You are on page 1of 34

-------------

የበጎአድራጎትማህበሩየራሱንማዕከላዊእሴቶችንከማንጸባረቅናእነዚህ
እሴቶችመከበራቸውንከማረጋገጥባለፈከተጠቃሚውማህበረሰብ፣ከመ
ንግስት፣በአጠቃላይከሕዝብናከሌሎችአጋሮችጋርውጤታማናቀልጣፋ
ቅንጅትናትብብርለማድረግየሚያስችልየሥነ-
ምግባርደንብመቅረጽናመተግበርእንዳለበትበማመን፣የ

በጎአድራጎትድርጅቶችናማህበራትራሳቸውንየሚቆጣጠሩበትሥርዓት
መዘርጋቱበበጎአድራጎትማህበረሰብውስጥከፍተኛየአሰራርደረጃንየሚ
ያራምድእናለሙያዊአሰራርናኃላፊነትማዕቀፍየሚፈጥርመሆኑንበማ
ስታወስ፣
የበጎአድራጎትድርጅቶችየሚንቀሳቀሱበትንየሕግማዕቀፍእናማዕቀፉየ
ፈጠራቸውንአዳዲስእድሎችናተግዳሮቶችበመገንዘብ፣በኢትዮጵያየ
ሚንቀሳቀሱየበጎአድራጎትድርጅቶችናማህበራትየሥነ-
ምግባርደንብፈራሚዎችጠቅላላጉባኤይህንንየተሻሻለየሥነ-
ምግባርደንብአጽድቋል፡፡

1
ማውጫ

መግቢያ .................................................................................1
ክፍልአንድ
ጠቅላላ

አንቀጽ 1 ርዕስ...........................................................2

አንቀጽ 2፡ትርጉም ...........................................................2

አንቀጽ 3፡የደንቡዓላማዎች .......................................................4

አንቀጽ 4፡የሥነ-ምግባርደንቡየተፈፃሚነትወሰን..........................4

አንቀጽ 5፡የሥነ-ምግባርደንቡፈራሚስለመሆን............................4
ክፍልሁለት
ደንቡየሚመራባቸውመሰረታዊመርሆዎች

አንቀጽ 6፡ተጠያቂነት .............................................................5

አንቀጽ 7፡ግልጽነት..................................................................5

አንቀጽ 8፡ተሳትፎ ..................................................................6

አንቀጽ 9፡የወንዶችናሴቶችእኩልነት.......................................7

አንቀጽ 10፡ሰብአዊመብቶችንማክበር.......................................7

አንቀጽ 11፡የአካባቢጥበቃተቆርቋሪነት.....................................8

አንቀጽ 12፡ነፃነትናገለልተኛነት................................................8

አንቀጽ 13፡ያለማዳላትናእኩልነት.............................................8

አንቀጽ 14፡ተዓማኒነት.............................................................9

አንቀጽ 15፡ሕጋዊነት..............................................................9

አንቀጽ 16፡ቅንጅትናትብብር...................................................9
ክፍል ሶስት
የሥነ ምግባር ደንቡ አመራር
አንቀጽ 17፡ ተቋማዊአመራር......................................................11
አንቀጽ 18፡ የመርሃ ግብር አቀራረጽና አመራር.......................................................12
አንቀጽ 19፡ የፋይናንስ አመራር.............................................................................12

2
አንቀጽ 20፡ የሰው ሃብት አሰተዳደር.......................................................................12

አንቀጽ 21፡ የውስጥና የውጭ ቅሬታ ሰሚና ምላሽ ሰጪ አደረጃጀት.........................13


አንቀጽ 22፡ የሃብት አሰባሰብና አጠቃቀም...............................................................14
አንቀጽ 23፡ የጥቅም ግጭት እንዳይፈጠር መከላከል.................................................15
ክፍል አራት
የሥነ-ምግባር ደንቡን ስለማስፈጸም
አንቀጽ 24፡ መመስረት..........................................................................................16
አንቀጽ 25፡ የፓነሉ አመራረጥና የአባላት ሥብጥር.................................................17
አንቀጽ 26: የአገልግሎት ዘመን............................................................................17
አንቀጽ 27፡ የፓነሉ ተግባርና ሃላፊነት...................................................................17
አንቀጽ 28፡ የዝጋቤ (ሪፖርት) አቀራረብ ሥነ-ሥርዓት............................................18
አንቀጽ 29፡ የብቃት ማረጋገጫ ስለመስጠት.............................................................19
አንቀጽ 30፡ ስለማሳወቅ (ቅሬታ ስለማቅረብ)............................................................19
አንቀጽ 31፡ ለፓነሉና ለሕብረቶች ሥለሚቀርቡ አቤቱታዎች....................................20
አንቀጽ 32፡ የሥልጣን ክልል.................................................................................21
አንቀጽ 33፡ ፓነሉ ምርመራ የሚያካሂድበት ሥርዓት..............................................21
አንቀጽ 34፡ አቤቱታዎችን የመስማት ሂደት............................................................22
አንቀጽ 35፡ የይግባኝ ሥነ-ሥርዓት.........................................................................23
አንቀጽ 36፡ የፓነሉን ውሳኔ ማሳወቅ.....................................................................24
አንቀጽ 37፡ በሕብረቶች አቤቱታዎችን ስለመመልከት...............................................24
አንቀጽ 38፡ የዲስፕሊን እርምጃዎች........................................................................24
አንቀጽ 39፡ ውሳኔዎችን መመዝገብና ማሰራጨት....................................................25
ክፍል አምስት
ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች
አንቀጽ 40፡ ፈራሚ ድርጅት ከአባልነት ስለሚለቅበት ሁኔታ....................................26
አንቀጽ 41፡ የፈራሚነት ክፍያ ……......................................................................26
አንቀጽ 42፡ የሥነ-ምግባር ደንቡን ስለማሻሻል.........................................................26
አንቀጽ 43፡ ደንቡ የሚጸናበት ጊዜ.........................................................................27

3
አንቀጽ 44፡ የመጨረሻ ሕጋዊ ዕውቅና ያለው ቅጂ.........................................27

ክፍል አንድ
ጠቅላላ
አንቀጽ 1፡ ርዕስ
ይህደንብ የ‹ጀምዒያቱል መሻሪዒል ኸይሪያ››በጎ አድራጎት ማህበር
የሥነ-ምግባር ደንብ ሲሆን ከዚህ በኋላ ‹‹ደንብ›› ተብሎ ሊጠቀስ
ይችላል፡፡

አንቀጽ 2፡ ትርጉም
1) “ተጠያቂነት” ማለት አንድ አባል በውሳኔ አሰጣጥ ሂደቶቹ እና
በክንውኖች አፈፃጸም ሂደት ለባለድርሻ አካላት (ተጠቃሚዎች፣
ሕዝብ፣ መንግስት፣ ለጋሾችና ሰራተኞች) ፍላጎት ምላሽ ሰጪና
ሚዛናዊ ለመሆን ቁርጠኛ አቋም የሚይዝበት እና የሚተገብርበት
ሂደት ነው፤
2) “የብቃት ማረጋገጫ መሥጠት” ማለት ነፃና ገለልተኛ የሆነ ሦስተኛ
ወገን አግባብነት ያላቸው የጥራት መመዘኛዎች ስለመተግበራቸው
ማረጋገጫ የሚሰጥበት ሂደት ነው፤
3) “ቅሬታ” ማለት በአንድ አባልድርጊትበደልደርሶብኛልወይምአባሉ
በዚህየሥነ-
ምግባርደንብየተደነገጉትንግዴታዎችአላሟላምበሚልበማንኛውምሰ
ውየሚቀርብክስነው፤ለክሱምክንያትየሆነውድርጊትበፈራሚውስምወ
ይምምትክበሚሰሩኃላፊዎች፣ሰራተኞች፣በጎፈቃደኞች፣ለማጅሰራተ
ኞችወይምአማካሪዎችየተፈጸመሊሆንይችላል፤
4) “ቅሬታአቅራቢ” ማለትበማህበሩ አባል
ላይአቤቱታየሚያቀርብማናቸውምሰውነው፤
5) “የአመራር አካል” ማለት በማህበሩ አወቃቀር የመጨረሻው ውሳኔ ሰጭ
አካል ሲሆን የድርጅቱ ጠቅላላ ጉባኤ ወይም የዳይሬክተሮች ቦርድ
ሊሆን ይችላል፤ ይህንን የሥነ-ምግባር ደንብ ለመፈረምና
4
ተፈፃሚነቱን ለማረጋገጥ በኃላፊነት ሊወስን የሚችለው ይህ አካል
ይሆናል፤
6) “የጥቅም ግጭት” ማለት በበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ድንጋጌ አንቀጽ 27 መሰረት ማንኛውም
ሰራተኛ፣ የቦርድ አባል፣ ተራ አባል፣ አማካሪ፣ በጎ ፈቃደኛ፣ ተለማማጅ
ሰራተኛ ወይም ሌላ ማንኛውም ሰው ለራሱ ወይም ለሌላ ሰው
ወይም ድርጅት በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ የግል ጥቅም ሊያስገኝ
በሚችል ውሳኔ ላይ ተጽእኖ ሊያደርግ የሚችልበት ሁኔታ ማለት ነው፡፡
በአጭሩ የእነዚህ ግለሰቦች የግል ወይም የሙያ ጥቅም ከድርጅቱ
ተቀዳሚ ጥቅም ጋር የሚጋጭበት ወይም ሊጋጭ የሚችልበት ሁኔታ
ሲከሰት የጥቅም ግጭት አለ ይባላል፡፡
7) “ተሳትፎ” ማለት በማህበሩ በማህበሩ አወቃቀር ባለድርሻ አካላትን
በሚመለከቷቸው ውሳኔዎችና ክንውኖችየማካተት እና የሚያቀርቧቸውን
ስጋቶችና ሃሳቦች ተቀብሎ ምላሽ የመስጠትተግባር ነው፤ በማህበሩ
ውሳኔዎቹና ክንውኖቹ ተጽእኖ የሚደርስባቸውዋና ዋና ባለድርሻ አካላት
በአሰራሩ ውስጥ ሚና እንዲኖራቸው የሚያደርግበትሂደት ነው፤
8) አጋሮች ማለት በእርዳታ ወይም የልማት ክንውኖች የጋራ
ሥምምነትየተደረሰባቸው ዓላማዎችን ለማሳካት ከማህበሩ ጋር
በትብብርየሚሰሩ ናቸው::
12) “ሰው” ማለት ማናቸውም የተፈጥሮ ሰው ወይም ሕጋዊ ሰውነት ያለው
አካልነው፤
13) “ፈራሚ አባል” ማለት ይህንን የሥነ- ምግባር ደንብ ፈርሞ እንደፈራሚ
ተቀባይነት ያገኘ እና ራሱን ያላገለለ ወይም እንዲገለል ያልተደረገ እና
ሁሉንም የአባልነት ክፍያዎች አጠናቆ የከፈለ ድርጅትነው፤
14.“መልስ ሰጭ” ማለት የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ሕብረትን ጨምሮ
አቤቱታየቀረበበት ፈራሚ ድርጅት ነው፤
15.“ባለድርሻ አካላት/ማህበረሰብ” ማለት በአንድ ተቋም ፖሊሲዎችና
ክንውኖች ተጽእኖሊደርስባቸው የሚችል ወይም በተቋሙ ፖሊሲዎችና
ክንውኖች ላይ ተጽእኖሊያሳድሩ የሚችሉ ግለሰቦችና ቡድኖች ናቸው፤

5
16 “ግልጽነት” ማለት አንድ ተቋም ስለሚያከናውናቸው ተግባራት
ድብቅያለመሆኑን፣ ምን እንደሚሰራ፣ የት እንደሚሰራ፣ እንዴት
እንደሚሰራእና የስራዎቹን አፈፃጸም የተመለከተ መረጃ ለመስጠት ፈቃደኛ
መሆኑንይመለከታል፡፡

17. የፆታ አገላለፅበወንድ ፆታ የተገለፀው የሴትንም ፆታ ያካትታል፡፡

ህዝብ ማለት ተጠቃሚው ማህበረሰብ፣ የተቋሙ አባላትና ደጋፊ ማህበረሰብን


ያካትታል፡፡ የማህበሩ አቅም ተደራሽ እስከሆነበት ማህበረሰብ፣ አባላትና ደጋፊ
ማህበረሰብን ያካትታል፡፡ ኮሚቴው የሚከተሉት ተግባርና ኃላፊነቶች ይኖሩታል፡-

6
አንቀጽ 3፡ የደንቡ ዓላማዎች
ይህ ደንብ የሚከተሉት ዓላማዎች ይኖሩታል፡-
1. የማህበሩሥራ አመራር ተጠሪዎችና በአጠቃላይ አባል ኢስላማዊውን
አዳብ (ሥርዓት) እንዲላበሱ፣ አጠቃላይ ተቀባይነት ያገኙ የሥነ-ምግባር
ደረጃዎችና የአሰራር ልማዶችን ጠብቀው እንዲንቀሳቀሱ ማበረታታት፣
2. የአባላቱ እና የማህበሩን ተአማኒነት ማስጠበቅ፣
3. ከፍተኛ የሥነ-ምግባር መመዘኛዎችን በመቀበል በማህበሩ የሚሰጡ
አገልግሎቶችን ጥራት ማሻሻል እና ቀልጣፋ የውሳኔ አሰጣጥ ሂደቶችን
መቅረጽ፣
4. በማህበሩ እናበማህበረሰቡ መካከል ያለውን ግንኙነትና ትብብር ወደ ላቀ
ደረጃ ማሳደግ፣
5. የልምድ ልውውጥን እና ውጤታማነታቸው ከተረጋገጠ ተሞክሮዎች
መማርንበማበረታታት የማህበሩ አሰራርና ውጤታማነት ማሳደግ፣
6. የሥነ-ምግባር ደንቦችን ማስጠበቅ፣ ሕዝቡ በማህበሩ ላይ ያለውንእምነት
ማረጋገጥ እና የመርሃ ግብሮቻቸውን ጥራትና ውጤታማነትማጠናከር፣
7. የማህበሩን መዋቅር በማጠናከር የበለጠ ዴሞክራሲያዊእና ለባለድርሻ
አካላት ግልፅና ተጠያቂ እንዲሆኑ ማድረግ፡፡

7
አንቀጽ 4፡ የሥነ-ምግባር ደንቡ የተፈፃሚነት ወሰን
1. ይህ ደንብ በማህበሩመተዳደርያ ደንብ በሚንቀሳቀሱ እና በዚህ ደንብ
ውስጥበተካተቱት መሰራታዊ የሥነ-ምግባር መርሆዎች ለመገዛት
ፈቃደኛ በሆኑየማህበሩ አባላትላይ ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
2. ይህ ደንብ ተፈፃሚነቱ በማህበሩ ፈራሚላይ ሆኖ ፈራሚዎች
በስማቸው ወይምበምትካቸው ለሚሰሩ ኃላፊዎች፣ ሰራተኞች፣ አጋር
በጎ ፈቃደኞች፣ ተለማማጅሰራተኞች ወይም አማካሪዎች ድርጊት
ተጠያቂ ይሆናሉ፡፡
አንቀጽ 5፡ የሥነ-ምግባር ደንቡ ፈራሚ ስለመሆን
1. አግባብነት ባለው የ‹ጀምዒያቱል መሻሪዒል ኸይሪያ›› የበጎ አድራጎት
ማህበር መተዳደርያ ደንብ መሰረት የተመዘገበ እና በሥነ-ምግባርደንቡ
ለመገዛት ፈቃደኛ የሆነ ማናቸውም ፈራሚ ሊሆን ይችላል፡፡
2. የደንብ አስከባሪ ኮሚቴ ለፈራሚው ፈራሚነትንየሚያረጋግጥ የምስክር
ወረቀት አንድ ቅጅ ለአመልካቹ ይሰጣል፡፡

8
ክፍል ሁለት
ደንቡ የሚመራባቸው መሰረታዊ መርሆዎች

አንቀጽ 6፡ ተጠያቂነት
1. ፈራሚዎች ለሚፈጽሙት ማናቸውም ድርጊት ወይም ውሳኔ
ለጋሾችን፣ አጋሮችን፣ መንግስትን፣ አጠቃላይ ሕዝብን፣
ተጠቃሚውን፣ ሰራተኛውን እና አጋሮችን ጨምሮ ለሁሉም ባለድርሻ
አካላት ተጠያቂነትአለባቸው፡፡
2. ፈራሚ አባላትየሚያራምዱት ዓላማና የአሰራር ሂደቶቻቸው
በጠቅላላ ጉባኤ ፍላጎትና ጥቅም ላይ የተመሰረቱ መሆናቸውን፣
ሥራቸውም በአባላቶች፣ በአጋሮችና በአፈፃጸም ሂደት በሚሳተፉ
ሌሎች አካላት ግምገማና አስተያየት ክፍት መሆኑን ያረጋግጣሉ፡፡
በማናቸውም ሁኔታ ቢሆን በልማት ሥራዎች አፈፃጸም ተጽእኖ
የሚደርስባቸው አካላት ተቀዳሚ ባለድርሻ ተደርገው ሊታሰቡና
አስተያየታቸውም ቅድሚያ ሊሰጠው ይገባል፡፡
3. ማንኛውም የማህበሩ የስራ አስፈፃሚዎች ሥራቸውን
በሚያከናውኑበት አካባቢ የሚገኙ ማህበረሰቦችና ተወካዮቻቸው
በልማት ክንውኖች ትክክለኛ፣ በበቂ መረጃ የታገዘና በፈቃደኝነት ላይ
የተመሰረተ ተሳትፎ እንዲኖራቸው ለማድረግ ይጥራሉ፤ በተቻለ
መጠን ለክንውኖቹ አቀራረጽ፣ ትግበራ፣ ክትትልና ግምገማ እውነተኛ
አስተዋጽኦ ለማድረግ እድል ማግኘታቸውንም ያረጋግጣሉ፡፡
4. ዓመታዊ የሥራ አፈፃጸም ዘገባ ተዘጋጅቶ ለአባላት፣ ሰራተኞች፣
በጎፈቃደኞች፣ ደጋፊዎች፣ አጋራቶች እና ለህዝብ ተደራሽ ይደረጋል፡፡

አንቀጽ 7፡ ግልጽነት
1. ፈራሚ የማህበሩ አባላቶች ከባለድርሻ አካላት ጋር በሚኖራቸው
ግንኙነት ማእከላዊና የጋራ የሆኑ እሴቶቻቸውን በግልጽ ያሳውቃሉ፡፡

9
2. ፈራሚ የማህበሩ ሥራ አስፈፃሚዎች ለባለድርሻ አካላት ትክክለኛ፣
ተደራሽና ጊዜውን የጠበቀ መረጃ ለማቅረብ አስፈላጊውን እርምጃ
በተነሳሽነት ይወስዳሉ፡፡
3. የማበሩን መሰረታዊ የፋይናንስ መረጃ፣ የሥራ አመራር መዋቅር፣
ክንውኖች እና የሥራ ኃላፊዎችና አጋሮች ዝርዝር የድርሻቸው
ለሕዝብ ግልጽና ተደራሽ መሆንአለበት፡፡
4. ፈራሞዎች የማህበሩ ፋይናንስ የፋይናንስ አፈፃጸምን የተመለከተ
ማንኛውም ጉዳይ በተጠቀሰ ጊዜ ባለድርሻ አካላት የተሟላ የፋይናንስ
ዘገባዎችን የማግኘት መብት እንዳላቸው እንዲያውቁ መደረጉን
ያረጋግጣሉ፡፡
5. ማንኛውምፈራሚና የማህበሩ ሥራ አስፈጻሚ የሚተገብራቸውን
መርሃግብሮችና የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች የተመለከተ መረጃ
አዘጋጅቶ ለሕዝብ ያቀርባል፤ አግባብነት ያላቸው የእነዚህን
መርሃግብሮችና አገልግሎቶች መዛግብት ለሕዝብ ተደራሽ ያደርጋል፡፡
6. ማንኛውም አባል የድርጅቱን ወይም የማህበሩን መሰረታዊ የፋይናንስ
መረጃ በየአመቱ አዘጋጅቶ ለሕዝብ ያቀርባል፡፡ ይህም መረጃ
የድርጅቱን የገንዘብ ምንጮችና ገንዘቡ ለምን ተግባር እንደዋለ እና
ለአገልግሎትና መርሃግብሮች፣ለአስተዳደራዊ ወጭዎችና ለገቢ
ማሰባሰብ የዋለውን የገንዘብ መጠን በመቶኛ የሚያሳይ እና ለሥራ
አመራር አካል አባላት የተደረገ ማናቸውም ክፍያ የሚገልጽ መሆን
አለበት፡፡

7. ማንኛውም አባል የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን፣ ዋና ሥራ አስፈፃሚ እና


ሌሎች የሥራ አመራር አባላትን ማንነት ለሕዝብ ግልጽ ማድረግ አለበት፡፡
8. በዚህ አንቀጽ ንዑስአንቀጽ (7) የተደነገገው ቢኖርም የሚመለከተው
ግለሰብካልፈቀደ በቀር ወይም መረጃው እንዲገለጽ በሚያዝ አስገዳጅ የሕግ
ድንጋጌመሰረት ካልሆነ በቀር ድርጅቱ ወይም ማህበሩ የሰራተኞች፣ የደንበኞች
ወይም ሌሎች ግለሰቦችን የግል መረጃ በምስጢር መያዝ አለበት፡፡

10
9. ማንኛውም የማህበሩ አባል ስለግለሰቦችና ድርጅቶችየሚሰበስበውን መረጃ
ዓይነት፣ የተሰበሰበው መረጃ ለምን ዓላማና እንዴት ጥቅም ላይ እንደሚውል፣
የተሰበሰበን የግል መረጃለመመልከትና እርማት እንዲደረግ ለመጠየቅ
ስለሚቻልበት አግባብ፣ ግለሰቡ የግል መረጃዎቹ ከድርጅቱ ውጭ ተላልፎ
እንዲሰጥ እንደማይፈልግ ለድርጅቱ ወይም ማህበሩየሚያሳውቅበት አግባብ
እና የግል መረጃን ለመጠበቅ የተቀመጡ አሰራሮችን ለሕዝብ የሚያሳውቅበት
ግልጽና በቀላሉ ሊደረስ የሚችል የግል ምስጢር አጠባበቅ ፖሊሲ ሊኖረው
ይገባል፡፡

አንቀጽ 8፡ ተሳትፎ
1. ፈራሚ አባላት በራስ አቅም መተማመንን ለማበረታታትና ለማስቻል
አስፈላጊውን እርምጃ በተነሳሽነት ይወስዳሉ፤ የሰዎችን በሕይወታቸው ላይ
ተጽእኖ በሚያሳድሩ ውሳኔዎች የተሟላ ተሳትፎ የማድረግ መብትና ራስን
የማስተዳደር ራእይ እውን ለማድረግ ይሰራሉ፡፡
2. ፈራሚ ድርጅቶች ወይም ማህበራት ሁሉንም ተጠቃሚ ማህበረሰቦች
በተቻለ መጠን ሁሉ በክንውኖችና በመርሃግብሮች እቅድ፣ አፈፃጸምና
ግምገማ ሂደት በቀጥታ ያሳትፋሉ፡፡
3. ፈራሚ ድርጅቶች ወይም ማህበራት በተቋማዊ አመራር የተለያዩ
ደረጃዎች የተጠቃሚዎችን ቀጥተኛ ተሳትፎ እና ተደማጭነት ያረጋግጣሉ፡፡
4. ፈራሚ ድርጅቶች ወይም ማህበራት ማህበረሰቦች ለክንውኖች ኃላፊነት
እንዲወስዱና የሥራቸው ባለቤት እንዲሆኑ በማብቃት ውጤታማ
የማህበረሰብ ተሳትፎን ያራምዳሉ፣ ይደግፋሉ፡፡
አንቀጽ 9፡የወንዶችና ሴቶች እኩልነት
1. ፈራሚዎች ሚዛናዊና ፍትሃዊ የወንዶችና የሴቶች እኩልነት
እንዲረጋገጥይጥራሉ፡፡ ኢስላማዊ ሸሪዓ ጋር ግጭት እስካልፈጠረ ድረስ
በሁሉም የልማት ሥራዎችና መርሃግብሮች የሴቶችን እኩልተሳትፎ
ለማረጋገጥ ይሰራሉ፡፡

11
2. ፈራሚዎች በሰው ሃብት ልማት ውስጥ የፆታ ግንዛቤ በተሟላ
ሁኔታእንዲካተት ያደርጋሉ፤ ከመድልዎ የፀዳ የሥራ ሁኔታና ግንኙነት
ያራምዳሉ፡፡
3. ፈራሚዎች በሁሉም ደረጃ በውሳኔ ሰጭነት የሥራ መደቦች ላይ
የሴቶችንቁጥር ለመጨመር ጥረት ያደርጋሉ፡፡
4. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 የተደነገገው እንደተጠበቀ ሆኖ የፈራሚ
ድርጅቶች ፖሊሲዎችና የሥራ መመሪያዎች በምልመላ፣ ቅጥር፣ሥልጠና፣
የሙያ ማሻሻያና በእድገት የሴቶች እኩልነትን ለማረጋገጥየሚቀረጹ ይሆናሉ፡፡
5. ፈራሚዎች ተቋማዊ የሴቶች ጉዳይ ፖሊሲ ለማዘጋጀትና የሚቻል
ከሆነየሴቶችን ጉዳይ በባለቤትነት የሚከታተል የሥራ ክፍል ለማቋቋም
ይጥራሉ፡፡

አንቀጽ 10፡ ሰብአዊ መብቶችን ማክበር


1. ፈራሚዎች በተለይም ከሰራተኞቻቸውና ከተጠቃሚዎች ጋር
በሚኖራቸውግንኙነት በብሔራዊና ዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና የተሰጣቸውን
ሰብአዊመብቶች ያከብራሉ፡፡
2. ፈራሚዎች ለሴቶች፣ ሕፃናት፣ ድሆች፣ አካል ጉዳተኞች፣
አረጋውያንናሌሎች የተገለሉ ወይም ለጥቃት የተጋለጡ የማሕበረሰብ
ክፍሎች መብቶችናፍላጎቶች ያልተቋረጠ ትኩረት ይሰጣሉ፡፡
3. ፈራሚዎች ለሚያገለግሉት ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች
የሞራልናየኃይማኖት እሴቶች፣ ብሔራዊ ማንነት፣ ባሕል፣ ልማድና ዘይቤ
ያልተቋረጠትኩረት ይሰጣሉ፡፡
4. ሁሉም ሰራተኞች እንደ ሰብአዊ መብቶች ባለቤት መታየትና
በፍትሃዊናሚዛናዊ መንገድ መያዝ አለባቸው፡፡ በተለይም የሰራተኞች
የመደራጀትመብት፣ ሃሳብን በነፃነት የመያዝና የመግለጽ ነፃነት መከበርና
መጠበቅአለበት፡፡

አንቀጽ 11፡የአካባቢ ጥበቃ ተቆርቋሪነት

12
1. ፈራሚዎች በሚያደርጉት ማንኛውም እንቅስቃሴ ለአካባቢ ክብካቤና
ለተፈጥሮሀብት ጥበቃ በኃላፊነትና በተነሳሽነት ላይ የተመሰረተ አሰራር
መከተልአለባቸው፤ ለዚህም አስፈላጊ በሆነ ጊዜ የአካባቢ ተጽእኖ ግምገማ
ያደርጋሉ፡፡
2. የሚቻል ሲሆን ፈራሚዎች በአካባቢ አጠባበቅ እና የተፈጥሮ
ሃብትእንዲያገግም በማድረግና በድጋሚ በመጠቀም ዙሪያ ያላቸውን
እውቀትለሌሎች ያካፍላሉ፡፡

አንቀጽ 12፡ነፃነትና ገለልተኛነት


1. ፈራሚዎች የሚደረግላቸው የገንዘብ ድጋፍ በተቋማዊ ነፃነታቸው
ላይአሉታዊ ተጽእኖ በማሳደር ሕዝባዊ ወገንተኝነታቸውን ለአደጋ
እንደማያጋልጥማረጋገጥ አለባቸው፡፡
2. ተቋማዊ ነፃነታቸውን ለመጠበቅ እና ከተልእኳቸውና ከመርሆዎቻቸው
ጋርሊጣረሱ የሚችሉ ቅድመ-ሁኔታዎችን ለመቋቋም ጥረት ማድረግ
አለባቸው፡፡
3. ፈራሚዎች ገለልተኛነታቸውን መጠበቅ አለባቸው፤ ከማንኛውም
ተቃዋሚወይም ገዢ የፖለቲካ ፓርቲ መወገን ወይም የቅርብ ትስስር
መፍጠርየለባቸውም፡፡
4. ፈራሚዎች ከማንኛውም መንግስታዊ ወይም መንግስታዊ ያልሆነ አካል
ጋርየአጋርነት ስምምነት የሚፈጽሙት ለድርጅቱ ዓላማዎች ስኬት ጠቃሚ
ከሆነእና ተቋማዊ ነፃነትና ገለልተኛነታቸውን የማይፃረር ከሆነ ብቻ ነው፡፡

አንቀጽ 13፡ያለማዳላትና እኩልነት


1. ፈራሚዎች ተጠቃሚዎችን በእኩልነት ያስተናግዳሉ፤
የሚያቀርቡትንአገልግሎት ከመጠቀም አኳያ በሚያገለግሉት ማህበረሰብ
አባላት መካከልበፆታ፣ እድሜ፣ በዘር፣ ብሄር በማህበራዊ አመጣጥ፣ በፖለቲካ
ወይምበሃብት ምክንያት ያልተፈቀደ ልዩነት አያደርጉም፡፡

13
2. ፈራሚዎች የሥራ አመራርና የበታች ሰራተኞች ግንኙነት በእኩልነት
ላይየተመሰረተ መሆኑን ያረጋግጣሉ፡፡
3. ፈራሚዎች በምልመላ፣ እድገትና የሰው ሃብት ልማት እኩል እድል
ለመፍጠርያላቸውን ቁርጠኝነት የሚያረጋግጥ ፖሊሲ በጽሁፍ ያዘጋጃሉ፡፡

አንቀጽ 14፡ ተዓማኒነት


1. ፈራሚዎች የሚያካሂዷቸው የእርዳታና የልማት ክንውኖችከተቋሙ
ራዕይ፣ግብና እሴቶች ጋር በግልጽ የተጣጣሙ መሆናቸውን እና ይህም
ከሁሉምባለድርሻ አካላት ጋር በሚኖራቸው ግንኙነት በግልጽ መታወቁን
ማረጋገጥአለባቸው፡፡
2. ፈራሚ ድርጅቶች በሚያደርጉት ማናቸውም ግንኙነት
የሚጠቀሙባቸውሴቶችና ወንዶችን፣ ሕፃናትን የሚወክሉ ምስሎችና
መልእክቶችለሚያሳዩዋቸው ሰዎች ሰብአዊ ክብር፣ እሴቶች፣ ታሪክ፣
ኃይማኖትና ባህልክብር የሚሰጡ መሆናቸውን ማረጋገጥ አለባቸው፡፡

አንቀጽ 15፡ ሕጋዊነት


1. የማንኛውም ድርጅት የሥራ ክንውኖች፣ አመራር እና ሌሎች
ጉዳዮችየአገሪቱን ሕግጋትና ደንቦች የተከተሉ መሆን አለባቸው፡፡
2. የፈራሚ ድርጅቶች የሥራ አመራር አካላት የድርጅቱን
መርሃግብሮችናአገልግሎቶች ከድርጅቱ ተልእኮ እና ከሕግ ድንጋጌዎች ጋር
አጣጥመውመቅረጽና አፈፃጸሙን መከታተል አለባቸው፡፡
3. ማንኛውም ድርጅት በሥራ ላይ የሚገኙ ሕግጋት መከበራቸውን
ለማረጋገጥበየግዜው መደበኛ የውስጥ ግምገማ ማካሄድ አለበት፤ የዚህ
ግምገማ ውጤትበአጭሩ ተዘጋጅቶ ለሥራ አመራር አካል መቅረብ አለበት፡፡

አንቀጽ 16፡ ቅንጅትና ትብብር


1. ፈራሚዎች የድርጅታቸውን ወይም የማህበራቸውንየሚያገለግሉትን
ማህበረሰብ ጥቅም ለማረጋገጥ በአጋርነትና በድጋፍግንኙነቶቻቸው ውስጥ
የትብብርና አብሮ የመስራት መንፈስእንዲዳብር ጥረት ያደርጋሉ፡፡
14
2. ፈራሚዎች በበጎ አድራጎት ዘርፍ ውስጥና ውጭ የስምምነት፣
የመደጋገፍ፣የመተባበርና በጋራ የመስራት መንፈስ እንዲሰፍን ጥረት ያደርጋሉ፡
3. ፈራሚዎች በበጎ አድራጎት ዘርፍ ውስጥና ውጭ መማማርና የጋራ
መረዳትንለማስፋፋት በማሰብ ለተልእኳቸውና ለክንውኖቻቸው አግባብ የሆነ
መረጃ፣ልምድና ግብአቶችን በጋራ የመጠቀምና የመለዋወጥ አሰራር
ይተገብራሉ፡፡
4. የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ሕብረቶች
መርሃግብሮችንከመተግበር ባለፈ የርስ በርስ መደጋገፍና አንድነትን የሚገልጹ
የጋራ ማህበረሰባዊ ራዕይ እና ግቦችን መሰረት አድርገው የሚቋቋሙ ይሆናሉ፡፡
5. ማንኛውም የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ሕብረት ለልዩነት ዋጋ
በሚሰጥ አካታች መንፈስ መመሥረት አለበት፡፡
6. የማንኛውም የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ሕብረት
አባላትአንዳቸው የሌላውን ነፃነትና ገደቦች የሚያከብሩ እና በሁሉም
የአጋርነት ክንውኖች የመተማመን መንፈስን ለማጎልበት የሚጥሩመሆን
አለባቸው፡፡
7. ማንኛውም ድርጅት የትኛውንም የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት
ሕብረት የሚቀላቀለው ከድርጅቱ ተልእኮ ጋር የሚጣጣም ከሆነ ብቻ ነው፡፡
8. ተመሣሣይ ወይም ተጠላላፊ ተልእኮ፣ እሴቶችና ተጠቃሚዎች
ያሏቸውድርጅቶችና ማህበራት እርስ በርሳቸውና ከሌሎች የሲቪል
ማህበረሰብ ተቋማት ጋር ከመወዳደር፣ ተደራራቢ አገልግሎቶችን ከማቅረብ
እና አንዳቸው የሌላውን መርሃግብር ከማሰናከል መቆጠብ አለባቸው፡፡
9. ተመሣሣይ ወይም ተጠላላፊ ተልእኮ፣ እሴቶችና ተጠቃሚዎች
ያሏቸውድርጅቶችና ማህበራት አግባብነት ያለውን የመርሃግብር መረጃ
ከሌሎች ድርጅቶችና ማህበራት ጋር መለዋወጥና እርስ በርስ መደጋገፍ
አለባቸው፡፡
10. የድርጅቱን ነፃነት ወይም እሴቶች የሚፃረር ካልሆነ በቀር ማንኛውም
ድርጅትወይም ማህበር በሌሎች ድርጅቶችና ማህበራት ለሚካሄዱ

15
ዘመቻዎችና ለሚወሰዱ እርምጃዎች አጋርነትን መግለጽ እና ለሌሎች
ድርጅቶችና ማህበራት ውጤታማነትና ስኬታማነት ድጋፍ ማድረግ አለበት፡፡

ክፍል ሶስት
የሥነ ምግባር ደንቡ አመራር
አንቀጽ 17፡ተቋማዊ አመራር
1. ፈራሚዎች ተልእኳቸውን፣ ዓላማዎቻቸውንና ድርጅታዊ
መዋቅራቸውንበግልጽ የሚያስቀምጥ ማቋቋሚያ ሰነድ ወይም መተዳደሪያ
ደንብ ይኖራቸዋል፡፡
2. በሥራ አመራር አካል አባላት የሚሰጠው አገልግሎት ከሥራው ጋር
በተያያዘአንድ አባል ያወጣውን ወጪ ለመሸፈን ከሚሰጥ ማካካሻ በቀር
በነፃናበፈቃደኝነት የሚሰጥ ይሆናል፡፡
3. ማንኛውም በቀጥታ ወይም በተዘዋዋሪ ተከፋይ የሆነ ሰው
በዳይሬክተሮችቦርድ ወይም በሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ውስጥ ሊያገለግል
አይችልም፡፡
4. በትውልድ ወይም በጋብቻ የሚዛመዱ ሁለት ሰዎች በአንድ ጊዜ
የዳይሬክተሮችቦርድ አባላት ሊሆኑ አይችሉም፡፡
5. የሂሳብ መርማሪዎች (የውስጥ ወይም የውጭ) እና ገንዘብ ያዥ
ሆነውየሚያገለግሉ ሰዎች ከዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ከአንዱ ወይም
ከድርጅቱየሥራአስፈፃሚ ዳይሬክተር ጋር በትውልድ ወይም በጋብቻ
የሚዛመዱመሆን የለባቸውም፡፡
6. የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ስብጥር የድርጅቱን ተጠቃሚዎች
ስብጥር፣የፆታ ሚዛን፣ ክህሎትና ለድርጅቱ ዓላማ ተገዢነትን ያገናዘበ መሆን
አለበት፡፡
7. የድርጅቱ የዳይሬክተሮች ቦርድ የራሱንና የሥራአስፈፃሚ
ዳይሬክተሩንየሥራ አፈፃጸም በመደበኛነትና በየጊዜው መገምገም አለበት፡፡

16
8. የድርጅቱ የሥራ አመራር አካል የድርጅቱን የሥነ-ምግባር ደንብ
ያፀድቃል፤ይህ የሥነ-ምግባር ደንብ በድርጅቱ መከበሩንም ያረጋግጣል፡፡
9. የአመራር አካላት መደበኛና በየጊዜው የሚደረጉ ስብሰባዎች
ይኖሯቸዋል፤የአመራር አካል ስብሰባዎች ቃለ-ጉባኤ ተዘጋጅቶ ለሁሉም
አባላት ይሰራጫል፣
እንደአስፈላጊነቱ ለሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ይላካል፣
ለወደፊትማመሳከሪያ የሚሆን ቅጂ ተዘጋጅቶ ይቀመጣል፡፡
10. ከሰራተኞች ግምገማና ሌላ በምስጢር መያዝ ካለበት መረጃ በቀር ቃለ-
ጉባኤው ለድርጅቱ አባላት፣ የሥራ አመራር አባላት፣ ሰራተኞች እና
ለሕዝብተደራሽ ይሆናል፡፡

አንቀጽ 18፡ የመርሃ ግብር አቀራረጽና አመራር


1. የድርጅቱ የአመራር አካል በረጅም ጊዜና የአጭር ጊዜ የስትራቴጂ
እቅድአዘገጃጀት ሂደት ከድርጀቱ ሰራተኞች ጋር በንቃት ይሳተፋል፡፡
2. የድርጅቱ የአመራር አካል የድርጅቱን መርሃግብሮችና
አገልግሎቶችይወስናል፣ ከተልእኮው ጋር መጣጣማቸውን፣ ውጤታማና
ቀልጣፋአፈፃጸምን ያረጋግጣል፡፡

አንቀጽ 19፡ የፋይናንስ አመራር


1. የድርጅቱ የአመራር አካል ድርጅቱ ተልእኮውን ለማሳካት
የሚያስችልአግባብነት ያለው የሃብት ግብአት እንዳለው ያረጋግጣል፡፡
2. የድርጅቱ የአመራር አካል አመታዊ በጀት ያፀድቃል፣ በገቢ ማሰባሰብ
ሂደትበንቃት ይሳተፋል፡፡
3. የድርጅቱ የአመራር አካል አመታዊ በጀት ከማፅደቁ በፊት
ለአስተዳደራዊናለዓላማ ማስፈጸሚያ የተመደበውን የሃብት መጠን ከሕግ
ድንጋጌዎች አንፃርይፈትሻል፡፡
4. የድርጅቱ የሥራ አመራር አባላት የድርጅቱ የአመራር አካል
ያፀደቀውንአመታዊ የበጀት ዝርዝርና ገደብ ጠብቀው ይሰራሉ፤ ማንኛውም

17
ለውጥለድርጅቱ የአመራር አካል ቀርቦ መፅደቅ አለበት፡፡ ነገር ግን የድርጅቱ
ቦርድቀድሞ በተወሰነ ገደብ ውስጥ የሚወድቁ ማሻሻያዎችን የማፅደቅ
ሥልጣንሊሰጠው ይችላል፡፡
5. ድርጅቱ ለሚያከናውናቸው መርሃግብሮች የሚመጥን የገቢና
ወጭክፍያዎችን፣ ቋሚ ንብረቶችን አስተዳደር፣ የግዢ አሰራርና
የፋይናንስቁጥጥር ሥነ-ሥርዓቱን የሚሸፍን የፋይናንስ ፖሊሲ ይኖረዋል፡፡
6. ድርጅቱ በበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት አዋጅ ድንጋጌዎች
መሰረትየሂሳብ አያያዝና ምርመራ ሙያዊ መመዘኛዎችን እና ሁሉንም
የፋይናንስናየክንውን ሪፖርት አቀራረብ ድንጋጌዎች ማሟላት አለበት፡፡
አንቀጽ 20፡ የሰው ሃብት አሰተዳደር
1. የድርጅቱ የአመራር አካል ብቃት ያለውን ሰው ለማግኘት አስፈላጊውን
ፍለጋካደረገ በኋላ ለድርጅቱ የሥራአስፈፃሚ ዳይሬክተር ይቀጥራል፡፡
2. የድርጅቱ የአመራር አካል የሥራ አስፈፃሚ ዳይሬክተሩን ክፍያ
ይወስናል፣የድርድቱን ዓላማዎች ለማስፈጸም አስፈላጊውን ድጋፍ ማግኘቱን
ያረጋግጣል፣በየጊዜው የስራ አፈፃጸሙን ይገመግማል፡፡
3. ድርጅቱ ብቃት ያላቸው፣ ኃላፊነት የሚሰማቸውና ለድርጅቱ ተልእኮ
ተገዢየሆኑ ሰራተኞችን መቅጠር አለበት፡፡
4. የሰራተኞች ቅጥር በብቃት ላይ የተመሰረተ እና በዘር፣ በፆታ፣
በብሔር፣በወገን፣ በሃይማኖት ወይም ሌላ ሁኔታ የማያዳላ መሆን አለበት፡፡
5. ድርጅቱ ሴቶችና አካል ጉዳተኞች በክፍት የሥራ ቦታዎች
ለመቀጠርእንዲያመለክቱና እንዲወዳደሩ የሚያበረታታ ፖሊሲ አዘጋጅቶ
ይተገብራል፡፡
6. ከብቃት በተጨማሪ የድርጅቱ አሰራር በብዙህነት መርህ (በዘር፣
በሃይማኖት፣በፆታ ወይም ሌላ ሁኔታ) የሚመራ ይሆናል፡፡
7. ድርጅቱ ለግላዊ ሰብእና እድገትና ለሰው ሃብት ልማት እድል የሚሰጥሁኔታ
ይፈጥራል፤ እንዲሁም የሥራ ኃላፊዎች የሰራተኞችን የግል ስብእናለማሳደግ
ድጋፍ የሚያደርጉበትን ከባቢ ሁኔታ ያዘጋጃል፡፡

18
8. የመርሃግብሮቹን መጠን ታሳቢ በማድረግ ድርጀቱ በጽሁፍ
የሰፈረናበዳይሬክተሮች ቦርድ የፀደቀ የሰው ሃብት ልማት ፖሊሲ ይኖረዋል፡፡
9. ሰራተኞች ማናቸውንም ክብደት የሚሰጣቸው አሳሳቢ ሁኔታዎች
ለድርጅቱየአመራር አካል የሚያቀርቡበት ሁኔታ ይፈጠርላቸዋል፡፡

አንቀጽ 21፡የውስጥና የውጭ ቅሬታ ሰሚና ምላሽ ሰጪ አደረጃጀት


1. ፈራሚ ድርጅቶች በሚሰጡት ውሳኔና በክንውኖቻቸው ዙሪያ
ባለድርሻአካላት አቤቱታ የሚያቀርቡበትን ስርዓት ያዋቅራሉ፣ የቀረቡ
አቤቱታዎችምበአግባቡ መታየታቸውንና አስፈላጊው እርምጃ መወሰዱን
ያረጋግጠሉ፡፡
2. ፈራሚ ድርጅቶች ሰራተኞችና በጎ ፈቃደኞችን ጨምሮ ከውስጥ
ባለድርሻአካላት አግባብ ያልሆነ ሥነ-ምግባር ስለመታየቱና የድርጅቱ
ፖሊሲዎችአልተከበሩም በሚል የሚቀርቡ አቤቱታዎችን ለማስተናገድ
የሚያስችሉአሰራሮችን በሁሉም ደረጃዎች ይዘረጋሉ፡፡
3. ፈራሚ ድርጅቶች ተጠቃሚዎችን፣ ሕዝቡን፣ ለጋሾችንና የመንግስት
አካላትንጨምሮ ከውጫዊ ባለድርሻ አካላት ለሚቀርቡ አቤቱታዎች ምላሽ
ለመስጠትየሚያስችል ተቋማዊ ፖሊሲ ይኖራቸዋል፡፡
አንቀጽ 22፡ የሃብት አሰባሰብና አጠቃቀም
1. ማንኛውም ድርጅት መደበኛ የሃብት አሰባሰብና አጠቃቀም ፖሊሲ
ይኖረዋል፤በተለይም የኢትዮጵያ፣የኢትዮጵያ የነዋሪዎች የበጎ አድራጎት
ድርጅቶችና ማህበራትን በተመለከተ ይህ ፖሊሲ ከአገር ውስጥ ለሚሰበሰብ
ገቢ ትኩረት የሚሰጥ መሆን ይሆናል፡፡
2. ቦርዱ መዋጮ በማሰባሰብና በግል መዋጮ ማድረግን ጨምሮ በገቢ
ማሰባሰብሂደት ውስጥ በንቃት ይሳተፋል፡፡
3. ማንኛውም ድርጅት ከየትኛውም ምንጭ ገቢ የሚሰበስበው ከድርጅቱ
ተልእኮጋር የሚጣጣም፣ ማእከላዊ መርሆዎቹን የማይጣረስ እና አግባብነት
ያላቸውንጉዳዮች በነፃነት፣ በጥልቀትና በትክክል የማስተናገድ አቅሙን
የማይገድብመሆኑን ካረጋገጠ በኋላ ብቻ ይሆናል፡፡

19
4. ማንኛውም ድርጅት በገቢ አሰባሰብና አጠቃቀም ዙሪያ በሚነሱ ጉዳዮች
ሁሉበግልጽነት መንቀሳቀስ አለበት፡፡
5. መርሃግብሮች የሚቀረጹት የድርጅቱን ተልእኮ ለማሳካት እንጂ
ፈጽሞየለጋሾችን ፍላጎት ለማሟላት ብቻ አይሆንም፡፡
6. ማንኛውም ድርጅት ለአንድ ክንውን ድርብ የገንዘብ ድጋፍ መቀበል፣
ለአንድክንውን ተወስኖ የተሰጠን የገንዘብ ድጋፍ ከታለመለት ዓላማ ውጭ
ለሌላክንውን መጠቀም ወይም ውጤቶችን በማጋነን ማቅረብ የመሳሰለውን
እኩይምግባር ፈፅሞ በመታገስ ወይም በመሸፋፈን ማለፍ የለበትም፡፡
7. ማንኛውም ድርጅት የገቢ ማሰባሰቢያና የማስተዋወቂያ ሰነዶች ትክክለኛ
እናየድርጅቱን ማንነት፣ ተልእኮና መርሃግብሮች በእውነተኛነት
የሚያቀርቡመሆናቸውን በጥንቃቄ ማረጋገጥ አለበት፡፡ በየትኛውም መልኩ
የማጋነንወይም ተገቢውን መረጃ የመደበቅ ሁኔታ መኖር የለበትም፤ ሃሰተኛ
ወይምአሳሳች መረጃ ወይም ስእል አይቀርብም፡፡
8. ማንኛውም ድርጅት የተቀበለው የገንዘብ መዋጮ በመርሃግብር እቅድ
ሰነዱውስጥ በግልጽ ወይም በአንድምታ ለተጠቀሰው ወይም በለጋሾች
ለታሰበውዓላማ መዋሉን ያረጋግጣል፡፡ ድርጅቱ የገንዘብ ድጋፍ የተደረገበትን
ሁኔታሊያሻሻል የሚችለው ከለጋሹ አካል ግልጽ ስምምነት ካገኘ ብቻ
ይሆናል፡፡
9. ማንኛውም ድርጅት እያንዳንዱ የገንዘብ ድጋፍ ለምን ዓላማ ወጪ
እንደተደረገየሚከታተልበት ስርዓት ይዘረጋል፡፡
10. ማንኛውም ድርጅት ገንዘብ አለአግባብ እንዳይጠፋ ለማድረግ ወይም
አለአግባብየሚወጣበትን እድል ለመቀነስ የሚያስችል የውስጥ ቁጥጥር
ሥርዓትይኖረዋል፡፡
11. ማንኛውም ድርጅት የገንዘብ አጠቃቀምና አስተዳደር ዘገባ
በየጊዜውያለመዘግየት ያዘጋጃል፡፡
12. የተሰበሰበን ገቢ የተመለከቱ የሂሳብ መግለጫዎች በተጠየቀ ጊዜ
ለለጋሹናለሚመለከታቸው አካላት መቅረብ አለበት፡፡

20
አንቀጽ 23፡ የጥቅም ግጭት እንዳይፈጠር መከላከል
ማንኛውም ፈራሚ ድርጅት ወይም ማህበር የሚከተሉትን ጨምሮ አግባብነት
ያላቸውን ጉዳዮችየሚሸፍን የጥቅም ግጭት ፖሊሲ ሊኖረው ይገባል፡-
1. ሁሉም የድርጅቱ ወይም የማህበሩ የሂሳብ ክንውኖች ከግልና ከሙያዊ
የጥቅም ግጭት ነፃ መሆን አለባቸው፤
2. የቦርድና ተራ አባላት፣ የሥራ መሪዎች፣ አማካሪዎች፣ ተለማማጅ
ሰራተኞችናበጎ ፈቃደኞች ወይም ሌሎች ሰራተኞች የድርጅቱን ሥራዎች
በቅንነትናበትጋት ማከናወን እና ለድርጅቱ ጥቅም ብቻ ከፍተኛ ጥንቃቄ፣
ክህሎትናየማመዛዘን ብቃት የመተግበር ኃላፊነት አለባቸው፡፡
3. የአመራር አካል አባላት፣ ተከፋይ ሰራተኞች እና በጎ ፈቃደኞች
ማናቸውንምየጥቅም ግጭት ወይም የቁሳቁስና አገልግሎት አቅራቢዎች ከሆኑ
ወይምሊሆኑ ከሚችሉ አካላት ጋር፣ የድርጅቱን ገንዘብ ከሚቀበሉ ወይም
ተወዳዳሪናተፃራሪ ዓላማ ካላቸው ድርጅቶች ጋር ማናቸውም ዝምድና
ቢኖራቸውለድርጅቱ አመራር አካል ማሳወቅ ይኖርባቸዋል፡፡
4. የቀደመው ንዑስ አንቀጽ ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆነው የአመራር
አካልአባላትና ተከፋይ ሰራተኞች የጥቅም ግጭት ሊከሰት በሚችልበት ጉዳይ
ላይከሚደረግ ውይይት ወይም የድምጽ መስጠት ሂደት ራሳቸውን
ማግለልወይም በውሳኔ አሰጣጥ ከመሳተፍ መቆጠብ አለባቸው፡፡
5. እነዚህ ሰዎች ኃላፊነታቸውን በመወጣት ሂደት የሚያከናውኗቸውን
ተግባራትበፍጹም ቅን ልቦና መፈጸም እና የያዙትን የኃላፊነት ቦታ ወይም
በሥራቸውአጋጣሚ ያገኙትን መረጃ ለግል ጥቅማቸው ከማዋል መቆጠብ
አለባቸው፡፡
6. በሁሉም ውሳኔዎችና ተግባራት የድርጅቱ ጥቅም ቀዳሚ ታሳቢ
መሆንአለበት፡፡
7. የድርጅቱ ወይም ማህበሩ የጥቅም ግጭት ፖሊሲ የጥቅም ግጭት
ሊከሰትባቸው የሚችልባቸውን ሁኔታዎች፣ የጥቅም ግጭቱን ባሕሪ፣
የተከሰተና ሊከሰት የሚችል የጥቅም ግጭት ስለሚገለጽበት አግባብ እና
ከውሳኔ አሰጣጥ ስለመታቀብ በዝርዝርና በግልጽ የሚተነትን መሆን አለበት፡፡
21
8. የድርጅቱ ወይም የማህበሩ አመራር አካል የጥቅም ግጭት መግለጫ ሰነድ
አዘጋጅቶ በእያንዳንዱ ሰራተኛ በአገልግሎት ዘመኑ መጀመሪያ ላይ ወይም
ሰራተኛው ድርጅቱን በሚቀላቀልበት ጊዜ እንዲፈረም ያደርጋል፡፡
9. የትኛውም አባል፣ ዳይሬክተር ወይም ሰራተኛ በቀጥታ በሚመለከተው
ውሳኔላይ እንዲሳተፍ አይፈቀድም፡፡
ክፍል አራት
የሥነ-ምግባር ደንቡን ስለማስፈጸም
አንቀጽ 24፡መመስረት
1. በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት የራስ
አስተዳደር ሕብረት መተዳደሪያ ደንብ በሚደነገገው መሰረት በዚህ ደንብ
የተጠቀሱትን መሰረታዊ የሥነ-ምግባር መርሆች ለማስፋፋትና በፈራሚዎች
መተግበራቸውን ለማረጋገጥ የስነ ምግባር አስከባሪ ፓነል በሕብረቱ ውስጥ
ይቋቋማል፡፡
2. ፓነሉ ተጠሪነቱ ለጠቅላላ ጉባኤው ይሆናል፡፡
3. ፓነሉ ባላቸው ከፍተኛ የሞራል እሴቶች፣ በታማኝነታቸውና
በገለልተኝነታቸውበማህበረሰቡ ውስጥ መልካም ስም ያተረፉና እና በሲቪል
ማህበረሰብ ተቋማትአደረጃጀትና አሰራር ዙሪያ ብቃት ያላቸው ዘጠኝ አባላት
ይኖሩታል፤ በተለይምየሕግ ትምህርትና ልምድ ያላቸው ግለሰቦች ለአባልነት
ትኩረት ይሰጣቸዋል፡፡
4. የሕብረቱ ሥራአስፈፃሚ ዳይሬክተር ድምጽ የመሥጠት መብት
ሣይኖረውበቀጥታ የፓነሉ አባልና ጸሃፊ ይሆናል፡፡

አንቀጽ 25፡ የፓነሉ አመራረጥና የአባላት ሥብጥር


1. የፓነሉ አባላት ምርጫ ዴሞክራሲያዊና አሳታፊ በሆነ አኳኋን ይካሄዳል፡፡
2. የዚህ ደንብ አንቀጽ 30 ንዑስ አንቀጽ (3) ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ
ሆነውየፈራሚዎች ጠቅላላ ጉባኤ ለፓነሉ አባላት ጥቆማና አመራረጥ
መመዘኛዎችንሊያስቀምጥ ይችላል፡፡

22
3. የፓነሉ አባላት ከፈራሚ ድርጅቶች፣ ከመንግስት፣ ከለጋሽ ድርጅቶች፣
ከንግዱማህበረሰብና ከመገናኛ ብዙሃን የሚወከሉ ይሆናሉ፡፡ የአባላቱ
ስብጥርምእንደሚከተለው ይሆናል፡ -
ሀ) አምስት የፈራሚዎች ተወካዮች፣
ለ) አንድ ከለጋሽ ድርጅቶች፣
ሐ) አንድ ከመንግስት አካላት፣
መ) አንድ ከንግዱ ማህበረሰብ፣
ሠ) አንድ ከመገናኛ ብዙሃን፡፡
4. ማንኛውም ፈራሚ ድርጅት ለፓነሉ አባላት ምርጫ ጥቆማ ሊያቀርብ
ይችላል፡፡
5. የፓነሉ አባላት አገልግሎት የሚሰጡት ራሳቸውን በመወከል ይሆናል፡፡
አንቀጽ 26: የአገልግሎት ዘመን
የፓነሉ አባላት የአገልግሎት ዘመን ሦስት ዓመት ሲሆን ማንኛውም አባል
ከሁለትተከታታይ የአገልግሎት ዘመን በላይ ሊያገለግል አይችልም፡፡

አንቀጽ 27፡ የፓነሉ ተግባርና ሃላፊነት


የሥነ ምግባር ደንብ አስከባሪ ፓነል የሚከተሉት ተግባራትና ኃላፊነቶች
ይኖሩታል፡
1. የሥነ-ምግባር ደንቡ የበላይ ጠባቂ በመሆን የደንቡን አፈፃጸምና
አስተዳደርበበላይነት ይቆጣጠራል፤ በተለየ ምክንያት አስፈላጊ ካልሆነ በቀር
ትኩረቱንበፖሊሲ ጉዳዮች እንጂ በቀን-ተቀን እንቅስቃሴዎች ላይ አያደርግም፡፡
2. ከፈራሚ ሕብረቶች ጋር በመተባበር በዚህ ደንብ የተጠቀሱ የሥነ-
ምግባርመመሪያዎችን ተፈፃሚነት ያራምዳል፡፡ በተለይም፡-
ሀ) በሲቪል ማህበረሰብ ተቋማት የሥነ-ምግባር ተግዳሮቶች ዙሪያ
ሰነዶችንያሰባስባል፣ ጥናትና ምርምር ያካሂዳል፤

23
ለ) የሥነ-ምግባር ደንቡን አፈፃጸም ለማገዝ ሴሚናሮችን፣
ሲምፖዚየሞችንናጉባኤዎችን ያዘጋጃል፣ መረጃ ያሰራጫል፤
ሐ) የሥነ-ምግባር ተግዳሮቶችን ለመፍታት የሚያግዙ መርሆዎችንና
ድንጋጌዎችንያዘጋጃል፣ ያወጣል፤
መ) የሥነ-ምግባር መመሪያዎችን አፈፃጸም ለማስፋፋትና ለማስጠበቅ
ከሕብረቶችጋር ይተባበራል፤
ሠ) የዚህን ደንብ ድንጋጌዎች ይተረጉማል፡፡
3. የተለያዩ የአሰራር ስልቶችን በመጠቀም የዚህ ደንብ ድንጋጌዎች
በፈራሚዎችመተግበራቸውን ያረጋግጣል፤ በተለይም፡-
ሀ) ዝጋቤዎችን ይቀበላል፤
ለ) አቤቱታዎችን ያስተናግዳል፣
ሐ) ድርጅቶችን ይጎበኛል፤
መ)የጥራት ማረጋገጫ ሰርትፊኬት ይሰጣል፤
ሠ) ለተለየና አርአያ ለሆነ በጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት የሥነ-ምግባር
ሽልማት ይሰጣል፡፡
4. በጠቅላላ ጉባኤው የሚሰጡትን ሌሎች ተግባራት ያከናውናል፡፡
አንቀጽ 28፡ የዝጋቤ (ሪፖርት) አቀራረብ ሥነ-ሥርዓት
1. እያንዳንዱ ፈራሚ ድርጅትና ማህበር የዚህን ደንብ ድንጋጌዎች ለመተግበር
ስለወሰዳቸው እርምጃዎች በመደበኛነትና በየጊዜው ዝጋቤ ለማቅረብ
ኃላፊነት ይወስዳል፡፡
2. ፈራሚዎች ዝጋቤያቸውን በየሦስት ዓመት ፓነሉ በሚያዘጋጀው የጊዜ
ሰሌዳመሰረት ያቀርባሉ፡፡
3. የሚቀርበው ዝጋቤ በደንቡ አፈፃጸም የተገኙ ውጤቶችና ያጋጠሙ
ተግዳሮቶችንጨምሮ የተሟላ መረጃ የያዘ መሆን አለበት፡፡
4. ፓነሉ የቀረበለትን ዝጋቤ ከቃኘ እና የዝጋቤውን ይዘት ለማረጋገጥ
የሚያግዙየትኛቸውንም የመረጃ ምንጮች ከተመለከተ በኋላ በደንቡ
24
አፈፃጸም በድርጅቱየተገኙ ውጤቶችና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን የሚያካትት
የማጠቃለያ ምልከታይሰጣል፤ እንዲሁም ለወደፊት መሻሻል ስላለባቸው
ጉዳዮች ምክረ-ሃሳብያቀርባል፡፡
5. ማንኛውም ሌላ ፈራሚ ድርጅት ወይም ማህበር ወይም ጉዳዩ
የሚመለከተው ሰው በፈራሚድርጅቱ በቀረበው ዝጋቤ ላይ አስተያየት ሊሰጥ
እና አስተየያቱን በጽሁፍአድርጎ ዝጋቤውን ለሚመለከተው አካል አቅርቦ
እንዲታይለት ማድረግይችላል፡፡
6. ፓነሉ የዝጋቤ አቀራረብ ሥነ-ሥርዓት ደንቦችና የሥነ-ምግባር
ደንቡንአፈፃጸም የተመለከቱ መመሪያዎችን ሊያዘጋጅ ይችላል፡፡
አንቀጽ 29፡ የብቃት ማረጋገጫ ስለመስጠት
1. ይህ ደንብ ስልጣን በተሰጠው አካል የሚሰጥ የብቃት ማረጋገጫ
የራስቁጥጥርን ለማጠናከር አስተዋጽኦ እንደሚያበረክት እውቅና ይሰጣል፡፡
2. በፈራሚዎች ጠቅላላ ጉባኤ በሚወሰነው መሰረት ፓነሉ የብቃት
ማረጋገጫየመስጠት ሚና ሊኖረው ይችላል፡፡
3. በብቃት ማረጋገጫ የመስጠት ሂደት ያለፉ ወይም አግባብነት ባለው
አካልየብቃት ማረጋገጫ የተሰጣቸው ፈራሚ ድርጅቶች ማረጋገጫው
ተፈፃሚለሆነበት ጊዜ በዚህ ደንብ አንቀጽ 11 መሰረት ለፓነሉ ዘገባ የማቅረብ
ግዴታአይጣልባቸውም፡፡
4. የቀደመው ንኡስ አንቀጽ ድንጋጌ ቢኖርም የብቃት ማረጋገጫ
የተሰጠበትስርዓት በዚህ ደንብ በተካተቱት የሥነ-ምግባር መመዘኛዎች ጋር
የተጣጣመስለመሆኑ ፓነሉ ምርመራ ሊያደርግ ይችላል፡፡ ከዚህ ምርመራ
ውጤትላይ በመነሳት ፓነሉ የብቃት ማረጋገጫውን ለመቀበል ወይም
ላለመቀበልሊወስን ይችላል፡፡
5. ፓነሉ የብቃት ማረጋገጫ የመስጠቱን ሂደት በተመለከተ ዝርዝር
መመሪያዎችናየሥነ-ሥርዓት ድንጋጌዎችን ያወጣል፡፡
አንቀጽ 30፡ስለማሳወቅ (ቅሬታ ስለማቅረብ)

25
1. ፈራሚ ድርጅቶችና ማህበራት ፣ ለጋሾች፣ የመንግስት አካላት፣
ተጠቃሚዎች ወይም ሕዝቡ ወይም ሌላ ማንኛውም ሰው የዚህ ደንብ
ድንጋጌዎች በየትኛውም ፈራሚ ድርጅት ወይም ማህበር ተጥሰዋል
የሚያስብል ምክንያት ሲኖር ለፓነሉ አቤቱታ ከማቅረብ በፊት ስለሁኔታው
ለፈራሚው ድርጅት ወይም ማህበር በጽሁፍ ማስታወቅ አለባቸው፡፡
ሁኔታውን በአግባቡ መከታተል እንዲያስችል ይህን ማስታወቂያ ፓነሉ ወይም
ድርጅቱ አባል የሆነበት ሕብረት እንዲያውቀው ሊደረግ ይችላል፡፡
2. ማስታወቂያ ወይም አቤቱታ የደረሰው ፈራሚ ድርጅት ወይም
ማህበርማስታወቂያው ወይም አቤቱታው በደረሰው በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ
ለአቤቱታ አቅራቢው ሰው በጽሁፍ የተሰጠውን መፍትሄ ወይም በቀጣይ
ሊወሰዱ ስለሚችሉ አማራጮች ጨምሮ ስለሁኔታው የሚተነትን ማብራሪያ
ወይም መግለጫ መስጠት አለበት፡፡
3. ጉዳዩ አመልካቹን ወይም አቤቱታ አቅራቢውን በሚያረካ መልኩ
የመጀመሪያውማስታወቂያ ለፈራሚው ድርጅት ወይም ማህበር ከደረሰ
በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ መፍትሄ ያላገኘ እንደሆን አመልካቹ ጉዳዩን ለፓነሉ
ወይም ፈራሚ ድርጅቱ አባል ለሆነበት ሕብረት ሊያቀርብ ይችላል፡፡
አንቀጽ 31፡ ለፓነሉና ለሕብረቶች ሥለሚቀርቡ አቤቱታዎች
1. ለፓነሉ ወይም ለሕብረቱ በማንኛውም ሰው አቤቱታ ሊቀርብ
ይችላል፤አቤቱታውም፡ -
ሀ) በጽሁፍ ወይም በቃል ሆኖ ለፓነሉ ሊቀ-መንበር ወይም በሕብረቱ
ለተሰየመውሰው ሊቀርብ ይችላል፤
ለ) አቤቱታው የቀረበው በቃል ከሆነ የፓነሉ ሥራአስፈፃሚ ዳይሬክተር
(ጸሐፊ) አቤቱታውን በጽሁፍ ካሰፈረ በኋላ አቤቱታ አቅራቢው በፊርማ
እንዲያረጋግጥያደርጋል፤
ሐ) አቤቱታ በየትኛውም የአገሪቱ ቋንቋ ሊቀርብ ይችላል፤ የመተርጎም
ኃላፊነትየፓነሉ ይሆናል፡፡
መ) የአቤቱታ አቅራቢውን ስምና አድራሻ የያዘ መሆን አለበት፤

26
ሠ) በዚህ ደንብ ውስጥ በተካተቱት የሥነ-ምግባር መመዘኛዎች መሰረት
መቅረብ አለበት፤
ረ) በበቂ መረጃ የተደገፈ መሆን አለበት፤ በመረጃ ያልተደገፈ ወይም
በአሉባልታላይ የተመሰረተ ሊሆን አይገባም፡፡
ሰ) ጥሰት ተፈፅሟል ከተባለበት ጊዜ በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ መቅረብ
አለበት፤
ሸ) በቂ ምላሽ በተሰጠው ወይም በሌላ አግባብ በመታየት ላይ ያለን
ጉዳይየሚመለከት መሆን የለበትም፡፡
2. የተቀመጡት የመፍትሄ አማራጮች ከሚገባው በላይ ጊዜ
እንደሚወስዱለፓነሉ ወይም ለሕብረቱ ግልጽ ሆኖ ካልሆነ በቀር ፓነሉ ወይም
ሕብረቱየቀረበለትን ጉዳይ ሊመለከት የሚችለው በድርጅቱ ወይም ማህበሩ
ውስጥ የሚገኙ የመፍትሄ አማራጮች በሙሉ ጥቅም ላይ መዋላቸውን
ካረጋገጠ በኋላ ብቻ ነው፡፡
አንቀጽ 32፡ የሥልጣን ክልል
1. ፓነሉ የመጀመሪያ ደረጃና የይግባኝ ሥልጣን ይኖረዋል፡፡
2. በፈራሚ ሕብረት ወይም የየትኛውም ሕብረት አባል ባልሆነ አንድ
ፈራሚድርጅት ላይ ከሆነ አቤቱታው በቀጥታ ለፓነሉ ይቀርባል፡፡
3. የቀደመው ንኡስ አንቀጽ ድንጋጌዎች ቢኖሩም የዚህ ደንብ ፈራሚ
የሆነሕብረት አባል በሆነ ፈራሚ ድርጅት ላይ የሚቀርብ አቤቱታ
በመጀመሪያበሕብረቱ ደረጃ መቅረብና መታየት አለበት፤ በዚህ ሁኔታ ፓነሉ
የይግባኝሥልጣን ብቻ ይኖረዋል፡፡
4. የሚከተሉት ጉዳዮች በፈራሚ ሕብረቶች የዳኝነት ሥልጣን ሥር
ይወድቃሉ፡
ሀ) አግባብነት ያላቸውን ተቋማዊ ፖሊሲዎች ስለማውጣት፣
ለ) ከሰው ሃብት አስተዳደር የሚመነጩ ጉዳዮች፣

27
ሐ) ዘገባዎችን ለተጠቃሚዎች፣ ለሕዝብ፣ ለለጋሾችና ለሰራተኞች
ተደራሽማድረግን ጨምሮ ዘገባ የማዘጋጀትና የማቅረብ ግዴታዎችን
ስላለማሟላትየሚመለከቱ ጉዳዮች፡፡
5. ለሕብረቶች በግልጽ ያልተሰጡ ጉዳዮች በፓነሉ ሥልጣን ሥር ይወድቃሉ፡፡

አንቀጽ 33፡ ፓነሉ ምርመራ የሚያካሂድበት ሥርዓት


1. ፓነሉ የትኛውም ፈራሚ ድርጅት ወይም ማህበር የሥነ-ምግባር ደንቡን
ድንጋጌዎች ስለመጣሱ የቀረበ ማንኛውንም ሥሞታ በራስ ተነሳሽነት
ሊመረምርና ከደንቡ መመዘኛዎች ጋር የተጣጣመ አሰራር እንዲኖር የሚያግዝ
እርምጃ ሊወስድ ይችላል፡፡
2. ፓነሉ ማናቸውንም አግባብነት ያላቸው የምርመራ ዘዴዎች ሊጠቀም
ይችላል፤የሌሎች ፈራሚ ድርጅቶች ወይም ማህበራትን ወይም
ማህበራት፣የመንግስት አካላትን፣ ለጋሽ ድርጅቶችን፣የሕዝቡን ወይም ሌላ
አግባብነት ያለውን መረጃ ሊሰጥ የሚችልን ሰው አስተያየት ሊያዳምጥ
ይችላል፡፡
አንቀጽ 34፡ አቤቱታዎችን የመስማት ሂደት
1. ለፓነሉ የሚላኩ አቤቱታዎች በስራ አስፈፃሚው አካል አድራሻ
ተልከውለፓነሉ ሊቀ-መንበር እንዲደርሱ ይደረጋል፡፡
2. የሥራ አስፈፃሚው ዳይሬክተር አቤቱታው እንደደረሰው ከላይ በአንቀጽ
31(1)
(ሀ) እና (ለ) ድንጋጌዎች መሰረት አቤቱታው የተሟላ መሆኑን ያረጋግጣል፡፡
3. የፓነሉ ሊቀ-መንበር ከፓነሉ አባላት ውስጥ ሦስቱ የሚገኙበት
ጉዳዩንየሚመለከት ኮሚቴ ያቋቁማል፡፡
4. ኮሚቴው የቀረበው አቤቱታ በቂ መሰረት ያለው ስለመሆኑ ያረጋግጣል፡፡
ኮሚቴው አቤቱታው በቂ መሰረት የሌለው መሆኑን ሲያምን
አቤቱታየቀረበበትን ፈራሚ ድርጅት ወይም ማህበር መጥራት ሳያስፈልገው
ክሱን ውድቅ ያደርገዋል፡፡

28
5. ኮሚቴው አቤቱታው በቂ መሰረት ያለው መሆኑንና አቤቱታው
የቀረበበትፈራሚ ድርጅት ወይም ማህበር ምላሽ ሊሰጥበት እንደሚገባ
ሲያምን የአቤቱታውን ቅጅ ለፈራሚ ድርጅቱ በመላክ ድርጀቱ ወይም
ማህበሩ በሰላሳ ቀናት ውስጥ ምላሹን በጽሁፍ እንዲያቀርብ ይጠይቃል፡፡
6. የሥራአስፈፃሚ ዳይሬክተሩ ፓነሉ አቤቱታውን ለመመርመር ውሳኔ
ላይመድረሱን እና አቤቱታው የሚስተናገድበትን የጊዜ ሰሌዳ ለአቤቱታ
አቅራቢውመሳወቅ አለበት፡፡
7. መልስ ሰጪው በቂ ምክንያት ካላቀረበ በቀር ዘግይቶ የሚቀርብ
መልስተቀባይነት አይኖረውም፤ በመሆኑም ጉዳዩ በአቤቱታው መሰረት
መታየትይጀምራል፡፡ ከተቀመጠው የጊዜ ገደብ በኋላ ምላሽ ለማቅረብ
ማመልከቻሊቀርብ የሚችለው ኮሚቴው የመጨረሻ ውሳኔ ላይ ከመድረሱ
በፊት ብቻይሆናል፡፡
8. ኮሚቴው አቤቱታውን እና ክስ በቀረበበት ፈራሚ የተሰጠውን
ምላሽይመረምራል፡፡ ኮሚቴው በተጨማሪ ከአቤቱታ አቅራቢው፣ መልስ
ሰጪውወይም ከሌላ ማናቸውም ሰው ተጨማሪ መረጃ ሊፈልግ ወይም
በጽሁፍእንዲቀርብለት ሊጠይቅ ይችላል፡፡
9. ኮሚቴው የሚከተሉትን በጽሁፍ ሊወስን ይችላል፡ -
ሀ) አቤቱታው ውድቅ መሆን እንዳለበት፣
ለ) ፈራሚው የደንቡን ድንጋጌዎች መጣሱን እና በፈራሚው መወሰድ
ያለባቸውንእርምጃዎች፡፡

አንቀጽ 35፡ የይግባኝ ሥነ-ሥርዓት


1. በኮሚቴው ወይም ፈራሚው አባል በሆነበት ሕብረት በተሰጠው ውሳኔ
ቅሬታያደረበት የትኛውም ወገን ውሳኔው ከተሰጠ በሰላሳ ቀናት ውስጥ
ከፓነሉይግባኝ ሊጠይቅ ይችላል፡፡ ይህ የጊዜ ገደብ ፓነሉ በተቀበለው በቂ
ምክንያትለተጨማሪ ሰላሳ ቀናት ሊራዘም ይችላል፡፡

29
2. ይግባኙ የፓነሉ አምስት አባላት በሚገኙበት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ይታያል፡፡
ጉዳዩን በመጀመሪያ ደረጃ ሥልጣን የተመለከተው ኮሚቴ አባላት ያንኑ
ጉዳይበሚመለከተው ችሎት አይቀመጡም፡፡
3. የይግባኝ ማመልከቻ የሚከተሉትን የያዘ መሆን አለበት፡-
ሀ) ይግባን የሚጠየቅበትን ውሳኔ የሰጠው ሕብረት ስያሜ፣
ለ) የይግባኙ ምክንያት፣
ሐ) የሚጠየቀው መፍትሄ፣
መ) ይግባኝ የሚጠየቅበት ውሳኔ የተሰጠበትን ሂደትና ውሳኔውን
የሚያሳይየተሟላ ሰነድ በተረጋገጠ ቅጂ ከይግባኝ ማመልከቻቸው ጋር ተያይዞ
መቅረብአለበት፡፡
4. ችሎቱ በይግባኝ ማመልከቻው በቀረቡት ምክንያቶች ሳይወሰን
ሌሎችጉዳዮችን ሊመረምር ይችላል፡፡
5. ችሎቱ የይግባኝ ማመልከቻውን የሚቀበለው ከሆነ የይግባኝ
ማመልከቻውለመልስ ሰጭ እንዲደርስ ያደርጋል፣ አቤቱታውን ለመስማት
ቀጠሮ ይቆርጣል፡፡ በዚህ ቀን መልስ ሰጭው ተገኝቶ መልሱን እንዲያቀርብ
መጥሪያ ይልካል፡፡ የሚላከው መጥሪያ የተላከለት ሰው ባይቀርብም አንኳ ጉዳዩ
መታየት እንደሚቀጥል የሚገልጽ መሆን አለበት፡፡
6. ችሎቱ ውሳኔ ከመስጠቱ በፊት አቤቱታውን፣ የይግባኝ
ማመልከቻውን፣በፈራሚው የቀረቡ ሰነዶችን፣ ለይግባኝ ማመልከቻው
የተሰጠውን ምላሽ፣በሕብረቱ ወይም በኮሚቴው የተሰጠውን ውሳኔ እና ሌላ
ማንኛውንም አግባብሆነ ያገኘውን መረጃ ይመረምራል፡፡
7. ችሎቱ በሚከተሉት ጭብጦች ላይ በድምጽ ብልጫ ውሳኔ ይሰጣል፡-
ሀ) የበታች ውሳኔውን ውድቅ ለማድረግ፣
ለ) የበታች ውሳኔውን ሙሉ በሙሉ ለማጽናት፣
ሐ) የበታች ውሳኔውን ከማሻሻያ ጋር ለማጽናት፡፡
8. የችሎቱ ውሳኔ የመጨረሻ ይሆናል፡፡

30
አንቀጽ 36፡ የፓነሉን ውሳኔ ማሳወቅ
ፓነሉ ወይም ሕብረቱ የደረሰበትን ውሳኔ፣ መወሰድ ያለባቸውን
ቀጣይእርምጃዎችና ይግባኝ የመጠየቅ መብታቸውን ለአቤቱታ አቅራቢና
ለፈራሚውድርጅት በጽሁፍ ያሳውቃል፡፡
አንቀጽ 37፡በሕብረቶች አቤቱታዎችን ስለመመልከት
1. ሕብረቶች አቤቱታ የማስተናገድ ስልጣናቸውን ሲፈጽሙ ከላይ
ለፓነሉየተቀመጡትን መርሆዎችና ሥነ-ሥርዓቶች ተከትለው ይሆናል፡፡
2. ሕብረቶች ተጠሪነቱ ለጠቅላላ ጉባኤ የሆነና የሥነ-ምግባር ጉዳዮችንና
የዚህንደንብ ድንጋጌዎች የተመለከቱ አቤቱታዎችን ለመቀበል ሥልጣን
ያለውገለልተኛ አካል ያቋቁማሉ፡፡
3. ይህንን አካል ያላቋቋሙ ወይም ሊያቋቁሙ የማይችሉ ሕብረቶች
በአባላቶቻቸውላይ የሚቀርቡ አቤቱታዎችን የመቀበል ሥልጣን
አይኖራቸውም፤ ይህሥልጣን በፓነሉ የሚተገበር ይሆናል፡፡
አንቀጽ 38፡ የዲስፕሊን እርምጃዎች
1. ፓነሉ ወይም አቤቱታው የቀረበለት ሕብረት ፈራሚው ድርጅት ወይም
ማህበር የዚህን ደንብ ድንጋጌዎች መጣሱን ሲወስን በመጀመሪያ ጉዳዩን
በድርድር ለመፍታት ይሞክራል፡፡
2. ሕብረቶች የመተዳደሪያ ደንባቸውን መሰረት በማድረግ
ማስጠንቀቂያመስጠት፣ ማገድ እና ከአባልነት ማስወገድን ጨምሮ በአባል
ድርጅቶች ወይም ማህበራት ላይ አግባብነት ያለውን እርምጃ ሊወስዱ
ይችላሉ፡፡ በተጨማሪም ፓነሉ በአባል ድርጅቱ ወይም ማህበሩ ላይ ሊወስድ
ስለሚገባው እርምጃ የውሳኔ ሃሳብ ሊያቀርቡ ይችላሉ፡፡
3. የቀደመው ንኡስ አንቀጽ ድንጋጌ ቢኖርም ሕብረቶች ማንኛውንም
የዚህንደንብ ፈራሚ ድርጅት ወይም ማህበር ከደንቡ አባልነት ሊሰርዙ
አይችሉም፤ ይህንን የማድረግ ሥልጣን የፓነሉ ብቻ ይሆናል፡፡

31
4. ፓነሉ በራሱ አነሳሽነት ወይም ጉዳዩ ከቀረበለት ሕብረት በተሰጠው
የውሳኔሃሳብ መሰረት ከሚከተሉት አንዱን የዲስፕሊን እርምጃ ወይም
በተደራራቢነትሊወስድ ይችላል፡-
ሀ) ማስጠንቀቂያ መስጠት፣
ለ) ማገድ፣
ሐ) ከፈራሚነት መሰረዝ፡፡
5. በአንቀጽ 35 የተደነገገው የይግባኝ ማቅረቢያ ጊዜ ሳይጠናቀቅ ወይም
ይግባኝከተጠየቀ በፓነሉ የመጨረሻ ውሳኔ ሳይሰጥ የትኛውም ዓይነት
የዲሲፕሊንእርምጃ ሊወሰድ አይችልም፡፡
አንቀጽ 39፡ ውሳኔዎችን መመዝገብና ማሰራጨት
1. ግልጽነትን ከማጠናከር አንፃር በፓነሉ ወይም ፈራሚው አባል
በሆነበትሕብረት የተደረሰው ማንኛውም ውሳኔ በአግባቡ መመዝገብና
መሰራጨትአለበት፡፡
2. በውሳኔው ውስጥ በተለየ መልኩ ካልተቀመጠ በቀር የውሳኔው
መዝገብቢያንስ ለሁለት አመታት ተፈፃሚ ይሆናል፤ ወደፊት ለሚከሰት
ጥፋትየቅጣት ማክበጃ ሆኖም ያገለግላል፡፡
3. በፓነሉ ወይም ፈራሚው አባል በሆነበት ሕብረት የተደረሰው
ማንኛውምውሳኔ ፈራሚ ድርጅቱ ለጋሾች፣ ህዝቡ፣ ተጠቃሚዎችና
የመንግስት አካላትእንዲያውቁት በተለያየ የግንኙነት ዘዴ ይሰራጫል፤
4. ፓነሉ ወይም ፈራሚው አባል የሆነበት ሕብረት አስፈላጊ ሆነ
ሲያገኘውበማንኛውም ጊዜና በመረጠው በየትኛውም ዘዴ የሚከተለውን
መረጃሊያሰራጭ ይችላል፡-
ሀ) የአቤቱታ አቅራቢውንና አቤቱታ የቀረበበትን ፈራሚ ድርጅት ወይም
ማህበርሥያሜ ጨምሮ አቤቱታው ስለመቅረቡ፣
ለ) አቤቱታ ቀርቦ ሊመረመር መሆኑን፣ በመመርመር ላይ እንደሆነ
ወይምእንደተመረመረ፣ እና
ሐ) የምርመራውን ውጤት እና የተወሰደ ማንኛውንም የዲሲፕሊን እርምጃ፡፡
32
ክፍል አምስት
ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች
አንቀጽ 40፡ ፈራሚ ድርጅት ወይም ማህበር ከአባልነት ስለሚለቅበት ሁኔታ
1. ማንኛውም ፈራሚ ድርጅት በማንኛውም ጊዜ ለጠቅላላ ጉባኤው
በፅሁፍበማሳወቅ አባልነቱን ሊተው ይችላል፡፡
2. በቀደመው ንኡስ አንቀጽ የተቀመጠው ቢኖርም ማንኛውም አቤቱታ
የቀረበበትፈራሚ ቅሬታ ቀርቦበት አቤቱታው በመታየት ላይ እያለ አባልነቱን
ቢተውየዲሲፕሊን እርምጃ መወሰዱንም ሆነ ይህንኑ ለሕዝብ ማሳወቅን
ጨምሮየአቤቱታውን ምርመራና ውሳኔ ሂደት አያቋርጠውም፡፡
አንቀጽ 41፡ የፈራሚነት ክፍያ ክፍያ
1. የአባልነት ክፍያ በበጀት አመቱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ተከፋይ ይሆናል፡፡
2. በበጀት አመቱ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አባል የሆነ ፈራሚ
የአመቱንየአባልነት ክፍያ መክፈል አለበት፡፡
3. በበጀት አመቱ ሁለተኛ ሩብ ዓመት አባል የሆነ ፈራሚ የአባልነት
ክፍያመክፈል የሚጀምረው ከቀጣዩ የበጀት ዓመት ጀምሮ ይሆናል፡፡
4. በአባላት የሚከፈለው ዝቅተኛው አመታዊ የአባልነት ክፍያ በጠቅላላ
ጉባኤውይወሰናል፡፡
አንቀጽ 42፡ የሥነ-ምግባር ደንቡን ስለማሻሻል
1. ይህንን የሥነ-ምግባር ደንብ የማሻሻል ሃሳብ ከደንቡ ፈራሚዎች
ቢያንስአስር በመቶ የሚሆኑት ወይም የሥነ-ምግባር ደንቡን አፈፃጸም
ለመከታተልየተቋቋመው ፓነል ወይም ቢያንስ ሦስት የሥነ-ምግባር ደንቡ
ፈራሚ የሆኑሕብረቶች የደገፉት እንደሆነ ለውይይት ይቀርባል፡፡
2. ማንኛውም የማሻሻያ ሃሳብ ከደጋፊ የማብራሪያ ጋር በጽሁፍ
ለጠቅላላጉባኤው መቅረብ አለበት፡፡

33
3. ይህ የሥነ-ምግባር ደንብ ሊሻሻል የሚችለው ምልአተ ጉባኤ
በተሟላበትየጠቅላላ ጉባኤው ስብሰባ ከተገኙትና ድምጽ ከሰጡት አባላት
3/4 ኛ የሆኑትሲደግፉት ይሆናል፡፡
አንቀጽ 43፡ ደንቡ የሚጸናበት ጊዜ
1. ይህ የተሻሻለው የሥነ-ምግባር ደንብ በፈራሚ ድርጅቶች ጠቅላላ
ጉባኤከፀደቀበት ቀን ጀምሮ የጸና ይሆናል፡፡
2. የሥነ-ሥርዓት ደንቡ ለሁሉም በኢትዮጵያ ውስጥ በፌደራልም ሆነ
በክልልደረጃ ለሚንቀሳቀሱ የኢትዮጵያ፣የኢትዮጵያ ነዋሪዎች እና የውጭ በጎ
አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት ፊርማ ክፍት ይሆናል፡፡
አንቀጽ 44፡ የመጨረሻ ሕጋዊ ዕውቅና ያለው ቅጂ
የዚህ የሥነምግባር ደንብ የአማርኛ ቅጂ የመጨረሻው ሕጋዊ ዕውቅና
ያለውይሆናል፡፡

34

You might also like