You are on page 1of 12

1 የመተማ ወረዳ ትም/ት ጽ/ቤት

የ 2010 የመልካም አስተዳደር ዕቅድ


2 የመተማ ወረዳ ትም/ት ጽ/ቤት

መግቢያ

መንግስት የህ/ሰቡን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል በልማትና መልካም አስተዳደር ዙሪያ በርካታ ስራዎችን እየሰራ
ይገኛል፡፡ እስካሁን ባለዉ ሁኔታ በየዘርፉ በርካታ አበረታች ዉጤቶች ተመዝግበዋል፡፡ ኪራይ ሰብሳቢነት
በማስወገድና ፖለቲካዊ ኢኮኖሚ ከማሳደግ አኳያ ትክክለኛ ፖሊሲና አቅጣጫ ተቀምጦ ከየትኛዉም ጊዜ
የተሻለ እንቅስቃሴ በመደረጉ ተጨባጭ የሆኑ ዉጤቶችን ማስመዝገብ ተችሏል፡፡ ከዚህ ጎን ለጎን መልካም
አስተዳደርን ለማስፈንና በተሰሩ ስራዎችም የማይናቁ ለዉጦች ታይተዋል፡፡

ነገር ግን መልካም አስተዳደርን ከማረጋገጥ አኳያ ገና ያልተሸጋገርናቸዉ ችግሮች አገልግሎትን በትዉዉቅና


በአማላጅ መስጠት አንድ አንድ አገልግሎቶች በሚፈልገዉ ደረጃ ተደራሽ አለመሆን ወ.ዘ.ተ ዛሬም
የትምህርት ጽ/ቤት መገለጫ ሁነዉ የቀጠሉበት ሁኔታ ይታያል በችግሩም ጽ/ቤታችን ሰለባ ሆኖ እናየዋለን

መልካም አስተዳርና ፈጣን ልማት የማይነጣጠሉ ከመሆናቸዉ አኳያ ከላይ የተጠቀሱት እና መሰል
የመልካም አስተዳደር ችግሮች ባልተፈቱበት ሁኔታ ፈጣን እድገት ማስመዝገብ ቀርቶ የተጀመረዉንም ዳር
ማድረስ የሚቻልበት ሁኔታ በፍጹም ሊኖር አይችልም ፡፡

ስለሆነም እስካሁን ያስመዘገብናቸዉን የመልካም አስተዳደር ፍሬዎች ጠብቀን ጎን ለጎን ደግሞ ተገልጋዩ
ህ/ሰብ በችግርነት የሚያሳያቸዉንና በተለያዩ ዘዴዎች ተጠቅመን ያገኘናቸዉን የመልካም አስተዳደር
እጥረቶች በአጭር በመካለኛና በረጀም ጊዜ መፍታት ስለሚገባ ይህን የመልካም አስተዳደር ችግር
ለመፍታት የሚያገለግል ዕቅድ አቅደናል ፡፡

1. የእቅዱ መነሻ ሁኔታዎች


1.1 የትምህርት አመራር ሁኔታ
አመራሩ ከስሩ በየደረጃዉ ያለዉን አመራር እና መላዉን የትምህርት ቤቶች ባለድርሻ አካላት በማነቃነቅና
በመምራት የመንግስትን የልማትና የመልካም አስተዳደር ፖሊሲዎች ከማሳካት አኳያ ቁልፍና የማይተካ
ሚና ያለዉ አካል ነዉ፡፡ አመራሩ ባለፉት ዓመታታ የተሰጡትን ተልዕኮዎች ለማሳካት ሲንቀሳቀስ
ቆይቷል እንደ ሁኔታዉ እቅድ በማዘጋጀት በዕቅዱ ላይ ግልጽነት በመፍጠርና ሰራተኛዉን በማንቀሳቀስ

የ 2010 የመልካም አስተዳደር ዕቅድ


3 የመተማ ወረዳ ትም/ት ጽ/ቤት

እቅዱን ለመፈጸም ጥረት አድርጓል፡፡ በሁሉም አንደኛና ሁለተኛ ደረጃና ት/ቤቶች መንግስት
የቀየሳቸዉን የሪፎርሙን ፕሮግራሞች ተግባራዊ ለማድረግ ስፊ እንቅስቃሴዎች ተደርገዋል፡፡ በተደረጉ
ጥረቶች መልካም አበረታች ዉጤቶች ተገኝተዋል፡፡ እነዚህ በጎ ዉጤቶች ያለ ትምህርት አመራርና
ፈጻሚዎች ጥረት የመጡ እንዳልሆነ ሊሰመርበት ይገባል ፡፡

ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ የእስካሁኑ የለዉጥ ሥራን ውጤት የሚያሳየን ሌላኛው ገፅታም አለ ይሄውም


የለውጥ ሥራችን የመንግስት አደረጃጀቶችና አሠራሮችን በማስተካከል በመጣው ለውጥ ልክ አደረጃጀቱንና
አሠራሩን ተጠቅሞ ውጤት እንዲያስመዘግብ የሚጠበቀው የሰዉ ኃይላችን በአመለካከትና በክህሎት
ያሉበትን ክፍተቶች ለይቶ እነዚህን ክፍተቶች ለማጥበብ ብሎም ለመድፈን የሚያስችል አቅም የመገንባት
በዋነኝነት የአመራሩ ነዉ፡፡ በእስካሁን የለዉጥ ስራችን ሂደት የተስተዋለዉና የሰዉ ኃይሉን ከማብቃት ጋር
ተያይዞ በግልጽ የታየዉን ጉድለት ከትምህርት አመራሩ ሚና መጓደል ጋር በቀጥታ የተያያዘ መሆኑ
የሚታወቅ ነዉ ሌላዉ ዉስንነት ደግሞ ህዝቡ በለዉጥ ሂደቱ የተደራጀ ተሳታፊና የት/ቤቱ ባለቤት እንዲሆን
ከማድረግ ጋር በተያያዘ የታየ እጥረት ነዉ በእርግጥ አንዳንድ ት/ቤቶች የተቋማቸዉ አገልግሎት ተጠቃሚ
የሆነዉን የህ/ሰብ ክፍል ለይቶ ለማሳተፍ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እንቅስቃሴ የጀመሩበት ሁኔታ እንዳለ
ይታወቃል ሆኖም አብዛኛዎቹ ት/ቤቶች በዚህ ረገድ ትርጉም ያለዉ እርቀት አልሄዱም የተቋሙን ተገልጋይ
በአግባቡ በመለየት ተቋሙ ለህዝብ እንዲሰጥ የሚጠብቀዉን የአገልግሎት አይነት መጠነኛ ጥራት
እንዲሁም እነዚህ አገልግሎቶች ለማግኘት በህዝቡ በኩል መሟላት ያለባቸዉን መስፈርቶች በማስቀመጥና
በማሳወቅ እነዚህ ጉዳዮች በሁለቱም አካላት በኩል ተከብረዉ እየተፈፀሙ ስለመሆናቸዉ በቋሚነት ሁለቱም
ተገናኝተዉ እየገመገሙና በሚታዩ ጉድለቶችቸ ላይ የጋራ የእርምት እርምጃ እየወሰዱ ለመጓዝ
በሚያስችል ተቋማዊ አሰራር መምራት ጀምሯል ተብሎ ሊወሰድ የሚችል አይደለም፡፡

በድምሩ የለዉጥና የመልካም አስተዳደር እንቅስቃሴያችን መሰረታዊ ዉስንነት መንስኤ ሲታይ አመራሩ
የመልካም አስተዳደር ስራችን ትኩረት ሰጥቶን በባለቤትነት መምራት ካለመቻሉ ጋር የሚያያዝ ነዉ ይህ
በመሆኑ አመራሩ ራሱን ጨምሮ ከስሩ ያለዉን ሰራተኛ እና የህዝቡን አመለካከት ፣ክህሎት፣ የአደረጃጀት
፣የአመራርና የአቅርቦት ማነቆዎችን የመፍታት የሚያስችል የአቅም ግንባታ ስራ በዋና በባለቤትነት
ያልሰራበት ሁኔታ በሰፊዉ ታይቷል ፡፡ስለሆነም በየደረጃዉ ያሉ አመራሮችን የግንዛቤ ችግሮችን በመፍታት
የአመለካከት፣የክህሎትና የአቅርቦት ያለዉን ማነቆ በማስወገድ ከስሩ ያሉትን ሰራተኞችንና ህዝቡን
የአመለካከት ፣የክህሎትና የአቅም ክፍተቶች ቆጥሮ በመለየት ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችል ሰፊ
የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ በመስራት የአጠቃላይ የትምህርት ጥራት ፓኬጅን ከምንጊዜዉም በላይ ተግባራዊ
ማድረግ ይገባናል ፡፡

2.2 የትምህርት ሠራተኞች ሁኔታ

ቀደም ሲል የነበረዉ ስርአት እጅግ ኋላቀር የስራ ባህል የመፈጸም አቅሙም የደከመ
የአገልግሎት አሰጣጡ የቀዘቀዘ የተጠያቂነት ስሜት ያልያዘ ኋላቀር አሰራር ለመቀየር ብዙ
ጥረቶች ተደርገዋል መሻሻሎችም ታይተዋል፡፡ ይህ አበረታች ለዉጥ በተጨባጭ የሚታይ
ቢሆንም ጠንካራ የመፈጸም አቅም ያለዉ ከኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና ተግባር የጸዳ

የ 2010 የመልካም አስተዳደር ዕቅድ


4 የመተማ ወረዳ ትም/ት ጽ/ቤት

የልማታዊ ዲሞክራሲያዊ መንግስት ተልዕኮ በተሟላ ሁኔታ ተገንዝቦ ይህንኑ መፈጸም


የሚችል እዉቀት አመለካትና ክህሎት ያለዉ ባለሙያ አልተፈጠረም ባለሙያው ቀድሞ
ከነበረዉ ሁኔታ ጋር ሲነጻጸር በግንዛቤዉም ሆነ በአመለካከቱ ያሳየዉ ለዉጥ ቢኖርም
ባለሙያ ሆኜ የተቀጠርኩት ከምንም በላይ ዜጋን ለማገልገል ነዉ የሚል አመለካከትና አቋም
በጽናት አሁንም አልያዘም፡፡ አብዛኛዉ ጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር የሚጠይቅ ነዉ ክህሎቱ
አሁንም በተገቢዉ ደረጃ አልተሻሻለም የጠባቂነት ስሜት ዉሳኔን የማጓተት ተገልጋዩን
ማመላለስና በተለያየ መልኩ የሚገልጽ የኪራይ ሰብሳቢነት ችግር ይታያል፡፡

በመሆኑም የአሰራር ስርአቱን ግልጽነት ለማሻሻል የተጠያቂነት ስሜት ይበልጥ ለማዳበር


በተለይም የልማታዊ ዲሞክራሲያዊ መንግስት ፖሊሲና ፕሮግራሞች ላይ ግልጽነት ይዞ
በብቃት መፈጸም የጸና አመለካከት ያለዉና በክህሎቱ የዳበረ ባለሙያ ለመፍጠር ትልቅ
ጥረት መደረግ አለበት፡፡

2.3 ተቋማዊ ሁኔታ

በመ/ቤታችን በታሪክ አጋጣሚ የመልካም አስተዳር ስራዎችን የመፈጸም ተልዕኮ


የተሰጠዉ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በአመራሩም ሆነ በፈጻሚዉ ደረጃ የሚታየዉ እንቅስቃሴ
አበረታች ቢሆንም በክህሎትም ሆነ በአመለካከት ደረጃ ግንባር ቀደም ሆኖ በመስራት ረገድ
ገና ብዙ የሚቀረዉ ነዉ ፡፡

ከተገልጋዩ ለሚቀርቡ ጥያቄዎች በወቅቱ አፋጣኝ ምላሽ የማይሰጡ ሰራተኞች እስካሁን


ባለመጥፋታቸዉ በተቋማችን የመልካም አስተዳደር እጦት አልፎ አልፎ መከሰታቸው
አልቀረም፡፡ በአጠቃላይ የተቋማችን አመራርም ሆነ ፈጻሚ መልካም አስተደዳርን ከማስፈን
በተለይም መሪ ከመሆኑ አኳያ የተሟላ ቁመና ላይ የሚገኝ ባለመሆኑ በቀጣይ ይህን
ለማሻሻል ጥረት የሚጠይቅ ነዉ፡፡

1. የመልካም አስተዳደር ዋና ዋና ችግሮችና መግለጫዎች

1.1 ከአመለካከት አንጻር

የ 2010 የመልካም አስተዳደር ዕቅድ


5 የመተማ ወረዳ ትም/ት ጽ/ቤት

1.1.1 ከአመራር አመለካከት አንጻር


- ሰራተኛን አስተባብሮና ደግፎ አለመምራት
- የአስተሳሰብና የአመለካከት ለዉጥ እንዲመጣ በጋራ ከሚሰሩ ባለሙያዎች ጋር መታገል
አለመፈለግ
- አቅምና ተነሳሽነት ያላቸዉን ሰራተኞችን በመለየትና በማበረታታት ወደ ስራ
አለማስገባት፡፡
- የተቋሙ ሰራተኞችን በመለየትና በማበረታታት ወደ ስራ አለማገባት
- የተቋሙ ሰራተኞችም እየሰሩ እንዳሉ የተሟላ ዕዉቀት መረጃ አለመኖር
- ተግባርን በተለመደዉ አስተሳሰብ የመምራት ችግር መኖር
- የሰራተኞችንና የሥራ ዘርፎችን የሥራ ኃላፊነትና ተግባራትን ከተጠያቂነት ጋር ለይቶ
ሰጥቶ እየገመገመ መምራት አለመቻል
- ህዝብን በቅንነትና በእኩልነት በማገልገልና ዕድገት በማምጣት የለዉጡ ተጠቃሚ
ከመሆን ይልቅ ለራስ ጥቅም ብቻ ቅድሚያ መስጠት
- መልካም አስተዳደር ችግር ሲፈጠር ዝም ብሎ የማየትና ችግርን ከሚፈጥሩ ሰራተኞች
ጋር ላለመጋጨት ድክመቶችንና ጉድለቶችን አቻችሎ የመሄድ ችግር
- ከአገልግሎት አሰጣጥ አንጻር የተሰሩትን ሰራዎች ከቅልጥፍና አንጻር ብቻ ማየት
ዉጤትን ግምት ዉስጥ አለማስገባት
- መልካም አስተዳደርን ለማስፈን የታሰቡትን ግቦች ዳር ለማድረስ በባለቤትነትና
በቁርጠኝነት ነክሶ በመያዝ ወጥነትና ዘላቂነት ያላቸዉን ተግባራት አለመፈፀም
- የለዉጥ ፕግራሞችን በተቀናጀና በተደራጀ መልኩ ለመተግበር በእቅድና በመርሃ ግብር
የመታገዝ ስራ መስራት አለመቻል
- ስራን ቆጥሮ የመስጠትና ቆጥሮ የመቀበል ባህልን አለማጠናከር

1.1.2 ከሰራተኛው አመለካከት አንፃር

 ከተቋሙ የሚሰጠዉን ተልዕኮ ከመፈጸም ይልቅ የለዉጥ ፕግራሞችን ከፖለቲካዉ


ጋር የማላትም ችግር
 ከተገልጋዮች ጋር ቀጥተኛ የሥራ ግንኙነት ያላቸዉን ሰራተኞች ለተገልጋይ
የአገልጋይነት ስሜት በመላበስ ተገቢዉን አገልግሎት ለመስጠት ተነሳሽነቱ
የቀዘቀዘ መሆኑ
 የተገልጋዮችን ጥያቄና ፍላጎት መሰረት በማድረግ በቀና ስሜት በትዕግስትና ትህትና
በተሟላበት መንገድ አገልግሎት የመስጠት ፍላጎት አለመኖር መልካም አስተዳደር
በመስፈኑ በሚመጡ ለዉጦች የጋራ ተጠቃሚ መሆኑን አለመረዳት

የ 2010 የመልካም አስተዳደር ዕቅድ


6 የመተማ ወረዳ ትም/ት ጽ/ቤት

 መልካም አስተዳደር በአገልግሎት አሰጣጥ እየተመዘገቡ ያለዉን ለዉጥ እንደቀላል


የማየትና የማንቋሸሽ
 የመንግስት ፖሊሲ ስትራቴጂና መልካም አስተዳደር ፓኬጆች በዉል ተረድቶ
ከመፈጸም ይልቅ ለግል ጥቅም መሯሯጥና ኪራይ ሰብሳቢነት በጽናት ያለመታገል
 የሚከፈለዉን ደመወዝ ከተገልጋዮችን የሚሰበሰብ ግብር መሆኑን በመዘንጋት
የመንግስት የስራ ሰዓት በአግባቡ አለመጠቀም ይህም የመልካም አስተዳደር ችግር
ምንጭ መሆኑ
 በሰዉ ኃይል ስምሪት ህግና ደንብን ጠብቆ ለመፈጽም አለመቻል
 ብሰራም ባልሰራም ወር ቆጥሬ ደመወዜን ለመዉሰድ የሚከለክለኝ የለም የሚል
አስተሳሰብ ስር የሰደደ መሆኑ
2. ከክህሎት አንጻር
1.2.1 ከአመራር ክህሎት አንጻር
 በሚዘጋጀዉ ዕቅድና የዕቅድ አፈጻጸም ሰራኛዉን ተገልጋዩንና አጋር አካላትን
አለማሳተፍ
 እራስንና ፈጻሚዎችን የማዘጋጀትና የማብቃት ስራ አለመስራት
 መልካም አስተዳደርን ማስፈን የሚያስችሉ ጠንካራ የድጋፍና የክትትል አግባብ
ፈጥሮ ወደ ስራ አለመግባት
 ሰራተኛን በማሳመንና የተሻለ አገልግሎት በመስጠት ቅልጥፍናና ዉጤታማነትን
አለማምጣት
 በመልካም አስተዳደር አተገባበር የሚታዩ ክፍተቶችን የሚለዩበትን ስልትና
ሰራተኛን የማብቂያ መንገዶችን ቀይሶ አለመስራት
 ለአዳዲስ አሰራሮችና ለጥናት ግኝት ራስን ማዘጋጀት አለመቻል

1.2.2 ከሰራተኛዉ ክህሎት አንጻር

 ለመመሪያዉ የተሟላ እዉቀት አለመኖር ይኸዉም መመሪያዎችን


፤ፖሊሲዎችንና ስትራቴጂዎችን ለማወቅ ፍላጎት አለመኖር/
 አገልግሎት ለመስጠት ተነሳሻነቱ የቀዘቀዘ መሆኑ
 በመልካም አስተዳደር ዙሪያ የሚመጡ ለዉጦችን ከራሱ አቅም ጋር
እያዛመዱ መስጋት
 ከሌሎች ባለሙያዎች ልምድን በመቅሰም ራስን አለማዘጋጀት
 እራስን ለማብቃት ጥረት አለማድረግ
 ከአንድ አቅጣጫ አውቆ ሁሉንም አውቃለሁ ብሎ መወሰን
 ከአሰራር አንጻር የሚፈጠሩ ችግሮችን አለመታገል
 ተሞክሮዎችን አለመተንተን ፤አለመቀመርና ለማስፋፋት ጥረት አለማድረግ
1.3 ከግብዓት አንጻር

1.3.1 ከአመራሩ አንጻር

የ 2010 የመልካም አስተዳደር ዕቅድ


7 የመተማ ወረዳ ትም/ት ጽ/ቤት

 ለፈጣን አገልግሎት አመች /quik wins/ መሳሪያዎች በተቋማት የስራ ባህሪ አንጻር
አለመሟላት
 የተሟላ ዕዉቀት ያለዉ የሰዉ ኃይል አለመሟላት
 የመረጃ ሀብት ተጠናክሮ አለመያዝ
 ልዩ ልዩ ደንቦችን መመሪያዎችን አደራጅቶ አለመያዝና አለመጠቀም
ለሚመለከታቸዉ ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ አለመስራቱ
 የተመደበዉን በጀት በአግባቡ አለመጠቀም
 የቴክኖሎጂ መሳሪያዎችን ለሚፈልገዉ አገልግሎት በአግባቡ አለመጠቀም

3.የመተማ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት የ 2011 ዓ.ም የመልካም አስተዳደር ዕቅድ

3.1 የመልካም አስተዳደር እቅዱ አስፈላጊነት

በሀገራችን እየታዩ ያለዉን የልማትና የመልካ አስተዳደር ተግባራትን ስኬት በተሻለ


መንገድ፣በተፋጠነና ዘላቂነት ባለዉ መንገድ ለማስቀጠል በአገልግሎት ሰጭዉና አገልግሎት
ተቀባዩ በኩል እየታየ ያለዉን የአፈጻጸም ወይም የአገልግሎት አሰጣጥ ችግር አንጻር
የሚፈልገዉን ለዉጥ ለማምጣት በተደራጀ በተቀናጀ መንገድ ለመንቀሳቀስ ዜጎች በእኩልነት
ቀልጣፋነቱንና ዉጤታማነቱን ያረጋገጠ አስተማማኝ ልማት በማምጣት እምርታ ያለው
መልካም አስተዳደር ለማስፈን ነዉ፡፡

1.2 ለእቅዱ መፈጸም ምቹ ሁኔታዎች


 ልማታዊ መንግስታችን ልማትን መልካም አስተዳደርን ለማስፈን ቁርጠኛ አቋም
ያለዉ መሆኑ
 በየጊዜዉ የተነደፉትን ፖሊሲዎች፣ስትራቴጂዎች የሚሰሩ መሆናቸዉ
 ልዩ ልዩ አደረጃጀቶችና አሰራሮች እስከ ታችኛዉ አካል ድረስ የተዘረጉ መሆኑ
 ዜጋ በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ የሚስማዉን አስተያት መስጠት የሚችልበት
 ከወረዳ አስከ ቀበሌ ድረስ የተቋማት የዜጎች ቻርተር መዘጋጀቱ በአገልግሎት
ሰጭውና በአገልግሎት ተቀባዩ የሚደረግ ስምምነት
 የአገልግሎት አሰጣጡ የአገልግሎት አሰጣጥ ደረጃ ተቀምጦለት እየሰጠ መሆኑ
/standrde/
 ባለሙያዉ መልካም አስተዳደርን ለማስፈን ያለዉ ዝግጁነት
ስጋቶች
 በየደረጃዉ የሚገኙዉ አመራር ከወረዳ አስከ ቀበሌ ተግባሩን በትግል ያለመምራት
ችግር ሊገጥም ይችላል፡፡

የ 2010 የመልካም አስተዳደር ዕቅድ


8 የመተማ ወረዳ ትም/ት ጽ/ቤት

 የመልካም አስተዳደር መስፈን ሚናን አሳንሶ ማየትና ከልማቱ ሰራ ጋር አስተሳስሮ


አለማየት
 ተገቢዉን ዕቅድ አዘጋጅቶ ኦሬንቴሽን አለመስጠት
 ተግባሩን በክትትልና ግምገማ አለመምራት
 በወቅታዊ ተግባራት መጠመድ ምክንያት ማድረግ
 የኃላፊዎች በየጊዜዉ መለዋወጥ

3.4 ዓላማ

 የቀልጣፋና ዉጤታማ አገልግሎት በመስጠትና በመቀበል ሂደት ላይ የሚያጋጥሙ


የሰራ ችግሮችን ለማቃለልና ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዕድገትን ለማፋጠን አመች
ሁኔታ መፍጠር
 በተገልጋይ ህ/ሰብ የነቃ ተሳትፎ መልካም አስተዳደርን በላቀ ደረጃ ማረጋጥ
 ፍትሃዊ ቀልጣፋ አገልግሎትን መስጠቱን ማረጋገጥ
 ከት/ጽ/ቤት አስከ ቀበሌ ድረስ የሚገኙ ተቋሞች 3 ቱ ኃይሎች /መንግስት፣ድርጅትና
ህዝብ/ ተቀናጅተዉ የ 5 ዓመቱን የትምህርት የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ
በማሳካት መልካም አስተዳደር ማስፈን አለባቸው ፡፡

ግብ
 የልማት የመልካም አስተዳደርና የዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ግቦችን በተሟላ መንገድ
ለማሳካት
 ተነሳሽነቱ ከፍተኛ የሆነ በህዝቡ ተቀባይነት በተለይም ኪራይ ሰብሳቢነት አመለካትን
ለመናድ በጽናት የሚታገል ኃይል መፍጠር
 ዉጤታማና ቀልጣፋ እንዲሁም ወጭ ቆጣቢ አገልግሎት በመስጠት መልካም አስተዳደር
እንዲሰፍን ማድረግ
 ለተገልጋዮች ፍትሃዊ ግልጽና ዉጤታማ አገልግሎት ለማበርከትና ለፍላጎታቸዉ አፋጣኝ
መልስ መስጠት
 የህዝብ አገልጋይነት አመለካከት ማዳበር
 በአሰራር አደረጃጀትና በአመለካከት የሚታዩ ክፍተቶች ለይቶ በማዉጣት ዜጎች
የሚፈልጓቸዉን የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች መመለስ
 ተደራሽ ያልሆነ አገልግሎቶችን ተደራሽ በማድረግ የዜጎችን እንግልት መቀነስ ከመልካም
አስተዳደር ችግሮች ዙሪያ ፈጻሚዎችንና አመራሩን በማነቃነቅ የተጀመረዉን የልማት
ሰራ ግንባታ ተግባር ማጠናቀር
 በተለያየ ምክንያት ምላሽ ያልተሰጠዉን ለይቶ በመፍታት የዜጎችን እርካታ ማሳደግ
 ከወረዳ እስከ ቀበሌ ድረስ ባለዉ የተቋማችን እርከን የሚስተዋሉ /የሚታዩ/ የመልካም
አስተዳደር ችግሮችን መፍታት

የ 2010 የመልካም አስተዳደር ዕቅድ


9 የመተማ ወረዳ ትም/ት ጽ/ቤት

 አገልግሎት ፈላጊዎች ወደ ተቋሙ ሲመጡ የሚመለከታቸዉን የስራ ክፍሎችና


ባለሙያዎች በቀላሉ ለማግኜት የሚያስችል አቅጣጫ ጠቋሚ ታፔላዎች የተሟሉ
አለመሆን ምቹ የሆነ የቢሮ አደረጃጀት አለመኖር
 በሚከሰቱ የመልካም አስተዳደር ችግሮች መነሻ ልምድ ያላቸዉ ሰራተኞች ከትምህርት
ተቋማት መልቀቅ
 በተናጠል ለሚቀርቡ አንዳንድ ጥያቄዎች የሚሠጡ ምላሾች የሁሉንም ሰራኞች መብት
የሚያስከብሩ ሆነዉ አለመገኜት
 ተገልጋይ የማይገባ ጥያቄ ማንሳትና ምላሹ እንደጠበቁት ሳይሆን ሲቀር ተቋሙን
ማጥላላት
 የወጡ ልዩ ልዩ መመሪያዎችንና ደንቦችን አክብሮ ስራ ያለመስራት
 መመሪያዎችን በማስተዋወቅም ሆነ ለጥያቄዎች ምላሽ በመስጠት ረገድ በባለሙያዎች
መካከል አለማንበብ መኖር
 ተቋማት በራሳቸዉ መፍታት የሚገባዉቸዉን ጥያቄዎችና ችግሮች ወደ ላይ በመላክ
በተገልጋዮች ዘንድ እየተፈጠረ ያለዉ አገልግሎት እየሰፋ መሄዱ
 መ/ቤታችን በተለያዩ ምክንያቶች ወቅቱን የጠበቀ የድጋፍና ቁጥጥር ስራ አለመሰራቱ ስምሪት
በተፈጸመላቸዉ አካላት ዘንድ ዘግይቶ ችግር መፍጠሩ

5 በሴክተሩ ዉስጥ የተለያየ የመልካም አስተዳር ችግሮችን ለመፍታት የተቀመጡ የመፍትሄ


ሃሳቦች

 በተለያዩ የመልካም አስተዳር ችግሮችና መፍትሄዎች ዙሪያ በየደረጃዉ ለሚገኙ የትምህርት ተቋማት
ፈጻሚዎችና አመራሮች ግንዛቤ መፍጠር
 ምላሽ ሳያገኙ የተቀመጡ ልዩ ልዩ ጉዳዮችን ፈትሾ በአፋጣኝ ምላሽ መስጠት
 ለአገልግሎት አሰጣጥ አጋዥ የሆኑ የፈጣን አገልግሎት አምጭ /quick wines/ በቋሚነት ማሟላትና
ሰነዶችን የተሟሉ ማድረግ
 በጥናት የተደገፈ ሃሳብ በማቅረብ የቅሬታ ስርአቱ ሀብት ቆጣቢ በሆነ መልኩ በወረዳችን ላይ
ተደራሽ እንዲሆን ማድረግ
 ከተገልጋዮች ጋር የምክክር መድረክ በመፍጠር መብቶቻቸዉና በግዴታቸዉ ዙሪያ ግንዛቤ የማስጨበጥ
ስራ መስራት

6.የድርጊት መርሃ ግብር

የሚፈቱበት ጊዜ

የ 2010 የመልካም አስተዳደር ዕቅድ


10 የመተማ ወረዳ ትም/ት ጽ/ቤት

ተ በተቋሙ የተለያዩ የመ/አስ/ችግሮች ለመፍታት የተቀመጡ የመፍትሄ በአጭር በመካከለኛ በረጅም ፈጻሚ
. ሀሳቦች ጊዜ ጊዜ ጊዜ አካላት
1 በተለያዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮችና መፍትሄዎች ዙሪያ ለፈጻሚዎች  ትምህርት
ኦሬንቴሽን መስጠት ጽ/ቤት
2 ምላሽ ሳያገኙ የተቀመጡ ልዩ ልዩ ጉዳዮችን ፈትሾ ምላሽ መስጠት  ›
3 ለአገልግሎት አሰጣጥ አጋዥ የሆኑ ታፔላችንና ሌሎች አሰራሮች  ››
ማስተካከል ›
4 አስተዳደር ፍ/ቤቱን ወረዳችን ላይ ተደራሽ እንዲሆን ማድረግ √ ›
5 ከተቋሙ ተገልጋዮች ጋር የምክክር መድረክ በመፍጠር  ››
ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ መስራት ›
6 በትምህርት ቤቶች የሰዉ ኃይል አስተዳደር መመሪያና አፈጻጸም መካል  ›
ያለዉን ክፍተት እንዲሞላ ለዞን ትምህርት መምሪያ ማሳወቅ ›
7 ጉዳዩ ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር በመገናኜት የአዲስ ቅጥር    ›
ሰራተኞችን ጥያቄ መፍታት ›
ማሳሰቢያ ፡- በአጭር ጊዜ የሚፈታ ማለት እስከ ጥቅምት 30/2010 ዓ.ም የመካከለኛ ጊዜ
ማለት እስከ ጥር 30 ሲሆን የረጅም ጊዜ ማለት ደግሞ እንደ ሁኔታዉ እስከሚቀጥለዉ
ዓመት አጋማሽ ድረስ የሚፈቱ ማለት ነዉ፡፡

3.6 የሚከናወኑ ተግባራት

 በየሶስት ቀኑ በተቋማችን ደረጃ የስራ ሂደቶች በመልካም አስተዳር የመጡ ለዉጦችን


ያጋጠሙ ችግሮች የተሰጡ መፍትሄዎችንና ያልተፈቱ ችግሮችን ከነምክንያታቸዉ
በመገምገም አቅጣጫ ያስቀምጣል፡፡
 በየሳምንቱ በተቋም ደረጃ በስራ አመራር ኮሚቴ የሚገኙ የስራ ሂደቶች በአካል በመገኜት
ምን ያህል የመልካም አስተዳደር ችግሮች እንደተፈቱ የጋራ ማድረግና አቅጣጫ
ማስቀመጥ
 ትምህርት ጽ/ቤቱ ከአጋር አካላት ጋር በእቅድ በተደገፈ የምክክር መድረክ ለማዘጋጀትና
የምክክር መድረኩ የተገኘዉን አስተያየት በግብአትነት በመጠቀም ስራ ላይ ማዋል ፡፡
 ቼክሊስቶች በማዘጋጀት የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች በማሳካት የሱፐርቪዥን ስራ
ማከናወን
 የእቅድ አፈጻጸምን በዝግጅት፣በትግበራ እና በማጠቃለያ ምዕራፍ የሁሉን ተሳትፎ ባካተተ
መልኩ መገምገም
 ለፈጻሚ አካላት ኦሬንቴሽን መስጠት
 አሰራርና አደረጃጀቶችን ማጠናከር
 የመልካም አስተዳደር ማሻሻያ ተግባሮችን መፈጸምና የአፈጻጸም አቅጣጫዎችን
ማጠናከር
 በወረዳ እና በቀበሌ ከሚገኙ አመራሮችና የስራ ሂደት አስተባባሪዎች ጋር የመልካም
አስተዳደር ስራን በጋራ መገምገም

የ 2010 የመልካም አስተዳደር ዕቅድ


11 የመተማ ወረዳ ትም/ት ጽ/ቤት

 በጽ/ቤቱና እና በት/ቤት ደረጃ ከሚገኙ ሰራተኞች ጋር የመልካም አስተዳደር ስራን በጋራ


መገምገም
 የተቋማችን የተገልጋይ እርካታ ማረጋገጥ
 በተቋማት ደረጃ የሚገኙ ልዩ ልዩ አደረጃጀቶች በእቅዳቸዉ መሰረት ተግባራቸዉን
እንዲፈጽሙ ማስቻል፡፡
 በተቋሙ ደረጃ የተዘጋጀዉ የመልካም አስተዳደር እቅድ ላይ ለተቋሙ ሰራተኞች
ኦሬንቴሽን መስጠት
 ከሌሎች የመንግስት ተቋማትና አደረጃት ተግባራትን በፖምፕሌት ማሳወቅ፡፡
 የተገኙ ዉጤቶችን የመመዝገብና የማረጋገጥ ስራ መስራት

1.8. ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮች


 የትምህርት አመራሮች ተገቢዉን እቅድ አዘጋጅቶ ኦረንቴሽን መስጠት ተግባሩን
በጥብቅ ዲስፕሊን በክትትልና በትግል ያለመምራት ችግር ሊገጥም ይችላል፡፡

1.9 መፍትሄዎች
 ከወረዳ እስከ ቀበሌ የተደራጁትን የተለያዩ ኮሚቴዎች በማጠናከርና የልማት ሰራዊት
አደረጃጀቶችን በማሳለጫነት መጠቀም
 በመልካም አስተዳር አፈጻጸምና ችግሮች ላይ የተሟላ ግንዛቤ መፍጠር
 የመልካም አስተዳር ምንጮችን በመለየትና ባለቤት ሰጥቶ መፍትሄ የመስጠት ስራ
መስራት
 ለመልካም አስተዳር ስኬታማነት ስራ የሚያግዝ ማረቂያ ስትራቴጂ መንደፍ
 በሁሉም ስራዎቻችን ግልጽና ተጠያቂነት የተላበሰ ስርአት በመዘርጋት ሙስናንና አድሎን
መሸከም የማይችል ዜጋ መፍጠር
 ቀጣይነት ተከታታይነት ያለዉ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራ መስራት

1.10 የክትትልና ግምገማ ስርዓት


 የልማት እና የመልካም አስተዳደር እቅዶች በአግባቡ መፈጸማቸዉን መከታልና ማረም
 በአፈጻጸም ሂደት የሚያጋጥሙ ችግሮች ካሉ በየደረጃዉ በማስተካከል የእርምት እርምጃ
መዉሰድ
 በወረዳ በሚገኙ የትምህርት ተቋማት ሙያተኞች አማካኝነት በሚደረገዉ የድጋፍና
የክትትል ስርዓት የሚያጋጥሙ ችግሮችን በመለየት መፍትሄ ማስቀመጥ
 በአመቱ ማጠቃለያ የስራ ሂደት አስተባባሪዎች በተገኙበት አፈጻጸሙን እንዲገመግም
በማድረግ ስራዎችን በደረጃ መለየትና ችግሮችን ለይቶ የመፍትሄ አቅጣጫ ማስቀመጥ
ዋና ዋናወቹ ናቸዉ

ማጠቃለያ

የ 2010 የመልካም አስተዳደር ዕቅድ


12 የመተማ ወረዳ ትም/ት ጽ/ቤት

የመልካም አስተዳርን ለማስፈን ጥረት በማድረግ የተቋሙ ባለሙያዎችንና የምንደግፋቸዉን


የትምህርት ተቋማት በማብቃት የመልካም አስተዳደር ችግሮች እንዳይከሰቱ በመጣር
ሙስናን በመቀነስ በወረዳችን ጥሩ የሆነ የመልካም አስተዳደር እንዲሰፍን የሚያግዝ እቅድ
ከዞን የመልካም አስተዳደር እቅድ በመነሳት ይህን እቅድ አቅደናል፡፡

የ 2010 የመልካም አስተዳደር ዕቅድ

You might also like

  • 2012
    2012
    Document25 pages
    2012
    Lij Dani
    No ratings yet
  • 2012 e
    2012 e
    Document5 pages
    2012 e
    Lij Dani
    No ratings yet
  • 2011 1 5
    2011 1 5
    Document5 pages
    2011 1 5
    Lij Dani
    100% (1)
  • 2011
    2011
    Document9 pages
    2011
    Lij Dani
    No ratings yet
  • 2011 e
    2011 e
    Document5 pages
    2011 e
    Lij Dani
    No ratings yet
  • 2011
    2011
    Document9 pages
    2011
    Lij Dani
    No ratings yet
  • 2011
    2011
    Document6 pages
    2011
    Lij Dani
    No ratings yet
  • 2010
    2010
    Document4 pages
    2010
    Lij Dani
    No ratings yet
  • 2009 .
    2009 .
    Document36 pages
    2009 .
    Lij Dani
    No ratings yet
  • 2010
    2010
    Document4 pages
    2010
    Lij Dani
    No ratings yet
  • 2009
    2009
    Document4 pages
    2009
    Lij Dani
    100% (2)
  • 2009 1 5
    2009 1 5
    Document10 pages
    2009 1 5
    Lij Dani
    No ratings yet
  • 2009
    2009
    Document10 pages
    2009
    Lij Dani
    No ratings yet
  • 2009
    2009
    Document10 pages
    2009
    Lij Dani
    100% (1)