You are on page 1of 61

በአብክመ ከተማ ልማት ቤቶችና ኮንስትራክሽን ቢሮ

የሕበረተሰብ ተሳትፎ ለመሰረተ -ልማት ስራችን

ግንቦት/2013
ደብረ ታቦር
መግቢያ

 በልማትና መልካም አስተዳደር ስራዎቻችን ሁሉ


የህብረተሰብ ተሳትፎን ማረጋገጥ የህዝቡን ፍላጎት
ለመረዳት ከማገዙም ባሻገር መልካም አስተዳደርንና
የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታን ከግብ ለማድረስ ጉልህ ሚና
ይጫወታል፡፡
በከተሞቻችን መንግስት ከዘረጋው ያልተማከለ አስተዳደር
ስርዓት አንጻር የህዝብ ተሳትፎ ያለበት ደረጃ መሻሻል
የሚታይበት ቢሆንም ስራዎቻችንን በህዝብ ተሳትፎ
በመታገዝ ለማስፈጸም ከተቀመጠው አቅጣጫ አንጻር
ሲታይ አሁንም ገና ብዙ ችግሮች ይስተዋላሉ፡፡
የቀጠለ---------
 በከተሞች የሚገኙ ወጣቶች፣ ሴቶች፣ ባለሃብቶች፣
የመንግስት ስራተኞችንና ሌሎች የህብረተሰብ
ክፍሎችን በማስተባበር ማሳተፍ ይገባል
 የህብረተሰብ ተሳትፎ በማህበረሰቡ ዘንድ መቀራረብንና
መተሳሰብን ለማምጣት፣ ለጋራ ጉዳይ በጋራ መቆም
የሚያስችል ሁኔታ በመፍጠር የጋራ ችግርን በቅንጅት
ለመፍታትና የመንግስትና የህዝብ አደረጃጀቶች
በአጋርነት ተቀናጅተው መስራት ይገባቸዋል፡፡
የቀጠለ-------
 ህዝቡ ከልማቱ ተጠቃሚነቱን በቀጥታ ማረጋገጥ
እንዲችልና ልማቱን በባለቤትነት በሚገባ ተገንዝቦ
ራሱን የሚመራበትን እና የሚደግፍበትን ሁኔታ
ለመፍጠር ይችል ዘንድ ይህ የግንዛቤ ማስጨበጫ
ሰነድ ተዘጋጅቷል፡፡
ሰነዱም በህዝብ ተሳትፎ ስራዎች ፋይዳዎች፣ ስልቶችና
የተገኙ ልምዶች ላይ ያተኮረ ሆኖ ተዘጋጅቱዋል፡፡
2. የህብረተሰብ ተሳትፎ ምንነት
 

የህብረተሰብ ተሳትፎ ማለት የመንግስት አካላትና


ህብረተሰቡ በአጋርነት ተቀናጅተው ፖሊሲና ፕሮግራሞችን
የሚነድፉበትና የሚተገብሩበት ሂደት ሲሆን
 በዚህ ሂደት ህብረተሰቡ ከማማከር አልፎ በልማትና
መልካም አስተዳደር ጉዳዮች ላይ ውሳኔ እንዲሰጥና
የበኩሉን ኃላፊነት እንዲ ወጣ የሚያስችል ሂደት ነው፡፡
የተባበሩት መንግስታት በአካባቢ ልማት ጉዳዮች ዙሪያ
በሬዮዴጂኔሪዮ እ.ኤ.አ በ1992 ባካሄደው ውይይት ላይ
በቀረበ ሰነድ እንደ ተመላከተው

 
 የህዝብ ተሳትፎ ቀጣይነት ባለው ሀገራዊ የልማት
ስትራቴጂ ስኬታማነት ላይ እንደ ወሳኝ ቅድመ ሁኔታ
የሚወሰድ መሆኑን ይገልጻል፡፡

 የህዝብተሳትፎን የማረጋገጥ አጀንዳ ሁሉም


የሕብረተሰብ ክፍል በሁሉም አገራዊ ጉዳዮች ላይ
በዕቅድ ዝግጅት፣በትግበራና በአፈፃፀም ግምገማ
በሚኖሩ ሂደቶች ላይ በንቃትና በፍቃደኝነት
እንዲሳተፉ የተመቻቸ ሁኔታ የመፍጠር ጉዳይ ነው
3.የህብረተሰብ ተሳትፎ ጠቀሜታዎች

 ዜጎች የጋራ ፍላጎታቸውን መሠረት አድርገው


በሚፈጥሯቸው አደረጃጀቶች አማካኝነት
በአካባቢያቸው በሚከናወኑ የልማት ሥራዎች ላይ ጉልህ
አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ የሚያስችል ነው፡፡
 ሕብረተሰቡ የተሟላ ግንዛቤ ይዞ ልማቱን በባለቤትነት
የመደገፍ ፣ የመጠበቅና ቀጣይነት እንዲኖረው የማድረግ
ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል፡፡
 ዜጎቹን በልማት እና መልካም አስተዳደር ስራዎች ላይ
በማሳተፍ ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ
 የህብረተሰብ የነቃ ተሳትፎ ለዘላቂ ልማት መረጋገጥ እንደ
ቁልፍ ቅድመ ሁኔታ የሚታይ ሲሆን ዜጎች የጋራ
ፍላጎታቸውን መሠረት አድርገው በሚፈጥሯቸው
አደረጃጀቶች አማካኝነት በአካባቢያቸው በሚከናወኑ
የልማት ሥራዎች ላይ ጉልህ አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ
የሚያስችል ነው፡፡
 የዜጎች የተደራጀ ተሳትፎ መረጋገጥ በርካታ ጠቀሜታዎች
ያሉት ሲሆን ሕብረተሰቡ የተሟላ ግንዛቤ ይዞ ልማቱን
በባለቤትነት የመደገፍ፣ የመጠበቅና ቀጣይነት እንዲኖረው
የማድረግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል፡፡
በልማትና በዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታው ሂደት
ላይ ህብረተሰቡ በባለቤትነት ስሜትና በሙሉ አቅሙ
እንዲሳተፍ ያግዛል፣
ህብረተሰቡ ባለው እውቀት፣ጉልበት እና ሀብት
አስተዋጽኦ ስለሚያደርግ የልማት ስራዎች ወጪ
ቆጣቢ በሆነ መልኩ እንዲከናወኑ እድል ይፈጥራል፣
የሚሰሩት የልማት ስራዎች ከህብረተሰቡ ባህል እና
እሴት ጋር የተናበቡና የተጣጣሙ እንዲሆኑ ያስችላል፣
የሁሉንምተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ስለሚያስችል
ልማት እየተስፋፋ እንዲሄድ ያግዛል፣
የልማት ስራዎች አፈፃፀም ውጤታማ እንዲሆንና
ዘላቂነት እንዲኖራቸውም ያደርጋል፡፡
4.የህብረተሰብ ሀብት ምንነት

የህብረተሰብ ሀበት (Community Asset) ምንድን ነው

አንድ ማህበረሰብ ከነበረበት ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ አኗኗር ወደተሻለ


ደረጃ እንዲሸጋገር በቀጥታም ሆነ በተዛዋዋሪ የሚደግፍ ማንኛውም ቁሳዊም ሆነ
ሰዋዊ ሀብት ነው፡፡
የሚከተሉትን ለአብነት መጥቀስ ይቻላል
የቀጠለ…
የማህበረሰብ አባላት ወይም ግለሰቦች፡-

ግለሰቦች በእውቀት፣ በጉልበት፣ በገንዘብና በመሳሰሉት


መንገዶች የሚያደርጉት አስተዋጽኦ ለማህበረሰብና
ለከተማ ልማት ሽግግር መተኪያ የሌለው ሀበት መሆኑ
ይገለጻል፡፡
ቦታዎች፡-

የሀይማት ተቋማት፣ ትምህርት ቤቶች፣


የመዝናኛ ቦታዎች፣ የቱሪስት መስህብ የሆኑ
ቦታዎች፣ ቤተመጻህፍትና ሌሎች መሰል ተቋማት
የማህበረሰብ ልዩ ሀብቶች ናቸው፡፡  
 
አገልግሎት ሰጪ ተቋማት፡-

ማንኛውም በመንግስት፣ በግለሰቦችም ሆነ በሌሎች


ድርጅቶት የተገነቡ የትራንስፖርት፣ የሆቴል፣
የመዝናኛና ሌሎች ተቋማትን አገልግሎት ሰጪ
ተቋማት እንላቸዋለን፡፡
እነዚህ ተቋማት በስራ እድል፣ በእውቀት ሽግግር፣ አካባቢን
በመጠበቅና መሰረተ ልማቶችን በመገንባት ባላቸው
አስተዋጽኦ የህዝብ ሀብት ተብለው ተቀምጠዋል፡፡
የቀጠለ…
ማንኛውም በገንዘብ፣ በእውቀትና በጉልበት የሚተመን ቁስ
ወይም አገልግሎት፡-

አንድ ህብረተሰብ የሚኖርበትን አካባቢ ያመቻቸው መልካም


አጋጣሚ በራሱ ወደ ሙሉ ሀብትነት ሊቀየር አይችልም፡፡ የግድ
የማህበረሰቡ እውቀት፣ ገንዘብና ጉልበት ሊታከልበት ዘንድ
ያስፈልጋል፡፡
5.የህብረሰብ ሀብት አሰባሰብ ጽንሰ ሀሳብ
 የህብረተሰብ ሀብት አሰባሰብ ስራ ጽንሰ ሀሳብ
የህብረተሰብንና የአከባቢን ጥንካሬ ከማየት የጀመረ ነው
 የህብረተሰብን ሀብት ለማሰባሰብ ሲጀመር አንድ ህበረተሰብና
አካባቢው የነዋሪዎቹን ፍላጎት ማርካት የሚችል ሀብትና
ሪሶርስ ባለቤት መሆኑን ከማመን ይጀምራል
 በውጫዊ አካል እርዳታና ጣልቃ ገብነት ውስጣዊ ፍላጎቶችን
ለማሟላት ሲደረግ የነበረው አቀራረብ የህዝብን ችግር
የሚፈታ ሆኖ አልተገኘምና
 ሀገራችን የበርካታ ተፈጥሮአዊና ሰው ሰራሽ ሀብት ባለቤት
በመሆንዋ በውስጣዊ አቅም ማህበረሰባዊ አገልግሎቶችን
ማስፋፋት ተገቢ ይሆናል፡፡
በአንድ ማህበረሰብ ውስጥ የሚገኘውን በገንዘብ፣
በእውቀት፣ በጉልበትና ሌላም በዋጋ የሚተመን ሀብት
ካለበት ቦታ ወይም ከሚሰጠው አካል የተለያዩ
ስልቶችን በመጠቀም በማሰባሰብ በተደራጀ መልኩ
ቀደም ተብሎ ለታለመለት ዓላማ እንዲውል
የሚደረግበት ሂደት ነው፡፡
በሀብት አሰባሰብ ሂደት ሀብት፣ ሀብት ሰጪ፣ ሀብት
የሚሰበስብና በሀብቱ የሚከናወኑ ተግባራት በግልጽ
ተለይተው ሲቀመጡ የሀብት አሰባሰብ ሂደት
ውጤታማ እንደሚሆን ይገለጻል፡፡
6.የህብረተሰብ ተሳትፎን በማረጋገጥ ሂደት የሚታዩ ዋና ዋና
ተግዳሮቶች፡-

6.1.በየደረጃው ህዝቡን የሚያሳትፍ ግልጽ አሰራር


አለመዘርጋ
ህዝብ በየደረጃው በሚከናወኑ የልማትና የመልካም አስተዳደር
ሥራዎች ላይ በቀጥታ ወይም በወኪሎቹ አማካኝነት እንዲሳተፍ
የሚያስችል ግልጽ አሰራር አለመዘርጋትና አሰራሩ ቢኖርም
በህብረተሰቡ በቂ ግንዛቤ ያልተያዘበት መሆን የህብረተሰብ
ተሳትፎን በማረጋገጥ ሂደት የሚታይ አንዱ ችግር ነው፡፡
6.2.የተደራጀና ሥራውን ለመሸከም የሚችል ተቋም አለመኖር፡-
የህብረተሰብ ተሳትፎን የማረጋገጥ ጉዳይ እንደ ዋነኛ ሥራ
ወስዶ ስራውን በሚገባ ለመምራት የሚችል የተደራጀ ተቋም
መፍጠርና በተሟላ የሰው ኃይል ማደራጀት ካልተቻለ
ህብረተሰቡን በበቂ ሁኔታ ለማንቀሳቀስ ስለሚያዳግት የልማትና
መልካም አስተዳደር ሥራዎች ውጤታማነት ላይ ተጽዕኖ
ከመፍጠሩም ባሻገር የህብረተሰቡን ቀጥተኛ ተጠቃሚነትና
የልማት ባለቤትነት በተጨባጭ ለማረጋገጥ አያስችልም
6.3. የማስፈጸም አቅም ደካማ መሆን፡-
የማስፈጸም አቅም ደካማ መሆን በየደረጃው የታቀዱ
የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን ወደ
ሕብረተሰቡ በማውረድ በአግባቡ ግንዛቤ ለማስያዝና
መተማመን ለመፍጠር ስለማያስችል የህብረተሰብ የነቃ
ተሳትፎ በማረጋገጥ በኩል መሰናክል መሆኑ አይቀርም
6.4.የፍቃደኝነትና የተነሳሽነት መጓደል

የመንግስት ተቋማት ለሕዝቡ ተገቢውን አገልግሎት ለመስጠት


በሚደርጉት ጥረት በየደረጃው ያሉ ህዝባዊ አደረጃጀቶች እና
የህብረተሰብ ተወካዮች ከዕቅድ ዝግጅት ጀምሮ በሚኖሩ
ሁሉም ሂደቶች ላይ በንቃት በመሳተፍ የሚጠበቅባቸውን
ሚና ሊጫወቱ ይገባል፡፡
6.5. የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከት መኖር፡-

የህብረተሰብን ተሳትፎ በማረጋገጥ ሒደት


የሚያጋጥመው ሌላው ተግዳሮት የግል ጥቅምና
ፍላጎትን መሰረት ያደረገ ተሳትፎ የማድረግ ዝንባሌ
እና የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከት ነው፡:
7. የህብረተሰብ ተሳትፎ መገለጫ ደረጃዎችና ስልቶች፡-
የህብረተሰብ ተሳትፎ ደረጃዎች
የህብረተሰብ ተሳትፎ አይነቶች በርካታ ሲሆኑ በዋናነት በአምስት
ደረጃዎች ሊገለጹ ይችላሉ፡፡
ሀ/ በመረጃ ልውውጥ (Informative)፡-
የመረጃ ልውውጥ ማድረግ የህብረተሰብ ተሳትፎ አንዱ መገለጫ ሲሆን
ለሌሎች የተሳትፎ አይነቶች እንደመንደርደሪያ የሚወሰድ ነው
ለ/ሀሳብ/ ምክር መስጠት /Consultation/፡-
በየአካባቢው የሚሰሩ የልማት ስራዎች ላይ አስተያየት፣ሃሳብ፣ትችትእና
አማራጮችን የማቅረብ ዕድልን ስለሚሰጠው ከመረጃ ልውውጡ በዘለለ
ሀሳቡን የመስጠትና ምክር የመለገስ ተግባራትን የሚያካትት ተሳትፎ
እንዲኖረው ያስችላል፡፡
ሐ/ማካተት/Involvement/፡-
ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ፍላጐታቸውን በአግባቡ ባካተተ
እና ጥቅማቸው በጠበቀ ሁኔታ የልማት ስራዎች መሰራታቸውን
የሚያረጋግጡበት የተሳትፎ ሁኔታነው፡፡
መ/በትብብር መሥራት /Collaborative/፡-
ህብረተሰቡ ዋነኛው የሥራው ባለቤት ሆኖ ከዕቅድ ዝግጅት
ጀምሮ እስከ ትግበራ ድረስ ባሉሂደቶች እንዲሳተፍ የሚያደርግ
የተሳትፎ ደረጃ ሲሆን በየአካባቢው በሚከናወኑ የልማት ስራዎች
ላይ ከሕዝብጋር አጋርነት በመፍጠር በጋራ ለመስራት የሚያስችል
ዕድልን ይፈጥራል፡፡
8. የህብረተሰብ ተሳትፎ ስልቶች
ሀ/ ህብረተሰብን ለማሳወቅ የምንጠቀመው ስልት
/Techniques to inform the public/
በማስታወቂያ/Advertising /
በአጭር ገለፃ / Briefings /
በህዝባዊ በአላት/ Community events/
በመረጃ ዴስክ/Information Desk /
በአውደ ርዕይ / Exihibition/
በመስክ ጉብኝት/Site tour /
በአውደ ጥናት/Panel discussion/
ለ/ ህብረተሰብን ለማማከር የምንጠቀመው ስልት /Public
consultation techniques/
በሻይ ቡና ፕሮግራም/ Coffee ceremonies /
በአስተያየት መስጫ ቅፅ /Comment forms /
በአትኩሮት ቡድን ውይይት/ Focus groups discussion/
በቃለ መጠይቅ/Interview/
በህዝባዊ ስብሰባ/Public meetings/
ሐ/ ህብረተሰቡን በስራዎች ለማሳተፍ የምንጠቀመው
ስልት /Techniques to involve the public/
በክብ ጠረጴዛ በመወያየት /Round tables/
በአውደ ጥናት/ Workshops/
በቴክኒክ ቡድን ውይይት/ Technical team
discussion /
መ/ ህብረተሰቡን በሚሰራው ስራ አጋርለማድረግ
የምንጠቀመው ስልት/ Collaboration techniques/
በአማካሪ ቡድን /Advisory groups/
በጋራ ስምምነት ሰነድ /Consensus-building techniques/
በግብረ ሀይል /Task force/

ረ/ ህብረተሰቡን በሚሰራው ስራ የውሳኔ ሰጭነት ድርሻ እንዲኖረው


ለማድረግ የምንጠቀመው ስልት /Empowering techniques/
በተወካዩ አማካኝነት በሚሰጠው ውሳኔ /Citizen juries/
በአጠቃላይ ምርጫ /Ballots/
9.የህብረተሰብ ተሳትፎ ተሞክሮዎችና የተገኙ
ውጤቶች
9.1 በደብረ ማርቆስ ከተማ 08 ቀበሌ የተወሰደ ተሞክሮ

ምርጥ ተሞክሮው በደ/ማርቆስ ከተማ በቀበሌ 08 በህብረተሰብ ተሳትፎ


የተሰሩ የልማት ስራዎችና የአካባቢ ደህንነት ጥበቃ ስራዎችን የሚያሳይ
ነው፣
 ምርጥ ተሞክሮው በምን አግባብ ተለየ
በዞኑና በከተማ አስተዳደሩ የጋራ መድረክ በማዘጋጀት የአፈጻጸም
ግምገማ ወቅት በህብረተሰብ ተሳትፎ የተሻለ አፈጻጸም ያለው ቀበሌ
ሆኖ በመገኘቱ
ከተማ አስተዳደሩ፣ዞን መምሪያው እንዲሁም ክልሉ
ለመስክ ድጋፍ በወጣባቸው ሰዓት በአካል ስራዎችን
በማየት የተረጋገጡ በመሆኑ የደብረ ማርቆስ ከተማ
የቀበሌ 08 አስተዳደር በህብረተሰብ ተሳትፎ ስራዎች
ማለትም በመሠረተ ልማትና በአካባቢ ጥበቃና
ደህንነት ስራዎች የተሻለ አፈጻጸም የታየበት ቀበሌ
በመሆኑ ነው፡፡
በዝግጅት እና በትግበራ ምእራፍ የተከናወኑ ተግባራት
. በዝግጅት ምእራፍ የተከናወኑ ተግባራት
የጋራ እቅድ የማቀድ
የተለያዩ መድረኮችን በመፍጠር በነዋሪዎች የሚነሱ
የመልካም አስተዳደርና የልማት ጥያቄዎችን የመለየት፣
ከተነሱ የልማትና የመልካም አስ/ጥያቄዎች መካከል
 የጠጠር መንገድ ስራ ፣
 የጎርፍ ማፋሰሻ ቦዮች ግንባታ፣
 የቀበሌ አስተዳደር ጽ/ቤት ግንባታ፣
 የትምህርት ቤት ማስፋፊያ ግንባታ፣
 የመንገድ ከፈታ/ጥርጊያ መንገድ ስራዎች/
 ከአካባቢ ደህንነት አንጻር ህገወጥ የመሳሪያንግድ፣ ተኩስ፣ ዝርፊያ፣
የተደራጀ የቤት ስርቆት የአካባቢው የደህንነት ስጋት የመሳሰሉት
ችግሮች በመነሳት የጋራ እቅድ ማቀድና ለእቅዱ መፈጸም ህብረተሰቡን
ባለቤት የማድረግ ስራ ተሠርቷል፡፡
የመሰረተ ልማት ስራዎችን በአንዴ መስራት ስለማይቻል የሚሰሩበትን
ቦታ እና የሚሰሩትንና ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገባ የመሠረተ ልማት
ስራዎች በጋራ የመለየት ስራዎች ተሰርተዋል፡፡
ፈጻሚን የማዘጋጀት
የተለዩ የልማትና የመልካም አስተዳደር እቅዶችን ለቀበሌው
የማህ/ሰብ ክፍል፣ ለልማት ኮሚቴዎችና ቡድኖች፣ ለቀበሌ
አስተዳደር አመራርና ባለሙያዎች፣ መግባባት ላይ የተደረሰበትን
እቅድ የማስተዋወቅ፣ የሚከናወኑበትን ጊዜ እና
ስራውን ለማከናወን በመንግስት የፋይናንስ አቅም ብቻ ማከናወን
የማይቻል መሆኑንና የቀበሌው ነዋሪ በጥሬ ገንዘብ፣ በቁሳቁስ፣
በጉልበት እንዲሁም በእውቀት አስተዋጽኦ ማድረግ
እንደሚኖርበት በእቅዱ ላይ መግባባት ላይ መድረስ ተችሏል፡፡
ተግባራቱን በተሳካ ሁኔታ ለመፈጸም የሚያስችሉ መደበኛና ኢ-
መደበኛ አደረጃጀቶችን ለመጠቀም ተችሏል፡፡
ማህበረሰቡ በልማት እቅዶች ላይ ውይይት ሲደረግ
በተሞክሮ ቅመራው ወቅት የታዩ አበይት ጉዳዮች
የተለዩ ችግሮች እና የተለዩበት አግባብ፤
በቀበሌው ወንድ 5920 ሴት 6093 በድምሩ 12613 የህብረተሰብ
ክፍሎች በልማት ቡድን የተደራጁ ሲሆን የቀበሌውን የመልካም
አስተዳደር ችግሮች በመለየት የእቅድ አካል ማድረግና
ከህብረተሰቡ ጋር መስማማት የተቻለ ሲሆን ህ/ሰቡ ፈጻሚን
የማዘጋጀት ስራ ተሰርተዋል፡፡
በዚህም የተለዩ የመልካም አስተዳደር/የልማት ችግሮች
 የመሠረተ ልማት ማለትም የመንገድ፣ የዲች/ተፋሰስ/የኮብል
እና የጥርጊያ መንገድ ከፈታ ድልድይ ስራዎች የተም
ግንባታ/ምሳሌ የቀበሌ አስተዳደር ጽ/ቤት የፖሊስ ጣቢያ፣
የትምህርት ቤት ግንባታ ስራዎች ወዘተ
 የአካባቢ ደህንነትና ጥበቃ ችግሮች/ የቤት ስርቆት፣ ዝርፊያ፣
ህገወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር፣ህገወጥ ተኩስ የመሳሰሉት
ችግሮች፣ በመንግስታዊ መዋቅሩና በህ/ሰቡ የተለዩ ችግሮች
ነበሩ
ችግሮችን ለመፍታት የተጠቀሙባቸው ስልቶች፤
የማህበረሰብ ተከታታይ ውይይት በማካሄድ፣
ህብረተሰቡን በልማት ቡድን በማደራጀትና የልማት ኮሚቴ
በመምረጥ፣
ኢ- መደበኛ አደረጃጀቶችን በመጠቀም/እድሮች፣ በአካባቢው ያሉ
የቤት ማህበር አመራሮች/ምሳሌ መስቀልማ ፣ንጹህ አየር ወዘተ/
ችግሮችን እንደ ቅደም ተከተላቸውና እንደሚፈቱበት አግባብ መለየት
መቻላቸው፣
የበጀት ችግር
የወሰን ማስከበር እና ቦታዎችን ከ3ኛ ወገን ነጻ ማድረግ፣/ለካሳ
ከፍተኛ ገንዘብ የሚጠይቅ መሆኑ/
የከተማው ማዋቅራዊ ፕላን / ከሳተላይት ምስል የተወደ በመሆኑ
ስህተቶች እየተፈጠሩ ለቅየሳ መቸገር፣
የመሰረተ ልማት ተቀማት ተግባሮቻቸውን ተቀናጅተው መፈጸም
አለመቻል እና ተናብቦ አለመስራት/ መንገድ፣መብራት ውሃ ስልክ
በፕላን መሰረት አለመዘርጋትና አንዱ ሲሰራ ሌላው ማፍረስ/
በካሳ ክፍያ ላይ አነሰኝ በሚል ስራዎችን ፍ/ቤት በመሄድ
ማዘግየት፣
የባለሙያ እጥረትና፣ የክህሎትና ልምድ ማነስ፣
ተግባሮችን ለመፈጸም ከፍተኛ የሆነ የመንግስት ተቋማት
ፋይናንስ አቅም ውስንነት የመሳሰሉት፣
ለቀበሌ አስተዳደር ጽ/ቤት ግንባታ
የደ/ማርቆስ ዩኒቨርስቲ፣ ዲማ ቴክኖሎጂ ኮሌጅ፣ ዋሸራ
ብሮድቪው ኮሌጅ ህብረ ብሄር ኮሌጅ፣ ጊዮን ቴክኖሎጂ ኮሌጅ
በቀበሌው ስር የሚገኙ 10 እድሮች፣ ከኢትዮጵያ መንገዶች
ባለስልጣን፣ ከቀበሌ አስተዳደሩ ሰራተኞች፣ ከተለያዩ ግለሰቦችና
ማህበራት፡-
ስሚንቶ፣ 41 ቤርጋ ብረት ፣ብሎኬት፣ ፊኖ/00ጠጠር/ ድንጋይ፣
እንጨት/ ለአውራጅ፣ድምድምና ቆርቆሮ፣ ማገር አገልግሎት
የሚውል/ በገንዘብ ሲተመን 115,690 ብር በጥሬ ገንዘብ 741,310
ብር በእውቀት 1,500 ብር በድምሩ 858,500 ብር ባለ13 ክፍል
ቢሮ ሙሉ በሙሉ በህብረተሰቡ አስተዋጽኦ ብቻ ለመስራት
ተችሏል፡፡
ሙሉ በሙሉ በህ/ሰብ ተሳትፎ የተገነባ በቀበሌ አስተዳደር
ጽ/ቤት
የቦይ ተፋሰስ ቁፋሮ ስራ
በተለምዶ ከቄሴ ሱቅ እስከ የኔ ትምህርት ቤት ድረስ ርዝመቱ
500 ሜትር ቆፋሮ በህብረተሰቡ መሰራት መቻሉና ለዚህም
55000 ብር የህብረተሰቡ አስተዋጽኦ ማድረግ መቻሉ፣/ለማሽን
ኪራይ ወጭ የተደረገ/
ከዶ/ር ጥላሁን እስከ ጤናው ቤት ድረስ የተሰራ የቦይ ተፋሰስ
የቆፋሮ ስራ 350 ሜትር በብር 52000 ብር ማስቆፈር መቻሉ፣/
በጉልበት የተቆፈረ/
ከአቶ በላቸው ቤት በአቶ አስናቀ በኩል አልፎ እስከ ተክለሃይማኖት
የተሰራ ዲች ርዝመቱ 250 ሜ በብር 30000 ብር /ለማሽን ኪራይ
ወጭ የተደረገ/
ከወ/ሮ ትበይን አሸንፍ ቤት አድርጎ ጃይካ ትምህርት ቤት ርዝመቱ
528 ሜ በብር 79000
በጠቅላላ የተሰራ የቦይ ተፋሰስ ርዝመት 1.628 ኪ.ሜ መስራት
ተችሏል፡፡ /በህ/ሰብ ተሳትፎና በአለም ባንክ/ ለመስራት ተችሏል፡፡
በህብረተሰብ ተሳትፎ መዋጮ የተቆፈረ የተፋሰስ ስራ
የቀጠለ-------
የጠጠር መንገድ ስራ
 የብራጌ ሀሣሪያ የጠጠር መንገድ ስራ ርዝመቱ 3 ኪ.ሜ በብር 1.5
ሚሊዮን ብር 300 ቢያጆ ጠጠር የፈጀ የጠጠር መንገድ መስራት
ተችሏል፡፡
 ቦሌ ተክለሃይማኖት የውስጥ ለውስጥ መንገድ ሳይት፣ጃይካ ሳይት
ተብሎ የሚከፈል ሲሆን በተክለ ሃይማኖት ሳይት 94 ቢያጆ ጠጠር
በብር 126000፣ በጃይካ ሳይት 121 ቢያጆ ጠጠር በብር 191944
ብር ፣ በጠቅላላ በ2ቱ ሳይቶች 215 ቢያጆ በብር 318244 ብር
 ጠቅላላ ለጠጠር መንገድ 1.9 ሚሊዮን ብር ከህ/ሰቡ ተሰብስቦ
ስራወን ማከናወን ተችሏል፣
ቦሌ ተክለሃይማኖት ሳይት በህ/ሰብ ተሳትፎ የተደፋ የጠጠር መንገድ
1ኪ.ሜ
የተጠናቀቀ ጠጠር መንገድ ስራ
ለብሩህ ተስፋ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ማስፋፊያ ግንባታ
ተህብረተሰቡ አስተዋጽኦ
የብሩህ ተስፋ ትምህርት ቤት ማስፋፊያ ህብረተሰቡ መዋጮ በጥሬ
ገንዘብ 314000 ብር አስተዋጽኦ ማድረግ ተችሏል፡፡
የብሩህ ተስፋ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት በህብረተሰብ መዋጮ ጭምር
የተገነባ
ህብረተሰቡን የመብራት ተጠቃሚ የማድረግ ስራ
በቀበሌ 08 ሙሉ ቦሌ ሳይት የቤት ማህበር አባላት ለ 1586
የህብረተሰብ ክፍል በአካባቢው የቤት ልማት ፕሮግራም ተመርተው
ቤት ሰርተው እኖሩ ሲሆን መብራት ያልገባላቸው በመሆኑ ሙሉ
ውጭውን ማህበራት /የ5 ትራንስፎርመር፣ የጋንች፣ የፖል እና መሠል
ወጭዎችን ሙሉ በሙሉ በራሳቸው በመሸፈን
ለትራንስፎርመር 2471705
ለፖል፣ለገመድ፣ ለጋንችቸና ለመሳሰሉት ወጭዎች 4528295 ብር
በድምሩ 7000000 ብር በመክፈል የመብራት ተጠቃሚ ማድረግ
ተችሏል፡፡
ሙሉ በሙሉ በህብረተሰብ ተሳትፎ የተዘረጋ መብራት
ከአካባቢ ደህንነትና ጥበቃን በተመለከተ
 እድሮች የአካባቢ ጥበቃን የህገ ደንባቸው አንድ አካል አድርገው
እየሰሩ ይገኛሉ፣
 ከጥበቃ ስራ አኳያ በቀበሌ ደረጃ ለ5 ቀጠናዎች በ202 ብድን በ21
በሎኮች በአጠቃላይ 1370 አባላት ተደራጅተው አካባቢያቸውን
እየጠበቁ ይገኛሉ፣
 ሠፈሮች በ1ለ5 በመደራጀት ውይይት በማድረግ ሠፈራቸውን በንቁ
ሁኔታ ይጠበቃሉ፣
 በቀበሌው ተመድበው ላሉ የፖሊስ አባላት ስራቸውን በሚገባ
ያከናወኑ ዘንድ ግብዓት እንዲያሟላ ለማድረግ ከህ/ሰቡ በ2500 ብር
ወጭ የጽህፈት መሳሪያ ገዝተው ማስረከብ ተችሏል፣
የቀጠለ------
 በሃገራችን በስሜት ክፍል በተቃጣብን ጦርነትና የህግ ዘመቻ
203000 ብር ለመከላከያ ለአማራ ልዩ ሃይልና ለአማራ ሚሊሺያ
አስተዋጽኦ አበርክቷል፣
 ለጥበቃ ያመች ዘንድ የአካባቢው ማህበረሰብ የውስጥ ለውስጥ
መንገዶች መብራት በራሱ እንዲያወጣ ተደርጓል፡፡
 በአጠቃላይ ከጸጥታ አንጻር ወንጀለኛ በህብረተሰቡ ዘንድ ተሸሽጎ
እንዳይቀር በማጋለጥ የአካባቢው ሠላም ህብረተሰቡ የኔ ሰላም
ነው በማለት እየጠበቀ ይገኛል፡፡
የተመዘገበ ውጤት
 በጊዜያዊ ለ 151 ወንድ ለ 99 ሴት በድምሩ ለ250 ወጣቶች
የስራ እድል መፍጠር መቻሉ፣
 የአካባቢው ማህበረሰብ ለሚሰራቸው የልማት፣ የአካባቢ
ደህንነትና የጥበቃ ስራዎች የባለቤትነት ስሜት መፍጠር
መቻሉና የተሰሩ የልማት ስራዎችን በባለቤትነት ቁጥጥርና
ጥበቃ ማድረግ ማስቻሉ፣
 ለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ተጋልጠው የቆዩ
የማህበረሰብ ክፍሎች በተለይ ወላጅ እናቶችን ከሠፈር ወደ
ጤና ተቋማት ማድረስና መቻሉ ወላድ ህክምና ቦታ ሳትደርስ
ሰምትሞትበትን መቀነስ አስሏል፣
 ህብረተሰቡ የውስጥ ለውስጥ መንገዶች መብራት
እንዲያወጣ በማድረግና ተደራጅተው ሰፈራቸውን
እንዲጠብቁ በማድረግ ለጸጥታ ሃይሉ አጋዥ በመሆን
ቀደም ሲል ይታዩ የነበሩ ዝርፊያ፣ ህገወጥ መሳሪያ
ዝውውር፣ እና የተለያዩ ወንጀሎች መቀነስ
መቻላቸው፣
 የቀበሌው ጽ/ቤት በህብረተሰብ ተሳትፎ በአጭር ጊዜ
መገንባቱ ህዝብ አገልግሎቱን በአቅራቢያው
እንዲያገኝ አስችሎታል፣
. ከተሞክሮው የሚወሰዱ ትምህርቶች
 ማንኛውም የልማት እቀዶች ሲታቀዱ ከላይ ወደታች ከሚታቀዱ

የህብረተሰቡን የመልካም አስተዳደር ችግር መሠረት ያደረገ እና


ህብረተሰቡ የእቅዱ ባለቤት በማድረግ አሳታፊ እቅድ መታቀድ
ያለበት መሆኑ፣

 አንዱ ቀበሌ ከሌላው ቀበሌ ትምህርት የሚወስድበትና ለቀጣይ

የልማትና መልካም አስተዳደር ስራዎቻችን በቀበሌዎች መካከል


የውድድር መንፈስ የፈጠረ መሆኑ በዚህም ከአሁኑ መልካም
ጅምሮች እየታዩ መሆኑ /ለምሳሌ ባታ ሳይት ከከተማው 30%
ከህብረተሰቡ 70% ለትራንስፎርመር ግዥ፣
 ለፖል፣ለጋንችና መሠል ሙሉ ወጭዎች ክፍያ በድምሩ 12.5

ሚሊዮን ብር ለመብራት ሃይል ክፍያ ተከፍሎ ማህበረሰቡ ወደ


2042 እማወራና አባወራ በመጠባበቅ ላይ ይገኛል፡፡

 ሌሎች ቀበሌዎች ለምሳሌ ቀበሌ 02፣05 እና ቀበሌ 10

ተሞክሮውን ወስደው በህብረተሰብ ተሳትፎ ቢሮ እያስገነቡ


መሆኑን
ማጠቃለያ
ከተሞቻችን ከአካባቢ ልማት ጋር በተያያዘ ያለባቸውን ዘርፈ ብዙ
ችግር ለመፍታት የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ ሕብረተሰብ አቀፍ
የመሰረተ-ልማት ስ ነድፎ መንቀሳቀስ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡
ከዚህ አኳያ እየተደረገ ያለው እንቅስቃሴ ከጊዜ ወደ ጊዜ
እየተሻሻለ የመጣ ቢሆንም ህብረተሰቡ ካለው አቅም አንጻር
ሲታይ አሁንም ውስንነቶች ይስተዋላሉ፡፡
ህብረተሰሰብን የልማት ባለቤት እንዲሆን ማድረግ ደግሞ ከፍተኛ
የፋይናንስ እጥረት ባለባት ሀገራችን ወሳኝነት ይኖረዋል፡፡
በሌላ መልኩ ህብረተሰቡን ማዕከል ያደረገ ተሳትፎ ማድረግ
መልካም አስተዳደርን ለማስፈን፣ የተደራጁ የልማት ስራዎች
መሰረት ለመፍጠር፣ የነዋሪውን ፍላጎት መሰረት ያደረገና
ባለቤት ያለው ልማት እንዲኖር ለማድረግ፣ አሳታፊ እና ችግር
ፈቺ እቅድ አዘጋጅቶ መንቀሳቀስ ተገቢ ይሆናል፡፡
በአጠቃላይ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል በጉልበቱ፣ በገንዘቡና፣
በዕውቀቱ ቀጣይነት ያለውን አስተወጽኦ እንዲያደርግ
በማድረግ ሁሉም በአካባቢው የሚደረጉ የልማት
እንቅስቃሴዎችን በራሱ ተነሳሽነት ከመፈጸም አልፎ እራሱ
እንዲያስተዳድራቸው ስለሚያደርግ የፕሮጀክቶችን ቀጣይነት
የበለጠ የማያረጋግት በመሆኑ የሚመለከታቸዉ የዘርፉ
አመራሮችና ባለድርሻ አካላት ርብርብ ሊያደርጉ ይገባል፡፡፡፡
ለ ሁ
ግ ና
መ ሰ

You might also like