You are on page 1of 38

ቀን

ሶስት
ስነ-ምግባር እና የሙያ ስነ-ምግባር
የስልጠናው ይዘት
 ስነ-ምግባር
 የሙያ ስነ-ምግባር

1 4-3
ዓላማ
የዚህ ክፍል ዋና ዓላማ ተሳታፊዎችን ስለ ስነ-ምግባር እና የሙያ
ስነ-ምግባር ንድፈ ሃሳቦችን እና ተግባራትን ምንነት እንዲገነዘቡ
እና እንዲተገብሩ ማስቻል ነው፡፡

1 4-4
ዝርዝር ዒላማዎች
ከዚህ ስልጠና በኋላ ሰልጣኞች፡-
 የስነ-ምግባርን ጽንሰ ሐሳብ ይገነዘባሉ፣
 የሙያን ምንት ይገልጻሉ፣
 የስነ-ምግባር መርሆችን መግለጽ ይችላሉ፣
 የባለሙያ መገለጫዎችን ያብራራሉ፣
 የሙያ መርሆችን ይገነዘባሉ፡፡

1 4-5
"ስነ-ምግባር የሌለው ሰው በዓለም ላይ ብኩን የሆነ
እና ያበደ የዱር እንስሳት ማለት ነው" (ካሙስ)

4 - 66
1. የሥነ-ምግባር ጽንሰ ሃሳብ

A Video-Lecture by the
Institute of Public Development and
Management Studies
at the Ethiopian Civil Service University
የመነሻ ጥያቄዎች

1. ስነ-ምግባር ምን ማለት ነው?


2. የሥነ-ምግባር መሰረቶች ምን ምን ናቸው?

8
የስነ-ምግባር ምንነት

 ስነ-ምግባር ማለት የባህርይ ደረጃን የሚያሳይ ሲሆን የሰውን


ልጅ ደህንነት እና መልካም ነገሮችን የሚሰብክ ነው፡፡
 ስነ-ምግባር መልካም ነገሮችን እንዴት እንደምንፈጽም
የሚያሳይ ነው፡፡
 ስነ-ምግባር ግዴታ ላልሆን ነገር መታዘዝ ማለት ነው፡፡
 ስነ-ምግባር የአንድ ማህበረሰብ ደንብ ነው፡፡

9
የስነ-ምግባር መሰረቶች 

የግለሰብ
ስነ-ምግባር

ግብረ
ገብ/እሴቶች

ልምድ ቤተሰብ

ነባራዊ
አቻዎች ሁኔታዎች

10
ስነ-ምግባራዊ ቁርጠኝነትን ለማጎልበት የሚረዱ
ነገሮች
 የምናውቀውን ስነ-ምግባር ያለው ሰው ማሰብ
 ከዚህ ሰው ጋር የሚሄዱ ባህርያት ምን ምን
ናቸው?
 ለዚህ ሰው ስነ-ምግባር ጠቃሚ ነው ይላሉ?
 አንድ ሰው ስለ አንተ ቢጠየቅ፣ ስንቶቹ ለአንተ ስነ-
ምግባር ጠቃሚ ነው ይላሉ?
 አንተ ለሌሎቹ አርዓያ ብትሆን ምን ይሰማሃል?

11
4 - 11
የስነ-ምግባር መገለጫዎች 

ስነ-
ምግባር

ዜግነት

እንክብካቤ ታማኝነት

ፍትሃዊነት አክባሪነት

ኃላፊነት
12
ታማኝነት

 በማንኛውም ስራ ታማኝና ግብረ-ገባዊ መሆን


 ሚስጥራዊ መረጃዎችን መጠበቅ
 ውሸትን፣ ስርቆትን እና ማታለልን አለመታገስ
 ቃል የገቡትን ሆኖ መገኘት
 ሐቀኝነት

13
አክባሪነት

 በስራ ቦታችን ያሉ የባህላዊ ልዩነቶችን ከግንዛቤ በማስገባት


ማንኛውንም ሰው በትህትና እና በክብር ማስተናገድ
 ማዳመጥና በግልጽ ከደንበኞች ጋር መነጋገር፡፡ ይህም ጤናማ
የሆነ የእርስ በእርስ ግንኙነት እንዲፈጠር ያግዘናል፡፡
 ታጋሽነት
 ትጉህነት

14
ኃላፊነት

 ሰበብ አለማብዛት
 በስራ ቦታችን ለወሰናቸው ውሳኔዎች ኃላፊነት መውሰድ
 ግዴታዎቻችንን በሙሉ መውጣት
 ለደንበኞቻችን ከምንችለው በላይ ቃል አለመግባት

“ላለመምረጥ መምረጥ ምርጫ ነው"

15
ፍትሐዊነት
 የደንበኞችን፣ የሰራተኞችን እና የአጋሮችን ጭንቀት ማዳመጥ
 ለሁሉም ሰው በእኩል ማገልገል/ማስተናገድ
 ውሳኔዎችን ከመወሰናችን በፊት ጉዳዮችን ደግመን ደጋግመን
ማጤን

16
ተንከባካቢነት
 ከልብ በመነጨ ሁሉንም ደንበኛ እና ሰራተኛ መንከባከብ
 የጋራ ተጠቃሚነትን መሰረት ያደረገ የረጅም ጊዜ ግንኙነት
ለመገንባት መትጋት
 ከፍ ያለ ርህራሄ እና ለሌሎች መጨነቅ
 ይቅርባይነት
 አመስጋኝነት እና ቀና አመለካከት

17
ዜግነት

 የድርሻን መወጣት
 ታዛዥ መሆን
 ሕግን መሰረት አድርጎ መስራት
 የተቋማትን መረጃ በተደራጀ መልኩ መያዝ
 ደንቦችንና መመሪያዎችን ማክበር
 ጥሩ የሥራ ባልደረባ መሆን

18
ዓለም አቅፍ የስነ-ምግባር እሴቶች
1. ሀቀኝነት
2. አንድነት
3. ቃል ጠባቂነት
4. እምነት
5. ፍትሐዊነት
6. ተንከባካቢነት
7. አክባሪነት
8. ኃላፊነት
9. ለልህቀት ማገልገል
10. ተጠያቂነት
19
የስነ-ምግባር ፋይዳዎች

 ሰራተኞች ቁርጠኛ እንዲሆኑ ያደርጋል


 የተገልጋይ አመኔታ እና ዘላቂነት ያረጋግጣል
 የህግ ጥሰቶችን እና ቅጣቶችን ይቀንሳል
 የተገልጋይ እርካታን ይጨምራል
 ከባለ ድርሻ አካላት ጋር መልካም ግንኙነት ለመፍጠር ያስችላል
 ወጭን ለመቆጣጠር ይረዳል
 አፈጻጸምን ለማሳደግ ያግዛል
20
የስራ ስነ-ምግባር
 በሥራ ቦታ በጊዜ መገኘት
 ከሥራ አለመቅረት
 የሥራ ስነ-ስርዓት
 የሥራ መሳሪያዎችን በጥንቃቄ መያዝ
 ከሥራ ባልደረቦች ጋር ተባብሮ/ተመካክሮ መሥራት
 እምነት የሚጣልብን መሆን
 ትሁት መሆን
 የሥራ ተነሳሽነት
 ሥራ ወዳድነት
 አርዓያ መሆን
21
በሥራ ላይ የሚታዩ የስነ-ምግባር ጉድለቶች
 የጥቅም ግጭት
 አድሎ
 የሀብት ብክነት
 ማጭበርበር
 መረጃን ማዛባት
 መረጃን በትክክል አለመያዝ
 በጥቅማ ጥቅም መደለል
 ጉቦ
 አደራ መብላት
 ሀሜት/የአሉባልታ ወሬ
22
በሥራ ላይ የሚታዩ የስነ-ምግባር ጉድለቶች … የቀጠለ

 ውሳኔዎችን ከራስ ጥቅም አንጻር ብቻ መወሰን


 አለመግባባት/አለመናበብ
 ዝቅተኛ የደንበኛ አገልግሎት
 ውሸት
 ያለሙያ ሥራ መስራት
 ስንፍና
 ተስፋ ቢስነት

23
ለስነ-ምግባር ጉድለት እንደ ምክንያት የሚቀርቡ ሰበቦች

 ሁሉም ሰው እንደዚያ ነው/እኔ ከሰው በምን እለያለሁ


 የእኔ ስራ አይደለም
 ማንም ሰው ሊያውቅብኝ አይችልም
 የሚከፈለኝ በቂ አይደለም
 ይህ የእኔ ኃላፊነት አይደለም
 በመመሪያዎች እና ደንቦች ማመካኘት

24
የስራ ስነ-ምግባርን ለማጠናከር የሚረዱ መንገዶች
 ሁሉንም ሰራተኛ በእኩል ማየት
 እውቅና መስጠት
 ተገቢውን እርምጃ መውሰድ
 መግባባት
 ግልጸኝነት
 ስልጠናዎችን ማዘጋጀት
 የትግበራ እቅድ ማውጣት
 ገምቢ ግብረ መልስ መስጠት

25
የመወያያ ጥያቄዎች
1. እንደ አገርም ሆን እንደ ክፍለ ከተማችሁ የሚታዩ የጥሩ ስነ-
ምግባር መገለጫዎችን ዘርዝሩ፡፡
2. እንደ አገርም ሆነ እንደ ክፍለ ከተማችሁ የሚታዩ የስነ-ምግባር
ክፍተቶችን ለይታችሁ ተወያዩ፡፡
3. የስነ-ምግባር ክፍተቶች መነሻቸው ምን እንደሆነ ተወያዩ፡፡
4. በአገርም ሆነ በክፍለ ከተማችሁ ደረጃ የሚታዩ የስነ-ምግባር
ክፍተቶችን ለማረም የሚረዱ ምክረ ሃሳቦችን አቅርቡ፡፡
(ከግለሰብ፣ ከትምህርት ቤት፣ የስራ ኃላፊዎች፣ ደንበኞች፣
ከመንግስት ወዘተ ምን ይጠበቃል?) 26
2. የሙያ ስነ-ምግባር

27
የምንሰራው ሥራ ሳይሆን አሰራሩ ትልቅ ቦታ አለው፡፡

28
4 - 28
የመነሻ ጥያቄዎች

• ሙያ ምን ማለት ነው?

• ባለሙያዊነት ምን ማለት ነው?

• ባለሙያዊነት ምን ምን ጥቅሞች አሉት?

29
4 - 29
የሙያ እና የባለሙያዊነት አጭር መግለጫ

 አሁን ባለንበት ዘመን፣ የሲቪል ሰርቪስ መስሪያቤቶች


 ቀልጣፋ/ፈጣን ምላሽ የሚሰጡ እና
 ከዘመኑ ጋር አብረው የሚሄዱ መሆን አለባቸው
ይህም የሚያስፈልገው ለዜጎች የሚቀርቡ ምርቶች እና
የሚሰጡ አገልግሎቶች ወጪ ቆጣቢ መሆን ስላለባቸው ነው፡፡
 ይህ ደግሞ በቀጥታ ከዘመናዊው የመልካም አስተዳደር ጽንሰ
ሃሳብ ጋር የተገናኘ ነው፡፡ ይህም ደግም በሲቪል ሰርቪሱ
ባለሙያዊነት እንዲኖር ይሻል፡፡

30
የሙያ ምንነት

ሙያ
 አንድ ሰው የተሰማራበት/የሚሰራው ሥራ ወይም
 የተለየ የሥራ መስክ
 ከእነዚህ በተጨማሪም ሙያ ከሚከተሉት ጋር ግንኙነት
አለው፡-
ከፍ ያለ ማህበራዊ ክብር
ትምህርት
ብቃት
የባለሙያዎች ስብስብ
የሙያ ስነ-ምግባር ያለው ተብሎ ይገለጻል፡፡
31
ባለሙያ

ባለሙያ የሚባል ሰው፡-


 የተማረ/የሰለጠነ፣
 ብቃት ያለው፣
 ተነሳሽነት ያለው፣
 ያለአድሎ ህዝብን የሚያገለግል እና
 ማህበረሰቡን ለማገልገል በተዘረጋ ስርዓት በቁርጠኝነት
የህብረተሰቡን ፍላጎት የሚያሟላ ነው፡፡

32
ባለሙያዊነት

ባለሙያዊነት ማለት፡-
ጠንቃቃ ፣ የማይናወጥና ቀጣይነት ያለው

 ትህትና፣
 ቅንነት፣
 ታታሪነት፣
 በኃላፊነት ስሜት ሕዝብን የሚያገለግል እና
 ልህቀቱ ህግና ወቅቱ ከሚጠይቀው ቀድሞ የሚገኝ ነው፡፡
33
የሕዝብ አገልጋይ ባለሙያ መለያዎች

1. ታማኝነት
2. ገለልተኝነት
3. ግልጸኝነት
4. ትጉህነት
5. ሰዓት አክባሪነት
6. ውጤታማነት
7. ሚዛናዊነት
8. ብቁነት

34
2. ሁልጊዜም ለመማር
ቁርጠኛ መሆን
3. እውቀት
1. የንድፈ ሃሳብ የመፍጠር ችሎታ
እውቀት

የባለሙያ ብቃቶች
4. የንድፈ ሃሳብ እውቀትን
ተግባር የመለወጥ ችሎታ

6. ችግርን የመፍታት
አቅም

5. ትጋትና ቁርጠኝነት

4 - 35
ቁልፍ የሙያ ስነ-ምግባር የሚባሉት፡-

ለህብረተሰቡ
  ደህንነት፣ ጤንነት እና በጎ አድራጎት መትጋት
 በሙያው (ባለው አቅም) ብቻ ማገልገል
 ማንኛውንም ነገር ትክክለኛውን እና እውነት ተከትሎ መስራት
 የጥቅም ግጭት ውስጥ የማይገባ በሙያው እና በሙያው
መሰረት ብቻ መስራት
 ከአድ ውድድር ነጻ መሆን
 የሙያውን ክብር ጠብቆ መስራት
 እራሱንና ሌሎችን በቀጣይነት ማልማት

36
በኢትዮጵያ ውስጥ ባለሙያዊነትን የሸረሸሩት ነገሮች፡-

 በሲቪል ሰርቪሱ ያለ ኋላቀር አስተሳሰብ


 የእነሱ እና የእኛ አመለካከት
 በቂ ያልሆን የስራ መሳሪያዎች አቅርቦት እና ምቹ ያልሆነ የሥራ
ቦታ
 ፖለቲከኞች በባለሙያው ሥራ ጣልቃ መግባት
 ባለሙያው የፖለቲካ ውሳኔዎችን ወደ ጎን የመተው ችግር
 መሰረታዊ ፍላጎትን የማያሟላ የሲቪል ሰርቫንት ደመወዝ
 ምሁራን በፖለቲከኞች መገለላቸው
 ምሁራን ዳር ቆመው መመልከታቸው

37
የመወያያ ጥያቄዎች

1. በቦሌ ክፍለ ከተማ ከሙያ እና ባለሙያዊነት ጋር በተያያዝ


የሚታዩ ጠንካራ እና ደካማ ጎኖችን ለዩ፡፡
2. የቦሌ ክፍለ ከተማ ሰራተኞችን እና ኃላፊዎችን የሙያ ስነ-
ምግባር ገምግሙ፡፡
3. በቦሌ ክፍለ ከተማ ሙያ እና የሙያ ስነ-ምግባር እንዲጠናከር
መደረግ ያለባቸውን የመፍትሔ ሐሳቦች አስቀምጡ፡፡

38

You might also like