You are on page 1of 5

በመተማ ወረዳ ት/ጽ/ቤት

የ 2011 በጀት
የዕቅድ ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ቡድን

ዓመት
የ 1 ለ 5 እቅድ

ሰኔ 2010
ገንዳ ውሃ

መግቢያ

የዕቅድ ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ቡድን ያለበትን ደረጃ በየጊዜው በመገምገምና በማስተካከል የቡድኑ አባላት
ለዜጎች ቀልጣፋ ፣ ዉጤታማና ተጠያቂነት ያለው አገልግሎት መስጠት ይጠበቅብናል፡፡ ስለሆነም የሲቪል ሰርቪስ

የዕቅድ ዝግጅት የ 2011 የ 1 ለ 5 ዕቅድ Page 1


የለውጥ ፕሮግራም እውን ለማድረግ ሁሉም የ 1 ለ 5 አባላቶች ለታቀደዉ እቅድ መሳካት ከፍተኛ ርብርብ ማድረግ
አሰፈላጊ ነዉ፡፡

በአጠቃላይ ይህ የዕቅድ ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ቡድን የ 2011 በጀት ዓመት የ 1 ለ 5 እቅድ ውስጥ የእቅዱ
ራዕይ፣ ተልዕኮ፣ እሴቶች፣ መርሆች፣ ዓላማ፣ የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት፣ ስጋቶች፣ መፍትሔዎችና የ 1 ለ 5
አባላትን ስም ዝርዝር አካቶ የታቀደ ነው፡፡

ተልዕኮ፡- በቡድኑ ቀልጣፋና ዉጤታማ አደረጃጀት አሰራርና የሰዉ ሀይል በመገንባት ተጨባጭ
ለውጥ

ማምጣትና መልካም አስተዳደር ማስፈን የሚያስቸል አቅም መገንባት ፡፡

የዕቅድ ዝግጅት የ 2011 የ 1 ለ 5 ዕቅድ Page 2


ራዕይ፡- ተግባራትን በተቀመጠላቸው የጊዜ ገደብ የመፈፀም አቅም በ 1 ለ 5 አባላቶቻችን ተፈጥሮ
ማየት ፡፡

እሴቶች

 ለዉጥ ናፋቂና አራማጅ እንሆናለን ፡፡


 የስራ ፍቅር ከበሬታና ስነ-ምግባር መለያችን ይሆናል
 ለተገልጋዮች /ለዜጋዉ/ ፍላጎት ቅድሚያ መስጠት መለያችን ባህላችን እናደርጋለን
 ግልጽነትና ተጠያቂነት እናሰፍናለን
 ፍትሃዊነትን ማስፈን የመልካም አስተዳደር ገጽታችን ዋነኛ አካል መሆኑን
እንገነዘባለን
 ሁሌም ተማሪና አስተማሪ መሆን እንደሚገባን እንገነዘባለን
 ቀልጣፋና ዉጤታማነትን እናረጋግጣለን

መርሆች

 12 ቱን የስነ-ምግባር መርሆች ማክበርና መከተል

 ከኪራይ ሰብሳቢነት ነፃ መሆን

 ታማኝነትና ሚስጥር ጠባቂ መሆን

 ንብረትና በጀትን በአግባቡ መጠቀም


 የአገልግሎት አሰጣጡን ማሻሻልና ተገልጋዮች እርካታ እንዲያገኙ የሚያስችል
ስርአት መፍጠር
 ሀቀኛ፣ገለልተኛና ሚዛናዊ የሆነ አገልግሎት መስጠት
 የቅሬታ አቀራረብ ስርአቱን ዉጤታማ ማድረግ
 የተለያዩ መረጃወችን ግልፅ በሆነ መንገድና ቦታ ማስቀመጥ መቻል
 በመልካም የስራ ዲሲፒሊን የታነፀ ሃይል መፍጠር

የዕቅድ ዝግጅት የ 2011 የ 1 ለ 5 ዕቅድ Page 3


ዓላማ
 የቡድኑ አባላትን ተሳትፎና የባለቤትነት ስሜት ማሳደግ
 የቡድኑ አባላትን የዉሎ ስነ ምግባር መከታተልና ማረም
 የ 1 ለ 5 አደረጃጀቱን በማጠናከር ተከታታይነት ያለው ግምገማ ፣ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ የአገልግሎት
አሰጣጥ ጥራትን ማረጋገጥ

በ 1 ለ 5 አደረጃጀቱ የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት

 በዋናነት የቡድኑን አባላት ክህሎት፣ ዕውቀት፣ አመለካከትና አሰራር ማሳደግ


 በወረዳችን የትምህርት ተቋማቶች ውስጥ እየታዩ ያሉ ጥንካሬዎችንና እጥረቶችን እየለዩ የጋራ
በማድረግ ወደ ተሻለ የአፈጻጸም ስርዓት በማምጣት ትግል ማድረግ
 በየቀኑ የተሰሩ ስራዎችን የውሎ ግምገማ ማድረግ
 የመረጃ አያያዝ ስርዓትን ማሻሻል
 አባላቱን የስራ ሰዓት እንዲያከብር ማድረግ
 ቢሯችን አዲስና ችግኝ የሌለው በመሆኑ ችግኝ በመትከል እንክብካቤ ማድረግ
 ሁሉም የ 1 ለ 5 አባላት የመንግስትን ስራ እንዲያከብሩ ማድረግ
 የቡድኑ አባላት በተደራጁበት ጉዳይ ላይ ያለውን አላማና አስፈላጊነት ዙሪያ ግልጽነት እንዲኖራቸው
ማድረግ
 የ 1 ለ 5 አደረጃጃቱ ዘውትር ከሰኞ እስከ ረቡ ከ 11፡30 ስዓት ጀምሮ በእውቀት ፣ በክህሎትና
በአመለካከት ዉይይት ማካሄድ ፡፡
 እንደ አስፈላጊነቱ ተጨማሪ ርዕሶችን በመምረጥ መወያየት ፡፡
 ሁሉም አባላት የሲ/ሰርቪስ ሪፎርሞችን ቁልፍ ተግባር አድርጎ እንዲቀሳቀስ ማድረግና ማስቻል
 በስሩ ላሉት አባላት በሪፎርሙ ዙሪያ ልዩ ልዩ ድጋፍና ክትትል ማድረግ
 ከለይ የተቀሱትን ተጋባራት ለማካናወን በዓመቱ ውስጥ 144 ጊዜ ውይይት ማድረግ
ስጋቶች
 ውይይቱ የአባላቱ ቁጥር አንድ ሲሆን፣ በመስክ ስራ፣ በህዝባዊና ሀይማኖታዊ በዓላት፣ በደራሽ ስራ፣
በስልጠና እና በሰብስባ ምክንያት ተከታታይነትና ወጥነት ላይሆን ይችላል ፡፡
መፍትሄ
 የ 1 ለ 5 ዉይይት ተከታታይነት ያልሆነበትን ቀን ተጨባጭ ምክንያት በቃለጉባኤ እንዲሰፍር ማድረግ ፡፡

የዕቅድ ዝግጅት የ 2011 የ 1 ለ 5 ዕቅድ Page 4


የ 1ለ 5 አባላት ስም ዝርዝር
1. አታላይ ሹሜ የዕቅድ ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ቡድን መሪ ---------------- ስብሳቢ
2. አትንኩት አዛናው የዕቅድ ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ባለሙያ ------------------ ፀሐፊ
3. ሙቀት እሸቴ የዕቅድ ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ባለሙያ ------------------------አባል
4. ወ/ሮ እስከዳር ደሳለኝ የዕ/ዝ/ክ/ግ ቡድን የጽህፈትና ቢሮ አስተዳደር ባለሙያ -------አባል

የዕቅድ ዝግጅት የ 2011 የ 1 ለ 5 ዕቅድ Page 5

You might also like