Professional Documents
Culture Documents
መሪ ዕቅድ አቅጣጫዎች
ጥቅምት/2013 ዓ.ም
አዲስ አበባ
1
ማውጫ ገጽ
1 መግቢያ 3
2 ዓላማ 4
6 ስትራቴጂያዊ ግቦች 7
10 የሪፖርት ስርአት 11
12 ማጠቃለያ 14
1. መግቢያ
የፌደራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ሁለተኛውን ሀገራዊ የእድገትና የትራንስፎሜሽን ዕቅድ ለማሳከት የአምስት
ዓመት ስትራቴጂያዊ እቅድ አቅዶ ተግባራዊ ሲያደርግ መቆየቱ ይታወቃል፡፡
ባለፉት አምስት ዓመታት በተከናወኑ ተግባራት ተስፋ ሰጪ ስኬቶች ተመዝግበዋል፤ ተግዳሮቶችም አጋጥመዋል፡፡
ከተመዘገቡት ስኬቶች መካከል ህብረተሰቡ በፀረ-ሙስና ትግል ተሳታፊ እንዲሆን ለማድረግ የተለያዩ
አደረጃጀቶችን ለመፍጠር መሞከሩ፣ በመንግስት ተቋማትና የልማት ድርጅቶች ውስጥ ለሙስናና ብልሹ
አሠራር የሚያጋልጡ አሠራሮችን በመፈተሽ ምክረ-ሃሳቦችን ለመስጠት ጥረት መደረጉ፣ ሀገር አቀፍ የህፃናትና
ወጣቶች ሥነ-ምግባር ግንባታ ስትራቴጂ መቀረጹና በተወሰነ መልኩም ቢሆን ከዚህ ጋር በተያያዘ ለወጣቶች
2
የሥነምግባር ትምህርት የሚያግዙ ተግባራት መከናወናቸው፣ የሀብትና ንብረት ምዝገባና ማሳወቅ ተግባራት
መከናወኑ በዋናነት ይጠቀሳሉ፡፡
ኮሚሽኑ ከገጠሙት ተግዳሮቶች ውስጥ ደግሞ በፌዴራልና በክልል የፀረ-ሙስና ኮሚሽኖች መካከል የነበረው
ግንኙነት ለአንድ ዓላማ በጋራ የመሥራት ሳይሆን በተናጠል የሚደረግ፣ በመደጋገፍ፣ አቅም በመገንባትና
በተደራጀ መልክ መረጃ በመለዋወጥ ላይ የተመሠረተ አለመሆን፣ በፀረ-ሙስና ትግል ቀጥተኛ ሚና ያላቸውንና
ተጽዕኗቸው ከፍተኛ የሆነ ባለድርሻ አካላትን በተለይም የሲቪክ ማህበራትን በትክክል ለይቶና ትኩረት ሰጥቶ
አለመሥራት፣ በቅንጅት አለመስራት፣ በመልካም ሥነምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ሥራ ላይ የሚዲያ
ተቋማትን አቅም አሟጦ አለመጠቀምና ሚናቸውን እንዲወጡ አለማድረግ፣ በተቋማት የተቀናጀ የሙስና
መከላከል ስትራቴጂ ትግበራ ውስንነት ያለበት መሆኑ እንዲሁም የሀብት ማሳወቅና ምዝገባ ህጉ በሚፈቅደው
ሥርዓት መሠረት ማስመዝገብ የሚገባቸውን በተሟላ መንገድ መመዝገብ አለመቻል፣ የተሟላ መረጃ
አለመያዝ፣ ያላስመዘገቡትን ተጠያቂ አለማድረግ፣ በመንግስት ተቋማትና የልማት ድርጅቶች ውስጥ
ለሙስናና ብልሹ አሠራር የሚያጋልጡ አሠራሮችን በመፈተሽ የተሰጣቸውን ምክረ-ሀሳብ ተግባራዊ
የማያደርጉትን፣ ግልፅነትን ከማስፈን ተጠያቂነትን ከማረጋገጥ አንፃር ተቋማትን ተጠያቂ የሚያደርግ የህግ
ማዕቀፍ ክፍተቶች መኖራቸው እንዲሁም በተቋማት ዉስጥ የተደራጁ የሥነምግባር መከታተያ ክፍሎች ሚና
ዉስን መሆን ካጋጠሙ ችግሮች መካከል ግንባር ቀደሞቹ ነበሩ፡፡
እነዚህንና ሌሎች ዝርዝር ጉዳዮችን ግምት ውስጥ በማስገባት ውስጣዊና ውጫዊ ዳሰሳ በማካሄድ እንዲሁም የሀገሪቱን ረቂቅ
መሪ እቅድ መነሻ በማድረግ ኮሚሽኑ ሃገር አቀፍ የሥነምግባር ግንባታና የሙስና መከላከያ መሪ እቅድ ያዘጋጀ ሲሆን ይህን
መሰረት ባደረገ መልኩ የሥነምግባር መከታተያ ክፍሎች የቀጣይ አመት እንቅስቃሴን የሚያመላክት መሪ ዕቅድ አዘጋጅቷል፡፡
የሥነምግባር መከታተያ ክፍሎችም ይህን መሪ ዕቅድ መነሻ በማድረግና ከራሳቸው ነባራዊ ሁኔታ ጋር
አጣጥመው የራሳቸውን ስትራቴጂያዊ ዕቅድ እንዲያቅዱ ይጠበቃል፡፡
መሠረታዊ የዕቅድ አቅጣጫው ሀገራዊ ራዕይን፣ የኮሚሽኑን ተልዕኮ፣ ራዕይን፣ እሴቶችን፣ ስትራቴጂያዊ
የትኩረት መስኮችንና ግቦችን እንዲሁም በስትራቴጂያዊ ግቦች ሥር የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትን ያካተተ
ነው፡፡
2. ዓላማ
ተቋማት የራሳቸውን ነባራዊ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ ዕቅዳቸውን በመከለስ ተቋማዊ የተቀናጀ የሙስና
መከላከል ስትራቴጂ ዕቅድ እና የ 2013 በጀት ዓመት ዕቅዳቸውን እንዲያዘጋጁ ለማድረግ፣
በተለያዩ ተቋማት የሚደረገውን የተናጠል የሥነምግባርና የፀረ-ሙስና ትግል ከማቀናጀት በተጨማሪ የሚዘጋጁ
ዕቅዶች ከኮሚሽኑ ዕቅድ ጋር ተቀራራቢ ይዘት እንዲኖረው ለማድረግ ነው፡፡
3
3. በሥነምግባር መከታተያ ክፍሎች የሚታዩ ዋናዋና ችግሮች
የፌዴራል የሥነምግባር እና የፀረ-ሙስና ኮሚሽን ለሁለተኛ ጊዜ ባዘጋጀው የአሥር ዓመት (2013-2022 ዓ.ም)
የሀገር አቀፍ የሥነምግባር ግንባታና ሙስና መከላከል ስትራቴጂያዊ መሪ ዕቅድ መነሻ በማድረግ ለ2013 በጀት ዓመት የሥራ
ዕቅድ የማዘጋጀትና ዕቅዱንም መተግበር በሚያስችል መልኩ እራሱን በአዲስ መልክ አደራጅቷል፡፡
በኮሚሽኑ የተዘጋጀን ይህን ዕቅድ ተግባራዊ ከማድረግ አንፃር ደግሞ በተለያዩ ተቋማት የሚገኙ የሥነምግባር
መከታተያ ክፍሎች የማይተካ ሚና አላቸው፡፡ የሥነምግባር መከታተያ ክፍሎችን አቅም ሙሉ ለሙሉ አሟጦ
ለመጠቀም ደግሞ በቅድሚያ ለሥራቸው እንቅፋት የሆኑ አሠራሮች በመለየት ሊቀረፉ ይገባል፡፡ በሥነምግባር
መከታተያ ክፍሎች ለሥራቸው እንቅፋት እንደሆኑ በተደጋጋሚ የሚነሱ ዋና ዋና ችግሮችን ለመለየት አጠር
ያለ ዳሰሳዊ ጥናት ከማድረግ በተጨማሪ በኮሚሽኑ በተለያየ ጊዜ በተዘጋጁ የውይይት መድረኮች የተነሱ
ሃሳቦችን በማጠቃለል እንደሚከተለው ቀርቧል፤
ከሥነምግባር መከታተያ ክፍሎች ተጠሪነት ጋር በተያያዘ ወጥ አሠራ አለመኖር፣
በተቋም ውስጥ ሊፈጸም የሚችል ሙስናን የመከታተል ኃላፊነት የሥነምግባር መከታተያ ክፍል ብቻ አድርጎ
ማየት፣
በአንዳንድ ተቋማት የሥነምግባር መከታተያ ክፍልን የማኔጅመንት ኮሚቴ አባል እንዲሆን አለማድረግ፣
1. የህብረተሰብ ዕይታ
5
1.1. የህብረተሰብና የባለድርሻ አካላት ዕርካታ ማሳደግ
2. የበጀት ዕይታ
7
በዪኒቨርስቲዎች ውስጥ የሥነምግባርና የፀረ ሙስና ክበባት እንዲደራጁና እንዲሟሉ በማድረግ ወደ
ሥራ ማስገባት፣
ለዩንቨርስቲ ተማሪዎች የሥነምግባርና ፀረ ሙስና ክበባት የአደረጃጀትና የአሠራር መመሪያና ማኑዋል
ማዘጋጀት፣
የተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ የሥነምግባር መከታተያ ክፍሎች፣ ተቋማትና ዩኒቨርስቲዎች በመመሪያው
መሠረት መለየትና ዕውቅና እንዲሰጥ ማድረግ
ክትትልና ድጋፍ ለሚደረግላቸው በሁሉም ተቋማት ውስጥ ያሉ የሥነምግባር መከታተያ ክፍል ፈፃሚ
ባለሙያዎች ሥልጠና እንዲያገኙ ማድረግ፣
የተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ የሥነምግባር መከታተያ ክፍሎች፣ ተቋማት በመመሪያው መሠረት ሲለዩና
ዕውቅና እንዲሰጥ ሲደረግ የክትትልና ድጋፍ በማድረግ የተቋማት መረጃ መያዝ፤
8. የኮሚሽኑን ግብና ዋና ዋና ተግባራትን መሠረት በማድረግ የሥነምግባር መከታተያ ክፍሎች ቀጣይ የዕቅድ
አቅጣጫዎች
በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በጸደቀ የሰው ኃይል አደረጃጀት መሠረት የክፍሉ የሰው ኃይል እንዲሟላ
ለሚመለከተው አካል ጥያቄ ማቅረብ መከታተልና ማስተግበር፣
በሁሉም ተቋማት ውስጥ ተቋማዊ የተቀናጀ የሙስና መከላከል ስትራቴጂ ተግባራዊ እንዲሆን
ማድረግ፣
በኮሚሽኑ የተዘጋጀን የመነሻ መሪ ዕቅድ መሠረት በማድረግ በሁሉም ተቋማት የሚገኙ የሥነምግባር
መከታተያ ክፍሎች የራሳቸውን ዕቅድ ያዘጋጃሉ ወይም ይከልሳሉ፣
ለሥነምግባር መከታተያ ክፍል የተሰጠን ተግባርና ኃላፊነት በአግባቡ ለመወጣት የሚያስፈልግ ተግባር
ተኮር የአቅም ማጎልበቻ የሥልጠና ፍላጎትን በወቅቱ ለኮሚሽኑ ማሳወቅ፣
በኮሚሽኑ በሚዘጋጅ ተግባር ተኮር የአቅም ማጎልበቻ ስልጠና የሚመለከተው ባለሙያ እንዲሳተፍ
ማድረግ እና ስልጠናው በባለሙያው ላይ ያመጣውን ለውጥ በተቋሙ የአፈፃፀም ሪፖርት ውስጥ
በማካተት ለኮሚሽኑ ማሳወቅ፣
በሥነምግባር እና በሙስና መከላከል ስትራቴጂዎች ላይ ለተቋሞቻቸው አመራርና ሠራተኞች
ሥልጠና መስጠት፣
ለተቋማት አመራርና ሠራተኞች በሥነምግባር ደንብ ወይም ኮድ ላይ ግንዛቤ ማስጨበጥ፣
ተግባራዊነቱን መከታተል፣
ለሙስና እና ብልሹ አሠራር ተጋላጭ የሆኑ አሠራሮችን በመለየት ጥናት ማካሄድ እና በጥናት የተለዩ
የአሠራር ክፍተቶችን ለመቅረፍ የሚሰጡ የመፍትሄ ሃሳቦች ተግባራዊ እንዲሆኑ ማድረግ፣
8
የመጀመሪያ ምዝገባ፣ የእድሳት ምዝገባና የአገልግሎት ማቋረጥ ምዝገባ የሚመለከታቸው የተቋሙ
ሠራተኞች ምን ያህል እንደሆኑ በመለየት ለኮሚሽኑ ማሳወቅ፣
ሁሉንም የተቋሙን አመራርና ሠራተኞች ሀብትና ንብረት መመዝገብ፣ ከተመዘገቡ ሁለት ዓመት
የሞላቸውን ሀብት አስመዝጋቢ ሠራተኞች እንዲያሳድሱ ማድረግ እንዲሁም የአገልግሎት ማቋረጥ
ምዝገባ ማካሄድ፤
ለፌደራል ሥነምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ወርሀዊ የአፈፃፀም ሪፖርት ወር በገባ እስከ ሦስተኛ ቀን
ድረስ በጽሁፍ ተዘጋጅቶና በተቋሙ የበላይ አመራር ተፈርሞ እንዲቀርብ ማድረግ፣
በወራዊ አፈፃፀም ሪፖርቶች ላይ በኮሚሽኑ የሚሰጥ ግብረ መልስን መሠረት በማድረግ ቀጣይ
አሠራሮች እንዲስተካከሉ ማድረግና የተከናወኑ ሥራዎችን የሚያሳዩ መረጃዎችን በአግባቡ አደራጅቶ
መያዝ፣
በኮሚሽኑ በየ 6 ወር በሚዘጋጅ የሥነምግባር መከታተያ ክፍሎች የተሞክሮና ልምድ ልውውጥ
የምክክር መድረክ በንቃት መሳተፍ እንዲሁም ለሌሎች ተቋማት በተሞክሮነት ሊተላለፉ የሚችሉ
አሠራሮችን በአግባቡ ቀምሮ መያዝ፣
በኮሚሽኑ የተዘጋጀን የተማሪዎች የሥነምግባርና ፀረ ሙስና ክበባት የአደረጃጀትና የአሠራር መመሪያ
መሠረት በማድረግ በዪኒቨርስቲዎች ውስጥ የተማሪዎች የሥነምግባርና የፀረ ሙስና ክበባት
እንዲደራጁና እንዲሟሉ በማድረግ ወደ ሥራ ማስገባት፣ (ከዩኒቨርሲቲ የመጡ የሥነምግባር
መከታተያ ክፍሎችን ብቻ የሚመለከት ይሆናል)፣
ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀንን ምክንያት በማድረግ በተቋሙ ውስጥ የተለያዩ የመልካም ሥነ ምግባር
አስፈላጊነትን እና የሙስና አስከፊነትን የሚያስገነዝቡ መርሀ ግብሮችን ማዘጋጀትና ማካሄድ፡፡
ሙስና በመከላከልና መልካም ሥነምግባር በማስረጽ የተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ አካላትን እዉቅና
እንዲያገኙ ማድረግ
በእለት ከለት ሥራዎች ለሚቀርቡ የድጋፍ ጥያቄዎች አመቺ በሆነ አግባብ የማማከርና
የመደገፍ ሠራ በተቀናጀ መልኩ ማከናወን
ወርሃዊ የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት የማሰባሰብና የጽሁፍ ግብረመልስ ሥርአት ይኖራል
በአካል ጉብኝት በማድረግ የተገኙ ተሞክሮዎች ለሌሎች ማስተላለፍ፣
9
በጋራ መድረክ በተቀመጠው ቀጣይ አቅጣጫ መሰረት ተግባራዊ ስለመሆኑ ክትትልና
ድጋፍ ይደረጋል፣
በተቀናጀ የሙስና መከላከል ስትራቴጂና/ሥነምግባር ግንባታ ሥራ ላይ የመፈጸም አቅም
ማጎልበቻ ሥልጠና መስጠት፣
በሙስና መከላከል ስትራቴጂዎች ላይ የአቅም ማጎልበቻ ሥልጠና መስጠት፣
የልምድ ልዉዉጥ መድረክ የማመቻቸትና ማስተባበር
1 ኛ ሩብ 2 ኛ ሩብ 3 ኛ ሩብ 4 ኛ ሩብ ምርመራ
ተ ዓመት ዓመት ዓመት ዓመት
መለኪያ
ዒላማ
. የሚከናወኑ ተግባራት
ቁ
10
የክንውን ጊዜ በሩብ ዓመት
1 ኛ ሩብ 2 ኛ ሩብ 3 ኛ ሩብ 4 ኛ ሩብ ምርመራ
ተ ዓመት ዓመት ዓመት ዓመት
መለኪያ
ዒላማ
. የሚከናወኑ ተግባራት
ቁ
11
የክንውን ጊዜ በሩብ ዓመት
1 ኛ ሩብ 2 ኛ ሩብ 3 ኛ ሩብ 4 ኛ ሩብ ምርመራ
ተ ዓመት ዓመት ዓመት ዓመት
መለኪያ
ዒላማ
. የሚከናወኑ ተግባራት
ቁ
12. ማጠቃለያ
ኮሚሽኑ ለ2013 በጀት ዓመት የሥራ ዕቅድ የማዘጋጀትና ዕቅዱንም መተግበር በሚያስችል መልኩ እራሱን
በአዲስ መልክ አደራጅቷል፡፡ ይህን ዕቅድ ተግባራዊ ከማድረግ አንፃር የሥነምግባር መከታተያ ክፍሎች
ያላቸውን አቅም ሙሉ ለሙሉ አሟጦ መጠቀም የማይተካ ሚና ይኖረዋል፡፡ ስለሆነም በተለያዩ ተቋማት
የሚገኙ የሥነምግባር መከታተያ ክፍሎች በኮሚሽኑ ከተዘጋጀው መሪ ዕቅድ ጋር የተናበበ የራሳቸውን
ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበ ዕቅድ እንዲያዘጋጁ ይህ መሪ ዕቅድ ተዘጋጅቷል፡፡
አባሪ
የዕቅድና የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ቅጽ
ቅጽ- 1
የሚከናወኑ ተግባራት ዕቅድ ማቅረቢያ ቅጽ
ዕቅዱ የሚሸፍነዉ ጊዜ ከ--------------------- እስከ--------------------
የክንውን ጊዜ በሩብ ዓመት
ተቋማዊ የተቀናጀ 1 ኛ ሩብ 2 ኛ ሩብ 3 ኛ ሩብ 4 ኛ ሩብ ምርመራ
ተ ዓመት ዓመት ዓመት ዓመት
መለኪያ
የሙስና መከላከል
ዒላማ
ቁ
ተግባራት
12
ዕቅዱን ያዘጋጀው የሥነምግባር መከታተያ ክፍል ዳይሬክተር / ባለሙያ
ስም-------------------
ፊርማ--------------
ቀን--------------
ቅጽ -2
የሥነምግባር መከታተያ ክፍሎች ወርሃዊ የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ማቅረቢያ ቅጽ
ሪፖርቱ የሚሸፍነዉ ጊዜ ከ--------------------- እስከ--------------------
የአፈፃፀም ሪፖርት
ተቋማዊ የተቀናጀ
የሙስና መከላከል
ተ.ቁ ያጋጠመ
ስትራቴጂ ዕቅድ
ዋና ዋና / ዝርዝር ችግርና
ተግባራት መለኪያ ዒላማ ክንውን ንጽጽር
ተግባራት የተወሰደ
መፍትሄ
13