You are on page 1of 30

ክፍል ሁለት

ስስቸኳይ ሙስና መከላከል ምንነት፣


አስፈላጊነትና አሰራር

ነሐሴ /2015 ዓ.ም አዲስ አበባ


አስቸኳይ ሙስና መከላከል
ማለት

በተቋማት ውስጥ ሙስና ለመፈፀም የሚያስችል ዝግጅት


እየተደረገ መሆኑን ሲገመት ወይም ሲጠረጠር ወይም ጥቆማ
ሲደርስ ድርጊቱ ከመፈፀሙ በፊት አስቸኳይ የሙስና መከላከል
ሥራ በመሥራት ሂደቱ እንዲቋረጥ ወይም እንዲመክን ወይም
አስፈላጊውን የማስተካከያ እርምጃ እንዲወሰድ የማድረግ ተግባር
ነው፡፡
የአስቸኳይ የሙስና መከላከል ዓላማ

የመንግሥትንና የህዝብ ሀብት ለመመዝበር፣


ለማጭበርበር፣ ለመስረቅ፣ ለመዝረፍ፣ ግልጽ
የሆነ የመንግስት አሠራርን ለመጣስ በሀሳብ ደረጃ
የተጠነሰሰ ወይም በአሠራር ደረጃ የተዘጋጀ
የጥፋት አቅምን በማምከን ሙስናን የወንጀል
ድርጊት ከመሆኑ በፊት ወይም አስቀድሞ
የጥፋት አቅሙን ማድከም/ማሳጣት ነው፡፡
የአስቸካይ የሙስና መከላከል አስፈላጊነት

ሙስና ለመፈፅም የታቀደውን ድርጊት በማምከን የሙስና መከላከል ሥራን


ውጤታማ ማድረግ ስለሚያስፈልግ፣

በእውቀት እና በልምድ ማነስ ወደ ስህተት የሚገቡ አመራሮችንና


ሠራተኞችን እንዲሁም የመወሰን ሥልጣን የተሰጣቸውን አካላት ስህተት
ከመፈፃማቸው በፊት ጉዳዩን በማምከን አስፈላጊውን ማስተካካያ
እንዲያደርጉ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ፣

ሆነ ብለው ሙስና የመፈፀም ሃሳብ ያላቸው አካሎች ድርጊቱን


ከመፈፀማቸው እና የህዝብ ሃብት ከመዝረፋቸው በፊት ማስቀረት
ስለሚገባ፤
አስፈላጊነት....

ለምርመራና ክስ የሚባክነው ገንዘብ፣ ጊዜ፣ ጉልበት ለማስቀረት፤


በተቋም ውስጥ የግልፅነትና የተጠያቂነት አሠራር ለማስፈን፤
የሙስና ወንጀል ተከስቶ ወይም ተስፋፍቶ የሚያስከትለውን ኢኮኖሚያዊ፣
ማህበራዊ፣ ከባቢያዊና ፖለቲካዊ ኪሳራን ለማስቀረት አስቀድሞ መከላከል
ተገቢ በመሆኑ፤
ሙስና ለመሥራት የተመቻቹ ሁኔታዎችን በማምከን በአገሪቱ ውስጥ ጥራት
ያለው አገልግሎት ለመሥጠት ስለሚያግዝ፤
1. በቂ ዕውቀትና ልምድ፡-
በተቋም ውስጥ ለሙስና ተጋላጭ የሆኑ አሠራሮችን ለመገመት ወይም
የአስቸኳይ ሙስና ለመጠርጠር በሙስና ወንጀል ምንነት፣ መንስኤዎችና በሚያስከትለው ጉዳት
በመከላከል ዘዴዎች ላይ በቂ ዕውቀትና ልምድ መያዝ፣
መከላከል ጥቆማዎችን ለመቀበልና ለማጣራትና መፍትሄ ለመጠቆም በተከሰተው ጉዳይ
መርሆዎች ላይ በቂ ዕውቀትና ክሂሎት መያዝ፣
2. ቅንነት
በተቋም ለሙስና ተጋላጭ በሆኑ አሠራሮች ላይ የራስ ግምት ወይም ጥርጣሬ
ወይም በጠቋሚዎች የቀረቡ የሙስና መከላከል ጥቆማዎችን ተጨባጭ
መረጃዎችን በማግኘት ያለአድልዎ ሙያዊ ዕውቀትንና ክህሎትን ብቻ
በመጠቀም በቅን ልቦና መሥራትና አደናቃፊ አለመሆን፣
3. ምስጥር ጠባቂነት
በተቋም ለሙስና መከላከል የሚቀርቡ ጉዳዮችና ጠቋሚዎች ማንነት ምስጥራዊትን
መጠበቅ እና እንዲመለከት በህግ ከሚፈቀድ አካል ውጭ ለሌላ አካል ወይም ወገን
የአስቸኳይ ሙስናአሳልፎ አለመስጠት፣
መከላከል የማጣራት ሥራው ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ የመረጃ ምስጥራዊነትን በጥብቅ
ዲስፕሊን መከታተል፣
መርሆዎች 4. ቁርጠኝነት
በተቋም የሥራ እንቅስቃሴ ላይ በራስ ግምት በመነሳት ወይም በመጠራጠር ወይም
በጠቋሚዎች የቀረቡ የሙስና መከላከል ጥቆማዎችን በማጣራት ወቅታዊ የሆነ
የመከላከለያ እርምጃ እንዲወሰድ ለማድረግ የህዝብና የመንግሥት ሀብት ከምዝባራና
ብክነት ከማዳን አንፃር ሙሉ አቅምና እውቀትን አሟጦ መጠቀም፣
መርሆዎች….
5. ታጋሽነት
 በራስግምት ወይም በመጠራጠር ወይም በጥቆማ የቀረቡ
የሙስና መከላከል ጉዳዮችን በሰከነ አእምሮ በትዕግስት
በማየት በተጨባጭ መረጃ የተመሠረተ ማጣራት ሥራ
መሥራት፣
መርሆዎች….
6. በጋራ መሥራት
 በተለያዩ ዘዴዎች የቀረቡ የሙስና
መከላከል ጥቆማዎች ላይ
የተቋሙን የበላይ አመራርና
ኮሚሽኑን በማማከር መወሰን፣
 በተቋሙ ላይ የቀረቡ ጥቆማዎች
ስለተወሰዱ እርምጃዎችን
ለጠቋሚዎችን ማሳወቅ፣ ጥቆማ
አቅራቢዎችን ማመስገን፣
የአስቸኳይ የሙስና መከላከል አሠራር ሥርዓት መዘርጋት

 በተቋም የሥራ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ለሙስና


ያላቸው ተጋላጭነት ባለቸው አሠራሮች ላይ ቋሚ
የአስቸካይ መከላከል ሥራ ለመሥራት የሚያስችል
የአሠራር ሥርዓት መዘርጋትና መተግበር የሥነምግባር
መከታተያ ክፍል ዋና የሥራ አካል ማድረግ፣
በተቋም የአሰራር እንቅስቃሴ ሙስና እንዳይፈጸም በንቃት
መከታተል
 በተቋሙ ሙስና ለመፈጸም እንቅስቃሴ
እየተደረገ ያለውን ሙስና ለመገመት
ወይም ለመጠርጠር፣
 በመደበኛና ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ
የሚሰጡ አስተያየቶችን በልዩ ትኩረት
መከታተል፣
 ሙስና ይፈፃማል በተባሉ ጉዳዮች ላይ
ልዩ ትኩረት በመስጠት በመከታተል
መረጃ መያዝ፣
 በመሥሪያ ቤቱ ሠራተኞች የሚወሩ
ሃሜቶችን አና ሹክሹክታዎችን ሁሉ
ሳያቃልሉ ትኩረት በመስጠትና በመቃኘት
መከታተል፣
የአስቸኳይ
ሙስና መከላከል
እንዴት
ይከናወናል?
የሥነምግባር መከታተያ ክፍል ከጠቀቋሚዎች ወይም ከሌላ አካል የተገኘው
መረጃ አስቸኳይ የሙስና መከላከል ስራ ሊሰራበት እና በአፋጥኝ የማስተካከያ
እርምጃ ሊወሰድ የሚገባ መሆኑን ሲያምንበት አስቸኳይ የሙስና መከላከል
ስራ በመስራት ሂደቱን ማስተካከል እንዲሚችል የስነ-ምግባር ግንባታ እና
ሙስና መከላከል አሰራር ደንብ ቁጥር 11/2015 አንቀጽ 22 መሰረት
ተደንግጓል፡፡ በዚህ መሠረት ተገቢውን የሰነድ እና የሰው ማስረጃ በማደራጀት
ከተቋሙ የበላይ ሀላፊ ጋር ስለ ጉዳዩ በቅድሚያ ያሳውቃል፡፡
በሚቀር
በው
የውሳኔ ስለ አስቸኳይ የሙስና
መከላከል ስራው
ሀሳብ እውቅና እንዲኖረው፤
ላይ
የመጨ እንዲቆም
ረሻ ለሚመለ
ውሳኔ ከተው
የስራ
እንዲሰ ክፍል
ጥና ትዕዛዝ
ተፈጻሚ እንዲሰጥ
እንዲሆ ፤

የሚያደ ለስራው አስፈላጊውን
ርግ ድጋፍ እንዲያደርግ፤
በመሆኑ
ነው፡፡
የቀጠለ

የበላይአመራሩ እናመከታተያ ክፍሉ ከተስማሙበት የአስቸኳይ የሙስና መከላከል ሥራው


ሊቋራጥ ይችላል፡፡
ከተቋም የበላይ አመራር የሚጠበቅ ቁርጠኝነት፣ ክትትልና ድጋፍ

የተቋማት የበላይ አመራሮች


 የተቋም የበላይ አመራር ሙስና መከላከል የሥራቸዉ

ዋነኛ አካል የማድረግ፣


 ለሚከናወኑ የአስቸኳይ ሙስና መከላከል ሥራ
አስፈላጊዉን ድጋፍ የመስጠት፣
 ለሚቀርቡ የአስቸካይ ሙስና መከላከል ጥያቄዎች

አፋጣኝ ምላሽ በመስጠት ድርጊቱ እንዲመክን አፈጣኝ


ውሳኔ የመስጠት፣
 የሥራ ክፍሎች የተለያዩ ማስረጃዎች ሲጠየቁ እንዲሰጡ

መመሪያ የመስጠት፣
 የተጠቆሙ የመፍትሄ ሀሳቦች ተግባራዊ እንዲሆን
የማድረግ፣
የቀጠለ
 በአስቸኳይ ሙስና መከላከል ጉዳይ ላይ የተቋሙ የበላይ አመራር በሚሰጠው
ማብራሪያ ላይ ሁለቱም (የሥነምግባር መከታተያ ክፍሉና የበላይ አመራሩ
በመረጃ በተደገፋ ማብራሪያ) ከተስማሙበት የአስቸኳይ የሙስና መከላከል
ሥራውን ማቋራጥና ስለአፈፃፀሙ ለኮሚሽን ሪፖርት ማቅረብ፣
 የሥነምግባር እና የፀረ ሙስና መከታተያ ክፍል በተቋሙ የበላይ አመራር
የተሰጠው ማብራሪያ ላይ ከስምምነት ካልደረሰና የያዘቸው መረጃዎች
አስቸኳይ ሙስና መከላከል ሥራ መሥራትን የሚጠይቅ መሆኑ በቂ ማሳያዎች
ካሉት ጉዳዩን ለሥነምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ማቅረብ፣
 ከኮሚሽኑ የመጨረሻ ውሳኔ ማግኘት፣ ፣
የቀጠለ

 በኮሚሹ ውሳኔ የአስቸካይ ሙስና መከላከል ስራ ጥናት ከተካሄደ


በዋላ የውሳኔ ሀሳብ ይቀርባል፤
 የተሰጠው ምክረ ሀሳብ በተቋም የበላይ አመራር ተቀባይነት
አግኝቶ እርምጃ ካልተወሰደበት የሥነምግባር መከታተያ ክፍሉ
ለኮሚሽኑ ሪፖርት ያደርጋል ፤
 ኮሚሽኑም ጉዳዮን የመመርመርና የመክሰስ ሥልጣን ለተሰጠው
አካል ያሳውቃል፡፡
ዝርዝር ሂደት በሚያሳይ
የማጣራት ስራ በማከናወን ሁኔታ ከውሳኔ ሀሳብ ጋር
ለበላይ ሀላፊ የውሳኔ ሀሳብ
ማቅረብ ሪፖርት ለተቋሙ የበላይ
ሀላፊና ለኮሚሽኑ ማቅረብ ፡፡

የውሳኔ ሀሳቡ እንደተገኘው


መረጃ እና ማስረጃ አንጻር
ሊቀርብ ይችላል፡፡
በተደረገው ለሙስና /
የማጣራት
ሥራ ለዝርፍያ ከዝርፊያ
ስምምነት ተባባሪ የዳነውን
ላይ የነበረ የመንግስት
የተደረሰበት የሥራ ና የህዝብ
ና በተቋሙ ሃብት
የበላይ
ክፍል በጥንቃቄ
ሃላፊ አመራርና በማስላት
እውቅና ሠራተኞች መረጃ
ያገኘውን አግባብ መያዝና
የውሳኔ ባለው ህግ ለኮሚሽኑ
ሃሳብ ተጠያቂ ሪፖርት
ተግባራዊ
መሆኑን እንዲሆኑ ማድረግ፡፡
መከታተል ማድረግ፣
ውጤት

ዉስን የሆነዉን ሃብት ጠንካራ የአሰራር


ሊባክን የሚችልን ሃብት
ለታለመለት አላማ ለማዋል ሥርዓት እንዲፈጠር
መታደግ ያስችላል፤ ያስችላል፣
ያደርጋል፡
ችግሩ ከተከሰተ በኋለ የችግሩን ለሃገር ጠቃሚ በሆነ ተግባር ላይ
በችግሩ ምክንያት በወንጀለኞች
ፈጣሪና የባከነውን ሃብት ሊሰማሩ የሚችሉ ዜጎችን በችግሩ
በቤተሰቦች ሊደርስ የሚችለውን
ለማግኘት የሚባክነውን ተጨማሪ ውስጥ ተዘፍቀው እንዲባክኑ ከማድረግ
ያድናል፣ ማህበራዊ ቀውስ ይቀርፋል፣
የሃብት ብክነት ያስቀራል፣

ወንጀለኞችን ለማስተዳደር
የሚወጣ ወጪን ይቀንሳል
የማጣራት ሥራው እንዴት ይከናወናል?

 ለሙስና ዝግጅት ላይ ስለመሆኑ በአሠራሩ ላይ በቂ ግንዛቤ መያዝ፣


 ስለአስቸካይ ሙስና መከላከል የተቋም የበላይ አመራር ማማከር፣
 ለሙስና ዝግጅት ላይ ያለውን አሠራር ሂደት የሥራ ፍሰትን መረዳት፣
 ለአሠራር ቅልጥፍና በተዘጋጀው የሥራ መመሪያ ላይ ግንዛቤ መያዝ፣
የማጣራት ሥራው እንዴት ይከናወናል?

 ለሙስና ዝግጅት ላይ ያለው አሠራርን ተቋሙ ካለው ህግና ከአሠራር መመሪያ


ጋር በማነፃፀር ልዩነትን መፈለግ፣
 በሙስና ዝግጅት ላይ የሚገኘው የሥራ ሂደት የሥራ እንቅስቃሴ ላይ ቅኝት
ማካሄድ፣
 የአሰራር ሂደት አሠራር ላይ ዕውቀትና ልምድ ካለቸው አካላት መረጃ ማግኘት፣
 የተመሳሳይ አሠራር ተሞክሮዎችን ማግኘት፣
 አስፈላጊ ሲሆን የሙያ ዕገዛ ከኮሚሽኑ መጠየቅ፣
ባህርያቸው ለሙስና ተጋላጭ የሚሆኑ አሠራሮችና የስራ ክፍሎች

 የዕቃና አገልግሎት ግዥዎች፣


 የቅጥር፣ የደረጃ ዕድገት፣ ዝውወርና ምደባ አሰጣጥ፣
 ከሥልጠና ጋር የተያየዙ ክፍያዎች ፣
 የተሽከርካሪ ጥገና ሥራዎች፣
 የተሽከርካሪ ስምሪትና የነዳጅ አጠቃቀም፣
 የአበል ክፍያዎች፣
 የጥናትና ምርምር ሥራዎች፣
 የሆቴል አገልግሎት ግዥዎች፣
 የግንባታ ግዥና አፈፃፀሞች ወዘተ ናቸው
የአስቸኳይ የሙስና መከላከል ሥራ ሪፖርት አቀራረብ

 የአስቸኳይ የሙስና መከላከል


የማጣራት ሥራ ዝርዝር ሂደት
በሚያሳይ ሁኔታ ከውሳኔ ሀሳብ ጋር
ሪፖርት ማዘጋጀት፣
 የውሳኔ ሀሳቡ እንደተገኘው የመረጃ
ምንጭና ዓይነት እንዲሁም ማስረጃ
አንጻር ማቅረብ፣
የአስቸካይ ሙስና መከላከል የውሳኔ ሃሳብ አማራጮች

1. የተጀመረው ጉዳይ ሂደት ሙሉ በሙሉ በመሰረዝ አዲስ ሂደት እንዲቀጥል


የውሳኔ ሀሳብ ማቅረብ፣
2. የተጀመረው ጉዳይ ሂደት ክፍተት ተስተካክሎ እንዲቀጥል የሚል የውሳኔ ሀሳብ
ማቅረብ፤
3. የቀረበው ጥቆማ ወይም መረጃ መሠረተ ቢስ ነው በሚል ሂደቱ በተጀመረበት
ሁኔታ እንዲቀጥል ማድረግ፣
4. ጉዳዩ የመመርመርና የመክሰስ ሥልጠን ለተሰጠው አካል እንዲላክ ማድረግ፣
የአስቸኳይ ሙስና መከላከል ሥራ ሪፖርት አቀራረብ አጻጻፍ

 የቀረበው ጉዳይ ምንነት


 የመረጃ ምንጭ
 በማጣራት ሂደቱ ወቅት የታዩ ሠነዶችና ልዩ ልዩ መረጃዎች፣
 መረጃው የተሰበሰበበት መንገድ
 ግኝትና የውሳኔ ሀሳብ፣
 ማዳን የተቻለውን ጉዳይ በገንዘብ በመተመን፣
 የማጣራት ሥራውን ያካሄደው ባለሙያ ስም፣ፊርማ፣ቀን
 የበላይ ኃላፊ ውሳኔ፣ ማህተም፣
የሰው ልጅ ሰው በመሆኑ ምክንያት ለሚኖርባት ምድር ልዩ ሃላፊነት
አለበት

በ1930 በካናዳ
የውሃማስተላፊያ
ቱቦ ጥራት
ሲፈተሽ
ማጠቃለያ
 መገመት፣ መጠራጠር፣ ጥቆማ መቀበል
 ማማከር፣ መረጃ መሰበሰብ፣ ማጣራት፣ የማሻሻያ ሀሳብ ማቅረብ
 ሪፖርት ማቅረብ፣ የውሳኔ ሀሳብ ተግባራዊነትን መከታተልና ማረጋገጥ

You might also like