You are on page 1of 36

ከጤናው ዘርፍ ጋር ተያይዞ የሚከሰት

የግዥና የፋይናንስ አስተዳደር


ሙስና
ተስፋዬ አየለ (MA)

አበክመ የሥነ-ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ጎ/ቅ/ጽ/ቤት


የትምህርትና ስልጠና የስራሂደት

ህዳር 2010 ዓ.ም


ጎንደር

ማውጫ
1. መግቢያ ……………………….........................................................................3
2. ሙስና (Corruption) ……………....………........................................................4
2.1. ሙስና ማለት ምን ማለት ነው……............................................................4
2.2. የሙስና መገለጫዎች……..........................................................................7

1
2.3. የሙስና ተዋናዮች......................................................................................9
2.4. በጤና ዘርፍ ውስጥ የሚከሰቱ የሙስና አይነቶች ……................................10
3. የጤና ፖሊሲዉ ስለጤና ፋይናንስ ምን ይላል ................................................12

4. በጤና ዘርፍ በግዥና በፋይናንስ አስተዳደር የሚከሰት ሙስና .......................14

5. የመድሃኒትና የህክምና ቁሳቁሶች ግዥ ሙስና፣.................................................14

6. የህክምና ዘርፍ ክፍያዎች ሙስና፣……............................................................24

7. የህክምና ፕሮጀክት ግንባታ ሙስና፣……........................................................24

8. የጤና አገልግሎት አሰጣጥ ሙስና ናቸዉ፡፡……..............................................25

9. ለሙስና የሚያጋልጡ ምክንያቶች……...............................................................25


10. በጤና ዘርፉ በግዥና ፋይናንስ አስተዳደር ላይ የሚፈጸም ሙስና የሚያስከትለው ጉዳት
…….....................................................................................................32
11. በጤና ዘርፉ በግዥና ፋይናንስ አስተዳደር ላይ የሚፈጸም ሙስናዎችን የመከላከያ ስልቶች
…………………......................................................................................35
12. የሞጁሉ ማጠቃለያ ጥያቄዎች……...................................................................41

መግቢያ
ሙስና በየትኛውም የአለም አገራት የሚከሰት ክስተት ነው፡፡ መጠኑ ይለያይ እንጅ ሙስና የሌለበት አገር
የለም፡ እንደ ተራነሰፓርንሲ ኢንተርናቲናል (TI) የ 2013 ጥናት 177 አገሮች የሙስና ሁኔታ ጥናት
እንደሚያመለክተው ጥናቱ ከተደረገባቸው 70% ያህሉ አሳሳቢ የሆነ የሙስና ችግር እንዳለባቸው
ያሳያል ፡፡
በተመሳሳይ በኢትዮጵያ ሙስና በከፍተኛ ሁኔታ ተንሰራፍቶ እንደሚገኝ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ እንደ 2006
ግሎባል ኢንተግሪቲ ሪፖርት ሙስና በኢትዮያ የፖለቲካ፤ ኢኮኖሚ እና ማህበረሰብ ውስጥ ስር ሰዶ

2
የሚገኝ አሳሳቢ ችግር ነው ፡፡ Transparency International (TI) በ 2014 ሪፖርቱ እንዳስቀመጠው
ኢትዮጵያ ከ 176 አገሮች 110 ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች ፡፡
ለሙስና እጅግ ተጋላጭ ከሆኑ አካባቢዎች መካከል ግዢ ዋነኛው ነው፡፡ መንግስት ከግብርና ቀረጥ
የሚያገኘውን ገቢ የሚያውለው ለደሞዝ ለሥራ ማስኬጃ /ለዕቃ ፤ለአገልግሎትና ለኮንስተራክሽን ስራ
መግዣ ሲሆን ለግዥ ተግባር የሚውለው ገንዘብ ከአጠቃላይ አመታዊ ባጀት ውስጥ ከፍተኛውን ድርሻ
ይይዛል፡፡ በሃገራችን ለፌዴራል መንግስት ከሚመደበው ዓመታዊ በጀት ውስጥ ከ 60-70% እንዲሁም
ከአጠቃላይ አገራዊ ምርት (GDP) ደግሞ 15% የግዥ ድርሻ እንደሆነ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡
በግዥ ውስጥ ካለው ከፍተኛ የሙስና አጋጣሚ የተነሳ የግዢ ውል ከተደረገበት ግዢ ውስጥ ከ 10% እስከ
25% አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ከ 40% እስከ 50% በሙስና ሊመዘበር እንደሚችል አንዳንድ ጥናቶች
ያመለክታሉ፤ ከዚህ አንጻር ዘርፉ ለሙስና እጅግ ተጋላጭ መሆኑን መገመት አያዳግትም፡፡
በተለይ ከግዠና ፋይናንስ አስተዳደር ጋር ተያይዞ የሚፈጸም ሙስና ከጤና ሴክተሩን እየጎዳ ያለ ችግር ነዉ፡፡
እንደሚታወቀው መንግስት ባለፉት ዓመታት የጤና አገልግሎቱን ተደራሽነት ለማሻሻል ትኩረት አድርጎ
በመንቀሳቀሱ በአብዛኛው የዞናችን አካባቢዎች የጤና ተቋማት ተደራሽነቱ በእጅጉ ተሻሽሏል፡፡ይህን
ተከትሎ በዋና ዋና የጤና ችግሮቻችን ላይ ከፍተኛ መሻሻል እየተመዘገበ ነው፡፡ ይሁን እንጅ ለዘርፉ
የሚመደበዉ በጀት ከፍተኛ ከመሆን ጋር ተያይዞ የጤናዉ ዘርፍ ለሙስና እንዲጋለጥ አድርጎታል፡፡
በሙስና ምክንያት በግለሰብና በቤተሰብ ላይ የጤናና የአካል ጉዳት እየጨመረ ነዉ፡፡በጤና ተቋማት መድሃኒት
የለም፣የሚፈለጉት የላብራቶሪ እና የራጅና መሰል ምርመራዎች የሉም፣የነጻ ህክምና ታካሚዎች በአግባቡ አገልግሎቱን
እያገኙ አይደለም፣ከፍተኛ የገንዘብና የህክምና ቁሳቁስ ብክነት ይታያል፣አገልግሎቶች ቢኖሩም ባለሙያ ስለሌለ ወደ ግል
የጤና ተቋማት ሂዱ በሚል ህዝቡ ለከፍተኛ እንግልት እና ወጭ እየተዳረገ ነው፡፡ለእነዚህ ችግሮች እንደምክኒያት
ከሚጠቀሱ ጉዳዮች ውስጥ አንዱ ሙስና እና ከአንዳንድ የግል ተቋማት ጋር የሚፈጠር የትቅም ትስስር ነው፡፡ ስለሆነም
በጤናዉ ዘርፍ የሚከሰተዉን ሙስና መግታት ጠቀሜታዉ እጅግ የጎላ ነዉ፡፡

1. ሙስና (Corruption)
1.1. ሙስና ማለት ምን ማለት ነው
የቃሉን አመጣጥ ስንመለከት “Corruption” የሚለው ቃል”Corruptus” ከሚለው የላቲን ቃል የተወሰደ
ሲሆን ሙስና ደግሞ “Corruption” የሚለውን የእንግሊዝኛውን ቃል እንዲገልጽ የምንጠቀምበት ከግዕዝ
የተወረሰ ቃል ነው። ትርጉሙም ማጥፋት፣ ማበላሸት፣ ህግን መጣስ….ወዘተ. ማለት ነው፡፡
በሙስና መስክ ጥናትና ምርምር ያካሄዱ ምሁራኖች፣ ዓለምአቀፋዊ፣ አህጉራዊና ሃገር በቀል ድርጅቶች
የተለያዩ መገለጫዎችን መሰረት በማድረግ ሙስና ለሚለው ቃል ልዩ ልዩ ፍቺዎችን ቢሰጡም ፍቺዎቹ
ሲስተዋሉ በይዘት ረገድ ተቀራራቢ መሆናቸው ይስተዋላል::
ሙስና ለሚለው ቃል ሁሉን አቀፍ እና ሁሉም በየደረጃው ያሉ አካላት የተስማሙበት አንድ ወጥ የሆነ
ትርጉም ማግኘት እንደማይቻል ነው፡፡
በመስኩ ጥናትና ምርምር ያካሄዱ ምሁራን፣ ዓለም አቀፋዊ፣ አህጉራዊ ድርጅቶች የተለያዩ መገለጫዎችን
መሠረት በማድረግ ሙስና ለሚለው ቃል የሰጧቸው ትርጉሞች ለመከላከል የሚፈልጉትን የሙስና ወንጀል

3
ነው ፡፡ ስለሆነም በአለም ደረጃ በሁሉም ተቀባይነት ያለው የሙስና ትርጉም አሁን ባለው ሁኔታ ለማግኘት
አስቸጋሪ ነው፡፡ ሙስና ለሚለው ቃል የሚሰጠው ትርጉም እንደተርጓሚው እይታ፤ አላማና ስረ መሰራት
(background) የሚለያይበት አጋጣሚ መታዘብ ይቻላል፡፡ ለምሳሌ ተርጓሚዎች የንግድ ወይም የኢኮኖሚ
ተቋማት ከሆኑ (Economic or commercial models) የንግድ ጉዳዮችንና የኢኮኖሚውን ደህንነት አደጋ
በሚጥል ጉዳይ ላይ ሊያተኩሩ ይችላሉ፤ ተርጓሚዎች የህግ ጥበቃ የሚያደርጉ አካላትም (Legal models)
ወንጀልን ከመከላከል እይታ ሊያዩት ይችላሉ ፤ የፖለቲካ ሞዴሎች ሙስናን የሚያዩበት መነጸር ስልጣንን
ያለአግባብ መገልገል (the abuse of power or influence) ሊሆን ይችላል፡፡
ለአብነት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ትርጉሞች እንመልከት፡-
1. ሙስና የመንግስትን ሥራ ሥነ ምግባራዊ እና ህጋዊ መሠረት ባለው መመሪያና ደንብ ላይ ተመርኩዞ
ማከናወን አለመቻል ነው / የሙስና ቅኝት በኢትዮጵያ 1993/፡፡
2. ሙስና በግል ወይም በቡድን፣ በፖለቲካ መሪዎች ወይም በቢሮክራቶች ሥልጣንና ኃላፊነትን መከታ
በማድረግ፣ የህዝብን ጥቅምና ፍላጐት ለግል ጥቅም የማዋል ኢ-ሥነ-ምግባራዊ ድርጊት ሲሆን፣
በመንግስትና በህዝብ ሃብትና ንብረት ላይ ስርቆት መፈጸም፣ ዝርፊያ ማካሄድ፣ ማጭበርበር፣ ህግና
ሥርዓትን ተከትሎ ከመሥራት ይልቅ በዝምድና፣ በትውውቅ፣ በፖለቲካ ወገንተኝነት፣ በጐሰኝነት፣
በኃይማኖት ትስስር ላይ ተመርኩዞ በመሥራት አድሎ መፈፀም፣ ፍትህን ማጓደልና ሥልጣንና ኃላፊነትን
በህገወጥ መንገድ የጥቅም ማግኛ የማድረግ እኩይ ተግባር ነው /ኬምፔሮናልድና ሰርቦርዌል 2000/፡፡
3. ሙስና የፖለቲካና የመንግስት አስተዳደራዊ ኃላፊነትን ካለመወጣት የሚመነጭ፣ማህበራዊና
አስተዳደራዊ ሥርዓቶችን የመጣስ የሥነ-ምግባር ግድፈት ሲሆን ይህም ለግል ጥቅም ሲባል በህዝብ የተሰጠ
ሥልጣንና ኃላፊነተን አላግባብ በመጠቀም ህግና ደንብ የመጣስ እኩይ ተግባራትን ያካትታል / ቻርለስ ሳን
ፎርድ 1998/፡፡
4. ሙስና በመንግስትና በህዝብ የተሰጠን ስልጣንና ኃላፊነትን ለግል ጥቅም ወይም ሌላን ለመጥቀም ወይም
ለመጉዳት ሲባል አላግባብ መገልገል ነው (Kimberly,1997, Klitgaard, 1990, vishny 1993 & stapen
Horst, Ric, 1999) የኢትዮጵያ ቋንቋዎች ጥናት ምርምር የአማርኛ መዝገበ ቃላት /1993/፣ ዓለም አቀፍ
የኢኮኖሚ ልማት ተበብር ድርጅት (OECD‚ Transparency International/2005/)፡፡ World Bank፡ “the
abuse of public office for private gain.”
እነዚህ ትርጉሞች በመንግስትና በህዝብ ሃብት ላይ ለሚፈጸሙ የሙስና ወንጀሎች በቂ ቢሆኑም
በግል ሴክተሩ የሚፈጸመውን የሙስና ወንጀል ግን አያሳዩም፡፡ ሙስናን በሁለት ከፍለን ማየት
እንችላለን እነሱም በግል ዘርፉ የሚፈጸም ሙስና (private corruption) እና በመንግስት ተቋማት
የሚፈጸም ሙስና ( public corruption)::የግል ዘርፉ የሚፈጸም ሙስና(private corruption)በግል
ዘርፉ ባሉ ተቋማት የሚታይ ሲሆን በመንግስት ተቋማት የሚፈጸም ሙስና(public corruption)
በመንግስት ሰራተኞች ተሳታፊነት በመንግስት ተቋማት የሚታይ የሙስና አይነት ነው::

4
ይህ ማለት ሙስና ምንም የመንግስት አካላት ባልተሳተፉበትና የግል ዘርፉ ብቻውን በሚፈጽመው
ግብይትም ሊፈጸም ይችላል፡፡ ለምሳሌ የጤናማ ውድድርን መርህ በማቃወስ አንዳንድ ተናንሽ የንግድ
ተቋማትን ከውድድር ውጭ ማድረግ ፤የአሰሪና ሰራተኛ ህጎችን በመጣስ ህጉ ከሚፈቅደው የስራ ሰአት
በላይ ማሰራት ወይም ለተመጣጣኝ ስራ ተመጣጣኝ ክፍያ ያለመክፈል፤ ስለዚህ ከላይ የተጠቀሰውን
ለሙስና የተሰጠውን ትርጉም አንዳንድ ሃገሮችና ድርጅቶች ሰፋ በማድረግ የግል ዘርፉን
በሚያጠቃልል መልኩ ይተረጉሙታል ፡፡ ለምሳሌ የሚከተሉትን ትርጉሞች እንመልከት፡-
5. ሙስና አደራን አለመጠበቅ፣ እምነትን ማጉደል ወይም አለመታመን፣ በጉቦ፣ በምልጃና በአድሎ ሃቅን፣
ውሳኔን ወይም ፍትህን ማዛባት ነው (Transparency International 2008)፡፡
6. ሙስና ለግል ወይም ለቡድን ጥቅም ሲባል ሥርዓቶችን፣ ህጎችን፣ ደንቦችን፣ አሰራሮችን፣ መርሆዎችን
የመጣስ ማንኛውም ተግባር ነው (Kato, 1995)፡፡
7. ሙስና በመንግስት ወይም በግል የተሰጠን ስልጣንና ሃላፊነት ለግል ጥቅም ማዋል (“the abuse of a
public or private office for personal gain”) (OECD Glossaries 2008,p.22.)
8. የተሠጠን ስልጣንና ሃላፊነት ለግል ጥቅም ማዋል (Transparency International (TI) defines
corruption as the abuse of entrusted power for private gain)::
እነዚህን ትርጉሞች ስንመለከት ደግሞ ሙስና በግልና በመንግስት ተቋማት የሚፈፀሙትን ሁሉ
ያጠቃላል፡፡ በአጠቃላይ ግን ከላይ የቀረቡትን የሙስና ትርጉሞች ስናጤን ሙስና የሚለው ቃል በእርግጥም እጅግ
በጣም ሰፊና ውስብስብ የሆኑ ኢ-ሥነምግባራዊ ተግባራትን እና የወንጀል ድርጊቶችን አካቶ መያዙን መረዳት ይቻላል።
በተራ ቁጥር 5-8 የተገለጹትን ትረጉሞች ስንመለከት የሙስና ወንጀል በግልም ይሁን በመንግስት ተቋማት ውስጥ ሊፈጸም
የሚችል መሆኑን የሚያሳዩ ሲሆን በሌላ በኩል ከ 1-4 የተዘረዘሩት ሙስና በመንግስት ተቋማት የሚፈጸም ህገወጥ ድርጊት
መሆኑን ያመለክታሉ::
እዚህ ላይ የክራይ ሰብሳቢነት(Rent seeking)ጽንስ ሃሳብ አያይዞ ማብራራት ተገቢ ነው፡፡የኪራይ
ሰብሳቢነት (Rent seeking) ተግባር በመሠረቱ አዲስ ሀብት ወይንም እሴት በመፍጠር ላይ የተመሠረተ
ሳይሆን የተፈጠረን ሀብት በመቀራመት አቅጣጫ የሚጓዝ ነው፡፡
“It occurs when a company, organisation, or individual uses its
resources to obtain economic gain from others without
reciprocating any benefits back to society through wealth
creation.” (Frew Mengistu Truneh (2013) p.458)

በመሆኑም ኪራይ ሰብሳቢነት ማለት ሸቀጥን አምርቶ ወይንም አገልግሎትን አቅርቦ በተሻለ አቅርቦት፣
ጥራትና ዋጋ በነፃ ገበያ ውስጥ ተወዳድሮ በማሸነፍ የሚገኝ ሀብት ሳይሆን የመንግስትን ስልጣን በመያዝ
ወይንም ከባለስልጣናት ጋር በመቀራረብና በመጠጋት ወይንም ደግሞ የጥቅም ትስስር በመፍጠር ተገቢ
ባልሆነ መንገድ የህዝብና የመንግስት ሀብትና ንብረት ለግል ጥቅም የሚውልበት ስርዓት ነው፡፡

5
የኪራይ ሰሰብሳቢነት አስተሳሰብና ተግባር በመንግስት ውስጥ ብቻ የሚፈፀም ነው ብሎ መውሰድ
አይቻልም፡፡ ይልቁንም ይህ ችግር በግሉ ዘርፍም ጭምር የሚስተዋልበት ዕድል በጣም ሰፊ ነው ፡፡
በሀገራችን ሁኔታ በሀገር ሃብትና ሁለንተናዊ እድገት ላይ የሚያስከትለው ጉዳት ከፍተኛ በመሆኑ የበለጠ ትኩረት
የተሰጠው በመንግስትና በህዝብ አገልግሎት መስጫ ተቋማትና የመንግስት የልማት ደርጅቶች ውስጥ በሚፈጸም ሙስና
ላይ ሁኖ የቆየ ቢሆንም በ 2007 በወጣው አዋጅ (881/2007) የተወሰኑ የግል ዘርፎች ማለትም ህዝባዊ ድርጅቶች
በጸረ ሙስና ህጉ እንዲካተቱ ተደርጓል፡፡
1.2. የሙስና መገለጫዎች
የሙስና መገለጫዎችን በተመለከተ ብዙ ሰዎች ሙስና የሚለውን ቃል ሲሰሙ በመጀመሪያ ወደ
አዕምሮአቸው የሚመጣው ጉቦ ነው፡፡ ነገር ግን ከዚህ በተጨማሪ በርካታ የሙስና መገለጫዎች አሉ፡፡
የተለያዩ ተቋማት የተለያየ የሙስና መገለጫዎች ሊኖሯቸው ይችላል፡፡ በመሆኑም በዚህ ትምህርት ውስጥ
በግዥና ፈይናንስ የሚከሰቱ የሙስና መገለጫዎችን የምንመለከት ይሆናል::
1.2.1. ከአገልግሎት ተቀባይ የሚሰጥ ጉቦ
ይሄኛው የጉቦ ዓይነት ከአገልግሎት ተቀባይ /ከተገልጋይ/ የሚነሳ ሲሆን ለአገልግሎት ሰጪው መደለያ በመስጠት ሕጋዊ
አሠራርን ለማስለወጥ የሚፈጸም ተግባር ነው።
በግዥ ሥርዓት ውስጥ ውሳኔዎችን ለሚወስኑ የስራ ሃላፊዎች ውሳኔያቸው ለተወሰነ ሰው ወይም ቡድን
ተስማሚ እንዲሆን ለማድረግ ከሚሰጥ ትልልቅ ጉቦ ጀምሮ በተለምዶ ስራን ለማቀላጠፍ በሚል ለበታች
ሰራተኞች የሚሰጠውን ትንንሽ ጉቦ ይመለከታል፡፡
ጉዳይ ከመጀመሩ በፊትና በኋላ ክፍያ፣ ጀርባ መደገፍ፣ ማጣፈጫ፣ ማፋጠኛና ማለስለሻ፣ ንግድ ማመቻቸት፡መንግስት
የሚያወጣቸውን ጨረታዎች ለማሸነፍ ፣የዋጋ ቁጥጥር እንዳይኖር ለማድረግ፣መረጃ ለማግኘት /የጨረታ
መረጃዎች፣/ተወዳዳሪዎችን ከገበያ ለማስወጣት/፡፡ የኮንትራትና የግንባታ ፈቃድ ለማግኘት፣ የህክምና
መድሃኒቶችን፣ ቁሳቁሶችንና አገልግሎቶችን ለማቅረብ፣ የኮንትራት ዉልን ቀጣይነትን ለማረጋገጥ፣ ሰነድና መረጃዎችን
ለመቀየር፣ ለማዛባት፣ዉሳኔን ለማፋጠን ወዘተ በሚል የሚሰጥ ነዉ፡፡

1.2.2. በአገልግሎት ሰጪ አካል የሚጠየቅ ጉቦ


ይህኛው የጉቦ ዓይነት መሰጠት የሚገባውን ህጋዊ አገልግሎት በመከልከል ከአገልጋይ የሚጠየቅ ሲሆን ተገልጋዩን
በማስፈራራት፣በማስጨነቅ ፣ተጽእኖ በማሳደር ተገቢ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት የሚፈጸም ተግባር ነው፡፡ በጨረታ
ሂደት ተሳታፊዎችን በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ በማስጨነቅ ወደ ሙስና አንዲያመሩ ማድረግን
እንደምሳሌ ማንሳት ይቻላል፡፡
ባጠቃላይ በመንግስት አገልግሎት አሰጣጥ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ የመንግስት ሰራተኛ ውሳኔ
ላይ ተጽእኖ ሊያሳድር የሚችል ዋጋ ያለው ስጦታ ማቅረብ (offering)፣ መስጠት (giving)፣ መቀበል

6
(receiving)፣ ለመስጠት ማነሳሳት(መጠየቅ) (soliciting)፤ የሙስና ተግባር (Corrupt practice) ተብለው
ሊወሰዱ ይችከላሉ፡፡
1.2.3. የተጫራቾች ስምምነት (Collusion):-
ተጫራቾች በቡድን በመደራጀትና ከቡድናቸው ውስጥ አንዱ እንዲያሸንፍ ለማድረግ ልዩ ልዩ ዘዴዎችን
መጠቀምን ይመለከታል፤ይህም በሁለት ዓይነት መንገድ ሊፈጸም ይችላል አንደኛውተጫራቾች
በመመካከር አሸናፊ የሚሆኑ ቡድኖችን ተራ በማስያዝ፤አንተ መጀመሪያ አሸናፊ ትሆናለህ አንተ ደግሞ
ቀጥሎ በመባባል ሲሆን፣ሌላው ደግሞ የመጫረቻ ዋጋን ሆን ብሎ ከፍ በማድረግ ከአሸናፊ ተጫራች
የተወሰነ ገንዘብ የሚከፋፈሉበት ዘዴ ነው ፡፡
1.2.4. የማይገባ ጥቅም መቀበል
ማንኛውም የመንግስት ሰራተኛ ወይም ህዘባዊ ደርጅት ሰራተኛ ማድረግ የሚገባውን ተግባር ለማከናወን
ሲል ወይም ስላከናወነ ጥቅም የጠየቀ/ያገኘ/የተስፋ ቃል የተቀበለ፡፡ታካሚዎች የተሻለ የህክምና አገልግሎት
ለማግኘት ከመደበኛ ክፍያ በተጨማሪ ሌሎች ክፍያዎችን ማስከፈል፡፡

1.2.5. ስጦታ (Gift)


የሚሰጥን አገልግሎት መነሻ በማድረግ ለአገልግሎት ሰጪው ዋጋ ያለው ስጦታ በመስጠት በኃላፊው ወይም
በሠራተኛው ላይ ተጽእኖ በማሳደር ተገቢ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት የሚፈጸም ተግባር ነው፡፡ በአንዳንድ
አገሮች አንድ ሰራተኛ ሊቀበለው የሚገባ የስጦታ መጠን በህግ የተወሰነ ሲሆን ከተወሰነው መጠን በላይ
በሚሆንበት ጊዜ የማሳወቅ ግዴታ እንዳለበትም በህጋቸው ያስቀምጣሉ፡፡
በእኛም አገር በወንጀል ህጉ አንቀጽ 409 ማንኛውም የመንግስት ሰራተኛ በተሰጠው ኃላፊነት መሰረት ማድረግ
የሚገባውን ተግባር ለማከናወን ሲል ይህንኑ ተግባር ከመፈጸሙ በፊት ወይም ከፈጸመ በኋላ ጥቅም እንዲሰጠው
የጠየቀ፣ያገኘ ወይም የተስፋ ቃል የተቀበለ እንደሆነ እስከ አምስት አመት ሊቀጣ እንደሚችል ይደነግጋል::
1.2.6. ማጭበርበር
ይህ ድርጊት በከፍተኛ ተንኮልና ቅንብር የሚፈጸም ነው፡፡ የተጭበረበሩ ሰነዶች በማዘጋጀትና እንዲዘጋጁ ሁኔታዎችን
በማመቻቸት ሲሳተፉ፣ እንዲጠብቁና እንዲቆጣጠሩ ኃላፊነት የተሰጣቸው የመንግስት ባለሥልጣኖች በንግድም ሆነ
በሰነዶች ዙሪያ ሙስና ሲፈጸም እያዩ እንዳላዩ በመሆን የሚፈጽሙት ድርጊት … ወዘተ ነው፡፡ላልተገዙ የህክምና ቁሶችና
መድሃኒቶች የግዥ ሰነድ በማቅረብ፣ ላልተሰሩ ስራዎች ወይንም ለሌሉ ሰራተኞች ክፍያ በመፈጸም፡፡ባልሰሩበት አበል
መውሰድ በስፋት የሚታይ ችግር ነው፡፡ለምሳሌ ወገራ ወረዳ ጤና ጣቢያ ጽ/ቤት፡፡ፎርጅድ የትምህርት
ማስረጃ የአንድ ወረዳ ጤና ሃላፊ ፎርጅድ የትምህርት ማስረጃ በመያዙ ምክንያት ተገቢው ማጣራት
ተደርጎ 2 ዓመት ከ 6 ወር ተቀጥቷል፡፡
1.2.7. ምዝበራ

የህክምና ቁሳቁሶችን፣ መድሃኒቶችን ሰርቆ በመሸጥ ወይንም ለግል በማዋል፣ ከታካሚዎች የሚገኝ ክፍያን ለግል
በመዉሰድ፣ የተጋነነ ዋጋ በማቅረብ፣ በህጋዊ ሽፋን መስረቅ (በመዝገብ አሉ የተባሉ መድሃኒቶችና የህክምና ቁሳቁሶች

7
በቆጠራ አለመኖር)፣ መድሃኒቶች ለሌሉ ታካሚዎች ወጭ ማድረግ፣ በሽተኞቹ ቢኖሩም በነሱ ስም የወጣዉ መድሃኒት
መሰወር፣ በሽተኞች ከከፈሉ በኋላ መድሃኒቱ ወጥቶ ክፍያዉ በሰራተኞች እጅ መግባት ፣ የመንግስት መድሃኒት ለግል
ፋርማሲ መሸጥ፡፡ ደንቢያ ወረዳ አጎበር ጠፍቷል፣ በተመሳሳይ ዳባት ወረዳ 466 ሽ ብር የሚገመት አጎበር እንዲጠፋ
ባደረጉ ሰራተኞች የኮሚሽኑ ቅ/ፅ/ቤት አንዲጣራ አድርጓል፡፡በየግዜው መድሃኒት ማጉደል ይታያል፡፡አለፋ ወረዳ የጤና
ጣቢያ ሞተር ሳይክል ጠፍቷል፡፡ሻሁራ ጤና ጣቢያ ይሰሩ የነበሩ የፋርማሲ ባለሙያዎች ብር 54 ሽህ
አጉድለው ተገኝተዋል ጉዳያቸው በፍርድ ቤት በመታየት ላይ ነው፡፡

ከስራ መቅረት፡የጤና ባለሙያዎች ከስራ ሲቀሩና ያልሰሩበትን ደመወዝ መዉሰድ፡፡


1.3. የሙስና ተዋናዮቸ
ከዚህ በታች ዋና ዋና የሙስና ተዋንያኖች የሚባሉትን እናያለን፡፡
 የመንግስት ሃላፊዎች ወይም ሰራተኞችና ተጫራቾች
ሥነ-ምግባር የጎደላቸው የመንግስት ሃላፊዎች ወይም የመንግስት ሰራተኞች ውሳኔ ከመወሰናቸው በፊት
ውሳኔዉን ለተጫራቹ ለማመቻቸት ሙስና ውስጥ ሊገቡ ይችላሉ፡፡ ባንጻሩም ተጫራቾች በፊናቸው
ሙሰኛ ሃላፊዎች ወይም ሰራተኞች ሁኔታዎችን እንዲያመቻቹላቸውና ያለአግባብ አሸናፊ ሆነው
እንዲቀርቡ የሙስና ተግባር ውስጥ ሊገቡ ይችላሉ፡፡
 ወኪሎች፣አቀባባዮች፣ አማካሪዎችና እህት ኩባንያዎች
ዋነኞቹ የኢኮኖሚው አንቀሳቃሾች ጉዳያቸውን በመንግስት ዉሳኔ ላይ ተጽእኖ በማሳረፍ ሙስና ለመፈጸም
ፈልገው ነገር ግን በቀጥታ እነሱ ተሳታፊ ከሚሆኑ ይልቅ ወኪሎቻቸውን፣አቀባባዮችን፣ አማካሪዎች
ወይም እህትማማች ኩባንያዎችን የሚጠቀሙበት ጊዜ አለ፡፡
 የፖለቲካ ሰዎች
አንዳንድ ጊዜ ሥነ-ምግባር የጎደላቸው የፖለቲካ ሰዎች በመንግስት መዋቅር ውስጥ ሁለት ሃላፊነት
(የፖለቲካ እና የሲቪል ሰርቪስ) በመያዛቸው ምክንያት የፖለቲካወን ስልጣን ሽፋን በማድረግ ሙስና ውስጥ
ሊዘፈቁ ይችላሉ፡፡
1.4. በጤና ዘርፍ ውስጥ የሚከሰቱ የሙስና አይነቶች
1.4.1. ዝቅተኛ ሙስና (Petty Corruption) እና ከፍተኛ ሙስና (Grand Corruption)
በሙስና ወንጀል የሚመዘበረውን የገንዘብና የሃብት መጠን ግምት ውስጥ በማስገባት ሙስና ዝቅተኛና
ከፍተኛ ሙስና በመባል ሊከፈል ይችላል ፡፡ ዝቅተኛ ሙስና ከከፍተኛ ሙስና አንጻር ሲታይ መጠኑ አነስተኛ የሆነ
የህዝብና የመንግስት ገንዘብ በሙስና ዝውውር ውስጥ የሚውልበት ነው፡፡ ይሁን እንጂ ዝቅተኛ ሙስና ስሙ
እንደሚያመለክተው ዝቅተኛ ሳይሆን የሚያስከትለው ጉዳት ከፍተኛ ነው፡፡
ዝቅተኛ የሙስና ወንጀል የሚፈጸመው ከመንግስትና ከህዝብ አገልግሎት አሰጣጥና አቅርቦት ጋር በተያያዘ ሲሆን፣ በዚህ
የሙስና ወንጀል ውስጥ ተሳታፊ የሚሆኑት በቢሮክራሲው መዋቅር ውስጥ በየደረጃው ያሉ አንዳንድ የመንግስት
ሠራተኞችና ባለስልጣናት እንዲሁም ህገወጥ አገልግሎት ፈላጊ ግለሰቦች ናቸው፡፡

8
ከፍተኛ ሙስና (Grand Corruption)
ይህ የሙስና አይነት መጠኑ ሰፊ የሆነ የህዝብና የመንግስት ሀብት በአጭር ጊዜ ውስጥ የሚመዘበርበትና
የሚዘረፍበት የሙስና ወንጀል ሲሆን በአፈጻጸሙም ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ከፍተኛ የፖለቲካ
አመራር አካላት እና ሀብትና ዕውቀት ያላቸው ግለሰቦች የሚሳተፉበት ነው፡፡ ይህ የሚሆነው ፈጻሚዎቹ
ከፍተኛ ስልጣን፣ እውቀትና ሃብት ያላቸው በመሆናቸው ድርጊቱን በረቀቀ ስልት የመፈጸምና ሚስጢራዊ
የማድረግ አቅሙ ስላላቸው ነው፡፡ የከፍተኛ ሙስና መገለጫ መንገዶች
 ህገወጥ በሆኑ ጨረታዎች በሚፈጸሙ ከፍተኛ የግንባታ ውሎች /ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ሃይል
ማመንጫ ግንባታዎች፣ ከፍተኛ የመስኖ እና የመጠጥ ውሃ ግድብ ግንባታዎች፣የመንገድ ሥራዎች፣
በከባድ ፋብሪካዎች ግንባታዎች /
 ልዩ ልዩ ለአገር ውስጥ ምርት አገልግሎት የሚውሉ እንደ ማዳበሪያ፣ ኬሚካሎች፣መድሐኒቶች፣የህክምና
መገልገያ መሳሪያዎች እና የትምህርት መገልገያ መሳሪያዎች ለመግዛት በሚፈጸሙ ህገወጥ
ግዥዎች፣
1.4.2. ፖለቲካዊ ሙስና (Political corruption) እና ቡሮከራቲክ ሙስና (bureaucratic
corruption)
ሙስና የፈፃሚወችን የስልጣን ደረጃና ሙስና የተፈጸመበትን የስልጣን ደረጃ (ህግ አውጮች ወይስ ህግ
አስፈጻሚዎች) እንዲሁም የፈጻሚወችን ተመርጠው፤ተሹመው ነው ወይስ ተቀጥረው የሚለውን ጉዳዮች
ግምት ውስጥ በማስገባት ፖለቲካዊ ሙስና ቡሮከራቲክ ሙስና በሚል ሊከፈል ይችላል፡፡
ፖለቲካዊ ሙስና በፖለቲካ ፓርቲዎች፣ በማንኛውም ደረጃ የፖለቲካ ውሳኔ በሚሰጡ ከፍተኛ የፖለቲካ
አመራር አካላትና በመንግስት ባለስልጣናት በውሳኔ አሰጣጥ ላይ የሚፈጸም የሙስና ወንጀል ነው፡፡
ፖለቲካዊ ሙስና ብዙ ጊዜ ፖለቲካዊ ውሳኔዎች ለግልና ለቡድን ጥቅም በሚያመች መንገድ መወሰንን
ወይም እንዲወሰኑ ማድረግንና የአንድን ማህበረሰብ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት፣እሴቶችንና ልማዶችን
የመጣስ ማንኛውንም ተግባር የሚመለከት ነው፡፡ ፖለቲካዊ ሙስና በተለያዩ መልኮች የሚገለጽ ቢሆንም
ጐልተው የሚታዩ ዋና ዋናዎቹ የፖለቲካዊ ሙስና ዓይነቶች በምርጫ ወቅት የሚፈጸም ሙስና (Electoral
Coruption) ፣የመንግስት ቢሮክራሲንና የመንግስት ሥራን ለፖለቲካ ጥቅም ማዋል (Politicization of
bureaucracy) እንዲሁም በህግ አወጣጥ ሂደት ላይ የሚፈጸም ሙስና (Corruption in the legislative
process) ናቸው፡፡
1.4.3. (Riley 1998): ኢንሲደንሻል (incidental); ሲስተማቲክ (systematic) እና ሲስተሚክ
(systemic corruption)
 የአጋጣሚ ሙስና(incidental)፡- ይህ አይነት ሙስና የሚገለጸው በግለሰብ ደረጃና በ ትናንሽ
ተቋማት በሚፈፀሙ ትናንሽ ተግባራት ሲሆን ባጋጣሚና የተገኘውን ሁሉ አጋጣሚ በመጠቀም

9
ነው፡፡ በስፋቱ ቡዙ የመንግስት አካላትን ሊሸፍን ይችላል ነገርግን በተነፃፃሪ በዚህ መልኩ
የሚመዘበረው የመንግስት ሃበት ወይም የሚያደርሰው ተጽእኖ ውስን ነው፡፡
 በጥበብ የሚፈጸም ሙስና(systematic)፡-ይህ አይነት ሙስና አፈፃጸሙ በርካታ የመንግስት
ሰራተኞች በተሳተፉበትና በተደራጀ አስቀድሞ በታቀደ መንገድ ነው፡፡
 ስርአታዊ ሙስና (systemic corruption) ፡-በዚህ አይነት ሙስና የመንግስት ስርአቱ በራሱ
ለሙስና አመች ተደርጎ በሚቀረጽ መልኩ የተደራጀ ነው፡፡ ሙስና የመንግስት ስርአቱ አካል ነው፡፡
እዚህ ላይ በርካታ ምሳሌ ማቅረብ ይቻላል፡- የሞብቱ መንግስት በዛየር፤የሲያካ ሰቴቨንስ መነግስት
በሴራሊዎን በተጨማሪም በተከታታይ በናይጀርያ፤ጋቦንና፤ኢኳቶርያል ጊኒ የነበሩ ወታደራዊ
መንግሰታቶች ጥቂቶች ናቸው፡፡ “kleptocracy”, or government by theft ፡፡

ከዚህ በተጨማሪ የተላያዩ በሞያው ጥናት ያደረጉ ሙሁራን ሙስናን ከተለያየ እይታ በመመልከት በተለያየ
መልኩ ይከፋፍሉታል ከነዚህም ውስጥ፡-According to rule’ corruption (ህግን ሳይተላለፍ የሚፈጸም
ሙስና) and ’against the rule’ corruption (ህግን በመጻረር የሚፈጸም ሙስና)፣ተቋማዊ
(institutional)፣ በግለሰብ ደረጃ (individual)፣ ግለሰቦች ተደራጅተው (organized) እንዲሁም ሳይደራጁ
(disorganized)….ወዘተ፡፡
I.3.4. በጤና ዘርፍ የሚታዩ የሙስና አይነቶች በሚከተለው መልኩ ሊከፈሉ ይችላሉ

I. የመድሃኒትና የህክምና ቁሳቁሶች ግዥ ሙስና፣


II. የህክምና ዘርፍ ክፍያዎች ሙስና፣
III. የህክምና መድሃኒቶችና ቁሳቁሶች አቅርቦትና ስርጭት ሙስና
IV. የህክምና ፕሮጀክት ግንባታ ሙስና፣
V. የጤና አገልግሎት አሰጣጥ ሙስና ናቸዉ፡፡
2. የጤና ፖሊሲዉ ስለጤና ፋይናንስ ምን ይላል

2.1. የጤና ወጪ እንዴት ይሸፈናል?

1. ጥቅል ከመንግስት የሚመደብ በጀት

2. ከኪስ ቀጥታ ክፍያ (የውስጥ ገቢ)

3. በእይነትም ሆነ በገንዘብ ከአጋሮች የተገኘ ቀጥተኛ እርዳታ

4. ከሌሎች ተመሳሳይ ገቢዎች

2.2. የውስጥ ገቢ ምንጮች

1. ከልዩ ልዩ የጤና የምርመራ አገልግሎቶች

10
2. ከተኝቶ ታካሚዎች ከመኝታ አገልግሎት

3. ከመድሃኒትና አላቂ የህክምና መገልገያ እቃዎች ሽያጭ

4. ከነጻ ኅክምናና ከጤና ኢንሹራንስ ጋር በተያያዘ ከሶስተኛ ወገን ከሚሰበሰብ ገቢ

5. ሆስፒታሎች/ጤና ጣቢያዎች ከሚሰጡት የስልጠናና የምርምር አገልግሎት(ለምሳሌ፡-የተማሪዎች


የተግባር ልምምድ/Aparentship/

6. ጤና ነክ ካልሆነ ሌሎች እቃዎች ሽያጭ (ከቤት ኪራይ፣የሣር ሽያጭ….)

2.3. የሂሳብ ምርመራ(ኦዲት)

1. የሆስፒታሉ ገቢና ወጭ በሆስፒታሉ/በቢሮው የውስጥ ኦዲተር አማካኝነት ይመረመራል

2. የጤና ጣቢያ ገቢ እና ወጭ በጤ/ጥ/ጽ/ቤት ወይም የገ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በሚመድበው የውስጥ ኦዲተር


አማካኝነት መመርመር ይኖርበታል፡፡

3. የክልሉ ጤ/ጥ/ቢሮ ወይም የገ/ኢ/ል/ቢሮ በጤና ተቋሙ የፋይናንስ እንቅስቃሴ ወቅቱን የጠበቀ
ወይም ድንገተኛ ምርመራ ሊያደርግ ይችላል፡፡

4. የጤና ተቋማት ሂሳብ በበጀት አመቱ መጨረሻ መዘጋትና በክልሉ ዋና ኦዲተር ኦዲተሮች ኦዲት
ይደረጋል፡፡

5. የውጭ ዖዲት ሪፖርቱ ለጤና ተቋሙ ቦርድ( መሰረታዊ የጤና አገልግሎት ሥራአመራር ኮሚቴ)
መቅረብ ይኖርበታል፡፡

2.4. የነፃ ሕክምና አገልግሎት ስርአት

ነጻ ሕክምና ማለት ወጭው አግባብ ባለው የመንግስት አካል ተሸፍኖ የሚከፈል አቅም ለሌላቸው ግለሰቦች
ወይም ቤተሰቦች ያለምንም ክፍያ የሚሰጥ የጤና አገልግሎት ነው፡፡አንድ የጤና ድርጅት የነጻ አገልግሎት
በመስጠቱ ምክንያት ከሶስተኛ ወገን ክፍያ ያገኛል፡፡የነፃ ህክምና ሥርአትን በተመለከተ ለህዝብ፣ለጤና
ድርጅቶችና ጉዳዩ ለሚመለከታቸው አካላት ሁሉ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ መሰራት ይኖርበታል፡፡

እያንዳንዱ የጤና ድርጅት ሁሉንም የነፃ ሕክምና መረጃዎች የሚመዘግብበትን አንድ የተለየ መዝገብ
መያዝ ይኖርበታል፡፡ በነጻ ሕክምና ተጠቃሚ መዝገብ ላይ የሚመዘገቡ መረጃዎች የሚከተሉትን
ያጠቃልላል

1. የተከታታይ ቁጥር ቦታ

2. የተጠቃሚው ሙሉ ስም

11
3. ቀበሌ እና የታካሚው የመታወቂያ ቁጥር

4. የበሽተኛው/የታካሚው አይነት(ተኝቶ ታካሚ/ ተመላላሽ)

5. የተሰጠው የህክምና አገልግሎት አይነትና ወጭ(የህክምና ምርመራ፤የላብራቶሪ፣ የመድሃኒት አይነትና


ዋጋ)

ከዚህ በታች በዝርዝር የተመለከቱት ያለክፍያ የሚሰጡ የጤና አገልግሎቶች ናቸው፡፡

1. የሳንባ ነቀርሳ በሽታ ህክምናና ክትትል

2. የቤተሰብ ምጣኔ፣የቅድመ ወሊድ፣ወሊድና ድህረ ወሊድ አገልግሎት

3. የክትባት አገልግሎት

4. የ HIV/AIDS ምርመራ

5. የስጋደዌ ህክምና

6. የወረርሽኝ ክትትልና ቁጥጥር

7. የፊስቱላ ሕክምና

8. ወደፊት ያለክፍያ እንዲሰጡ የሚወሰኑ ሌሎች የጤና አገልግሎቶች

3. በጤና ዘርፍ በግዥና ፋይናንስ አስተዳደር የሚከሰት ሙስና

3.2. የመድሃኒትና የህክምና ቁሳቁሶች ግዥ ሙስና፣

3.2.1. የግዥ ጽንሰ ሃሳብ


ግዥ ማለት ዕቃዎችን፣የምክር አገልግሎቶችን፣የግንባታ ዘርፍ ሥራዎችን እና አገልግሎቶችን በግዥ፣
በኪራይ ወይም በማናቸውም ሌላ ተመሳሳይ ውል ማግኘት ነው፡፡
 የግንባታ ዘርፍ ስራ - ከህንጻ፣ ከመንገድ ወይም ከመሰረተ ልማት ጋር የሚከናወን፤
 እቃ - በጠጣር፣በፈሳሽ ወይም በጋዝ መልክ የሚገኝ ጥሬ ዕቃ፣ ምርት፣መሳሪያ፣ሸቀጥ፣ለገበያ የተዘጋጀ
ሶፍትዌር፣ እንስሳን ያጠቃልላል፤
 አገልግሎት - ከእቃ፣ከግንባታ ዘርፍ ስራ እና ከምክር አገልግሎት ውጭ ያለ ሲሆን የጥገና፣ የጥበቃ፣ የጽዳት
አገልግሎት፤ የኤሌትሪክ ኃይል…ወዘተ
 የምክር አገልግሎት - አማካሪዎች ያላቸውን ሙያዊ ክህሎት በመጠቀም የሚሰጡት የጥናት፣ የዲዛይንና
ቁጥጥር የተለያዩ ፕሮጄክቶችን የማደራጀት፣ ለደንበኞች ምክር የመስጠት፣ ስልጠና የመስጠት እና እውቀትን
የማስተላለፍ አማካሪነት ባህሪ ያለው የአእምሮ አገልግሎት ነው፡፡
3.2.2. የመንግስት ግዥ ምንነት

12
የመንግስት ግዥ ማለት በመንግስት መስሪያ ቤት በመንግስት ገንዘብ የሚከናወን ግዥ ነው፡፡
3.2.3. የግዥ አፈጻጸም መርሆዎች
 ገንዘብ ሊያስገኝ የሚችለውን ጥቅም ማስገኘት፣ (Value for money)
 በአዋጁ ከተፈቀደው ልዩ አስተያት በስተቀር በእጩ ተወዳዳሪዎች መካከል አድልዎ
አለማድረግ፣(non discrimination)
 የግዥ አፈጻጸምን ቀል ጣፋና ውጤታማ በማድረግ የሃገሪቱን ኢኮኖሚያዊ እድገት መደገፍ፣
(efficiency,and effectiveness)
 ማናቸውም የግዥ ውሳኔ የሚሰጥበት መስፈርት እና በእያንዳንዱ ግዥ ላይ የሚሰጠውን ውሳኔ
ጉዳዩ ለሚመለታቸው ሁሉ ግልጽ ማድረግ፣(transparency)
 ከግዥ አፈጻጸም ጋር በተያያዘ የሚሰጡ ውሳኔዎች እና ሚወሰዱ እርምጃዎች የሚያስከትሉት
ተጠያቂነት መኖሩን ማረጋገጥ፤(accountability)
 የሀገር ውስጥ አምራቾችን፣ ኩባንያዎችን እና አነስተኛና ጥቃቅን ኢንዱስትሪዎችን ማበረታታት
ናቸው(Domestic preference)፡፡
3.2.4. የመንግስት ግዥ ዋነኛ ዓላማ
የመንግስት ግዥ ዋነኛ ዓላማ ገንዘብ ሊያስገኝ የሚችለውን ከፍተኛ ጥቅም ማስገኘት (Value for
money) ነው፡፡ እሱም ቢሚከተሉት ሁኔታዎች ሊገለጽ ይችላል፡፡
 ትክክለኛ ጥራት (Right Quality)
 ትክክለኛ መጠን (Right Quantity)
 ትክክለኛ ዋጋ (Right Price)
 ትክክለኛ ጊዜ (Right Time)
 ትክክለኛ ቦታ (Right Source)
I. ትክክለኛ ጥራት (Right Quality)
አንድ እቃ ወይም አገልግሎት ትክክለኛ ጥራት አለው የሚባለው እቃው ወይም አገልግሎቱ የሚፈለገውን
ተግባር በብቃት እንዲያከናውን የሚያሥችሉትን ብሃርያት (quality characteristics) እንደ እቃው
ዓይነት ማቴሪያልን ፤ዲይዛይንን፤ያመራረት ዘዴንና አሰራርን ፤ልክ ቅርፁን ወዘተ አካቶ ሲገኝ ሲሆን
እነዚህን በሃሪያት በአንድ አይነት እቃ ላይ በከፍተኛ፤ በዝቅተኛ ፤ ወይም በትክክለኛ መጠን ሊገኝ
ይችላሉ፡፡
II. ትክክለኛ መጠን (Right Quantity)
የሚገዙት የህክምና ቁሳቁሶችና መድሃኒቶች መጠን በማነሱ ምክንያት መ/ቤቱ /ድርጅቱ በሚያከናውነው
ተግባር ላይ ችግር ይፈጠራል፡፡ ከሚፈለገው በላይ በብዛት በመገዛታቸው ምክንያት ደግሞ የማከማቻ ቦታ

13
ችግር ወይም ተጨማሪ የክምችት ወጭ እንዲኖር ከማድረጉም በላይ ለብልሽት ይዳረጋሉ፡፡ ሰለዚህ እቃዎች
ከተጠቃሚ ክፍሎች ፍላጎት በመነሳት በተዘጋጀ እቅድ ላይ በመመስረት በትክክለኛው መጠን መግዛት
ይኖርባቸዋል፡፡
III. ትክክለኛ ዋጋ (Right Price)
ይህ መሰረተ ሃሳብ ከላይ ትክክለኛ ጥራት ተብሎ ከተገለፀው ጋር በጣም የተሳሰረ ነው፡፡ ለምንገዛው እቃ
እንድንከፍል የምንጠየቀውን ዋጋ ትክክለኘነት ለማረጋገጥ አስቸጋሪ ቢሆንም የውድድር መንፈስ እንዲሰፍን
በማድረግ በድርድር በገቢያ ጥናት(marekete intelligence) ወዘተ …ወደ ትክክለኛ ዋጋ መቅረብ ይቻላል፡፡
በአንጻራዊ አመለካከት ግን ትክክለኛ ጥራት ላለው እቃ የሚከፈለው ዋጋ ትክክለኛ ዋጋ የሚል ስያሜ
ይኖራቸዋል፡፡
IV. ትክክለኛ ጊዜ (Right Time)
ትክክለኛ ጊዜ ማለት እቃ/ አገልግሎት በሚፈለግበት ጊዜ ከመገኘቱ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ በትክክለኛው ጊዜ
ሳይደርስ የቀረ እቃ ክንውንን የሚያስተጓጉል እንደሚሆን ሁሉ ከሚፈለግበት ጊዜ ቀድሞ የቀረበ እቃም
በስራ ላይ እስኪውል ድረስ ማከማቸት ስለሚጠይቅ ከማከማቻ ቦታ ችግር ወይም የእቃ ክምችት ወጭን
ያስከትላል፡፡ የትክክለኛ ጊዜ አስተሳሰብ ምንጭ ከጊዜ ጋር የተያያዘ እንደመሆኑ መጠን በጥንቃቄ
መንደፍ ያስፈልጋል፡፡በተለይ መድሃኒቶች ግዜው ሳያልፍባቸው ለመጠቀም ያሥችላል፡፡
V. ትክክለኛ ቦታ (Right Source)
የትክክለኛ አቅራቢ መሰረተ ሀሳብ ተገቢውን አቅራቢ ከመምረጥ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ እቃ አቅራቢው
የምንፈልገውን እቃ ለማቅረብ ፤
 የቴክኒክ ብቃት አለው ወይ ድርጅታዊ አቋሙ በቂ ነው ወይ?
 ከሽያጭ በኋላ ተገቢውን ድጋፍ ለመስጠት ይችላል ወይ?
 ከዚህ በፊት የኮንትራት ግዴታዎችን በመወጣት ረገድ ችግር ፈጥሯል ወይ? ወዘተ…. የሚሉትን
ጥያቄዎች በመመለሰ ላይ ተመርኩዞ የእቃ አቅራቢዎች ግምገማ በማካሄድ አቅራቢዎችን
መምረጥ ይገባል፡፡
3.2.5. የመንግስት ዋና ዋና የግዥ ዓይነቶች
የግዥ ዘዴ ማለት የግዥ ፈጻሚው አካል እቃዎችን፤የግንባታ ዘርፍ ስራዎችንና አገልግሎቶችን ለመግዛት
የሚጠቀምበት ዘዴ ነው፡፡ በመንግስት ግዥ አፈጻጸም ውስጥ ግልጽ ጨረታ ተመራጭና ቅድሚያ
የሚሰጠው የግዥ ዘዴ ሲሆን፤ሌሎች የተፈቀዱ የግዥ ዘዴዎች ጥቅም ላይ ሊውሉ የሚችሉት በአዋጁና
በመመሪያው የተገለጹት ሁኔታዎች ሲሟሉ ብቻ ነው፡፡
1. ግልጽ ጨረታ
2. የሁለት ደረጃ ጨረታ
3. ውስን ጨረታ

14
4. የመወዳደረያ ሀሳብ መጠየቂያ
5. ዋጋ ማቅረቢያ
6. ከአንድ አቅራቢ የሚፈጽመው ግዥ
I. ግልጽ ጨረታ
ግልጽ ጨረታ ማለት ለማንኛውም ግብር ከፋይ ዕኩል እድል የሚሰጥ እና የመንግስት የግዥ መርሆችን
ከሌሎች የግዥ ዘዴዎች በተሻለ መልኩ ማ V ላት እና ሰፊ ውድድርን መጋበዝ የሚችል የግዥ ዘዴ ነው፡፡
ከበርካታ ተጫራቾች የውድድር ተሳትፎ ከፍተኛ የእቃ፤አገልግሎት ጥራት እና ያልተጋነነ/ተመጣጣኝ
ዋጋ ያስገኛል፡፡
II. የሁለት ደረጃ ጨረታ
 የመጀመሪያው ደረጃ የመስሪያቤቱ የጽንስሀሳብ ዲዛይንና የተለዩ የክንዋኔ መስፈርቶችን
ባካተተው የጨረታ ሰነድ መሰረት በጨረታ ማስታወቂያ ዋጋን ያልጨመረ የመወዳደሪያ ሃሳብ
እንዲቀርብለት ጥሪ የሚደረግበት ነው፡፡
 በመጀመሪያው ደረጃ ብቁ የነበሩ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያን ጨምሮ ዋጋ የተገለጸበትን
የመጨረሻ ጨረታ በሁለተኛ ደረጃ ጨረታው መሰረት እንዲያቐርቡ መጋበዝ አለበት፡፡
III. የውስን ጨረታ ግዥ አፈጻጸም
ከሚከተሉት አንዱ ሲ V ላ ግዥው በውስን ጨረታ ሊፈጸም ይችላል
1. እቃው ወይም አገልግሎቱ ወይም የግንባታ ስራው ውስብስብ ወይም የተለየ በመሆኑ በተወሰኑ
አቅራቢዎች ብቻ የሚገኝ ሲሆን፤
2. በተደጋጋሚ ጨረታ ወጥቶ ምንም ተጫራች ካልቀረበ፤
3. የጨረታ ሰነዶችን ለመመርመር የሚወጣው ወጭ ከግዥው ዋጋ ጋር የማይመጣጠን ሢሆን፡፡
በውስን ጨረታ የተጋበዙት ተጫራቾች በሙሉ የመጫረቻ ሰነዳቸውን ሲያቀርቡ ሁሉም በጨረታ መክፈቻ
ጊዜው እንዲገኙ በማሳወቅና እንዲገኙ በማድረግ ጨረታው ይከፈታል፡፡
የውስን ጨረታ የግዥ ዘዴ ከግልጽ ጨረታ የሚለየው ለተጫራቾች በሚደረግ ጥሪና በጨረታ አከፋፈት
ነው፡፡
IV. በዋጋ ማቅረቢያ የሚፈጸም ግዥ
 የመንግስት መስሪያቤቶች አስቐድመው ማቀድ እስከቻሉ ድረስ ግዥን በግልጽ ጨረታ
መፈጸም ይኖርባቸዋል
 ሆኖም ሊታቀዱ ያልቻሉና ወድያውኑ ጥቅምላይ የሚውሉ ወይም በጀምላ ሊገዙ ያልቻሉ
እና ዋጋቸው ከዚህ በታች በተመለከተው ገደብ ውስጥ ሲሆን (ከብር 25000-60000) በዋጋ
ማቅረቢያ ዘዴ ለመፈጠም ይቻላል

15
 ተቀራራቢ የጥራት ደረጃ ያላቸውና በመስሪያ ቤቱ የሚፈለገውን የጥራት ደረጃ የሚያ V ሉ
አቅርቦቶችን በማወዳደር ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበውን ተጫራች አሸናፊ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡
 መ/ቤቱ በዋጋ ማቅረቢያ በተደጋጋሚ ለሚፈተጽማቸው ግዥዎች በግዥ ስራ ክፍሉ የሚካሂድ
የገብያ ጥናትን በመጠቀም ዝቅተኛ ተብሎ የሚመረጠው ዋጋ ትክክለኛ የገብያ ዋጋ መሆኑን
ማመን ይኖርበታል፡፡
V. ከአንድ አቅራቢ የሚፈጸም ግዥ
 ይህ የግዥ ዘዴ ያለውድድርና ዋጋን ጨምሮ ድርድር በማድረግ ግዥ ለመፈጸም የሚያስችል
የግዥ ዘዴ ነው
 የጨረታ ሰነድ ማዘጋጀትና ብቸኛውን ተጫራች የመገምገሙ ስራ ለግልጽ ጨረታ የተቀመጠውን
ሥነሥርአት ተከትሎ መፈጸም የሚገባ ሲሆን ጨረታውን ለሚያጸድቀውን ኮሚቴ የሚቀርበው
የጨረታ የግምገማ ሪፖርት አንዱ አቅራቢ የተመረጠበትን ምክንያት በግልጽ ማመልከት
ይኖርበታል፡፡
3.3. በግዥ ውስጥ የሚፈጸሙ የሙስና መከሰቻ አጋጣሚዎች (ዝርዝር የሙስና መገለጫዎች)
በእያንዳዱ የግዥ ዑደት ውስጥ ሙስና ሊፈጸም ይችላል፡፡ ለመሆኑ የግዥ ዑደት የሚባሉት ምንድን ናቸው? የግዥ
ዑደት ከግዥ ፍላጎት(እቅድ) ጀምሮ እስከ ማስወሰገድ ያሉትን የግዥ ተግባራት ያጠቃልላል፡፡ ቀጥሎ የዕቃ ግዥ
ዑደትን ለአብነት እንመልከት፡

16
ማቀድ የግዥ ዘዴ መምረጥ

ጨረታን መገምገምና
ግምገማ አሸናፊን መለየት

ለዕቃ ግዥ

ግዥ ተግባራዊ
ንብረት ማስወገድ የሚሆንበት ሂደት

የሂሳብ ማጣሪያ
የሚደረግበት ወቅት

የመንግስት ግዥ ዑደት ከግዥ ፍላጎት መመንጨት ጀምሮ የዕቃዎች አገልግሎት ዘመን እስከሚጠናቀቅበት
ጊዜ ድረስ ያለውን ዑደት የሚያካትት ነው፡፡

የግዥ ዑደት
1. በግዢ እቅድና ፍላጎት ዳሰሳ ወቅት
 ፍላጎትን በማሰባሰብ የሚገዙ እቃዎችን አገልግሎቶችንና የግንባታ ሥራዎችን
መለየት
2. በጨረታ ሰነድ ዝግጅት ሂደት
 እንደግዥው ዓይነትና ብሃሪ ከተፈቀዱት የግዥ ዘዴዎች ውስጥ ተስማሚ የግዥ ዘዴ
መምረጥ
3. አሸናፊ በሚለይበት ሂደት
 በተጫራቾች የቀረበን ሰነድ መስፈርቱን መነሻ በማድረግ መገምገም
 አሸናፊ ተጫራቾችን መለየትና ውጤቱን ለሁሉም ተጫራቾች ማሳወቅ

17
4. ግዥ ተግባራዊ በሚሆንበት ሂደት(ውል ተፈጻሚ በሚሆንበት ወቅት)
 ግዥ ተግባራዊ በሚሆንበት ሂደት(ውል ተፈጻሚ በሚሆንበት ወቅት)
 የክፍያ አፈጻጸም ሂደትን መከታተል
5. የሂሳብ ማጣሪያ በሚደረግበት(በክፍያ) ወቅት
6. በንብረት አወጋገድ ሂደት
7. ግምገማ
በዋና ዋና የግዢ ዑደቶች ውስጥ ከሚከሰቱ የሙስና አጋጣሚዎች መካከል ከዚህ በታች የተገለጹት
የሚጠቀሱ ናቸው፡፡
ሀ/ የግዥ ዕቅድና የፍላጎት ዳሰሳ በሚደረግበት ጊዜ የሚፈጠሩ የሙስና አጋጣሚዎች፡-
 የጤና ተቋማት የመድሃኒት ፈላጎቶቻቸውን በአግባቡ ተንትነው የግዥ ጥያቄ አስቀድመው
እይጠይቁም
 የህክምና ቁሳቁስና መድሃኒቶች ግዥ አስፈላጊ ላይሆን ይችላል፤ይሁን እንጂ አንድ የተወሰነ
ድርጅትን(ኩባንያ) ለመጥቀም ሲባል ግዥው አስፈላጊ እንደሆነ ተደርጎ ሊቀርብ ይችላል፤
 በትንሽ ወጪ ሊጠገን የሚችል የህክምና መሳሪያ በአዲስ እንዲተካ በማድረግ ሻጭ ተጠቃሚ
እንዲሆን ማድረግ፤ ለምሳሌ ሹፌር ፤ከግዥ ባለሙያና ከባለጋራዥ ጋር በመመሳጠር ያልተበላሸ እቃን
ተበላሽቷል በማለት ግዥ እንዲፈጸም ማድረግ፡፡
 ሥነምግባር የሌላቸው ሰራተኞች ለግል ጥቅማቸው ሲሉ ለስራው ከሚያስፈልገው መጠን በላይ
የህክምና ቁሳቁስና መድሃኒቶች ሊጠይቁ ይችላሉ፤
 ሆን ብሎ የግዥ ጥያቄ አለማቅረብ፡፡በጤና ተቀዋሙ መድሃኒት የለም፤የሚፈልጉት የላብራቶሪ እና
የራጅና መሰል ምርመራዎች የሉም ስለዚህ ወደግል የጤና ድርጅቶች ሂዱ በሚል ተጠቃሚ
እንዲሆኑ ማድረግ(በሚፈጠር ህገወጥ የጥቅም ትስስር)
ለ/ በጨረታ ሰነድ ዝግጅት ሂደት የሚፈጠሩ የሙስና አጋጣሚዎች፡-
 የመለያ መስፈርቶች ሲዘጋጁ አንድን የተለየ አቅራቢ ብቻ ለመጥቀም ሲባል መስፈርቶችን
ማዘጋጀት ፤
 በጤና ተቋሙ ያለው የመድሃኒት ግዥ በተቀመጠው ስታንዳርድ ያለማዘጋጀት
 የሚገዙ የህክምና ቁሳቁስና መድሃኒቶች ከሚፈለጉበት ጉዳይ በላይ ወይም በታች እንዲገመቱ
በማድረግ፤
 የጨረታ ሰነድ ዝግጅትን ውስብስብ በማድረግ ወይም መለያ መስፈርቶችን ውስብስብ በማድረግ
መወናበድ እንዲፈጠር በማድረግ ለሙስና መከሰት አጋጣሚዎች እንዲፈጠሩ ማድረግና ፤
ሐ/ አሸናፊ በሚለይበት ሂደት የሚፈጠሩ የሙስና አጋጣሚዎች

18
 ውሳኔ ሰጪ አካላት በእከከኝ ልከክህ፣ በጥቅም ግጭት፣ በጉቦ አማካኝነት ውሳኔዎችን ሊያጣምሙ
ይችላሉ፤ለምሳሌ ለጥገና የሚወጣውን ወጭ ጥገና የሚያደርገው አካል ለሚያስጠግነው
ባለሥልጣን የሚያካፍል ሲሆን (ፈርቅ)፡፡
 ሚስጥራዊ የሆኑ ጉዳዮችን ለአንዱ ተጫራች ብቻ በማሽሎክ አንዱ ተጠቃሚ እንዲሆን ማድረግ

 አሸናፊን የመምረጫ መስፈርት ግልጽ(ይፋ) በማይደረግበት ጊዜ፣
 የጨረታ ግምገማ ውጤትን ለአሸናፊ ተጫራች አሳውቆ ለተሸናፊ ተጫራች ሳያሳውቁ ወደ ውል
መግባት፣
 ጨረታ ሳይወጣ ጨረታ ወጥቷል በሚል ግዥ ያለጨረታ በመፈጸም በጨረታ እንደተፈፀመ
በመቁጠር የመንግስት ገንዘብ ማጭበርበር፡፡
 የጨረታ መቆያ ጊዜን ሳይጠብቁ ጨረታ መክፈት፤
 ተጫራቾች በመመሳጠር አንዱ ተጫራች ከገብያ ዋጋ እጅግ በተጋነነ ዋጋ እንዲገዛ ማድረግ
 ቀደም ብሎ በጨረታ ሰነድ ላይ ያልተመላከቱ የማወዳደሪያ መስፈርቶችን ለጨረታ ግምገማ
ጥቅም ላይ እንዲውሉ በማድረግ የሙስና አጋጣሚዎች ሊከሰቱ ይችላሉ፡፡

መ/ ግዥ ተግባራዊ በሚሆንበት ሂደት የሚፈጠሩ የሙስና አጋጣሚዎች


 ከስፔስፍኬሽን ወይም ከውል ስምምነት በታች (ጥራት የሌለው) የህክምና ቁሳቁስና መድሃኒቶች
ሲቀርብ በጉቦ ወይም በሌላ ሥጦታ አማካኝነት ዝም ተብሎ ሊታለፍ ይችላል፤
 አቅራቢ በሸፍጥ (በሃሰት) ለሚያቀርበው ቅሬታ የሚመለከታቸው ሃላፊዎች ቅሬታውን እንደ
ትክክለኛ ቅሬታ በመውሰድና በመስማማት የሙስና አጋጣሚ ሊፈጠር ይችላል፡፡
 ለጤና አገልግሎት የማያስፈልጉ መድሃኒቶች የመጠቀሚያ ግዚያቸው ሊያልፍ ጥቂት ግዜ ሲቀር ወደጤና
ተ g ማት የሚገፉበትና ጥቅም ላይ የማይውሉ የሚወገዱበት ሁኔታ ይታያል፡፡
ሠ/ የሂሳብ ማጣሪያ በሚደረግበት ወቅት የሚፈጠሩ የሙስና አጋጣሚዎች
 የሂሳብ ባለሞያዎች ወይም ኦዲተሮች የተጭበረበሩ ሰነዶች በሚቀርቡላቸው ጊዜ በተጭበረበረዉ
ሰነድ ሆን ብለው በመስማማት የሙስና አጋጣሚዎችን ሊፈጥሩ ይችላሉ፡፡
ረ/ በመንግስት ንብረት አስተዳደርና አወጋገድ ላይ ስለሚገጥሙ የሙስና አጋጣሚዎች
የሚወገዱ ንብረቶች ለዚያ መስሪያ ቤት አገልግሎት የማይሰጡ ቢሆንም የህዝብ ሃብት ናቸውና ባግባቡ
ሊወገዱ ይገባል፡፡ በመሆኑም ግዥ በውል ሲፈጸም እንደሚደረገው ሁሉ፣ የሚወገዱ ንብረቶችንም
የማስወገድ ሂደት በእቅድና የገንዘብን ዋጋ ባገናዘበ መልኩ መሆን ይገባዋል፡፡ በማስወገድ ሂደትም የሚፈጠሩ
የሙስና አጋጣሚዎችን ለመከላከል በሚያስችል መልኩ መሆን ይገባቸዋል፡፡ ከዚህ በታች የተገለጹት
ንብረትን በማስወገድ ሂደት ሊከሰቱ የሚችሉ የሙስና አደጋዎች ናቸው፡፡

19
 የሚገለገሉበትን ንብረት አገልግሎት በማሳነስ( የማይሰራ በማስመሰል) ከሚወገዱ እቃዎች ውስጥ
እንዲመደብ ሊያደርጉ ይችላሉ፤
 የሚወገዱ የህክምና መሳሪያዎች፤መድሃኒቶች በቀጥታ ሊሸጧቸው የሚችሉበት ሁኔታ ሊፈጠር
ይችላል፤
 የሚወገዱ የህክምና መሳሪያዎች፤መድሃኒቶች በጨረታ በማስወገድ ሂደት ለእጩ ተወዳዳሪዎች
መረጃዎችን አስቀድመው ሊሰጡ ይችላሉ፤

4. የህክምና ዘርፍ ክፍያዎች ሙስና፣

 ተገቢ ያልሆኑ ክፍያዎች ማለትም ታካሚዎች የተሻለ የህክምና አገልግሎት ለማግኘት በሚል ከመደበኛ ክፍያ
በተጨማሪ ሌሎች ክፍያዎችን ማስከፈል፡፡

 ከታካሚዎች የሚገኝ ክፍያን ለግል መዉሰድ፣

 ከመንግስት እውቅና ውጭ የገቢ ደረሰኝ በማሳተም ገንዘብ መሰብሰብና ለግል ማዋል፣

 የግል የህክምና አገልግሎት ወደጤና ጣብያው እንዲመጡ በመቅጠር መስራትና ገንዘቡን ለግል
ማዋል፣ለምሳሌ ደባርቅ ላይ አቦርሽን ለማድረግ ከቤቱ ይስማማና ገንዘብ ተቀብሎ ውርጃውን
ሆስፒታል በመቅጠር እንዲከናዎን ማድረግ፣

 ላልተገዙ የህክምና ቁሶችና መድሃኒቶች የግዥ ሰነድ ማቅረብ፣

 ላልተሰሩ ስራዎች ወይንም ለሌሉ ሰራተኞች ክፍያ መፈጸም፣ ባልሰሩበት አበል ማወራረድ በስፋት ይታያል፡፡
ለምሳሌ ወገራ ወረዳ ጤና ጣቢያ ጽ/ቤት……..፡፡በተለይ ከዱቲ ክፍያ ጋር ተያይዞ ያልሰሩበትን
ክፍያ መውሰድ፡፡የዱቲ ክፍያን እንደመደበኛ ደሞዝ እንጅ አገልግሎት ስንሰጥ ብቻ የሚከፈል
አድርጎ አለመውሰድ፡፡

 በህጋዊ ሽፋን መስረቅ (በመዝገብ አሉ የተባሉ መድሃኒቶችና የህክምና ቁሳቁሶች በቆጠራ አለመኖር፣)

 በሽተኞች ከከፈሉ በኋላ መድሃኒቱ ወጥቶ ክፍያዉ በሰራተኞች እጅ መግባት፣

 ህጉ ከሚፈቅደው የገንዘብ መጠን በላይ በካዝና ማስቀመጥና በህጉ መሰረት ገንዘቡን በወቅቱ ወደባንክ
አለማስገባት፣

 የተሰበሰበውን ገንዘብ ወደ ባንክ ከማስገባት ይልቅ ለግል ጥቅም ማዋልና ሌላ ጊዜ ማስገባት እችላለሁ ማለት፣

 ገንዘብ ያዡ የባንክ እስተትመንት ለሂሳብ ኦፊሰሩ አለማቅረብ፣

20
 ስነምግባር የጎደላቸው የጤና ተቋማት ገንዘብ ያዦች አራጣ ማበደር፣

 በገንዘብ ያዡ የገንዘብ ጉለት እያጋጠመ ነው፡፡የገንዘብ ጉለት በተገኘባቸው በአስቸኳይ ገንዘቡን እንዲመልሱ
ተደርጎ ወደህግ አለማቅረብና ጉድለት ያለባቸውን ሰራተኞች በነበሩበት የስራ መደብ ማስቀጠል፣

 ፋከቱር አለመስጠት ወይም ፋከቱር ላይ ማጭበርበር በሂያጅና ቀሪ ካርኒዎች መካከል ልዩነትን መፍጠር፣ ካርኒ
የማበላለጥ ለምሳሌ በራሪው ላይ 2000 ቀሪው ላይ 1000 ብር መዝግቦ የነበረ ተይዟል፣

 የገንዘብ መሰብሰቢያ ደረሰኝ በአግባቡ ስራ ላይ መዋላቸውን ያለመቆጣጠር ከዚህ ጋር ተያይዞ የገቢ ደረሰኝ
መሰወር፣

 ሰነዶችን መሰረዝ ፣ መደለዝ…ወዘተ.የሚፈጸም የሙስና ወንጀል ነው፣

 በነጻ መሰጠት የነበረባቸው መድሃኒቶችና የህክምና መሳሪያዎች መሸጥ፡፡ለምሳሌ አጎበር፣የቲቨ


መድሃኒቶች፣አልሚ ምግቦች፣..ወዘተ

5. የህክምና መድሃኒቶችና ቁሳቁሶች አቅርቦትና ስርጭት ሙስና

 ስርቆትና ዝርፊያ፡ የህክምና ቁሳቁሶችን፣ መድሃኒቶችን ሰርቆ በመሸጥ ወይንም ለግል በማዋል፣ ዉድ የሆኑ
መድሃኒቶች በየቦታዉ በስፋት መዘረፍ፣ ወጥተዉ መሸጥ፣

 ላልተገዙ የህክምና ቁሶችና መድሃኒቶች የግዥ ሰነድ በማቅረብ፣ የተጋነነ ዋጋ በማቅረብ፣

 በህጋዊ ሽፋን መስረቅ (በመዝገብ አሉ የተባሉ መድሃኒቶችና የህክምና ቁሳቁሶች በቆጠራ አለመኖር፣

 መድሃኒቶችን ለሌሉ ታካሚዎች ወጭ ማድረግ፣

 በሽተኞቹ ቢኖሩም በነሱ ስም የወጣዉ መድሃኒት መሰወር፣

 ለወረዳ የሚመደቡ መድሃኒቶች ከተማ ላይ በድብቅ የሚከማቹ፣

 መድሃኒቶች ቢሆን ጊዜ ያለፈባቸዉና ጉዳት የሚያደርሱ መሆን፣

 የህክምና ቁሳቁሶችን እና ንብረቶችን እያወቁ ማበላሸት ፡ የመንግስት የህክምና ቁሳቁሶች ወይንም ንብረቶች
ታስቦበት ጉዳት እንዲደርስባቸዉ አድርጎ ጉቦ የሰጡ የግል ጤና ተቋሞችን ማስጠቀም፣

 የመንግስት ቁሳቁሶችን(ለምሳሌ የላብራቶሪ መሳሪያዎችን)ለግል ትቅም ማዋል

 በነፃ በርዳታ የሚመጡ መድሃኒቶችና የህክምና መሳሪያዎች ገቢ ሳይደረጉ መዘረፍ፡፡ለምሳሌ አጎበር


ዳባት ላይ እንዲከፋፈል ከመጣ በኋላ የጠፋበት ሁኔታ አለ፣

21
 የህክምና መሳሪያዎች ተከላ በሚድረግበት ወቅትም አስፈላጊው ቅድመ ሁኔተ ሳይሟላ ስራ
እንዲጀምሩ የተደረገባቸውና ለብልሽት የሚዳረጉ መሳሪያዎች መኖራቸው፡፡

6. የህክምና ፕሮጀክት ግንባታ ሙስና፣

 ያልተጠናቀቁና ደረጃቸዉን ያልጠበቁ ግንባታዎች መረከብ ፣

 ተገቢውን የግንባታ ብረት አለመጠቀም ወይም ከተፈላጊ ደረጃ በታች የሆኑ ግንባታ ተግባሮች
(substandard building practices) መፈጸም ናቸዉ፡፡

 ከግንባታ ጋር ተያይዞ የውሸት ሪፖርት ማቅረብ፡፡ከሽንት ቤት ጋር ተያይዞ …ወዘተ

7. የጤና አገልግሎት አሰጣጥ ሙስና ናቸዉ፡፡

 ለገንዘብ ጥቅም ሲባል ሰዎችን ለህክምና ሙከራ ማዋል፡ ተመራማሪዎች ድሃና ያልተማሩትን በመመልመል
የህክምና ሙከራ በማድረግ ከህክምና ኩባንያዎች ክፍያ ያገኛሉ፣

 መታከም ከሚገባቸዉ ዉጭ ሌሎች ህክምናዎችን በማዘዝ ለተጨማሪ ወጭ መዳረግ፡፡ የጤና ዘርፍ ሙስና
የዚህ ጽሁፍ ትኩረት ስላልሆነ አይቀርብም፡

8. ለሙስና የሚያጋልጡ ሁኔታዎች /ምክንያቶች/


8.2. ደካማ አስተዳደር (Poor governance)

ከተለያዩ ተሞክሮዎች መረዳት እንደሚቻለው መልካም አስተዳደር በሌለበት ሁሉ ከፍተኛ የሆነ


የሙስና ችግር አለ (TI)፡፡ ሳምሶን ካሳሁን(2011) የመልካም አስተዳደርን ሙስናን ለማሰወገድ ያለውን
አስተዋጾ ለማሳየት ባጠናው ጥናት ላይ የሚከተለው መደምደሚያ ላይ ደርሷል፡-
“Corruption, which undermines development, is generally an outcome and a symptom of poor
governance.” ሙስና እድገትን የሚያዳክምና ¾Å"T ¨ÃU ¾SØö ›e}ÇÅ` (Poor governance) ›Ã’}
— SÑKÝ“ ¨<Ö?ƒ ’¨<::
እዚህ ላይ ክሊትጋርድ የተባለ ግለሰብ ሙስናን የገለፀበትን ቀመር መመልከት ተገቢነት ይኖረዋል C =
M+D-A ይኸውም C = Corruption, M = monopoly, D = discretion, A = accountability
(Klitgaard 1998,p3-6) ፡፡ ይህ አገላለፅ ይበልጥ ተቀባይነት እያገኘ የመጣ ሲሆን የተባበሩት መንግስታት
የልማት ፕሮግራም (UNDP) እየተባለ የሚጠራው ድርጅት ይህን ቀመር በማሻሻል C = (M+D) -
(A+I+T) በሚል ገልፆት እናገኘዋለን፡፡ የቀመሩ ወካዮችም C= corruption, M= monopoly, D=
discretion, A= accountability, I= integrity, T= transparency የሚሉ ናቸው፡፡ የህ የሚያሳየው

22
የ AIT መቀነስ፤ ስልጣን በሞኖፖል መያዝና፤ሰፊ የመወሰን ስልጣን መኖር ሙስናን እያባባሱት
እንደሚሄዱ ነው( Klitgaard 1998,p3-6)፡፡
የዚህ ቀመር መሠረታዊ ጭብጥም በአንድ የመንግስት አስተዳደር ውስጥ የመወሰን ስልጣን በጥቂቶች እጅ
ከተሰባሰበ እና የተሟላ ስብእና፣ ተጠያቂነትና ግልፅነት መርሆወች ካልዳበሩ ሙስና እየተስፋፋና እየጐለበተ
የሚመጣበት ሁኔታ ይፈጠራል የሚል ነው ይህ ማለት ግን ሠፊ የመወሰን ስልጣን ማግኘት ወይንም ስልጣን
በጥቂቶች እጅ መጠራቀም ብቻውን የሙስና ድርጊት ይወልዳል ማለት አይደለም ፤ይልቁንም ይህን ምቹ
ሁኔታ ወደ ተግባር ለመቀየር የሚያስችል ኢ- ሞራላዊ ወይንም ኢ ስነምግባራዊ ህሊናዊ ሁኔታ መኖር የግድ
ይላል ፡፡
I. የሠራተኞች የሥነምግባር ብልሹነትና የአቅም ማነስ
ወደ አስተዳደር ስርዓት ውስጥ የሚመጡ ሠራተኞች የተቋሙን ተልእኮ ለማሳካት በሚያስችል ሥነ-ምግባር የታነጹ ሊሆኑ
ይገባል፡፡ የተሟላ ስብእና ያለው ባለሙያ በሚሰራው ሥራ ህዝብን በማርካት እና አገልግሎቱን በሚፈለገው ሁኔታ
በማቅረብ ሕዝብ በመንግስት ላይ እምነት እንዲኖረው ያደርጋል::
የተሟላ ስብዕና የሚለው ጽንስ ሃሳብ አድልዎ አለመፈፀም፤ሕግን ማክበር፤ሀቀኝነት (Honesty) ታማኝነት (Loyality)
፤የሕዝብን ጥቅም ማስቀደም (Serving the Public Interest)…የሚሉትን ያጠቃልላል (UN-Habitat 2013)፡፡
ለምሳሌ የተለያዩ የህክምና መሳሪያዎች፣መድሃኒቶች፣ላብራቶሪ ኬሚካሎች ብክነት ስንመለከት ያለው አመራና ባለሙያ
ወቅታዊ የመፍትሄ አማራጭ ከመፈለግ ይልቅ ዝምታን ይመርጣል፡፡በጤና ተቋማት ያሉ መሳሪያዎችን ሆን ብሎ
በማበላሸት(ለምሳሌ የላብራቶሪ ምርመራ አንቀበልም) የሚያገለግሉበትን ሰዓት ያለአግባብ መገደብና ተገልጋይን
ላልተፈለገ ወጭ መዳረግ፡፡ከጥበቃ ጀምሮ ወደ ጤና ተቋም የሚመጣ ተገልጋይ በአክብሮት ሊስተናገድ ሲገባው
የማመናጨቅ፡፡ በካርድ ክፍል ያለው መስተንግዶም ብዙ ቅሬታ የሚነሳበት ነው፣የታካሚ ካርድ የሚጠፋበት፣ካርድ
ለማውጣት ረጅም ጊዜ የሚወስድበትና ተገልጋይ የሚመናጨቅበት ጉዳይ በስፋት ይታያል፡፡ የጥዋት ስብሰባ
መራዘም፣በገደብ የለሹ የሻይ እረፍት ተገልጋዩ ህክምና ለማግኘት ረዥም ሰአት ለመጠበቅ ይገደዳል፡፡
የባለሙያዎች መስተንግዶ ጋር ተያይዞም የሚነሱ ችግሮች አሉ፡፡በተለይም ለታካሚው ስለህመሙ ስለሚያስፈልጉት
ምርመራዎች እና ሊያገኘው ስለሚገባ የህክምና አይነት በአግባቡ ማስረዳት ከእለት ተእለት የህክምና አሰራር
እየጠፋ ያለ እሴት ነው፡፡ በተጨማሪም በተኝቶ ህክምና ነርሶች የታካሚዎችን የስነልቦና ማህበራዊ እና
የአካላዊ ጤንነታቸውን ሊያሻሽሉ በሚችሉ ሁሉን አቀፍ እንክብካቤ መሳተፍ ላይ እየቀረ የመጣ የነርሲግ
አገልግሎት ነው፡፡ በድንገተኛ ሕክምናም የባለሙያዎች ተነሳሽነት፣አገልግሎት ለመስጠት ያላቸው
ዝግጁነት፣እንዲሁም የሞያ ብቃት መሻሻል የሚገባው ጉዳይ ነው፡፡ ጤና ተቋማት ከሰው ሰው ማዳላት ፣በቂ
ምርመራ ያለማድረግ ማለትም በተለያዩ ተቋማት የሚደረጉ ምርመራዎች የተለያየ ውጤት መስጠት፡፡
አንዳንድ ጤና ባለሙያዎች ታካሚዎችን የማመናጨቅ፡፡አምቡላንስ በተገቢው መንገድ አገልግሎት
እየሰጡን አይደለም ገንዘብ እያስከፈሉን ነው ሹፌሮችም እያመናጨቁን ነው በሚል ተቃውሞ

23
ይነሳሉ፣የህዝብ ወገንተኝነት በሚገባ አለመዳበር እና ቸልተኝነት፣የአገልጋይነት ስሜት
አለመኖር፣የመንግስት የስራ ሰአት አለማክበር፣በባለሙያዎች መካከል ተቀራርቦና ተደጋግፎ
አለመስራት፣በአቅራቢያ ወደሚገኝ ከተማ መሄድና በዚያው መቅረት፣የግል ተግባራትን በማስቀደም
የተሰጠን የመንግስት ሃላፊነት ወደጎን መተው፡፡

“Corruption is a disease and integrity in the civil services its prevention” (UN-Habitat 2013)

II. ግልፅነት ያለመኖር


ግልፅነት ሰዎች መረጃዎችን በቀጥታ የሚያውቁበትን እና የሚያገኙበትን ሁኔታ ማመቻቸትን፣ ወይም የሁለት አካላትን
ቀጥተኛ እና ግልጽ ግንኙነትን የሚመለከት ነው፡፡
ለተገልጋይ አገልግሎት በሚሰጥበት ወቅት በተሰጠ ውሳኔ ላይ ውሳኔው ምን እና ለምን እንደሆነ ተገልጋዩ ሲጠይቅ
ሊገለጽለት ይገባል፡፡ ተገልጋዩ በመ/ቤቱ ስለሚያገኘው አገልግሎትም ሆነ ስለአሰራሩ ማወቅ ሲፈልግ በቂ መረጃ ማግኘት
አለበት፡፡ በዚህም ደንበኛው ለራሱ በእውቀት ላይ የተመሠረተ ውሳኔ እንዲወስን ያደርጋል፡፡
ለመንግስት ሰራተኛው የሚሰጥ ግቦ (bribary) የተወሳሰበ አሰራር ባለበትና ግልጽነት በሚጎልበት ጊዝ በከፍተኛ ደረጃ
ይንሰራፋል (TI Working Paper # 04/2011)፡፡ “ሙስና የሚያብበው በጭለማ ነው” የሚል አባባል አለ፡፡ ይህ
አባባል ከመረጃ ተደራሽነት ጋር ይያያዛል፡፡ የመረጃ ነጻነት ፖሊሲ የሌለው መንግስት በሃላፊዎች የሚወሰኑ ውሳኔዎችና
የመንግስት እንቅስቃሴዎች ላይ መረጃ ለማግኘት እንቅፋት ይሆናል፡፡ መረጃ የማይገኝ ከሆነ ደግሞ ሙስናን ለመደበቅ
አመቺ ስለሚሆን ሙስና ለመስፋፋቱ ምክንያት ይሆናል፡፡
ብዙ ግዜ ከተወሰኑ ተጫራቾች ጋር በመመሳጠር የጨረታ መረጃዎችን ግልጽነት በመገደብ ለሙስና
የተመቻቹ ሁኔታዎች ሲፈጠሩ ይታያሉ፡፡ለምሳሌ የጨረታ ማስታወቂያውን በትክክለኛ ቦታ
አለመለጠፍ፤በቶሎ ማንሳት ወይም ሌሎች ማስታወቂያዎች እንዲለጠፉበት ማድራግ… ወዘተ
የጤና ባለሙያዎች፣ መድሃኒት አቅራቢዎች፣ ተጫራቾች፣ ወዘተ ከታካሚዎችና ከመ/ ሰራተኞችና ሃላፊዎች ስለ
አገልግሎቱ የበለጠ መረጃና እዉቀት ያላቸዉ ሲሆን የታካሚዎችንና ተገልጋዮችን አለማወቅ ባለሙያዎች ይህንኑ
በመጠቀም እስከመጨረሻዉ የግል ሃብት ለማካበት መጠቀሚያ ያደርጉታል፡፡ ብዙ ጊዜ ህዝቡ ስለምግብ መድሃኒትና ጤና
ቁጥጥር ህጎች በቂ ግንዛቤ ስለሌለን መብታችን ማስከበር አልቻልነም በሚል ያነሳሉ፡፡ከዚህ ጋር ተያይዞ የሚድያ
ኮሚኒኬሽን ስራዎች በሚገባ አለመጠናከር ችግሩን አባብሶታል፡፡
III. የተጠያቂነት ችግር
ተጠያቂነት አንድ ሰው ለሚሰጠው ውሳኔም ሆነ ለሚወስደው እርምጃ ሃላፊነትን መውሰድ፣ ሲጠየቅ መልስ መስጠትን
የሚያመላክት ሲሆን ተጠያቂነቱ ከፖለቲካ፣ ከሕግ፣ ከገንዘብ፣ ከአስተዳደር ወዘተ.. አኳያ ሊሆን ይችላል፡፡ የመንግስት
ሰራተኛ ለሚሰራው ስራ ኃላፊነቱን ለመውሰድ ዝግጁ የሆነና ተጠያቂነትን የሚቀበል መሆን ይኖርበታል፡፡

24
የሙስና ተጤቂነትን የሚያረጋግጡ ተቋማት ማለትም ፍርድቤቶች፤ኦዲት መስሪያ ቤቶች፤የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋማት፤
የጸረ ሙስና ተቋማት….ወዘተ ስራቸውን በአግባቡ ካልሰሩ ወይም የፖለቲካ ጣልቃ ገብነት ካለባቸው በሙስና የተዘፈቁ
ሰወችን ተጠያቂ የማድረግ እድል አደጋ ላይ ይወድቃል፡፡ የተቀጀ የኦዲቲንግ ኢኒስፔክሽን አለማካሄድ ለምሳሌ የገንዘብ
መሰብሰቢያ ደረሰኝ በአግባቡ ስራ ላይ መዋላቸውን ያለመቆጣጠር ፣ በጤና ተቋማቱ የስነምግባር ክፍተት
የሚታይባቸውን ባለሙያዎች ተገቢውን እርምጃ አለመውሰድ፣ሹፊሮች ህጉንና ስነምግባርን ጠብቀው እንዲሰሩ ጥብቅ
ቁጥጥር አለማድረግ፣ ከሙስና ጋር በተያያዘም የስነምግባርና ፀረ ሙስና ከሚሽን በኩልም በሚመጡ ጥቆማዎች ላይ
አፋጣኝ ምላሽ ያለመስጠት ችግር አለ፡፡
IV. ገደብ የለሽ ስልጣን (Monopoly of Power)
አንድ ግለሰብ ገደብ የለሽ ስልጣን ካለው ሰፊ የሆነ የመወሰን ስልጣን ይኖረዋል የተጠያቂነት ሁኔታውም አደጋ ላይ
ይወድቃል፡፡ ስለዚህ የእርስበርስ ቁጥጥር (cheke and balance) እና በቂ የሆነ የስልጣን ክፍፍል (Separation of
power) በአንድ ተቋም ብሎም አገር ወሳኝ ጉዳዮች ናቸው፡፡
ስለዚህ ስልጣንን ማከፋፈልና (separation of power) በተለያዩ የመንግስት አወቃቀር ላይ ቼክ ኤንድ
ባላንስን በመፍጠር ተጠያቂነት እንዲሰፍን ማድረግ ተገቢ ነው፡፡ ይህ ሰተራቴጅ ዘመን ያስቆጠረውን ጥያቄ
ማለትም“ጠባቂውን ማን ይጠብቀዋል?” የሚለውን ጥያቄ የሚመልስ ነው፡፡
V. ሰፊ የመወሰን ስልጣን (Discretionary power)
ህጋዊ በሆነ ስልጣን በአግባቡ መገልገል (Exercising Legitimate Authority) የመንግስት ተሿሚ
ባለስልጣናት፣ የሥራ ሃላፊዎች እና ሰራተኞች ሥራውን ለማከናወን የተሰጣቸውን ስልጣን ሥራውን
በሚመጥን ደረጃ ብቻ እንዲገለገሉበትና ከገደቡ አብልጠው ወይም አሳንሰው አንዳይጠቀሙበት የሚገድብ
ነው፡፡ አስተዳደራዊ አሰራሮችና ውሳኔዎች በህግና መመሪያ ላይ የተመሰረቱ መሆን አለባቸው፡፡ ውሳኔዎች
በሃላፊዎችና ሰራተኞች ሰፊ የመወሰን ስልጣን (discretion) ላይ የሚወድቁ ከሆነ ለሙስና የመጋለጥ
አጋጣሚው ሰፊ ይሆናል፡፡
በመጨረሻም የተሟላ ስብዕና ሞያዊ ስነምግባር በሌለበት፤ግልፅነት በተጓደለበት ፤ተጠያቂነት በማይተገብርበት፤ገደብ

የለሽ ስልጣን በተንሰራፋበትና ከዚሁ ጋር ተያይዞ የሚከሰት ሠፊ የመወሰን ስልጣን ሙስና በከፍተኛ ደረጃ
እንዲስፋፋ ያደርጋል፡፡
8.3. በበጀት ዓመት መጨረሻ የሚፈጸም ግዥ (የግዥ እቅድ አለማዘጋጀት)
አንድ ተቋም ዓመታዊ ዕቅዱን ለማሳካት እያንዳንዱን ሥራ በሚገባ አቅዶ መንቀሳቀስ ይገባዋል፤ ከዚህ
ውስጥ የግዥ እቅድ ትልቁና ዋነኛው ነው፡፡ ግዥን አቅዶ መንቀሳቀስ የአፈጻጸም ክትትልና ግምገማን
ለማከናወን፣ ለግዥው የተመደበውን በጀት የግዥ ሥርዓት ተጠብቆ በወቅቱና በአግባቡ በሥራ ላይ
ለማዋል፣ የቁጥቁጥና የአስቸኳይ ግዥን ለመከላከል እንዲሁም የጨረታ ውድድር አድማስን በማስፋት
ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያለው አገልግሎት በተመጣጣኝ ዋጋ ለማግኘት ያስችላል፡፡

25
ባንጻሩ ግዥን ሳያቅዱ መንቀሳቀስ ለበርካታ ብልሹ አሰራርና ሙስና ሊያጋጥ ይችላል፡፡በተለይ በበጀት ዓመቱ
መጨረሻ የሚደረጉ አስቸኳይ ግዥዎች ለሙስና የመጋለጥ እድላቸው በጣም ሰፊ ነው፡፡ በተለይ በዚህ ጊዜ
የሚደረጉ የሂሳብ ዝውውሮች ተገቢው ቁጥጥር አይደረግባቸውም ፡፡ ምክንያቱም ያልተጠቀምንባቸው
ገንዘቦች እንዳይቃጠሉ በሚል ሰበብ ህግን (ደንብን) ያልተከተለ ወይም ከግልጽ ጨረታ ውጭ አስቸኳይ ግዥ
ይፈጸማል፡፡ ይህ አጋጣሚ ደግሞ ለሙስና በር የሚከፍትበትን ሁኔታ ያመቻቻል፡፡
8.4. በተፈጥሮ አደጋዎች፤ በወረርሽኝናና በሌሎች ጉዳዮች አስቸኳያ ምላሽ በሚሰጥበት ጊዜ
በተፈጥሮ አደጋ የተጎዱ ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም በርካታ ገንዘብና ሎጂስቲኮች ከማስፈለጉ ባሻገር
ስራው አስቸኳይ መሆኑ በራሱ ለሙስና ተጋላጭ ያደርገዋል፡፡ እንዲሁም በዚህ ጊዜ የሚፈጸሙ ግዥዎች
በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ስለሚፈጸሙ ሙስናን ለመፈጸም አመቺ የሚሆኑ በርካታ አጋጣሚዎች
ይፈጥራሉ፡፡
8.5. በጤናዉ ዘርፍ የሚታይ ዉስብስብነት፡
በአገልግሎቱ ዙሪያ ያለዉ (ማን ይታመማል? መቸ? ምን ይፈልጋሉ? የሚለዉ አለመታወቅ (uncertainty))፣መለትም
በዘርፉ ዉስጥ የሚገኙ በተለያየ አቅጣጫ የሚሄዱ ፍላጎቶችን ለመለየትና ለመቆጣጠር አስቸጋሪ መሆን ፡፡
የተሳታፊ አካላት መብዛት፣እጅግ የተበታተኑ ተሳታፊዎች (ለምሳሌ ከፋዮች፣ ተቆጣጣሪዎች፣ አቅራቢዎች፣ ተጠቃሚዎች)
የተወሳሰበ ግንኙነት፣ በተለያዩ ተሳታፊዎች ዉስጥ ያለ መረጃ የማግኘትና የእዉቀት ልዩነት፣ የመድሃኒት አቅራቢዎች፣
የጤና አገልግሎት ሰጭዎችና አመራሮች ግንኙነት ዉስብስብ መሆን፣የመድሃኒት ዋጋ ለመቆጣጠር የሚያስችል የህግ
ማእቀፍ አለመኖር፣
8.6. ከፍተኛ በጀት መመደብ፡
የሃብት ስርጭቱ እስከታች ድረስ የሚወርድና ለቁጥጥር የማያመች መሆን፣ የግል አቅራቢዎችና አገልግሎት ሰጭዎች
መንግስታዊ ሚና እንዲጫወቱ የተደረገ መሆኑ ለሙስና ተጋልጧል፣ የበጀት ምንጩ በርካታ መሆኑ ችግሩን
አባብሶታል፡፡
8.7. ስፔስፊኬሽን ወይም ተርምስ ኦፍ ሪፈረንስ በጥራትና በብቃት አለማዘጋጀት
ማንኛውም ግዥ ራሱን የቻለ መስፈርት ላይ ተመስርቶ እንዲገዛ የተፈለገው እቃ፣ አገልግሎት…ወዘተ
በዝርዝር ሊቀመጥና መመዘኛ ሊወጣለት ይገባል፡፡ መመዘኛውንም ለማውጣት ብቃት ያለው የሰው ሀይል
ያስፈልጋል፡፡ ይሁን እንጂ የጤና ተቋማት የመድሃኒት ፍላጎታቸውን በአግባቡ ተንትነው የግዥ ጥያቄ
አያቀርቡም፣ በዚህ ጊዜ የሚፈለገው ግዥ ለሚፈለገው ዓላማ በሚውልበት ወይም ስራው በሚጀመርበት
ጊዜ አላስፈላጊ ውጣ ውረዶች እንዲኖሩ ከማድረግ ባሻገር ተገቢ ያልሆኑ አሰራሮች እንዲያቆጠቁጡ
ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡
ባንጻሩ ደረጃቸውን የጠበቁ ሰነዶችን አለመጠቀም ውሳኔዎችን እንደፈለጉ በማዛባት ለሙስና መከሰት አመቺ
ሁኔታዎችን (በር) ይከፍታሉ፡፡
8.8. ፖለቲካዊ ተጽእኖ

26
በጨረታ ሰነድ ገምጋሚ ኮሚቴዎች ላይ የማይገባ ፖለቲካዊ፣ ዲፕሎማሲያዊ/ማግባቢያ/ ወይም የኃይል
እርምጃ በመጠቀም ጫና መፍጠር ለብልሹ አሰራርና ለሙስና በር ሊከፍት ይችላል፡፡
8.9. ረዥም የግዥ ሂደት
ረዥም የግዥ ሂደቶች አላስፈላጊ መጓተቶችና ማነቆዎች እንዲከሰቱ በማድረግ የማቀላጠፊያ ክፍያዎች
(Facilitation Payment) እንዲፈጠሩና እንዲስፋፉ በማድረግ የግዥ ስርዓቱን ለሙስናና ብልሹ አሰራር
እንዲጋለጥ ያደርጉታል፡፡በመድሃኒት ፈንድና አቅርቦት ኤጀንሲ በኩልም የግዥ ስርአቱ የተራዘመ ጊዜ
መውሰዱ፤የመድሃኒት ክምችትና ስርጭት ስራውም በሚጠበቀው ደረጃ እንዳይደርስ አድርጓል፡፡
9. በጤና ዘርፉ በግዥና ፋይናንስ አስተዳደር ላይ የሚፈጸም ሙስና የሚያስከትለው ጉዳት
9.2. በበጀት ላይ የሚያስከትለው ተጽእኖ (Financial Impact)
በበጀት ላይ የሚደርሰው ጉዳት የሚከተሉትን ሊያጠቃልል ይችላል፡፡
 ለአገልግሎት ወይም ለኢንቨስትመንት የተጋነነ ዋጋ (ገንዘብ) ሊፈስበት ይችላል፡፡በጨረታ ተገዝተዉ የሚላኩ
መድሃኒቶች ዋጋቸዉ እጅግ የተጋነነ መሆን
 ከስፔስፍኬሽን በታች የሚቀርቡ ማቴርያሎች፣ ስራዎች፣ ፍትሃዊ ያልሆነ የገንዘብ ክፍያ ይፈጸምባቸዋል፡፡

 መንግስት አስፈላጊ ባልሆኑ ግዥዎች ላይ ወይም በኢኮኖሚ አዋጭ ባልሆኑ ግዥዎች ላይ ገንዘቡን
እንዲያፈስ ይገደዳል፡፡
 መንግስት በሙስና የተሰሩ ግንባታዎችና የህክምና መሳሪያዎች የአገልግሎት ዘመናቸውን ሳይጨርሱ
ለእድሳት ስለሚዳረጉ ለአለአግባብ ወጪ ይዳረጋል፡፡ይህም በግዥ ላይ የሚፈጸመዉ ሙስና በገንዘብ ላይ
የሚያሳርፈውን ተጽእኖ የሚያመላክት ነው፡፡
9.3. በኢኮኖሚ ላይ የሚያደርሰው ተጽእኖ (Economic impact)
የሚገዙ የህክና ቁሳቁሶች ጥራት ደረጃቸዉ የወረደ በመሆኑ አገልግሎት ሳይሰጡ በቀላሉ መበላሸት፣ ለወረዳ የሚመደቡ
መድሃኒቶች ከተማ ላይ በድብቅ የሚከማቹና በህገወጥ የሚሸጡ፣ዉድ የሆኑ መድሃኒቶች በየቦታዉ በስፋት መዘረፍ፣
ወጥተዉ መሸጥ፣ያልተጠናቀቁና ደረጃቸዉን ያልጠበቁ ግንባታዎች መረከብ የሃገር ኢኮኖሚ እንዲቀጭጭ በማድረግ
ደሀው ህብረተሰብ ከልማት፣ ከመንግስታዊ አገልግሎቶች …ወዘተ ተጠቃሚ እንዳይሆን ምክንያት ይሆናል ፡፡
9.4. በአካባቢ ላይ የሚያደርሰው ተጽእኖ (environmental Impact)
በግዥ ላይ በሚፈጸም ሙስና ምክንያት የሃገሪቱ ወይም የአለም አቀፍ የአካባቢ ደህንነት መመዘኛዎችን
ሳያሟሉ የፕሮጄክቶች ፣ኢንቨስትመንቶች ግዥዎች የሚፈጸሙበት ሁኔታ ሊፈጠር ይችላል፡፡ በዚህ
ምክንያትም በአካባቢ ላይ ብሎም በረጅም ጊዜ የሰዎች ጤንነት ላይ አደጋ እንዲደርስ ምክንያት ይሆናል፡፡
9.5. በጤንነትና በሰው ልጅ ደህንነት ላይ የሚያደርሰው ተጽእኖ
በግዥ ላይ በሚፈጸም ሙስና ምክንያት በሚፈጠረው የጥራት መጓደል በህብረተሰብ ጤንነት ላይ አደጋ
የሚያስከትሉ ሁኔታዎች ሊፈጠሩ ይችላል፡፡ እንዲሁም ጥራታቸው የተጓደሉ ግንባታዎች (ድልድዮች፣

27
ህንጻዎች፣ ግድቦች…) ድንገት ፈርሰው ለህዝብ እልቂት ምክንያትም ሊሆኑ ይችላል፡፡ህገወጥ መድሃኒት
ንግድ መበራከት፣ እንዲሁም የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፈባቸው መድሐኒቶች፣ ምግቦች እንዲሁም
የህክምና መሳሪያዎች ተገዝተው በህዝብ ጤንነት ላይ ጉዳት ሊያስከትሉ የሚችሉበት ሁኔታ እንዲፈጠር
ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡
ለምሳሌ በቅርቡ በሪፖርተር ጋዜጣ የህዳር 11 ቀን 2009 እትሙ ባወጣው ጽሁፍ ላይ እንደተገለጸው
ካለፉት ሁለት አመታት ወዲህ የኤችአይቨ ኤድስ መመርመሪያ ኪት ግዥ ሂደት ከአገሪቱ ድንጋጌዎች ውጭ
እየሆኑ ነው በሚል ብዙ ትችቶች ሲሰነዘሩ ቆይተዋል፡፡ፀረ ሙስና ኮሚሺን የጨረታ ሂደቶቹ ላይ ምርመራ
አድርጎ ችግሩ መኖሩን እስከማረጋገጥ ደርሷል፡፡ሰለዚህ እነዚህ መሳሪያዎች ደረጃቸውን የጠበቁ
ስለመሆናቸው ቀድሞ ሳይመዘን መግባቱ የሚያስከትለው ጉዳት ከፍተኛ ነው፡፡ጨረታው በዚህ መንገድ
ለምን ተፈፀመ ተብሎ ለተጠየቀው ጥያቄ ሲመልሱ ምርቶቹ ከገቡ በኋላ የጥራት ደረጃቸው ተለክቶ
ለተጠቃሚው ይሰራጭ የሚል ነው፡፡ምርቱ አገር ውስጥ ከገባ በኋላ ከደረጃ በታች ከሆነ ምን ሊደረግ ነው?
በሚሊዮን የሚቆጠር የአገር ሃብት ሊባክን ወይስ የተገዛው ምርት ከደረጃ በታች መሆኑ እየታወቀ ሊሰራጭ
ነው?
የጤና ዘርፍ ሙስና አንዱ ትልቁ ጉዳት የሃሰትና የተጭበረበሩ መድሃኒቶች አገልግሎት ላይ መዋል ሲሆን እንደ ማላሪያ፣
ቲቪ፣ ኤች አይቪ በሽታዎች መድሃኒትን የሚቋቋሙ ይሆናሉ፡፡ በጤና ዘርፍ ሙስና ይበልጥ የሚጎዱት ድሆች፣ ህጻናትና
ሴቶች ሲሆኑ በመንግስት የጤና ተቋማት ተኮልኩለዉ ወረፋ ሲጠብቁ ይታያሉ፡፡
እንደዚሁም በኤች አይቪ ኤድስ ላይ የሚካሄደዉን ዘመቻ አደጋ ላይ ይጥላል፡፡ ኤድስን ለመግታት የሚደረገዉን
አለማቀፋዊ ጥረት ያደናቅፋል፣ ለበሽታዉ ተጠቂዎች የሚመደበዉ በጀት በጥቂት ዘራፊዎች እጅ ይገባል፡፡
ሙስና ጥራትና ደረጃዉን የጠበቅ የህክምና አገልግሎት እንዳይኖር በማድረግ፣ በጀት ጉድለት በመፍጠር፣ የህክምና
ወጭን በማጋነን፣ የአገልግሎት አሰጣጡን በማዉረድ፣ መድሃኒት የሚቋቋሙ ተዋህስያን እንዲበዙ በማድረግ ለአደገኛ
በሽታዎች መስፋፋት ምክንያት ይሆናል፡፡
በጨረታ ተገዝተዉ የሚላኩ መድሃኒቶች ደረጃቸዉ የወረደ፣ የሚገዙ የህክማ ቁሳቁሶች ጥራት ደረጃቸዉ የወረደ
በመሆኑ አገልግሎት ሳይሰጡ በቀላሉ መበላሸት፣ ለወረዳ የሚመደቡ መድሃኒቶች ከተማ ላይ በድብቅ የሚከማቹ፣
ጊዜ ያለፈባቸዉና ጉዳት የሚያደርሱ መድሃኒቶች በብዛት መሸጥ፣ ለወሊድ አገልግሎት የመጡ አንቡላንሶች የህዝብ
ትራንስፖርት መገልገያ ሆነዉ የግለሰቦች መጠቀሚያ መሆን፣ ዉድ የሆኑ መድሃኒቶች በየቦታዉ በስፋት መዘረፍ፣
ወጥተዉ መሸጥ በጥቅሉ መንግስት በጤናው ዘርፍ የሚያደርገውን ጥረት አደጋ ላይ ይጥላሉ፡፡
9.6. በህብረተሰቡ ዘንድ ተቀባይነት ያገኙ እሴቶች ላይ የሚያስከትለው ተጽእኖ
ሰዎች በጤናው ዘርፍ ባሉ ሠራተኞችና ሃላፊዎች እንዲሁም በግሉ የንግድ ማህበረሰብ ላይ ቅንነት ሲያጣ፣
እንዲሁም በግዥ ስርዓት ውስጥ የሚፈጸሙ ሙስናዎች ሃይ ባይ ሲያጡ አስቀድመው የተገነቡ የህብረተሰብ
የቅንነት እሴቶች እየተሸረሸሩ ይሄዳሉ፡፡
9.7. ህብረተሰቡ በመንግስት ላይ ያለው አመኔታ ላይ የሚያስከትለው ተጽእኖ

28
በመንግስት ግዥ ላይ ሃላፊነት ያላቸው ሰዎች በሙስና የሚዘፈቁና የማይቀጡ ከሆኑ፣ ህዝብ በመንግስት ላይ
ያለው አመኔታ እየተዳከመ ይመጣል፡፡ መንግስት የማይታመን ነው ወደሚል ማጠቃለያ እንዲደርሱ ምክንያት
ይሆናል፤ በመጨረሻም ስርዓተ አልበኝነት እንዲነግስ ምክንያት ይሆናል፡፡
9.8. በሃቀኛ የገበያ ተፎካካሪዎች ላይ የሚያስከትለው ተጽእኖ
ሙሰኛ ተጫራቾች ማእቀብ ካልተደረገባቸውና ሁሌም አሸናፊ ከሆኑ በጥራት፣ በአዳዲስ ፈጠራና
በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ ኢኮኖሚውን ሊደግፉ የሚችሉ ታማኝ ተፎካካሪዎች ከገበያ እየወጡ እንዲሄዱ
ምክንያት ይሆናል፡፡
ሙስና ተፎካካሪነትን ስለሚቀንስ የፈጠራ ስራ እንዲዳከም ምክንያት ይሆናል፡፡ በሙስና የሚተማመኑ
አቅራቢዎች ሃብታቸውን በፈጠራ ላይ በማዋል የተሻለ ነገር ይዞ ከመቅረብ ይልቅ የተለመደውን እቃ ወይም
አገልግሎት ይዘው መቅረብን ይመርጣሉ፤
9.9. በግልና በቤተሰብ የሚደርስ ጉዳት
አንድ ሰው በሙስና ወንጀል ተጠርጥሮ ሲፈረድበት በእሱና በቤተሰቡ ላይ ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም
ስነልቦናዊ ጉዳት ይደርሳል፡፡ ሰዎች ከሚወዱት ቤተሰብ ይለያሉ፣ ከስራ ገበታቸው ይፈናቀላሉ፤ በዚህ
ምክንያትም የቤተሰብ ኢኮኖሚ ይናጋል፤ ልጆች ትምህርት ቤት ሊያቋርጡ ይችላሉ፤ከሚኖሩበት አካባቢም
በመፈናቀል ማህበራዊ ኪሳራ ውስጥ ሊገቡ ይችላሉ፤ በሙስና መያዙ በራሱም በግለሰቡ እና በቤተሰቡ ላይ
የሚያደርሰው ስነ ልቡናዊ ጉዳት ቀላል አይደለም፡፡
10. በጤና ዘርፉ በግዥና ፋይናንስ አስተዳደር ላይ የሚፈጸም ሙስናዎችን የመከላከያ ስልቶች
10.1. የጥቅም ግጭትን መቆጣጠር (conflict of interest)
የጥቅም ግጭት ማለት በሰራተኛዉ መንግስታዊ ግዴታና በግል ጥቅም መካከል ግጭት መፈጠር ሲሆን
የሰራተኛዉ የግል ጥቅም (ፍላጎት) የመንግስትን ጥቅም፣ተግባርና ዉሳኔ ተገቢ ባልሆነ ሁኔታ እንዲዛባ
ያደርጋል፡፡
ለምሳሌ የጤና ተቋማት በሚያወጡት ጨረታ ላይ ለመሳተፍ ከሚፈልጉ ግለሰቦች ወይም ድርጅቶች ጋር
በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ መንገድ ግንኙነት ያላቸው ሰራተኞችና የሥራ ሃላፊዎች ይህንን ግንኙነት
በግልጽ እንዲያሳውቁና የውሉ ግዴታ እስከሚጠናቀቅ ድረስ በዚህ የግዥ ሂደት ውስጥ በማንኛውም ደረጃ
ከመሳተፍ ራሳቸውን እንዲያገልሉ ማድረግ፡፡
10.2. የሰራተኛውን የስነምግባር ደረጃ ማሳደግ
  የመስረቅና የስግብግብነት ባህሪን መቆጣጠር፣
 ሳይሰሩ በአቋራጭ የመክበር ፍላጎት የተደላደለና የተንደላቀቀ ሕይወት የመኖር ፍላጐት በጤና ዘርፉ ሰራጠኞች
መቀረፍ ያለበት ችግር ነው፣
 ሰራተኛው እራሱን ከተለያዩ ሱሶች እራስን መከላከል ለምሳሌ ቁማር፣ መጠጥ ወዘተ፣
 ለሌሎች የማሰብና ለሀገር የመቆርቆር ስሜት ማዳበር፣

29
 ህግንና ስርአትን ተከትሎ መስራት፣ የግድ የለሽነት ባህሪያትን ማስወገድ ::
 የግዥና ፋይናንስ አስተዳደር ስርዓት ሂደቱ አመኔታ እንዲጣልበት ማድረግ፣
10.3. የግልጽነት አሰራርን ማስፈን
ግልጽነት ማለት ስለሚሰራው ፕሮጄክት የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ሙሉ መረጃ እንዲደርሳቸው
ማድረግን እንዲሁም ማማከርን የሚጠይቅ ተግባር ነው፡፡ ለምሳሌ፡- ውሃን ከመገደብ ጋር በተያያዘ የሚሰሩ
ስራዎች በስራው ምክንያት ተጎጂ ሊሆኑ ይችሉ ይሆናል ተብለው የሚታሰቡ አካላት ሊማከሩ ይገባል፡፡
ሙስና የሚጠነሰሰው በጨለማ ውሰጥ ነው፤ የሚሳለጠው ደግሞ በድንግዝግዝ ሁኔታ ውስጥ ነው፡፡
የግምገማ ሂደቱና የጨረታው ውጤት ውሳኔ ለህዝቡ ክፍት የሚሆንበትን ሁኔታ ማመቻቸት፣የግምገማ
መመዘኛዎችን ገና ከጅምሩ ማዘጋጀትና ግልጽ ማድረግ፣አስፈላጊ መረጃዎችንም ሆነ ሌሎች ከህብረተሰቡ
የሚነሱ ጥያቄዎችን ምላሽ በመረጃ መረብ ሆነ በሌላ መንገድ ለህብረተሰቡ ተደራሽ ማድረግ፣
በአሁኑ ዘመን መንግስታትና የባለስልጣን መስሪያቤቶች ኢንተርኔትን ለግዢ ሂደት መገልገላቸው የተለመደ ተግባር
ሆኗል፡፡ የዚህ ደግሞ ዋነኛ ዓላማ መረጃዎችን ለሁሉም በማዳረስ ሳያዳሉ ግልጽ በሆነ መንገድ በማወዳደር ገንዘብ
ተገቢውን ዋጋ እንዲያገኝ ማድረግ ነው፡፡የነፃ ህክምና ሥርአትን በተመለከተ ለህዝብ፣ለጤና ድርጅቶችና ጉዳዩ
ለሚመለከታቸው አካላት ሁሉ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ መሰራት ይኖርበታል፡፡ ወቅጣዊ የፋይናንስ
አጠቃቀም ሪፖርቶችን በተናበበ መልኩ በየደረጃዎ ለሚመለከታቸው ማቅረብ፡፡

10.4. ተጠያቂነት ማስፈን


ተጠያቂነት የአንድን ተቋም ታማኝነት የሚያረጋግጥ ከመሆኑም ባሻገር ህገ-ወጥነትንና ሙስናን ለመግታት
ያስችላል፡፡ የስነምግባር ኮሚቴዎችን በማጠናከር የስነምግባር ጉድለት የሚታይባቸውን ጤና ባለሙያዎች
ተገቢውን እርምጃ መውሰድ፣
ሙስና ውስጥ የገቡት ካምፓኒዎችም ሆነ ግለሰቦች ተጠያቂ የሚሆኑበትን ሁኔታ ማመቻቸት ይገባል፡፡
ይህም በሁለት መንገድ ሊገለፅ ይችላል ይሄውም በህገወጥ መንገድ የተገኘ ትርፍ እንዲወረስ ወይም
እንዳይንቀሳቀስ ማድረግ ፡፡ በጉቦ ወይም በሌላ ሙስና ዓይነት የተገኘ ትርፍን እንዲከፈሉ ማድረግ አዋጪ
መከላከያ እንደሆነ ይጠቀሳል፡፡ በሙስና ውስጥ በሚዘፈቁ የመንግስት ተቀጣሪ ሰራተኞች
ተመጣጣኝ(አስተማሪ) የሆነ እርምጃ መውሰድ፡፡
ገለልተኛ በሆነ አካል ለመቆጣጠር የሚያስችል የቁጥጥር ስርዓት መዘርጋት፡፡ ራንደም(ድንገታዊ) የመስክ
ቁጥጥር ማድረግ የውል መቀያየርን ሊያመጡ የሚችሉ ቅድመ ሁኔታዎችን አስቀድሞ መወሰን፡፡ በሁሉም
የጤና ተቋማት ኦዲቲንግ ኢንስፔክሽን ማካሄድና መስፈርቱን በማያሟሉ አስፈላጊውን እርምጃ
መውሰድ፡፡ ከህብረተሰብ የሚመጡ ጥቆማዎች ፈጣን ምላሽ በማይሰጡ አካላት ተገቢውን እርምጃ
መውሰድ፣የውስጥ ኦዲት ስራዎችን ማጠናከር፣
10.5. አለማዳላት፣ ቁጠባ እና ውጤታማነት

30
የህዝብ ሃብት ጥቂት ግለሰቦችን ወይም ኩባንያዎችን ብቻ እንዲጠቅም መደረግ የለበትም፡፡ ሁሉም
በተዘጋጀ መስፈርት፣ በተወሰነ የጊዜ ገደብ፣ ተመሳሳይ መረጃዎችን በማግኘት ፍትሃዊ በሆነ መንገድ
ተስተናግደው መወዳደር አለባቸው፡፡ለምሳሌ የጨረታ አሸናፊን የመለየቱ ተግባር ከአድልዎ ነጻ መሆንን
ይመለከታል፡፡
ቁጠባዊ (ኢኮኖሚያዊ) ግዢ ሲባል ግዢው ለወጣበት ገንዘብ ጥራት ያለው እቃን ወይም አገልግሎትን
ማስገኘቱን ይመለከታል፡፡ በሌላ መንገድ በአነስተኛ ዋጋ ተቀባይነት ያለው (የሚፈለገውን የጥራት ደረጃ
የያዘ) እቃ ወይም አገልግሎት ማስገኘቱን ያመለክታል፡፡ ይህ ማለት ግን ዝቅተኛ ዋጋ ያላቸው እቃዎች
ወይም ግዢዎች ይፈጸሙ ወይም እጅግ በጣም ፍጹም የሆነ ጥራት ያለው እቃ ወይም አገልግሎት ይገዛ
ማለት ሳይሆን፣ ሁለቱንም በማጣጣም አንድን የግዥ ፍላጎት ሊያረካ የሚችል ግዢ ይፈጸም ማለት ነው፡፡
የግዢ ሂደት ወጤታማ እና ቀልጣፋ መሆን አለበት፡፡ አነስተኛ ዋጋ ለሚያወጡ ግዢዎች በፍጥነትና በቀላሉ
ግዢ ሊካሄድባቸው የሚያስችሉ ደንቦችና መመሪያዎች ያስፈልጋሉ፡፡ ይሁን እንጂ ለፍጥነት ሲባል ብቻ
በምንም ዓይነት ሁኔታ የቅንነት፣ የግልጽነትና የተጠያቂነት መርሆዎች ድርድር ውስጥ የሚገቡ ጉዳዮች
አይደሉም፡፡
ነገር ግን የግዢ ዋጋ እና ውስብስብነት እየጨመረ በመጣ ቁጥር የግዢ መርሆችን ለመጠበቅ(ለማረጋገጥ)
ሰፋ ያለ ጊዜ እና ጠለቅ ያለ መመሪያና ደንብ ያስፈልጋል፡፡ ለትልልቅ ግዢዎችም እንዲሁ ከብዙ ሰዎች
የተዋቀሩ ኮሚቴዎች ሊያስፈልጉ ይችላል፤ ይሁን እንጂ ውጤታማ ግዢን ለማከናወን የተንዛዙ
ቢሮክራሲዎች መቀነስ አለባቸው፡፡
10.6. የህጎችን ተግባራዊነት ክትትል ማድረግ
የትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል የሙስና አደጋ ሊያስከትሉ የሚችሉ ሁኔታዎችን በተመለከተ በ9 አገሮች
ላይ ባደረገው ጥናት ውስጥ ጥናቱ ከተጠቀመባቸው መስፈርቶች መካከል የህጎች ግልጽ አለመሆን፣ በህጎች
ውስጥ የሚታዩት የግልጽነት አሰራር አለመኖር የሚሉት መለኪያዎች ሲሆኑ፣ በእነዚህ መስፈርቶች
መሠረትም 35% የሙስና አደጋ የሚያስከትሉ ሆነው ሲገኙ፤ የህጎች ተግባራዊ አለመሆን ሙስና
የማስከተል አደጋ ደግሞ ወደ 65% እንደሚደርስ ተመልክቷል፡፡ የግዥ መመሪያን መሰረት ያደረገ ግዥ
ማከናዎን፡፡ግዥዎች በዕቅድ እንዲመሩ ማድረግ፡፡የጨረታ ሥራዎችን በወቅቱ እንዲከናዎኑ ማድረግ፡፡
10.7. ሰፊ የመወሰን ስልጣን (Discretionary power) መቆጣጠር
በፍላጎት ዳሰሳ፣ ጨረታ ዝግጅት፣ ምርጫ፣ውል እንዲሁም ሱፐርቪዥንና ቁጥጥሮች በተመለከተ
ለሚከናወኑ ቁልፍ ተግባራት ተለይተዉ ለተለያዩ ሰዎች ሃላፊነት የሚሰጥበት መንገድ መኖሩን ማረጋገጥ፣
ግዢን አስመልክቶ ተገቢውን አደረጃጀት መጠበቅ፤ ለምሳሌ፣ የግዢ ኮሚቴዎች ማደራጀት፣ ለሙስና
ለመጋለጥ ሰፊ እድል ያላቸው ወይም ስሱ(sensitive) በሆኑ ወሳኔ ሰጪ ቦታዎች ላይ
ሰራተኞችን(ስታፎችን) እያዘዋወሩ ማሰራት፤ በግዢ ሂደት ውስጥ የሚሳተፉ ሰራተኞች ባግባቡ የሰለጠኑ
መሆናቸውንና ለሚሰሩት ስራ ተመጣጣኝ ክፍያ (ሪዋርድ) ማግኘታቸውን ማረጋገጥ ይገባል፡፡

31
በግዥ ስራ ውስጥ የሚሰሩ ስራዎች ተለይተው ለተወሰኑ ክፍሎች የተሰጡ ሊሆኑ ይገባል፡፡ የግዢ
(የኢንቨስትመንት) ፍላጎቶች፣ ዝግጅት፣ መረጣ፣ ትግበራና ክትትል በተለያዩ ሰዎች (ቡድኖች) የሚፈጸሙ
መሆን አለባቸው፡፡ የጨረታ ግምገማ የሚሰሩትና አሸናፊን ወስነው የሚያሳውቁትን ሰዎች የተለያዩ
ማድረግ፣አሸናፊ ማን እንደሆነ የሚወስነው ሰው እና ጨረታውን የሚገመግመው ሰው የተለያዩ እንዲሆኑ
ማድረግ፣አሸናፊን የማሳወቅ ስራ ከአንድ ሰው ይልቅ በብዙዎች እንዲወሰን ማድረግ፣ሰራተኞች ተገቢ
ያልሆነ ግንኙነት እንዳያጎለብቱ እያዘዋወሩ ማሰራት፤ ወሳኝ የሆኑ ውሳኔዎች በአንድ ሃላፊ ብቻ ከሚሰጥ
በኮሚቴ የሚወሰንበት ሁኔታን መፍጠር ለመከላከል ጉልህ ድርሻ ይኖረዋል፡፡
10.8. ሙስናን መከላከል
ግልጽ የሆኑ የሥነ-ምግባር ደንቦች
በመንግስት ተቋማት፣ በግሉ ሴክተር ባሉ ደርጅቶች ውስጥ በሰራተኞች ተሳትፎ የተዘጋጀ ፣ ለተግባራዊነቱ
የከፍተኛ ሃላፊዎች የሚኖሩበትና አርአያነታቸውንም የሚያሳዩበት እንዲሁም ሁሉም ስታፎች
የሚያውቁትና የሚተገብሩት የሥነምግባር ደንብ ማዘጋጀት ይገባል፡፡
o የሥነምግባር ደንቡ ቅንነትና መልካም ባህርያት እንዲሰፍኑ ቁርጠኝነት ላይ መሰረት ያደረገ
ሊሆን ይገባዋል፡፡
o በደንቡ ውስጥ ሙስና ግልጽ አጀንዳ ሆኖ ሊቀርብ ይገባዋል፡፡
o ስጦታዎችን፣ ግብዣዎችንና ውለታዎችን አስመልክቶ ግልጽ መመሪያዎች ሊሰፍሩ ይገባል፡፡
o የዝምድና አሰራርን( Nepotism) አስመልክቶ ክልከላ የሚደረግባቸውን አሰራሮች በግልጽ
ማስቀመጥ ይገባል፡፡
o የሰራተኞችን ቁርጠኝነት ለማደስና ለማበረታታት በደንቡ ላይ ለሰራተኞች ቋሚ የሆነ
የተሃድሶ ስልጠና ማዘጋጀት፤
o በሚፈጸሙ የሥነምግባር መተላለፎች ላይ ግልጽ የሆኑ ርምጃዎች የሚወሰዱባቸው መርሆች
ሊገለጹ ይገባል፤
 የዋጋ ንጽጽር
በጨለማ የሚፈጸመውን የሙስና ተግባር ወደ ብርሃን በማውጣትና በማጋለጥ ረገድ ውጤታማ ከሆኑ
ተግባራት መካከል የዋጋ ንጽጽሮችን እያተሙ ማሰራጨት ዋነኛው ነው፡፡ይህ ተግባር በመንግስት የግዢ
ኤጀንሲዎች ወይም በሲቪል ማህበራት ሊከናወን ይችላል፡፡
 በመንግስት ተቋማት ውስጥ የስጋት ትንተና ማካሄድ
ተቋማት የሙስና ወንጀል ከመከሰቱ በፊት ለሙስና ሊያጋልጡ የሚችሉ አሰራሮችን በመፈተሸ የመከላከያ
እርምጃ እንዲወሰድባቸው ማድረግ አንዱ ሙስናን የመከላከያ መሳሪያ ነው፡፡ ለምሳሌ፡ በፌዴራል
ሥ/ፀ/ሙ/ኮሚሽን የሙስና መከላከል ዳይሬክቶሬት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመተባበር ሙስናና
ብልሹ አሰራርን አስቀድሞ በመከላከል ተግባር ላይ የተሰማራ ነው፡፡ ይህን ሃላፊነቱን ለመወጣት የተለያዩ

32
የመንግስት መስሪያ ቤቶችንና የልማት ድርጅቶችን የአሰራር ስርዓቶች በማጥናትና በመፈተሽ ለሙስናና
ለብልሹ አሰራር በር የሚከፍቱ አሰራሮች የሚወገዱበትን መንገድ ማመላከት እንዲሁም አሰራሮቹ
እንዲሻሻሉ እገዛና ክትትል ማድረግ ዋና ዋና ተግባሮቹ ናቸው፡፡
 የመንግስት ሃላፊዎችን እያዘዋወሩ የማሰራት
ሙስናን ለመከላከል በማሌዥያ በርካታ ጥረቶች ተካሂደዋል፡፡ የመንግስት ሃላፊዎችን እያዘዋወሩ የማሰራት
(job rotation) ስርኣት/ስልት ተዘርግቷል፡፡
 የአብክመ ስ/ፀ/ሙ/ኮሚሽን ከህብረተሰቡ በሚቀርቡለት ጥቆማዎች መሰረት በሂደት ላይ ያሉ
ጉዳዮችን አስቸኳይ ጥናት በማካሄድ ችግር ያለባቸው ሲገኙ እንዲታገዱና እንደገና እንዲታዩ ያደርጋል፡፡
ለምሳሌ በ2007 በጀት ዓመት በአስቸኳይ የአሰራር ሂደት ምርመራ ተካሂዶ በርካታ ጥቆማዎች ትክክል
ሆነው በመገኘታቸው እንዲታገዱ ወይም እንዲሰረዙ ከተደረጉ ጨረታዎች መካከል፡-
 ትምህርት ቢሮ ለግንባታ ባወጣው ጨረታ ላይ ጨረታን የማፈን ችግር መኖሩን ተከትሎ
በተሰራ ስራ 89,941,476.00 ብር ለመከላከል ተችሏል፡፡
 የጤና ቢሮ 6 ሆስፒታሎችን ለማስገንባት ባወጣው ጨረታ ላይ ጨረታን የማፈን ችግር
መኖሩን ተከትሎ በተሰራ ስራ 46,574,211 ብር ለመከላከል
ተችሏል፣(የአበክመ/ሥ/ፀ/ሙ/ኮሚሽን የ2007 በጀት ዓመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት የተወሰደ፣
ሃምሌ 2007)
 የጤና ፋይናንስ አሰራሮችን ማሻሻል
 የፋይናንስ አሰራሮችን ሙሉ ለሙሉ በቴክኖሎጅ የተደገፉ በማድረግ መተግበር፣
 የአደረጃጀት ችግሮችን በየጊዜው እየፈተሹ የማስተካከያ ስራዎችን ማከናዎን፣
 የመድሃኒት ምዝገባ ዳታቤዝን በአስቸኳይ ስራ እንዲጀምር ማድረግ
10.9. የምሃበረሰቡን ተሳትፎ ማሳደግ
የሙስና አንዱ ባህርይ በሚስጥር መፈጸሙ ነው፡፡ሰጪም ሆነ ተቀባይ በሙስና ወንጀል ተጠያቂዎች
እንደመሆናቸው መረጃዎች ሶስተኛ ወገን ዘንድ እንዳይደርሱጥንቃቄ ያደርጋሉ፡፡ በመሆኑም ምናልባት
ሙስና መፈጸሙን ሊያውቁ የሚችሉ የሙሰኛው የስራ ባልደረቦችና ተፎካካሪ ተጫራቾች ናቸው፡፡
አብዛኞቹ ግን የሙስና ድርጊት መፈጸሙን ለመጠቆም ቸልተኛ ሲሆኑ ይስተዋላል፡፡ስለዚህ ጥቆማ ዋነኛ
የሙስና ወንጀል መረጃ ምንጭ እንደመሆኑ መሃበረሰቡን ጥቆማ ኢንዲሰጥ ማድረግ ተገቢ ነው፡፡የህዝብ
ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን ስራዎችን ማጠናከር፡፡
10.10. በንብረት አወጋገድ ላይ የሚጋጥምን ሙስና ለመቀነስ መወሰድ የሚገባቸው ጥንቃቄዎች፡-
 የሚወገዱ ንብረቶች በየጊዜው የውስጥ ኦዲት እንዲደረግባቸው ማድረግ፤

33
 እቃዎች(ንብረቶች) በሚገዙበት ጊዜ ስለእቃዎቹ ዝርዝር መረጃዎችን መያዝ( የቆይታ ጊዜ፣
የተደረገ ጥገና…ወዘተ) ይህን ማድረግ እቃዎችን ለማስወገድ በሚደረግ ግምገማ ላይ ጠቃሚ
መረጃዎች ሆነው ያገለግላሉ፤
 እቃን በማስወገድ ተግባር ውስጥ ያሉትን እያንዳንዱን ሂደት በጥንቃቄ መከታተል (ለምሳሌ፡-
የንብረት የማስወገድ ውሳኔን፣ የሚወገዱ እቃዎች(ንብረቶች) ግምገማ(evaluation)፣ የሚወገዱ
እቃዎች(ንብረቶች) እንዲወገዱ ያጸደቀው ማን እንደሆነ፣ የአወጋገዱ ዘዴ(ለምሳሌ ግልጽ ጨረታ፣
በቀጥታ ሽያጭ….)
10.11. የሰራተኞችን አቅም ማሳደግ
 ተከታታይነት ያለው የአመለካከት ለውጥ የሚያመጡ ስልጠናዎች በመስጠት የአፈፃጸም አቅምን
መጨመር፣
 ለፋይናንስ ባለሙያዎች፣ለገንዘብ ሰብሳቢዎች ተከታታይነት ያለው የስራ ላይ ስልጠና መስጠት
 የሰለጠነ የፋይናንስ ባለሙያ መመደብ
 ለገንዘብ ሰብሳቢዎች ማበረታቻ መስጠት
የሞጁሉ ማጠቃለያ ጥያቄዎች
I. ሙስና ማለት ምን ማለት ነው ከክራይ ሰብሳቢነት ጋር ያለው አንድነትና ልዩነት እንዴት ይገለፃል?
II. ሙስናን በአይነት ከፋፍላቹህ አስቀምጡ ሙስናን በአይነት ከፍሎ ማስቀመጥ ለምን ይጠቅማል?
III. ቀጥሎ የቀረቡትን ጥያቄዎች አስተውላችሁ አንብቡና መልሶቻችሁን ስጡ፡፡
ሀ. አምስት የመንግስት ዋና ዋና የግዥ ዓይነቶች እነማን ናቸው?
ለ. በግዢ ስርዓት ውስጥ ዋና ዋና የሙስና መገለጫዎችን አስረዱ፡፡
ሐ. በጤናው ዘርፍ የፋይናንስ አስተዳደርና ግዥ ላይ የሚፈጸም ሙስና የሚያስከትለውን ጉዳት ግለጹ፡፡
መ. በጤናው ዘርፍ የፋይናንስ አስተዳደርና ግዥ ላይ የሚፈጸም ሙስና ውስጥ የሚፈጸሙ የሙስና
ወንጀሎች መከላከያ ስልቶችን ዘርዝሩ፡፡
ሠ. ሙስናና በመከላከሉ ሂደት የመገናኛ ብዙሃን ድርሻ ምን ሊሆን ይችላል?
II. የፌ/ሥ/ፀ/ሙ/ኮ የሙስና መከላከል ዳይሬክቶሬት የሙስናና ብልሹ አሰራር ስጋቶችን ለመከላከል የካቲት
2003ዓ.ም ዘውዲቱ መታሰቢያ ሆስፒታል የሕንጻ ጥገና ሥራዎች የአገልግሎት ግዥ የስራ ሂደት
አሰራር ስርዓት ላይ በቀረበው የጥናት ሪፖርት ውስጥ የግንባታ ንዑስ ስራ ሂደት ባጋጠመው የጊዜ
እጥረት ምክንያት የቴክኒክ ግምገማ ሳያካሂድ ተጫራቾች ያቀረቡትን ዝቅተኛ ዋጋ ብቻ መሰረት
በማድረግ አሸናፊው እንዲለይ ተደርጓል፡
ሀ. ከላይ በቀረበው ኬዝ ውስጥ የታየው ብልሹ አሰራር በየትኛው የግዥ ኡደት ውስጥ ነው?
ለ. የተከሰተው ክፍተት ለሙስና መከሰት የሚሆንበት ሁኔታ ምንድን ነው?
ሐ. አንተ የመስሪያ ቤቱ የበላይ ሃላፊ ብትሆን ምን ዓይነት እርምጃ ትወስዳለህ?

34
መ. እንዲህ አይነቱ አሰራር የሚያስከትለው ጉዳት ምንድ ነው?
III. በቡድን በመሆን በህክምና ቁሳቁሶችና መድሃኒቶች ግዥ ወቅት በእያንዳንዱ የግዢ ዑደት ውስጥ
ሙሰና ሊፈጠር የሚችልባቸው መንገዶች ላይ ተወያዩባቸው፡፡ (በወይይታችሁ ወቅት በስራ አጋጣሚ
ያገኛችኋቸውን ተሞክሮዎች በማጣቀስ ለመወያየት ሞክሩ)፡፡
ሀ. በግዢ እቅድና ፍላጎት ዳሰሳ ወቅት
ለ. በጨረታ ሰነድ ዝግጅት ሂደት
ሐ. አሸናፊ በሚለይበት ሂደት
መ. ግዥ ተግባራዊ በሚሆንበት ሂደት(ውል ተፈጻሚ በሚሆንበት ወቅት)
ሠ. የሂሳብ ማጣሪያ በሚደረግበት(በክፍያ) ወቅት
ረ. በንብረት አወጋገድ ሂደት
IV. በጤና ዘርፍ የሚታዩ የሙስና አይነቶች በሚከተለው መልኩ ሊከፈሉ ይችላሉ፡፡በእነአዚህ ዋና ዋና የጤና ዘርፍ
ሙስና አይነቶች ጋር የተያያዙ የሙስና መከሰቻ አጋጣሚዎችን አስረዱ፡፡

1. የመድሃኒትና የህክምና ቁሳቁሶች ግዥ ሙስና፣


2. የህክምና ዘርፍ ክፍያዎች ሙስና፣
3. የህክምና መድሃኒቶችና ቁሳቁሶች አቅርቦትና ስርጭት ሙስና
4. የህክምና ፕሮጀክት ግንባታ ሙስና፣

መወያያ ጥያቄዎች
1. ሙስና ማለት ምን ማለት ነው ከክራይ ሰብሳቢነት ጋር ያለው አንድነትና ልዩነት እንዴት ይገለፃል?
2. ሙስናን በአይነት ከፋፍላቹህ አስቀምጡ ሙስናን በአይነት ከፍሎ ማስቀመጥ ለምን ይጠቅማል?
3. በጤና ዘርፍ የሚታዩ የሙስና አይነቶች በሚከተለው መልኩ ሊከፈሉ ይችላሉ፡፡በእነአዚህ ዋና ዋና የጤና
ዘርፍ ሙስና አይነቶች ጋር የተያያዙ የሙስና መከሰቻ አጋጣሚዎችን አስረዱ፡፡

35
I. የመድሃኒትና የህክምና ቁሳቁሶች ግዥ ሙስና፣
II. የህክምና ዘርፍ ክፍያዎች ሙስና፣
III. የህክምና መድሃኒቶችና ቁሳቁሶች አቅርቦትና ስርጭት ሙስና
IV. የህክምና ፕሮጀክት ግንባታ ሙስና፣
4. በጤናው ዘርፍ የፋይናንስ አስተዳደርና ግዥ ላይ የሚፈጸም ሙስና የሚያስከትለውን ጉዳት ግለጹ፡፡
5. በጤናው ዘርፍ የፋይናንስ አስተዳደርና ግዥ ላይ የሚፈጸም ሙስና ውስጥ የሚፈጸሙ የሙስና
ወንጀሎች መከላከያ ስልቶችን ዘርዝሩ፡፡
6. ሙስናና በመከላከሉ ሂደት የመገናኛ ብዙሃን ድርሻ ምን ሊሆን ይችላል?

36

You might also like