You are on page 1of 10

የመተማ ወረዳ ት //

ጽ ቤት

የለውጥ ሠራዊት ግንባታ እቅድ 2009

መግቢያ

የመተማ ወረዳ ሲ/ሰርቪስ ጽ/ቤት ያለበትን ደረጃ በየጊዜው ለመገምገምና በማስተካከል ስራውን የተሳለጠ
ለማድረግ የመንግስት ተቋማት የዜጎች ቀልጣፋ ውጤታማና ተጠያቂነት ያለበት አገልግሎት መስጠት
ይጠበቅባቸዋል ይህንን እውን ለማድረግ የሲቪል ሰርቪስ ማሻሻያ ኘሮግራሞችና ሌሎችም የለውጥ
ኘሮግራሞች ተቀርፀው ከፌደራል እስከ ቀበሌ ተግባራዊ በመደረጋቸው የተሰጠውን ያህል ባይሆንም
በመንግስት ተቋማት የተሻለ የአገልግሎት አሠጣጥ የበለጠ የተሳለጠና በዜጎች ፈላጎት ላይ የተመሰረተ
ለማድረግ በሁሉም የመንግስት ተቋማት ተግባራዊ እንዲሆን ተደርጓል ፡፡

በቀጣይ ይህን የተጀመረ ለውጥ ዳር ለማድረስ የክልሉ መንግስት ተግባራዊ ለሚደረገው የእድገትና
ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ተቋማት የለውጥ ኘሮግራሞችን እንደዋነኛ ማሳኪያ መሳሪያ አድርገው በመጠቀም
ተግባራዊ ቢያደርጓቸው የመ/ተ/የለ/ኘ/ማስ/ዋና የስራ ሂደት ከምንጊዜውም በተሻለ ሁኔታ ተገቢውን ክትትልና
ድጋፍ ማድረግ ይኖርበታል ፡፡ በቀጣይ ስራ ላይ የሚውሉ ስልቶችን የድጋፍና ክትትል ስርዓቱን እቅድን መሰረት
ያደረገ ተግባር መፈፀሙን የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ በመስራት በለውጥ ኘሮግራሞች ላይ የባለቤትነት ስሜት
መፍጠሩን የለውጥ ኘሮግራሞች በተሻለ ደረጃ የፈፀሙ ተቋማትን ማወዳደርና መሸለም ይኖሩብናል ፡፡
የወረዳዉ ሴክተር መ/ቤቶች የሲ/ሰርቪስ ሰራተኞችን የተመለከተ አዋጆችን፣ ደንቦችና መመሪያዎች
ተግባራዊ በማድረግና አፈፃጸማቸዉን በመከታተል አገልግሎት በመስጠት የወረዳችን የሰዉ ሀያል አስተዳደር
ስርአት ፍትሃዊ ቀልጣፋና ዉጤታማ ማድረግ

የመተማ ወረዳ ት/ጽ/ቤት ራዕይና ተልኣኮ

ተልዕኮ፡- በመንግስት ተቋማት ቀልጣፋና ዉጤታማ አደረጃጀት አሰራርና የሰዉ ሀይል በመገንባት ብልፅግናን
ማረጋገጥና መልካም አስተዳደር ማስፈን የሚያስቸል የማስፈፀም አቅም መገንባት ፡፡

ራዕይ፡- የበለጸገችና መልካም አስተዳደር የሰፈነበት የመተማ ወረዳን እዉን የሚያደርግ የማስፈፀም አቅም
በሁሉም የመንግስ ተቋማት ተገንብቶ ማየት ፡፡

የመተማ ወረዳ ት/ጽ/ቤት እሴቶች

 ሁሌም ተማሪና አስተማሪ መሆን እንደሚገባን እንገነዘባለን


 የስራ ፍቅር ከበሬታና ስነ-ምግባር መለያችን ይሆናል
 ለተገልጋዮች /ለዜጋዉ/ ፍላጎት ቅድሚያ መስጠት መለያችን ባህላችን እናደርጋለን
 ግልጽነትና ተጠያቂነት እናሰፍናለን
 ቅልጣፋና ዉጤታማነትን እናረጋግጣለን
 ፍትሃዊነትን ማስፈን የመልካም አስተዳደር ገጽታችን ዋነኛ አካል መሆኑን እንገነዘባለን
 ለዉጥ ናፋቂና አራማጅ እንሆናለን ፡፡

//
የመተማ ወረዳ ት ጽ ቤት መርሆች

 የአገልግሎት አሰጣጡን ማሻሻልና ተገልጋዮች እርካታ እንዲያገኙ የሚያስችል ስርአት


መፍጠር
 ሀቅ፣ገለልተኛና ሚዛናዊ የሆነ አገልግሎት መስጠት
 የቅሬታ አቀራረብ ስርአቱን ዉጤታማ ማድረግ
 የተለያዩ መረጃወችን ግልፅ በሆነ መንገድና ቦታ ማስቀመጥ መቻል
 በመልካም የስራ ዲሲፒሊን የታነፀ ሃይል መፍጠር
 ከኪራይ ሰብሳቢነት ነፃ መሆን

 ታማኝነትና ሚስጥር ጠባቂ መሆን

 ንብረትና በጀትን በአግባቡ መጠቀም

 12 ቱን የስነ-ምግባር መርሆች ማከበርና መከተል

ዓላማ

የተጀመረዉን የለዉጥ እንቅስቃሴ እየተመዘገበ ያለዉን ተስፋ ሰጭ ዉጤቶች በዘላቂነታቸዉ ለማረጋገጥ


ጽ/ቤቱና ሰራተኛዉ የተቋሙን ተልዕኮና ራዕይ ለማሳካት በአንድነት በመነሳት ተግባራቸዉን ማከናወን
አፈፃፀማቸዉን በየጊዜዉ እየገመገመ የሚገኙ መልካም ተሞክሮችን አንዱ ከሌላዉ በመማርና የተሻለ
እንቅስቃሴ በማድረግ የሂደቱ እቅድ በስኬት እንዲፈፀም ማድረግ ፡፡

ግብ

የለዉጥ ስራዎችን ማለትም የልማት፣ የመልካም አስተዳዳር፣ የዲሞክራሲ ሰርዓት ግንባታ ግቦቻችን በተሟላ
መንገድ ተግባራዊ በማድግና በወረዳ የሚገኙ መ/ቤቶችን በመደገፍ የአገልግሎት አሰጣጥ በተከታታይ
ለማሻሻል የሚሰራ ከፍተኛ የሆነ በክህሎቱ ብቃት የኪራይ ሰብሳቢነትን አመለካከት በመናድ የተገልጋዮችን
እርካታ ለማሳደግና ተጠቃሚዎችን ለማርካት መንስኤ የሚሆኑ ስህተቶችን የሚያርም ተቋም መፍጠር ፡፡

በስራ ቡድን መደራጀት አስፈላጊነት

የልማትና የመልካም አስተዳደር ተግባራት ስኬት በተሻለ ፣በተፋጠነ፣ ተደራሽ በሆነና ዘላቂነት ባለዉ መንገድ
ለማስቀጠል በአስፈፃሚና በፈፃሚዉ በኩል እየታየ ያለዉን የአፈፃፀም ክፍተት በማስወገድ የሚፈለገዉን
ለዉጥ ለማምጣት በተደራጀና ወጥነት ባለዉ መንገድ መንቀሳቀስ አስፈላጊ በመሆኑ ነዉ ፡፡ ግቦች ዉጤት
የሚያስመዘግቡት ባላቸዉ የስራ ህብረት እንጂ በተናጠል እንደሆነ ሁሉ በሂደታችን የምናከናዉናቸዉ
ተግባራት ዉጤታማ የሚሆኑት በሂደቱ ዉስጥ ያለነዉ ሰራተኞች በምናደርገዉ የሥራ እንቅስቃሴ በመሆኑ
የስራ ቡድን አደረጃጀት አስፈላጊ ነዉ ፡

የሂደቱ ሰራተኞች በስራ ቡድን የተደራጁበት አግባብ

በሂደቱ ዉስጥ አስተባባሪዉን ጨምሮ ስምንት /7/ ሰራተኞች የሚገኙ ሲሆን እነዚህ ሰራተኞች
በአንድ የስራ ቡድን ዉስጥ ተደራጅተዋል ፡፡ ስለሆነም ይህ የስራ ቡድን በሂደት አስተባባሪዉ የሚመራ
ሆኖ አንድ የ 1 ለ 5 እና በአንድ የስራ ቡድን የተደራጀ ነዉ ፡፡
እቅዱን ተግባራዊ ለማድረግ ያሉ ምቹ ሁኔታዎችና ስጋቶች

ምቹ ሁኔታዎች

 በሂደቱ ያሉ ሰራተኞች በቡድን በመስራት የመደጋገፍና የስራ ክፍተት እንዳይኖር ማድረጉ


 አብዛኛዎቹ የሂደቱ ሰራተኞች በቡድን የመስራት ልምድ እየተሻሻለ የመጣ በመሆኑ
 አደረጃጀቱን ዉጤታማ ለማድረግ የሂደቱ ሰራተኞች በየሳምንቱ የሚያደርጉት የስራ ግምገማ
እየተጠናከረ መምጣቱ
 ሁሉም ባለሙያዎች ለስራ አምች መሆኑ የ BSC /ዉጤት ተኮር ሰርዓት/ መታቀድና
ፈፃሚዉ በዉጤት ለማሳካት ግቦችን ቆጥሮ በመረከብ ተግባራት ሳይንጠባጠቡ መፈፀም
የሚችሉበትን ሰርዓት መዘርጋት መቻሉ ፣
ሰጋቶች፣
 የሂደቱ አስተባባሪና የባለሙያዎች በመስክ ስራና በሌሎች ምክንያቶች በተቀመጠዉ ፕሮግራም
መሰረት ያለመወያየት ችግር ሊያጋጥም ይችላል ፡፡

ዉስጣዊ የሁኔታ ግምገማ


የሂደቱ ሰራተኞች ያሉበት ሁኔታ

1. በአመለካከት

1.1 በጥንካሬ

 በአለዉ አደረጃጃት መሰረት አፈፃፀም እየገመገሙ አቅጣጫ በማስቀመጥ ለመስራት ያለዉ ፍላጎት
እያደገ መሄድ
 ሰራተኞች ቡድናዊ አሰራርን በማጠናከር ተቀናጅቶ የመስራት ባህሉን በማጠናከር እየሰራ መሆኑ
 ሰራተኞች የአገልጋይነት ስሜትና የስራ ተነሳሽነትን በማሳደግ ለመስራት ግንዛቤያቸዉ እያደገ የመጣ
መሆኑ ፣
 በግንባር ቀደምትነት ተርታ የሚሰለፉ ሰራተኞች መኖራቸዉ ፣
 የጽ/ቤቱ ተልዕኮና ራዕይ ተገንዝቦ ለተግባራዊነቱ መንቀሳቀስ ሃገሪቱ ለምትፈልገዉ የልማት ፣
የመልካም አስተዳዳርና የዲሞከራሲ ስርዓት ግንባታ ያለዉን ፋይዳ በመገንዘብ የሚንቀሳቀሱ የሂደቱ
ሰራተኞች መኖራቸዉ ፣
 በተቋሙ በወር በቋሚነት በሲቪል ሰርቪስ /በለዉጥ/ ቀን ሰራተኞች በተመረጡ ርዕሶች ላይ
በመወያየት የተሸለ ግንዛቤ በመያዝ ተግበራትን ለመፈፀም ጥረት እየተደረገ መሆኑ
 በአመለካከት በእውቀትና በክህሎት ከሚሉት ማወያያዎች በተጨማሪ ባለሙያዎች ተጨማሪ
የማወያያ ርዕሶችን በመምረጥ በየሳምንቱ መወያየታቸው
1.2 በእጥርት
 የሰራተኛዉ የጊዜ አጠቃቀም ባህሉ እየተሻሻለ ቢሆንም ዉስንነት መኖር
 በየወሩ በሚከበረዉ የሲቪል ሰርቪስ ቀን ሁሉም ባለሙያ በመስክና በተለያዩ ምክንያቶች
አለመገኘት
2. በክህሎት

2.1 በጥንካሬ ፣

ቅንጅታዊ አሰራር መኖሩ


እርስ በርስ በመማር አቅምን ለማሳደግ የሚታዩ ጅማሮ መኖሩ
ተግባራትን በእቅድና በቼክ ሊስት ቆጥሮ ይዞ በደረጃዉ ለሚገኙ አካላት በመደገፍ በኩል የተሻለ
እንቅስቃሴ መኖሩ
2.2 በእጥረት
በመሰረታዊ የኮፕዩተር ክህሎት/አጠቃቀም/ ላይ በሂደቱ ሰራተኞች በኩል ዉስንነት መታዩቱ
ሁሉም ባለሙያ የቸክሊስት ድጋፎችን አለመቀበል
3. በዕዉቀት

3.1 በጥንካሬ

 በሂደቱ ዉስጥ ያሉ ባለሙያዎች ያላቸዉን ዕዉቀት ተጠቅመዉ የሂደቱን አፈፃፀም ከፍ እንዲል


ጥረት እያደረጉ መሆኑ
 ባለሙያዎች በአሰራር ማንዋሎች ፣ ሰነዶችና የስልጠና ማቴሪያሎች ላይ የተሻለ እዉቀት
እንዲኖራቸዉ ጥረት መደረጉ
 በሂደቱ ያሉ ሰራተኞች እዉቀታቸዉን ለማዳበር እርስበርስ ሚያደርጉት መማማር
 ስልጠና ሳይሰጣቸዉ ባለሙያዎች በሂደቱ የሚገኙና የሚመጡ ልዩ ልዩ ማቴሪያሎችን አንብቦ
የመረዳት ባህል እየዳበረ መምጣት መቻሉ
3.2 በእጥረት
 ከቴክኖሎጂ ጋር የተያያዙ አዳዲስ መረጃዎችን ከኢንተርኔት በመፈለግ በኩል አገልግሎቱን
ለማግኘት ጥረት አለማድረጉ
 ስልጠና ባይሰጣቸዉም ባለሙያዎች የተለያዩ ማቴሪያሎችን አንብበዉ የመረዳት እምብዛም
አለመደበሩ

4. ከግብአት አንጻር ፣
4.1 በጥንካሬ
 የመንግስት ሃብትና ንብረት በአግባቡ በመያዝ ለመጠቀምና በተቆርቋሪነት መንፈስ ለመንቀስቀስ
የሚያደርግ ጥረት መኖሩ
 የሚመደብ የጽህፈት መሳሪያ አብቃቀቶ በመጠቀምና ብክነትን በመቀነስ ለመስራት የሚያደርግ
እንቅስቃሴ እየተሻሻለ መምጣቱ
4.2 በእጥረት
 የመረጃ ሃብት በአግባቡ በመያዝ ለመጠቀምና የመረጃ ቋት ይዞ ለመስራት የሚታይ ዉስንነት

 በሂደቱ ዉስጥ የሚገኙ የተወሰኑ ኮምፕዩተሮች ምክንያት አገልግሎት አለመስጠትና የኢንተርኔት


አገልግሎት መቆረጥ
 በወረዳ ሴክተሮችም ሆነ በቀበሌዎች በተፈለገዉ መንገድና ጊዜ ተንቀሳቅሶ ለመስራት
የተሸከርካሪ እጥረት መኖሩ
 የበጀት እጥረት መኖሩ
የስራ ቡድን ሰራተኞች መገምገሚያ መስፈርት ፣

1. ከስነ - ምግባር አንፃር፣

 ራስን በራስና በስነ-ምግባር በማነጽ/አርያ ሆኖ መገኘትና ሌሎችንም እንዲስተካከሉ ጥረት ማድረግ


 ከኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከት ተግባር የፀዳና ሌሎችንም ለማረም የሚንቀሳቀሱ ስለመሆናቸው
 ከጓደኞቹና ከቅርብ ኃላፊዉ ጋር መልካም የሆነ የስራ ግንኙነት ያለዉ ስለመሆኑ
2. ከተልዕኮ አፈፃፀም አንፃር

የተሰጠዉን ኃላፊነት በእቅድ በሚሰራበት ወቅት ወጭ ቆጣቢ የሆነ፣ በብቃት የሚፈፀምና ሌሎች
እንዲፈፀሙ መደገፍ
የስራ ሂደቱ እንቅስቃሴ ቀልጣፋና ዉጤታማ እንዲሆን እንቅስቀሴ የሚያደርግ
በስራ ሂደቱ በአገልግሎት አስጣጥና ተዛማጅ ጉዳዮች ላይ የሚሰጠዉን አስተያየት በግብአትነት
በመዉሰድና በማጣራት ለተሻለ ስራ የሚጠቀምና በተሰጠዉ አስተያየት መሰረት የማስተካከያ
እርምጃዎች እንዲወሰድ ጥረት ማድረግ
በተለያዩ የዉይይት መድረኮች ያለማቆራረጥ በመገኘት ለስራ ሂደቱ ገንቢ የሆነ አስተያየት መስጠትና
በዉይይቱ ላይ የነቃ ተሳትፎ ማድረግ
የሲቪል ሰርቪስ ማሻሻያ ፕሮግራም የተለያዩ የለዉጥ ፕሮግራሞችን በእምነት በመቀበል የሚተገብርና
ሌሎችንም እንዲተገብሩ የሚያስተባብር
ለቡድን ስራ ተግባራዊነት ተገዥ በመሆን አስፈላጊዉን ሁሉ የሚፈጽም

3. ዲሞክራሲያዊ ግንኙነት

ከቅርብ ኃላፊዉ የሚሰጥ ተግባር ተልዕኮ በሙሉ ፍላጎትና ፈቃደኝነት ተቀብሎ የሚተገብር
ለስራ ባልደረቦቹና ለተገልጋዮች ተገቢ የሆነ ስነ-ምግባር በማሳየት የሚንቀሳቀስ ከዚህ ዉጪ
የሚሆኑ ስራ ባልደረቦች ቢኖሩ በምምከር/ሂስ/ በማድረግ ለማስተካከል ጥረት የሚያደርግ
በስራ ሂደቱ ከስራ ጋር በተያያዘ መንገድ የሚፈጠር አለመግባባት ቢኖር ለመፍታት ጥረት
የሚያደርግ
የ 2007 ዓ.ም በተቋሙ ባሉ የሂደት ሰራተኞች እንደ ስራ ቡድን የሚከናዉኑ ተግባራት

 የ 5 ዓመቱ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ በየዘመኑ የሚከናወኑት በመርሃ ግብር ተሸንሽነዉ


የተቀመጡ በመሆኑና የ 2007 ዓ.ም የበጀት አመት የእድገት ትርንስፎርሜሽን እቅዳችን 5 ኛዉ የትግበራ
ዘመን በመሆን በ 2005 ዓ.ም የነበሩ ቀሪና የተንጠባጠቡ ተግባራትና የዚህ በጀት ዓመት ተግባራት
ተደምረዉ ብዙ ጥርት የሚጠይቁ በመሆኑ ተግባራትን ሳናጠባጥብ የተቋማችን ተልዕኮ በቁርጠኝነት
ለማሳካት ቁልፍ ጉዳይ የሆነዉን የልማት ሰራዊት ግንባታ ስራችንን አጠናክረን በመቀጠል የተጣለብንን
ኃለፊነት ለመወጣት ማስፈፀም አቅማችን አጎልብተን መቀጠል ይገባናል ፡፡
 የሂደቱ አስተባባሪና ፈፃሚ በአለዉ ኃላፊነትና ሙያ በስራ ቡድን ግንባታ ሂደት እራሱን በማደራጀትና
በማብቃት ሂደቱን መምራት ይጠበቅብናል
 ከሂደቱ አስተባባሪና ሰራተኞች የሚጠበቀዉን ተግባር ጠቅለል አድርጎ በማስቀመጥ መፈፀም አለበት
 የሂደቱ አስተባባሪና ሰራተኞች አጠቃላይ የተቋሙንና የስራ ሂደቱን ግብ ፣ ተልዕኮ፣ራዕይና እሴቶች
ጠንቅቆ በማወቅና በመገንዘብ መንቀሳቀስና የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ለሃገራዊ እድገት ያለዉን
ፋይዳ በመገንዘብ በልማት ሰራዊት አደረጃጀት መሰረት ለተግባራዊ እንቅስቀሴ አርያ ሆኖ መገኘት ፣
 የስራ ቡድኑ አባላት ያለባቸዉን የክህሎት ፣ የአመለካከትና የግብዓት ችግሮች በየጊዜዉ እየለዩ መፍታት
 የሂደቱ አስተባባሪ ሰራተኞች ከሂደቱ ዋና ዋና ተግባሮች አንፃር መከናዎን ያለበትን ተግባራት በቼክ
ሊስት ቆጥሮ በማስረከብና በመረከብ አፈፃፀሙን በየጊዜዉ መገምገም ደረጃ መስጠትና የሚኖሩ
ችግሮችን በመፍታት አቅጣጫ እያስቀመጡ መሄድ
 የተለያዩ የአቅም መገንቢያ የሚሆኑ መንገዶች በመጠቀም ለመማር ጥረት በማድረግና ስልጠና መስጠት
 የሲቪል ሰርቪስ ማሻሻያ ፕሮግራም የለዉጥ ፕሮግራሞችን በእምነት በመቀበል ለተግባራዊነቱ
መንቀሳቀስ
 ሰራተኛዉ አቅሙን እንዲያሰደግ ወቅታዊ ጉዳዩች እንዲገነዘብ የተለያዩ መጽሄቶችንና ጋዜጦችን
በመከታተል ራሱን ማብቃት
 በ BSC /ባላንሰድ ስኮር ካርድ/ መሰረት አቅዶ ተግባርን መፈፀም
 በየቀኑ አፈፃፀም ከተደራሽ ግብ አንፃር መፈፀምና በየቀኑ አፈፃፀሙን እየመዘገቡ መያዝ

ዉጫዊ የሁኔታ ግምገማ

ማህበራዊ ጉዳዮች
የመተማ ወረዳ ሲቪል ሰርቪስ ጽ/ቤት ከጽ/ቤቱ ራዕይና ተልዕኮ አንፃር የጽ/ቤቱ ደንበኞች ላይ
ያለው ገጽታ ተገልጋይን የሚያስደስት ግልጽ በሆኑ አሰራሮችና አመለካከት በመገንባት በውይይት
ችግሮች እንዲፈቱ ማድረግ ኋላ ቀር(አዜዝ ) አሰራሮችን በማስወገድ ቀልጣፋ አሰራሮች በመቅረፅ -
የሚሰጡ አስተያየቶችን በመቀበል ክፍተቶችን በመሙላትና በመንቀሳቀስ የደንበኞችን ፍላጎት በማርካት
ለውጡን ቀጣይነት እንዲኖረው ማድረግ የዚህ የለውጥ ሰራዊት ዋና ተልዕኮና አላማው ነው ፡፡

ፖለቲካዊ ጉዳዮች

የመተማ ወረዳ ሲቪል ሰርቪስ ጽ/ቤት በፖለቲካዊ አደረጃጀትና ፖሊሲዎች አተገባበር ዙሪያ መንግስት
በሚያወጣቸው ፖሊሲዎች. መመሪያዎች. አዋጆች፣ ደንቦችን ተቀብሎ በመፈፀም የሚፈጠሩ ፖለቲካዊ
ሐሳቦችን በመተግበርና በማስተግበር አገሪቱ ያቀደቸውን የ 5 አመቱን የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ
ለማስፈፀም በፍጥነት ወደ ውጤት ለማስገባት ይኸ ነው የማይባል ሚና ይጫወታል ፡፡

ኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎች

የመተማ ወረዳ ሲቪል ሰርቪስ ጽ/ቤት የተሰጠውን ተዕልኮ ለመፈፀም የሚሰራቸውን ስራዎች ጊዜና
ወጭን ቆጣቢ በማድረግ ባለጉዳዮችንም የተጋነነ ወጭ ሳያወጡ እንዲገለገሉ በማድረግ የምንጠቀምበትን
ንብረት ፎቶ ኮፒ፣ካንፒውተር፣ወንበር፣ጠረጰዛና መረጃዎችን ወ.ዘ.ተ የጽ/ቤቱን በጀት በአግባቡ ለተመደበለት
አላማ እና ተግባር በማዋል ተገልጋዮችን ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከመቸውም ጊዜ በበለጠ ይሰራል ፡፡

የመ/ወ/ሲ/ሰ ጽ/ቤት የ 1 ለ 5 ቡድን መተዳደሪያ ደንብ

 ቡድኖች መወያያ እለት ሀሙስ ከ 11፡00 ጀምሮ እስከ 12፡00 ስዓት

 በወጣዉ የመወያያ መርሃግብር ማለትም ቀንና ሰአት ሁሉም የቡድኑ አባላት በሰአቱ መገኜት
ይጠበቅባችዋል፡፡

 ሁሉም የቡድን አባላት የራሱ የሆነ ቃለጉባኤ መዝገብ ይኖረዋል

 የቡድኑ ወረሃዊ ሪፖርት ለጽ/ቤት ኃላፊ ይቀርባል ፡፡

የመ/ወ/ሲ/ሰ ጽ/ቤት የሚከናናቸዉ ተግባራት

 ከ 26 ቱ ሴክተሮች የሚገኙ አመራሮችና ሰራተኞችን የለውጥ ሰራዊት ግንባታ የልማት ሰራዊት ግንባታ
በተመለከተ የግንዛቤ መፍጠር ክትትልና ግምገማ መፍጠር
 ለ 20 ቀበሌዎች የለውጥ ሰራዊት ግንባታ / የልማት ስራዎች ግንባታ) በተመለከተ ግንዛቤ መፍጠር
ክትትልና ግምገማ ማድረግ
 የለውጥ ሰራዊት ግንባታ ( የልማት ሰራዊት ግንባታ ) በተመለከተ ለአመራሮችና ለሰራተኞች ግንዛቤ
መፍጠሩን መገምገምና መደገፍ የሂደቱ አባላት አቀማመጥ ሂደት ተኮር አሰላለፍ መሆኑን በተግባር
በመጎብኘት መደገፍ
 የደንበኞችን ፍላጎት መሰረት ያደረገ ቀልጣፋ አገልግሎት በየሴክተሮች መስጠት
 የተዘረጋውን አዲሱን የውጤት ተኮር ስርዓት / BSC/ ተግባራዊ እንዲሆን እየገመገሙ መሬት እንዲነካ
ማድረግ
 የሴክተሮችን አፈፃፀም በተመለከተ ሲቪል ሰርቪስ በሚያወጣው መስፈርት መሰረት ማወደደሩን
ማረጋገጥ
 በየእለቱ የተከናወኑትን ተግባራት መስፈርት በማዉጣት መገምገም

 ከየእለት ስራዎች በመነሳት አፈጻጸምን መገምገም


 ለስራ የሚወጡትን ደንቦች ፤ አዋጆች ፤መመሪያዎችን ተግባራዊ ማድረግ
 በየእለቱ የተከናወኑ ተግባራትን መገምገም

 የአቅም ክፍተት ያለባቸውን ሰራተኞች በመለየት አቅማቸውን እንዲያጠናክሩ ማድረግ

 የሂደቱን መመሪያዎች ተግባራዊ ማድረግ

 የመንግስት ፖሊሲና እስትራቴጅዎችን ማስፈፀም

ማጠቃለያ

ይህ የልማት ሰራዊት (የለውጥ ቡድን) በተደራጀው መሰረት አገራችን መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገራት ተርታ
ለማሰለፍ የህብረተሰቡ አገልጋይ መሆን ተረድቶ ከኪራይ ሰብሳቢነት ፀድቶ ጊዜውንና በጀቱን በአግባቡ
ተጠቅሞ የአገልጋይነት ስሜት አድሮበት ለስራው እንቅፋት የሆኑትን በመለየት የአቅም ክፍተቶችን ለይቶ
እየሞላ የመንግስትን ፖሊሲ በትክክል እየተገበረ የሴቶችን እኩልነት ተረድቶ ተልዕኮውን በአግባቡ የሚወጣ
የልማት ሰራዊት (የለውጥ ቡድን) ሲሆን ከዚህ ዕቅድ በመነሳት እያንዳንዱ የስራ ሂደት የስራ ቡድንና የ 1 ለ 5
አባላት እያቀዱ በዕቅድ መሰረት እየተወያየ የተቋሙን ራዕይና ተልዕኮ ለማሳካት የሚረዳ ዕቅድ ነዉ

You might also like