Professional Documents
Culture Documents
ለውሳኔ ሰጪዎች
መስከረም 2009
ማውጫ
የቃላት ትርጉም.....................................................................................................................................................II
1. መግቢያ............................................................................................................................................................1
2. ስለ መርሃግብሩ መግለጫ..............................................................................................................................2
2.1 የልማታዊ ሴፍቲ ኔት መርሃግብር (ልሴኔመ) የፖሊሲ አቅጣጫና አላማዎች..................................2
2.2. የልማታዊ ሴፍቲኔት መርሃግብር ስልታዊ ዘዴዎች...........................................................................3
2.3. የልማታዊ ሴፍቲ ኔት መርሀ ግብርመሰረታዊ መመሪያዎች...............................................................4
2.4. መርሃ ግብሩ በተፈጥሮ አካባቢና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እንዳያስከትል
የሚደረጉ ጥንቃቄዎች.........................................................................................................................6
2.5. የልማታዊ ሴፍቲኔት መርሀግብር የዕቅድ አሰራር ሂደት...................................................................7
3. የልማታዊ ሴፍቲኔት መርሀግብር ዝርዝር ፕሮግራሞች................................................................................8
4. ለውሳኔ ሰጪዎች ትኩረትን የሚሹ ጉዳዮች................................................................................................10
4.1. የመረሃግብሩ አገባብና አወጣጥ፣ መሰረታዊ መመሪያዎች፣ ሀላፊነቶችና ግዴታዎች......................10
4.2. የክፍያ አፍጻጸም መሠረታዊ መመሪያዎች.........................................................................................13
4.3. የግዢ ሥርዓቶችና አጀማመራቸው....................................................................................................14
5. የውሣኔ ሠጪዎች ዋና ዋና ሥራዎችና ኃላፊነቶች........................................................................................15
5.1. በበጀት አስተዳደር..............................................................................................................................15
5.2. የልሴኔመ የምግብ አስተዳደር.............................................................................................................18
5.3. በልሴኔመ የቁሳዊ ሐብት አያያዝ ......................................................................................................20
6. በልማታዊ ሴፍቲኔት መርሀግብር ማህበራዊ ተጠያቂነት...........................................................................20
7. የልሴኔመ 4 ከቀደሙት ምዕራፎች ልዩ የሚያደርጉት ዋና ዋና ፈጠራዎች................................................21
8. በልሴኔመ 4 የተሻሉ ዉጤቶችን ለማምጣት መተግበር ያለባቸው ቁልፍ ተግባራት...............................23
8.1. የማስተባበር እቅድ............................................................................................................................23
8.2. የመርሀ ግብሩ ቅንጅትና ተደጋጋፊነቶች...........................................................................................24
8.3. ችግርን የመቋቋምን አቅም መገንባት................................................................................................24
8.4. የመረጃ አያያዝ ዘዴዎች....................................................................................................................25
8.5. የአቅም ግንባታ ስልት.......................................................................................................................26
I
የቃላት ትርጉም
ቅድመ ሁኔታ ሙሉ አካል ያላቸው ጐልማሳ ቤተሰቦች በማህበረሰብ ልማት ውስጥ እንዲሳተፉ
ይጠበቃል ፡፡ ነፍስጡርና ጡት የሚያጠቡ እናቶች የራሳቸውንና የሕፃኑን
ጤንነትና ደህንነት ለመጠበቅ እንዲችሉ ወደ ጊዜያዊ ተጠቃሚነት ይሸጋገራሉ፡፡
በቅድመ ሁኔታ አሠራር ውስጥ ቤተሰብ ስለአለበት ሀላፊነት የሚነገረው ሲሆን
ክትትልም ይደረግበታል፡፡ ነገር ግን በቅጣት አይነት ከሚያገኘው ጥቅም
ምንም አይቀነስበትም ፡፡
ክፍያ ክፍያ የጥሬ ገንዘብ ክፍያንና ወይም በልሴኔመ የሚከፋፈል ምግብ በማህበረሰብ
ልማት ስራ ተሳታፊዎች ውስጥ ወይም ለቀጥታ ቋሚ ተጠቃሚዎች የሚከፈል
ክፍያ ነው፡፡
II
ምህረ ቃላት
III
IV
I. መግቢያ
የልማታዊ ሴፍቲኔት መርሃ ግብር (ልሴኔት/PSNP/) በ1994/95 በኢትዮጵያ ውስጥ የተከሰተውን የድርቅ
አደጋ ተከትሎ በሰብአዊና በንብረት ላይ ያስከተለውን አደጋ መፍትሔ ለመስጠትና ችግሩ በተከሰተ ቁጥርም
የለጋሾችን እርዳታ መጠየቅ ህይወት እንዳይጠፋ ቢከላከልም የደሃውን ንብረት ከመጥፋት አላዳነውም፡
፡ የምግብ ዋስትናንም በኢትዮጵያ ውስጥ ለማረጋገጥ አልቻለም፡፡ ችግሩንም ለመፍታት ከተደረጉ ጥልቅ
ውይይቶች የልማታዊ ሴፍቲኔት መርሃ ግብር ሊጀመር ችሏል፡፡ መርሃ ግብሩ ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ
የቀሰማቸውን ልምዶች በመጠቀም እያደገ አራተኛ ምእራፍ ላይ ይገኛል፡፡
ይህ የልማታዊ ሴፍቲ ኔት መርሃ ግብር በህዝብ ብዛቷ 2ኛ በሆነች ኢትዮጽያ ትልቁ የሴፍቲ ኔት መርሀ ግብር
ሲሆን ብዙ ባለድርሻ አካላትንም ያሳትፋል፡፡ ይህ የአራተኛው ምእራፍ የልማታዊ ሴፍቲ ኔት መርሃ ግብር
አተገባበር መመሪያ ተዘጋጅቶና ተከልሶ የመርሃ ግብሩን መግለጫ፣ በቅደም ተከተል የሚሰሩ ድርጊቶችን፣
በተለያየ ደረጃ ያሉ የባለ ድርሻ አካላትን የስራ ድርሻና ኃላፊነቶችን ይዟል፡፡
የትኛውም የመርሃ ግብሩ ፈፃሚ አካል ኃላፊነቱን በአግባቡ መወጣት እንዲችል የመርሃ ግብሩን አተገባበር
ሙሉ በሙሉ ሊረዳው ይገባል፡፡ ሆኖም ለአያያዝና ለአጠቃቀም እንዲመች በአጭሩ የተዘጋጀ ለታዳሚው
አካል ማዘጋጀት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ፈፃሚ አካላትም በሶስት አይነት ተከፍለዋል፡፡ እነርሱም፡- ውሳኔ
ሰጪ አካላት፣ ባለሙያዎችና በመስክ ላይ የሚገኙ ፈፃሚዎች ናቸው፡፡ ይህም ትንሽ መፅሐፍ በክልል፣ በዞን፣
በወረዳ ደረጃ ለሚገኝ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች (መያድ) ውሳኔ ሰጪዎች እንዲገለገሉበት
የተዘጋጀ ነው፡፡
በዚች መመሪያ ውስጥ ለየልማታዊ ሴፍቲ ኔት መርሃ ግብር የፖሊሲ አቅጣጫዎች፣ በመርሃ ግብሩ የታቀዱ ግብና
ውጤቶች፣ መሰረታዊ መመሪያዎች፣ ውሳኔ ሰጪዎች ፣ በአካባቢያዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ያለተፈለጉና
ጎጂ የሆኑ ውጤቶች እንዳይፈጠሩ ማድረግ ስለሚገባቸው ጥንቃቄዎች፣ የልማታዊ ሴፍቲ ኔት መርሃ ግብር
እንደ አሰራር ስርዓት እና የዕቅድ ሂደቱን ይዟል፡፡ የአተገባበር መመሪያው የመርሃ ግብሩን የተለያዩ ክፍሎችና
እንዴት ከተለያዩ የፖሊሲ አቅጣጫዎች ጋር እንደሚገናኝ ያስረዳል፡፡ ቀጥሎም ውሳኔ ሰጪዎች የመርሃ
ግብሩ ተጠቃሚዎች አመራረጥና እንዴት መመረቅ እንደሚገባቸው፣ የጥቅማ ጥቅም ክፍያን ለተጠቃሚዎች
ማስተላለፍና፣ የግዢ ጣሪያንም ይዟል፡፡ በመመሪያው ውስጥ የውሳኔ ሰጪዎች በገንዘብ፣ በምግብና በሌሎች
ቁሳዊ ሀብቶች ላይ ያላቸው የስራ ድርሻና ኃላፊነቶች ተዘርዝረዋ፡፡ በተጨማሪም በልማታዊ ሴፍቲ ኔት መርሃ
ግብር ውስጥ ስለ ማህበራዊ ተጠያቂነትና ወሳኝ የሆኑ ፈጠራዎች በዚህ በአራተኛ ምዕራፍ ውስጥ ቀድመው
ከነበሩት ምዕራፎች የተሻለ እንዲሆን የሚያደርጉ ክፍሎችንም ይዟል፡፡ የመመሪያው የመጨረሻ ክፍል
የልማታዊ ሴፍቲ ኔት መርሃ ግብር አራተኛ ምዕራፍ ውጤታማ ሊያደርጉት የሚችሉትን ዝርዝር ጉዳዮች
ጠቅለል አድርጎ ያቀርባል፡፡
1
II. ስለ መርሃግብሩ መግለጫ
2
ከላይ በተዘረዘሩት የፖሊሲ ማዕቀፍ ላይ በመመስረት የልማታዊ ሴፍቲ ኔት መርሃ ግብር የሚጠበቀውን
ውጤት እንደሚከተለው አድርጓል፡፡
የመርሃ ግብሩ ግብ
“የምግብ ዋስትና ያልተረጋገጠላቸው የገጠር ቤተሰቦች ከሚገጥሟቸው ችግሮች በፍጥነት
የሚያገግሙ፣ አናኗራቸው የተሻሻለ፣ የምግብ ዋስትናቸውና ሥርዓተ-ምግባቸው የተሻሻለ ይሆናል፡፡”
ስለዚህም አራተኛው የልማታዊ ሴፍቲ ኔት መርሀ ግብር የአሰራር ለውጥን አምጥቷል፡፡የአሰራር ለውጡም
ወጥ የሆነ አስተዳደራዊ ስልቶችንና መሳሪያዎችን በመጠቀም የፖሊሲ፣ ተቋማዊና የተበጣጠሰ የበጀት
አስተዳደርን ለመቀነስ ይረዳል፡፡ የማህበራዊ ጥበቃውና የአደጋ ስጋት መቆጣጠሪያ ስልቶች ለአደጋ ተጋላጭ
ለሆኑ ቤተሰቦች የሚጠቅሙ መጠነኛ አገልግሎቶችን ያዘጋጀ ሲሆን የተለያዩ ፈፃሚዎችም ወጥ በሆነ ዕቅድና
የማስተባበሪያ መዋቅሮች ከስራ ድርሻቸውና ኃላፊነታቸው ጋር ይዟል፡፡ በመጨረሻም ተጠቃሚዎችን
የሚያገለግሉ ድርጅቶች ሁሉ ወጥ የሆኑ መጠቀሚያ ዘዴዎችን፣ መሳሪያዎችንና አቀራረቦችን በመጠቀም
ወጪን በአግባቡ መጠቀምና የተሻለ ውጤት ማምጣታቸውን ማረጋገጥ ይገባቸዋል፡፡ ለአገልግሎት
የሚውሉ ዘዴዎችና መሳሪያዎችም ለ6 ቅድሚያ ለሚገባቸው ጉዳዮች ማለትም የተጠቃሚዎች ምርጫ፣
የመረጃ ልውውጥ ዘዴዎች፣ የአደጋ ስጋት መከላከል ዘዴዎች፣ ዕቅድ ስራ የማስተባበርና ማስተዳደር፣
ማህበራዊ ተጠያቂነትና የአቅም ግንባታ ስልቶችን መንደፍ፣ መምከርና የተሻለውን ስልት አስፋፍቶ መጠቀም
ይገባቸዋል፡፡
የመርሃ ግብሩ የአሰራር ስልትና ለአራቱ ከላይ የተዘረዘሩት ፖሊሲዎች (ማህበራዊ ጥበቃ፣ የአደጋ ስጋትን
መከላከል፣ ለአየር ንብረት መለወጥ አለመበገር፣ የሥርአተ ምግብ) ትግበራ ውጤት አስተዋፅኦ የሚያደርግ
ሲሆን ለውጤቱ ግን የተቀናጀ የአሰራር መዋቅርና ጉዳዮችን በጥልቀት መመልከትን ይጠይቃል፡፡ የቀድሞው
የልማታዊ ሴፍቲ ኔት መርሀ ግብር እና የቤተሰብ ሃብት ግንባታ መርሃ ግብር (HABP) በዚህ ምዕራፍ በአንድ
ላይ ተጠቃለው የሚመዘኑ ሆነዋል፡፡ በዚህ ስራ ላይ የሚሳተፉት ዘርፎችና ሚኒስቴር መ/ቤቶችም ከቀድሞው
ጨምረዋል፡፡
3
2.3. የልማታዊ ሴፍቲ ኔት መርሀ ግብር መሰረታዊ መመሪያዎች
መርሃ ግብሩን በሁሉም ደረጃ ለመቅረፅና ለመተግበር የሚያገለግሉ የሚከተሉትን ዋነኛ መመሪያዎችን ይዟል፡
3. የክፍያዎች አስፈላጊነት (Primacy of transfers)፡ ዋናው የልማታዊ ሴፍቲ ኔት መርሀ ግብር አላማ
ሊከተል የሚችል አደጋን መከላከል እንደመሆኑ የመርሃ ግብሩ ተጠቃሚዎች ሊተላለፍላቸው
የሚገባቸውን እንዲያገኙ ከሁሉ ጉዳዮች ቅድሚያ ሊሰጣቸው ይገባል፡፡ በምንም ምክንያት ሊከፈላቸው
የሚገባቸው ክፍያ ሊዘገይባቸው አይገባም፡፡
5. የመተዳደሪያ መፍትሄ አምጪነት፡ የልማታዊ ሴፍቲ ኔት መርሀ ግብር 1ኛ/ ቤተሰቦችና ግለሰቦች እንደ
አቅማቸው 2ኛ/ ሶስቱም ዓይነቶች የመተዳደሪያ መንገዶች [Pathways](የሰብልና እንስሳት እርባታ፣
ከግብርና ጋር ተያያዥነት የሌላቸው የገቢ ምንጮችና ለደሞዝ ተቀጣሪነት) ተቋማዊ አቅምን ይገነባል፡፡
4
6. ከልማት ስራዎች ጋር መዋሃድ፡- የልማታዊ ሴፍቲ ኔት መርሀ ግብር በራሱ ፕሮጀክት አይደለም፡፡ ሆኖም
ከአካባቢያዊ የልማት ዕቅዶች ጋር ተዋህዶ የሚሰራ የልማት አካል ነው፡፡ ስለዚህ የልሴኔመ ከወረዳ፣
ከዞን፣ ክልልና የፌደራል ደረጃ ጋር የሚሰሩ የልማት ዕቅዶች አካል ነው፡፡
7. እንደ አስፈላጊነቱ የሚሰፋ፡- የልማታዊ ሴፍቲ ኔት መርሀ ግብር የህዝቡን አኗኗር የሚያቃውሱ ሁኔታዎች
ሲፈጠሩ ችግሮቹ በተፈጠሩባቸው ወረዳዎች ውስጥ በችግሩ ለተጎዱ ቤተሰቦች የምግብ ዋስትናቸው
ወደ ከፋ ሁኔታ እንዳይገባ ተጨማሪ ድጋፍ ይደረግላቸዋል፡፡ ሆኖም የልማታዊ ሴፍቲ ኔት መርሀ ግብር
የተጨማሪ ድጋፍ በሚያስፈልግበት ሁኔታ በችግሩ የተጎዱ ቤተሰቦች በአደጋ መከላከል መርሃ ግብር
(Emergency response) ድጋፍ ይደረግላቸዋል፡፡
9. የፆታ እኩልነት፡- የልማታዊ ሴፍቲ ኔት መርሀ ግብር የወንዶችና ሴቶችን ልዩ ፍላጎቶች፣ ጥቅሞችና
አቅምን ባገናዘበ ሁኔታ ከመርሃ ግብሩ በዕኩልነት መጠቀማቸውን ለማረጋገጥ ተዘጋጅቷል፡፡ ይህም
የሚደረገው የልማታዊ ሴፍቲ ኔት መርሀ ግብር ተጠቃሚ ወንዶችና ሴቶች በሚመለከታቸው ጉዳዮች
ላይ ውሳኔ ሰጪነት በመሳተፍ እና ሴቶችም በምርትና በፆታ ሃላፊነታቸው በሚመለከታቸው ስራዎች
ላይ ትኩረትን በማድረግ በተለየ ሁኔታ ሴቶች የቤተሰብ አስተዳዳሪ በሆኑበት ደግሞ የተለየ ድጋፍን
በማድረግ ነው፡፡
5
2.4. መርሃ ግብሩ በተፈጥሮ አካባቢና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እንዳያስከትል የሚደረጉ
ጥንቃቄዎች
የልማታዊ ሴፍቲ ኔት መርሀ ግብር በተፈጥሮ አካባቢና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እንዳያስከትል
ሆኖ ተዘጋጅቷል፡፡ መደረግ የሚገባቸውም ጥንቃቄዎች በየመርሃ ግብሮቹ ዓይነት እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡
6
2.5 የልማታዊ ሴፍቲኔት መርሀግብር የዕቅድ አሰራር ሂደት
የልማታዊ ሴፍቲ ኔት መርሀ ግብር የዕቅድ አሰራር ሂደት በተለያየ ደረጃ የሚካሄድ ሲሆን ከታች ወደላይና
ከላይ ወደታች የሚካሄዱ ዓመታዊ የሴፍቲ ኔት ዕቅዶችን ያዘጋጃል።
1. በቀበሌው የልማት ሰራተኛ ድጋፍ የቀበሌው ማህበረሰብ የቀበሌውን እቅድ በማዘጋጀት ይጀመራል፡፡
የተዘጋጀውም እቅድ በቀበሌው ተገምግሞ ከፀደቀ በኋላ የመርሃ ግብር ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከተመረጡት
ሰዎች ዝርዝር ጋር የቀበሌው የሴፍቲ ኔት እቅድ ይሆናል፡፡
2. የወረዳ ዓመታዊ የሴፍቲኔት ዕቅድ የቀበሌዎችን ዕቅድ በማጠቃለልና በወረዳዉ የሚያስፈልገዉን የስራ
ዕቅዶች ይጨምራል፡፡
3. የክልል ዓመታዊ የሴፍቲነት ዕቅድ የወረዳዎችን ዕቅድ አጠቃልሎና የክልሉን ሥራዎች ጨምሮ ይይዛል፡
4. የፌዴራል ዓምታዊ የሴፍቲኔት ዕቅድ በከፍተኛ ደረጃ የሚገኝ የዓመታዊ ዕቅድ አጠቃልሎ የያዘ
የመርሃ ግቡሩ ሠነድ ሲሆን በተከታይ የአመት በፌዴራል ደረጃ ሊሠጥ የሚገባችውን ስራዎች የያዘ
ነው፡፡
______________________
ዞኖች እቅዶችን የመገምገምና የማጠናቀር ሚና በሚጫወቱባቼው ክልሎች፥ ወረዳዎች እቅዳቸውን የሚሰጡት ለዞናቸው ይሆናል።
ዞኖችም እቅዱን አጠቃለው በተወሰነው የጊዜ ገደብ ውስጥ ለክልል ገቢ ማድረግ አለባቸው።
7
3. የልማታዊ ሴፍቲኔት መርሀግብር ዝርዝር ፕሮግራሞች
8
የሥራ ውጤት 4- የሥራ ውጤት 4- ተጠቃሚዎች የማጥፖ፣ የአስመፖ፣ አንለማአኢ፣
ተጠቃሚዎች በሦስት በሦስት የመተዳደሪያ መንገዶች ብስምፖ
የመተዳደሪያ መንገዶች ማለትም በስብልና እንስሳት ፤ከግብርና
ማለትም በስብልና እንስሳት ጋር ያልተያያዙ የገቢ ምንጮችና
፤ከግብርና ጋር ያልተያያዙ ከተቀጣሪነት/ደመወዝተኝነት ሊመነጩ
የገቢ ምንጮችና ከተቀጣሪነት/ ይችላሉ ፡፤
ደመወዝተኝነት ሊመነጩ
ይችላሉ ፡፤
የሥራ ውጤት 5- - የሰው ሃይል አስተዳደር የማጥፖ፣ የአስመፖ፣ አንለማአኢ፣
መርሃግብርሩን በአግባቡና - ተጠያቂነት ያለበት ብስምፖ
ውጤታማ ለማድረግ የመርሃግብሩ አስትዳደርና የተጠናከረ
የሚያስችሉ የሥራ አይነቶች የክትትል ግምገማ ሂደት በስራ ላይ
ይከናወናሉ። ይውላል
- ተጠያቂነት ያለበት የበጀትና
የገንዘብ አስተዳደር ይኖራል
- ተጠያቂነት ያለበት የምግብ
አያያዝ አስተዳደር ይተገበራል
- ተጠያቂነት ያለበት የንብረት
አስተዳደር ይተገበራል
9
4. ለውሳኔ ሰጪዎች ትኩረትን የሚሹ ጉዳዮች
• ተሳትፏዊ ማድረግ፡- ህዝቡ የመርሃግብሩ ተጠቃሚዎችን በመምረጥና በማጽደቅ ሂደት ውስጥ ተሳታፊ
መሆን ይገባዋል፡፡
10
የወረዳው የስራ እና
ማህበራዊ ጉዳይ የወረዳው የምግብ ዋስትና ግብረሃይል አባል ሆኖ አስተዋጽኦ ያደርጋል፡፡
ጽህፈት ቤት
የመተዳደሪያ
ለምረቃ ጠቃሚ ዘዴዎችን በማዘጋጀት በየቀበሌው የተመራቂ ቤተሰቦች
አካባቢዎች አጥኚ
ቁጥር ላይ መግባባት ያደርጋል፡፡
ቡድን
11
• የወረዳውን የመጠባበቂያ በጀት ያቀርባል፡
የወረዳው • ከፌዴራል ደራጃ የተላከውን የመጠባበቂያ በጀት ያስተዳድራል
የፋይናንስ ድ/ቤት • የመክፍያ ቀጽ በማዘጋጀት ከመጠባበቂ በጀት ክፍያ ለሚገባቸው ክፍያ
ይፈፅማል።
12
የቅድመ ማስጠንቀቂያና ምላሽ ዳይሬክቶሬት ድንገተኛ አድጋዎችን ለማስወገድ የሚያስችሉ የዕቅድ ስልቶችን
በእያንዳንዱ የስራው ወረዳዎች ለመስራት እንዲቻል አዘጋጅቷል፡፡ እነዚህ የድንገተኛ ዕቅዶች ስጋቶችን
ለማስወገድ ከሴፍቲነት ስራዎች ጋር ተጣጥመው እንዲሰሩ ይከለሳል፡፡ ይህ ሲደረግ ዕቅዶች የሚከተሉትን
ጉዳዮች ማካተት ይኖርባቸዋል፡፡
• ጥሬ ገንዘብ ክፍያ የመጀመሪያ አማራጭ ነው፡- በተቻለ መጠን ጥሬ ገንዘብ ክፍያ የመጀመሪያ
አማራጭ መሆን አለበት፡፡ የምግብ ክፍያ የሚደረገው በአካባቢውና በጊዜው የምግብ ሰብል በገበያ
በማይኖርበትና የገበያ ዋጋው በጣም ከፍተኛ በሚሆንበት ሁኔታ ነው፡፡ ይህም አሠራር የተጠቃሚዎችን
ምግብ እጥረትና ሃብታቸው እንዳይሸረሸር ይረዳል።
• የክፍያ ቀደምትነት፡- ክፍያዎች ለጉልበት ስራ የሚደረገውን ጨምሮ በምንም ምክንያት ሊዘገይ
አይገባም፡፡ ተጠቃሚዎች ሊቀበሉት የሚገባችው ክፍያ በቴክኒካዊም ሆነ አስተዳደራዊ ጉዳዩች
ሊዘገይባቸው አይገባም። በተጨማሪም ምን ክፍያና መቼ እንደሚቀርብለቸው የማወቅ መብት
አላቸው፡፡
• የቀጥተኛ ተከፋዮች የክፍያ ጊዜ ፡- በቋሚነት የነፃ ክፍያ ተጠቃሚዎች ከ 2009 በጀት ዓመት የመጀመሪያ
ወር ጀምሮ የተፈቀደላቸውን ክፍያ በየዓመቱ ለ12 ወራት ይቀበላሉ።
• በልማት ሥራ ላይ ለሚሣተፉ የክፍያ ጊዜ፡- በሥራ ላይ ለሚሳተፉ የክፍያ ጊዜያአቸውን የሚወስኑት
የአካባቢው የዝናብ ወቅት፡ የግብርና ሥራ የሚበዛበት ወቅት፤ የምግብ እጥረት የሚኖርበትና ወዘተ
ናቸው፡፡ አለበለዚያ ወረዳዎችና ክልሎች የልማት ስራዎችና ክፍያዎች የሚፈፀሙበትን ጊዜ እንደ
አካባቢያቸው ሁኔታ ሊወስኑ ይችላሉ፡ በወረዳዎች ፍላጎት ላይ ተመስርቶ በህዝቡ የሚሠሩት ሥራዎች
የክፍያ ጊዜ በሚከተሉት መርሆዎች ላይ መመሥረት ይገባቸዋል።
o ለአተገባበር ቅለት እያንዳንዱ ክልል ከ2-3 ያልበለጡ የክፍያ ጊዜ ለወረዳዎች ማውጣት
አለበት፡፡
o የክፍያ ጊዜን መጠበቅ ቅድሚያ የሚሠጠው ነው፡፡ የክፍያ ጊዜው መቼም ቢሆን ክልሎችና
ወረዳዎች የጥሬ ገንዘብ ክፍያን በ20 ቀናት ውስጥ፣ የምግብ ክፍያን በ30 ቀናት ውስጥ
ማጠናቀቅ ይገባቸዋል። ይህም ማለት ሥራው በታህሣሥ ወር የሚጠናቀቅ ከሆነ ህዝቡን
ለጉልበት ሥራ በጥር ወር ለማሣተፍ ክፍያውን በታህሣሥ ወር አጥናቆ ከ20-30 ቀን ውስጥ
መጠናቀቅ አለበት ፡፡
13
4.3 የግዢ ሥርዓቶችና መነሻ ተመኖች
የልማታዊ ሴፍቲ ኔት መርሀግብር የግዢ ሠነድ እንደ ግዢው ዓይነትና መጠን ሊለያይ ይችላል ፡፡ስምምነት
የተደረገባችው የአገለግሎቶች፤ ሥራዎችና ማማከርን የማይጠይቁ አገልግሎቶች ከዚህ የሚከተሉት ናቸው
በዓለም አቀፍ የጨረታ ውድድር የሚከናወን የዕቃዎችና አገልግሎቶች ግዢ በፌዴራል መንግስት ደረጃ ብቻ
የሚካሔድ ሲሆን የግዢ ሥርዓቱም በዓለም ባንክ የግዢ ደንብ ይካሔዳል፡፡ በሌላ በኩል በሀገር ውስጥ
የሚደረግ ግዢ በዓለም ባንክ ተቀባይነት ባለው የግዥ ስርአት በፌዴራል መንግስት የግዢ ሥርዓት መሠረት
የሚከናወን ሲሆን በመርሀ ግብሩ የአፈጻጸም መመሪያ 14.5.6 ማየት ያስፈልጋል።
14
V. የውሣኔ ሠጪዎች ዋና ዋና ሥራዎችና ኃላፊነቶች
በክልልና በወረዳ መንግስታዊ እንዲሁም መያድ ውሣኔ ሠጪዎች በልማታዊ ሴፍቲ ኔት መርሀግብር የየእለት
ሥራዎች ውስጥ ወሳኝ ሚና አላቸው፡፡ የአደጋ ስጋትን ለመከላከል፣ የገንዘብ አያያዝ፣ የምግብ አያያዝና
የሌሎች ሐብቶች አስተዳደር ላይ ዋነኛ የሆኑ ውሣኔዎችን ይሠጣሉ ፡፡
ከዚህ የሚከተሉት የወረዳ፣ የክልልና የመያድ ውሣኔ ሠጪዎች በበጀት አስተዳደር ላይ ያላቸውን ዋና ዋና
ሥራዎችና ኃላፊነቶች ናቸው፡፡
በክልል ደረጃ፡-
• አግባብ ያለው የሂሣብ አያያዝ ሥርዓት በክልልና በወረዳ ደረጃ
መቋቋማቸውን ያረጋግጣል ፡፡
• ለወረዳ የኢኮኖሚና ፍይናንስ ጽ/ቤቶች፣ ለክልል ግብርና፣ ለክልል
ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ፤ለማህበራት ማደራጃ ቢሮ፣ ለክልል
ጥቃቀንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ማስፋፊያ እንደ አስፍላጊነቱ ገንዘብ
ያስተላልፍላቸዋል ፡፡
• ከወረዳዎች ከግብርና ቢሮና ከሠራተኛና ማህበራዊ ቢሮ የሚሰበሰቡ
የፋይናንስና የበጀት ሠነዶችንና መረጃዎችን ያደራጃል።
• የወረዳዎችን የሂሣብ አያያዝ በመገመገም አስፈላጊውን የቴክኒክ ድጋፍና
ኢኮኖሚ ዕርዳታ ያደርጋል ፡፡
ትብብር • የሩብ እና ዓመታዊ የፍይናንስ ሪፖርት ያዘጋጃል
• ለስራ እንዲጠቁሙበት የተላለፈላቸውን በጀት በኃላፊነት ያስተዳድራል፡፡
በወረዳ ደረጃ
• ለሴፍቲኔት የተመደበላቸው በጀት በጊዜው መረከባቸውን ያረጋግጣሉ፡፡
• ለዓመቱ የተመደበውን በጀት ያቀርባል።
• ለተጥቃሚ ቤተሰቦች ወቅቱን ጠብቆ ክፍያ ይፈፅማል ፡፡
• አስፈላጊውን የበጀት አጠቃቀም ለክልል የፋይናንስ ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ
የወርና የሩብ አመት ሪፖርት ያቀርባል።
15
በክልል ደረጃ
• የክልሉን የሥራ ዕቅድና በጀት ያደራጃል
• ከክልሉ የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የሚተላለፍለትን የሥራ
ማስኬጃ በጀት የግብርና ቢሮን ወክሎ ያስተዳደራል ፡፡
• በክልል ደረጃ የሚገኙትን የመርሃ ግብሩ ፈፃሚዎችና ተቆጣጣሪዎች
የምግብ ዋስትና ለአስተዳደራዊ ና ካፒታል ወጪዎች የሚመደበውን ለመወሰን ስብስባ
ይጠራል ፡፡
ማስተባበሪያ
ዳይሬክቶሬት በወረዳ ደረጃ
• የወርዳ የሥራ ዕቅድና በጀት ያደራጃል
• የወረዳውን የመርሃ ግብሩን ፈፃሚዎችና ተቆጣጣሪዎች በመሰብሰብ
ለአስተዳደራዊና ካፒታል ወጪዎች የሚመደበውን በጀት ያስወስናል ፡፡
• የተጠቃሚዎችን የስም መቆጣጥሪያና ክፍያ መክፍያ ዝርዝር በማዘጋጀት
ለተጠቃሚዎች ክፍያ በወቅቱ እንዲከፈል ያደርጋል።
የክልሉ
• ከፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ የሚተላለፍለትን በጀት
የሰራተኛና ያስተዳድራል፡፡
ማህበራዊ ጉዳይ የወረዳ
• ለሚተላላፍበት በጀት ኃላፊነት ይወስዳል ፡፡
በክልል ደረጃ
• በህዝብ ሥራ ተሳትፎ ክፍሉ አማካይነት ከክልል የምግብ ዋስትና
የተፈጥሮ ሃብት የተላለፈለትን ማንኛውንም አይነት የሃብት አጠቃቀም ሁኔታ ሪፖርት
አጠቃቀም ያደርጋል
ዳይሬክቶሬት በወረዳ ደረጃ
• ለህዝብ ስራ ተሳትፎ የሚተላለፍለትን የካፒታል በጀት እያስተዳደረ
ለተገቢው ስራ መመደቡንና ሥራ ላይ መዋሉን ይከታተላል።
በክልል ደረጃ
• አመታዊ የአተገባበር እና ባጀት እቅድን አጠናቅሮ ለክልሉ ያቀርባል፡
• በክልሉ ፋይናንስ እና ኢኮኖሚ የሚተላለፍለትን ባጀት ያስተዳድራል፡፡
• የአስተዳደር እና ካፒታል ወጪ በተመለከተ ሰብሰባዎችን በመምራት
የምግብ ዋስትና ለሚመለከታቸው የትግበራ እና ተቆጣጣሪ አካላት እንዲመደብ
ማሰተባበሪያ ያስተባብራል
ዴስክ
በወረዳ ደረጃ
• ለህዝብ መተዳደሪያ ማሻሻያና አቅም ግንባታ የሚተላለፍለትን በጀት
እያስተዳደረ ለተጠቃሚዎች በአግባቡ መመደቡንና ለተለያዩ የሥራ
ክፍሎች መተላለፉን ያረጋግጣል ፡፡
16
• የሚያስፈልግውን ሃብት ያቀርባሉ።
መንግስታዊ • በመርሃ ግቡሩ የማስፈፀሚያ መመሪያ (Program Implementation
ያልሆኑ ድርጅቶች Manual) መሰረት የስራ ዕቅድና በጀት ያዘጋጀሉ፡፡
• ለሀብቱ ሃላፊነት እየወሰዱ ሪፖርት ይቀርባሉ።
17
አስተዳደራዊ በጀት፡- የአስተዳደራዊ በጀት ለሰዉ ሃይል፤ ለጥቃቅን የፅ/ቤት ዕቃዎችና መሳሪያዎች፤
ለጉዞና አበል፤ ለስልጠና፤ ለክትትልና ግምገማ፤ እና ሌሎች ወጪዎች (ከአስቸካይ ጊዜ ዕርዳታ ጋር የተያያዙ)
የሚይዝ ሲሆን የተጠቃሚዎች መተዳደሪያ ለማሻሻል የሚወጡ ወጪዎችን አያጠቃልልም። የወረዳው
የምግብ ዋስትና ግብር ሃይል ለፈፃሚ ጽ/ቤቶች ለአስተዳደራዊ ወጪዎች የሚስፈልገውን በጀት እየመደበ
ያፀድቃል ፡፡
በህዝቡ ላይ የባህርይ ለውጥ ለማምጣት የሚያስፈለገውን በጀት በጤና ጽ/ቤቶች በጀት የሚሽፈን ሲሆን
ለክትትልና ግምገማና ለአነስተኛ የማሣተሚያና ማባዥያ አገልገሎት የሚያስፈልጉ ወጪዎች ከልማመዊ
ሴፍቲኔት መርሀግብር የአስተዳደራዊ በጀት ሊሸፈን ይችላል፡፡ የቀበሌ ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ ለማቋቋምና
ሥራውን ለማከናውን የሚያስፈልጉ ወጪዎች በሁሉም የልማታዊ ሴፍቲኔት መርሀግብር ተጠቃሚ ወረዳዎች
በወረዳው የአስተዳደራዊ በጀት ይሸፈናል፡፡
ከዚህ የሚከተሉት የወረዳ፣ የክልልና የመያድ ውሣኔ ሠጪዎች በበጀት አስተዳደር ላይ ያላቸውን ዋና ዋና
ሥራዎችና ኃላፊነቶች ናቸው፡፡
በክልል ደረጃ
• ለምግብና ገንዘብ ክፍፍል ለውጥ እንዲደረግ ሲጠየቅ ያረጋግጣል
• የወረዳዎች የሩብ ዓመት የምግብ አጠቃቀም ሪፖርት ያጠናቅራል ፡፡
• በምግብ ላይ የተደረጉ የኦዲት ሥራ ግኝቶች በጊዜው መፍትሔ
የምግብ ዋስትና ማግኘታቸውን ይከታተላል፡፡
ማስተባበሪያ በወረዳ ደረጃ
ዳይሬክቶሬት • የምግብ እንቅስቃሴ መረጃዎችን በበቂ ሁኔታ ይይዛል
• የወርና የሩብ ዓመት የምግብ አጠቃቀም ሪፖርቶች ያዘጋጃል ፡፡
• በወረዳዎች የምግብ ሃብት አያያዝን ይከታተላል
• ለቅድመ ማስጠንቃቂያና እርዳታ ዴስክ አስፈላጊ መረጃዎችን ይሠጣል፡
በክልል ደረጃ
• የምግብ እንቅስቃሴን ይከታተላል
• በየወሩ ከወረዳዎች ሪፖርት እየተቀበለ በማቀናበር ለፌዴራል ደረጃ
ይልካል፡
• በመጋዘን ውስጥ ያለ አያያዝን ጨምሮ አስፈላጊ መመሪያ በአግባቡ
የምግብ መተግበራቸውን ይከታተላል፡፡
አስተዳደር • የአዲት ግኝቶችን እየተከታተለ አስፈላጊ የእርምት እርምጃዎች በክልል
ክፍል ውስጥ እንዲወስዱ ያደርጋል።
በወረዳ ደረጃ
• ምግብ ለወረዳው ይላካል በተባለው መሠረት መድረሱን ያረጋግጣል
• ምግብ በአግባቡ መከማቸቱንና መያዙን ያርጋግጣል
• የምግብ ጉድለት ከተገኘ ለሚመለከተው ኃላፊ ያሳውቃል፡፡
• ወርሃዊ የምግብ አጠቃቀምን ሪፖርት እያዘጋጀ ያቀርባል።
18
• በሱማሌ ክልል የሚሠሩትን የቤተሰብ ሀብት መጠሪያ ኮሚቴዎችን
(Hubs & Spokes) በአጋዥ ሊቀመንበርነት ይመራል
• ከምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት (ምዋማዳ) ወደ ምግብ
የዓለም ማድረሻ ጣቢያዎች እንዲደርስ ከአጓጓዦች ጋር ስምምነት ይፈፅማል
• ምግብ በማከፋፈያ ጣቢያዎች መድርሱን ያረጋጣል።
የምግብ • ምግብ በአግባቡ መከማቸቱንና መያዙን በቅርበት ይከታተላል
ፕሮግራም • በየአካባቢው የሚገኙ ሠራተኞችን በምግብ እህል አያያዝ ላይ የአቅም
ግንባታ ያደርጋል፡፡
• ምግብ በአግባብ ባለው መንገድ መድረሱን ወደሚገባው ሥፍራ ሁሉ
መሠራጨቱን ይከታተላል፡፡
19
5.3 በልሴኔመ የቁሳዊ ሐብት አያያዝ
የቁሳዊ ሐብት አያያዝ በአጠቃላይ የተሸከርካሪና ሞተር ብስክሌቶች፤ ህንፃዎችና መሣሪዎች እንዲሁም
የአሽከርካሪዎች የትራፊክ ጥንቃቄን ያጠቃልላል ፡፡
የቁሳዊ ሐብት አያያዝ በአግባቡ ለማከናውን የኢትዩጵያ መንግስት ፖሊሲዎችና መመሪያዎች እንደ የመንግስት
ቋሚ ንብረት አያያዝ መመሪያ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር የተሸከርካሪ አያያዝ አጠቃቀም መመሪያ
የኢትዮጵያ ትራንስፖርት ባለስልጣንና የልማታዊ ሴፍቲኔት መርሀግብር አተገባበር መመሪያ (Programm
Implementation Manual) እየታዩ መጠበቅ ይኖርባቸዋል፡፡
በወረዳ የቁሳዊ ሐብት አስተዳደር የሚመለከታቸው ተቋማት የወረዳ አስተዳደርን፣ የወረዳ ግብርና ጽ/ቤትና
የምግብ ዋስትና ፤የወረዳ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት፤ የወረዳ ንግድና ትራንስፖርትና ኢንዱስትሪ ጽ/
ቤቶች ናቸው ፡፡
እያንዳንዱ የልማታዊ ሴፍቲኔት መርሀግብር ፈፃሚ ተቋም የራሱን ቁሳዊ ሀብት የማስተዳደር ኃላፊነት
አለበት።
ማህበራዊ ተጠያቂነት በልማታዊ ሴፍቲኔት መርሀግብር 4 ዉስጥ በመርሃ ግብሩ አነዳደፍ ውስጥ የመርሃ
ግብሩ ተጠቃሚዎችና ሌሎች የማህበረሰቡ አባላት ሃሳባቸዉን በፕሮግራሙ አሠራር ላይ አስተያየት እየሰጡ
አፈፃፀሙ እንዲሻሻል ያደርጋሉ፡፡በተጨማሪም ተጠቃሚዎችና የማህበረሰቡ አባላት በመርሃ ግብሩ የአሰራር
መንገድና አፈፃፀም ላይ ቅሬታቸዉን እያቀረቡ መልስ እንዲያገኙበት የሚደረግበት አሰራር ነዉ፡፡
የኢመተማ የኢትዮጵያን መንግስት ወክሎ በሚሠራ ነፃ በሆነ የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በሚመራ
የባለ ደርሻ አካላት ኮሚቴ ይመራል፡፡
ኢመተማ ከህዝቡ ጋር ጠንካራ ግንኙነት ካላቸዉ የማህበረዊ አገልግሎት ከሚሰጡ የማህበረሰብ ድርጅቶች
ጋር አገልግሎታቸዉን እንዲያሻሽሉ አጠናክሮ ይሰራል፡፡ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች የተለያዩ ስራዎችን
ለመስራት እንዲችሉና አገልግሎት ሰጪዎችን ለማሳተፍ የስራ ማስኬጃ የገንዘብ ድጋፍ ከአስተዳደር ድርጅቱ
መጠየቅ ይችላሉ፡፡ የሲቪል ማህበረሰቦች አመቺ ነው የሚሉትን ዘዴ መጠቀም ቢችሉም በአብዛኛዉ
በልማታዊ ሴፍቲኔት መርሀግብር ለማህበራዊ ተጠቃሚነት መጠቀም ያለባቸዉ መሳሪያዎች የሚከተሉትን
ነው፡፡
20
• የማህበረሰብ የነጥብ መስጫ ካርድ (Community Score Card): ሁለቱንም የልማታዊ
ሴፍቲኔት መርሀግብር ተጠቃሚዎች የሚቀበሉትንና አገልግሎቱን አቅራቢዎች የሚሰጡትን
የአገልግሎት ጥራት ለመመዘን የሚያስችል አሰራር ነው። ምዘናው በሁለቱም አካላት ከተካሄደ
በኋላ አገልግሎት ተቀባዮችና አገልግሎት ሰጪዎች በስብሰባ ተገናኝተው ሁኔታዎች ለወደፊት
እንዲሻሻሉ ምክክር የሚያደርጉበት መድረክ መፍጠሪያ ነው።
• የዜጎች ሪፖርት ማቅረቢያ ካርድ፡ በአንድ ወረዳ ውስጥ አንድ አገልግሎት የሚጠቀሙ ሰዎች
የተሰጣቸውን አገልግሎት ጥራት ሁኔታ ለመግለጽ የሚጠቀሙበት መረጃ መሰብሰቢያ መንገድ
ነው። እንደ የማህበረሰብ የነጥብ መስጫ ካርድ ስህተቱ/ችግሩ ምን እንደሆነ የሚገለጽበት
አሰራር ሳይሆን የታዩ ችግሮች የሚፈቱበትን መንገድ ለመስማማት የሚያስችል አሰራር ነው።
ይህም አሰራር እያንዳነዱ ሰው የሚሰማውን ቅሬታ ለማቅረብ ሳይሆን የታዩ ግድፈቶችን
ማስተካከያ እርምጃ ለመውሰድ ትኩረት ይሰጣል።
1. ወደ ተቀናጀ የአገልግሎት አሰራር መሸጋገር፡- ይህ ምዕራፍ በጊዜ ከተገደቡ መርሃ ግብሮች ቀልጣፋና
ዉጤታማ ወደ ሆነ ማህበራዊ ጥበቃና የአደጋ ስጋት መከላከልን ወደ ማከናወን ተሸጋግሯል፡፡
5. የተጠናከረና ተከታታይ የሆነ ለአደጋ ድጋፍ መስጠት፡- በአንድ ወቅት የሚሰጠዉን የአደጋ ጊዜ ድጋፍ
በማጠናከር በአካባቢ የተወሰነ ወይም ተስፋፍቶ የሚገኝን ወቅታዊ አደጋ ለመቋቋም በአንድ ስፍራ
ያልተማከለ ነገር ግን በየአካባቢዉ ዉሳኔ በመስጠት ድጋፍ መጀመር ማስቻሉ፡፡
6. በህዝብ የሚሰሩ ስራዎች እንደ አስፈላጊነቱ ተለዋዋጭ መሆናቸዉ፡- የሚሰሩት የማህበረሰብ ልማት
ስራዎች በየአካባቢዉ በተመሰረተ ፍላጎት የማህበራዊ ተቋማትን፤ የሥርአተ ምግብ ፤ የአየር ንብረት
ለመቋቋምና የአደጋ ስጋቶችን ለመከላከል መቻሉ፡፡
7. የተለየ ድጋፍ የሚፈልጉ ሁኔታዎች መብዛታቸዉ፡- የቀደመዉ መርሃ ግብር ማስፈፀሚያ መመሪያ
ለተወሰኑ ዓይነት የሙያ ስልጠናዎችና የባህርይ ለውጥ ለማምጣት የሚያስችሉ መልእክቶችን ያጠቃለለ
ነበር። በዚህ ምእራፍ ግን መመሪያው ለብዙ ዓይነት ሁኔታዎች ፈቅዷል፡፡
21
8. ሦስት ዓይነት የመተዳደሪያ ማሻሻያ መንገዶች ድጋፍ ያደርጋል፡- ሦስቱ የመተዳደሪያ መንገዶች ማለትም
የሰብልና የእንስሳት እርባታ፤ ከግብርና ጋር ያልተያያዙ የገቢ ምንጮችና በደመወዝ ተቀጣሪነት ናቸዉ፡
፡እያንዳንዱ የመተዳደሪያ መንገድም በተሻለ ቅንጅትና ተከታታይነት ያላቸዉ ድጋፎች ይሠጣሉ፡፡
በተጨማሪም ለችግር ተጋላጭነታቸዉ የከፋ ቤተሰቦች እና የብድር አገልግሎት አማራጭ የሌላቸው
የመተዳደሪያ ክፍያ ተጠቃሚ ይሆናሉ።
9. የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር (ሰማጉሚ) ደረጃ በደረጃ የቋሚ ድጋፍ የሚያገኙ ተጠቃሚዎችን
ሙሉ ሃላፊነት ይወስዳል፡- የአቅም ግንባታን ለማድረግ በተደረገዉ ዕቅድ፤ የሰማጉሚ ሚና አቅም
ግንባታ በልማታዊ ሴፍቲኔት መርሀግብር ቀስ በቀስ በቋሚነት ተጠቃሚ የሆኑትን ተላልፈዉለት ወጥ
በሆነ የመርሃ ግብር አሰራር ይደግፋል፡፡
10. በፆታ እኩልነት ላይ የተጠናከረ ትኩረት ይደረጋል፡- የፆታ እኩልነት ከስምንቱ የልሴኔመ መሰረታዊ
መመሪያዎች አንዱ ቢሆኑም የሴቶችን ሙሉ ተሳትፎና ጥቅማቸዉን ሙሉ ለሙሉ አላስጠበቁም ነበር፡
፡ ስለዚህ የልሴኔመ በተቀናጀ መንገድ የሴቶችን የተለያዩ ፍላጎቶች ለሟሟላት በተለይም በሥርአተ
ምግብ፤ በቤተሰብ የንብረት አያያዝ፤ በማህረሰብ ዉስጥ ዉህደት፣ ዘለቄታዊና ትርጉም ያለዉ የፆታ
እኩልነትን በማምጣት ከሚገኙት የልማት ዉጤቶች እኩል ተጠቃሚ መሆን ይችላሉ፡፡
የልማታዊ ሴፍቲኔት መርሀግብር 4 ፈጠራዎች አዳዲስ የክፍያ ዓይነቶች እንደ ኤሌክትሮኒክስና የካርድ
ክፍያን ዘዴ ይይዛል፡፡ በኤሌክትሮኒክ የሚከፈለዉ የክፍያ ዓይነት በሦስተኛ ወገን (ማይክሮ ፋይናንስ
ተቋማት ፤ተንቀሳቃሽ የገንዘብ ማስተላለፍያ) የመሳሰሉትን ያጠቃልላል፡፡ የማህበራዊ ተጠያቂነት አሰራርን
ማስተዋወቁም ተጨማሪ ፈጠራ ነዉ፡፡
22
VIII. በልሴኔመ 4 የተሻሉ ዉጤቶችን ለማምጣት መተግበር ያለባቸው ቁልፍ ተግባራት
የልሴኔመ 4 የታሰቡ ዉጤቶችን ለማምጣት እንዲችል በተሻሻሉ አሰራሮች ላይ ትኩረት ያደርጋል እነዚህም
የማስተባበር ዕቅድ የመርሃ ግብር ቅንጅቶችን መዘርጋት እና የአቅም ግንባታ ናቸዉ፡፡
የልማታዊ ሴፍቲኔት መርሀግብር አላማን ለማስፈፀም ማስተባበር አስፈላጊ ነዉ፡፡ ማስተባበር እኛ ልንሰራዉ
የሚገባዉ እንጂ በራሱ የሚመጣ አይደለም፡፡ ስለዚህ እንደማንኛዉም ስራ ልናቅደዉ ይገባል፡፡በወረዳ ደረጃ
የሚሰራ የማስተባብር እቅድ ቅደ ተከተል ከዚህ እንደሚከተለዉ ነዉ፡፡
ደረጃ አንድ፡- የወረዳ ምግብ ዋስትና ግብረሀይል (ወምዋግሀ) በወረዳ ደረጃ ለማስተባበር የሚያስፈልጉትን
ሁኔታዎችና ለማስተባብር ጥቅም ላይ ሊውሉ የሚገባቸውን አሰራሮች ያዘጋጃል፡፡የስራዎችን አይነቶችና ቀኖች
እንደ ሌሎቹ ስራዎች በግልፅ ሊለያቸው ይገባል፡፡ለማስተባብር አስፈላጊዉን ጥንቃቄ የሚሹ ጉዳዮችም፣-
• ማህበራዊ አገልግሎቶች ለምሳሌ ፡-በማህበራዊ ሰራተኞች የሚሰሩ ስራዎችና ሌሎች የማህበራዊ ጥበቃ
ጅማሬዎች፣
• እንደ የጤና ኤክስቴንሽን መርሃ ግብር የመሳሰሉ የጤና አገልግሎቶች፣
• የሥርአተ ምግብ አገልግሎት እንደ በማህበረሰብ የሚሰሩ የሥርአተ ምግብ ስራዎችና ሌሎች የብሔራዊ
የሥርአተ ምግብ መርሃ ግበር ስራዎች
• የመተዳደርያና የኢኮኖሚ የማበልፀግ መርሃግብሮች ለምሳሌ ፡- የአርብቶ አደር ማህበረሰብ ልማት
መርሃ ግብር፤ የግብርና እድገት እና የ መያድ መርሃ ግብሮች
• የመሬት አያያዝ መርሃ ግብር ለምሳሌ፡- ዘለቄታዊ የመሬት አያያዝ መርሃ ግብር
• ለአየር ለዉጥ መቋቋም የሚሰሩ ስራዎች ለምሳሌ ፡- ከአየሩ ንብረት ጋር የሚስማሙ ጅማሮዎች
ደረጃ ሁለት፡- የወምዋግሀ ያዘጋጀዉን የማስተባበርያ ስራዎች ለሁሉም የባለድርሻ አካላት አስተላልፎ
እነርሱም ሀላፊነታቸዉን ለመወጣት በአመታዊ ዕቅዳቸዉ ዉሰጥ ማስገባታቸዉን ያረጋግጣል፡፡
ደረጃ ሶስት፡- የወምዋግህ ያዘጋጃቸዉን ዝርዝር የሥራ ዕቅዶች በሚከተለዉ አመት ዉሰጥ በስራ ላይ
እንዲውሉ ያደርጋቸዋል፡፡
ደረጃ አምስት፡- የወምዋግህ የማስተባበሪያ ዕቅዱን በወረዳዉ የሴፍቲ ኔት ዕቅድ ወስጥ አስገብቶ ለክልል
ያቀርባል፡፡
23
8.2. የመርሀ ግብሩ ቅንጅትና ተደጋጋፊነቶች
በልሴኔመ የማህበረሰብ ልማት ስራና ለመተዳደሪያ ድጋፍ የሚደረጉ ቅንጅቶችና ተደጋጋፊነቶች፣ ለመተዳደሪያ
የሚደረጉ ድጋፎች ከሌሎች የመተዳደሪያ ማሻሻያ ከሚደረጉ ስራዎች ጋር ያለው ቅንጅት ሌላው የልሴኔመ
ውጤታማ ተግባር ነው ፡፡ የልሴኔመ 4 ለሦስት የመተዳደርያ መንገዶች ማለትም የሰብልና የእንስሳት
፤ከግብርና ጋር ያልተያያዙ የገቢ ማግኛ ሥራዎች እና በደመወዝ ተቀጣሪነት ትኩረት ያለው ድጋፍ ያደርጋል፡
፡ የስብልና የእንስሳት እርባታ መተዳደሪያ ወይም ከግብርና ጋር ተያያዥነት ያለውን ሥራ የመረጡ የቤተስብ
አባለት ከዚህ የሚከተሉትን አገልግሎቶች ይቀበላሉ ፡፡
• የቴክኒክ ስልጠና
• የንግድና የግብይት ስልጠና
• የንግድ ስራ እቅድ አዘገጃጀት
• በግብይት ላይ ምክር
በተመሳስይ ሁኔታ በተቀጣሪነት የሚሳተፉት በሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ (ሰማጉቢ)፤ በየክልል ጥቃቅንና
አነስተኛ ልማት ኢነተርፕራይዞች (ጥአልኢ) እና የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ማዕከላት አሰራር መሰረት ለቅጥር
የሚፈልጉ ኢንደስትሪዎችንና ሰፋፊ እርሻዎች ያላቸውን የስራ እድል ይለያሉ፡፡ በተቀጣሪነት ለመሳተፍ
የመረጡ ተጠቃሚዎች በአንድ ያገልግሎት መስጫ ማአከል ውስጥ ስማቸው ይመዘገባል፡፡ የቴክኒክና ሙያ
ስልጠና ማዕከላት ስራ በሚፈለግበት ሞያ ስልጠና ይሰጣሉ፡፡ መርሀግብሩ በተጨማሪም በስራ ላይ ላሉት
የሙያ ስልጠና ወይም የስራ ላይ ልምምድ በተወሰነ ደረጃ ልምድ ላላቸው ስልጣኞች የተሻላ ተቀጣሪነት እና
ለመቀጠር እድላቸውን ለማስፋትና በራስ መቀጠርን ሙከራ እንዲያደርጉ ያበረታታል፡፡
መርሀግብሩ ለጤናና ለሥርአተ ምግብ አገልግሎቶች በተላይም ለነፍስጡርና ለሚያጠቡ እናቶች ቅድመ
ወሊድ ጥንቃቄ ለሚያደርጉት ወደ ቀጥታ ድጋፍ ተጠቃሚነት ይሸጋገራሉ፡፡ የጉልበት ስራ ተጠቃሚዎችን
በየሥርአተ ምግብ የባህሪ ለውጥ ለማግኘት በሚደረጉ ስብሰባዎች ሲሳተፉ ለጉልበት ስራ የሚያገኙትን
ጥቅም ያገኛሉ።
ከችግር የመቋቋም አቅም ግንባታ የልሴኔመ 4 የእቅዱ፤ የትግበራው ፤የክትትልና ሪፓርት ማእከል ነው፡፡
የልሴኔመ 4 የአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር ኢኮኖሚ ለመገንባት የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም
ቤተሰቦች አደጋዎችን ለመቋቋም እንዲችሉ የምግብ ዋስትናቸውንና አኗኗራቸውን በማሻሻል ነው፡፡
በተጨማሪም የካርበን ልቀትን በመቀነስና በሕዝብ ስራ ተሳትፎ የካርበን መጠን መመጠጥን በመጨመር
ነው። ለዚህም የሚያስፈልጉ ስራዎች፡
24
• ከአየር ንብረት ጋር ተስማሚ የሆኑትን አሰራሮችን በማልማትና በማላመድ፣
• የሚሰሩ የማህበረሰብ የልማት ስራዎችና የመተዳደሪያ ማሻሻያ ስራዎች ስለአየር ንብረት ለውጥ
ጥንቃቄ ማድረግና እና የካርበን ልቀት ዝቅተኛ እንዲሆን ልዩ ትኩረት መስጠት ያስፈልጋል።
• የአየር ንብረት ለዉጥን ዉጤት አና የካርበን አመጣጠጥ ማመሳከርያ በመዉሰድ እና ክትትል
በማድረግ ከአየር ንብረት ተቋማት ለስራ ማስኬጃ የገንዘብ ድጋፍ ለማግኘት ትኩረት ማድረግ፡፡
የልሴኔመ 4 ለድርቅ ድንገተኛ አደጋ ስጋቶችን ለመቋቋም ይረዳል፡፡በክፍለ አህጉር ደረጃ የምስራቅ አፍሪካ በይነ
መንግስታት ሕብረት የድርቅ አደጋ ዘለቄታዊ መቋቋምያ ጅማሮ (IGAD’s Drought Disaster Resileince
and Sustainability Initaitve) የኢኮኖሚ እድገትን ለማምጣት በመስራት ላይ ይገኛል፡፡ ይህ አካል የክፍለ
አህጉርና ብሔራዊ የመርሃ ግብር ሰነዶች እና ተያያዥ መዋእለኑዋይ መርሃግብሮች አሉት። በኢትዮጵያም ይህ
ሰነድ በ 2012 (እ.ኤ.አ) በግብርና ሚኒስቴር መሪነት የምግብና የሥርአተ ምግብን ለማሻሻልና የአደጋ ስጋቶችን
የመቋቋም አቅምን ለመገንባት በተለይም ለድርቅ ተጠቂ በሆኑ ማህበረሰቦች አካባቢ ይሰራል፡፡ይህም ሰነድ
6 ዋና ዋና ስራዎችን ሲይዝ እነዚህም ፡- የተፈጥሮ ሀብት አያያዝ፤ የገበያ ቀረቤታና ንግድ፣ የመተዳደሪያ
ማሻሻያ ድጋፍ፣ የአርብቶ አደር የአደጋ ስጋቶችን መቀነስ፤ ምርምርና የእውቀት አጠቃቀም እንዲሁም የሰላም
ግንባታና እርቅን ማምጣት ናቸው፡፡ የልሴኔመ 4 ከብሄራዊ መርሀግብር ሰነድ ጋር ጠንካራ ትስስርና ኖሮት
በተደጋጋፊነት በሚሠሩ ሥራዎች ለድርቅ አደጋ ተጠቂ የሆኑትን ማህበረሰቦች ለመድረስ ይሰራል፡፡
በዚህ ምዕራፍ ቀድመው የነበሩ በተጠያቂነትና የመጠባብቅያ በጀት አጠቃቀምና አጀማመር ላይ የነብሩትን
ጉድለቶች ለማሻሻል ይሰራል፡፡ ይህም ስራ የመጠባበቀያ በጀት አጠቃቀምን (ጥሬ ገንዘብና ምግብ) ቀላል
ለማድረግ፤ የመጠባበቀያ በጀት አጠቃቀም ከስልሴኔመ በጀት አጠቃቀም አንድ አይነት ሆኖ እንዲሰራ እና
ለድጋፍ አሰጣጥ የሚጠቅሙትን መሣሪያዎች አጠቃቀም አቅም ለመገንባት ያስፈልጋል፡፡
የልሴኔመ 4 የቅድመ ማስጠንቀቅያ መረጃ በኢትዮጵያ ዉስጥ በዋነኝነት ጥቅም ላይ ይውላል፡፡ በቅርብ
የተሰራው የአደጋ ስጋት መከላከያ ሰነድ ከቅድመ ማስጠንቀቅያና ምላሽ ዳይሬክቶሬት ሁሉን አቀፍ የሆነዉን
የተቀናጀ ማሕበረሰብ ጥበቃና የአደጋ ስጋቶችን መከላከያ ስርዐቶችን ለማደራጀት ይጠቅማል፡፡ የዚህም ሂደት
ውጤት ግልፅ የሆኑ መረጃዎችን ለመሰብሰብና ለመተንተን፣ የመጠባበቂያ በጀትን በተለያየ ደረጃ ለመጠቀም
ያስችላል፡፡ ይህን በመካሄድ ላይ ያለው የመንግስት የቅድመ ማስጠንቀቂያና የአደጋ ስጋቶችን መከታተያ ዘዴ
ነው፡፡ ይህም የሚያጠቃልለው፡-
• የቅድም ማስጠንቀቂያ መረጃ አሰባሰብ ስራዎችን የአደጋ መከላከል ስራዎች በተጠናከረ ሁኔታ እንዲሰራ
ድጋፍ ያደርጋል ፡፡ ለዚህም በወረዳና በክልል ደረጃዎች አቅምን ለመገንባት የሚያስፈልግ የገንዘብ
ድጋፍ ያደርጋል፣
• በወረዳና በክልል ደረጃ ለአደጋ ጊዜ የሚሰጡ ድጋፎችን አጀማመር እያደራጀ ስራ ላይ ማዋልን፣
• ወሳኝ የሆኑ ደረጃዎችነ ተንትኖ በወረዳና በክልል ደረጃ ውሳኔ ሰጪዎች የመተንተን አቅምን ይገነባል፡፡
ይህም አግባብ ያለው ውሳኔ በወቅቱ ለመወስን ያስችላል ፡፡
25
8.5. የአቅም ግንባታ ስልት
ዕቅዱ በኢትዮጵያ መንግስት የልሴኔመ ፈፃሚ ተቋማት የሚከናወን ሲሆን መንግስታዊ ባልሆኑ ፈፃሚ
አካላትና ለአቅም ግንባታ የሚያስፈልገዉን የገንዘብ ድጋፍ በሚያደርጉ አጋሮች ይከናወናል፡፡ የአቅም ግንባታን
የሚያደርጉ ማዕከላት የአቅም ግንባታ ስራ ብቻ ይሰራሉ እንጂ በልሴኔመ አተገባበር ዉስጥ ድርሻ የላቸዉም፡፡
26
28