You are on page 1of 5

በክልል ደረጃ የሚሰሩ ስራዎችን

1. የመፈጸምና የማስፈጸም አቅም መገንባትን በተመለከተ መከናወን ያለባቸው

1.1 የዘርፉን ሙያተኛ አመለካከት፣ እዉቀትና ክህሎት ማሳደግ፤

 በየደረጃው የሚገኙ የዘርፉ ባለሙያዎች ያለባቸውን የእውቀት፣ የክህሎትና የአመለካከት ክፍተቶችን


በዳሰሳ ጥናት መለየት፣
 የተለየውን ክፍተት በመተንተን በማን ሊፈታ እንደሚችል የመፍተሔ አቅጣጫ ማስቀመጥና
ለሚመለከታቸው አካላት ማድረስ፣
 የሚመለከተው አካል በተቀመጠው የመፍተሔ አቅጣጫ መሰረት የተለየውን ክፍተት ሊሞላ የሚችል
የስልጠና ሰነድ በማዘጋጀት የቅድመ ዝግጅት ስራ መስራት፣
 የስልጠና ሰነዱን ወይም የስልጠና ርዕሶችንና ይዘቶችን ከቢሮው ጋር የጋራ ማድረግ፣
 ስልጠና የሚሰጥበትን ጊዜ መወሰን፣አሰልጣኙን መለየትና እንዲዘጋጅ ማድረግ፣
 የስልጠና ቦታና አዳራሽ በማዘጋጀት ለሰልጣኞች ጥሪ ማስተላለፍና ስልጠናውን መስጠት፣
 በመጨረሻም ስልጠናው ያመጣውን ውጤት መገምገምና ለሚመለከተው አካል ሪፖርት ማድረግ፡፡

2. የኢኮኖሚ ሽግግር የሚያመጡ ፕሮጀክቶችን አፈጻጸም ማሳደግ በተመለከተ መከናወን


ያለባቸው

2.1 ትኩረት የተደረገ ባቸውን ንዑስ ዘርፎች በመለየት የእሴት ትስስሩን ክፍተት መሙላት

 የኢኮኖሚ ሽግግር የሚያመጡ የእሴት ሰንሰለቶችን በአምራች ኢንዱስትሪዎች ንዑስ


ዘርፍ ደረጃ ጥናት ማድረግና በአመራረት ሂደት ውስጥ ያሉ ክፍተቶችን መለየት
 በክፍተት የተለዩትን የምርት እሴት ሰንሰለቶች ሊሞላ የሚችል አሰራር በመዘርጋት ውጤታማ
እንዲሆኑ መደገፍ ወይም ድጋፍ እንዲያገኙ ማስቻል፣
 ድጋፍ ተደርጎ ክፍተቱ በመሞላቱ በእሴት ሰንሰለቱ ውስጥ የተገኘው ጭማሪ ምን ያህል እንደሆነ
ፋይዳውን መገምገም፣

2.2 ሁለንተናዊ ችግሮቻቸው በጥናት የተለየላቸውን አምራች ኢንዱስትሪዎች ከሚመለከታቸው


ተቋማት ጋር ትስስር በመፍጠር የኢንዱስትሪ ኤክስቴሽን ( የቴክኒካል አቅም ግንባታ ፣
የኢንተርፕረነርሽፕ አቅም ግንባታ፣ ጥራትና ምርታማ ነት አቅም ግንባታ እና የቴክኖሎጂ አቅም
ግንባታ ) በመስጠትና ችግራቸውን በመፍታ የማምረት አቅማቸውን የማሳደግ ስራ መስራት

1
2.2.1 ከዚህ በፊት የኢንዱሰትሪ-ዩኒቨርስቲ ትስስር ከተፈጠረባቸው ዩኒቨርሲቲዎች ጋር መካከለኛ
እና ከፍተኛ አምራች ኢንዱሰትሪዎች ትስስር እንዲፈጥሩ ድጋፍና ክትትል ማድረግ

 ያሉት መካከለኛና ከፍተኛ ኢንዱስትሪወች ተቆጥረው በመያዝ በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ ጥርት ያለ
መረጃ በዞኖችና ከተማ አስተዳደሮች እንዲዘጋጅ መደገፍ፣
 መረጃውን መሰረት በማድረግ ተቆጥረው የተያዙትን መካከለኛና ከፍተኛ ኢንዱስትሪወች በቅርበት
ካለው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር እንዴት እንደሚደገፉ አቅጣጫ ማስቀመጥና ክትትል
ማድረግ፣
 ከዚያም አንድ የዘርፉ አሰልጣኝ መምህርና የሚመለከተው የሴክተሩ የዘርፍ ባለሙያ ምን ያህልና
የተኞቹን መካከለኛና ከፍተኛ ኢንዱስትሪወች ቆጥረው እንደሚደግፉ ማረጋገጥና መረጃ መያዝ፣
 የዘርፍ ባለሙያ ከአሰልጣኝ መምህሩ ጋር በመሆን ወደ ኢንዱስትሪወች በመሄድ የሁኔታወች ትንተና
እንዲሰሩ መደገፍ፣
 በተዘጋጀው የሁኔታወች ትንተና መሰረት መካከለኛና ከፍተኛ ኢንዱስትሪወች ያለባቸውን
የአመለካካከት፣ የእውቀትና የክህሎት፣ የቴክኖሎጅ፣ የጥራትና ምርታማነት፣ የጥሬ እቃ አቅርቦትና
አጠቃቀም፣ እንዲሁም የሂሳባ አያያዝ ክፍተቶችን በተገቢው መንገድ መለየቱን መከታተል፣
 ከላይ የተጠቀሱትን ክፍተቶች ሊሞላ የሚችሉበትን የድርጊት መርሀ-ግብር ከኢንዱስትሪው ጋር በጋራ
እንዲዘጋጅ ድጋፍ መስጠት፣
 በተዘጋጀው የድርጊት መርሀግብር መሰረት የኢንዱስትሪወችን ክፍተት ሊሞላ የሚችል ድጋፍ
መስጠትና ክትትል በማድረግ ክፍተቶቹ እየተሞሉ፣ የኢንዱስትሪወች የውስጥ ችገሮች እየተፈቱ
ስለመሆኑና የመጣውንም ለውጥ እየገመገሙ መረጃውን ለቢሮው ሪፖርት ማድረግ፡፡
2.2.2 ከዚህ በፊት የኢንዱሰትሪ-ቴ/ሙያ ኮሌጆች ትስስር ከተፈጠረባቸው ቴ/ሙያ ኮሌጆች ጋር
አነስተኛ አምራች ኢንዱሰትሪዎችን ትስስር እንዲፈጥሩ ድጋፍና ክትትል ማድረግ፣

 ያሉት አነስተኛ ኢንዱስትሪወች ተቆጥረው በመያዝ በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ ጥርት ያለ መረጃ
በዞኖችና ከተማ አስተዳደሮች እንዲዘጋጅ መደገፍ፣
 መረጃውን መሰረት በማድረግ ተቆጥረው የተያዙትን አነስተኛ ኢንዱስትሪወች በቅርበት ካለው
የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ጋር እንዴት እንደሚደገፉ አቅጣጫ ማስቀመጥና ክትትል ማድረግ፣
 ከዚያም አንድ የዘርፉ አሰልጣኝ መምህርና የሚመለከተው የሴክተሩ የዘርፍ ባለሙያ ምን ያህልና
የተኞቹን አነስተኛ ኢንዱስትሪወች ቆጥረው እንደሚደግፉ ማረጋገጥና መረጃ መያዝ፣
 የዘርፍ ባለሙያ ከአሰልጣኝ መምህሩ ጋር በመሆን ወደ ኢንዱስትሪወች በመሄድ የሁኔታወች ትንተና
እንዲሰሩ መደገፍ፣

2
 በተዘጋጀው የሁኔታወች ትንተና መሰረት አነስተኛ ኢንዱስትሪወች ያለባቸውን የአመለካካከት፣
የእውቀትና የክህሎት፣ የቴክኖሎጅ፣ የጥራትና ምርታማነት፣ የጥሬ እቃ አቅርቦትና አጠቃቀም፣
እንዲሁም የሂሳባ አያያዝ ክፍተቶችን በተገቢው መንገድ መለየቱን መከታተል፣
 ከላይ የተጠቀሱትን ክፍተቶች ሊሞላ የሚችሉበትን የድርጊት መርሀ-ግብር ከኢንዱስትሪው ጋር
በጋራ እንዲዘጋጅ ድጋፍ መስጠት፣
 በተዘጋጀው የድርጊት መርሀግብር መሰረት የኢንዱስትሪወችን ክፍተት ሊሞላ የሚችል ድጋፍ መስጠትና
ክትትል በማድረግ ክፍተቶቹ እየተሞሉ፣ የኢንዱስትሪወች የውስጥ ችገሮች እየተፈቱ ስለመሆኑና
የመጣውንም ለውጥ እየገመገሙ መረጃውን ለቢሮው ሪፖርት ማድረግ፡፡
2.2.3 በተደረገላቸው የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፍ መሰረት የደረጃ ለውጥ ያመጡ
ኢንዱሰትሪዎችን በትክክለኛው መስፈርት ተመዝነው የሚያልፉ ከሆነ ወደ ሚቀጥለው ደረጃ
የማሸጋገር ስራ መስራት፡፡
 በተያዘው እቅድ መሰረት ሽግግር የሚደረግላቸውን ኢንዱስትሪዎች የመለየት ስራ እንዲከናወን ድጋፍና ክትትል
ማድረግ፣
 የተለዩትን ኢንዱስትሪወች አጠቃላይ የሆነ የመረጃ ታሪካቸውን የመመዝገብ ስራ እንዲከናወን ድጋፍና ክትትል
ማድረግ፣
 የተለዩትን እንዱስትሪወች ደረጃቸውን የሚመጥን የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ድጋፎችን መስጠትና መከታተል፣
 የሰጠናቸውን ድጋፎች ተጠቅመው የማምረት አቅማቸው ከፍ ማለቱን ወይም ባለበት መቆሙን የመፈተሽ ስራ
እንዲከናወን ክትትል ማድረግ፣
 ሁለቱን የኢንዱስትሪ የታሪክ ሪከርዶች እንዲመዛዘኑ የመደገፍ ስራ መስራት፣
 አሁን ያለበት የእድገት ደረጃ የተሸለ ከሆነ በሽግግር መስፈርቱ መሰረት መመዘንና ውጤቱን መወሰን፣
 ሽግግር ያደረጉትን ኢንዱስትሪወች በመለየትና መመሪያው ላይ በተቀመጠው መስፈርት መሰረት ሽግግራቸውን
ማብሰር፡፡

3 የዘርፉን ፕሮጀክት ክትትልና ድጋፍ ውጤታማነት ማሻሻል በተመለከተ መከናወን ያለባቸው

 አዲስ ፕሮጀክት በመቅረጽ ወይም ነባሩን ኢንዱስትሪ ለማስፋፋት ተጨማሪ ማሽነሪ


አስፈልጓቸው የማሽነሪ ዝርዝር መግለጫ ለሚጠይቁ ባለሀብቶች ድጋፍ ማድረግ፣
 በቀረበው ፕሮጀት ውስጥ የተዘረዘሩት ማሽኖች እና ሌሎች መሳሪያዎች ዝርዝር መግለጫ
ያለቸው መሆኑን ማረጋገጥ፣
 በፕሮጀቱ ውስጥ የተዘረዘሩት ማሽኖች እና ሌሎች መሳሪያዎች ለምርት ሂደቱ የተሟሉ፣
አስፈላጊና የሚመጥኑ መሆናቸውን መለየት፣
 የተጓደሉ እንዲካተቱ እና አላስፈላጊ የሆኑትን ደግሞ ከዝርዝሩ እንዲወጡ በማድረግ ባለሃብቱ
አስተካክሎ እንዲያመጣ ማስቻል፣

3
 በቀረቡት ማሽኖች እና ሌሎች መሳሪያዎች ዝርዝር መግለጫ መሰረት ማሽንና ፕላንት ለይ አውት
መቅረቡን በማረጋገጥና በመገምገም የሚያስፈልገውን የቦታ መጠን መወሰን፣
 በተወሰነለት ማሽንና ፕላንት ለይ አውት መነሻ መሰረት ያሸነፈበትን ፕሮፎርማና ተገዝተው
የቀረቡ ማሽኖችን ባለሀብቱ ሪፖርት እንዲያቀርብ በማድረግ ትክክለኛነታቸውን በአካል
የማረጋገጥ ስራ መስራት፡፡

4 የኢንዱስትሪዎችን ምርጥ ተሞክሮ መቀመርና ማስፋትን በተመለከተ መከናወን ያለባቸው


4.1 ምርጥ ተሞክሮዎችን ስለመቀመር

 ምርጥ ተሞክሮ የሚቀመርላቸው ኢንዱስትሪወችን እና ድጋፍ የሚያደርጉ አካላትን መለየት፣


 የሞዴል ኢንዱስትሪዎችን መመዘኛ መስፈርት ማዘጋጅት፣

 ምርጥ ተሞክሮዎችን ለመቀመር የሚያስችል ቼክሊስት ማዘጋጀት፣

 በቼክሊስት መሰረት መረጃ መሰብሰብ፣


1) የመስክ ጉብኝት እና ምልከታ በማድረግ፣
2) ሰነዶችን በመፈተሽ፣
3) ውይይት በማድረግ፣
4) ቃለ መጠይቅ በማካሄድ፣
5) የመረጃ ማሰባሰቢያ መንገዶችን በመጠቀም (በጽሁፍ፣በድምፅ፣በምስል)
 በቼክ ሊስቱ መሠረት የተሰበሰቡትን መረጃዎች ከመስፈርቶቹ አንፃር ማደራጀት፣
 መረጃዎቹን መተንተን፣
 ተሞክሮውን በሚያመች ዘዴ መቀመር (በምስል በድምፅና በጽሁፍ)
 ሪፖርት በመስራት ለቢሮው ማስተላለፍ፤
4.2 ምርጥ ተሞክሮዎችን ስለማስፋት

 የጠራ ራዕይ መያዝ፣

 ሁኔታዎችን ማወቅ፣

 ዕቅድ ማዘጋጀት፣

 የጋራ አመለካከት መፍጠር፣

 ደጋፊ የህግና የድጋፍ ማዕቀፎችን ማወቅ፣

 ፈፃሚ እና ባላድርሻ አካላትን መለየትና በአግባቡ ማሰማራት፣

4
 አስፈላጊ ግብዓቶች መሟላታቸውን ማረጋገጥ፣

 ውጤታማ የግምገማና የክትትል ስርዓት መዘርጋት፣

You might also like