You are on page 1of 42

ለፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን

አዲስ አበባ

ጉዳዩ፡- ሰነድ መላክን ይመለከታል፡፡

በቀን ግንቦት 08 2011 በቁጥር ሲሠኮ/ኮቢ/324 ከኮሚሽናችሁ በተጻፈው ደብዳቤ መሰረት በሀገር አቀፍ ደረጃ
በተማከል ሁኔታ ሲተገበር የነበረው የለውጥ ስራ አመራር ተቋም ተኮር ለማድረግ እንዲቻል የለውጥ
ፕሮጀክት ፕሮፖዛል አዘጋጅተን እንድናቀርብ መጠየቃችሁ ይታወሳል፡፡

በዚህ መሰረት በሚኒስቴር መስሪያ ቤታችን የለውጥ ሥራ አመራርን በተመለከተ የቴክኒክ ቡድን በማደራጀት
ጥናት ያስጠና ሲሆን ጥናቱን ተከትሎ የለውጥ ስራ አመራር ማስተገበሪያ መመሪያ አዘጋጅቷል፡፡

በመሆኑም የሚኒስቴር መ/ቤቱ ሥራ አመራር የዳሰሳ ጥናት ሰነድ ገፅ፣ የለውጥ ስራ አመራር
ማስተገበሪያ የተሻሻለ መመሪያ ገፅ እና የለውጥ ፕሮጀክት ፕሮፖዛል ገፅ ከዚህ ሸኝ ደብዳቤ
ጋር አባሪ አድርገን የላክን መሆኑን እገልጻለን፡፡

ከሠላምታ ጋር

ግልባጭ

 ለክቡር ሚኒስትር ዲኤታ/ከተማ ፕላንና መሬት ዘርፍ/


 ለክቡር ሚኒስትር ዲኤታ/ከተማ ልማትና ቤቶች ዘርፍ/
 ለክቡር ሚኒስትር ዲኤታ/ኮንስትራክሽን ዘርፍ/
 ለለውጥና መልካም አስተዳደር ዳይሬክቶሬት

ከ/ል/ኮ/ሚ/ር

i|P a g e
የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር

የለውጥ ሥራ አመራር ሥርዓት አተገባበር የተሻሻለ መመሪያ

ቁጥር 10

ጥር 2012 ዓ.ም

አዲስ አበባ

ii | P a g e
ማውጫ
መግቢያ........................................................................................................................................................1
ክፍል አንድ፡..................................................................................................................................................2
1. አጠቃላይ ሁኔታዎች.............................................................................................................................2
1.1. አጭር ርዕስ....................................................................................................................................2
1.2. ትርጓሜ........................................................................................................................................2
1.3. የጾታ አገላለጽ..............................................................................................................................6
1.4. የተፈጻሚነት ወሰን.......................................................................................................................6
ክፍል ሁለት...................................................................................................................................................7
2. የለውጥ ሥራ አመራር ሥርዓት አተገባበር መመሪያ ዓላማ እና መርህ...................................................................7
2.1. የመመሪያው ዓላማ...........................................................................................................................7
2.2. የመመሪያው አተገባበር መርህ..............................................................................................................7
ክፍል ሦስት...................................................................................................................................................9
3. የለውጥ ሥራ አመራር ሥርዓቱ አበይት ሥራዎች...............................................................................................9
3.1. ዕቅድ ዝግጅት.................................................................................................................................9
3.2. የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት..................................................................................................................12
3.3. የክትትል፣ ድጋፍና ሱፐርቪዥን ስርዓት................................................................................................14
3.4. የግምገማ ስርዓት............................................................................................................................15
3.5. የግብረ መልስ አሰጣጥ ስርዓት...........................................................................................................16
3.6. የአፈጻጸም ምዘና............................................................................................................................16
1) የተቋም አፈጻጸም ምዘና.......................................................................................................................16
2) የስራ ክፍሎች አፈጻጸም ምዘና................................................................................................................17
3) የቢሮ/ጽ/ቤት ሀላፊ/የዳይሬክተር/ቡድን መሪ የአፈጻጸም ምዘና.........................................................................19
4) የሰራተኛ አፈጻጸም ምዘና................................................................................................................19
5) የክልልና ከተማ አስተዳደሮች ምዘናን በተመለከተ................................................................................20
3.7. የውጤት ተኮር ሥራ አፈጻጸም ምዘና ደረጃ አሰጣጥ.................................................................................21
3.8. ድህረ ምዘና ተግባራት.....................................................................................................................22
3.9. ስለ ቅሬታ አቀራረብ........................................................................................................................22
ክፍል አራት.................................................................................................................................................23
4. የለውጥ ሰራዊቱ የመንግስት መዋቅር አደረጃጀት ሁኔታ.....................................................................................23
ክፍል አምስት...............................................................................................................................................24
5. የልዩ ልዩ አካላት ተግባርና ኃላፊነት.............................................................................................................24
5.1. የበላይ ኃላፊ ተግባርና ኃላፊነት..............................................................................................................24
5.2. የሚኒስትሩ ጽ/ቤት ተግባርና ኃላፊነት.......................................................................................................25

iii | P a g e
5.3. የዕቅድና ፕሮግራም በጀት ቢሮ ተግባርና ኃላፊነት........................................................................................25
5.4. የለውጥና የሰው ሀብት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ተግባርና ኃላፊነት....................................................................26
5.5. የሰው ኃብት ልማት እና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ተግባርና ኃላፊነት..................................................................27
5.6. የስራ ክፍል ሀላፊዎችና ተግባርና ኃላፊነት..................................................................................................27
5.7. የቡድን መሪዎች ተግባርና ኃላፊነት.........................................................................................................28
5.8. የሠራተኛ ተግባርና ኃላፊነት..................................................................................................................28
ክፍል ስድስት...............................................................................................................................................29
ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች........................................................................................................................................29
የተሻሩ ህጎች.................................................................................................................................................30
መመሪያውን አለመፈጸም የሚያስከትለው ተጠያቂነት...............................................................................................30
መመሪያውን ስለማሻሻል..................................................................................................................................30
መመሪያው የሚፀናበት ጊዜ...............................................................................................................................30

iv | P a g e
መግቢያ

የከተማ ዘርፍን የሚመራው ተቋም በተለያየ ጊዜያት የተለያዩ ስያሜዎችን አስተናግዷል፡፡ ከእነዚህም

መካከል የከተማና ቤቶች ሚኒስቴር፣ የሥራና ከተማ ልማት ሚኒስቴር፣ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን

ሚኒስቴር፣ የከተማ ልማት፣ ቤቶችና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር እና የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር

ይገኙበታል፡፡ የተሰጡት ሥልጣንና ተግባራትም በተወሰነ ደረጃ ይቀያየሩ የነበረ ሲሆን በየወቅቱ በተሰጠው

ስልጣንና ሃላፊነትም የዘርፉን ፖሊሲዎች፣ ስትራቴጂዎች፣ ፕሮግራሞች፣ ፕሮጀክቶችና ዕቅዶች በመቅረጽ

በርካታ እንቅስቃሴዎችን ሲያካሂድ ቆይቷል፡፡ በኢፌዴሪ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአስፈፃሚ አካላትን

ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 1097/2011 የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስቴር

ከኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ጋር እንዲዋሃድ በማድረግ “የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር” በሚል

የተሰየመ ሲሆን ከስልጣንና ተግባር አኳያም የዘርፉን ፖሊሲዎች፣ ስትራቴጂዎች እንዲቀርጽ፣ እንዲመራ፣

እንዲያስተባብር፣ እና እንዲከታተል ኃላፊነት ተሰጥቶታል፡፡

የተሰጡትን ተግባርና ኃላፊነት ለመወጣትም የክትትልና ግምገማ ስርዓት ዘርግቶ ሲተገብር ቆይቷል፡፡

የክትትልና ግምገማ ስርዓቱም ከሚሰጠው ተግባርና ሃላፊነት ጋር የተሳሰረ ነው፡፡ በተለይም ከ 2003 በጀት

ዓመት ጀምሮ በፌዴራል፣ በክልሎች፣ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና በድሬዳዋ አስተዳደር ከሚገኙ

የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ዘርፍ ተቋማት ጋር መመሪያ በማዘጋጀት የዕቅድ ማናበብ፣ ክትትል፣ ምዘና፣

ግምገማና ግብረመልስ እንዲሁም የሱፐርቪዥን ስዎችን ሲያከናውን ቆይቷል፡፡

ይሁን እንጂ የዘርፉ ስራዎች በክትትልና ግምገማ ስርዓቱ የጠራና ተናባቢ ዕቅድ ያለማዘጋጀት፣ የስራ

ድግግሞሽ መኖር፣ የማበረታቻ ስርዓት አለመኖር፣ የዕቅድና በጀት ትስስር አለመኖር፣ የለውጥ መሳርያዎች

አተገባበር ላይ ክፍተት መስተዋሉ፣ የቡድን አደረጃጀቶች ውጤታማ አለመሆን፣ የአፈጻጸም ምዘና ውጤትና

በተጨባጭ ስራዎች ያሉበት ደረጃ ተመሳሳይ አለመሆን፣ የመረጃ ልውውጥ ሥርዓቱ እስከታችኛው

የመንግስት መዋቅር ተናባቢ አለመሆን፣ ምልዑነትና ወቅታዊ ያለመሆን እንዲሁም የተጠያቂነት፣ ግልጽነትና

አሳታፊነት ክፍተቶች ተስተውለዋል፡፡ በተጨማሪም በአገር አቀፍ ደረጃ ሲተገበር የነበረውን የተማከለ

የለውጥ ሥራ አመራር አተገባበር ስርዓት ተቋማዊ ለማድረግ እንዲሁም በተቋሙ እየተተገበሩ የነበሩ

የተለያዩ የአሰራር መመሪያዎችና ማንዋሎች መፈተሸና በማጣጣም አንድ ወጥ መመሪያ ማዘጋጀት ተገቢ

ሆኖ ተገኝቷል፡፡

1|P a g e
መመሪያው በክፍል አንድ አጠቃላይ ሁኔታዎችን፣ በክፍል ሁለት የለውጥ ስራ አተገባበር መመሪያ ዓላማ እና
መርህን፣ በክፍል ሶስት የለውጥ ስራ አመራር አበይት ስራዎችን፣በክፍል አራት የለውጥ ሰራዊት የመንግስት
መዋቅር አደረጃጀት ሁኔታን፣ በክፍል አምስት የልዩ ልዩ አካላት ተግባርና ሀላፊነት እንዲሁም በክፍል ስድስት
ልዩ ልዩ ድንጋጌዎችን አካቷል፡፡

ክፍል አንድ፡

1. አጠቃላይ ሁኔታዎች

1.1. አጭር ርዕስ

ይህ መመሪያ “የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የለውጥ ሥራ አመራር ሥርዓት አተገባበር የተሻሻለ

መመሪያ ቁጥር ------------ 2012“ ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡

1.2. ትርጓሜ

የቃሉ አገባብ የተለየ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ መመሪያ ውስጥ፡-

1.2.1. ‘‘ሚኒስቴር“ ማለት የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ነው፡፡


1.2.2. "ሚኒስትር" ማለት የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ሚኒስትር ወይም ሚኒስትር ዴኤታዎች ማለት ነው፣
1.2.3. "የበላይ አመራር"፡- ማለት ሚኒስትር እና ሚኒስትር ዴኤታዎችን ማለት ነው
1.2.4. ‘‘ክልል“ ማለት በህገ መንግስቱ አንቀጽ 47 መሰረት የተቋቋመ የሀገሪቱ ፌዴራላዊ መንግስት አካል ነው፡፡

1.2.5. ‘‘የከተማ አስተዳደር“ ማለት አዲስ አበባና ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደሮች ለማለት ነው፡፡

1.2.6. ‘‘ተጠሪ ተቋማት“ ማለት በፌዴራል አስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን የወጣው አዋጅ ቁጥር

1097/2010 መሠረት ለሚኒስቴር መ/ቤቱ ተጠሪ የሆኑ ተቋማትን የሚያካተትት ነው፣

1.2.7. “ሥራ ክፍል” ማለት በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሚገኙ ቢሮዎች፣ ጽ/ቤቶች እና ዳይሬክቶሬቶች ማለት ነው፡፡
1.2.8. “አመራር” ማለት በሚኒስቴር መ/ቤቱ መዋቅራዊ አደረጃጀት መሠረት በተለያየ የዕርከን ደረጃ የሚገኙ
አስፈፃሚዎችን/ፈፃሚዎችን አስተባብሮ ወደ ግብ ሥኬት ለመምራት የተደራጀ በሥሩ የታቀፉ
አስፈፃሚዎችን/ፈፃሚዎችን የያዘ የተጠያቂነትና የውሳኔ ሰጪነት ኃላፊነት የተሰጠው ከከፍተኛ እስከ
ታችኛው የአመራር ዕርከን ድረስ ያለውን የአመራር ስብስብ ያካትታል፣
1.2.9. “የሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ማኔጅመንት ኮሚቴ”፡- ማለት ሚኒስትር፣ ሚኒስትር ዴኤታዎች፣ በሚኒስትር መስሪያ
ቤቱ ዉስጥ የሚገኙ የቢሮ ኃላፊዎች፣ የጽ/ቤት ኃላፊዎች እና የሴቶች፣ ህጻናትና ወጣቶች፣ የህዝብ ግንኙነት፣
ኦዲት፣ የህግ አገልግሎት፣ የዉሳኔ አፈጻጸም ክትትልና ድጋፍ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሚገኙበት መድረክ
ነው፡፡

2|P a g e
1.2.10. ‘‘አብይ ኮሚቴ“ ማለት በሚኒስትር ዲኤታ ደረጃ የሚመራ ከየዘርፉ የተውጣጡ የአመራር አካላት
ያካተተና ለሚቋቋመው የቴክኒክ ኮሚቴ አስፈላጊ የሆኑ ውሳኔዎችን በመስጠት የሚደግፍና
የሚያመቻች አካል ነው፡፡
1.2.11. ‘‘የምዘና ቡድን“ ማለት ስለዘርፉ ሥራዎች በቂ እውቀት ክህሎት ያላቸው ኃላፊዎችንና
ባለሙዎችን የያዘ በሚኒስቴር መ/ቤቱ ተጠሪ ተቋማትና የሥራ ክፍሎች፣ በክልሎችና ከተማ
አስተዳደሮች በአካል በመገኘት የእቅድ አፈፃፀም ለመመዝንና ድጋፍ ለመስጠት የተዋቀረ ቡድን
ነው፡፡
1.2.12. ‘‘ሴክተር ተቋማት‘‘ ማለት በፌዴራል፣ በክልሎች፣ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና ድሬዳዋ
አስተዳደር የሚገኙ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ዘርፍ ተቋማት ማለት ነው፡፡
1.2.13. “የተቋም መካከለኛ አመራር” ማለት በሚኒስቴር መ/ቤቱ የስልጣን ተዋረድ መሠረት ከበላይ አመራር ቀጥሎ ባለው
አደረጃጀት ውስጥ   በሙያው   አመራር   የሚሰጥ   በሜሪት   የተመደቡ ቢሮ ኃላፊዎችንና ዳይሬክተሮችን
የሚያጠቃልል አመራር ነው፣
1.2.14. “የቢሮ/ጽ/ቤት ኃላፊዎች” ማለት በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር መዋቅራዊ አደረጃጀት
መሠረት ተጠሪነታቸው ለሚኒስትሩ ወይም ለሚኒስቴር ዴኤታዎች የሆኑ ኃላፊዎችን ነው፣
1.2.15. "ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር” ማለት በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር መዋቅራዊ አደረጃጀት
መሠረት በመካከለኛ የአመራር ደረጃ የሚገኙና በዳይሬክተሩ ስር ያሉ ባለሙያዎችን የሚመሩ ተጠሪነታቸው
ለቢሮ ኃላፊዎች ወይም በቀጥታ ለሚኒስትሩ የሆኑ ዳይሬክተሮችን ነው፣
1.2.16. “የቡድን መሪ” ማለት በሚኒስቴር መ/ቤቱ የስልጣን ተዋረድ ከዳይሬክተር ቀጥሎ ያለውን አደረጃጀት የሚመራ በሜሪት
የተመደበ ታችኛው አመራር ነው፡፡
1.2.17. ‘‘የምዘና ቡድን“ ማለት ስለዘርፉ ሥራዎች በቂ እውቀት ክህሎት ያላቸው ኃላፊዎችንና ባለሙዎችን የያዘ

በሚኒስቴር መ/ቤቱ ተጠሪ ተቋማትና የሥራ ክፍሎች፣ በክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች በአካል በመገኘት

የእቅድ አፈፃፀም ለመመዘንና ድጋፍ ለመስጠት የተዋቀረ ቡድን ነው፡፡

1.2.18. ‘‘የሴክተር ጉባኤ‘‘ ማለት በፌዴራል፣ በክልሎች፣ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና ድሬዳዋ አስተዳደር

የሚገኙ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ዘርፍ ተቋማት መካከል የሚካሄድ የወቅታዊ አፈጻጸም ግምገማና

የምክክር መድረክ ነው፣

1.2.19. ‘‘ምዘና“ ማለት ክልሎች፣ ከተማ አስተዳደሮች፣ ተጠሪ ተቋማትና የሥራ ክፍሎች ዕቅድ በተናበባቸው

የውጤት ተኮር ሥራዎች አፈጻጸም ከዕቅድ አንጻር መመዘን ማለት ነው፣

1.2.20. ‘‘ደረጃ“ ማለት በዚህ መመሪያ መሰረት የተካተቱና የተመዘኑ ክልሎች፣ ከተማ አስተዳደሮች፣ ተጠሪ

ተቋማትና የሥራ ክፍሎች የእቅድ አፈጻጸም የሚያሳይ ነው፣

1.2.21. ‘‘ግብረ-መልስ“ ማለት ክልሎች፣ ከተማ አስተዳደሮች፣ ተጠሪ ተቋማትና የሥራ ክፍሎች የዕቅድ አፈጻጸም

ምዘና ተካሂዶ የምዘና ቡድኑ በሚያቀርበው ውጤት እና መጨረሻ ላይ ውሳኔ በሚሰጠው አካል በጸደቀው

3|P a g e
የተጠቃለለ ውጤት መሠረት በቃል እና በፅሑፍ፣ የሚሰጥ የሥራ አፈፃፀም ምላሽ ወይም ማበረታቻ ሆኖ

እንደ አስፈላጊነቱ ከእነዚህ ውስጥ በከፊል ወይም ሁሉንም ሊያካተት ይችላል፡፡

1.2.22. “የግብ አፈፃፀም ደረጃ“ (Performance level) በየፕሮጀክቱ/በየእቅዱ የተቀመጡ ግቦች የአፈፃፀም

ውጤት ደረጃ በመቶኛ የሚያመላክት ነው፡፡

1.2.23. “ዕቅድ„፡- ማለት አንድ ተቋም የተቋቋመበትን ዓላማ ለማሳካት እንዲችል ያለበትን የመፈጸምና የማስፈጸም

አቅም (ሰብዓዊ፣ ቁሳዊና የፋይናንስ ሀብቶች) ባገናዘበ ሁኔታ ውጤት-ተኮር/አመልካች ሥራዎቹን በቅደም

ተከተል የሚተልምበት የአሰራር ስርዓትና ሂደት ነው፡፡

1.2.24. “ክትትል„፡-ፕሮግራሞች/ፕሮጀክቶች/ተግባራት አተገባበር በተቀመጠላቸው የጌዜ ሰሌዳና ግብዓት (ገንዘብ፣

ቁሳቁስ፣ የሰውሃይል…) መሰረት እየተከናወኑ ሥለመሆናቸው የምናረጋግጥበት ተከታታይ የሥራ ሂደት

ሲሆን ይህም ሪፖርቶችን በመቀበል፣ በቢሮ የተሰሩ የወረቀት ሥራዎችን (Desk Review) በማየት፣ በመስክ

ምልከታ ወይም ተጠቃሚዎችን በመጠየቅ ሊከናወን የሚችል ነው፡፡ ትኩረቱም በአተገባበር ሂደት

የሚያጋጥሙና የተለመዱ እንቅፋቶችን (የቁሳቁስ፣ የገንዘብ፣ የክህሎት…) መፍትሄ እየሰጡ ስራው

እንዲፋጠን ማድረግ ነው፡፡

1.2.25. “የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት„፡- ተቋማት/የሥራ ክፍሎች የሥራቸውን ክንውኖች፣ ግኝቶችና አጠቃላይ

አፈጻጸሞች ሊሰሩ ካቀዱት ጋር በማነጻጸር ተንትነው ለሚመለከታቸው አካላት በጽሁፍ/በምስል ወይም

በመድረክ የማቅረብ ሂደት ሲሆን ይህንኑ መሰረት በማድረግም ፈጻሚዎች፣ አስፈጻሚዎችና ባለድርሻ

አካላት/ተጠቃሚዎች በአተገባበር ወቅት ያጋጠሙ ችግሮችንና የተገኙ ውጤቶችን ለመገምገም የሚረዳ

መረጃ ነው፡፡

1.2.26. “ሱፐርቪዥን„ በትግበራ ላይ ላሉት አላማ ፈጻሚዎች የፕሮጀክቱን/ ዕቅዱን አተገባበር የሱፐርቪዥን ቡድኑ

በመስክ በመመልከት ወይም ቀደም ሲል በሪፖርት/በክትትል ወቅት የተሰበሰቡ መረጃዎችን መሰረት

በማድረግ የአፈጻጸም የመረጃዎችን ተአማኒነትና ተቀባይነት የማረጋገጥበት ተግባርና ሙያዊ የማሻሻያ

አስተያየት ነው፡፡

1.2.27. “ግምገማ„ የፕሮግራሙ/ፕሮጀክቱ/ተግባሩ አፈጻጸም በትግበራው ጅማሮ፣ አጋማሽ ወይም መጨረሻ

ወቅቶች ክትትልንና ዕቅድን መሰረት በማድረግ የሚከናወን የአሰራር ሂደት ሲሆን በጭብጥም ስለዕቅዱ

ጠቃሚነት (Relevance)፣ ስለአፈጻጸሙ ቅልጥፍናና ውጤታማነት (Efficiency and Effectiveness)፣

በተጠቃሚዎች ዘንድ ስለፈጠረው ተጽዕኖና ፋይዳ (Outcome/Impact) እንዲሁም ስለ ስራው ቀጣይነትና

ተከታታይነቱ (Sustainability) ያተኮረ ነው፡፡

1.2.28. “የዕቅድ ግምገማ መድረክ” ማለት የዘርፉን የመካከለኛ ዘመን እቅድ በላቀ ደረጃ ለማሳካት የስራ ክፍሎችን

ወቅታዊ የአፈፃፀም ሁኔታ ለመገምገም የሚዘጋጅና በበላይ አመራሩ የሚመራ የግምገማ መድረክ ነው፡፡

4|P a g e
1.2.29. “መካከለኛ ዘመን ዕቅድ” ማለት አንድ መስሪያ ቤት /የስራ ክፍል ወደፊት ባሉ ከ 3 - 5 ዓመት ጊዜያት

ሊያከናውናቸው ያሰባቸውን ዋና ዋና ስራዎችና የአፈፃፀም አቅጣጫዎች የያዘ የመካከለኛ ጊዜ ዕቅድ ነው፡፡

1.2.30. “ግብ” ማለት አንድ የሥራ ክፍል እንዲያሳካ ወደሚፈልገው ዓላማ ለማሳካት ሊያስመዘግብ የሚገባውን

ውጤት የሚያመላክት የዕቅድ አካል ነው፡፡

1.2.31. “ተግባር” ማለት አንድን ግብ ለማሳካት እንዲያስችሉ ተደርገው የተቀረፁና በቅደም ተከተል የሚከናወኑ

ስራዎች ማለት ነው፡፡

1.2.32. “ክብደት” ማለት ስራዎች በሚወስዱት የዕውቀት፣ የገንዘብና ሌሎች ግብዓቶች እንዲሁም በስራዎቹ

ውስብስብነት አንፃር ደረጃ ለማውጣትና ለመለየት የሚሰጥ ነጥብ ነው፡፡

1.2.33. "የዘረፈ ብዙ ጉዳዩች” ማለት በልማትና በአቅም ግንባታ ስራዎች ሴቶች፣ ወጣቶች፣ ህጻናት፣ አካል

ጉዳተኞችንና አረጋውያንን ተሳታፊ፣ ፍትሀዊ ተጠቃሚና ተደራሽ ለማድረግ እንዲሁም የአከባቢ

እንክብካቤና ጥበቃ ጋር በተያያዙ የሚሰሩ ስራዎች ማለት ነው፡፡

1.2.34. "ሴክተር" ማለት የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ስራዎችን በባለቤትነት የሚፈጽሙና የሚያስፈጽሙ

ተቋማትን ያካትታል፡፡

1.2.35. "ዴስክ ሪቪው" ማለት በቢሮ ውስጥ የተከናወኑ ስራዎችን በአካል በመገኘት ማረጋገጥና ክትትል ማድረግ

ነው፡፡
1.2.36. “የመንግስት መዋቅር” ማለት በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ   ውስጥ የሚገኙና የተቋሙ የሠራዊት አካል ሆነው
ከከፍተኛ አመራር እስከ  ሰራተኞች ደረስ  እንደ አንድ አካል  የሚዋሃዱበትና የተቋም  ተልዕኮን
በጋራ ለማሳካት የሚንቀሳቀሱበት አደረጃጀት ማለት ነው፡፡
1.2.37. “የህዝብ አደረጃጀት” ማለት የዜጋውን ጥቅም ለማስጠበቅ ህዝብን ወክሎ ከተቋማት ጋራ የሚሰራ በተለያየ
መልኩ የተደራጀ የህዝብ አካል ማለት ነው፣
1.2.38. “የለውጥ ኃይል” በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ዘርፍ ውስጥ ተለይቶ የተሰጠውን ተልዕኮ ለማሳካት
የሚያስችለውን የጋራ ዓላማና አሰራር እንዲሁም አመላካከት፣ ክህሎትና ዕውቀትን በመያዝ በተደራጀና
በተቀናጀ መንገድ ለለውጥ በቁርጠኝነት የተነሳ የመንግሥትና የህዝብ የተደራጀ ኃይል ማለት ነው፡፡
1.2.39. “የተሻለ ሰራተኛ” በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ  ውስጥ ካሉ የሰራዊቱ አካላት ውስጥ በአመለካከቱ፣ በክህሎቱ፣
በዕውቀቱ፣ በሥነ-ምግባሩ፣ በሥራ አፈፃፀሙ፣ በፀረ ኪራይ ሰብሳቢነት አቋሙና ትግሉ፣ በተባባሪነቱና በሥራ
ተነሳሽነቱ ወዘተ. በተግባር ውጤቱ ጎላ ብሎ በአርአያነት የሚታይ የለውጥ ሰራዊት አባል ነው፡፡
1.2.40. “ቡድን” ማለት በዳይሬክቶሬት ወይም ከዚያ በታች ባሉት የሚኒስቴር መ/ቤቱ አደረጃጀቶች ውስጥ የሚገኙ
ፈጻሚዎች በተመሳሳይ ወይም በተዛማጅ ተግባራት ዙሪያ የሚደራጁበትና በምርጥ ወይም በአንድ የተሻለ
ሰራተኛ አስተባባሪነት የሚመራ የጋራ ተልዕኮ ያለው አደረጃጀት ነው፡፡
1.2.41. “ሌሎች ተገልጋዮች” የሚባሉት የህዝብ አደረጃጀት ያልሆኑ ነገር ግን ከሚኒስቴር መ/ቤቱ አገልግሎት
የሚያገኙ ግለሰቦች፣ የግል እና የመንግስት ተቋማት ናቸው፡፡

5|P a g e
1.2.42. “ሰራተኛ” ማለት በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ በቋሚነት ተቀጥሮ የሚሠራ ሰው ነው፡፡ ሆኖም ሚኒስትሩን፣
ሚኒስትር ዴኤታዎችን፣ ዳይሬክተሮችን፣ እንዲሁም በተመሣሣይ ደረጃና ከዚያ በላይ ያሉ የሥራ ኃላፊዎችን
ይጨምራል፣
1.2.43. “ባለሙያ” ማለት በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ውስጥ በቋሚነት ተቀጥረው በሙያቸው የሚሠሩ ሰዎችን
የሚያካትት ነው፡፡

1.3. የጾታ አገላለጽ


በዚህ መመሪያ ውስጥ ማንኛውም በወንድ ፆታ የተገለጸው የሴት ፆታንም ያካትታል፤

1.4. የተፈጻሚነት ወሰን


ይህ መመሪያ በከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር መስሪያ ቤት ስራ ክፍሎች ላይ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡
እንዲሁም ተጠሪ ተቋማት ይህንን መመሪያ በመውሰድ ወደ ራሳቸው ነባራዊ ሁኔታ በመጣጣም መተግበር
ይችላሉ፡፡

6|P a g e
ክፍል ሁለት

2. የለውጥ ሥራ አመራር ሥርዓት አተገባበር መመሪያ ዓላማ እና መርህ

2.1. የመመሪያው ዓላማ

የዚህ መመሪያ ዓላማ የዘርፉ ስራዎች በክትትልና ግምገማ ስርዓቱ የጠራና ተናባቢ ዕቅድ ለማዘጋጀት፣

የስራ ድግግሞሽ ለመቀነስ፣ የማበረታቻ ስርዓት ለማጠናከር፣ የአፈጻጸም ምዘና ውጤትና በተጨባጭ

ስራዎች ያሉበት ደረጃ ለማወቅ፣ የለውጥ መሳሪያዎች ቅንጅታዊ አተገባበርን ውጤታማ ለመድረግ፣

የቡድን አደረጃጀትን ለማጠናከር፣ የመረጃ ልውውጥ ሥርዓቱ እስከታችኛው የመንግስት መዋቅር ተናባቢ

ለማድረግ እንዲሁም የተጠያቂነት፣ የግልጸኝነትና የአሳታፊነት ክፍተቶች ለመድፈን፣ በዘርፉ ተቋማት


አፈጻጸም ወቅት የተሻሉ መልካም ተሞክሮዎችን በመለየት ወደ ሌሎች ተቋማት ለማስፋትና ድጋፍ
ለሚያስፈልጋቸው ድጋፍ ለመስጠት፣ በአገር አቀፍ ደረጃ ሲተገበር የነበረውን የተማከለ የለውጥ ሥራ

አመራር አተገባበር ስርዓት ተቋማዊ ለማድረግ እንዲሁም በተቋሙ እየተተገበሩ የነበሩ የተለያዩ የአሰራር

መመሪያዎችና ማንዋሎች መፈተሸና በማጣጣም አንድ ወጥ መመሪያ ማዘጋጀት ነው፡፡

2.2. የመመሪያው አተገባበር መርሆዎች

1. የተቋሙ ስትራቴጂያዊ ግቦች ከአገራዊ ፖሊሲና ስትራቴጂዎች የመነጩ መሆን አለባቸው፤


2. የተቋሙ የዕቅድ ዝግጅት፣ የአፈጻጸም ግምገማና ምዘና የውጤት ተኮር ሥርዓትን የተከተለ
መሆን አለበት፣
3. የስራ አፈጻጸም ግምገማና ምዘና በተቋም፣ በስራ ክፍልና በፈጻሚ ደረጃ በተናበበና ሚዛናዊ
በሆነ መልኩ መከናወን አለበት፣
4. በተቋሙ አመራርና መላው ሠራተኛ መካከል ስለውጤት ተኮር ሥርዓት በቂ ግንዛቤና የጋራ
መግባባት መፈጠር አለበት፤
5. በተቋሙ የውጤት ተኮር ዕቅድ ዝግጅትና የአፈፃፀም ግምገማ የህዝብ አደረጃጀት ሙሉ
ተሳትፎ መኖር አለበት፤
6. የውጤት ተኮር አፈጻጸም ክትትልና ግምገማ በአንድ የተወሰነ ወቅት ብቻ የሚከናወን
ሳይሆን ከዕቅድ ዝግጅት ምዕራፍ ጀምሮ በትግበራና ማጠቃለያ ምዕራፍ ውስጥ በለውጥ
ሠራዊት አግባብ በተከታታይ የሚከናወን የዕለት ተዕለት ተግባር ሊሆን ይገባል፣
7. የውጤት ተኮር ዕቅድ አፈጻጸም መረጃ በአግባቡ መያዝ አለበት፤
8. የውጤት ተኮር አፈጻጸም ምዘና ቀድሞ ስምምነት የተደረሰባቸውን ግቦች፣ መለኪያዎችና
ዒላማዎች በተግባር አፈጻጸም ከተገኙ ውጤቶች ጋር በማነጻጸር የሚከናወን ይሆናል፣

7|P a g e
9. የዘርፉን የውጤት ተኮር ዕቅድ ላይ የተቀመጡ ግቦች በላቀ ደረጃ ለማስፈጸም ቅንነተ፣ ግልጸኝነትና
ተጠያቂነት ያለው አሰራር መከተል፣
10. ተአማኒነት፣ ወቅታዊነትና ተደራሽነት ያለው መረጃ ላይ የተመሰረተ የዕቅድ ዝግጅት፣ የዕቅድ አፈጻጸም
ሪፖርት፣ ክትትል፣ ምዘና፣ ግምገማና ግብረመልስ ሥርዓት መከተል፣
11. የተቀናጀ፣ የተደራጀ፣ ተመጋጋቢና ተደጋጋፊ አሰራርን መከተል፣ እና ለጋራ ውጤት/ስኬት የመስራት
ባህልን ማጎልበት፣
12. የለውጥ መሳሪያዎች አቀናጅቶ መተግበር ናቸው፡፡

ክፍል ሦስት

3. የለውጥ ሥራ አመራር ሥርዓቱ አበይት ሥራዎች

3.1. ዕቅድ ዝግጅት


1) የመንግስት ፖሊሲና ስትራቴጂዎችን፣ አዳዲስ የመንግስት አቅጣጫዎችንና ሌሎች ነባራዊ

ሁኔታዎችን ከግምት ባስገባ መልኩ የሴክተር መነሻ የመካከለኛ ዘመን ዕቅድ በሚጠናቀቀው የዕቅድ

ዘመን መጨረሻ ላይ በዕቅድ እና ፕሮግራም በጀት ቢሮ ተዘጋጅቶ በአብይ ኮሚቴው ይተቻል፣

አቅጣጫም ይሰጥበታል፡፡

2) የሴክተሩ የመካከለኛ ዘመን ዕቅድ በሚመለከታቸው አካላት ከመጽደቁ በፊትም የባለድርሻና አጋር

አካላትን በማሳተፍ ሀገራችን መድረስ የምትፈልገውን ራዕይ እንዲሁም የዕቅድ ማስፈጸሚያ ቁልፍ

መሳሪያና የማስፈጸም አቅም የሆኑትን የአሰራር፣ የአደረጃጀት፣ የሰው ሃብት፣ የፋይናንስ እና የህግ

ማዕቀፎችን መሰረት አድርጎ የተዘጋጀና ከዘርፉ ተቋማት ጋር የተናበበ መሆን ይኖርበታል፡፡

3) የሴክተሩ የመካከለኛ ዘመን የውጤት ተኮር ዕቅድ በዋነኛነት ከአራቱ ዕይታዎች አንጻር የተቀረጹ

ስትራቴጂያዊ ግቦችን፣ የስትራቴጂያዊ ግቦች መግለጫ፣ የግቦችን የምክንያትና ውጤት ትስስር

የሚያሳይ ስትራቴጂያዊ ማፕ፣ መለኪያዎችንና የመለኪያ መግለጫዎችን፣ መነሻዎችን፣

ዒላማዎችን፣ ስትራቴጂያዊ እርምጃዎችን፣ የአፈጻጸም ክትትል ግምገማ ስርዓትን እንዲሁም

የሚያስፈልግ በጀትን ማካተት አለበት፣

4) የመካከለኛ ዘመን ዕቅድ ከጸደቀ በኋላም በማሳተም ለሚመለከታቸው አካላት መሰራጨት አለበት።

5) የሴክተሩ ተቋማት ዓመታዊ ዕቅድ ሲዘጋጅና ሲናበብም የመካከለኛ ዘመን ዕቅድ መሰረት በማድረግ

ያለፈውን ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም፣ የስራ ክፍሉ እንዲያከናውን የተቋቋመበትን ዋና ዓላማ፣

የመንግስት ፖሊሲና ስትራቴጂዎችን፣ አዳዲስ የመንግስት አቅጣጫዎችንና ሌሎች ነባራዊ

ሁኔታዎችን ከግምት ባስገባ መልኩ ከውጤት ተኮር ዕይታዎች (የተገልጋይ ዕይታ፣ የፋይናንስ ዕይታ

የውስጥ አሰራር ዕይታ፣ የመማማርና ዕድገት ዕይታ) አንጻር የተቃኘ መሆን አለበት፡፡

8|P a g e
6) በዕቅድና ፕሮግራም በጀት ቢሮ በኩል የተቋሙ ስራ ክፍሎች ዓመታዊ ዕቅድ ሲያዘጋጅ ለአመራሩም

እና ለሠራተኛው በቂ ዕውቀትና ክህሎት ባላቸው አሰልጣኞች የዕቅድና ሪፖርት አዘገጃጀትን

በተመለከተ መሰረታዊ የሆነ ስልጠና ይሰጣል፣

7) የሥራ ክፍሎች ዓመታዊ እቅድ ሲታቀድ ወጥ በሆነ ቅጽ ሁሉንም የስራ ክፍሎች ስራዎችን ያካተተ

አንድ እቅድ ስርዓት ይዘረጋል፡፡ (በተቋሙ እየተዘጋጁ የሚገኙ ልዩ ልዩ ዕቅዶች በአንድ ዕቅድ ብቻ

ይጠቃለላሉ)፡፡

8) በየስራ ክፍሉ የውጤት ተኮር እይታዎች ሲቀረጹ እንደየ ስራ ክፍሉ ስራ ባህሪ መሆን ይኖርበታል፡፡

ማለትም የውጤት ተኮር ግቦችና ተግባራት ከመካከለኛው ዘመን ዕቅድ የተቀዱ እንዲሁም ከስራ

ክፍሉ ነባራዊ ሁኔታ አንጻር የሚጨመሩ ግቦችን ያካትታል፡፡ በዚህ እይታ ስር የሚጣሉ ግቦች ስርዓተ

ጸታን ባማከለ መልኩ መታቀድ ይኖርባቸዋል፡፡

9) የሌሎቹ ዕይታዎች (የመማማርና ዕድገት ዕይታ፣ የተገልጋይ ዕይታ እና የፋይናንስ ዕይታ) ስር

የሚቀረጹ ግቦች ደግሞ እንደየ ሥራ ክፍሉ ባህሪ የሚቀረጹ ሆነው የውስጥ አሰራር ዕይታ ላይ

የተቀረጹ ግቦችን ለማሳካት የሚያስችሉ መሆን ይኖርባቸውል፡፡

10) በሥራ ክፍሎች የተገልጋይ ዕይታ የሚታቀዱ ግቦች በለውጥ እና ሰው ሀብት ልማትና አስተዳደር

ቢሮ በኩል በሚላከው መነሻ ዕቅድ ሆኖ እንደየ ስራ ክፍሉ ባህሪ የሚታቀዱ ይሆናሉ፡፡ ከቢሮው

የሚላከው መነሻ ዕቅድ የተገልጋይ እርካታ ደረጃን የሚሳድጉ፣ የእርስ በርስ መስተጋብርን

የሚያሳድጉ፣ የዜጎች ቻርተር ስታንዳርድን ወዘተ… ማካተት ይኖርበታል፡፡

11) በሥራ ክፍሎች የመማማርና ዕድገት ዕይታ የሚታቀዱ ግቦች በለውጥ እና ሰው ሀብት ልማትና

አስተዳደር ቢሮ በኩል በሚላከው መነሻ ዕቅድ መሰረት እንደየ ስራ ክፍሉ ባህሪ የሚታቀድ ይሆናል፡፡

ከቢሮዎቹ የሚላኩት መነሻ ዕቅዶች የዘርፈ ብዙ ጉዳዮችን፣ የሰው ሀይልን አቅምን የሚያገልብቱ

(ማለትም የራስ ማብቃትን፣ የእርስ በርስ መማማርን፣ ስልጠናን)፣ የቡድን ስሜትን የሚፈጥሩ

ወዘተ… ማካተት ይኖርበታል፡፡

12) በየሥራ ክፍሎች የሚታቀዱ የፋይናንስ ዕይታ ግቦች በዕቅድ እና በፕሮግራም በጀት ቢሮ በኩል

በሚላከው መነሻ ዕቅድ መሰረት የሚታቀድ ይሆናል፡፡ የፋይናንስ ዕይታ ላይ የሚቀረጹ መነሻ ግቦች

የበጀት አጠቃቀምን የሚያሻሽሉ እንዲሁም የውስጥ አሰራር ግቦች ለማሳካት የሚያስችሉ መሆን

አለባቸው፡፡

13) ለአራቱ ዕይታዎች የሚሰጠው ክብደት በተመለከተ ድምሩ 100% ሆኖ ለተገልጋይ ዕይታ ከ 15%፣

ለፋይናንስ ዕይታ ከ 15%፣ ለውስጥ አሰራር ዕይታ 60% እና ለመማማርና እድገት ዕይታ ከ 10%

9|P a g e
ይሆናል፡፡ ለውስጥ አሰራር ከተሰጠው 60% የዘርፈ ብዙ ጉዳዮችን ታሳቢ ያደረጉ ግቦች በተግባር

ደረጃ ክብደት ይሰጣል፡፡

14) የግብ ክብደት አሰጣጥ የመካከለኛው ዘመን እቅድ ከማሳካት አንፃር ያለውን ድርሻ፣ ግቡን

ለማከናወን ከሚያስፈልግ ግብዓት፣ ከሚፈጀው ጊዜ፣ ከሚጠይቀው የሰው ሃይል እና ከስራው

ውስብስብነት አኳያ እንዲሁም ቀና የውድድር መንፈስ ለመፍጠርና ማበረታቻ ለመስጠት

በሚያስችል መልኩ መቀመጥ ይኖርበታል፡፡ በዚህም መሰረት ለውጤት አመላካች ተግባራት ቢያንስ

የግቡን 50 በመቶ ክብደት ይሰጣል እንዲሁም የስራ ክፍሎች አመታዊ እቅዶችን በሚያቅዱበት

ወቅት በመካከለኛው ዘመን እቅድ ለበጀት ዓመቱ ለተያዙ ግቦች ቢያንስ 75 በመቶ መያዝ

ይኖርባቸዋል፡፡

15) በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለሚገኙ የስራ ክፍሎችና ተጠሪ ተቋማት፣ ክልሎች እና ከተማ

አስተዳደሮች በየደረጃውና በየፕሮግራሞች/ፕሮጀክቶች የጸደቀ የዘርፉ ዓመታዊ የበጀት ዕቅድ

ለፊዚካል ስራዎች አፈጻጸም ክትትል በሚመችና በተናበበ መንገድ መዘጋጀት አለበት፡፡

16) የዕቅዱ የድርጊት መርሐ-ግብር የዝግጅት፣ የተግባር እና የማጠቃለያ ምዕራፍ ሥራዎችን ያካተተ

ሆኖ በአራቱም ሩብ ዓመቶች ላይ ተመጣጣኝ የሆነ የስራ ክብደት በመደልደል መታቀድ ይኖርበታል፡፡

ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ ቢያንስ በመጀመሪያው ሩብ ዓመት የአጠቃላይ ሥራውን 15%፣ በሁለተኛው

ሩብ ዓመት 35%፣ በሦስተኛው ሩብ ዓመት 35% እና በአራተኛው ሩብ ዓመት 15% አድርገው

ማቀድ አለባቸው፡፡

17) የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የስራ ክፍሎችና ተጠሪ ተቋማት ከክልልና ከከተማ አስተዳደር አቻ የስራ

ክፍሎቻቸው ጋር ተናበው በማቀድ እንዲሁም ከበጀት ጋር በማስተሳሰር የቀጣይ በጀት ዓመታዊ

መነሻ ዕቅዶቻቸውን በሚጠናቀቀው በጀት ዓመት እስከ መጋቢት 30 ድረስ ለዕቅድና ፕሮግራም

በጀት ቢሮ ማቅረብ አለባቸው፡፡

18) የዕቅድና ፕሮግራም በጀት፣ የለውጥና ሰው ሀብት ልማትና አስተዳደር ቢሮና ሚኒስትር ጽ/ቤት

የስራ ክፍሎች አፅድቀው ለዚሁ ስራ በተዘጋጀ የጋራ መረጃ መለዋወጫ ኢ-ሜይል ወይም በሀርድ

ኮፒ (የኢንተርኔት አገልግሎት ማግኘት ማይቻል ከሆነ) ያቀረቡትን ዓመታዊ እቅድ ተቀብለውና

በተሰጡ አስተያየቶች መሰረት መስተካከላቸውን አረጋግጠው እስከ ሰኔ 30 ድረስ በየዘርፎቻቸው

በማፅደቅ ከሐምሌ 1 ጀምሮ ወደ ትግበራ እንዲገቡ ያደርጋል፡፡

19) ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች በዕቅድና በጀት የሥራ ክፍሎች አማካይነት የቀጣይ በጀት ዓመት

ዕቅዳቸውን የተስተካከለ የድርጊት መርሀ-ግብር በሩብ ዓመት ከፋፍሎ በማዘጋጀት ከግንቦት 1 እስከ

ሰኔ 30 ተዘጋጅቶ እና በሚመለከታቸው አካላት ጸድቆ ህጋዊ የሸኝ ደብዳቤ አባሪ ያለው ሶፍት ኮፒ

10 | P a g e
ሰነድ በተቋማዊ የድረ-ገጽ አድራሻ ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የዕቅድና ፕሮግራም በጀት ቢሮ መላክ

ይኖርባቸዋል፡፡ በዕቅዱም የክልል/የከተማ አስተዳደር የበላይ ሃላፊዎች ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ

የበላይ ሃላፊዎች ጋር እስከ ነሐሴ 30 በሚካሄደው የሴክተር የጋራ መድረክ የሚፈራረሙበት

ይሆናል፡፡ የሴክተር የጋራ መድረክ የሚካሄድበት ጊዜና ቦታ በበላይ አመራ የሚወሰን ይሆናል፡፡

20) የዕቅድ ክለሳን በተመለከተ የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት እንዲያውቁት በማድረግና

የተቋሙ የበላይ አመራሮች ውሳኔ ሲያሳልፉ የመካከለኛ ዘመን ዕቅድ የዕቅድ ክለሳ እንደአስፈላጊነቱ

መደረግ ይኖርበታል፡፡ የዓመታዊ ዕቅድ ደግሞ በዓመት እንደአስፈላጊነቱ አንድ ጊዜ በአንደኛው

ግማሽ ዓመት መጨረሻ ጥር ወር ብቻ ሆኖ ዕቅድ ሲከለስ የሚቀነሰ ወይም የሚጨመር ካለ በቂና

አሳማኝ ምክንያት በጽሁፍ ለበላይ አመራር መቅረብ ይገባዋል፡፡ ከበላይ አመራር ይሁንታ ሲያገኝ

ዕቅዱ የሚከለስ ይሆናል፡፡

21) የሰራተኛ የውጤት ተኮር ዕቅድ ሲዘጋጅ የሰራተኛው የግል ጠንካራና ደካማ ጎኖች በአግባቡ

በመለየት የራስን ማብቃት እቅድን በማካተት፣ በዳይሬክቶሬት ደረጃ ከተዘጋጁ ግብ ተኮር ተግባራት

በማውረድ ቀጣይ መሻሻልን በሚያመላክት መልኩ በግብ መልክ ማስቀመጥ፣ ከስራ መዘርዝር እና

ሰራተኛው ከተመደበበት ደረጃ ጋር የተናበበ መሆኑን ማረጋገጥ፣ ከአቅም በታች እንዳይሆን

ማድረግና ለስራ ክፍሉ ብሎም ለተቋሙ ግብ ስኬት ቀጥታ አስተዋጽዖ ሊያበረክት የሚችል

መሆኑን ማረጋገጥ እና ሰራተኛው የውጤት ተኮር ዕቅዱን ማሳኪያ የድርጊት መርሃ-ግብር

በማዘጋጀት ለቅርብ ኃላፊው በወቅቱ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡

22) የአፈፃፀም ስምምነትን በተመለከተ የቢሮ ሃላፊ የወረዱለትን ግቦች ለማሳካት ከዘርፍ የበላይ

ሃላፊ፣ ዳይሬክተር ከሚመለከተው የቢሮ ሀላፊ ጋር እንዲሁም ሰራተኛው ከቅርብ ሃላፊ የአፈፃፀም

ስምምነት መፈራረም አለበት፣ የአፈጻጸም ስምምነቶች የበጀት ዓመቱ ከገባ የመጀመሪያ አንድ ወር

ውስጥ መጠናቀቅ አለባቸው፡፡ እንዲሁም የተፈረሙ የአፈፃፀም ስምምነቶች በአግባቡ በሰነድነት

መያዝ አለባቸው፡፡

23) በዕቅድ ዝግጅት ወቅት የእቅድና ፕሮግራም በጀት ቢሮ እና የለውጥና ሰው ሐብት ልማትና

አስተዳደር ቢሮ በጋራ አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋሉ፡፡

24) የሚዘጋጁ ዓመታዊ እቅዶች ይህን መመሪያ ተከትሎ በሚዘጋጀው የአሰራር ማንዋል መሰረት መሆን

ይኖርባቸዋል፡፡

11 | P a g e
3.2. የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት
1) የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የስራ ክፍሎችና ተጠሪ ተቋማት ከክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ጋር

ወርሃዊ የአፈጻጸም መረጃዎችን አመቺ በሆኑ የመገናኛ ዘዴዎች (በስልክ፣ በኢ-ሜይል…) ልውውጥ

ያደርጋሉ፡፡

2) ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች በዓመት ውስጥ በበላይ ሃላፊዎች የተረጋገጡ 4 ወቅታዊ ሪፖርቶች

(የመጀመሪያ ሩብ ዓመት፣ የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት፣ የዘጠኝ ወር እና አመታዊ) በሶፍት/ሀርድ ኮፒ

ከዕቅድ አንጻር ተተንትነው ወጥ በሆነ ፎርማት መሰረት ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አቻ የስራ

ክፍሎች/ተጠሪ ተቋማት በተጠናቀቀው ሩብ ዓመት የመጨረሻ (28 ኛው) ቀን ድረስ ማቅረብ

አለባቸው፡፡

3) የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የስራ ክፍሎችና ተጠሪ ተቋማት ከክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የሚላኩ

ሪፖርቶችን የቀጣዩ ወር በገባ እስከ ሶስተኛው ቀን በዓመት 13 ሪፖርቶችን በስራ ክፍሎቹ/ተጠሪ

ኃላፊዎች ተረጋግጦ ለዕቅድና ፕሮግራም በጀት፣ የለውጥና ሰው ሀብት ልማትና አስተዳደር ቢሮ፣

ሚኒስትር ጽ/ቤት፣ የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ዳይሬክቶሬትና የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና ዳይሬክቶሬት

ለዚሁ ስራ በተዘጋጀ የጋራ መረጃ መለዋወጫ ኢ-ሜይል ወይም በሀርድ ኮፒ (የኢንተርኔት አገልግሎት

ማግኘት ማይቻል ከሆነ) መቅረብ ይኖርበታል፡፡ ይኸውም፡-

ሀ. 8 ወርሃዊ ሪፖርቶች፣

ለ. የመጀመሪያ ሩብ ዓመት፣

ሐ. የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት፣

መ. የዘጠኝ ወር፣

ሠ. የሁለተኛ ግማሽ ዓመት እና

ረ. ዓመታዊ የአፈፃፀም ሪፖርቶች ናቸው፡፡

4) የሚቀርቡ ሪፖርቶች በመረጃ የተደገፉና ስራዎች ያሉበትን ደረጃ በትክክል በሚያሳይ መልኩ መሆን

አለበት፡፡ በዚሁ መሰረት፡-

 በመረጃ ላይ ያልተደገፉና የሃሰት ሪፖርቶችን የሚያቀርብ ተቋም በሀስት የተገኘውን የምዘና

ውጤት መቀነስ እንደተጠበቀ ሆኖ ከተገኘ ተቋሙን በበላይነት ለሚመራው አመራር በጽሁፍ

ሪፖርት ይደረጋል፡፡ እንዲሁም የሀሰት መረጃ ያቀረበው የስራ ኃላፊ በአመራር ስነ ምግባር
መመሪያ (Code of Ethics) መሰረት ተጠያቂ እንዲሆን ይደረጋል፡፡

5) የሪፖርት ጥራት ጠብቀው የማይቀርቡ ሪፖርቶ ካሉ በሚዘጋጁ የአሰራር ማንዋል መሰረት

ከእይታው ጠቅላላ ድምር ውጤት ላይ እስከ 2 ነጥብ ተቀናሽ ይደረጋል፡፡

12 | P a g e
6) ለሪፖርት ማቅረቢያ ከተቀመጠው ጊዜ ያዘገዩ ተቋማት/የስራ ክፍሎች በሚዘጋጁ የአሰራር

ማንዋሎች መሰረት የዕቅድ እና ፕሮግራም በጀት ቢሮ እና የለውጥና ሰው ሃብት ልማትና

አስተዳደር ቢሮ ከሚያጠቃልለው የአፈጻጸም ውጤት ላይ እስከ 3 ነጥብ ተቀናሽ ይደረግባቸዋል፡፡

7) ተቋሙ ሪፖርት አቀራረብ ወጥነት ያለው እንዲሆን ሁሉንም የተቋሙ ስራዎችን ያካተተ አንድ

ሪፖርት ስርዓት ሊዘረጋ ይገባል፡፡ የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት በሚዘጋጀው ማንዋል ላይ በቀረበው

የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ፎርማት መሠረት መዘጋጀት አለበት፡፡ (ሆኖም ግን ተቋሙ ወደ ተለያዩ

ተቋማት የሚልካቸው የተለያዩ ሪፖርቶች እንደየ ተቋማቱ ፍላጎቶት መዘጋጀት ይኖርባቸዋል)፡፡

3.3. የክትትል፣ ድጋፍና ሱፐርቪዥን ስርዓት


1) በየደረጃው ያለው ሀላፊ የውጤት ተኮር ዕቅድ ክንውንን በተመለከተ ተገቢውን መረጃ በየጊዜው

መያዝና ማደራጀት አለበት፣

2) ዕቅድና ፕሮግራም በጀት ቢሮ እና ለውጥና የሰው ሀብት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በሚኒስቴር

መስሪያ ቤቱ ስራ ክፍሎች ውስጥ የጎንዮሽ ሥራ ክትትልና ድጋፍ በሚያደርጉበት ወቅት ችግር ፈቺ፣

ወቅቱን የጠበቀ እና አስተማሪ የሆነ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡

3) የዕቅድና ፕሮግራም በጀት፣ የለውጥና ሰው ሀብት ልማትና አስተዳደር ቢሮ የተጠሪ ተቋማትና

የሥራ ክፍሎችን ሪፖርት መሠረት በማድረግ የተሰሩ ሥራዎችን መረጃዎችና ሰነዶችን በቢሮዎች

በየወሩ በመገኘት ምልከታ (ዴስክ ሪቪው) በማድረግ ያረጋግጣሉ፡፡

4) የስርዓተ ፆታ ዳይሬክቶሬት የተጠሪ ተቋማትና የሥራ ክፍሎችን እቅድና ሪፖርት መሠረት

በማድረግ የተሰሩ ሥራዎችን መረጃዎችና ሰነዶችን በማየት ክትትልና ድጋፍ ያደርጋሉ፡፡

5) በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሚገኙ ሥራ ክፍሎች በክልልና ከተማ አስተዳደሮች ክትትልና ድጋፍ

ሲያደርጉ በቂ ዝግጅት በማድረግ በተቀናጀ እና ችግር ፈቺ በሆነ መልኩ ማድረግ ይኖርባቸዋል፣ ስለ

መቀናጀታቸውም በዘርፍ ኃላፊ መረጋገጥ ይኖርበታል፡፡

6) የዕቅድና ፕሮግራም በጀት ቢሮ ለሁሉም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ለሱፐርቪዥን የሚሆን

ቼክሊስት በማዘጋጀት እና የሱፐርቪዥን ቡድን በማደራጀት በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የበላይ

አመራር በማጸደቅ በዓመት ሁለት ጊዜ (ጥር እና ሐምሌ ወር) ሱፐርቪዥን እንዲካሄድ ያደርጋል፡፡

በሐምሌ ወር የሚደረገው ሱፐርቪዥን የዓመታዊ እቅድ አፈጻጸም ምዘናን የሚያካትት ይሆናል፡፡

7) ለስራ ክፍሎች፣ ለተጠሪ ተቋማት፣ ለክልልና ከተማ አስተዳደር ሱፐርቪዥን የሚያካሂድ ቡድን

አደረጃጀት በተመለከተ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ስራ ክፍሎች እና ተጠሪ ተቋማት የተውጣጣ

13 | P a g e
ይሆናል፡፡ የሱፐርቪዥኑ ቡድን አወቃቀር ተግባርና ኃላፊነት የዕቅድና ፕሮግራም በጀት ቢሮ

በሚያዘጋጀው ማንዋል መሰረት ይሆናል፡፡

8) በሚኒስቴሩ ስራ ክፍሎች፣ ተጠሪ ተቋማት እንዲሁም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች

ሱፐርቪዥኑን ያካሄደው ቡድን ያደረገውን ምልከታ ለሥራ ክፍሉ/ ተቋሙ/ ለክልሉ/ ከተማ

አስተዳደሩ የበላይ አመራር/ማኔጅመንት ጠንካራ ጎኖችን፣ ክፍተቶችንና መስተካከል ያለባቸውን

ጉዳዮች በመውጫ ውይይት (Exit Report) አመላክቶ ይመለሳል፡፡ ይህንኑ በሪፖርት አደራጅቶ

ለሱፐርቪዥን ለተደረገበት ሥራ ክፍል/ተቋም/ክልል/ከተማ አስተዳደር በግብረ መልስ አደራጅቶ

ይልካል፡፡ ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የበላይ አመራር ያቀርባል፡፡

9) የክትትል፣ ድጋፍ፣ ግምገማና ግብረ-መልስ ስርዓቱ በየተወሰነ የጊዜ ገደብ (Time Interval) የተወሰኑ

ከተሞችን በመምረጥ እና በከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ስራዎች በማብቃት የተገኙ

ተሞክሮዎችን ወደ ሌሎች ከተሞች የማስፋት ስራ በመስራት መተግበር ይኖርበታል፣

3.4. የግምገማ ስርዓት


1) በሚኒስቴር መስያ ቤቱ ሥራ ክፍሎች የቡድን ውይይት በቡድን/ዳይሬክቶሬት ደረጃ በየሳምንቱ

የውጤት ተኮር ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ይካሄዳል፡፡ ሆኖም ግን እንደየስራ ባህሪያቸው አንዳንድ

የስራ ክፍሎች ከሳምንት ባነሰ ጊዜ የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ማድረግ ይችላሉ፡፡

2) በተቋሙ የሥራ ክፍሎች አወቃቀር በአንድ ዳይሬክቶሬት ውስጥ ከአንድ በላይ የቡድን አደረጃጀት

ያላቸው የስራ ክፍሎች ቡድን መሪዎች ከዳይሬክተር ጋር በየሳምንቱ እንዲሁም ዳይሬክተሩ

ከሰራተኞቹ ጋር በየ 15 ቀኑ የውጤት ተኮር ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡

3) በቡድን ውይይት ወቅት በየ 15 ቀኑ የስራ ክፍሉ ሰራተኞች አቅም በሚገነቡ እና ከስራ ክፍሉ ጋር

ተያያዥነት ያላቸውን የመወያያ አጀንዳዎች በመቅረጽ የእርስ በርስ መማማር መደረግ

ይኖርበታል፡፡

4) የቢሮ ኃላፊ በየሳምንቱ ከሁሉም ዳይሬክቶሬቶች ጋር እንዲሁም በየወሩ ከሁሉም ሰራተኛ ጋር

የውጤት ተኮር አፈጻጸም ላይ ግምገማ መካሄድ ይኖርበታል፡፡

5) የዘርፍ ሃላፊዎች ከሚመለከታቸው የስራ ክፍልና ተጠሪ ተቋማት ሃላፊዎች ጋር በየ ወሩ የውጤት

ተኮር አፈጻጸም ላይ ግምገማ መካሄድ ይኖርበታል፡፡

6) የሚኒስቴር መ/ቤቱ የስራ ክፍሎች እና የተጠሪ ተቋማት የሩብ ዓመት፣ የግማሽ ዓመት፣ የዘጠኝ

ወራት እና ዓመታዊ እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ቢሮ ሃላፊዎችና ዳይሬክተሮች በሚሳተፉበት እና

ሚኒስትሩ/ሯ እና/ወይም ሚኒስትር ዴኤታዎች በሚመሩት የዕቅድ ግምገማ መድረክ በሪፖርቱ

14 | P a g e
ማቅረቢያ የመጨረሻ ቀን ጀምሮ ባሉት ሰባት(7) ቀናት ውስጥ ይገመገማል፡፡ ከግምገማ መድረኩ

በኋላ የተሰጡ አቅጣጫዎችና የግምገማ መደምደሚያዎችን በማከተት የዕቅድና ፕሮግራም ቢሮ

ለሚመለከተው አካል ሪፖርት ይልካል፡፡

7) በየወሩ በተቋም የበላይ ሀላፊ በሁሉም የስራ ክፍሎች የውጤት ተኮር አፈጻጸም ላይ በተቋም

ማኔጅመንት ክትትልና ግምገማ መካሄድ ይኖርበታል፡፡

8) በየሩብ ዓመቱ የተቋም የውጤት ተኮር አፈጻጸም እና በመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ላይ ግምገማ

በአጠቃላይ ሰራተኞች በዘርፍ ደረጃ ይካሄዳል፡፡ ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ በየግማሽ ዓመቱ የተቋም

የውጤት ተኮር አፈጻጸም እና በመልካም አስተዳደር ጉዳዮች ላይ በጠቅላላ ሰራተኞች በተቋም

ደረጃ ውይይት ይካሄዳል፡፡

9) በክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የሚደረጉ ሱፐርቪዥኖችና ምዘናዎች መሰረት በማድረግ

በከፍተኛ አመራሩ የሚመራ ክልሎች/ከተማ አስተዳደሮችና ባለድርሻ አካላት የሚሳተፉበት

የግምገማ/የምክክር መድረክ/ሴክተር ጉባኤ/ በዓመት ሁለት ጊዜ (በየካቲት ወር እና ነሐሴ ወር)

ይካሄዳል፡፡ በጉባኤዎቹ ላይ የሱፐርቪዥን ሪፖርት፣ የምዘና ውጤት፣ የተገኙ ተሞክሮዎችና ልዩ ልዩ

ጥናታዊ ጽሁፎች እንዲቀርቡ እንዲሁም በአዘጋጅ ከተማ የተሻለ የልማት ስራ እንዲጎበኝ

ይደረጋል፡፡

10) የህዝብ አደረጃጀቶች ከመንግስት መዋቅር ጋር በመሆን በየስድስት ወሩ የተቋም የውጤት ተኮር

አፈጻጸምን ይገመግማሉ፡፡

11) የቢሮ/ጽ/ቤት ሃላፊና ዳይሬክተሮች በአመራር ብቃትና የመልካም አስተዳደር ችግር አፈታት ላይ

በጠቅላላ የስራ ክፍል ሰራተኞች የዘርፍ ሃላፊ በተገኘበት በዓመት ሁለት ጊዜ ግምገማ ይካሄዳል፡፡

3.5. የግብረ መልስ አሰጣጥ ስርዓት


1) በየደረጃው የሚካሄደው የክትትልና ግምገማ ሂደት የመፈጸም ብቃት፣ ጥንካሬና እጥረትን በመለየት

መረጃዎችን የመያዝ፣ የአፈጻጸም አዝማሚያን የማመላከት እንዲሁም ግብረ መልስ የመስጠትንና

ለቀጣይ ግብዓት እያደረጉ መሄድን ማካተት አለበት፡፡

2) የሚዘጋጁ ዓመታዊ ዕቅዶች ከዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ፣ ከመንግስት ፖሊሲና

ስትራቴጂዎች፣ ከባለፈው ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም፣ የስራ ክፍሉ/ተቋሙ እንዲያከናውን

ከተቋቋመበት ዓላማ እና ሌሎች የእቅድ ጥራት (SMARTER) መገምገሚያ መስፈርቶችን ያሟላ

ስለመሆኑ ታይቶ በየደረጃው የጽሁፍ ግበረ-መልስ መሰጠት አለበት፡፡

15 | P a g e
3) በተቋሙ ሥራ ክፍሎችና ተጠሪ ተቋማት ለሚዘጋጁ ሪፖርቶች ከወቅታዊነት፣ ከጥራት፣

ከተአማኒነት እና ከአፈጻጸም ደረጃ አኳያ ታይቶና ተመዝኖ በየደረጃው የቃል እና የጽሁፍ ግብረ-

መልስ በዕቅድና ፕሮግራም በጀት ቢሮ፤ በለውጥና ሰው ሀብት ልማት ቢሮ እና በስርዓተ ፆታ

ዳይሬክቶሬት መሰጠት አለበት፡፡

4) ለክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ከሱፐርቪዥን እና ምዘና የሚገኙ መረጃዎች እና በሴክተር

ጉባኤው ላይ የተቀመጡ አቅጣጫዎችን በማካተት የቃልና የጽሁፍ ግብረ መልስ በዕቅድና

ፕሮግራም በጀት ቢሮ በኩል ተዘጋጅቶ ሱፐርቪዥን ለተካሄደባቸው ወይም ለተመዘኑ ተቋማት፣

ለክልል/ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት እና ለርዕሰ-መስተዳደር/ከንቲባ አካላት ይላካል፡፡

3.6. የአፈጻጸም ምዘና


1) የተቋም አፈጻጸም ምዘና
1. የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የስራ ክፍሎች እና ተጠሪ ተቋማት ምዘና በዓመት ሁለት ጊዜ
እንደቅደም ተከተሉ በጥር ወርና በሀምሌ ወር ውስጥ ይካሄዳል፣ ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ
ተቋሙ በአንደኛ የሩብ ዓመት እና በዘጠኝ ወር የአፈጻጸም አዝማሚያውን ይመዘናል፡፡
2. የተቋም የውጤት ተኮር አፈጻጸም ምዘና የሚካሄደው በተቋሙ የግቦች አፈጻጸም ውጤት
ላይ በመመስረት ነው፡፡
3. የአጠቃላይ የስራ ክፍሎቹ የምዘና ውጤት አማካኝ የተቋሙ የምዘና ውጤት ተደርጎ
ይቀመጣል፡፡
4. የተቋም የውጤት ተኮር አፈጻጸም ምዘና ውጤት በሰራተኛው የጋራ ውይይት ሊካሄድበትና
በተቋሙ የሚኒስትር መስሪያ ቤቱ ማኔጅመንት ኮሚቴ ሊጸድቅ ይገባል፡፡
2) የስራ ክፍሎች አፈጻጸም ምዘና
1. የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የስራ ክፍሎች በበጀት ዓመቱ መጀመሪያ ላይ የውስጥ እና የውጭ
ተገልጋዮቻቸውን በመለየት ለለውጥ እና ለሰው ሀብት ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ማሳወቅ
ይኖርባቸዋል፡፡
2. የተገልጋይ ዕይታ ምዘና በለውጥ እና ሰው ሀብት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በኩል በሚላከው
መነሻ ዕቅድ የሚታቀድ ሆኖ እንደየ ስራ ክፍሉ ባህሪ በታቀደው ዕቅድ መሰረት ከ 15%
የሚመዘን ይሆናል፡፡ የሚላከው መነሻ ዕቅድ የተገልጋይ እርካታ ደረጃን የሚያሳድጉ፣ የእርስ
በርስ መስተጋብርን የሚያሳድጉ፣ የዜጎች ቻርተር ስታንዳርድን ወዘተ… ማካተት
ይኖርበታል፡፡ የውስጥና የውጭ ተገልጋይ የእርካታ ደረጃ የለውጥና ሰው ሃብት ልማትና
አስተዳደር ቢሮ በኩል በሚካሄደው የዳሰሳ ጥናት መሰረት ይሆናል፡፡

16 | P a g e
3. የውጪ ተገልጋይ የሌላቸው የስራ ክፍሎች በውስጥ ተገልጋዮች ከ 10% የሚመዘኑ ሲሆን
የወስጥ እና የውጭ ተገልጋይ ያላቸው የስራ ክፍሎች በውስጥ ተገልጋዮች (5%) እና በውጪ
ተገልጋዮች (5%) እንዲመዘኑ ይደረጋል፡፡
4. የውስጥና የውጭ ተገልጋይ እርካታ ምዘና የዳሰሳ ጥናት ሁሉም ቢሮ /ጽ/ቤት ኃላፊዎች እና
ዳይሬክተሮች በተገኙበት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበት እንደ ቢሮ የተጠቃለለ የምዘና ውጤት
ይሰጣል፡፡ የሥራ ክፍሎች የተገልጋይ እርካታ ውጤት ከተጠቃለለ በኋላ በበላይ አመራሮች
በማፀደቅ የለውጥና የሰው ሀብት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ለሁሉም የሥራ ክፍሎች ግብረ -
መልስ እንዲሰጡ በማድረግ ውጤት ተጠቃሎ እንዲላክላቸው ይደረጋል፡፡
5. የመማማርና ዕድገት ዕይታ ምዘና በለውጥ እና ሰው ሀብት ልማትና አስተዳደር ቢሮ በኩል
በሚላከው መነሻ ዕቅድ መሰረት እንደየ ስራ ክፍሉ ባህሪ የሚታቀድ ሆኖ ከ 10% የሚመዘን
ይሆናል፡፡ የአፈጻጸም ምዘና ሂደቱም የስራ ክፍሎቹ ባከናወኑት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርትና
በዴስክ ሪቪው በተገኘ መረጃ ተደግፎ መደረግ ይኖርበታል፡፡ በለውጥ እና ሰው ሀብት ልማትና
አስተዳደር ቢሮ የሚላከው መነሻ ዕቅድ የዘርፈ ብዙ ጉዳዮችን ፣ የሰው ሀይልን አቅምን
የሚያጎለብቱ ፣ የቡድን ስሜትን ሚፈጥሩ ወዘተ… ማካተት ይኖርበታል፡፡
6. የፋይናንስ ዕይታ ምዘና የሚከናወነው በዕቅድ እና በፕሮግራም በጀት ቢሮ በኩል በሚላከው
መነሻ ዕቅድ መሰረት ሆኖ የፕሮግራም በጀትን የተመለከተ ዕቅድም ይሁን አፈጻጸም ሪፖርት
ማጠናቀርና ለግብዓትነት ሊያገለግል የሚችል መረጃ መያዝ፣ ስለአጠቃቀሙ ዝርዝርና
አጠቃላይ ሪፖርት ማቅረብን ያካትታል፡፡ ዕይታው የሚይዘው የነጥብ ክብደት 15 በመቶ
ይሆናል፡፡
7. የውስጥ አሠራር ዕይታ የሥራ ክፍሎች በዓመታዊ ዕቅዳቸው የሚጥሏቸው የውስጥ አሰራር
ግቦች 60 በመቶ ክብደት የሚኖራቸው ሲሆን የሚመዝነውም በእቅድና ፕሮግራም በጀት
ቢሮ ነው፡፡ በውጤት ተኮር ሥርዓት ማስፈጸሚያ ማንዋል መሰረት እያንዳንዱ ግቦቹ በሶስት
መለኪያዎች በመጠን፣ በጊዜና በወጪ የሚመዘን ሲሆን የወጪ መለኪያ በፋይናንስ ዕይታ
ላይ የሚለካ በመሆኑ በዚህ ዕይታ በመጠን እና በጊዜ ብቻ የሚለካ ሆኖ የመለኪያዎች
ክብደትም ለእያንዳንዳቸው 50 በመቶ ይሆናል፡፡ በውስጥ አሠራር ዕይታ ምዘና የሚካሄደው
በግቦች እና በተግባር ደረጃ የተገኙ ውጤቶች ላይ ተመስርቶ ሲሆን ያልተጠናቀቀ ወይም
በሂደት ላይ ያለ ተግባር አይመዘንም፡፡
8. እያንዳንዱ የስራ ክፍል ከተቋሙ የወረዱለትን ግቦች አፈጻጸም በመገምገም የውጤት ተኮር
አፈጻጸሙን መመዘን አለበት፡፡
9. የስራ ክፍል የውጤት ተኮር አፈጻጸም ምዘና የሚካሄደው ለስራ ክፍሉ በወረዱለት ግቦች
ክብደት ስሌት ላይ በመመስረት ይሆናል፡፡
10. የስራ ክፍል የውጤት ተኮር አፈጻጸም የምዘና ውጤት የስራ ክፍሉን ግቦች አማካኝ
የአፈጻጸም ውጤት ነው፡፡

17 | P a g e
11. የስራ ክፍል የውጤት ተኮር አፈጻጸም ምዘና የሚካሄደው በየስድስት ወሩ ሲሆን
ወቅታዊነታቸውን ጠብቀው በተከታታይ በተያዙ መረጃዎች ላይ ተመስርቶ መሆን አለበት፡፡
12. የስራ ክፍል የውጤት ተኮር አፈጻጸም ምዘና የተቋም የውጤት ተኮር የአፈጻጸም ምዘና
ከመካሄዱ በፊት መጠናቀቅ ይኖርበታል፡፡
13. የስራ ክፍል የውጤት ተኮር አፈጻጸም በዳይሬክቶሬት ደረጃ ውይይት ተካሂዶበት
በዳይሬክተሩ መረጋገጥና ቀጥሎ ባለው ሀላፊ መጽደቅ አለበት፡፡
3) የቢሮ/ጽ/ቤት ሀላፊ/የዳይሬክተር/ቡድን መሪ የአፈጻጸም ምዘና
1. የቢሮ /ጽ/ቤት ሀላፊ/የዳይሬክተር/ቡድን መሪ የውጤት ተኮር አፈጻጸም ምዘና የሚከናወነው
የቢሮ/ጽ/ቤት/የዳይሬክቶሬቱን/የቡድኑን የግብ አፈጻጸም ውጤት እና ሌሎች የአመራር
ውጤታማነት መመዘኛዎችን መሰረት በማድረግ ነው፡፡
2. የቢሮ /ጽ/ቤት ሀላፊ/የዳይሬክተር/ቡድን መሪ የውጤት ተኮር አፈጻጸም ምዘና ውጤት
የሚሰላው የቢሮ /ጽ/ቤቱን/የዳይሬክቶሬቱን/የቡድኑን የግብ አፈጻጸም ውጤት ከ 70%
በመለወጥና ሌሎች የአመራርነት ክህሎትና ብቃትን ለመመዘን የሚያስችሉ መመዘኛዎችን
የቅርብ ሃላፊው ከ 20% በመመዘን፣ የስራ ባልደረባ ከ 10% በመመዘን በሚገኘው የ 100%
አጠቃላይ ውጤት ይሆናል፡፡
3. የቢሮ /ጽ/ቤት ሀላፊ/የዳይሬክተር/ቡድን መሪው የሚመዘነው በየግማሽ ዓመቱ መጨረሻ ላይ
ይሆናል፡፡
4) የሰራተኛ አፈጻጸም ምዘና
1. የሰራተኛ የውጤት ተኮር አፈጻጸም አዝማሚያ ክትትልና ግምገማ የሚካሄደው በቡድን
አደረጃጀት በየሳምንቱ የሰራተኛውን የሳምንት ውጤት ተኮር ዕቅድ አፈጻጸም መሰረት
በማድረግ ነው፡፡
2. የሰራተኛው የባህሪ አፈጻጸም በባህሪ መመዘኛ መስፈርቶቹ መሰረት በየሳምንቱ በመረጃ
ተይዘው ክትትልና ግምገማ ሊደረግባቸው ይገባል፡፡ አፈጻጸም አዝማሚያ
በዳይሬክተሩ/በቡድን መሪው ተረጋግጦ በየወሩ በሰነድነት መቀመጥ አለበት፣
3. በቡድን አደረጃጀቱ በየሳምንቱ የተካሄደው የሰራተኞች የውጤት ተኮር ዕቅድ አፈጻጸም
አዝማሚያ በዳይሬክተሩ/በቡድን መሪው ተረጋግጦ በየወሩ በሰነድነት መቀመጥ አለበት፣
4. በሰራተኛው ወርሀዊ የውጤት ተኮር ዕቅድ አፈጻጸም አዝማሚያ መረጃ ላይ ተመስርቶ
በተከናወነ የአፈጻጸም ውጤት መሰረት በሩብ ዓመት የተሻለ ሰራተኛ በቡድን አደረጃጀቱ
ከተለየ በኋላ በዳይሬክተሩ ጸድቆ እንዲለጠፍ ይደረጋል፡፡
5. የሰራተኛ የግማሽ ዓመት የውጤት ተኮር አፈጻጸም ምዘና የሚከናወነው የየወሩን አፈጻጸም
መረጃዎች እንዲሁም የዳይሬክቶሬቱን የግማሽ ዓመት የውጤት ተኮር ዕቅድ አፈጻጸም
በመዛኝ አካላት በሚረጋገጠው ውጤት መሰረት በማድረግ በየግማሽ ዓመቱ መጨረሻ ላይ

18 | P a g e
የሰራተኛውን አፈጻጸም ከእቅድ ጋር በማነፃፀር ከ 70% እና በዕቅድ አፈጻጸም ሂደት አስፈላጊ
የሆኑ ባህሪያት አፈፃፀምን ከ 30% በመውሰድ ነው፡፡
6. ከ 30% የሚወሰደው የባህሪያት አፈፃፀም ምዘና የቅርብ ሀላፊ ከ 20%፣ የሥራ ባልደረባ 10%
ድርሻ በመስጠት በሶስትዮሽ በመድረክ ግምገማ ጥንካሬ እና ድክመትን በመገመገም
የሚካሄድ ይሆናል፡፡ ይህም በቃለ ጉባኤ መያዝ ይኖርበታል፡፡
7. በተራ ቁ.5 የተጠቀሰው የ 70% ምዘና እና በተራ ቁ.6 የተጠቀሰው የ 30% የሶስትዮሽ ምዘና
ድምር የተጠቃለለ የሰራተኛ የ 100% የውጤት ተኮር አፈጻጸም ምዘና ውጤት ይሆናል፡፡
8. የተጠቃለለ የሰራተኞች የውጤት ተኮር አፈጻጸም ምዘና በዓመት ሁለት ጊዜ ማለትም
የመጀመሪያው ስድስት ወር እና የበጀት ዓመቱ ከተጠናቀቀ በኋላ ባሉት ሁለት ሳምንታት
ውስጥ መከናወን አለበት፡፡
9. የተጠቃለለ የሰራተኞች የውጤት ተኮር አፈጻጸም ምዘና ከተጠናቀቀ በኋላ በተቋም
ማናጅመነት መፅደቅ ይኖርበታል፡፡
10. የስድስት ወሩ መጨረሻ ላይ የሚካሄደው የሰራተኞች የውጤት ተኮር አፈጻጸም ምዘና
ውጤት በሚመለከታቸው የቅርብ ሀላፊዎች ጸድቆ እና በሰራተኛው ተፈርሞ ምዘናው
ከተካሄደ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ከሰራተኛው የግል ማህደር ጋር መያያዝ አለበት፡፡
11. በየስድስት ወሩ መጨረሻ ላይ በሚካሄደው የምዘና ሂደት ለሰራተኞች የሚሰጠው የውጤት
ተኮር ውጤት አማካይ ለስራ ክፍሉ በአካል ከተሰጠው የውጤት ተኮር ምዘና ውጤት
መብለጥ የለበትም፡፡
12. በተቋም፣ በዳይሬክቶሬት እና በሰራተኞች ደረጃ የተካሄደው የውጤት ተኮር አፈጻጸም ምዘና
እርስ በርሱ የተናበበና ከግሽበት የጸዳ እንዲሆን አስፈላጊውን ክትትልና ድጋፍ ይደረጋል፡፡
የባህሪ የምዘናና የውጤት ተኮር ምዘና ውጤት እንዲናበቡ (Measure of Disperssion)
እንዲሆኑ ሲደረግ ልዩነቱ ከ 2 ነጥብ መብለጥ የለበትም፡፡
5) የክልልና ከተማ አስተዳደሮች ምዘናን በተመለከተ

1. ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የዘርፉን የውጤት ተኮር ስራዎች ዕቅድ መሰረት የክልሎች/ከተማ


አስተዳደሮች የስራ አፈጻጸም ይመዝናል፡፡
2. የዕቅድና ፕሮግራም በጀት ቢሮ ከሚኒስቴሩ ስራ ክፍሎች፣ ተጠሪ ተቋማት እንዲሁም
ክክሎችና ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጣ የምዘና ቡድን በማደራጀት በሚኒስቴር መስሪያ
ቤቱ የበላይ አመራር ያፀድቃል፡፡
3. የክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የዘርፉ የበጀት ዓመቱ እቅድ አፈጻጸም ምዘና በዓመት አንድ
ጊዜ ሆኖ የበጀት ዓመቱ በተጠናቀቀ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ የእቅድ እና ፕሮግራም በጀት ቢሮ
በሚያዘጋጀው ቼክሊስት መሰረት ይሆናል፡፡

19 | P a g e
4. የዕቅድ አፈጻጸም ምዘናው አስቀድሞ የጋራ ስምምነት በተደረሰባቸው የሴክተሩ ቁልፍ
የውጤት መስኮች እና ቁልፍ የአፈጻጸም አመልካቾችን መሰረት ባደረገ ማገናዘቢያ
(Checklist) ይሆናል፡፡
5. የሚኒስቴር መ/ቤቱ ዕቅድና ፕሮግራም በጀት ቢሮ የምዘና ቼክሊስት እና መስፈርቱን
ለማያሟሉ ግቦች የአፈፃፀም ደረጃ (Performance level) ያዘጋጃል፣
6. የተዘጋጀው የምዘና ቼክ ሊስት ከሳምንት በፊት ለተመዛኝ ተቋማት/የስራ ክፍሎች እንዲደርስ
ይደረጋል፤
7. የክልልና ከተማ አስተዳደር ተመዛኝ ተቋማት የምዘና አካሄድ፣ የምዘና ስልት፣ ለምዘናው
የሚያስፈልጉ ግብዓቶች፣ የምዘና ቡድን አባላት አወቃቀር፣ ተግባርና ሃላፊነት፣ የምዘና
ውጤት አሰጣጥ እንዲሁም የተመዛኝ ተቋማት ዝርዝርና የውድድር ምድብ በዕቅድና
ፕሮግራም በጀት ቢሮ በሚዘጋጀው ማንዋል መሰረት የሚተገበር ይሆናል፡፡
8. የምዘና ቡድኑ የምዘና ውጤት በተለይ የዕቅድ አፈጻጸም ደረጃና የታየው ጥንካሬና ድክመት
የተመዛኝ ተቋማት የበላይ ኃላፊዎች በተገኙበት በዋና ዋና ግኝቶች ላይ ጠቅለል ያለ
መግለጫ (Exit Report) ይሰጣል፤
9. የዕቅድና ፕሮግራም በጀት ቢሮ ከምዘና ቡድኖች በተቀበለው ሪፖርት መሰረት ምዘና
በተካሄደባቸው የውጤት ተኮር ዕይታዎች ተመዛኝ ተቋማት/የስራ ክፍሎች ከ 100% ያገኙትን
ውጤት በማጠናቀር የተጠቃለለ ሪፖርት ለአብይ ኮሚቴው አቅርቦ አስተያየት እንዲሰጥበትና
እንዲጸድቅ ያደርጋል፣
10. በምዘናና ሱፐርቪዥን የተገኙ ውጤቶችን መሰረት በማድረግ በሴክተር ጉባኤ መድረክ
የተደረሱ ድምዳሜዎችን የሚመለከታቸው የህዝብ ግንኙነትና ኮሚዩኒኬሽን አማካይነት
በሕትመት፣ በኤሌክትሮኒክስ እና በአየር ላይ የሚዲያ ሥርጭት ለህብረተሰቡ ተደራሽ
መደረግ አለበት፣

3.7. የውጤት ተኮር ሥራ አፈጻጸም ምዘና ደረጃ አሰጣጥ

በበጀት ዓመቱ በመጀመሪያው ስድስት ወር መጨረሻና በዓመቱ መጨረሻ ላይ የተሰጠና የጸደቀ


የተቋም፣ የዳይሬክቶሬቱ የሰራተኛ የውጤት ተኮር ሥራ አፈጻጸም ምዘና ነጥብ በሚከተሉት አምስት
የአፈጻጸም ደረጃዎች ውስጥ ይወድቃል፣

1. በጣም ከፍተኛ አፈጻጸም- በዚህ የአፈጻጸም ደረጃ የሚመደብ ተቋም፣ የስራ ሂደትና ሰራተኛ
የውጤት ተኮር ጥቅል የዕቅድ አፈጻጸም ውጤቱ የመቶኛ ስሌት 95% እና በላይ ባለው ነጥብ ስር
ያርፋል፤

20 | P a g e
2. ከፍተኛ አፈጻጸም፡- በዚህ የአፈጻጸም ደረጃ ውስጥ የሚመደብ ተቋም፣ የስራ ሂደትና ሰራተኛ
የውጤት ተኮር ጥቅል የዕቅድ የአፈጻጸም ውጤቱ የመቶኛ ስሌት ከ 80% -94.99% ባለው ነጥብ
ስር ያርፋል፣
3. መካከለኛ አፈጻጸም፡- በዚህ የአፈጻጸም ደረጃ ላይ የሚመደብ ተቋም፣ የስራ ሂደትና ሰራተኛ
የውጤት ተኮር ጥቅል የዕቅድ አፈጻጸም ውጤቱ የመቶኛ ስሌት ከ 65%-79.99% ባለው ነጥብ
ስር ያርፋል፤
4. ዝቅተኛ አፈጻጸም፡- በዚህ የአፈጻጸም ደረጃ ላይ የሚመደብ ተቋም፣ የስራ ሂደትና ሰራተኛ
የውጤት ተኮር ጥቅል የዕቅድ አፈጻጸም ውጤቱ የመቶኛ ስሌት ከ 55%-64.99% ባለው ነጥብ
ስር ያርፋል፤
5. በጣም ዝቅተኛ አፈጻጸም፡- በዚህ የአፈጻጸም ደረጃ ላይ የሚመደብ ተቋም፣ የስራ ሂደትና ሰራተኛ
የውጤት ተኮር ጥቅል የዕቅድ አፈጻጸም ውጤቱ የመቶኛ ስሌት ከ 55% በታች የሆነ ነው፣

3.8. ድህረ ምዘና ተግባራት

1. ከፍተኛ አፈጻጸምና ከዚያም በላይ ውጤት ያስመዘገቡ የስራ ክፍሎች፣ ዳይሬክተሮች እና


ባለሙያዎችን በመለየትና የሰራተኞች እና ተቋማት የዕውቅናና ሽልማት መመሪያን መሰረት
በማድረግ የትምህርትና ስልጠና፣ የእርከን ጭማሪ፣ የዕውቅና ሽልማትና የማበረታቻ ክፍያ
ለመስጠት አመቺ ሁኔታዎችን መፍጠርና ተግባራዊ ማድረግ ይገባል፡፡
2. በምዘና መስፈርቱ መሠረት የሠራተኞች የምዘና ውጤት መሰረት በማድረግ የጽሁፍ ግብረ-መልስ
በለውጥና ሰው ሀብት ልማት ቢሮ በኩል ተዘጋጅቶ ለተመዘኑ የስራ ክፍሎች ይላካል፡፡
3. በክትትል፣ ግምገማና ምዘና በተገኘው ውጤት መነሻነት የባለሙያዎችን እና የዳይሬክተሮችን
ብቃት በስልጠናና ምክር በማጎልበት ቀጣዩ ስራቸውን በሚጠበቀው የአፈጻጸም ውጤታማነት
ደረጃ እንዲያከናውኑ ለማድረግ ክፍተትን መሰረት ያደረገ የአቅም ግንባታ ስራዎችን ማከናወን
ይገባል፡፡
4. የአፈጻጸም ምዘና ሲከናወን ዝቅተኛ አፈጻጸም ያስመዘገቡ ሰራተኞች በዚህ በአንቀጽ ቁጥር (3)
መሰረት በተቋማት በሚደረግላቸው የአቅም ግንባታ ስራ ከዚያ በኋላ በተካሄዱት ሁለት ተከታታይ
ምዘናዎች አፈጻጸማቸውን ወደ መካከለኛ ደረጃ ካላሻሻሉ ካሉበት ደረጃ አንድ ደረጃ ዝቅ ብለው
እንዲሰሩ ይደረጋል፡፡
5. የአፈጻጸም ምዘና ሲከናወን በጣም ዝቅተኛ አፈጻጸም ያስመዘገቡ ሰራተኞች በዚህ በአንቀጽ
ቁጥር (2) መሰረት በተቋማት በሚደረግላቸው የአቅም ግንባታ ስራ ከዚያ በኋላ በተካሄዱት ሶስት
ተከታታይ የምዘና ጊዜ አፈጻጸማቸውን ካላሻሻሉ ከመስሪያ ቤቱ እንዲሰናበቱ ይደረጋል፡፡

21 | P a g e
3.9. ስለ ቅሬታ አቀራረብ

የለውጥና ልማት ስራዎች የዕቅድ ዝግጅት፣ የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት፣ ድጋፍ፣ ሱፐርቪዥን የክትትልና
ግምገማና ምዘናን በተመለከተ የሚነሱ ቅሬታዎች በቅሬታ አፈታት መመሪያ መሰረት የሚፈታ ይሆናል፡፡
ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ ከውጤት ጋር የተያያዘ ቅሬታ ያለው የስራ ክፍልም ሆነ ግለሰብ ቅሬታውን ውጤቱ
በአመራሩ ከመጽደቁ በፊት ባሉት 15 ቀናት ውስጥ ብቻ ማቅረብና ምላሽ ማግኘት ይጠበቅበታል ፡፡ ከዚህ
ቀን በኃላ የሚቀርብ የውጤት ማስተካከያ ቅሬታ ተቀባይነት የለውም፡፡

22 | P a g e
ክፍል አራት
4. የለውጥ ኃይሉ የመንግስት መዋቅር አደረጃጀት ሁኔታ

የቡድን አደረጃጀት የተቋሙን መደበኛ አደረጃጀት መሠረት በማድረግ በየደረጃው የሚደራጅ ይሆናል፤
በዚህም መሠረት በየቢሮዎች ውስጥ የቡድን አደራጃጀት ከዚህ በታች በተመለከተው መሠረት ይሆናል፤

4.1. በአንድ ዳይሬክቶሬት ውስጥ ያሉ ባለሙያዎች በአንድ ቡድን ይደራጃሉ፡፡ ሆኖም ግን


በዳይሬክቶሬቱ ስር በቡድን ደረጃ የተዋቀረ የስራ ክፍል ያላቸው ክፍሎች በመዋቅሩ መሰረት
እንዲደራጁ ይደረጋሉ፣
4.2. የቡድን አስተባባሪ ዳይሬክተሩ ወይም ቡድን መሪው ይሆናል፣
4.3. በተለያዩ ምክንያቶች በአንድ ዳይሬክቶሬት ወይም ቡድን የሚሰሩ ባለሙያዎች ቁጥር ከሦስት የሚያንስ ከሆነ
የቢሮ ኃላፊው እንደስራው ቅርበት በማየት በቢሮው ውስጥ ካሉ ሌሎች ቡድኖች ጋር እንዲደራጁ ያደርጋል፤
4.4. የቢሮ ፀኃፊና የመልዕክት ሰራተኞች ከ 3 በታች ከሆኑ እንደየአመችነቱ ወደሚቀርቧቸው ቡድኖች ተቀላቅለው
ይወያያሉ፡፡

23 | P a g e
ክፍል አምስት

5. የልዩ ልዩ አካላት ተግባርና ኃላፊነት


5.1. የበላይ ኃላፊ ተግባርና ኃላፊነት

1) የተቋሙ ዓመታዊ ዕቅድ ከመካከለኛው ዘመን ዕቅድ ጋር በማናበብ በመላው ሠራተኛ ተሳታፊነት
በውጤት ተኮር ስርዓት መሰረት እንዲዘጋጅ ማድረግ፣
2) የመካከለና ዘመን ዕቅድ ዝግጅት፣ ክትትልና ግምገማ ስራዎችን በበላይነት መምራት፡፡
3) ዕቅዱ ከአገራዊ ራዕይ፣ ከፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ጋር የተሳሰረና የተናበበ መሆኑን ማረጋገጥ፣
4) የውጤት ተኮር ስርዓቱ ከበጀት ጋር የተሳሰረ መሆኑን ማረጋገጥ፣
5) የተዘጋጀው ዕቅድ በህዝብ አደረጃጀት ተሳትፎና ግብዓት እንዲዳብርና የተሟላ ግንዛቤ
እንዲያዝበት አስፈላጊውን ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፣
6) የመካከለኛ አመራሩን የአመራር ክፍተቶች ለይቶ መደገፍና ማብቃት፣
7) ለዕቅድ ስኬቱ አስፈላጊ ግብዓቶችን በወቅቱ ማሟላት፤
8) የውጤት ተኮር ዕቅድ ትግበራና የአፈጻጸም ውጤታማነትን በየጊዜው መከታተል፣ መደገፍ፣
መገምገም እና በበላይነት መምራት፣
9) ለተጠሪ ተቋማት የበላይ ኃላፊዎች እንዲሁም በውጤት ተኮር ዕቅድ ዝግጅት፣ አፈጻጸም
ግምገማና ምዘና አተገባበር ዙሪያ ለሚመለከታቸው የስራ ክፍል ኃላፊዎችና ባለሙያዎች በዚህ
መመሪያ ተፈጻሚነት ላይ አቅጣጫ መስጠት እና የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እንዲያገኙ
ማድረግ፣
10) የዕቅድ ዝግጅት እንዲሁም የአፈጻጸም ክትትል፣ ግምገማና ምዘናን በሚመለከት ከውጤት ተኮር
መመሪያው ጋር የተጣጣመ አሰራር እንዲኖራቸው ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት
መስራት፣
11) የመመሪያውን አፈጻጸም መከታተል፣ መገምገምና አስፈላጊ ድጋፎችን መስጠት፣
12) በዕቅድና ፕሮግራም በጀት ቢሮ ተጠቃሎ የሚቀርበውን የሴክተሩና የተቋማትን ዕቅድ፣ የእቅድ
አፈጻጸም፣ የምዘናና የሱፐርቪዥን ሪፖርቶች ያስገመግማል፣ ያስጸድቃል፡፡
13) በዕቅድ ግምገማ እና በሴክተር ጉባኤ መድረኮች የምዘና ውጤቱን መሰረት በማድረግ ለተመዛኝ
የሥራ ክፍሎች እና ለመዛኝ አካላት አስተያየቶችን፣ አቅጣጫዎችን እና ውሳኔዎችን መስጠት፡፡
14) በዕቅድ ግምገማ እና በሴክተር ጉባኤ መድረኮች ለተመዛኝ እና መዛኝ የሥራ ክፍሎች የተሰጡ
አስተያየቶች፣ አቅጣጫዎችና ውሳኔዎችን ተፈጻሚነት ማረጋገጥ፡፡
15) አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ መመሪያውን እንዲሻሻል ማድረግ፡፡

24 | P a g e
5.2. የሚኒስትሩ ጽ/ቤት ተግባርና ኃላፊነት

1) የሚኒስቴር መ/ቤቱንና የተጠሪ ተቋማትን ወቅታዊ መድረኮች ዓመታዊ የጊዜ ሰሌዳ በማዘጋጀት
ለሥራ ክፍሎች እንዲደርስና አስፈላጊ ግብዓቶችን በማሟላት በጊዜ ሰሌዳው መሰረት መድረኮች
እንዲካሄዱ ማድረግ፡፡
2) የግምገማ መድረኮች ከመካሄዳቸው አስቀድሞ የዕቅድ እና የአፈጻጸም ሪፖርቶች ለበላይ አመራሩ
መቅረባቸውን ማረጋገጥ፡፡
3) በበላይ አመራሩ የተሰጡ አቅጣጫዎችን በሚመለከታቸው ስራ ክፍሎች ተፈጻሚ እንዲሆኑ
ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፡፡
4) በተሰጠው አቅጣጫ መሰረት ያልፈጸሙ የሚኒስቴር መ/ቤቱንና የተጠሪ ተቋማትን በቀጣዩ
የአፈጻጸም ግምገማ መድረክ ተገቢው የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ ሪፖርት ማድረግ፡፡

5.3. የዕቅድና ፕሮግራም በጀት ቢሮ ተግባርና ኃላፊነት


1) የዘርፉን ተቋማት/የሥራ ክፍሎችን ዕቅድና ሪፖርት አዘገጃጀት ላይ ኦረንቴሽን እና ስልጠና መስጠት፡፡
2) ከዘርፉን ተቋማት/የሥራ ክፍሎች የሚቀርቡ ዕቅድና የአፈፃፀም ሪፖርቶች ከዘርፉ ተልዕኮና ግቦች ጋር
ተጣጥመው እንዲዘጋጁ ክትትልና ድጋፍ መስጠት፡፡
3) የተጠሪ ተቋማት/የሥራ ክፍሎችን ወቅታዊ ዕቅዶች፣ ሪፖርቶች፣ ምዘናዎችና የግምገማ መድረኮች
እንዲዘጋጁና እንዲካሄዱ ማስተባበር፡፡
4) የተጠሪ ተቋማት/የሥራ ክፍሎችን ዕቅድና የአፈጻጸም ሪፖርት ማቅረቢያ ፎርማት ማዘጋጀት፣ እንደ
አስፈላጊነቱ ማሻሻያዎችን ማድረግ፡፡
5) የክልል፤ ከተማ አስተዳደሮች፤ የተጠሪ ተቋማት/የሥራ ክፍሎችን ዕቅድና የዕቅድ የአፈጻጸም ሪፖርት
በተቀመጠው የጊዜ ሠሌዳ መሠረት ማቅረባቸውን መከታተል፣ መመዘን፤ ግብረ መልስ መስጠት፡፡
6) የተጢሪ ተቋማት/የሥራ ክፍሎችን የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት መሰረት በማድረግ የተሰሩ ስራዎች በአካል
በመገኘት ምልከታ (Desk Review) በማድረግ ማረጋገጥና ከሚመለከታቸው ኃላፊዎች ጋር መግባባት ላይ
መድረስ::
7) የዘርፉን ተቋማት/የሥራ ክፍሎችን የአፈፃፀም ምዘና የአሰራር ስርዓት በቴክኖሎጂ የተደገፈ እንዲሆን
ማድረግ፡፡ በዘርፉ የሚካሄዱ የምዘና ውጤቶችን በማሰባሰብ የተጠቃለለ የምዘና ውጤት ማዘጋጀት::
ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን የግምገማ መድረኮች መርሀ-ግብር አዘጋጅቶ የእቅድ የአፈፃፀም
ሪፖርቶችና የምዘና ውጤቶች ተገምግመው እንዲጸድቁ ማድረግ፡፡ በዘርፉ ዕቅድ አፈጻጸም የግምገማ
መድረኮች ከበላይ አመራሩ የተሰጡ አስተያየቶችን፣ አቅጣጫዎችንና ውሳኔዎችን በማካተት ግብረ-መልስ
ያጠናቅራል፣ ለሚመለከታቸው አካላት እንዲደርሳቸው ማድረግ::
8) የተዘጋጀው፣ የተናበበውና የጸደቀው የ 5 ዓመቱና የበጀት ዓመቱ መሪ ዕቅድ በዝግጅት ምዕራፍ ተደራጅቶና
ታትሞ ለሚመለከታቸው አካላት ማሰራጨት፡፡
9) ለዕቅድ አፈጻጸም ምዘናና ሱፐርቪዥን የሚዘጋጁ ማገናዘቢያዎችን (Checklist) እና የአፈጻጸም ደረጃ
መወሰኛ (Performance Level) በእግባቡ ማዘጋጀት፡፡

25 | P a g e
10) ለዕቅድ አፈጻጸም ምዘናና ሱፐርቪዥን ቡድን መመልመያ መስፈርት ያዘጋጃል፣ መስፈርቱን ለአብይ
ኮሚቴ አቅርቦ ያጸድቃል፣ ሲፈቀድም የምዘና ቡድኑን መመልመል፣
11) ለዕቅድ አፈጻጸም ምዘናና ሱፐርቪዥን ቡድኑ የእርስ በርስ ትውውቅ ፕሮግራም በማዘጋጀት ስለምዘናው
ሂደት ተግባር ተኮር ስልጠና ይሰጣል፣ ቡድኖቹን ወደሚመደቡበት ተቋም ያሠማራል፣ ይከታተላል፤ ለምዘና
ቡድኑ ድጋፍ ማድረግ፣
12) ለዕቅድ አፈጻጸም ምዘናና ሱፐርቪዥን ወቅት በሚያጋጥሙ ችግሮች ላይ የመፍትሔ አቅጣጫ
ያስቀምጣል፣ ውሳኔም ይሰጣል ወይም እንዲሰጥ ማድረግ፣
13) የዘርፍ ተቋማቱን ዕቅድ ከእቅድ አዘጋጅ እና የዕቅድ አፈጻጸም ምዘና ውጤት ከምዘና ቡድኖቹ
በመሰብሰብና በማጠናቀር ለአብይ ኮሚቴ ማቅረብ፣ ማስገምገም፤ ማስፀደቅ፡፡
14) የዘርፉ ተቋማት የምዘና ውጤትና ሱፐርቪዥን ሪፖርት እና ግብረ-መልስ በሚዘጋጀው የሴክተር ጉባኤ
መድረክ ላይ ይፋ ማድረግ፡፡
15) የምዘናና ሱፐርቪዥን ቡድን አባላት የምዘና ሥራቸውን ካጠናቀቁ በኋላ የተሳትፎ ምስክር ወረቀት
እንዲሰጣቸው ማስደረግ፡፡
5.4. የለውጥና የሰው ሀብት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ተግባርና ኃላፊነት
1) በውጤት ተኮር አፈጻጸም ምዘና መመሪያ ላይ የተቋሙ የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች በቂ ግንዛቤ
መያዛቸውን ማረጋገጥ፣
2) የውጤት ተኮር ስርዓት በተቋሙ በአግባቡ መተግበሩን መከታተል፣
3) በውጤት ተኮር ስርዓት ትግበራ ዙሪያ ቴክኒካዊ ድጋፍና ምክር መስጠት፣
4) በተቋም፣ በስራ ክፍሎች እንዲሁም በፈጻሚዎች ደረጃ የተካሄደው የውጤት ተኮር አፈጻጸም ምዘና እርስ
በርሱ የተናበበና ከግሽበት የጸዳ እንዲሆን አስፈላጊውን ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፣
5) የውጤት ተኮር አፈጻጸም ምዘና ስርአቱ ለተቋሙ እያስገኘ ያለውን ውጤት መከታተልና መገምገም፣
6) በየስራ ክፍሉ የተደራጁ ቡድኖች የስራ ግምገማ ውጤታማነትን መከታተል እና መደገፍ፣
7) በተገልጋይ እና በመማማርና ዕድገት ዕይታዎች ሊካተቱ የሚገባቸውን ጉዳዮች መነሻ ለስራ ክፍሎች
በመስጠት የታቀዱ እቅዶችን አፈጻጸም መከታተል እና ድጋፍ ማድረግ፣
8) በዕቅዱ መሰረት የሥራ ክፍሎችን የለውጥ ስራዎች የአፈጻጸም ሪፖርት ከዕቅድ አንጻር መመዘን፣ የዝንባሌ
ትንተና ማዘጋጀት፣ ሞያዊ አስተያየት መስጠት፣ በግምገማ መድረኮች ማስገምገም፡፡
9) በተገልጋይና በመማማርና እድገት ዕይታ ሥራዎች ላይ ለሚኒስቴር መ/ቤቱ የስራ ክፍሎች አስፈላጊውን
ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፡፡
5.5. የሰው ኃብት ልማት እና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ተግባርና ኃላፊነት
1) የሰራተኞች የውጤት ተኮር አፈጻጸም ምዘና ውጤት ወቅቱን ጠብቆ እንዲሞላና ለሰው ኃብት ልማት እና
አስተዳደር ዳይሬክቶሬት እንዲደርስ ክትትል ማድረግ፣
2) የሰራተኞች የውጤት ተኮር የአፈጻጸም ምዘና ውጤት መረጃዎችን በማደራጀት በሰራተኞች የግል ማህደር
ላይ በማያያዝ የአፈጻጸም መረጃ ትንተና በማዘጋጀትም ጥቅም ላይ እንዲውሉ ማድረግ፣
3) ከውጤት ተኮር አፈጻጸም ውጤት በመነሳትም የሠው ኃብት ልማትን ለማሳደግ የሚያስችል አሠራር
መዘርጋት እና ተግባራዊ ማድረግ፣
5.6. የሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት

26 | P a g e
1) ከዘርፉን ተቋማት/የሥራ ክፍሎች የሚቀርቡ ዕቅድና የአፈፃፀም ሪፖርቶች ከዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ጋር
ተጣጥመው እንዲዘጋጁ ክትትልና ድጋፍ መስጠት፡፡
2) ከዘርፉን ተቋማት/የሥራ ክፍሎች የሚቀርቡ ዕቅድና የአፈፃፀም ሪፖርቶች ከዘርፈ ብዙ ጉዳዮች አንፃር
የምዘና ውጤቶችን መገምገምና ድጋፍ መስጠት
3) ለመስክ ክትትልና ድጋፍ የሚያግዙ የቸክሊስት ዝግጅቶች ከዘርፈ ብዙ ጉዳዮች አንፃር በመፈተሸ ግብዓት
መስጠት
4) የዕቅድና ሪፖርት ግምገማ መድረኮች ላይ በመገኘት ግብረ መልስ መስጠት
5) በዕቅድና በጀት ዝግጅትና ግምገማ ሂደት ላይ ከዕቅድና ፕሮግራም በጀት ቢሮ ጋር በቅንጅት መስራት
5.7. የስራ ክፍል ሀላፊዎችና ተግባርና ኃላፊነት

1) የተቋሙን ተልዕኮ፣ ዕሴቶች፣ ራዕይና ስትራቴጂ በሚገባ መረዳትና ከሠራተኞች ጋር የጋራ ማድረግ፣
2) የሥራ ክፍሉን ጠንካራና ደካማ ጎን መለየት፣
3) የተቋሙን ስትራቴጂያዊ ግብ በመመንዘር የሥራ ክፍሉን ግብ እንዲሁም የግብ መግለጫዎችን እና
የሚጠበቁ ውጤቶችን ከሠራተኛው ጋር በመሆን ማዘጋጀት፣
4) ለሠራተኞች አፈጻጸም ሪፖርት ተገቢውን ግብረ-መልስ በወቅቱ መስጠት፣
5) የሥራ ክፍሉን የአቅርቦት ችግር መፍታት፤
6) የሥራ ክፍሉን አፈጻጸም የሚሻሻልበትን ስልት መቀየስና ተግባራዊ ማድረግ፤ የሚገኙ ምርጥ
ተሞክሮዎችንም መቀመር፣
7) በራሱና በሥሩ ባሉ ሠራተኞች ዘንድ በአመለካከት፣ እውቀትና ክህሎት ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን ለመድፈን
የግል አቅም ማጎልበቻ አሰራርና ዕቅድ በማውጣት ተግባራዊ እንዲሆን አስፈላጊውን ክትትልና ድጋፍ
ማድረግ፤
8) የሥራ ክፍሉን የማብቃትና ማቅናት ሥራዎችን የመስራት እና ጥሩ የሥራ ከባቢን መፍጠር፤
9) የሥራ ክፍሉን ተከታታይ መረጃዎች ላይ በመመስረት የስራ ክፍሉንም ሆነ የሰራተኞችን

ወቅታዊ የውጤት ተኮር አፈጻጸም ግምገማና ምዘና ማካሄድ፤

27 | P a g e
5.8. የቡድን መሪዎች ተግባርና ኃላፊነት
1) የተቋሙን ተልዕኮ፣ ዕሴቶች፣ ራዕይና ስትራቴጂ በሚገባ መረዳትና ከሠራተኞች ጋር የጋራ
ማድረግ፣
2) የቡድኑን ጠንካራና ደካማ ጎን መለየት፣
3) ለሠራተኞች አፈጻጸም ሪፖርት ተገቢውን ግብረ-መልስ በወቅቱ መስጠት፣የቡድኑን አፈጻጸም
የሚሻሻልበትን ስልት መቀየስና ተግባራዊ ማድረግ፤ የሚገኙ ምርጥ ተሞክሮዎችንም መቀመር፣
4) በራሱና በሥሩ ባሉ ሠራተኞች ዘንድ በአመለካከት፣ እውቀትና ክህሎት ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን
ለመድፈን የግል አቅም ማጎልበቻ ዕቅድ በማውጣት ተግባራዊ እንዲሆን አስፈላጊውን ክትትልና
ድጋፍ ማድረግ፤
5) የሥራ ክፍሉን የማብቃትና ማቅናት ሥራዎችን የመስራት እና ጥሩ የሥራ ከባቢን መፍጠር፤
6) የሥራ ክፍሉን ተከታታይ መረጃዎች ላይ በመመስረት የቡድኑን ሆነ የሰራተኞችን ወቅታዊ
የውጤት ተኮር አፈጻጸም ግምገማና ምዘና ማካሄድ፤
5.9. የሠራተኛ ተግባርና ኃላፊነት
1) የተቋሙን ተልዕኮ፣ ራዕይ፣ ዕሴቶችና ስትራቴጂዎች በሚገባ መረዳት፣
2) የተመደቡበትን የሥራ መደብ ኃላፊነትና ተግባራት በሚገባ ማወቅ፣ መረዳትና ራስን ለትግበራ
ዝግጁ ማድረግ፣
3) የውጤት ተኮር ስርአትን በአግባቡ መረዳትና ተግባራዊ ማድረግ፣
4) የግለሰብ የውጤት ተኮር ዕቅድ አዘጋጅቶ መፈጸም፣
5) በተጨባጭ የአፈጻጸም መረጃ ላይ በመመስረት አሠራርን ለማሻሻል ተገቢውን ጥረት ማድረግ፣
6) ከአመለካከት፣ ከዕውቀትና ከክህሎት አንጻር ጠንካራና ደካማ ጎኖችን መለየትና የመፈጸም
አቅምን ለማሳደግ ተገቢውን ጥረት ማድረግ፣
7) ሚዛናዊ በሆነ መልኩ የባህሪ ምዘና ውጤት መስጠት፣
8) በሳምንታዊ የስራ አፈጻጸም ግምገማዎች ወቅት ንቁ ተሳትፎ ማድረግ፣
9) በእቅድ ዝግጅት፣ በአፈጻጸም ሪፖርት ዝግጅት በክትትልና ግምገማ እንዲሁም በምዘና ወቅት
የድርሻውን አስተዋጽኦ መወጣት፣

28 | P a g e
ክፍል ስድስት

ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች

1) የውጤት ተኮር ስርዓት ውስጥ ያልገቡ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱና የተጠሪ ተቋማት የሥራ ክፍሎች ሌሎች
በመመሪያው ውስጥ የተቀመጡት ጉዳዮች እንደተጠበቁ ሆነው የምዘና ነጥብ አሰጣጡ የውስጥ አሰራር
ዕይታ ከ 55% ተመዝኖ ውጤቱ ወደ 100% ተለውጦ ይቀመጣል፡፡
2) በወሊድ ምክንያት ስራ ላይ የማይገኙ ሴት ሰራተኞችን በሚመለከት ከወሊድ ፍቃድ ጋር በተያያዘ ምዘናው
በሚካሄድበት ግማሽ ዓመት ውስጥ ሶስት ወር እና በላይ በስራ ገበታቸው ላይ ከተገኙ ስራ ላይ የነበሩበት
ጊዜ ታስቦ የውጤት ተኮር ስራ አፈጻጸም ምዘና ይሞላላቸዋል፤ ስራ ላይ የተገኙበት ጊዜ ከሶስት ወር በታች
ከሆነ ግን ከዚያ በፊት የነበረው ግማሽ ዓመት የውጤት ተኮር ስራ አፈጻጸም ምዘና ውጤት እንዲያዝላቸው
ይደረጋል፣
3) በህክምና የተረጋገጠ ስራ ለመስራት የማያስችል ህመም፤ በማረሚያ ቤት ሆኖ ጉዳዩን በወቅቱ ለሚሰሩበት
ተቋም ማሳወቅ ያልቻሉ እና በሰው ሰራሽ፣ በተፈጥሮ አደጋ ምክንያት ወይም ደግሞ መስሪያ ቤቱ
ባወቀውና ተቀባይነት ባለው በሌላ ምክንያት፣ በመደበኛ ሥራቸው ላይ ያልተገኙ እና ህጋዊ ማስረጃ
ማቅረብ የሚችሉ ሰራተኞችን በሚመለከት ምዘናው በሚካሄድበት ግማሽ ዓመት ውስጥ ሶስት ወር እና
በላይ በሥራ ገበታቸው ላይ መገኘታቸው ከተረጋገጠ ስራ ላይ የነበሩበትን ጊዜ መሰረት ያደረገ የውጤት
ተኮር ስራ አፈጻጸም ምዘናና ይሞላላቸዋል፣ ከሶስት ወር ካነሰ ግን ከዚያ በፊት የነበረው ግማሽ ዓመት
የውጤት ተኮር ስራ አፈጻጸም ምዘና ውጤት እንዲያዝላቸው ይደረጋል፣
4) ለሙከራ ጊዜ የተቀጠሩ ሰራተኞች አፈጻጸም በዚህ መመሪያ መሰረት የቋሚ ሰራተኞች የውጤት ተኮር ስራ
አፈጻጸም ምዘና አሞላል ስርዓትን በመከተል የሚፈጸም ሆኖ የሙከራ ጊዜው የሚጠናቀቀው ከግማሽ
ዓመት አፈጻጸም ምዘና ወቅት ጋር በአንድ ጊዜ ከሆነና ሰራተኛው በሙከራ ምዘና ውጤቱ ቋሚ ሆኖ
ከተቀጠረ የሙከራ ጊዜ ምዘና ውጤቱ የግማሽ ዓመት አፈጻጸም ውጤት ተደርጎ ይያዛል፡፡ ከዚያ ውጭ
ከሆነ ቋሚ ከሆነበት ጊዜ በኋላ ላለው ጊዜ የውጤት ተኮር አፈጻጸም ምዘና የሚሞላለት ይሆናል፣
5) በዝውውር የሚመጡ ሰራተኞች በምዘናው ወቅት ሶስት ወር እና በላይ በተዛወሩበት መስሪያ ቤት ከሰሩ
ይኸው ተመዝኖ የግማሽ ዓመት የምዘና ውጤት ሆኖ የሚሞላላቸው ሲሆን የሰሩበት ጊዜ ከሶስት ወር
በታች ከሆነ በፊት በነበሩበት መስሪያ ቤት ውጤታቸውን ተመዝኖ መምጣት አለበት፣
6) በዕቅድ ውስጥ ያልተካተቱና በበላይ አመራሩ አስፈላጊነታቸው ታምኖበት እና ተረጋግጦ የሚሰጡ ተጨማሪ
ስራዎች እንዲሁም ከተቋሙ ተልዕኮ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ወር እና ከዛ በላይ ጊዜ የሚወስዱ የኮሚቴ
ስራዎች ክብደት ተሰጥቷቸውና በመረጃ ተደግፈው የምዘና ሂደቱ ውስጥ የሚካተቱ ሲሆን አፈጻጸሙም
የኮሚቴ አባላት እንደ ቡድን በመገምገም፣ የአፈጻጸም ምዘና በማድረግና በኮሚቴው ሰብሳቢ በማጸደቅ
ውጤቱ ለሚመለከታቸው የስራ ሂደቶች እንዲደርስ በማድረግ ይሆናል፡፡ ለሰራተኛው ከወረዱለት ግቦች
ምዘና ውጤት በተጨማሪ በኮሚቴ ያከናወነው ስራ ተደማሪ ሆኖ ውጤቱ ከመቶኛ የሚጠቃለል ይሆናል፡፡
7) የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ዘርፍ ፖሊሲ ጥናት አማካሪ ቢሮና የሚኒስትሮች ልዩ ረዳቶች የአፈፃፀም
ምዘና በልዩ ሁኔታ በበላይ አመራሮች የሚመዘን ይሆናል፡፡

29 | P a g e
የተሻሩ ህጎች

ከዚህ መመሪያ ጋር የሚቃረን ማንኛውም መመሪያ ወይም የአሰራር ልማድ በዚህ መመሪያ ላይ በተሸፈኑ
ጉዳዮች ላይ ተፈጻሚነት አይኖረውም፣

መመሪያውን አለመፈጸም የሚያስከትለው ተጠያቂነት

1) ይህ መመሪያ አለመፈጸሙ ሲረጋገጥ መመሪያው እንዳይፈጸም ባደረገ ማንኛውም አካል ላይ አግባብ


ባለው ህግ፣ በፌደራል የመንግሥት ሠራተኞች አዋጅ፣ ደንብና የፐብሊክ ሰርቪስ የሥራ መመሪያዎች
መሠረት እንደ ጥፋቱ ሁኔታ እየታየ ቀላልና ከባድ የዲሲፕሊን ቅጣት ሊወሰን ይችላል፣
2) ቀላልና ከባድ የዲሲፕሊን ቅጣት የሚወሰነው ኃላፊው ወይም ሠራተኛው ተጸጽቶ እንዲታረምና
ብቁ መሪ/ሠራተኛ እንዲሆን ለማስቻል ወይም የማይታረም ሆኖ ሲገኝ ለማሰናበት ነው፣

መመሪያውን ስለማሻሻል

አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ይህ መመሪያ በከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ሊሻሻል ይችላል፡፡

መመሪያው የሚፀናበት ጊዜ

ይህ መመሪያ ---------------- ቀን 2012 ዓ/ም ጀምሮ የፀና ይሆናል፡፡

አይሻ መሐመድ (ኢንጂነር)


የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ሚኒስትር
------- 2012
አዲስ አበባ

30 | P a g e
አባሪዎች

31 | P a g e
ቅጽ-1

የግለሰብ ፈፃሚዎች የ 6 ወር የባህሪ መገምገሚያ መነሻ መስፈርት ቅጽ

ምዘናው የተሞላለት ፈጻሚ ስም ምዘናውን የሞላው ሃላፊ ስም___________

የአፈጻጸም ደረጃ
ተ/ቁ የባህሪ መገለጫ መስፈርቶች ለመስፈርቱ አስተያየት
የተሰጠው ክብደት 5 4 3 2 1
1 የተቋምን ራዕይና ዕሴቶች ተላብሶ ስራን መተግበር 10 %

2 የቅርብ ሀላፊን ሳይጠብቅ ስራን ማከናወን 10 %

3 ከስራ ክፍሉ ሰራተኞች ጋር በመግባባትና በቡድን ስሜት መስራት 15 %

4 ልምድን በማካፈል ሌሎች በአመለካከት፣ በክህሎትና በዕውቀት ያለባቸውን 15 %


ክፍተት ለመሙላት ያለ ጥረት

5 ለውጥ የሚያመጡ አዳዲስ ሀሳቦችንና አሰራሮችን ማመንጨትና መተግበር 15%

6 ተገልጋዮችን በተገቢው ክብር እና በስነምግባር ማስተናገድ


10 %
7 ታታሪ እና ስራ ወዳድ መሆን 10 %

8 ከሙስናና ብልሹ አሰራር በመራቅ በመልካም ስነምግባርና ተልዕኮ 15 %


ፈጻሚነት ለሌሎች ምሳሌ መሆን የተቋሙን ንብረት በአግባቡ የመያዝ እና
መጠቀም
የተጠቃለለ ውጤት 100%

ማስታወሻ ፡-

ከላይ የተመለከቱት መስፈርቶች በየሳምንቱ ከመመማርና ዕድገት ግቦች ጋር በመተሳሰር ከዕለት ተዕለት ስራ ጋር በተያያዘ መልኩ
መታቀድ፣ መተግበርና መገምገም አለባቸው፡፡ ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ በግማሽ ዓመቱ መጨረሻ ላይም አጠቃላይ የሰራተኛ ባህሪ
ከ 30% በዚህ ቅጽ የሚመዘን ይሆናል፡፡ ተቋሙ እንደ ተልዕኮው እና የስራ ባህሪው ሁኔታ ሌሎች የባህሪ መገምገሚያ መስፈርቶች
ካሉት በመጨመርም ሆነ ያሉትን በማጣጣም ቅጹን በማሻሻልና በተቋሙ የስራ አመራር ኮሚቴ በማጸደቅ ሊጠቀም ይችላል፡፡

ቅጽ- 2

9. የስራ ክፍል መሪዎች የ 6 ወር የአፈጻጸም ምዘና ማጠቃለያ

የሠራተኛው ሙሉ ስም ከነአያት የሥራ መደቡ መጠሪያ ደረጃ

32 | P a g e
የሥራ ሂደት መጠሪያ

የአፈጻጸም ምዘናው ጊዜ ከ እስከ

የአፈፃፀም ምዘናው ውጤት መግለጫ

የውጤት ተኮር ዕቅድ አፈፃፀም


ስራዎች በሚከናወንበት ሂደት አስፈላጊ የሆኑ ባህሪያት
የምዘና ጊዜያት አፈፃፀም (30%)
አፈፃፀምን ከእቅድ ጋር በማነፃፀር
በቡድን የተሰጠ የአፈፃፀም ደረጃ
(70%) በቅርብ ኃላፊ የተሰጠ
ውጤት
ውጤት (20%)
(10%)
የግማሽ ዓመት የተጠቃለለ
አፈፃፀም

በአፈፃፀም ወቅት ሰራተኛው ያሳያቸው ጠንካራ ጎኖች

በአፈፃፀም ወቅት በሰራተኛው የታዩና መስተካከል የሚገባቸው ክፍተቶች

የቅርብ ኃላፊው ሙሉ ስም ፊርማ ቀን

በውጤት ተኮር አፈጻጸም ምዘና ውጤት ተስማምቻለሁ

የሰራተኛው ስም ፊርማ ቀን

በውጤት ተኮር አፈጻጸም ምዘናው ውጤት በሚከተለው ምክንያት አልተስማማሁም

የሰራተኛው ስም ----------------------------ፊርማ ቀን -----------------------

ቅጽ -3

የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የሁለተኛ ግማሽ ዓመት የዓመት ማጠቃለያ የአፈጻጸም ደረጃ
የአፈጻጸም ውጤት የአፈጻጸም ውጤት (አማካይ የአፈጻጸም
ውጤት)

33 | P a g e
የስራ አፈጻጸም ግምገማውን ያጸደቀው ሃላፊ አስተያየት

ፊርማ ________________ቀን ________________

የፈጻሚው አስተያየት

ፊርማ ________________ቀን ________________

10. የግለሰብ ፈጻሚ የዓመቱ ምዘና ማጠቃለያ ቅጽ

ቅጽ -4
11. የሀላፊ የመሪነት ክህሎትና ብቃት የአፈጻጸም መመዘኛ ቅጽ

ምዘናው የተሞላለት ሀላፊ ስም ምዘናውን የሞላው የቅርብ ሃላፊ ስም -----------------

ለመስፈርቱ የአፈጻጸም ደረጃ


ተ/ቁ የአመራርንት ክህሎትና ብቃት መገለጫ መስፈርቶች የተሰጠው ውጤት አስተያየት
ክብደት 5 4 3 2 1

34 | P a g e
1 አፈጻጸምን የመከታተል፣ወቅታዊ ግብረ-መልስ የመስጠት ብቃት እና 10 %
ሠራተኞችን የመደገፍና የማብቃት አቅም

2 የስራ ክፍሉን በማስተባበር በቡድን አግባብ የመምራት ብቃት 10 %

3 በስራ ክፍሉ ተልዕኮዎች ላይ ያለው ተጨባጭ የዕውቀትና 10 %


የክህሎት ደረጃ
4 የሙስናና ብልሹ አሰራር አመለካከትና ተግባርን መራቅና የመታገል 10 %
ሁኔታና የተቋሙን ንብረት በአግባቡ የመያዝ እና መጠቀም

5 ህዝብን የማገልገልና ህዝብን ጥቅም የማስቀደም ብቃት 10 %

6 በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ተልዕኮን የመወጣት ብቃት እና ከተቋም 10 %


የሚሰጥን ተልዕኮ በወቅቱ የመፈጸም ብቃት

7 ምላሽ ሰጪነት 10 %

8 እንደተቋም በማስብ ስራን ከሌሎች የስራ ክፍሎች ጋር በቅንጅት የመምራት 10 %


ብቃት

9 ውሳኔ የመወሰን ቁርጠኝነት እና ብቃት 10 %

10 ለውጥ የሚያመጡ አዳዲስ ሀሳቦችንና አሰራሮችን ማመንጨትና መተግበር 10%

የባህሪ ውጤት ድምር የመዛኙ ድርሻ


መቶኛ ውጤት

የባህሪ ውጤት ከ ከ 30 % የተቀየረ

የዕቅድ አፈጻጸም ውጤት ከ ከ 70 %

የተጠቃለለ የኃላፊው ውጤት ከ 100 %

ምዘናው የተሞላለት ሀላፊ ስም ምዘናውን የሞላው ስም ________________

ፊርማ__________

ቀን________

35 | P a g e
ቅጽ- 5

12. የህዝብ አደረጃጀቶች የስራ ክፍል አፈጻጸም መመዘኛ ቅጽ (10%)

ምዘናው የተሞላለት ስራ ክፍል ስም፡ _______________________

ለመስፈርቱ የአፈጻጸም ደረጃ ውጤት


ተ/ቁ መመዘኛ መስፈርቶች የተሰጠው 5 4 3 2 1 አስተያየት
ክብደት
1 የህዝብ አደረጃጀቱን በዕቅድ ዝግጅትና አፈጻጸም 10 %
ውይይት ላይ በተቀመጠው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት
ከማሳተፍ ብቃት
2 ህዝብን የማገልገልና ህዝብን ጥቅም የማስቀደም ብቃት 15 %

3 የስራ ክፍሉን የዜጎች ቻርተር ለተገልጋዩ/ዜጋው ግልጽ 15 %


የማድረግና በስታንዳርዱ መሰረት አገልግሎት የመስጠት
ብቃት

4 በዜጋው/በተገልጋዩ የሚሰጡ አስተያየቶችን በመቀበልና 10 %


እንደ ግብአት ወስዶ ማስተካከያ የማድረግ ብቃት

5 የተለዩ የውጭ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን 15 %


በተቀመጠው እቅድ መሰረት የመፍታት ብቃት
6 የስራ ክፍሉ አመራር ቁርጠኛ ሆኖ ዘርፉን አውቆ 10 %
የመምራት ብቃት

7 የተለዩ ኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና ተግባርን 15 %


በስትራቴጂው መሰረት የመቀነስ ብቃት

8 ስታንዳርድ፤ ኮድና የማስፈፀሚያ ስትራቴጂ በማዘጋጀት 10 %


የህዝብ አደረጃጀት ችግሮችን መፍታት

የተጠቃለለ ውጤት (100%) 100 % ከ 5 % የተቀየረ

የህዝብ አደረጃጀት ተወካይ ስም ________________


ፊርማ__________
ቀን________

36 | P a g e
ቅጽ 6፡ የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር የውስጥ ተገልጋይ እርካታ ደረጃ ምዘና ቅጽ
የመዛኝ ቢሮ ስም፡ __________________________________________ የምዘናው ጊዜ : ___________
ተ የተገልጋዩ የእርካታ ደረጃ
የውስጥ ተገልጋይ እርካታ ደረጃ መለኪያ መስፈርቶች
ቁ. 5 4 3 2 1 0
1 በዕቅድ፣ ሪፖርት፣ አፈጻጸም ክትትል፣ ግምገማ፣ ምዘና እና ከሌሎች የድጋፍ አገልግሎቶች አንጻር የዕቅድና ፕሮግራም በጀት
ቢሮ የሰጠው ድጋፍ ወቅታዊና የተሟላ ከመሆን አንጻር ለመዛኙ ቢሮ ያስገኘው የእርካታ ደረጃ፣
2 በሚኒ ካቢኔ እና በበላይ አመራሩ የተሰጡ ውሳኔዎች፣ የስብሰባ አጀንዳዎች፣ የጊዜ ሰሌዳን በወቅቱ በማሳወቅ እና
በአፈጻጸማቸው ላይ ከመደገፍ እንዲሁም ከሌሎች የድጋፍ አገልግሎቶች አንጻር የሚኒስትር ጽ/ቤት የሰጠው ድጋፍ ወቅታዊና
የተሟላ ከመሆን አንጻር ለመዛኙ ቢሮ ያስገኘው የእርካታ ደረጃ፣
3 በሴቶች፤ህፃናትና ወጣቶች ፍትሃዊ ተጠቃሚነትና የድጋፍ አገልግሎቶች ዙሪያ የሴቶች፤ህፃናትና ወጣቶች ዳይሬክቶሬት
የሰጠው ድጋፍ ወቅታዊና የተሟላ ከመሆን አንጻር ለመዛኙ ቢሮ ያስገኘው የእርካታ ደረጃ፣
4 በለውጥ መሳሪያዎችና ፕሮግራሞች ትግበራ፣ ምዘና እና ከሌሎች የድጋፍ አገልግሎቶች አንጻር የለውጥና ሰው ሀብት ልማትና
አስተዳደር ቢሮ የሰጠው ድጋፍ ወቅታዊና የተሟላ ከመሆን አንጻር ለመዛኙ ቢሮ ያስገኘው የእርካታ ደረጃ
5 ለአገልግሎትና ድጋፍ ጥያቄዎች እና በሌሎች የድጋፍ አገልግሎቶች የኮርፖሬትና ሀብት ሥራ አመራር ቢሮ የሰጠው ድጋፍ
ወቅታዊና የተሟላ ከመሆን አንጻር ለመዛኙ ቢሮ ያስገኘው የእርካታ ደረጃ፣
6 ኢኮቴ በብቃት እና በውጤታማነት ለመጠቀም (ሲስተም ዝርጋታ፣ ስልጠና እና ጥገና) እና ከሌሎች የድጋፍ አገልግሎቶች
አንጻር የኢንፎርሜሽን ተክኖሎጂና ዳታ ቤዝ ልማት ቢሮ የሰጠው ድጋፍ ወቅታዊና የተሟላ ከመሆን አንጻር ለመዛኙ ቢሮ
ያስገኘው የእርካታ ደረጃ፣
7 በልማታዊ ኮሙኒኬሽን እና በሌሎች የድጋፍ አገልግሎቶች ዙሪያ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት የሰጠው ድጋፍ ወቅታዊና
የተሟላ ከመሆን አንጻር ለመዛኙ ቢሮ ያስገኘው የእርካታ ደረጃ፣
8 ከኦዲት አገልግሎት እና ከሌሎች የድጋፍ አገልግሎቶች ጋር ተያይዞ የኦዲት ዳይሬክቶሬት የሰጠው ድጋፍ ወቅታዊና የተሟላ
ከመሆን አንጻር ለመዛኝ ቢሮ ያስገኘው የእርካታ ደረጃ፣
9 ከስነ ምግባርና የሀብት ብክነትን ከመከላከል እና ከሌሎች የድጋፍ አገልግሎቶች ጋር ተያይዞ የስነ ምግባርና ፀረ ሙስና
ዳይሬክቶሬት የሰጠው ድጋፍ ወቅታዊና የተሟላ ከመሆን አንጻር ለመዛኝ ቢሮ ያስገኘው የእርካታ ደረጃ፣
10 የከተማ ፕላን ዝግጅት ትግበራና ክትትል ቢሮ የድጋፍ አገልግሎት ለማግኘት ማሟላት የሚገባውን በትክክል ወቅቱን ጠብቆ
ከማሟላት፣ ከሌሎች ሥራ ክፍሎች ጋር በቅንጅት ከመስራት እና ከምላሽ ሰጪነት አንጻር ለመዛኙ ቢሮ ያስገኘው የእርካታ
ደረጃ፣
11 የመሬት ልማትና ማኔጀመንት ቢሮ የድጋፍ አገልግሎት ለማግኘት ማሟላት የሚገባውን በትክክል ወቅቱን ጠብቆ ከማሟላት፣
ከሌሎች ሥራ ክፍሎች ጋር በቅንጅት ከመስራት እና ከምላሽ ሰጪነት አንጻር ለመዛኙ ቢሮ ያስገኘው የእርካታ ደረጃ፣
12 የከተሞች አየር ንብረት ተፅዕኖ መቋቋሚያ ቢሮ የድጋፍ አገልግሎት ለማግኘት ማሟላት የሚገባውን በትክክል ወቅቱን ጠብቆ
ከማሟላት፣ ከሌሎች ሥራ ክፍሎች ጋር በቅንጅት ከመስራት እና ከምላሽ ሰጪነት አንጻር ለመዛኙ ቢሮ ያስገኘው የእርካታ
ደረጃ፣
13 የከተሞች መልካም አስተዳደርና አቅም ግንባታ ቢሮ የድጋፍ አገልግሎት ለማግኘት ማሟላት የሚገባውን በትክክል ወቅቱን

37 | P a g e
ጠብቆ ከማሟላት፣ ከሌሎች ሥራ ክፍሎች ጋር በቅንጅት ከመፈጸም እና ከምላሽ ሰጪነት አንጻር ለመዛኙ ቢሮ ያስገኘው
የእርካታ ደረጃ፣
14 የከተሞች ገቢ ማሻሻያ ፈንድ ሞቢላይዜሽንና ፋይናንስ ቢሮ የድጋፍ አገልግሎት ለማግኘት ማሟላት የሚገባውን በትክክል
ወቅቱን ጠብቆ ከማሟላት፣ ከሌሎች ሥራ ክፍሎች ጋር በቅንጅት ከመስራት እና ከምላሽ ሰጪነት አንጻር ለመዛኙ ቢሮ
ያስገኘው የእርካታ ደረጃ፣
15 የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ የድጋፍ አገልግሎት ለማግኘት ማሟላት የሚገባውን በትክክል ወቅቱን ጠብቆ ከማሟላት፣
ከሌሎች ሥራ ክፍሎች ጋር በቅንጅት ከመስራት እና ከምላሽ ሰጪነት አንጻር ለመዛኙ ቢሮ ያስገኘው የእርካታ ደረጃ፣
16 የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ተወዳዳሪነት ማበልፀጊያ ቢሮ የድጋፍ አገልግሎት ለማግኘት ማሟላት የሚገባውን በትክክል
ወቅቱን ጠብቆ ከማሟላት፣ ከሌሎች ሥራ ክፍሎች ጋር በቅንጅት ከመስራት እና ከምላሽ ሰጪነት አንጻር ለመዛኙ ቢሮ
ያስገኘው የእርካታ ደረጃ፣
17 የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ አሰራር ማሻሻያ ቢሮ የድጋፍ አገልግሎት ለማግኘት ማሟላት የሚገባውን በትክክል ወቅቱን
ጠብቆ ከማሟላት፣ ከሌሎች ሥራ ክፍሎች ጋር በቅንጅት ከመስራት እና ከምላሽ ሰጪነት አንጻር ለመዛኙ ቢሮ ያስገኘው
የእርካታ ደረጃ፣
18 የኮንስትራክሽን ምክር ቤትና ባለድርሻ አካላት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት የድጋፍ አገልግሎት ለማግኘት ማሟላት የሚገባውን
በትክክል ወቅቱን ጠብቆ ከማሟላት፣ ከሌሎች ሥራ ክፍሎች ጋር በቅንጅት ከመስራት እና ከምላሽ ሰጪነት አንጻር ለመዛኙ
ቢሮ ያስገኘው የእርካታ ደረጃ፣
19 የመንግስት ህንጻዎች ግንባታ ፕሮጀክት ጽ/ቤት የድጋፍ አገልግሎት ለማግኘት ማሟላት የሚገባውን በትክክል ወቅቱን ጠብቆ
ከማሟላት፣ ከሌሎች ሥራ ክፍሎች ጋር በቅንጅት ከመስራት እና ከምላሽ ሰጪነት አንጻር ለመዛኙ ቢሮ ያስገኘው የእርካታ
ደረጃ፣

ማሳሰቢያ፣
1) የድጋፍ ሰጪ ቢሮዎች በዚህ መመዘኛ ከ 10% ይመዘናሉ፣
2) ዓላማ አስፈጻሚ ቢሮዎች በዚህ መመዘኛ ከ 5% ይመዘናሉ፣
3) ሁሉም ቢሮዎች ራሳቸውን አይመዝኑም፣
4) ዜሮና 5 ውጤት ከተሰጠ ምክንያት መጻፍ ይኖርበታል፡፡

38 | P a g e

You might also like