You are on page 1of 18

HELVETAS Swiss Intercooperation Ethiopia- SKY Project

ሄሌቬታስ ስዊዝ ኢንተርኮኦፐሬሽን ስካይ ፕሮጀክት

የሕይወት ክህልት የሥሌጠና ማኑዋሌ

አዘጋጅ፡ ስካይ ፕሮጀክት ጽ/ቤት


ባህር ዲር
2010 ዓ.ም

Life Skills Training 2017 Page 1


HELVETAS Swiss Intercooperation Ethiopia- SKY Project

ማውጫ

ይዘት ገጽ

1. መግቢያ .................................................................................................................................................. 3
1.1. የሕይወት ክህልት ምንዴን ነው? .................................................................................................. 3
1.2. የሕይወት ክህልት ትምህርት ዓሊማዎች ................................................................................... 3
1.3. የሕይወት ክህልት ትምህርት መርሆች ..................................................................................... 3
1.4. የሕይወት ክህልት ዓይነቶች ....................................................................................................... 4
1.5. የሕይወት ክህልት ትምህርት ጥቅሞች...................................................................................... 4
2. እሴቶችን ማወቅና መሇየት/Knowing and Identifying Values/.................................................... 5
3. ሥነሌቦናዊና ማኅበራዊ ክህልት/Psychosocial Skills/................................................................... 5
3.1. ራስን ማወቅና ራስን ከማወቅ ጋር የተዛመደ ክህልቶች ......................................................... 5
3.1.1. ራስን ማወቅ/Self-awareness/ .......................................................................................... 5
3.1.2. ራስን መገምገም/ Evaluating oneself/............................................................................. 7
3.1.3. ግብን ማስቀመጥ/Setting Goals/ ...................................................................................... 7
3.1.4. የግብ ምንነትና ጠቀሜታ/Concept and Importance of Goals/.................................. 8
3.1.5. ስሜትን የመቆጣጠር ክህልት/Controlling Emotions/ .................................................. 8
3.2. ማኅበራዊ ክህልት/Social Skills/ .............................................................................................. 8
3.2.1. ውጤታማ የሆነ የሀሳብ ሌውውጥ/Effective Communication/...................................... 8
3.2.2. ሌበ ሙለነት፣ ሇዘብተኝነትና ሞገዯኛነት ....................................................................... 11
3.2.3. የአቻ ግፊትን መሇየትና መቋቋም/Identifying &Coping Peer Pressure/ ............... 13
3.2.4. ግጭትን መፍታት/Resolving Conflicts / ..................................................................... 14
3.2.5. አሳቢነት ወይም ሀዘኔታ/Empathy/ ................................................................................. 16
3.2.6. ችግሮችን የመፍታት ክህልት/ Problem Solving/ ........................................................ 16
3.2.7. የውሳኔ አሰጣጥ ክህልት/Decision-making/ .................................................................. 17

Life Skills Training 2017 Page 2


HELVETAS Swiss Intercooperation Ethiopia- SKY Project

1. መግቢያ
1.1. የሕይወት ክህልት ምንዴን ነው?

የሕይወት ክህልት ሰዎች ሇዕሇት ተዕሇት ኑሯቸው የሚያስፈሌጋቸውን ፍሊጎት


ሇማሟሟሊትና የሚያጋጥሟቸውን ፈተናዎች በአወንታዊ መሌኩ ሇመፍታት የሚጠቀሙበት
አቅምና ብቃት ነው፡፡

የሕይወት ክህልት የሰውን ሌጅ ባህሪ በመሇወጥና በማሳዯግ ሊይ መሠረት ያዯረገ


ሌምምዴና ተከታታይ ትምህርት በመስጠት የሚገኙ ሲሆን ሂዯቱ ዕውቀትን፣
አመሇካከትንና ክህልትን በተመጣጠነ ሁኔታ በማሳዯግ ሊይ ያተኩራሌ፡፡

የሕይወት ክህልት በዕሇት ከዕሇት የማኅበረሰብ የአኗኗር ዘዳዎች፣ በሕይወት ገጠመኞች፣


በአንዴ ተግባር ሊይ ዯጋግሞ በመሳተፍ እንዱሁም ተከታታይ በሆነ ሥሌጠናና ትምህርት
ሉዲበር ይችሊሌ፡፡

1.2. የሕይወት ክህልት ትምህርት ዓሊማዎች


 ወጣቶች ራሳቸውንም ሆነ ማኅበረሰባቸውን በተገቢው መንገዴ ተገንዝበው
ጤናማ ሕይወት ሇመኖር የሚያስችሊውን እውቀትና ችልታ ማስረጽ፣
 አዎንታዊና ውጤታማ የሆኑ አማራጮችን በመውሰዴ ጤናማና በጎ ጠባያትን
እንዱያዲብሩ ማዴረግ፣
 በመረጃ፣ በዕውቀት በክህልት ሊይ መሠረት ያዯረጉ ውሳኔዎችን የመወሰን ብቃት
እንዱያዲብሩ ማዴረግ፤
 በሕይወት የሚያጋጥሙ የተሇያዩ ፈተናዎችንና ሇአዯጋ የሚያጋሌጡ ጎጂ
ጠባያትን ሇይተው በማወቅ ችግሮቹን ሇማስወገዴ የሚጠቅም ዕውቀትና ክህልት
ማስጨበጥ፣

1.3. የሕይወት ክህልት ትምህርት መርሆች

አሳታፊነት፡ ተሳታፊነትን የማበረታት፣ የመዯማመጥ፣ የላልችን አመሇካከት የማክበርና


በመግባባት ሀሳብን የመግሇጽ ነጻነትን ማረጋገጥ፣
በጎ ፈቃዯኝነት፡ የሕይወት ክህልት ሥሌጠና የሚከተሌ ወጣት/ግሇሰብ ክህልቱን በብቃት
ሇመጨበጥ ሙለ ፍሊጎት ያሇውና ፈቃዯኛ መሆን ይገባዋሌ፡፡
ሥርዓተ ጾታ ተኮርነት፡ ሴቶች በማኅበረሰባቸው የፖሇቲካ፣የኢኮኖሚ፣ ማኅበራዊና ባህሊዊ
ተጽእኖዎች የተነሳ ከወንድች የበሇጠ ሇተሇያዩ ችግሮች የተጋሇጡ ናቸው፡፡ ስሇሆነም
የሚዯርሱባቸውን ችግሮች ሇመቋቋምና ራሳቸውን እንዱከሊከለ ሇማዴረግ የሕይወት
ክህልት ትምህርት ሥርዓተ ጾታ ተኮርነት ባህርይ ያሇው መሆን ይገባዋሌ፡፡
ጠባይ ተኮርነት፡ ከተሇያዩ አዯገኛና ጎጂ የሕይወት ሌምድች ማሊቀቅ የሚቻሇው በተሇያዩ
የማስተማሪያ ስሌቶች በመጠቀም የጠባይ ሇውጥ ማምጣት ሲቻሌ ነው፡፡ ስሇሆነም
የሕይወት ትምህርት አሰጣጥ በጠባይ ሇውጥ ሊይ ያተኮረ መሆን አሇበት፡፡

Life Skills Training 2017 Page 3


HELVETAS Swiss Intercooperation Ethiopia- SKY Project

የማኅበረሰብ እሴቶችን መሠረት ማዴረግ፡ ማኅበረሰቡ ሇኑሮውና ሇሕይወቱ ጠቃሚና


ይበጃለ ያሊቸውን እሴቶች ተገንዝቦ በእነዚህ እሴቶች ሊይ የተመሠረቱ ክህልቶችን
ማዲበር፡፡
1.4. የሕይወት ክህልት ዓይነቶች
የሕይወት ክህልት በአራት ዋና ዋና ክፍልች ይከፈሊለ፡፡ እነርሱም፡-

 አካሊዊ ክህልት
 አእምሯዊ ክህልት
 ቴክኒካዊና ሙያዊ ክህልት
 ሥነ ሌቦናዊና ማኅበራዊ ክህልት

አካሊዊ ክህልት፡- ሰዎች በአካሊዊ እንቅስቃሴ አማካኝነት ሌዩ ሌዩ ተግባራትን ሇማከናወን


የሚያስችሊቸው ብቃት ነው፡፡
ምሳላ፡ሩጫ፣ ጭፈራ፣ እስክስታ፣ ....
አእምሯዊ ክህልት፡- ሰዎች በማኅበረሰብ ውስጥ ሲኖሩ በሌዩ ሌዩ ጉዲዮች ሊይ ውሳኔ
ሊይ ሇመዴረስ የሁኔታችንና የክስተቶችን ሌዩ ሌዩ ገጽታዎች የሚያመዛዝኑበት ችልታ
ነው፡፡
ምሳላ፡ ሂሳብ ማስሊት፣ ሚዛናዊ ውሳኔ መስጠትና መተንተን፣...
ቴክኒካዊና ሙያዊ ክህልት፡- የቁሳዊ ነገሮችና የመገሌገያ መሣሪያዎችን ጠባይ ጠንቅቆ
በመረዲት ሥራዎችን ሇማከናወን የሚያስቸለ አቅሞች ናቸው፡፡
ምሳላ፡ አናጺነት፣ መካኒክነት፣ ሸክሊ ሥራ፣ ባሌትናና ዕዯ ጥበብ፣....

ሥነሌቦናዊና ማኅበራዊ ክህልት፡- በግሊዊና ማኅበራዊ ሕይወት ውስጥ የሚያጋጥሙ


ግጭቶችን፣ ቅራኔዎችንና ችግሮችን ሇመቋቋም የሚያስችለ ክህልቶች ናቸው፡፡

ምሳላ፡- በራስ መተማመን፣ የኣቻ ግፊትን መቋቋም፣ መዯራዯር፣ ውሳኔ መስጠትና ችግርን
መፍታት፣..
ሥነሌቦናዊና ማኅበራዊ ክህልቶች በሶስት ይከፈሊለ፡፡ እነርሱም፡-
 ራስን ማወቅና ራስን ከማወቅ ጋር የተዛመደ ጉዲዮች ክህልት
 ላልች ሰዎችን የማወቅና ከላልች ሰዎች ጋር አብሮ የመኖር ክህልትና
 የውሳኔ አሰጣጥ ክህልት ናቸው፡፡

1.5. የሕይወት ክህልት ትምህርት ጥቅሞች


የጤና ጥቅሞች፡ ሰዎች ጤናቸውን ሉጎደ ከሚችለ አዯገኛ ጠባያት ራሳቸውን እንዱጠብቁ
ብቃትን ይሰጣቸዋሌ፡፡

Life Skills Training 2017 Page 4


HELVETAS Swiss Intercooperation Ethiopia- SKY Project

ማኅበራዊ ጥቅሞች፡ መሌካም ማኅበራዊ ግንኙነትን ሇመመስረት፤ ሥራ አጥነትንና ላልች


ማኅበራዊ ቀውሶችን ሇመቀነስ፣ በጣም አስፈሊጊ እንዯሆነ ጥናቶች ያመሊክታለ፡፡
ባህሊዊ ጥቅሞች፡ የተሇያየ ባህሌና ሌምዴ ባሊቸው ማኅበረሰብ ውስጥ ሇሚኖሩ ሰዎች
ሌዩነቶችን አውቀው እርስ በእርስ በመከባበርና በመቻቻሌ አብሮ የመኖር ጥበብን
እንዱያጎሇብቱ ይረዲለ፡፡
ኢኮኖሚያዊ ጥቅሞች፡ ሰዎች በተሠማሩበት የስራ መስክ ሁለ ውጤታማና አትራፊ በሆነ
መሌኩ እንዱንቀሳቀሱ የሕይወት ክህልት ትምህርቶች ከፍተኛ ሚና ይጫወታለ፡፡
ፖሇቲካዊ ጥቅሞች፡ ሰዎች ፍሊጎቶቻቸውንና መብታቸውን ሇማሰከበር በሚያዯርጉት ሂዯት
ውስጥ የላልች ሰዎችን መብት ሳይነኩና ግጭት ሳይፈጥሩ ሰሊማዊ በሆነ አካሄዴ
ሃሳባቸውን መግሇጽ የሚችለበትን ጥበብና ብቃት እንዱያሳዴጉ ይረዶቸዋሌ፡፡
ትምህርታዊ ጥቅሞች፡ ሰዎች በትምህርታቸው ውጤታማ የሚሆኑበትን ብቃት ከማሳዯጉም
በሊይ በአስተማሪና በተማሪ መካከሌ ጤናማ ግንኙነት እንዱፈጠር ይረዲለ፡፡ በላሊ በኩሌ
አሳታፊ የመማማሪያ መንገድችን ማእከሌ ያዯረገ አቀራረብ በሕይወት ክህልት ትምህርት
ውስጥ ከፍተኛ ስፍራ ስሇሚሰጠው ውጤታማ የትምህርት አሰጣጥ ዘዳንም ያስተዋውቃሌ፡፡

2. እሴቶችን ማወቅና መሇየት/Knowing and Identifying Values/


እሴት አንዴ ማኅበረሰብ ወይም በማኅበረሰቡ ውስጥ የሚኖሩ ግሌሰቦችና የማኅበረሰቡ
አባሊት አስተሳሰቦችንና ዴርጊቶችን በበጎ ወይም በመጥፎነት ፈርጀው የሚያበረታቱበትን
ወይም የሚያወግዙበትን የአስተሳሰብ ሥርዓት ነው፡፡

ምሳላ፡ ዯግነትን፣ ቅንነትን በበጎ ተግባራት ፈርጀው ማበረታታት፤ ስስትንና ፈሪነትን በክፉ
ፈርጆ ማውገዝ፣

ማኅበረሰባዊ እሴቶች ማሇት ሰዎች በኅበረተሰባቸው ውስጥ እርስ በእርሳቸው የተቆራኘ


ግንኙነት እንዱኖራቸው ማኅበራዊ አንዴነትና አቅም እንዱፈጥርሊቸው የሚያግዙ ዯምቦች
እና እነዚህም የታቀፉበትን ተቋማት የሚያመሇከቱ ናቸው፡፡

ማኅበራዊ እሴቶች እንዯየማኅበረሰቡ የግሌ ሥነሌቦና የሚወሰኑ በመሆናቸው እንዯ


አካባቢው ተቀባይነት ያሊቸውና የሚበረታቱ ተግባራት በላልች አካባቢዎች ሊይበረታቱ
ይችሊለ ተቀባይነት ሊይኖራቸውም ይችሊሌ፡፡

የአንዴን ማኅበረሰብ ማኅበራዊ እሴቶች ሇማወቅ ማኅበረሰቡ በጎ ናቸው ብል


የሚቀበሊቸውን ወይም መጥፎ ናቸው ብል የሚያወግዛቸውን ዴርጊቶች የሰዎች ጠባዮችንና
የሥነ ምግባር ገጽታዎችን ማወቅ ያሻሌ፡፡ ሇምሳላ በኢትዮጵያውን ዘንዴ ዯግነት፣
ሇጋስነት፣ ጀግንነት ማኅበረሰቡ በጎ ናቸው የሚሊቸው ናቸው፡፡

3. ሥነሌቦናዊና ማኅበራዊ ክህልት/Psychosocial Skills/


3.1. ራስን ማወቅና ራስን ከማወቅ ጋር የተዛመደ ክህልቶች
3.1.1. ራስን ማወቅ/Self-awareness/

Life Skills Training 2017 Page 5


HELVETAS Swiss Intercooperation Ethiopia- SKY Project

ውዴ አመቻች፡

የሚከተሇውን ትረካ ካነበባቡ በኋሊ ከታች በቀረቡት ጥያቄዎች ሊይ እንዱወያዩ ያዴርጉ፡፡

ትረካ አንዴ

የኤሉና የሁሇት የቁራዎች ጓዯኝነት፡

አንዴ ኤሉና ሁሇት ቁራዎች ጓዯኝነት መሠረቱ፡፡ ጓዯኝነታቸው በጣም ጠንክሮ በተሇያዩ
ርዕሰ ጉዲዮች ሊይ ይወያዩ ጀመር፡፡ አንዴ ቀን ኤሉ እንዯጓዯኞቿ መብረር አማራትና
«ሇምን አሌበርም?» ስትሌ ራሷን ጠየቀች፡፡ ጓዯኞቿ ከዋለበት እንዯመጡ እሷም
እንዯነርሱ መብረር እንዲሇባት አሳመነቻቸው፡፡ ግን በራሷ አቅም መብረር ስሇማትችሌ
ሁሇቱ ቁራዎች በአፋቸው አንዴ እንጨት ይዘው ኤሉን መሃሌ በማስገባት እንጨቱን በአፏ
አስይዘው መብረር ጀመሩ፡፡ ከዚያም ኤሉ መሬት ሊለት ኤሉዎች «እናንተ ዯካሞች እንዯ
እኔ አትበሩም» ሇማሇት ፈሌጋ አፏን በመክፈቷ እንጨቱን ሇቃ ተከስክሳ ሞተች፡፡

 ይህ ትረካ ራስን ማወቅና መቀበሌ ከሚሇው ሀሳብ ጋር ያሇው ተያያዥነት


ምንዴነው?
 ራስን አውቆ አሇመቀበሌ እንዳት ሉጎዲ ይችሊሌ?
 ራስን አውቆ መቀበሌስ ምን ጥቅም አሇው?

ራስን ማወቅ አንዴ የሥነሌቦናዊና ማኅበራዊ ክህልት አካሌ እንዯመሆኑ በኅብረተሰብ


ውስጥ አወንታዊና ንቁ ሕይወት ሇመኖር ያስችሊሌ፡፡ ራስን ማወቅ በጥሌቀት በማሰብ ሊይ
የተመሠረት መሆን አሇበት፡፡ ይህም የሕይወት ውጣ ውረድችን ሇመጋፈጥ እንዱቻሌ ምን
ማዴረግ እንዯሚገባ፣ ተገቢውን ውሳኔ ሇመወሰንና ሇችግሮችም ፈጣን መፍትሔ ሇመስጠት
ያስችሊሌ፡፡ ችግርን ሇመቋቋምም ሆነ ሇመዯራዯር፣ሌዩ ሌዩ አስቸጋሪ የሕይወት ገጠመኞች
ራስን ዝግጁ ሇማዴረግ መነሻ ይሆናሌ፡፡

ራስን ማወቅ ሇራስ ከፍተኛ ግምት ወዯ መስጠት ያመራሌ፡፡ ሰዎች ስሇችልታቸውና


በማኅበረሰብ ውስጥ ስሊሊቸው ቦታ ሲያውቁ ሇራሳቸው ያሊቸው አክብሮት ይጨምራሌ፡፡
በጥሌቀት ከማሰብ የመነጨ ሇራስ የተሰጠ ከፍተኛ ግምት የራስን ጠንካራና በጎ ጎን
መረዲትን ይጨምራሌ፡፡ ይህም በራስ የመተማመን ስሜትን ያዲብራሌ፡፡

አንዴ ሰው ያሇው በራስ የመተማመን ስሜት በማኅበራዊ ግንኙነቱ ሊይ ማኅበራዊ


ግንኙነቱም በራስ የመተማመን ስሜቱ ሊይ ተጽእኖ ይኖራቸዋሌ፡፡ ግሇሰቦች
በማኅበረሰባቸው ውስጥ ያሊቸው አዎንታዊ ግንኙነት በራስ የመተማመን ስሜታቸውን
ሉያጎሇብተው ይችሊሌ፡፡

Life Skills Training 2017 Page 6


HELVETAS Swiss Intercooperation Ethiopia- SKY Project

በራስ መተማመን ወጣቶች ዯስተኞች እንዱሆኑና ሰብእናንና ጤናን ከሚጎደ ተግባራት


እንዱርቁ ያዯርጋቸዋሌ፡፡ ዝቅተኛ የሆኑ በራስ የመተማመን ጠባያት ጤናማ ያሌሆኑ
አማራጮን ያበረታታሌ፡፡

ራሳቸውን የተቀበለ ሰዎች በክህልታቸው ይኮራለ፤ ይጠቀሙባቸዋሌ፤ ያሌሆኑትን


ሇመምሰሌ አይሞክሩም፡፡ ራሳቸውን በትክክሇኛው ማንነታቸው ይገሌጻለ፡፡ እውነተኛ
ጠባያቸውን አይዯብቁም፡፡

ራሳቸውን የተቀበለ ሰዎች ሕይወታቸውን በእውነታ ሊይ ተመስርተው ይመራለ፡፡


በእውነታ ሊይ ተመስርተው ከሕይወት ውሳኔ ሊይ ይዯርሳለ፡፡ ይህም በኑራቸው ስኬታማ
እንዱሆኑ ይረዲቸዋሌ፡፡

ራስን ማወቅ፣ ሇራስ ግምት መስጠትና በራስ መተማመን ራስን ማክበርንና ራስን መቀበሌን
ያስከትሊሌ፡፡ የራሳቸውን ቤተሰባዊና ማኅበራዊ ሁኔታ የተገነዘቡ ችልታቸውንና
ውሱንነታቸውን ያወቁ ሰዎች ሇራሳቸው ግምት ይሰጣለ፤ በራሳቸው ይተማመናለ፤
ራሳቸውን ያከብራለ፡፡ ራስን ማክበርም የራስን ማንነት ሇመቀበሌ ያስችሊሌ፡፡

3.1.2. ራስን መገምገም/ Evaluating oneself/

አብዛኛውን ጊዜ ሰዎች ራሳቸውን የሚገመግሙት ሰዎች ስሇነሱ ባሊቸው አመሇካከትና


በሚሰጣቸው አስተያየቶች በመነሳት ነው፡፡ ይህ ዯግሞ ጠቃሚ ቢሆንም ራስን
ሇመገምገምና ሇራስ በምንሰጠው ግምት ዙሪያ እንዯመሠረታዊ ነገር ተቀጥሮ መወሰዴ
የሇበትም፡፡ አንዴ ሰው ስሇራሱ በማወቅ በሚያዯርገው ጥረት «ችልታ የሇኝም» ወዯሚሌ
መዯምዯሚያ ከመዴረሱ በፊት አንዲንዴ ሁኔታዎችን ተመሌሶ ሇብቻ ማጤን
ይኖርበታሌ፡፡ምክንያቱም ራሱን በመገምገም ሂዯት ክህልቱን አዲብሮ ከፍ ካሇ ዯረጃ
ማዴረስ ይችሊሌና ነው፡፡ ራስን የመገምገም ሂዯትም ቀጣይነት ያሇውና በዘሊቂነት
የሚዯረግ ተግባር ነው፡፡

3.1.3. ግብን ማስቀመጥ/Setting Goals/

ወዴ ተሳታፊዎች፡ በጋሻው ውስጥ የተካተቱትን አራቱን ጥያቄዎች በምትፈሌገው/ጊው


ሥፍራ ቁጭ በማሇትና በጥሞና በማሰብ የራስህን/ሽን ጋሻ ሠርተህ/ሽ አሳይ፡፡

Life Skills Training 2017 Page 7


HELVETAS Swiss Intercooperation Ethiopia- SKY Project

በሕይወት
ዘመኔ
እኔ ልደርስበት
ማነኝ? የምሻው ደረጃ
ምንድን ነው?
ከሞት በኋሊ
ከአሁን ጀምሮ
ሰዎች
ሇሚቀጥለት በምን
አሥር ዓመታት እንዱያስታ
ምን መሆን ውሱኝ
እፈሌጋሇሁ?
እፈሌጋሇሁ
?

3.1.4. የግብ ምንነትና ጠቀሜታ/Concept and Importance of Goals/


 ግብ አንዴ ግሇሰብ የተወሰኑ ተግባሮችን በመፈጸም ሉዯርስበት የሚሻው ውጤት
ነው፡፡
 ግብ ማስቀመጥ አንዴ ሰው በተወሰኑ ጉዲዩች ሊይ በማተኮር ወዯ ውጤት
እንዱያመራ ያግዘዋሌ፡፡
 ግብን ማስቀመጥ አንዴ ሰው በተሰጥኦውና በክህልቶቹ ሇመጠቀም ያስችሇዋሌ፡፡
 ሇምሳላ መካኒክ የመሆን ግብ ያሇው ወጣት የቴክኒክና ሙያ ክህልቶችን
ሇማዲበርና ውጤታማ ሇመሆን ይጥራሌ፡፡
 የተሇያዩ ግቦች አስቀምጦ ስኬታማ መሆን በራስ መተማመንን ያሳዴጋሌ፡፡
ያሌተሳኩ ግቦች የራስን ዴክመቶች ሇማረምና ሇማስተካከሌ ይጠቅማለ፡፡
 ግብ ማስቀመጥ ስሇራስ ማንነትና የወዯፊት ዕቅዴ ሇመግሇጽ አቅም ይፈጥራሌ፡፡

3.1.5. ስሜትን የመቆጣጠር ክህልት/Controlling Emotions/


ሰዎች ሃሳባቸውን ሇመሇዋወጥ የሰውነት እንቅስቃሴና ዴምፅን ጨምሮ በርካታ መንገድች
ይጠቀማለ፡፡
ውዴ ተሳታፊዎች፡
«ኦ፣ አበበ» የሚሇውን ሐረግ በተሇያዩ ሁኔታዎች ውስጥ ሇምሳላ የቁጣ፣ የዯስታ፣ የሳቅ፣
የፍርሃት ስሜቶችን በሚያንጸባርቅ መሌኩ ሇመግሇጽ ሞክሩ፡፡
እያንዯንደ አባሌ አንዴ ወይም ሁሇት ጊዜ ከተሳተፈ በኋሊ በሌምምዴ የተንጸባረቁትን ሌዩ
ሌዩ ስሜቶች በፊሉፕ ቻርት ጻፉ፡፡

3.2. ማኅበራዊ ክህልት/Social Skills/


3.2.1. ውጤታማ የሆነ የሀሳብ ሌውውጥ/Effective Communication/

Life Skills Training 2017 Page 8


HELVETAS Swiss Intercooperation Ethiopia- SKY Project

የሃሳብ ሌውውጥ መረጃን የመስጠት ወይም የመቀበሌ ሂዯት ሲሆን ይህ ሂዯት በሁሇት
ግሇሰቦች መካከሌ ወይም ከሁሇት በሊይ በሆኑ ሰዎች መካከሌ የሚካሄዴና ግቡም የጋራ
መረዲት ሊይ መዴረስ ነው፡፡

 ተግባቦት ማሇት ሰዎች ሃሳቸባውን ስሜታቸውን እንዱሁም መሌእክቶቻቸውን


የሚያስተሊሌፉበት ዘዳ ነው፡፡
 ስኬትን/ውጤታማነትን/ ከሚወስኑ ነገሮች አንደና ዋናው ተግባቦት ሲሆን የየዕሇት
ስሜቶቻችንም የተግባቦት ውጤቶች ናቸው፡፡
 ስሇሆነም እያንዲንደን ተግባቦት ዓይነቶች መረዲት እና እንዯ አስፈሊጊነቱ በተግባር
ሊይ ማዋሌ ይጠበቅብናሌ፡፡
 ተግባቦት/የሃሳብ ሌውውጥ ግቡ የጋራ መረዲት ሲሆን ቁሌፉ በጥሞና ማዴመጥ
ነው፡፡
የተግባቦት ዓይነቶች፡-
 የንግግር
 የጽሑፍ/የምስሌ
 የዓይን
 የዴርጊት
ስኬታማ ተግባቦት
 ተግባቦት ስኬታማ ነው የሚባሇው መሌእክቱ የታሰበሇትን ዓሊማ ሲፈጽምና
መሌእክት ተቀባዩ የተፈሇገውን ምሊሽ ሲሰጥ ነው፡፡

ሇስኬታማ ተግባቦት የሚያበቁ ሁኔታዎች፡-

 ግሌጽነት/አሽሙር ያሌተቀሊቀሇበት መቀራረብ፣


 ሰዎች ሃሳባቸውን እንዱሰጡ እዴሌ መስጠት፣
 ጥሩ አዴማጭ መሆን፣
 የምንስተሊሌፈውን መሌእክት፣ የምናስተሊሌፍበትን ዘዳና ቦታ መረዯት፣
 ከፍጹም ግዴዯሇሽነት የራቀ ትኩረትን የሚስብ አቀራረብ መከተሌ፣
 የእኔ ጉዲይ ብቻ ይቅዯም/ይፈጸም አሇማሇ፣
 የመሌእክት ተቀባዩን ትክክሇኛ ሁኔታ መረዲት፣
አስተያየት ከመስጠት/ውሳኔ ሊይ ከመዴረሳችን/ በፊት ሚዛናዊ መረጃ መያዝ

የተግባቦት ዑዯት፡- መሌእክቱ ከመሌእክት አስተሊሊፊው እስከ ተቀባዩ ዴረስ ያሇውን


ሂዯት ያሳያሌ፡፡

 መሌእክት አስተሊሊፊው
 መሌእክቱ
 የማስተሊሇፊያው ዘዳ
 መሌእክት ተቀባዩ
 ምሊሽ

Life Skills Training 2017 Page 9


HELVETAS Swiss Intercooperation Ethiopia- SKY Project

 እንቅፋቶች ናቸው፡፡
የተግባቦት ዑዯት እንዱሰምር እና የተሻሇ ዯረጃ እንዱዯርስ፡-
 ግሌጽና አጭር መሌእክት ማስተሊሇፍ፣
 ተስማሚ የሆነ የመርጃ መሣሪያ መጠቀም፣
 በመሌእክቱ ሊይ በቂ ዝግጅት ማዯረግ፣
 የምሌክት ግንኙነት ክህልትን ማሳዯግ፣
በምናሰተሊሌፈው መሌእክት እርግጠኛነት ሊይ መተማመን፣
የሃሳብ ሌውውጥ ግቡ የሆነውን የጋራ መረዲት ሲያመጣ ውጤታማ ተግባቦት ቁሌፉ
በጥሞና ማዴመጥ ነው፡፡

3.2.1.1. በጥሞና ማዴመጥ

ውዴ አመቻች፡ ተሰታፊዎችን በአራት ቡዴን በመክፈሌ በሚከተለት አጅንዲዎች ሊይ


ክርክር እንዱያካሂደ ያመቻቹ፡

 ሴት ሌጅ ወንዴን ሇፍቅር ጓዯኝነት ወይም ሇትዲር መጠየቅና ሽማግላ መሊክ


ትችሊሇች/ አትችሌም፡፡
 ከጋብቻ በፊት የግብረ ግንኙነት መጀመር/ማዴረግ/ ሇትዲር ዝግጅት ጠቃሚ
ነው/አይዯሇም፡፡

በመቀጠሌም በየቡዴኑ በመዘዋወር ክርክሩን በመከተሌ በጥሞና የማዴመጥ ሁኔታ መኖር


ያሇመኖሩን ቅኝት ያዴርጉ፡፡

3.2.1.2. የተግባቦት መሰናክልች

ተግባቦት የተዋጣ እንዲይሆን የሚያሰናክለ በሊኪና በተቀባይ መካከሌ ሉከሰቱ የሚችለ


አበይት ምክንያቶች፡-

 ተሰሚነት ሇማግኘት መፎካከር፣


 ቋንቋ
 የዕዴሜ ሌዩነት
 የማኅበራዊ ኢኮኖሚያዊ ሌዩነቶች
 የጠባይና/የምንነት ሁኔታዎች ናቸው፡፡
3.2.1.3. የተዋጣ ተግባቦት መርሆዎች

የተዋጣ ተግባቦት እንዱኖር የሚያስችለ ዋና ዋና መርሆዎች፣

 አስተማማኝ የመሌእክት ምንጭ


 አስተማማኝ መሌእክት ተቀባይ
 ስሇተቀባዩ በቂ እውቀት፣
 መሌእክቱን ግሌጽ አዴርጎ ማዯራጀት

Life Skills Training 2017 Page 10


HELVETAS Swiss Intercooperation Ethiopia- SKY Project

o የማያሻማ ቅዯም ተከተሌ የያዘ የመሌእክት አወቃቀር


o ተስማሚ የመሌእክት ማስተሊሇፊያ ዘዳ
o የተግባቦት እንቅፋቶችን በእጅጉ መቀነስ
o የተቀባዩን ምሊሽ መጠንና ግሌጽነት ማጉሊት መሆናቸውን መረዲት፣
3.2.1.4. የሃሳብ ሌውውጥ ዯረጃዎች
የሃሳብ ሌውውጦች አራት ዯረጃዎች ያሊቸው ሲሆን፡-
 ከራስ ጋር መነጋገር
 በግሇሰቦች መካከሌ ያሇ የሃሳብ መሇዋወጥ
 በቡዴን የሚዯረግ የሃሳብ መሇዋወጥና
 በአካሌና በስሜት በጊዜና በቦታ የተሇዩ ሰዎች ጋር የሚዯረግ ናቸው፡፡

3.2.2. ሌበ ሙለነት፣ ሇዘብተኝነትና ሞገዯኛነት

ትረካ ሁሇት

ካሳነሽ በአንዴ ዴርጅት ውስጥ በጊዜያዊነት በፀሐፊነት ተቀጥራ የምትሠራ የ20 ዓመት
ወጣት ነች፡፡ አንዴ ቀን አሇቃዋ ሇተከታዩ ቀን ስብሰባ የሚዯርስ በርካታ ሥራዎችን
በአስቸኳይ እንዴትሠራ አዘዛት፡፡ ተቀብሊ እንዲትሠራ ከሥራ መውጫ ሰዓቷ ዯርሷሌ፡፡
ስሇዚህ ባሇው አጭር ጊዜ ሥራውን መጨረስ እንዯማትችሌ ሇአሇቃዋ ገሇጸች፡፡ አሇቃዋም
ሥረው አስቸኳይ መሆኑን በአጽንኦት በመናገር ሁሇት አማራጮችን ሰጣት፡፡

1. አምሽታ ሥራውን እንዴትጨርስ

2. ቤቱ ሄዲ በግሌ ኮምፒውተሩ እንዴትሠራ

ይህን ማዴረግ የማትችሌ ከሆነ ከሥራ እንዯምትሰናበት አስታወቃት፡፡ ካሳነሽ ምን


ታዯርግ? አሌሠራም ካሇች ከሥራ ተባራ ራሷንና ቤተሰቧን ትጎዲሇች፡፡ የተሰጧትን
አማራጮች ከተቀበሇች ተገዲ በመዯፈር ሇኤች አይ ቪ እና የአባሊዘር በሽታዎች
ሌትጋሇጥ ትችሊሇች፡፡ ምን ታዴርግ?

3.2.2.1. ሇዘብተኝነት
 አንዴ ሰው ተገቢ ያሌሆኑ የላልች ሰዎች ሀሳቦችን ወይም ዴርጊቶችን በቸሌታ
እንዱቀበሌ ወይም እንዱመሇከት የሚያዯርግ ከዝቅተኛ የመግባባት ክህልት ወይም
ከፍርሃት የሚመነጭ ባህሪ ነው፡፡
 ሇዘብተኛ ሰው ስህተቶች ሲፈጸሙ ሀሳብ ከማቅረብ ይቆጠባሌ፡፡ ትችቶችን
ሇመሰንዘርና ሇማረሚያ ሃሳብ ሇማቅረብ ዴፍረት የሇውም፡፡ ሇዘብተኛ ሰው በዯሌ
ቢፈጸምበት እንኳን ሆዴ ይፍጀው ብል መቀበሌን ይመርጣሌ፡፡
የሇዘብኛነት/ተነሳሽነት የማጣት ጠባይ መገሇጫዎች

Life Skills Training 2017 Page 11


HELVETAS Swiss Intercooperation Ethiopia- SKY Project

 ሇላልች ፍሊጎት መሸነፍ፣ አንዴ ሰው የሚፈሌገውን ነገር ሳንጠይቅ ሇማግኘት


መመኘት /መፈሇግ/
 መብትን ሇማስከበር ምንም እርምጃ ያሇመውሰዴ
 ራስን በመጉዲት የላልችን ጥቅም ማስቀዯም
 ላልች የሚፈሌጉትን ማዴረግ
 አንዴ የሚያስጨንቅ ነገር ሲያጋጥም በዝምታ መያዝ
 አብዝቶ /ዯግሞ ዯጋግሞ/ ይቅርታ መጠየቅ
 ተሸናፊነት፣ ሇምሳላ በዝግታ መናገር፣ የጭንቀት ሳቅ፣ ትከሻ መስበቅ፣ ክርክሮችን
/ያሇመግባባትን/ ማስወገዴ፣ ፊትን በእጅ መሸፈን
3.2.2.2. ቁጡነት/ሞገዯኛነት
 ቁጡነት ከሇዘብተኛነት የሚሇይ ቢሆንም በመግባባት ሊይ የተመሠረተ ውጤትን
ሇማምጣት የሚያስችሌ ጥቅም የሇውም፡፡
 መቆጣት ስሜትን መቆጣጠር ካሇመቻሌ የሚመጣ ግሌፍተኝነት በመሆኑ በሰዎች
መካከሌ የሚፈጠር አሇመግባባትን ሇመፍታት ወይም ስህተትን ሇማረም የሚኖረው
አስተዋጽኦ ዯካማ ነው፡፡
 ቁጡነት ሃሳብን የመግሇጽና ላልችን የማስረዲት እንዱሁም የላልችን ሃሳብ
የመረዲት አቅም በማዲከም ጎጂ ውጤት ሉያስከትሌ ይችሊሌ፡፡

የቁጡነት/ሞገዯኛነት መገሇጫዎች

 ላልችን በመጫንና በማስፈራራት መሌኩ የራስን ስሜትና አስተሳሰብ መግሇጽ


 ላልች ሰዎች መብት መከበር ምንም ትኩረት ሳይሰጡ የራስን መብት ሇማስከበር
መጣር፣
 በላልች ኪሳራ ራስን አስቀዴሞ መገኘት፣
 ላልችን ከስሌጣን ሥር ሇማወሌ መመኮር
 በላልች ኪሳራ ከራስ ግብ ሇመዴረስ መጣር
 መጫን፡- ሇምሳላ፡- መጮህ፣ አምጡ ስጡኝ ብል መጠየቅ፣ ላልችን ያሇማዲመጥ፣
ላልችን ተሳስታችኋሌ ማሇት፣ ላልች ሊይ ማፍጠጥ፣ ዝቅ አዴርጎ ማየት፣በላልች
ሊይ ጣትን መቀሰር ወይም መዛት፣ ማስፈራራት ወይም መዯባዯብ፡፡
3.2.2.3. ሌበ ሙለነት/ Assertiveness/
 ሌበ ሙለነት በማስተዋሌና በራስ መተማመን ሊይ የተመሠረተ፣ ሃሳብንና አቋምን
ያሇምንም ጥርጣሬና ፍርሃት በተረጋጋ መንፈስ የመግሇጽ ችልታ ነው፡፡
 ሌበ ሙለ ሰው ስህተቶች ሲፈጸሙ ያሇምንም ጥርጣሬና ፍርሃት በተረጋጋ መንፈስ
ሃሳብን የመግሇጽ ችልታ ነው፡፡
 ሌበ ሙለ ሰው ስህተቶች ሲፈጸሙና መብቱ ሲጣስ በቸሌታ
አይመሇከትም፡፡ስሜቱን መቆጣጠር ተስኖት አይቆጣም ሉሆን የሚችሌ ጥረት

Life Skills Training 2017 Page 12


HELVETAS Swiss Intercooperation Ethiopia- SKY Project

ያዯርጋሌ፡፡ መግባባትን ሇመፍጠር ይዯራዯራሌ፡፡ በዴርዴር ሂዯት የሰዎችን ሀሳብ


ይቀበሊሌ፤ የራሱንም ሃሳብ እንዱቀበለት ያዯርጋሌ፡፡ ሌበ ሙለነት በማኅበራዊ ኑሮ
ውስጥ ችግሮችን ሇመፍታት የሚያስችሌ ክህልት ነው፡፡

በሌበ ሙለነት ራስን የመግሇፅ ባህሪያት (Assertive behavior)

ማስፈራራት በማይመስሌ ወይም እብሪት ባሌተሞሊበት መሌኩ በትክክሌ ምን


እንዯምትፈሌግ ወይንም እንዯምትፈሌጊ ላልች በግሌጽ እንዱያውቁት መንገር፡፡

 የላልችን መብት ሳይነኩ የራስን መብት ሇማስከበር ታጥቆ መነሳት ሇዚህም መቆም
 ራስንና ላልችንም ማክበር
 በሚገባ ማዲመጥና መናገር
 አዎንታዊና አለታዊ ስሜቶችን በአግባቡ መግሇጽ
 ላልችን ሳይገፋፉ በራስ የመተማመን ሁኔታን ማንፀባረቅ
ሚዛናዊ አቋም መያዝ፡- ምን ማሇት እንዯምትፈሌግ አውቀህ “እንዯሚመስሇኝ” በማሇት
ፈንታ “እንዯሚሰማኝ” በማሇት ግሌጽ መሆን፡፡ “እኔ” በማሇት፣ ፊት ሇፊት እያዩ መናገር፣
ያሇማንጓጠጥና ያሇማሽሟጠጥ፤ እንዱሁም የሰውነት እንቅስቃሴ ቋንቋን መጠቀም፣ ሇያዙት
አሊማና አቋም በጽናት መቆም፤ አቋምን ማንፀባረቅ፡፡

3.2.3. የአቻ ግፊትን መሇየትና መቋቋም/Identifying &Coping Peer Pressure/

ውዴ አመቻች፡ ተሳታፊዎችን በትንንሽ ቡዴኖች በመክፈሌ የአቻዎችን ግፊት ሇማሳየትና


ሇመረዲት እንዱችለ ሌምምዴ እንዯሚሠሩ ይግሇጹሊቸው፡፡

 እያንዲንደ ተሳታፊ ከዚህ ቀዯም አቻዎቻቸው ጋር በነበራቸው ግንኙነት ያዩትን፣


የተማሩትንና የተገበሩትን አለታዊም ሆነ አወንታዊ ጠባይ አመሇካከትና ዴርጊት
በግሊቸው እንዱዘረዝሩ አዴርጉ፡፡ ሇምሳላ፡ አዱስ ቃሊቶች ወይም አባባልች
የአሇባበስ ዓይነቶች የተሇያዩ ሌምድች...
 ተሳታፊዎች በግሌ ያሰሊሰለትንና የጻፉትን በመያዝ በክብ ሇተቀመጡ ጓዯኞቻቸው
በመግሇጽ ውይይት ያዯርጋለ፡፡
 የቡዴን ውይይቱ እንዯተጠናቀቀ ተሳታፊዎች በቡዴን ወኪልቻቸው አማካኝነት
ሇመዴረክ በማቅረብ ይወያያለ፡፡
 በመጨረሻም የሚከተለትን ጥያቄዎች በማንሳት ውይይቱን ያጠቃለ፡፡

Life Skills Training 2017 Page 13


HELVETAS Swiss Intercooperation Ethiopia- SKY Project

o ከአቻዎቻችሁ በተማራችኋቸው ነገሮች ተዯነቃችሁ?


o ከአቻዎቻችሁ ሇሚዯርስባችሁ ቻና ወቅታዊ ምሊሽ ሰጥታችሁ ነበር?
o የተማራችኋቸውን ነገሮች ስታስቡ ምን ተሰማችሁ?
o ከአቻዎቻችሁ ምን ጥሩ ነገር ተማራችሁ?
o ከአቻዎቻችሁ የወሰዲችኋቸው ግን ሌታስወግዶቸው የሚገቡ ነገሮች ምን ምን
ናቸው?
3.2.4. ግጭትን መፍታት/Resolving Conflicts /

ውዴ አመቻች፡ ተሳታፊዎችን በቡዴን በመክፈሌ በኅበረተሰባቸው ውሰጥ የሚታዩ የግጭት


ዓይነቶችን ሇይተው በማውጣት፣ ሇግጭቶቹ መፈጠር ምክንያት የሚሆኑ ነገሮችን
በኅብረተሰባቸው ውስጥ ያለ የግጭት መፍቻ ዘዳዎች ሊይ እንዱወያዩ ያዴርጉ፡፡

በመቀጠሌም ያመቻቹ፡፡ተሳታፊዎች በግሊቸው ከዚህ በፊት ከሰው ጋር የተጋጩበትን


አጋጣሚ በማሰብና እንዳት እንዯፈቱት ያሊቸውን ሌምዴ ሇላልች እንዱያካፍለ ያዴርጉ፡፡

በመጨረሻም ተሳታፊዎች የተወያዩበትን ርዕሰ ጉዲዮች በፊሉፕ ቻርት ሊይ በማስፈር


በተወካዮቻቸው በኩሌ ሇሁለም እንዱያቀርቡ በማዴረግ በቀረቡት ሀሳቦች ሊይ አጠቃሊይ
ውይይት እንዱካሄዴ

ማጠቃሇያ

ግጭቶች በማኅበራዊ ኑሮ ውስጥ በማንኛውም የዕዴሜ ክሌሌ በሚገኙ ሰዎች መካከሌ


መፈጠራቸው የማይቀር ቢሆንም ጤናማ የሆነ ማኅበራዊ ኑሮን ሇመምራት ግጭቶችን
በሰሊማዊ መንገዴ መፍታት የመቻሌ ጥበብ ግጭቶች አፍራሽ የሆነ ችግር ሳያስከትለ
ሇማስወገዴ ይረዲሌ፡፡ ግጭቶችን በመፍታት ሂዯት ውስጥ በሥራ ሊይ የሚውለ አራት
የግጭት መፍቻ ዘዳዎች አለ፡፡ እነሱም፡- አስታራቂነት፣ቁጣን ማብረዴ፣ መዯራዯርና፣
አማሊጅነት ናቸው፡፡ እነዚህ አራት ዘዳዎች እርስ በእርሳቸው የሚዯጋገፉና ግጭትን
ውጤታማ በሆነ መንገዴ ሇመፍታት ዯረጃ በዯረጃ ሥራ ሊይ የሚውለ ናቸው፡፡

አስታራቂነት በሦስተኛ ወገን አማካኝነት ሁሇት ወይም ከዚያ በሊይ የሚሆኑ ግጭት ውስጥ
የገቡ ወገኖች ተቀራርበው ይቅር እንዱባባለ የሚዯረግ ጥረት ነው፡፡ ይቅር መባባሌ ያሇፈን

Life Skills Training 2017 Page 14


HELVETAS Swiss Intercooperation Ethiopia- SKY Project

ቂም ሇመርሳትና ቀዴሞ የነበረ ግንኙነትን እንዯገና ሇማካሄዴ የሚዯረግ የግጭት አፈታት


ዘዳ ነው፡፡

ግጭቶች ተካረው ወዯ አምባጓሮና ኃይሌን ወዯመጠቀም ሲያመሩ ቁጣን የማብረዴ ዘዳ


ሉያገሇግሌ ይችሊሌ፡፡ ይህ ዘዳ ስሜታቸውን መቆጣጠር ያቃታቸውን ግጭት ውስጥ ያለ
ወገኖች ወዯ አእምሯቸው ተመሌሰው ከኃይሌ እርምጃ እንዱቆጠቡ ሇማዴረግ የሚያገሇግሌ
ነው፡፡ ቁጣን የማብረዴ ተግባር በሶስተኛ ወገን ጣሌቃ ገብነት የሚፈጸም ሉሆን ይችሊሌ፡፡
በግጭት ውስጥ ባለ ወገኖች ተነሳሽነትም ይፈጸማሌ፡፡

አማሊጅነት በግጭት ውስጥ ካለ ወገኖች የአንዯኛውን ፍሊጎት በውክሌና ወዯ ላሊው ወገን


ሄድ በማማሇዴ ግጭትን ሇመፍታት ሥራ ሊይ የሚውሌ ዘዳ ነው፡፡ ይህ በተሇይ በዯሌ
ፈጽሜያሇሁ ብል የሚያምን ወገን ወዯላሊው ወገን የይቅርታ ጥያቄ የሚያቀርብበት
መንገዴ ነው፡፡

መዯራዯር ግጭትን ሇመፍታት በሁሇት ወይም ከዚያ በሊይ በሚሆኑ የተጋጩ ወገኖች
መካከሌ ወዯ ጋራ አቋም ሇመምጣትና ሌዩነትን ሇመፍታት የሚዯረግ ጥረት ነው፡፡
ግጭትን የመፍታት ክህልት በኅብረተሰብ ውስጥ ቅራኔዎች ወዯ ኃይሌ እርምጃና ጥፋት
እንዲያመሩና ሰሊምና ዯህንነት እንዱኖር የሚያስችሌ ጉሌህ ማኅበራዊ ጠቀሜታ ያሇው
ክህልት ነው፡፡

መዯራዯር በሰዎች መካከሌ የሚኖር ግንኙነትና የአንዴን ሰው መርህ ሳይነኩ ወይም


ሳይጋፉ እንዯአስፈሊጊነቱ ሇመሇወጥ ዝግጁ መሆንን ያጠቃሌሊሌ፡፡ አሇመግባባት ምናሌባት
አዯገኛ፣አስፈሪና ብቀሊን ሉያመጣ ይችሊሌ፡፡ በምንዯራዯርበት ጊዜ በሚገባ መገንዘብ
ያሇብን ነገር፡-

 ሌበ ሙለ መሆን
 እሴቱን ማወቅ
 ምንነትን ማወቅ
 የሕይወት መመሪያን ማወቅ
 ላሊውን ሰው ማክበርና አሇመናቅ
 አዘኔታና ርኅርኄ ሉኖረን ይገባሌ፡፡

Life Skills Training 2017 Page 15


HELVETAS Swiss Intercooperation Ethiopia- SKY Project

ግጭትን የመፍታት ክህልት በኅብረተሰብ የጋራ ኑሮ ውስጥ ሇረጅም ጊዜ በካበተ ሌምዴ


የሚፈጠር ክህልት ከመሆኑም በሊይ በኢኮኖሚ፣ ማኅበራዊና ፖሇቲካዊ ኑሮ ባዯገ
ኅብረተሰብ ውስጥ ግጭትን የመፍታት ክህልት በከፍተኛ ትምህርትና ሌምዴ ይዲብራሌ፡፡

3.2.5. አሳቢነት ወይም ሀዘኔታ/Empathy/

አሳቢነት ወይም ሀዘኔታ፡ በራሳቸው ዴርጊት ወይም በአንዲንዴ ሁኔታዎች ምክንያት ከባዴ
ችግሮች በገጠማቸው ሰዎች ቦታ ራስን ተክቶ ማየትን ይመሇከታሌ፡፡ ይህም የሰዎችን
ሁኔታ መረዲትንና ያሇውን ጫና ሇመቀነስ ከማውገዝ ወይም ዝቅ አዴርጎ ከመመሌከት
ይሌቅ ችግሩን በመጋራት መፍትሔ መፈሇግ ማሇት ነው፡፡

አሳቢነት ሰዎች የራሳቸውን ውሳኔ መወሰን እንዱችለና በተቻሇ መጠን በራሳቸው እግር
መቆም እንዱችለ ዴጋፍ መስጠትን ያመሊክታሌ፡፡

3.2.6. ችግሮችን የመፍታት ክህልት/ Problem Solving/

ውዴ አመቻች፡ ተሳታፊዎችን በቡዴን በመከፍሌ በሚኖሩበት ማኅበረሰብ ውስጥ ጎሌተው


የሚታዩ አምስት ችግሮችን እንዱዘረዝሩ ያዴርጉ፡፡ በመቀጠሌም፡ ተሳታፊዎች
በየቡዴናቸው፡-

የችግሮቹን ምንጮች ተራ በተራ ሇመረዲት ይሞክሩ፣



ችግሮቹ በግሌም ሆነ በማኅበረሰብ ዯረጃ የሚስከትለትን ጉዲት በአጭር በአጭሩ

ያብራሩ፤
 ችግሮቹን እንዯአሳሳቢነታቸው በዯረጃ ይሇዩ፣
 ችግሮቹን ሇመፍታት ምን መዯረግ እንዯሚያስፈሌግ ይዘርዝሩ፣
 ቡዴኖቹ በተወካዮቻቸው አማካኝነት ሇጥያቄዎቹ የሰጧቸውን መሌሶች ሇጠቅሊሊ
ተሳታፊ ያቅርቡ፣
በመጨረሻም ቡዴኖቹ ባቀረቧቸው መሌሶች ሊይ በቂ ገሇጻ በማዴረግ ማጠቃሇያ ይስጡ፡፡

ችግሮችን የመፍታት ክህልት የሰው ሌጅ በኑሮ ሂዯት ውስጥ ካዲበራቸው መሠራታዊ


ክህልቶች አንደ ነው፡፡ ከቀሊሌ እስከ ከባዴ የኑሮ ችግሮችን ሇመፍታት ጥረት ማዴረግ
ሰዎች ሇመኖር የሚያዯርጉት ትግሌ አካሌ ነው፡፡

ዯረጃው ይሇያያሌ እንጅ ሰዎች ሁለ ችግሮች ይኖሯቸዋሌ፡፡ ከችግሮቹ ሇመውጣትም


የማያቋርጥ ጥረት ያዯርጋለ፡፡ ችግሮቹ የተሇያዩ እንዯመሆናቸው መጠን
መፍትሄዎቻቸውም የሚጠይቀው ጊዜና አቅም ይሇያያሌ፡፡

ችግርን በመፍታት ሂዯት ሌንከተሇው የሚገባ መሠረታዊ አካሄዴ፡

Life Skills Training 2017 Page 16


HELVETAS Swiss Intercooperation Ethiopia- SKY Project

 ችግሩን ሇይቶ ማወቅና መረዲት፣


 ሇችግሩ መከሰት ምክንያት የሆኑ ነገሮችን በጥሌቀት መሇየት፣
 ችግሩን ሇመፍታት የሚያስችሌ አማራጭ የመፍትሄ እቅጣጫዎችን መንዯፍና
መወሰን፣
 የችግሩን ሥር/ምንጭ ሇማስወገዴ የሚያስችሌ አቅምና ሃብት ማሰባሰብ
 ተግባራዊ እንቅስቃሴ በማዴረግ ችግሩን መፍታት ሂዯቱን በመገምገም መማር፣

የሥራ አጥነት ችግርን በመፍታት ሴተኛ አዲሪነትን መቀነስ፣ ሴቶችንና ወንድችን


ከተረጂነት ማሊቀቅ፣ የኤች.አይ.ቪ/ኤዴስን ሥርጭት መቀነስ ይቻሊሌ፡፡ የማኅበረሰቡን
ችግሮች በመፍታት ሂዯት ወስጥ አንገብጋቢ የሆኑትንና መፍትሔ ሉሰጣቸው የሚችለትን
ሇይቶ ማውጣት ያስፈሌጋሌ፡፡ ችግርን የመፍታት ክህልትን በማበሌጸግ፣ ወጣቶች
ሇራሳቸውና ሇኅብረተሰባቸው ችግሮች መፍትሄ የመፈሇግ ሚና እንዱጫወቱ ይረዲቸዋሌ፡፡

3.2.7. የውሳኔ አሰጣጥ ክህልት/Decision-making/

ውዴ አመቻች፡ ተሳታፊዎችን በቡዴን በመከፍሌ በግሊቸው መሌስ እንዱሰጡ በጥሞና


የማሰሊሰያ ጊዜ ይሰጣቸው፡፡

 ውሳኔ ምንዴን ነው?


 ውሳኔ ሊይ እንዳት ይዯረሳሌ?
 እስከዛሬ ውሳኔዎችን ስንወስን ምን ምን ነገሮችን እንጠቀም ነበር?
 ባሳሇፍነው ውሳኔ ተጸጽተን እናውቅ ይሆን?

በጥሞና ጊዜ ያገኙትን ውጤት ይዘው በየቡዴናቸው ውይይት በማዴረግ ሃሳባቸውን


በፍሉፕ ቻርት እንዱያሰፍሩ ይግሇጹሊቸው፡፡

ወጣቶች በሕይወታቸው በርካታ ፈተናዎች ይገጥሟቸዋሌ፡፡ ከእነዚህም ውስጥ


ከተጓዲኛቸው ወይም ከአቻዎቻቸው ሇማግኘት የሚፈሌጉት ወሲባዊ ዯስታ አንደ ሉሆን
ይችሊሌ፡፡አንዲንዴ ጊዜ ፈጣን ውሳኔ መወሰን መቻሌ ያስፈሌጋሌ፡፡ አሇበሇዚያ ሇበሇጠ
አዯጋ ራሳቸውን ይዲርጋለ፡፡

ምሳላዎች፡-

 አዯጋን ሉያስከትሌ የሚችሌ ሁኔታን መገምገምና መወሰን


 ጥንቃቄ የጎዯሇው ወሲብ መፈጸም የሚያስከትሇውን ውጤት መረዲት
 የተጓዲኝ ወሲባዊ ጠባይን ማወቅ፣

ውሳኔ የሰው ሌጅ በዕሇት ተዕሇት ኑሮው ውስጥ የሚያጋጥሙትን ችግሮችና ምርጫዎች


ሇመፍታት የምንጠቀምበት አንዴ የሕይዎት ክህልት ዓይነት ነው፡፡ ውሳኔ የመስጠት
ሂዯት እንዯችግሮቹ ስፋትና እንዯምንወስዯው የምርጫ ዓይነት ቀሊሌና ከባዴ ሉሆን

Life Skills Training 2017 Page 17


HELVETAS Swiss Intercooperation Ethiopia- SKY Project

ይችሊሌ፡፡ አንዲንዴ ጊዜ በቀሊለ ውጤታማ የሆነ ውሳኔ ሇመስጠት ክህልት የሚዲብረው


የሚከተለትን ነጥቦች በየዯረጃው በመተግበርና ሌምዴ አዴርጎ በመውሰዴ ይሆናሌ፡፡
 ውሳኔ ሇመስጠት የፈሇግነውን ጉዲይ መሇየትና በጥሌቀት መገንዘብ፣
 በቂ ጊዜ መወሰዴ
 ስሇጉዲዩ በጥሌቀት ማሰብ፣
 ከላልች ምክር መጠየቅ፣
 የሚሰጠውን ምክር በጥንቃቄ ማዲመጥ፣ በጉዲዩ ዙሪያ በቂ መረጃዎችን ማሰባሰብ፣
 መጸሇይ/እረፍት መውሰዴ፣
 የቤተሰብና የማኅበረሰብ እሴቶችን ከግንዛቤ ማስገባት፣
 የአካባቢው ባህሊዊ ዴርጊቶችና ምንነቶችን ከግንዛቤ ማስገባት፣
 ውሳኔ ሇመወሰን ያለትን አማራጮች ሁለ በዝርዝር ሇይቶ ማውጣት፣
 እያንዲንደ አማራጭ የሚያመጣውን ውጤትና የሚያሳዴረውን ተጽእኖ መገመት
ማወዲዯር፣
 ውሳኔው በሰዎች ሊይ የሚያሳዴረውን ተጽእኖ መገመት ማወዲዯር፣
 ውሳኔው በሰዎች ሊይ የሚያሳዯረውን ተጽእኖ መገንዘብ፣
 ጥሩ የምትሇውን ምርጫ ምረጥ፣
 ውሳኔህን ስጥ፣
 ውሳኔህን ተግባራዊ አዴርግ፣
 ውሳኔህን ተከትል የሚመጡ ማንኛውንም ጉዲት በኃሊፊነት ሇመቀበሌ ዝግጁ ሁን፡፡

Life Skills Training 2017 Page 18

You might also like