You are on page 1of 2

no 6

EAC Ad hoc
information communication kit

ለግንዛቤ
የሙስና ወንጀሎች
በኢፌዲሪ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 81 ላይ ሕግን አለማወቅ ይቅርታ አያሰጥም የሚል የሕግ መርህን
አስቀምጧል፡፡ ስለዚህ ይህንን መርሕ መሠረት በማድረግ ሠራተኛው በሙስና ወንጀሎች ላይ አጠቃላይ
ግንዛቤ እንዲኖረው ለማድረግ ይህንን የግንዛቤ ማስጨበጫ መልእክት ማስተላለፍ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡

የሙስና ወንጀሎችን ለመደንገግ በወጣው አዋጅ ቁጥር 881/2007 መሠረት 25 ድርጊቶች በሙስና
ወንጀልነት የተፈረጁ ሲሆን ከወንጀሉ ፈጻሚዎች ማንነት አንፃር በሶስት ተከፍለው ከዚህ እንደሚከተለው
ቀርበዋል፡፡

የመንግሥት ሠራተኞች ቅንነትና ታማኝነትን


በማጓደል የሚፈጽሟቸው የሙስና ወንጀሎች

- በሥልጣን ያለ አግባብ መገልገል / አንቀፅ 9/


- ጉቦ መቀበል /አንቀፅ 10/
- የማይገባ ጥቅም መቀበል /አንቀፅ 11/
- የመንግሥት ወይም የሕዝባዊ ድርጅት ሥራን በማያመች አኳኋን መምራት /አንቀፅ 13/
- አደራ በተሰጠው ዕቃ ያለአግባብ ማዘዝ /አንቀፅ 14/
- በሥራ ተግባር ላይ የሚፈጸም የመውሰድና የመሰወር ወንጀል(አንቀፅ 15)
- በሥልጣን ወይም በኃላፊነት መነገድ (አንቀፅ 16)
- በህገ ወጥ መንገድ መሰብሰብ ወይም ማስረከብ ( አንቀፅ 17)
- ያላግባብ ጉዳይን ማጓተት (አንቀፅ 18)
- ዋጋ ያለውን ነገር ያለክፍያ ወይም ያለበቂ ክፍያ ማግኘት (አንቀፅ 19)
- ያለአግባብ ፍቃድ መስጠት ወይም ማፅደቅ (አንቀፅ 20 (1)
- ምንጩ ያልታወቀ ንብረት እና ገንዘብ (አንቀፅ 21 )
- የሥራ ሚስጢርን መግለጽ /አንቀፅ 22/
- ከባድ የእምነት ማጉደል (አንቀፅ 31)
- ከባድ አታላይነት (አንቀፅ 32)

Published by: Internal Communications Section

1
no 6
EAC Ad hoc
information communication kit

ማንኛውም ሰው /የመንግሥት ሠራተኞችን ጨምሮ / በመንግሥት ሥራ


ላይ የሚፈጽሟቸው የሙስና ወንጀሎች
- መንግሥታዊ ወይም የሕዝባዊ ድርጅት ሰነዶችን አስመስሎ ማዘጋጀት ፣ ወደ ሐሰት መለወጥ
ወይም በሐሰተኛ ሰነድ መገልገል (አንቀፅ 23 )
- መንግሥታዊ ወይም የሕዝባዊ ድርጅት ሰነዶችን ማጥፋት ወይም ጉዳት ማድረስ /አንቀፅ 24/
- ጉቦ ወይም ተገቢ ያልሆነ ጥቅም መስጠት (አንቀፅ 25)
- ዋጋ ያለውን ነገር ያለክፍያ ወይም ያለበቂ ክፍያ መስጠት (አንቀፅ 26)
- ማቀባበል (አንቀፅ 27)
- በሌለው ሥልጣን መጠቀም /አንቀፅ 28/
- በግል ተሰሚነት መነገድ (አንቀፅ 29)
- በምርጫ ላይ የሚሰጥ መደለያ (አንቀፅ 30)
- በሙስና ወንጀል የተገኘን ገንዘብ ወይም ንብረት ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብና በወንጀሉ
ስለመርዳት (አንቀፅ 33 )

የተለዩ ሰዎች በተለዩ አገልግሎቶች ላይ የሚፈጽሟቸው


የሙስና ወንጀሎች

አስታራቂ ሽማግሌዎች እና ሌሎች ሰዎች የሚፈጽሙት ጉቦ የመቀበል ወንጀል /አንቀፅ 12 /


ያለአግባብ ፍቃድ መስጠት ወይም ማፅደቅ (አንቀፅ 20(2)

ከዚህ በላይ የተጠቀሱትን የወንጀል ድርጊቶች ፈጽሞ የሚገኝ ሠራተኛም ሆነ የሥራ ኃላፊ ከወንጀል ቅጣት
በተጨማሪ አስተዳደራዊ ቅጣት እና በፍትሐ ብሔር ኃላፊነት እንደሚጠየቅ እያስታወቅን የኩባንያው ማሕበረሰብ ተገቢውን
ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡

የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና መምሪያ


ጥር 2009 ዓ.ም

Published by: Internal Communications Section

You might also like