መጨረሻ ይሆናል፡፡
 የሠራተኛው ዕቅድ አፈጻጸም ስምምነት የነባራዊ ሁኔታዎችን ግምገማ
መሰረት ያደረገ ለውጥ ሊደረግበት ይችላል፤
 የመንግስት ሠራተኞች የሥራ አፈፃፀም ውጤታማ አሠራር እንዲሰፍን
የሚያስችል የአቅም ግንባታ ስራ በየተቋሙ መከናወን ይኖርበታል፡፡
 በሥራ አፈፃፀም ምዘና ውጤት ላይ የሚቀርብ ቅሬታ በክልሉ
የመንግሰት ሠራተኞች የቅሬታ ማስተናገጃ ሥርዓት አግባብ
ይስተናገዳል፤
አንድ ሠራተኛ የ6 ወር ውል ከያዘ በኋላ በዝውውር ወይም በደረጃ ዕድገት
የሥራ መደብ ቢቀይር ወይም ወደ ሌላ መ/ቤት ቢዛወር በነበረበት
ውሉን ከያዘ እስከ ሶስት ወራት እና በላይ ሰርቶ ከሆነ ከነበረበት
እንዲመዘን ይደረጋል፡፡ ሆኖም ከሶስት ወራት በታች ከሆነ በተዛወረበት
ወይም የደረጃ ዕድገት ባገኘበት የስራ መደብ የዕቅድ ውል ይዞ
እንዲመዘን ይደረጋል፡፡
አንቀጽ 18
መመሪያውን ስለማሻሻል

ኮሚሽኑ ሲያምንበት ይህን መመሪያ ወደፊት


ሊያሻሽል ይችላል፡፡
 
አንቀጽ 19
ያስከመመሪያውን አለመፈጸም የሚትለው
ተጠያቂነት
በዚህ መመሪያ የተደነገገውን በማወቅም ሆነ
በቸልተኝነት ያልፈጸመ ወይም እንዳይፈጸም ያደረገ
፣ አላግባብ የሚጠቅም ወይም ሌላውን የመንግስት
ሠራተኛ መብት የሚጎዳ ተግባር የፈፀመ ማንኛውም
ሃላፊ ወይም የመንግስት ሠራተኛ አግባብ ባለው
ወንጀል ፣ የፍታ ብሄር እና የአስተዳደር ህግ መሰረት
ተጠያቂ ይሆናል ፡፡
 አንቀጽ 20
የተሻሩና ተፈፃሚ የማይሆኑ መመሪያዎች

 በጥቅምት ወር 2005 ዓ.ም የወጣውን መመሪያ ጨምሮ ከዚህ


መመሪያ በፊት የወጡ የመንግስት ሠራተኞች የሥራ አፈፃፀም ምዘና
መመሪያዎች እና ሰርኩላሮች ተሽረው በዚህ መመሪያ ተተክተዋል፡፡
 በዚህ መመሪያ ስለተመለከቱት ጉዳዮች ከዚህ መመሪያ ጋር የሚቃረኑ
መመሪያዎች ተፈፃሚ አይሆኑም፡፡
አንቀጽ 21
መመሪያው የሚጸናበት ጊዜ
 
ይህ መመሪያ ከ……ወር 2014 ዓ.ም ጀምሮ የጸና
ይሆናል ፡፡
እናመሰግናለን

You might also like