You are on page 1of 48

1

1. መግቢያ
1.1 ታሪካዊ ሂደት፣
መንግሥት ሙስና የሚያስከትለውን ከፍተኛ የሆነ
ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ቀውስ በመረዳት ችግሩ
የከፋ ደረጃ ላይ ከመድረሱ በፊት ለመከላከል እና ለመዋጋት
እንዲረዳ ተገቢውን ትኩረት በመስጠት ግንቦት 1993 ዓ.ም
የሥነ ምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽንን እንዲቋቋም
አድርጓል፣

ኮሚሽኑም የተሰጡትን ተግባር እና ኃላፊነቶች


እንዲወጣ አስፈላጊውን የአደረጃጀት፣ ቁሳዊና የገንዘብ
ሀብት በመመደብና በማጠናከር ምቹ ሁኔታዎችን
በመፍጠር መንግስት ቁርጠኝነትና ድጋፍ ያለው
ለመሆኑ አሳይቷል፡፡
2
ሆኖም ግን እያንዳንዱ ተቋም ሙስናን ለመከላከልና
ለመዋጋት የሚረዳው አደረጃጀት ፈጥሮ ወደ ትግሉ
በቁርጠኝነት እንዲገባ ያግዘው ዘንድ የሥነምግባር መከታተያ
ክፍሎችን የሚመለከት ደንብ ቁጥር 144/2000 ፀድቆ ወደ
ተግባር የተገባ ቢሆንም በተለያዩ ምክንያቶች የተገኘዉ
ዉጤት በሚጠበቀው ደረጃ ላይ አልደረሰም፡፡
ይህም የእስካሁኑ ሂደት በሙስና መከላከል ረገድ የተቋማት
3

ሚና ውስንነት እንደነበረበት በመረዳት እያንዳንዱ ተቋም


በራሱ የተቀናጀ ሙስናን የመከላከል ስትራቴጂ በመንደፍ
ሙሰናን የመከላከል ተግባር እንዲያከናውን አዲስ አሠራር
መዘርጋት አስፈልጓል፡፡

3
1.2 የተቀናጀ ሙስናን የመከላከል ስትራቴጂ
ዝግጅት ዓላማ
o ሙስናን በመከላከል ዙሪያ የተቋማትን ሚና ማመላከት፣
o ስትራቴጂና ዕቅድ ነድፎ ቀጣይነት ባለው መልኩ መንቀሳቀስ
አስፈላጊ መሆኑን ማስገንዘብ፣
o የተቀናጀ ሙስናን የመከላከል ስትራቴጂ አዘገጃጀቱን
በማመላከት፣ ስርአቱ እንዲዘረጋ ሙያዊ ድጋፍ ለማድረግ
የሚቻልበትን ሁኔታ ማመቻቸት፣
o በተለያየ ደረጃ የሚገኙ የመቆጣጠርና መከታተል ሃላፊነት
ያለባቸዉ የመንግስት አካላት በተቋማት ውስጥ ሙስና
ለመከላከል የሚከናወኑ ተግባራትን በቅርበትና በትኩረት
ለመከታተልና አቅጣጫ ለመስጠት የሚረዳ ስርአት
ለመቀየስ፣

4
• ተቋማቱ ሙስናን ከመከላል አንጻር ከኮሚሽኑ፣ እርስ
በርሳቸዉና ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር
ተቀናጅተው ሊሰሩ የሚችሉበትን ሁኔታ ለማሳየት፣
• የሙስና መከላከያ ሥራን በማከናወን በተቋማት
መካከል መሰረታዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ የተጠናከረ
ወጥነት ያለዉ አሰራር ለመቀየስ፣
• የኪራይ ሰብሳቢነት ዝንባሌንና ሙስናን በመከላከሉ
የሚከናወኑ ሥራዎችን ለመመዘንና ለመገምገም
የሚያስችል ሥርአት በመዘርጋት፣ የእርምት እርምጃ
ለመውሰድ፣
• ጠንካራ አፈጻጸሞችን እዉቅና ለመስጠት የሚያግዝ
ስርዓት ለመዘርጋት፣
5
1.3 የተቀናጀ ሙስናን የመከላከል ስትራቴጂ
አስፈላጊነት/ጠቀሜታዎች
• በሙስናና ብልሹ አሰራር ምክንያት ሊባክን የሚችልን ሃብት
መታደግ ያስችላል፤
• ዉስን የሆነዉን ሃገራዊ ሃብት ለታለመለት አላማ ለማዋል
ያስችላል፣
• በመንግስት ተቋማት ለሙስናና ብልሹ አሰራር ክፍተት
የማይፈጥር ጠንካራ የአሰራር ሥርዓት እንዲፈጠር ያደርጋል፡
• ችግሩ ከተከሰተ በኋለ የችግሩን ፈጣሪና የባከነውን ሃብት
ለማፈላለግና ለማግኘት የሚባክነውን ተጨማሪ የሃብት ብክነት
ያስቀራል፣
• በቀላሉ ተምረውና ተስተካክለው ለሃገር ጠቃሚ በሆነ ተግባር ላይ
ሊሰማሩ የሚችሉ ዜጎችን በችግሩ ውስጥ ተዘፍቀው እንዲባክኑ
ከማድረግ ያድናል፣
• በችግሩ ምክንያት በወንጀለኞች ቤተሰቦች ሊደርስ የሚችለውን
ማህበራዊ ቀውስ ይቀርፋል፣
• ወንጀለኞችን ለማስተዳደር የሚወጣ ወጪን (ከማረሚ ቤቶችና6
• ተቋማት በባለቤትነት መንፈስ የሚያደርጉት ቀጥተኛ
ተሳትፎ መሆኑ፣
• የአንድ ተቋም/የሥራ ክፍል ጉዳይ ሳይሆን የሁሉም
አካላት ድርሻ የሚረጋገጥበት አሠራር መፍጠር
የሚያስችል መሆኑ፣
• የተቀናጀ አሠራር የሚፈጥር መሆኑ፣
• ሙስናና ብልሹ አሠራርን ከመከላከል አንጻር
በእያንዳንዱ ተቋም ያለውን ተጨባጭ የሆነ
ቁርጠኝነት መመዘን የሚያስችል መሆኑ፣
እውቅና ለመስጠትና ስህቶችን/ችግሮችን በወቅቱ
• •
ለማረም የሚያስችል መሆኑ፣
7
• የእስካሁን የተቋማት እንቅስቃሴ በአመለካከትም ሆነ
በድርጊት ሲመዘን አመርቂ አለመሆን፣
• አለም አቀፍ ፈጣን ለውጦችና ተለዋዋጭ የሆነው
የሙስና አፈጻጸም ባህሪያት/ዘዴዎች፣
• የተቀናጀ የሙስና መከላከል ስትራቴጂን ተግባራዊ
ያደረጉ ሀገራት ስኬታማ ተሞክሮዎች፣
• እየተባባሰ በመጣው የመልካም አስተዳደር ችግር እና
ኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከት ሳቢያ የመንግስት
የመልካም አስተዳደር ግንባታ አቅጣጫ ዋነኞቹ
ተጠቃሾች ናቸው፡፡
8
 መንግስት የሙስና ወንጀል አስከፊ ደረጃ ላይ ከመድረሱ
በፊት ተገቢዉን ትኩረት ሰጥቶ በቁርጠኝነት ችግሩን
ለመጋፈጥ እየተንቀሳቀሰ የሚገኝ በመሆኑና ተቋማትም
የዚሁ ስርዓት ፖሊሲዎችንና ህጎችን የማስፈጸም ሃላፊነት
ያለባቸዉ እንደመሆኑ ሙስናን እና ብልሹ አሰራርን በጽናት
የመከላከልና የመዋጋት ሃላፊነት ይኖርባቸዋል፡፡
 ሙስናና ብልሹ አሠራርን ለመታገልና ለማታገል በመንግስት
በኩል ያለው ፖለቲካዊ ቁርጠኝነት እንደመልካም አጋጣሚ
በመዉሰድ የፀረ ሙስና ትግሉን ማቀጣጠል ከእያንዳንዱ
የመንግስት አስፈጻሚ አካል የሚጠበቅ ምላሽ መሆን
ይኖርበታል ፡፡

9
የኢፌዲሪ ሕገ መንግስት ከተመሠረተባቸው መርሆዎች አንዱ በህገ
መንግስቱ አንቀጽ 12 የተመለከተው የመንግስት አሠራርና ተጠያቂነት
የሚለው ነው፡፡
አንቀጽ 12
• የመንግሥት አሠራርና ተጠያቂነት
1. የመንግሥት አሠራር ለሕዝብ ግልጽ በሆነ መንገድ መከናወን አለበት፡፡
2. ማንኛውም ኃላፊ የህዝብ ተመራጭ ኃላፊነቱን ሲያጓድል ተጠያቂ ይሆናል፡፡
3. ሕዝብ በመረጠው ተወካይ ላይ እምነት ባጣ ጊዜ ከቦታው ለማንሳት
ይችላል፡፡ ይላል
ይህ የሚያሳየው ማንኛውም የመንግስት መስሪያ ቤት አሠራሩን ለሕዝብ ግልጽ
የማድረግ ሕገመንግስታዊ ግዴታ እንዳለበት ነው፡፡ ስለሆነም አንድ
የመንግሥት መስሪያ ቤት አሠራሩን ግልጽ የሚያደርገው ስለፈለገ ሳይሆን
ሕገመንግስታዊ ግዴታም ስለአለበት ነው፡፡

10
• የሥነ ምግባር መከታተያ ክፍሎችን አሠራር
ለመወሰን የወጣ ደንብ ቁጥር 144/2000፣
 በእያንዳንዱ ተቋማት ውስጥ ሙስናንና ብልሹ አሠራርን የመከላከሉ
ተግባር የተቋሙ በዋነኝነትም የበላይ ሃላፊዎች ድርሻ ሲሆን የሥነ
ምግባር መከታተያ ክፍሎችን ለማቋቋም በወጣው ደንብ ቁጥር
144/2000 አንቀጽ 9 መሠረትም የተቋሙ የበላይ ኃላፊ በርካታ
ሃላፊነቶች ተሰጠዋቸዋል፡፡
ከነዚህም ውስጥ ፡-
1. በመሥሪያ ቤቱ ወይም በልማት ድርጅቱ መልካም
ሥነምግባር ያለው የሥራ መሪና ሠራተኛ እና የሰመረ
የሥራ ግንኙነት እንዲኖርና መልካም አስተዳደር እንዲሰፍን
ክትትል የማድረግ፣
11
2. የመሥሪያ ቤቱ ወይም የልማት ድርጅቱ የአሠራር ሥርዓት
ለሙስናና ለብልሹ አሠራር የማይመች፣ ግልጽነትና
ተጠያቂነት ያለበት እንዲሆን የማድረግ፣
3. የመሥሪያ ቤቱን ወይም የልማት ድርጅቱን የሥነምግባር
መከታተያ ክፍል ኃላፊነቱን ለመወጣት በሚያስችለው
አኳኋን በተፈላጊው የሰው ኃይልና አገልግሎቶች በማሟላትና
ጥቅማ ጥቅሞች በመስጠት ለክፍሉ ምቹ የሥራ ሁኔታን
የመፍጠርና ሌሎችም ተያያዥነት ያላቸው ኃላፊነቶች
ተደንግገዋል፡፡
እነዚህን ኃላፊነቶች አለመወጣት ተጠያቂነትን ከማስከተል
ባሻገር ለሙስናና ብልሹ አሰራር መስፋፋት እድል የሚፈጥር
በመሆኑ የተቋማት የበላይ ኃላፊዎች ትኩረት ሰጥተዉ
ሊተገብሯቸዉ ይገባል ማለት ነው፡፡

12
ተጨማሪ ህጎች፡-
• የኮሚሽኑ የተሻሻለዉ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር
433/97 እና 883/2007፣
• የፀረ-ሙስና ልዩ የሥነ-ሥርዓትና የማስረጃ ህግ
አዋጅ ቁጥር 434/97 እና 882/2007፣
• የሙስና ወንጀሎች ለመደንገግ የወጣ አዋጅ
881/2007፣
• የሀብት ማሳወቂያና ማስመዝገቢያ አዋጅ ቁጥር
668/2002፣
እነዚህና መሰል አዋጆችና ደንቦች እያንዳንዱ ተቋም፣
የተቋሙ የበላይ ሃላፊ እና መላው አባላት በፀረ-ሙስና
እንቅስቃሴ ዙሪያ ሊኖራቸው የሚገባን ሚና
አመላክተዋል፡፡

13
 ሁሉም የመንግስት ተቋማት ለህዝብ ጥቅምና አገልግሎት የተቋቋሙ
መሆናቸው፣
 የመንግስት ተቋማት በህዝብ ሃብት ላይ የተመሰረቱ መሆናቸው፣
 የህዝብን ሁለንተናዊ ጥቅም የመጨረሻ ግብ መሠረት በማድረግ
የተቋቋሙ መሆኑ፣
በዚህም ሳቢያ፡-
 የህዝብ ሃብትን መሠረት አድርገው የሚሰጡት ህዝባዊ አገልግሎት
ውጤታማ ይሆኑ ዘንድ አሠራራቸው በግልፅነትና በተጠያቂነት
መርህ ላይ የተቃኘ መሆኑ ወሳኝነት ይኖረዋል፡፡ ካልሆነ ግን
በውስጣቸው የሙስናና የብልሹ አሠራር ችግር እንዲያቆጠቁጥና
እንዲስፋፋ እድል በመስጠት ተቋማቱን ለሃብት ብክነትና ለመልካም
አስተዳደር እጦት በመዳረግ አጠቃላይ የተቋቋሙለትን ዓላማ
እዳያሳኩ ከፍተኛ የሆነ እንቅፋት የሚፈጥር ይሆናል፡፡

14
 የኪራይ ሰብሳቢነት ዋነኛ ምንጭ ከሰዎች አመለካከት ጋር በእጅጉ
የተቆራኘ ነው፡፡ የዚህ ችግር መገለጫ የሆነው ሙስናና ኢ-
ሥነምግባራዊ ድርጊት መንስዔው ከሥነምግባር ዝቅጠትና
የሥነምግባር መላሸቅ ወይም መሸርሸር ጋር የተያያዘ ሆኖ
ይስተዋላል፡፡ ይህም በመሆኑ በተቋማት ውስጥ በተለያየ ደረጃ
የሚገኙ የሥራ ሃላፊዎች ራሳቸውንም ሆነ አካባቢያቸውን ከዚህ
አይነቱ ስብዕናን ከሚያጎድፍ ተግባር በመጠበቅ የየተቋማቱን
መልካም ሥም ጠብቀው የመንቀሳቀስ ሃላፊነት ከመወጣት ጋር
የተያያዘ ሞራላዊ ግዴታ ነው፡፡
 ሙስና የሀገራችን ሁለንተናዊ ልማት ሊያናጋ የሚችል አደጋ በመሆኑ
ማንኛውም ሀገር ወዳድ ዜጋ በንቃት ሊታገለው የሚገባ ስጋት
እንደመሆኑ በመንግስት ተቋማት ውስጥ የሚገኙ የበላይ
ሃላፊዎችም ሆኑ በየደረጃው የሚገኙ ባለሙያዎች ይህን ችግር
በመቅረፍ ዙሪያ ካሉ አስገዳጅ ህጋዊ ሁኔታዎች በዘለለ ለትውልድ
የሚጠቅም ቅርስ ከማበርከት አንጻር በእኔነት ስሜትና በያገባኛል
ባይነት መንፈስ የበኩላቸውን የዜግነት ሞራላዊ ግዴታ የመወጣት
ሃላፊነት አለባቸው፡፡
15
ተቋማት ኃሃላፊነታቸውን በአግባቡ
ለመወጣት እንዲችሉ የተቀመጠ
አደረጃጀት
 በተቋማት ውስጥ ሙስናን የመከላከል ኃላፊነቱ ሙሉ
በሙሉ የመንግስት መስሪያ ቤቱ የበላይ ሃላፊ ነው
ቢባልም ይህን ሃላፊነት ለመወጣት የኮሚሽኑ ድጋፍ
እንደተጠበቀ ሆኖ እገዛ የሚያደርግና የሚያማክር
በእያንዳንዱ የመንግስት መሥሪያ ቤት እና የመንግስት
የልማት ድርጅት የሥነምግባር መከታተያ ክፍል ሊኖር
እንደሚገባ በተሻሻለዉ የኮሚሽኑ ማቋቋሚያ አዋጅ
ቁጥር 433/97 እና 883/2007 ተደንግጓል፣

16
5. ¾}k“Ë S<e“” ¾SŸLŸM eƒ^‚Í= U”’ƒ
• የ}k“Ë ¾ሙስና መከላከያ ስትራቴጂ ስንል የረዥም ጊዜ
ግብን ከማሳካት አንጻር በተቋማት ዉስጥ ሙስናን
በመከላከል ረገድ የሚቀረጹና የሚከወኑ ተልዕኮዎችን
ለማሳካት የሚረዱ አጠቃላይ የረዥም ጊዜ አቅጣጫዎችን፣
እቅድን፣ ተግባራትንና ዉሳኔዎችን የሚያካትት ይሆናል፡፡
• የተቋማት መሪዎችንና ሰራተኞችን ስለድርጅታቸው ከሙስናና
ብልሹ አሰራር አኳያ ያሉበትን ነባራዊ ሁኔታ፣ የመጪዉን
ጊዜ በአግባቡ ለመረዳትና በማስተካከል የተሻለ ደረጃ ላይ
ለመድረስ ያስችላል፣
የሙስና ወንጀልን መከላከል ሲባል እንደማንኛውም የወንጀል
(የአደጋ) መከላከል ተግባር ሆኖ ነገር ግን ከሙስና ልዩ ባህሪያት
አንጻር፣ የሙስናና ብልሹ አሰራር ወንጀሎች የሚያስከትሉትን
ከፍተኛ የሆነ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ኪሳራ
ለማስቀረት ወይም ለመቀነስ በሚያስችል መልኩ በማከናወን
የችግሩን ምንጭ የማድረቅ ተግባር ነው፡፡
17
• ¾}k“Ë S<e“” ¾SŸLŸM eƒ^‚Í=” ሰፋ ባለዉ
አካባቢያዊ ሁኔታ ስንመለከተዉ
– ሁለንተናዊ በሆነ መልኩ ሊታይና በሃገራችን ዉስጥ
ጠንካራ የሆነ /National Integrity System/
በመፍጠርና በማጠናከር የሚፈጸም ሲሆን ይህም
ሙስናን በቁጥጥር ስር ለማዋል የህግ አውጪው
(ፓርላማ)፣ የህግ አስፈጻሚው፣ የዳኝነት አካሉ፣ የዋና
ኦዲተር፣ የሙያ ማህበራት፣ ነጻ ሚዲያዎች እና
ህብረተሰቡ በተለያዩ አደረጃጀቶቻቸው የሚጫወቱትን
ሚና በማጠናከር አንዱ ሌላውን በአግባቡ
የሚጠብቅበትን ሁኔታና ኃላፊነት በአግባቡ እንዲወጣ
የሚከታተል፣ የሚጠበቅበትን ሚናና ኃላፊነት ባልተወጣ
ጊዜ ከፍተኛ ጉዳት ከመድረሱ በፊት ተገቢውን
ማስተካከያና እርማት በማድረግ ወደስርዓቱ እንዲመለስ
ለማድረግ የሚያስችል ስርዓት ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ 18
• ጠባቡን ከባቢያዊ ሁኔታን ስንመለከት ደግሞ
ከላይ በተገለፀው አጠቃላይ ስርአት ላይ
በመመስረት ተቋማት በዉስጣቸዉ ግልጽነትና
ተጠያቂነት ያለበት አሰራር ከማስፈን አኳያ በተቀናጀ
መልኩ የሚያከናዉኗቸዉ ተግባራት ላይ ትኩረት
ያደርጋል፡፡

19
6. የሙስና መከላከያ ስልቶችና
አተገባበራቸዉ
2.1. የሙስና መታገያ ስልቶች
በስፋት የሚታወቁትና እየተተገበሩ ያሉት የሙስና
መዋጊያ ስልቶች በሶስት ናቸው፡፡
አንደኛው ስልት፡-
ሕብረተሰቡ ስለሙስና ወንጀል ጎጅነት እንዲያውቅና
እንዲጠላው (እንዲጠየፈው) ያለመሰልቸትና
ያለማቋረጥ የማስተማርና የመቀስቀስ ስራ በመስራት
በፀረ-ሙስና ትግሉ ተሳታፊ እንዲሆኑ ማድረግ፣

20
ሁለተኛው ስልት፡-
ወንጀሉ እንዳይፈጸም ለመከላከል ግልፅነትና
ተጠያቂነት ያለው አሠራር በመንግስት አሠራር ውስት
መዘርጋት (የሥነምግባር ደንቦችን ማዘጋጀትና
መተግበር)፣
• የጥቅም ግጭት የሚያስወግዱ አሰራሮችን
መዘርጋት፣
• የሀብት ማሳወቂያና የንብረት ምዝገባ ሥርዓት
መዘርጋት፣
• ለምስክሮችና ጠቋሚዎች የጥበቃና የከለላ ሥርዓት
መዘርጋት፣
• በተቋማት ግልፅነትና ተጠያቂነት ያለው አሠራር21
ሶስተኛው ስልት፡-
ህግን ማስፈፀም ነው፡፡
አጥፊዎች ጥፋተኝነታቸውን በማስረጃ አረጋግጦ ለህግ
ማቅረብና ተገቢው ቅጣት እንዲጣልባቸው ማድረግና
የዘረፉትን ንብረት ተከታትሎ ማስመለስ)፡፡ በዚህም
አጥፊው ይማራል ሌሎች ቅጣቱ ሲፈፀም ያዩ ሰዎች
የሙስና ወንጀል አትራፊ እንዳልሆነ በመገንዘብ
ተመሳሳይ ጥፋት ከመፈጸም እጃቸውን እንዲሰበስቡ
ያደርጋል፡፡

22
ከላይ የተገለጹትን የመታገያ ስልቶች
በጥቅሉ በሁለት ከፍሎ ማየት ይቻላል፡-

1. ቀጥተኛ ያልሆነ (Indirect or Implicit


Technique)
በመንግስት የፖለቲካና የአስተዳደር እንዲሁም በዜጎች
ብሔራዊ ቁርጠኝነት፣
በሥነምግባር ደንቦች፣
በሀብት ማሳዎቅና ማስመዝገብ ዘዴ እና
በመገናኛ ብዙሃን በመጠቀም የሚከናወን የመከላከያ
ስልት/ዘዴ ነው፡፡
23
2. ቀጥተኛ የሆነ (Direct Technique)

• ይህ የሙስና መከላከያ ስልት የስራ ማስፈጸሚያና መቆጣጠሪያ


መመሪያዎች (ለምሳሌ የፋይናንስ፣ የግዥና የንብረት አስተዳደር፣
ቁጥጥር ሥርዓት መመሪያና የፀረ-ሙስና ሕጎችና ደንቦችን)
በማውጣት የሚፈቀዱና የሚከለከሉ ጉዳዮችንና ሥራዎችን
በማመላከት ተጠያቂነትና ግልፅነት የሚንፀባረቅበትን የአሰራር
ሥርዓት መዘርጋትና የእነዚህ የሥራ ማስፈጸሚያ ህጎች፣ የአሰራር
ደንቦችና መመሪያዎች የአፈጻጸም ውጤታቸው በድንጋጌዎች
መሠረት መሆኑን ወይም አለመሆኑን በመቆጣጠር፣ በመከታተል
እንዲሁም ጥናት በማካሄድ ሕግና ደንቦቹ ተጥሰው ከሆነም
በተዘረጉ የሕግ ማዕቀፎች መሠረት እርምጃ የመውሰዱ ተግባር
ላይ በንቃት መሳተፍ የተቋማት ቀጥተኛ የመከላከል ሥራን
ያመለክታል፡፡
– (ለምሳሌ የውጭና የውስጥ ኦዲት፣ የፀረ-ሙስና ተቋማት፣ የፍትህ
አካላት ጋር ተባብሮ መስራት)

24
7. ለሙስና መከሰት የሚረዱ ሁኔታዎች

እÁ”Ç”Æ ¾S”Óeƒ }kTƒ ¬eØ ¾T>Ÿ}K<ƒ” feƒ


u•
KS<e“ SŸcƒ/S”c^óƒ ¾T>[Æ ሁኔታዎች u›Óvu<
¾SÑ”²w“ ¾Sq×Ö` G<’@• ታ /Fundamental
Conditions for Corruption in the Public Sector/
1. U‡ ›Ò×T> S•` /The presence of corruption
opportunities (COs)
2. eM×”/Authority
3. ÁM}Ñv õLÔƒ /Corrupt intention ናቸው፡፡

25
• ¾S<e“ SŸLŸM ›ÖnLÃ
S`J‹/Corruption Prevention Principles/
FAST - Fair, Accountable, Simple and
Transparent ›c^` ŸS}Óu` Ò`
¾}ÁÁ²< •እ`UÍ‹” መጠቀም ያስፈልጋል፡፡
. ÁM}Ñu< õLÔ„‹” KSÓ• ታ•ƒ ¾›vLƒ”
Ó”³u? uTÇu`“ uY’UÓv` uT’ê ¾T>Ÿ“¨’<
}Óv^ƒ” SŸ¨”” ¾ሚያካትት ’¬::

26
የመከላከያ ሥልቶች/ዘዴዎች በዋናነት የሚከተሉትን ተግባራት
የሚያካትቱ ሊሆኑ ይችላል፡-
• ሙስናን የማይሸከም ሰራተኛ ለመፍጠር ግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ መስራት፣
• የሥነምግባር ደንብ በማዘጋጀት የፀረ-ሙስና ህጎች መከበራቸውን ክትትል
በማድረግ የእርምት አርምጃ መውሰድ፣
• የአገልግሎት አሰጣጥ ደረጃዎችን የማዉጣትና ተፈጻሚ የማድረግ፣
• በተቋሙ ዉስጥ ባሉ በተለዩት የሥራ ዘርፎች የአሠራር ስርዓት ጥናት ማካሄድ፣
• ለጥቅም ግጭት የሚዳርጉ አሰራሮችን የመለየትና የማረም፣
• የተገልጋዮችን እርካታ መገምገምና የማሻሻያ እርምጃዎችን መዉሰድ፣
• የሥነምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽንን ጨምሮ ከሌሎች ተቋማት የሚቀርቡ
የማሻሻያ ሃሳቦችን መከታተልና ማስተግበር፣
• በሚከሰቱ ችግሮች ላይ ማጣራት/ምርመራ እንዲካሄድባቸውና ተገቢዉ ወቅታዊ
ህጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃ እንዲወሰድባቸዉ ማድረግ፣
• በሙስና መከላከል እንቅስቃሴ ለተገኙ ስኬቶች እዉቅናና ድጋፍ መስጠት ወዘተ
የሚሉት

27
በሙስና መከላከል ስትራቴጂ ሰነድ ውስጥ ተቋማት
የሙስናና ብልሹ አሠራር ችግሮች ወይም ስጋቶች በመከላከል
ሥራ ላይ የሚያውሏቸውን ስልቶች አቅጣጫ የሚያስቀምጥ
ሆኖ፡-
• ከሙስናና ብልሱ አሰራር ችግሮች አንጻር ተቋሙ
የሚገኝበትን ነባራዊ ሁኔታ፣
• የስጋት ትንተና ዉጤትና የትኩረት አቅጣጫ፣
• በተቋሙ ውስጥ የሥነምግባር ትምህርት፣ እሴትና ባህል
የሚገነባበት ስልት፣
• በተቋሙ ውስጥ ሊከሰቱ የሚችሉ የጥቅም ግጭቶችና
የአፈታታቸውን ስልት፣
• ለሙስናና ለብልሹ አሠራር የሚያጋልጡ ሥጋቶች መለየትና
የሚሻሻሉበት ስልት፣ 28
• ሙስናና ብልሹ አሠራሮችን የሚያጋልጡ እና የሚታገሉ
ሰራተኞች እውቅና የሚያገኙበትን እና ጥቃት
እንዳይደርስባቸው ወይም ሲደርስባቸው ከለላ መስጠት
የሚያስችል ስልት፣
• ከሙስናና ብልሹ አሠራር፣ በአገልግሎት አሠጣጥ ዙሪያ
ከባለድርሻ አካላትን፣ ተገልጋይ ህብረተሰብን እና የተቋሙን
ሰራተኞች ያሳተፈ የውይይት መድረክ ማዘጋጀት፣
• የሙስና መከላከያ ዝርዝር መርሃ ግብር፣
• የክትትልና ግምገማ ዘዴዎችና የመርሃ ግብር ግምገማ ስርአት
ወዘተ...
ባካተተ ሁኔታ መዘጋጀት ይኖርበታል፡፡

29
 በበላይ ኃላፊ የሚተላለፍ መልእክት/መግለጫ ሆኖ
አጠቃላይ የስትራቴጂዉን መነሻ ፣
 ከሙስናና ብልሹ አሰራር ችግሮች አንጻር ተቋሙ
የሚገኝበትን ነባራዊ ሁኔታ፣
 ሙስና በተቋሙ ዉስጥ በማንኛዉም ጊዜ ሊከሰት
የሚችል መሆኑን፣ አዝማሚያዉንና ሊታገሉት የሚገባ
ችግር መሆኑን ፣
 የስትራቴጂዉን ጠቀሜታና አስፈላጊነት የሚገልጽ
አጠቃላይ ይዘት ይኖረዋል፡፡

30
 ስትራቴጂዉ የሚቀየስበት ምክንያት/ዓላማ፣
 በተቋሙ አመራርና ሰራተኞች ላይ የሚኖረዉ ትርጉም፣
 ከተቋሙ ጋር የሥራ ግንኙነት ባላቸዉ አካላት ላይ የሚኖረዉ
ትርጉም፣

 የሙስና አጠቃላይ ትርጓሜ፣


 ከተቋሙ አንጻር ያለዉ ትርጓሜ፣
 የጥቅም ግጭት ምንነትና ከተቋሙ አንጻር የሚኖረዉ
ትርጓሜ፣
 ከተቋሙ የሥራ እንቅስቃሴ አንጻር በምን መልክ ሊከሰቱ
እንደሚችሉ፣
 ከችግሩ አንጻር የተቋሙ ታሪካዊ ሁኔታ፣
 ከችግሩ አንጻር የተቋሙ ነባራዊ ሁኔታ፣
 ከመከላከል አንጻር የተቋሙ ነባራዊ ሁኔታ ዳሰሳ፣
31
 ስትራቴጂዉ በዋናነት መከላከልን መሰረት ያደረገ መሆኑ፣
 ቅንጅታዊ አሰራርን መሰረት ያደረገ ስለመሆኑ፣
 ደረጃ በደረጃ ሊከናወኑ የሚገባቸዉ እርምጃዎች፣
 የአመራሩ፣ የሠራተኛዉና የባለድርሻ አካላት ኃላፊነትና
ሚና፣
 የአመራሩን ወሳኝ ሚና፣
 ለተግባራዊነቱ የሚፈጠሩ የካውንስል አደረጃጀትና የሥራ
መመሪያዎች፣
 አተገባበሩ የሚመራበት አጠቃላይ ዲሲፕሊን፣
 ተቋሙ ሊደርስበት የሚያስበዉን የመጨራሻ ግብ፣
32
ስትራቴጂዉን ተፈጻሚ ለማድረግ እንደ መነሻ
የሚያገለግሉ የህግ ማዕቀፎች ዝርዝር ፡-
 ከተቋሙ የማቋቋሚያ አዋጅ ጀምሮ ተያያዥነት
ያላቸዉ ህጎች (የሀገሪቱ ሕገ መንግሥት፣ ዓለም አቀፍ
ስምምነቶችና የመሳሰሉ ህጎች)፣
ከሰዉ ኃይል አስተዳደር፣
ከግዥ፣ሽያጭና ንብረት አስተዳደር ስርአት፣
ከፋይናንስ አስተዳደር፣
የጸረ ሙስናና ተያያዝ ህጎች፣…ወዘተ
ዳሰሳና ጥንቅር፡፡
33
 ተቋሙ ከተቋቋመበት ዓላማ አንፃር የሚከናወኑ ተግባራት
በቅድሚያ መዘርዘር፣
 ያላቸዉን ተጋላጭነት ማሳየት፣
 መገለጫዎችን ማመላከት፣
 የስጋት ትንተና ዉጤትና የትኩረት አቅጣጫን ማመላከት፣

 ቀጥተኛና ቀጥተኛ ያልሆኑ የመከላከያ ስልቶችን መንደፍ፣


 ሙስናን ከመከላከል፣ ከማጋለጥ፣ ከለላና ጥበቃ ከማድረግ
አንጻር ሊከናወኑ የሚገባቸዉን ጉዳዮች መዘርዘር፣
 የእያንዳንዱን ስልት ከችግሩ አንጻር ያለዉን ተዛምዶና ጠቀሜታ
ማስቀመጥ፣

34
• የበላይ ኃላፊዉና የአመራሩ (ቦርድ ወይም ተቆጣጣሪ
አካላት) ኃላፊነትና ተግባር፣
• የካዉንስሉ ኃላፊነትና ተግባር፣
• የሥነምግባር መከታተያ ክፍሉ ኃላፊነትና ተግባር፣
• የመላ ሠራተኛዉ ኃላፊነትና ተግባር፣
• የተገልጋዩ ኃላፊነትና ተግባር፣
• የባለድርሻ አካላት ኃላፊነትና ተግባርን በዝርዝር
ማሳየት፡፡

35
 እንዴት ?
 የትና መቼ ? ለማን ?
 አጠራጣሪ የሙስና መረጃዎች ለሚመለከተዉ ህጋዊ
ተቋም ሪፖርት መደረግ ያለባቸዉ መሆኑን፣

 ጠቋሚዎች በተቋሙ ዉስጥ ከሚፈጸም ማንኛዉም


ጥቃት የሚጠበቁ መሆኑን፣
 ጥበቃ ሊደረግላቸዉ የሚችልበትን አግባብ፣
 ጥቃት ፈጻሚዎች የሚኖርባቸዉን ተጠያቂነት፣
 የህግ ከለላ መኖሩን ማሳየት፣
36
 በስትራቴጂዉ አፈጻጸም ዙሪያ በቡድንና በተናጠል
በሚደረጉ እንቅስቃሴዎች በሚገኙ የተሻሉ አፈጻጸሞች
ስለሚሰጥ የማበረታቻ ስርአት፣

 በስትራቴጂዉ አተገባበር ዙሪያ ለሚታዩ ችግሮች


ተጠያቂነት ሊያስከትሉ የሚችሉ የህግ ማዕቀፎችን
ማመላከት፣

 ለስትራቴጂዉ ተፈጻሚነት የሚያስፈልጉ የአቅም ግንባታ


ሥራዎችን ማመላከት፣
 በሰዉ ኃይል፣
 በማቴሪያል፣
 በአደረጃጀት፣ 37
 መቼ እንደሚከለስ፣
 በማን እንደሚከለስ፣
 እንዴት እንደሚከለስ፣
 ለምን እንደሚከለስ ፣
 በሂደቱ የባለድርሻዎች ሚና፣
 በሂደቱ የሠራተኛዉ ሚናን ማካተት፣

 የስትራቴጂ ሰነዱ ተፈጻሚ የሚሆንበት ጊዜ፣


 ልዩ ሁኔታዎች ሊታዩ የሚችሉበት አግባብ፣
 ለስትራቴጂዉ አፈጻጸም የሚያግዙ ዝርዝር መርሃ ግብር
ስለሚዘጋጅበት ሁኔታ ይገለፃል፡፡
38
39
ለዕቅድ
የተለየው
ተ ዘመኑ የበጀት
የሥጋት የሚከናወንበ የሚያስፈል የሚያከናውነ
/ የተመረጠው ምን ምርመራ
አካባቢ/ተግባ ት ጊዜ ግ በጀት ው አካል
ቁ የመከላከያ ጭ

ሥልት/ዘዴ

40
ተ. የሚከናወንበ ምርመ
ተግባር የሚከናወንበት አግባብ
ቁ ት ጊዜ ራ
1 መደበኛ የተገልጋይ አስተያየት በየእለቱ በመረጃ ዴስክ

2 የተገልጋዮች ሰርቬይ በየሩብ አመቱ በካውንስሉ አስተባባሪነት

3 የሰራተኞች ሥነምግባር ሰርቬይ በየሩብ አመቱ በካውንስሉ አስተባባሪነት

4 የድርጅቱ አመራርና /የቦርድ በየወሩ አመራሩና ካውንስሉ


አመራር ሪፖርትና ግምገማ በሚያቀርቡት የእቅድ
አፈጻጸምና መደበኛ
የተገልጋዮች አስተያየት
መሰረት

41

የሚከናወ
. ተግባር የሚከናወንበት አግባብ ምርመራ
ንበት ጊዜ

5 የተቋሙ በየሩብ አመራሩና ሰራተኛው በጋራ የሚያደርጉት ግምገማ፤ ሪፖርቱ ለቦርድ
አጠቃላይ አመራርና
ግምገማ አመቱ የሩብ አመት የተገልጋይና ስነምግባር ሰርቬይ እና ለኮሚሽኑ ይቀርባል
የተገልጋይ አስተያየትን እንዲሁም የዕቅድ አፈጻጸም
ውጤትን መሰረት አድርጎ

6 የተቋሙ፣ በየስድ አመራሩ፣ ሰራተኛው፣ ተገልጋይና ባለድርሻ አካላት ሪፖርቱ ለተወካዮች


ተገልጋይና ም/ቤት፣
ባለድርሻ ስት በጋራ የሚያደርጉት ግምገማ፤ የሁለት ሩብ አመት ለሚመለከተው
አካላት ወሩ የተገልጋይና ስነምግባር ሰርቬይ እና የተገልጋይ ተቆጣጣሪ አካል፣
የጋራ ለቦርድ አመራርና
መድረክ አስተያየትን እንዲሁም የዕቅድ አፈጻጸም ውጤትን ለኮሚሽኑ ይቀርባል
መሰረት አድርጎ

42
 በበላይ ስራ አመራሩ የጸደቀ አጠቃላይ የፀረ ሙስና
ስትራቴጂ ተነድፏል?
 የሙስና ስጋት ማመዛዘኛ (ደረጃ በተግባራት)
ተከናውኗልን? ወቅታዊ ነው?
 ከተለየው ችግር አንጻር መፍትሄ ሊሆኑ የሚችሉ
የሙስና ስልቶች/ዘዴዎች ተቀርጸዋል?
 በዝግጅቱ ወቅት የበላይ ሃላፊዎች፣ በየደረጃዉ ያሉ
አመራሮች፣ ሠራተኞችና ባለድርሻ አካላት
ተሳትፈውበታልን?
43
 በተቋሙ ዉስጥ በዕቅዱ አዘገጃጀትና አተገባበር ዙሪያ
የአመለካከት ለውጥ ለማምጣት የሚያስችሉ
ፕሮግራሞች ተከናውነዋል?
 በተቋሙ መደበኛ ሪፖርት ሥርአት ዉስጥ የሙስና
መከላከል እንቅስቃሴዎች እንዲካተቱ ተመላክቷል?
 መደበኛ የክለሳና የማሻሻያ ስርአት ተቀይሷል?
 አስፈላጊ አደረጃጀቶች ተፈጥረዋል?
 የአቅም ግንባታ ስራዎች ተነድፈዋል?

44
የተቀናጀ የሙስና መከላከያ ስትራቴጂ ተቋማት ሙስና የመከላከሉን
ተግባር በባለቤትነት ተግባራዊ እንዲያደርጉ ከማድረግ ባሻገር ሊከተሏቸው
የሚገቡ አጠቃላይ አቅጣጫዎችን የሚያመላክት ሆኖ በዋነኝነት
• የሙስና መከላከያ ስትራቴጂና ዝርዝር መርሃግብር መዘጋጀት
እንዳለበት፣
• የአዘገጃጀቱ ሁኔታ ምን መምሰል እንዳለበትና ከመደበኛ ዕቅድ ጋር
ሊፈጠር ስለሚገባ መስተጋብር፣
• የመንግስት ተቋማት ሙስናን ለመከላከል በሚያዘጋጁት ዕቅድና
አተገባበር ዙሪያ ከኮሚሽኑ ባሻገር ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር
ሊኖራቸዉ ስለሚገባ መስተጋብር፣
• የዕቅድ፣ ክትትልና የመረጃ አቀራረብ ስርአቶችን፣
• ለተፈጻሚነቱ በተቋማት ዉስጥ የሚያስፈልጉ አደረጃጀቶችን፣
በጥቅሉ የሚያመላክት ሲሆን ዝርዝር ሁኔታዎች ከየተቋማቱ ባህሪ አንጻር
እየተቃኙ ተፈጻሚ እንደሚደረጉ ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡
45
46
47
የሙስና መከላከልና የሥነምግባር ካዉንስል
አደረጃጀት
• የተቋሙ የበላይ ኃላፊ……………… ሰብሳቢ
• የፋይናንስ ኃላፊ…………………….. አባል
• የዉስጥ ኦዲት ኃላፊ………………… አባል
• ከሠራተኞች/ባለሙያዎች ተወካይ…… አባል
•የስነምግባር መኮንን/ዳይሬክተር.. አባልና የካውንስሉ ፀሐፊ
የሚለውን አደረጃጀት መነሻ በማድረግ እንደ ሁኔታዉ
ጉልህ የሆኑ የሥጋት አካባቢዎችን ባካተተ መልኩ
ተጨማሪ አባላትን ሊይዝና ከተቋማት ነባራዊ ሁኔታ ጋር
ሊጣጣም ይችላል፡፡ 48

You might also like